Wednesday, May 20, 2015

ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በኢትዮጵያ ባሕል ውስጥ፡- <አቦ> እንደ ማሳያ

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ማን ናቸው?

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ ተክለ ሃይማኖት(EMML 3051) 18ኛው መክዘ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በ13ኛው መክዘ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻዊ ቅዱስ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መረጃዎች መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ የሚባለው በዐፄ ላሊበላ ዘመን ነው፡፡ የትውልድ ቦታቸው በላዕላይ ግብጽ ንሒሳ   (የአሁኑ ባሕቢት አል ሐጋራ) ነው፡፡ [በርግጥ አንዳንድ ሊቃውንት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው፤ ነገር ግን የወላጆቻቸው ስም በሚገባ ለመታወቅ ባለመቻሉ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እናታቸው አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን)፣ አባታቸውም ስምዖን (ካህን) እንደተባሉና የዚህም ምክንያቱ ከቤተ ክርስቲያን የተገኙ ለማለት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አንድ መጽሐፈ ታሪክም ‹አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብጹዐን ወቅዱሳን ተወልዱ በኢትዮጵያ› ይላል፡፡EMML 5538,f 55]
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከ500 ዓመታት በላይ በዚህ ምድር ላይ መኖራቸውንና ከትግራይ እስከ ሸዋ ባለው ክፍል ተዘዋውረው ማስተማራቸውን፡፡ በዚህም ምክንያት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስንና ምድረ ከብድ ገዳማትን መትከላቸውን ታካቸው ያሳያል፡፡ ያረፉት በዐፄ ሕዝብ ናኝ ዘመን (1414-1418ዓም) ነው፡፡ ጻድቁ በትግራይ አቡዬ፣ በአማራው አቡነ፣ በኦሮሞዎች ዘንድ ደግሞ አቦ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ዋናዎቹ ገዳሞቻቸው ሁለት ሲሆኑ ዝቋላ በኦሮምያ ክልል፣ ምድረ ከብድ ደግሞ በደቡብ ክልል ይገኛሉ፡፡ 

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
1.      ከውጭ መጥተው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኖሩ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚታወቁት ቅዱሳን ከአመጣጣቸውና አኗኗራቸው አንጻር በሦስት ይመደባሉ፡፡ ኢትዮጵያ ተወልደውና ኖረው ኢትዮጵያ ያረፉ(አብዛኞቹ ቅዱሳን በዚህ ምድብ ናቸው)፣ ከውጭ መጥተውና ኖረው ኢትዮጵያ ያረፉ(ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣ማኅበረ ጻድቃን፣ ተሰዓቱ ቅዱሳን፣ አባ ሊባኖስ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እጨጌ ዕንባቆም) ኢትዮጵያ ተወልደው ውጭ ኖረው ያረፉ(አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ሙሴ ጸሊም፣ ሙሴ ሐበሻው(ሙሳ አል ሐበሽ)፣ገብረ ክርስቶስ(አብዱል መሲሕ))፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በውጭ ሀገር ተወልደው ኢትዮጵያ መጥተው ኖረው ካረፉት ቅዱሳን የሚመደቡ ናቸው፡፡
2 1በቁም ከሚሳሉ ጥንታውያን ሥዕሎች አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የግድግዳና የብራና ላይ ሥዕሎች መካከል ለብቻቸው በቁም በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ከሚሳሉት አራት ቅዱሳን (አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ) አንዱ ናቸው፡፡ የቁም ሥዕላቸው ከወሎ ገነተ ማርያም እስከ አዲስ አበባ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ ላይ ይገኛል፡፡
3 2. ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ ጻድቅ ናቸው፡፡ በ1990 ዓም በነበረው የሰበካ ጉባኤ የአብያተ ክርስቲያናት ቅጽ መሠረት በመላ ሀገሪቱ ከ2620 በላይ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡
4 3. የንጉሥ ዐዋጅ ቅድስናቸውን ካወጀላቸው ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ በዓላቸው በመጋቢትና በጥቅምት 5፣ በጥቅምት 27 እና በታኅሣሥ 29 እንዲሆን ንጉሥ ሕዝብ ናኝ ዐውጇል፡፡
5 4. በ14/15ኛው መክዘ የጸሎት መጻሕፍት የሥርዓተ ጸሎት ቅደም ተከተል መሠረት ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው ለምልጃ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡
6 5. በሰዓታትና ኪዳን ጸሎት ጊዜ ገድላቸው ከሚነበቡ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን (አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ አረጋዊ) አንዱ ናቸው፡፡
7 6. የአራዊት አባቶች ከሚባሉት(አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ በርተሎሜዎስ) አንዱ ናቸው፡፡

