Friday, May 22, 2015

ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል


ደራሲ፡- ሮማን ፕሮቻዝካ
ትርጉም፡- ደበበ እሸቱ
አሳታሚ፡-  ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት
ቦታና ዘመን፡- ሎስ አንጀለስ፣ መጋቢት 2007
ዋጋ፡- 10 ዶላር
ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ ለሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ የኦስትሪያ ቆንስላ ውስጥ ተመድቦ ሠርቷል፡፡ ከአዲስ አበባ የወጣው ከዲፕሎማት ሥራውና መብቱ ጋር የሚፃረር ተግባር ሲያከናውን በመገኘቱ በ1926 ዓም ተባርሮ ነው፡፡ ፕሮቻዝካ Abyssinia the Powder Barrel" በሚል ርእስ በ1927 ቪየና ላይ አውሮፓውያን ትዮጵያን ሊወርሩና ሊይዙ የሚገባበትን ምክንያት የሚያቀርብ መጽሐፍ አሳተመ፡፡ መጽሐፉ ABISSINIA PERICOLO NERO (አቢሲንያ፡- ጥቁሯ አደጋ/ሥጋት) በሚል ርእስ የጣልያን ወረራ ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት በ1927 ዓም በጣልያንኛ ተተርጉሞ ወጣ፡፡  ጣልያን ሀገሪቱን በወረረበት በ1928 ዓም ከወረራው ትንሽ ወራት ቀደም ብሎ በዋና ዋና የአውሮፓ ቋንቋዎች ተተርጉሞ እየታተመ ተሠራጭቶ ነበር፡፡ 

ፕሮቻዝካ ኢትዮጵያን አምርሮ የሚጠላ መሆኑን በጽሑፉ ሁሉ ይገልጠዋል፡፡ ነጮችን የሚጠሉ ሕዝቦች ያሉባት፣ የነጮች ክብርና መብት የማይጠበቅባት፣ ሥልጣኔ ያልጎበኛት፣ ብሔረሰቦች የሚጨቆኑባት፣ ጽዳት የሌለባት፣ አረመኔነት የነገሠባት፣ እምነቷ ከጥንቆላ ጋር የተቀላቀለ፣ ዜጎቿ ዓይናቸውን ጨፍነው ፎቶ የሚነሡ፣ መኳንንቱ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱ፣ አንድነት የሌላት ሀገር መሆኗን ማስረጃ የሚለውን ሁሉ እየጠቀሰ ለማስረዳት ይሞክራል፡፡ ‹ኢትዮጵያውያን ጠላትን ለመመከት  አንድ ናቸው› የሚለውን ሕዝቡ አያምንበትም ይላል፡፡ በንጉሡ የንግሥና በዓል የአውሮፓ መሪዎች ተወካዮች መገኘታቸው እጅግ ራስን ማዋረድና ክብር የማይጋባቸውን ጥቁሮች ከፍ ማድረግ ነው ይላል፡፡
የአድዋ ጦርነት ድል ነጮችን እንዲንቁ እንዳደረጋቸው፣ ነጮች ምኒሊክን በማባበላቸው የተነሣ በሌላ ሀገር ያገኙትን መብት እንዳጡ፣ ስለ ሀገሪቱ በአውሮፓ ቋንቋዎችና ጋዜጦች መልካም ነገር የጻፉት ሁሉ አንድም ገንዘብ ተከፍሏቸው፣ አለያም ደግሞ ለንግዳቸው ሲሉ መሆኑን ያትታል፡፡
ሀገሪቱን ለማስተካከል ሦስት መፍትሔዎችን ያቀርባል፡፡ አገሪቱን የሚገዟትን ጥቂት አማራዎች ማስወገድ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ነገዶች በዘር፣ በቋንቋ፣ በባህል ከኢትዮጵያ ገዥዎች ጋር ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲሰጣቸው (‹እስካሁን ቢሰጣቸው ኖሮ ኢትዮጵያዊነትን አውጥተው ይጥሉት ነበር፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ግን ከአውሮፓውያን ተሰሚነትና ተራማጅ አስተሳሰብ አራርቀው (አማራ ገዥዎች) በተዕጽኖ እየገዟቸው ነው› ይላል)፣ ኢትዮጵያውያን አውሮፓውያን ታላላቅ ሕዝቦች ናቸው ብለው እንዲቀበሉ ቅኝ መግዛትና ማሠልጠን፡፡ ‹ክርስቲያን ያልሆኑት ሕዝቦች በነጻነት ድምጽ ስጡ ቢባሉ በአውሮፓውያን ሥር መሆንን የሚመርጡ ናቸው› ሲል ያስቀምጣል፡፡ ሀገሪቱ መገጣጠሚያዋ የላላ ነው፣ አንድነቷ እንደታሰበው አይደለም ባይ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ጀምራው የነበረው ግንኙነት አውሮፓውያንን በእስያውያን የመተካት ሂደት ነው፡፡ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ አውሮፓውያን በኢትዮጵያ ቦታ አይኖራቸውም ይላል፡፡ ጃፓናውያኑ ጥጥና አደንዛዥ ዕጽ እንዲያመርቱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ይኼ ደግሞ የዓለም መንግሥታት ማኅበርን ደንብ ይጻረራል በማለት ይከሳል፡፡
የሮማን ፕሮቻዝካን መጽሐፍ ስታነቡ ሀገሪቱ እንዴት ባለ ጥርስ ውስጥ የገባች ሀገር እንደሆነች ታያላችሁ፡፡ ኢትዮጵያን አምርረው የሚጠሉ ሰዎችን አስተሳሰብና ሀገሪቱን የማዳከሚያ ስልትም ታገኙበታላችሁ፡፡ ከ80 ዓመት በኋላ ዛሬ ላይ ሆናችሁ መጽሐፉን ስታነቡት አንዳንድ ሁኔታዎች የዛሬ እንጂ የጥንት አይመስሉም፡፡ ስለ ሀገራችን በጎ እንጂ ክፉ ለማንወድ ሰዎችም ጽሑፉ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም ነው፡፡
ደበበ እሸቱ እኤአ በ1935 የታተመውን የእንግሊዝኛውን ቅጅ ወደ አማርኛ ሲመልሰው አመላለሱ ትርጉም እንዳይመስል የሚያደርግ ነው፡፡ ደበበ መጽሐፉን የተረጎመው ሁኔታው ጠልቆ ተሰምቶት እንጂ ነገሩን ተረድቶት ብቻ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ በዚህ በ54 ገጽ መጽሐፍ ውስጥ የምታዩት ጉድ ከመጽሐፉ ገጽ በላይ ነው፡፡ ሲያጠቃልልም ‹‹አፍሪካ አንድ አህጉር ነው፤ በዚህ ታላቅ አህጉር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች የአውሮፓ ታላላቆች ከሌሎች ሕዝቦች ያላቸውን ቀዳሚነት ማረጋገጥ አለባቸው››
አንቡና ጉድ በሉ፡፡    


