Sunday, May 24, 2015

‹አያሌው ሞኙ›
click here for pdf

ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው መክዘ ከተነሡት ኃያላን መኳንንት አንዱ ናቸው፡፡ የራስ ብሩ ወልደ ገብርኤል ልጅና የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ ሲሆኑ የወገራ አውራጃ ሹም፣ የስሜን አውራጃ ገዥ፣ ልጅ ኢያሱ ከተያዙ በኋላ ደግሞ የንጉሠ ነገሥቱ ጦር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡ 
 
ደጃዝማች አያሌው ብሩ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ሰዎች መካከል ናቸው፡፡ መኢሶ ላይ ከልጅ ኢያሱ ጦር ጋር በተደረገው ጦርነት ተፈሪ መኮንን እንዲያሸንፉ ደጃዝማች አያሌው ከፍ ያለ ሚና ነበራቸው፡፡ ራስ ጉግሣን ለመያዝ አንቺም ላይ በተደረገው ውጊያም የደጃዝማች አያሌው ጀግንነት ወሳኝ ነበር፡፡ እንዲያውም በዚህ ጦርነት ለሚያበረክቱት ውለታ የራስነትን ማዕረግ እንደሚያገኙ ከንጉሥ ተፈሪ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን በአንድ በኩል የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ በመሆናቸው፣ በሌላ በኩልም ከቀድሞዎቹ የዐፄ ምንሊክ ባለ ሥልጣናት ወገን ስለሆኑ ተፈሪ ቃላቸው አጠፉባቸው፡፡

ከሁሉም በላይ ደጃዝማች አያሌውን ያሳዘናቸው በንጉሡ ግብዣ ላይ የነበራቸው ፕሮቶኮል መወሰዱ ነበር፡፡ እንደ ከፍተኛ መኳንንት በንጉሡ ቀኝ በኩል የነበራቸውን የክብር ወንበር ለራስ ደስታ እንዲለቁ መደረጉ ደጃዝማች አያሌውን ‹እጄ አመድ አፋሽ ነው› እንዲሉ አደረጋቸው፡፡ በኋላም ከንጉሥ ተፈሪ ጋር ይበልጥ ተቃቃሩና በቅጣት መልክ አሩሲ ተመደቡ፡፡


ደጃዝማች አያሌው ከንጉሡ ጋር እንደገና ለመስማማት የሞከሩት የጣልያን ጦርነት እየገፋ ሲመጣ ነበር፡፡ ወደ ኤርትራ ድንበር እንዲዘምቱ ትእዛዝ የተሰጣቸው ደጃዝማች(ፊታውራሪ) አያሌው ብሩ መንገድ ላይ ታመሙ፡፡ በኋላም የንጉሡ ሐኪም ስዊድናዊው ዶክተር ሓራልድ ኒስትሮም በአውሮፕላን ተላከላቸው፡፡ በተደረገላቸው ሕክምና ጤናቸው ሲመለስ ረዥም ጉዞ ወደሚጠይቀው የጦር ግንባር ጦራቸውን ይዘው ተጓዙ፡፡ ስዊድናዊው ሐኪምም አብሯቸው ዘመተ፡፡ የጉዞውንም ማስታወሻ በሚገባ ጻፈልን፡፡

ደጃዝማች አያሌው ብሩ ንጉሥ ተፈሪን አምነው ዘመዳቸውን ራስ ጉግሣን ቢዋጉም ቃል የተገባላቸውን የራስነት ማዕረግ ሳያገኙት በመቅረታቸው የጎንደር ሕዝብ
አያሌው ሞኙ
ሰው አማኙ፣ ሰው አማኙ እያለ ዘፍኖላቸዋል፡፡ ዘፈኑም እስከ ዘመናችን ድረስ ደርሷል፡፡