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሕዝቡ ባሕል ውስጥ፤ ለምን?
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በተለየ በሕዝቡ ባሕል ውስጥ ቦታ አላቸው፡፡ በሕዝቡ ባሕል ውስጥ ቦታ በመያዝ ከቅድስት ድንግል ማርያም ቀጥሎ ያለውን ቦታ ሳይዙ አይቀሩም፡፡ የዚህን ምክንያት በርግጠኛነት መናገር ከባድ ይመስለኛል፡፡ የእኔ ግምት ግን ከሁለት ነገር የመነጨ ነው፡፡
1.      አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሽምግልናቸው የሚታወቁ ጻድቅ በመሆናቸውና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሽማግሌ ካለው የከበሬታ ሥፍራ የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡
2.     ሲመጡ ከቅዱስ ላሊበላ፣ ሲያርፉ ከንጉሥ ሕዝብ ናኝ ጋር ከነበራቸው ግንኙነት ባለፈ ከቤተ መንግሥቱ ርቀው የኖሩ ሕዝባዊ አባት በመሆናቸው የተነሣ የተፈጠረ ሕዝባዊ ቅቡልነት ሊሆን ይችላል፡፡

ማሳያዎች
፩. በይትበሃሎች
1.      አስታራቂነት፡- ነብርና አንበሳ አይስማሙም፤ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥዕል ሥር ግን ነብርና አንበሳ ተስማምተው ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሣ ለመታረቅ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለማስታረቅ የሚሄዱ ሽማግሌዎች ‹አቦን ሆነን መጥተናል› ይላሉ፡፡
2.     የአቦ ጠበል፡- አንድ ሰው እየተመገበ ቢያንቀው ‹የአቦ ጠበል› እያልክ ውኃን ሦስት ጊዜ ጠጣው ይባላል፡፡
3.     የአቦ ብቅል፡- አንድ ሰው ከማያውቀው ቦታ ስሙ ቢጠራና በአካባቢው የሚያውቀውን ሰው ቢያጣ የጠራው ሰይጣን ሊሆን ስለሚችል ‹‹የአቦን ብቅል እፈጫለሁ› በል ይባላል፡፡
4.     የአቦ መገበሪያ፡- አንድ ሰው አንድን ነገር አጥፍቶ ተሠውሮ እንደማይቀመጥ ለመግለጥ ‹‹የአቦን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይውላል›› ይባላል፡፡
5.     አቦ ሰጥ፡- አንድ ሰው የማያውቀውን ነገር በግምት ሲናገር ‹አቦ ሰጥ› ይባላል፡፡
6.     በአቦ ይዤሃለሁ፡- አራዊት የቤት እንስሳትን እንዳይበሉባቸው ገበሬዎች ‹በአቦ ይዤሃለሁ› ብለው ይገዝቷቸዋል፡፡
7.     የአቦ መንገድ፡- በሰሜን ሸዋ መራኛ አካባቢ ባሉ ሕዝቦች ዘንድ ‹የአቦ መንገድ› የሚባል ብሂል አለ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሚዳ ከሚገኘው የአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም ጥቂት ጊዜ ቆይተዋል ይባላል፡፡ በኋላ ከዚያ ገዳም ሲወጡ አቡነ መልከ ጼዴቅ ‹‹የት ሊሄዱ ነው›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹እርሱ ወደ መራኝ›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ከተማው ‹‹መራኛ›. የተባለው በዚህ ምክንያት ነው ይባላል፡፡ ታድያ በዚህ ምክንያት አንድ ሰው መድረሻውን በውል ሳያውቀው መንገድ ሲጀምር መንገዱ ‹የአቦ መንገድ› ይባላል፡፡
8.     የአቦ ቁራ፡- ሰይጣን በቁራ ተመስሎ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዓይናቸውን ሊያወጣ ስለመጣ በጎ ነገር የያዘ መስሎ የሚመጣ ክፉ ሰው ‹የአቦ ቁራ› ይባላል፡፡
9.     በአቦ በሥላሴ፡- በሕዝቡ ብሂል ውስጥ ከሥላሴ ጋር ተያይዘው ብዙ ጊዜ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ‹በአቦ በሥላሴ› ሲባል አጥብቆ መለመን ነው፡፡ በሕዝባዊ መዝሙሮችም ውስጥ ‹በአምስት አቦ ናቸው በሰባት ሥላሴ› የሚል ሐረግ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
፪. በባሕላዊ ዘመን ቆጠራ
አቦ በገበሬው የወቅት አከፋፈል የዘመን መክፈያ ናቸው፡፡
1.      በገበሬው የዘመን ቆጠራ ክረምት የሚገባው ‹የሐምሌ አቦ› ዕለት ነው፡፡ የሚወጣው ደግሞ ‹የጥቅምት አቦ›፡፡
2.     በልግ ይገባል የሚባለው በየካቲት አቦ ስለሆነ ገበሬው ‹የካቲት አቦን አይተህ ተሰደድ› ይላል፡፡ በየካቲት አቦ ዝናብ ካልጣለ በልግ የለም ማለት ስለሆነ ሀገርህን ልቀቅ ነው፡፤
3.     በገበሬው ዘንድ የወሩ መግቢያ የአቦ ቀን ነው፡፡ ቀጠሮ ሲይዝ ‹አቦ በዋለ በዚህኛው ቀን› ብሎ ነው፡፡