አሌክሳንደርያ፣ ቨርጅንያ
 

21 comments:

 1. Wow , how did you find out this? what a surprise?

  ReplyDelete
 2. Glad you find this. recommend us or share us if possible for many Ethiopians as far as possible. So that we learn that unity is only means to continue as a nation and otherwise we fail seriously. I suspect Meles has read this book somewhere some time.

  ReplyDelete
 3. እምዬ ኢትዬጵያን ምን ባደረገች ነው እንዲ አይነት ጥላቻ? ለምን? ለምን ይሆን እንዲህ አይነት አመለካክት የኖራቸው? ማን ይሆን ይህንን ጥያቄ የሚመልሰልን? እንዲህም በመባሏ ሳይከፋት ይቅር ብላቸው ትኖራለች! ሁሉን ችለሽ የምትኖሪ አገራችን ትንሣሔሽን ያሳየን! ዲያቆን ዲኒ, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 4. THIS IS JUST FOR COUNTER ARGUMENTS (TO DIFFERENTIATE EUROPEAN COLONIZER MIND FROM GENUINE JUSTICE SEEKER)

  ON THE QUESTION OF NATIONALITIES IN ETHIOPIA[1]

  By Walleligne Mekonnen
  Arts IV, HSIU
  Nov. 17, 1969

  …….
  What are the Ethiopian peoples composed of? I stress on the word peoples because sociologically speaking at this stage Ethiopia is not really one nation. It is made up of a dozen nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity. And what else is a nation? It is not made of a people with a particular tongue, particular ways of dressing, particular history, particular social and economic organization? Then may I conclude that in Ethiopia there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo [Wolayta] Nation, the Adere [Harari] Nation, and however much you may not like it the Somali Nation.
  This is the true picture of Ethiopia. There is of course the fake Ethiopian Nationalism advanced by the ruling class and unwillingly accepted and even propagated by innocent fellow travellers.
  What is this fake Nationalism? Is it not simply Amhara and to a certain extent Amhara-Tigre supremacy? Ask anybody what Ethiopian culture is? Ask anybody what Ethiopian language is? Ask anybody what Ethiopian music is? Ask anybody what the “national dress” is? It is either Amhara or Amhara-Tigre!!
  To be a “genuine Ethiopian” one has to speak Amharic, to listen to Amharic music, to accept the Amhara-Tigre religion, Orthodox Christianity and to wear the Amhara-Tigre Shamma in international conferences. In some cases to be an “Ethiopian”, you will even have to change your name. In short to be an Ethiopian, you will have to wear an Amhara mask (to use Fanon’s expression). Start asserting your national identity and you are automatically a tribalist, that is if you are not blessed to be born an Amhara. According to the constitution you will need Amharic to go to school, to get a job, to read books (however few) and even to listen to the news on Radio “Ethiopia” unless you are a Somali or an Eritrean in Asmara for obvious reasons.
  ……….
  And what is this genuine national-state? It is a state in which all nationalities participate equally in state affairs, it is a state where every nationality is given equal opportunity to preserve and develop its language, its music and its history. It is a state where Amharas, Tigres, Oromos, Aderes [Harari], Somalis, Wollamos [Wolaytas], Gurages, etc. are treated equally. It is a state where no nation dominates another nation be it economically or culturally.