ይህንን ቅሬታቸው ያወቁት ጣልያኖች በተደጋጋሚ ከጎናቸው ሊያሰልፏቸው ሞክረዋል፡፡ ንጉሥ ተፈሪ ደጃዝማች አያሌውን ባለማመናቸው የተነሣ ወደ ጦርነት ሲዘምቱ እንኳን የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር ይሰልሏቸው ነበር፡፡ አብሯቸው እስከ ጦር ግንባር ዘምቶ፣ የኢትዮጵያ ጦር ተሸንፎ ሲመለስም እስከ ደብረ ታቦር አብሯቸው ተጉዞ A memoir of the Italian – Ethiopian war of 1935-36 የተሰኘውን መጽሐፍ እኤአ በ1938 የጻፈው ዶክተር ሐራልድ ኒስትሮም ምናልባት በንጉሡ ላይ ባደረባቸው ቅሬታ ተገፋፍተው ወደ ጣልያኖች ይገቡ እንደሆን ሲጠይቃቸው ‹‹እውነት ነው ንጉሡ በድለውኛል›› አሉ ደጃዝማች አያሌው ‹‹ነገር ግን እኔ ሀገሬን በምንም ያህል ገንዘብ የምከዳ አይደለሁም፤ ጣልያኖች እኔን ይከዳል ብለው ማሰባቸው የሚያሳፍር ነው›› ብለው ነበር መልስ የሰጡት፡፡ 


አንዳንዴ መንግሥታት፣ ነገሥታት፣ መሪዎች፣ ባለ ሥልጣናት በግለሰቦች፣ በሕዝቦችና በቡድኖች ላይ የሚያደርሱት ግፍና በደል ይኖራል፡፡ ሀገር ግን አትበድልም፡፡ ሀገርና መንግሥት፣ ሀገርና ንጉሥ፣ ሀገርና ፓርቲ፣ ሀገርና መሪ የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ደጃዝማች አያሌው መሪዎችን ከሀገር መለየት ሲሳን በየዘመናቱ የተነሡ ባለጊዜዎች የሠሩትን ጥፋት፣ በዘመናት ሁሉ ለምትኖር ሀገር ማሸከምን ያመጣል፡፡

ዶክተር ሐራልድ ኒስትሮም የንጉሥ ተፈሪ የግል ሐኪም ሆኖ የተቀጠረው እኤአ በ1927 ነው፡፡ ዶክተር ሐራልድ በቤተ መንግሥትና በቤተ ሳይዳ ሆስፒታል ይሠራ ነበር፡፡ በኋላም ደጃዝማች አያሌው ብሩን ተከትሎ እስከ ጦር ግንባር ድረስ ተጉዟል፡፡ ዶክተር ሐራልድ ጉዞውን በተመለከተ የዛሬ 77 ዓመት ያሳተመው መጽሐፍ በዶክተር ገበየሁ ተፈሪና በደሳለኝ ዓለሙ ‹የተደበቀው ማስተዋሻ› በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ርእስ በጥቅምት 2014(እኤአ) ታትሟል፡፡ 

አንቡት፤ በሌሎች የታሪክ መጻሕፍት የማናገኛቸውን የጦርነቱን መረጃዎች ከቅርብ የዓይን ምስክር እናነባለን፡፡ ዶክተር ሐራልድ አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገር፣ የሀገሪቱንም ጠባይ የተረዳ ሰው በመሆኑ የሚነግረን ነገር ትኩረት የሚስብ ነው፡፡ በተለይም በመጽሐፉ መጨረሻ የኢትዮጵያ ጦር በማይጨው ዐውደ ውጊያ ለምን ሊሸነፍ እንደቻለ የራሱን አምስት የግምገማ ነጥቦች አስቀምጧል፡፡ ሁላችንም ደግመን ደጋግመን ልናስብባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው፡፡

መልካም ንባብ፡፡     

15 comments:

 1. lega grom ylaw tarek new lsletan wendem wendemen mwegat ysaznal!! blala bekul mnem bnakwere ydero balsltanoch bager guday lay and mhonachwen lewec talat agarachawn asalfew aystwen neber !! katlebten mchersawe tafelen lega egezabher ybarkh!!  11