  The above article was written by Walleligne Mekonnen 39 years ago, while he was a fourth year student in the Faculty of Arts, PSIR, and was published on STRUGGLE[ Vol. V, No. 2, November 17, 1969] by the University Students’ Union of Addid Ababa ( USUAA).

  ReplyDelete
  Replies
  1. Unfortunately He died before Andargachew Tsige wrote about it indepth and very critically than him.

   Delete
 5. አሁን ይሄንን ምን ይሉታል

  ReplyDelete
 6. TheAngryEthiopian/ቆሽቱ የበገነውMay 24, 2015 at 8:59 AM

  ይኸንን መፅሃፍ በእንግሊዘኛ ለማግኘት እንክዋን ይከብድ ነበር። አንዳንድ ቤተ-መፅሃፍት ቤት ብቻ ነው የሚገኘው። እንኳን በአማርኛ ተገኘ። ሆኖም ቀረም ዋነኛውን የእንግሊዘኛ ትርጉም ማግኘቱም አይከፋም። ከላይ ያለው ስምየለሽ ሃሳብ ሰጪ - ዋለልኝ የተባለውን ወንጀለኛና የጀብሃ ቅጥረኛ እንደዚህ ብሎ ተናገረ ብሎ የፃፈው የዚሁ የፕሮቼዝካ ቢጤ አይነትና ሚሲዮናዊ ካባ ለባሽ ፈረንጅ ቦለቲክሞች የነዙትን መርዝ ተከትሎ ነው። ይህቺ ፅሁፍ ትነበብ http://www.ethiopatriots.com/pdf/meftehawYeamara150420.pdf - የመጣጥፉ ፀሃፊ ፕሮቼዝካን ይጠቅሳል፣አንዳንድ ቁንስል ነጥቦችም እነሆ- "....የፋሽስት የቅኝገዥነት ወረራ ዘላቂ የሚሆነው፣ሶስት ነገሮች በኢትዮጵያ ሲጠፉ ነው....፩- ዘውድ ፪- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ፫- የዐማራ ህዝብ...." በሁለተኛው የጣልያን ወረራ ዋዜማ ይኼ ፕሮቼዝካ የተባልው ፀረ-ኢትዮጵያዊ የፃፈው ደግሞ እንዲህ ይላል "..የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ከጃፓን ጋር ተባብሮ በነጭ ዘር ላይ ያሳድማል፣ ያፍሪካ ቅኝ ገዥዎች እንዲሁም መላው የነጭ ዘር መንግስታት ተጠቅተዋል።....በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ግዛት ውስጥ የሚኖሩት ህዝቦችና ልዩ ልዩ ነገዶች በጥቂት ገዥ አበሻዎች በዘር፣ በቋንቋ፣ በባህልና በሐይማኖት የተለያዩት የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ቢሰጣቸው ኖሮ የአበሻን በኅይል መግዛት ይጥሉት ነበር። በግዳጅ ከአውሮፓ የባሕልና ቅኝ መገዛት የሚያመጣውን እድገትና መሻሻልን እንዳያገኙ ተደርገዋል።..." (ገፅ፲፩) "...በርግጥ አንድ አይነት አበሻ ህዝብ የለም፣ያለው አንስተኛው ፳መቶኛው የሚደርሰው ዐማራ ነው ሌሎቹን የሚገዛው። ክርስትያን ያልሁኑ ነገዶች ነፃ ሊወጡ ይፈልጋሉ፤በግልፅ ቢጠየቁ የአውሮፓውያን የበላይ ጠባቂነትና የተረጋገጠ እድገትና ልማት ይፈልጋሉ።..." (ገፅ፹-፹፩)

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኦርጂናሉ በጀርመንኛ ነው! ጸሓፊው ከኦስትሪያ ነውና

   Delete
 7. እምዬ ኢትዬጵያን ምን ባደረገች ነው እንዲ አይነት ጥላቻ? ለምን? ለምን ይሆን እንዲህ አይነት አመለካክት የኖራቸው? ማን ይሆን ይህንን ጥያቄ የሚመልሰልን? እንዲህም በመባሏ ሳይከፋት ይቅር ብላቸው ትኖራለች! ሁሉን ችለሽ የምትኖሪ አገራችን ትንሣሔሽን ያሳየን! ዲያቆን ዲኒ, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ግዚክስ

  ReplyDelete
 8. Until citizens of Ethiopia such as 'TheAngryEthiopian' stop living in denial of the facts the misery of the country continues.
  For example: why would you call Walleligne 'Jebha' and 'ፕሮቼዝካ'? Why don't you check the facts he stated and criticize them?
  The generation in denial is the very same generation whose parents were among the best educated as himself.
  These citizens like you are the best the country could have for its prosperity and advancement.
  However, until 'The generation in denial' stop the disillusion and accommodate the reality in ground:
  1. The current government rules endlessly
  2. Any effort which disregards the identity of the nation nationalities of the country results in the country's disintegration.
  3.If people in denial kept associating themselves with the Ethiopian Orthodox church, which normally preaches for all humanity, they will suck the blood out of her. Theses same people will be headache of the church as we already saw in UK and USA.

  Note: Please do not associate yourself with Orthodox Christian Church. The church do not have citizenship. The church, while rooting in Ethiopia, is for all mankind who opens his heart to listen the good news and to be part of the church's sacred rituals.

  ReplyDelete
  Replies
  1. cheers u reasonable&realistic man!!ignore ቆሽቱ የበገነው and z likes!!they r now just toothless dogs!!that is why r barking and using the sacred EOTC as their shield!!

   Delete
  2. Dear Wallelign Mekonen idolizer,
   Wallelign Mekonen was just one among many immature young people who were deliberately bamboozled by foreign spies posing as scholars in HSI university using strange doctrines (in Tilahin's case Marxism) to bring Roman Prochazka's recommendation to bear. The foreign forces succeeded in the disuniting systems that followed his majesty's. Wallelign and his foreign-junk-collecting generation may not have risen as enemies of Ethiopia but they were nevertheless used by Ethiopia's enemies.

   Delete
 9. We ethiopian have to work together for better tomorow

  ReplyDelete
 10. get English version below
  =========
  https://drive.google.com/file/d/0B3JRaDHaMYO2OV8wS2dLNXBlR1k/view

  ReplyDelete
 11. get English version below
  =========
  https://drive.google.com/file/d/0B3JRaDHaMYO2OV8wS2dLNXBlR1k/view

  ReplyDelete
 12. https://drive.google.com/file/d/0B3JRaDHaMYO2OV8wS2dLNXBlR1k/view

  ReplyDelete
 13. https://drive.google.com/file/d/0B3JRaDHaMYO2OV8wS2dLNXBlR1k/view

  ReplyDelete
 14. Get the english version of the book here:
  https://drive.google.com/file/d/0B3JRaDHaMYO2OV8wS2dLNXBlR1k/view

  ReplyDelete
 15. https://drive.google.com/file/d/0B3JRaDHaMYO2OV8wS2dLNXBlR1k/view

  ReplyDelete
 16. Ohh really amaizing why he did it?????

  ReplyDelete
 17. ሮማን ፕሮቻዝካ በሀገራችን በነበረ ጊዜ ምን ያህል አንጀቱን እንዳሳረሩት ግልጽ ነው። አባቶቻችን ጫማም ባያደርጉ ባለጫማውን ፈረንጅ ንቀው የሚያዩ፥ የነጩን ቆዳ በለምጽ የተመታ ብለው ለመንካት የሚጠሉ በማምነታቸው የሚኮሩ ልዩ ሕዝብ መሆኑን ሲያይ ለቅኝ አልተመቸነውም። አበደ! በአድዋ የተገኘው ድል እስከዛሬም በነጮቹ ልብ ውስጥ አለ። ያ የባንዳ ልጅ መለስ ይቺን አንብቦ የሮማንን ሃሳብ ስራ ላይ ያዋለ የተረገመ ከይሲ ነው። ለ27ዓመት ስራውን ሰርቶ አለቀ። እድፉ ግን ገና ለዐመታት ካልታጠበ አይጠራም። አምላካችን ግን ይህቺን ሀገር ጥሎ አይጥልምና እንዲሁ ነጩም በልቡ የኛን ነገር ሲያስብ መሰሪነቱን ሲያሰላ አብረን እንኖራለን እንጂ ኢትዮጵያ ጠፍታ ኣትጠፋም። የሚጠብቃት አይተኛም አያንቀላፋም። ሮማንም መለስም አፈር በልተው አፈር ሆነዋል። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። መጽሐፉ የሚያውቃት ሀገር ወዴት ትጠፋለች?

  ReplyDelete