  ReplyDelete
 2. This is a true story which was told several times in our society to make it a good lesson for every generation after the Italian aggression. In the former decades ,in addition to the so called "modern " schools our folk tales ,songs , poems, short stories and etc were ways and methods of educating the country's youth .These ways and methods had a good continuity until the 1966 EC revolution for that generation before us .But today and even until the coming few decades , we have no resources and potential knowledge in our hearts and minds except following the electronics medias and tell each other by repeating what they posted . Because of the discontinuity of our good lesson methods, it is very hard to pass the good lessons of our fathers to the present youth which is totally taken by others culture due to the shortsightedness of his own recent fathers. This article has a magnificent important lesson for every one of us . It is not as easy as most of us say " I love Ethiopia " . Love of a country is not expressed by having a symbol of flag in a car , dressing and eating cultural food , participating different types of parties and their meetings or going to church some Sundays just for socialization and so on .It needs a big courage to love a country with its people like Dejazmatch Ayalew knowing the unity and difference between state and governor , party and country , king and country . አንዳንዴ መንግሥታት፣ ነገሥታት፣ መሪዎች፣ ባለ ሥልጣናት በግለሰቦች፣ በሕዝቦችና በቡድኖች ላይ የሚያደርሱት ግፍና በደል ይኖራል፡፡ ሀገር ግን አትበድልም ፡፡ ሀገርና መንግሥት፣ ሀገርና ንጉሥ፣ ሀገርና ፓርቲ፣ ሀገርና መሪ የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ደጃዝማች አያሌው መሪዎችን ከሀገር መለየት ሲሳን በየዘመናቱ የተነሡ ባለጊዜዎች የሠሩትን ጥፋት፣ በዘመናት ሁሉ ለምትኖር ሀገር ማሸከምን ያመጣል፡፡
  Thank you Dear Daniel for your continuous effort by making us learn more from our fore fathers and our present mistakes so that the future will be bright with the help of the Almighty God

  ReplyDelete
 3. ዲያቆን ዳኒ, ልናነበው የሚገባ መፅሀፍ ነው የጠቆምኮን. አቤት ያላቸው የአገር ፍቅር, ጉብዝናና, የእምነታቸውን ጥንካሬ ሰናሰብ በጣም የምናደንቃቸው ጀግኖች አባቶች ነው የነበሩን. ዶክተር ሐራልድንም አብረው ዘምተውና ታሪኩንም ፅፈው ሰላሰቀምጥሉን እናመሰግናቸዋለን. ዲያቆን ዳኒ, ሁልጊዜ ጥሩ ነገር ሰለምታቀርብልን መድሃሂያለም ጥበቡን ይጨምርልህ ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 4. አንዳንዴ መንግሥታት፣ ነገሥታት፣ መሪዎች፣ ባለ ሥልጣናት በግለሰቦች፣ በሕዝቦችና በቡድኖች ላይ የሚያደርሱት ግፍና በደል ይኖራል፡፡ ሀገር ግን አትበድልም፡፡ ሀገርና መንግሥት፣ ሀገርና ንጉሥ፣ ሀገርና ፓርቲ፣ ሀገርና መሪ የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ደጃዝማች አያሌው መሪዎችን ከሀገር መለየት ሲሳን በየዘመናቱ የተነሡ ባለጊዜዎች የሠሩትን ጥፋት፣ በዘመናት ሁሉ ለምትኖር ሀገር ማሸከምን ያመጣል፡፡ ከሸክምም በላይ ሸክም ሆኖ አሁን ስንተኛው የድል ቀን ሊከበር አይደለም ምናለ ብለህንው እሱ ይፍታው

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን ዳኒ, ልናነበው የሚገባ መፅሀፍ ነው የጠቆምኮን. አቤት ያላቸው የአገር ፍቅር, ጉብዝናና, የእምነታቸውን ጥንካሬ ሰናሰብ በጣም የምናደንቃቸው ጀግኖች አባቶች ነው የነበሩን. ዶክተር ሐራልድንም አብረው ዘምተውና ታሪኩንም ፅፈው ሰላሰቀምጥሉን እናመሰግናቸዋለን. ዲያቆን ዳኒ, ሁልጊዜ ጥሩ ነገር ሰለምታቀርብልን መድሃሂያለም ጥበቡን ይጨምርልህ ይጠብቅህ አሜን!!!
  ግዚክስ

  ReplyDelete
 6. ይህን መጻህፍ ከየት አገኛለሁ ?

  ReplyDelete
 7. ይህ ታሪክ ለኛ ላብዛኞቻችን ወበከንቱ ትውልዶች አይገባንም ገንዘብ ታውጣ እንጂ ሀገርን ከመሸጥ የማንመለስ መሆናችንን አለም ያውቅልናል እድሜ ለወያኔ ትውልዱ ከራስ ጥቅም ወጪ ስለሀገሩና ስለ ወገኑ እንዳይስብ እራሱ በተግባር እያሳየ እስተምሮታል።

  ReplyDelete
 8. መጽሐፏ የምትገኘው ከኃ/ስላሴ መቃብር ቤት ውስጥ ካለቸው ትንሽዬ የፈጠራ ታሪክ ማኅደር ቤት ታገኛታለህ ሂድና ቆፍረህ ለማንበብ ሞክር እሺ? ጎበዝ!!!

  ReplyDelete
 9. አንዳንዴ መንግሥታት፣ ነገሥታት፣ መሪዎች፣ ባለ ሥልጣናት በግለሰቦች፣ በሕዝቦችና በቡድኖች ላይ የሚያደርሱት ግፍና በደል ይኖራል፡፡ ሀገር ግን አትበድልም፡፡ ሀገርና መንግሥት፣ ሀገርና ንጉሥ፣ ሀገርና ፓርቲ፣ ሀገርና መሪ የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ደጃዝማች አያሌው መሪዎችን ከሀገር መለየት ሲሳን በየዘመናቱ የተነሡ ባለጊዜዎች የሠሩትን ጥፋት፣ በዘመናት ሁሉ ለምትኖር ሀገር ማሸከምን ያመጣል፡፡

  ReplyDelete
 10. ይህን ታሪክ ግንቦት ልደታ 2007 ሰምቸው ነበርና ያንን የግንቦት ልደታ ንፍሮ / ጥሬ እየበላን የነገሩንን አባት ድጋሜ ላመሰግን ወደድኩ መለያየትን እንጅ መለየትን ገንዘብ ለማናደርገ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው ና::

  ReplyDelete
 11. ሰላም ዳኒ እንዴት አለህ ምነው ጠፋህ አረ ተው ደግሞ መጣብህ
  እንዲህ ሲል ያውካል ይላሉ አበው በትርጒሜያቸው እናም አንተ ስትጠፋ በትንሽ ሳይሆን በብዙ ያውካል እባክህ ብቅ በል መቼም እንዲህ ቆይተህ የምትደግስልን ድግስ እስኩ ድግሙ ድግሙን የሚያስዘምር መሆን አለበት ቸር ያሰማን።

  ReplyDelete
 12. አንዳንዴ መንግሥታት፣ ነገሥታት፣ መሪዎች፣ ባለ ሥልጣናት በግለሰቦች፣ በሕዝቦችና በቡድኖች ላይ የሚያደርሱት ግፍና በደል ይኖራል፡፡ ሀገር ግን አትበድልም ፡፡ ሀገርና መንግሥት፣ ሀገርና ንጉሥ፣ ሀገርና ፓርቲ፣ ሀገርና መሪ የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ደጃዝማች አያሌው መሪዎችን ከሀገር መለየት ሲሳን በየዘመናቱ የተነሡ ባለጊዜዎች የሠሩትን ጥፋት፣ በዘመናት ሁሉ ለምትኖር ሀገር ማሸከምን ያመጣል፡፡

  ReplyDelete
 13. ዳኔ እድሜና ጤና ከነሞላው በተሰብሕ እመኝልህ አለሁ።

  ReplyDelete
 14. very funny I want more please but make it more funny next time thank you from tesfamichale Atlanta Georgia
  age 10

  ReplyDelete
 15. ሠላም ወንድም ዳንኤል እባክህን ይህንን ታሪክ በቴሌቪዥን ለማቅረብ ሞክር እባክህ ምናልባት የሃገር ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ አብዛኛውን ህዝብ ታስተምር ወይም ታስታውስ ይሆናል ያክብርልኝ፡፡

  ReplyDelete