      . አቦና ዐርበኛነት
የአቦ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በአንኮበር፣ በጎንደርና በአዲስ አበባ ስማቸው ከዐርበኛነት ጋር ይነሣል፡፡ በሦስቱም ቦታ የሚገኙት የአቦ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በአምስት ዓመቱ የጣልያን ወረራ በግልጽ አርበኞችን ደግፈዋል፣ ወደ በረሐ ወርደውም ታግለዋል፡፡ በዚህ ምክያትም ሦስቱም አብያተ ክርስቲያናት በጣልያን ዝርፊያና አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የሦስቱም ካህናት ወደ በረሐ ሲገቡ የገጠሙት ግጥምም በሥነ ቃላችን ተላልፎ እኛ ዘመን ደርሷል፡፡
አንኮበር፡-
አቡዬን ብዬ እንጂ ይህን ሁሉ ማይ
አገሬ አይደለም ወይ ዠማና አዳባይ
ጎንደር
ፊት አቦ ጎንደር፡-
እንኳን እኔ ጀግናው የፊት አቦ ልጅ
ጎንደሬ ለጣልያን አይሰጠውም እጅ
ቀበና አቦ፣ አዲስ አበባ፡-
ወግጅልኝ ድጓ ወግጅልኝ ቅኔ
ወንዶች ከዋሉበት እውላለሁ እኔ
፬. ስምና አቦ
እስከ አሁን ድረስ ባለው ባሕል ከእግዚአብሔርና ከቅድስት ድንግል ማርያም ስሞች ውጭ ስማቸው ስም የሚሆነው አቦ ናቸው፡፡ ‹አቦ ነሽ፣ አቦ ነህ› የሚል ስም አለን፡፡ በሌሎቹ ቅዱሳን ግን የለም፡፡ ዘርፍ ይጨመርበታል፡፡ ወለተ፣ ገብረ እንደሚለው ያለ፡፡
፭. አቦና ጠበል
የገጠር ሰው ትዳር ሲይዝ መጀመሪያ የሚጠጣው አቦን ነው፡፡ አቦን ቀድሞ የጠጣ ትዳሩ ይሠምራል፣ ከሰውም ጋር በሰላም ይኖራል ተብሎ ይታመናል፡፡
፮. አቦ የቅኔ መማሪያ
‹አቦ ቅኔ› ለቅኔ ተማሪ የመማሪያ ሁለት ቤት ቅኔ ነው
‹አቦ ውርዝው እምነ ኩሉ በለጡ
አንድ እንጀራ በጨው እስመ በማለዳ ለምጠጡ
ማጠቃለያ
ከላይ ያየናቸውን ሥነ ቃላውያን መረጃዎች መሠረት ስናደርግ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከሌሎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን በላይ በሕዝቡ ውስጥ ባሕላዊ ቦታ እንዳላቸው ያሳየናል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ምናልባት ‹ሽምግልናቸው› ሽምግልናን ከሚያከብረው ባሕላችን ጋር ተስማምቶ ወይም አብዛኛው ታሪካቸው ከቤተ መንግሥት የራቀ መሆኑ ሕዝባዊ ቅቡልነትን ስላስገኘላቸው ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጃ፡፡ በዚህ ረገድ ከእርሳቸው የላቀ ባሕላዊ ቦታ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያላት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት(የማርያም መቀነት፣ የማርያም አራስ፣ የማርያም ፈረስ፣ የማርያም ግርዝ፣ ማርያም በሽልም ታውጣሽ፣ ማርያም ትቅረብሽ፣ ወዘተ)፡፡
ይህ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ባሕላዊ ቦታ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በእምነት ውስጥ ካላቸው ቦታ በተጨማሪ በሕዝቡ ውስጥ ያላቸውን ሀገራዊ ሥፍራ የሚያሳይ፣ እነርሱን በተመለከተ የምንሠራቸው ሥራዎች የት ድረስ የሕዝቡን ታሪካዊና ባሕላዊ መሠረት ጭምር ሊያንጹ ወይም ሊንዱ እንደሚችሉ ደግመን እንድናስብ የሚያመለክተን ማሳያ ነው፡፡ 

ላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ

41 comments:

 1. እግዚአብሔር ይስጥልን፣ የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን ዲያቆን ዳንኤል። የሚገርም ነው አብዛኛውን የጻፍከውን አባባል ገጠር ስላደግሁ አውቀዋለሁ፥ ደግሞ ትክክል ነው። የደነቀኝ ግን ይህን ያህል ትኩረት ሰጥተህ በደንብ አብስለህ ያቀረብክበት እይታ ነው። እይታህን አብዝቶ ያስፋልህ ዲ/ዳንኤል!!!

  ReplyDelete
 2. Egziabhare yitbikih wendimie ageligilothinim yibaik.

  ReplyDelete
 3. ጥሩ ነው ያስተማርከን እግዚአብሔር ይስጥልን ፡፡

  ReplyDelete
 4. Very interesting post.
  It is good to find such an article which elaborates religiously and traditionally tied myths. Please keep it up! But I have few comments, though. My comment is related to the way you present the article, and not to the content. I have given you the same criticism before and I am still not clear why you prefer to mix research (scientific) method and a diary way of writing. Majority of this text is research based and you wrote most of its part that way, except some regularities like the sentence below.
  "...ታሪካቸው ከቤተ መንግሥት የራቀ መሆኑ ሕዝባዊ ቅቡልነትን ስላስገኘላቸው ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጃ፡፡"

  I would say, you should stick with passive form of sentence and may be never use active sentence like above

  ReplyDelete
 5. አቦ ርእሰ ባህታዊ፣ካህናተ ሰማይ ፣ፓትርያርከ ኢትዮጺያ በመጨረሻው ሰአት በኢትዮጺያ ምድር ላይ የተበተውን እርኩስ መንፈስ ለማሰር የመሚመጡ ቅዱስ አባታችን በረከታቸው ይደርብን፡፡

  ReplyDelete
 6. ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማልን! ለእኔ ትልቅ ቦታ አላቸው አባታችን. ሥዕላቸውን መመልከት በራሱ የተሥፋ መልዕክት ነው የሚያሰተላልፉልን. ከምንወዳቸውና ከምናከብራቸው ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈሰ ቅዱሰ ምልጃቸውና በረከተቸው, እንዲሁም እረድኤታቸው አይለየን. አሜን!!!

  ReplyDelete
 7. የሚገርም ዕይታ ነው፡፡ለብዙ ጥናትም በር የሚከፍት ይመስለኛል፡፡
  አቡሄ ፃድቁ ይራዱህ!!

  ReplyDelete
 8. አመሠግናለሁ እግዚአብሄር እድሜ እና ጤና ይሦጥ።

  ReplyDelete
 9. ታቦትን በእኛ ኅብረተሰብ ባህልና ሕይወት ውስጥ በስፋት እንዲታወቅ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መሃከል ዋነኛው ታምረኛነቱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እመቤታችን ጻድቅና ኃጥዕ ሳትለይ ሁላችንንም በምትጎበኝበት ተአምራቶቿ የኢትዮጵያውያን ሁሉ እናት ሁናለች፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም በገዳማቸውና በየደብሮቻቸው ለምዕመናን የሚያደርጉት ተአምራት አይነትና ድንቅነት መወደድና ዝናን ሰፊ ተቀባይነትንም አድሏቸዋል፡፡ ወደድንም ጠላንም ተአምራት ታላቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ ጌታ ስብከቶቹን በተአምራት ባይቀምም ኖሮ ተከታይ ባላፈራም ነበር፡፡ ተአምራት ጎልተው የማይታዩባቸው ታቦታት በገዛ አጥቢያቸው እንኳ ዕውቅናቸው ያነሰ ነው፡፡

  ReplyDelete
 10. ዳኒ የኔ አክስት ሙስሊም ናት ግን ያአቦ ጸበል በየአመቱ ታደርጋለች እኔም ደፍሬ ጠይቂአት አላውቅም ብዙ ጊዜ ይሄን ሳስብ እገረማለሁ

  ReplyDelete
 11. ዳኒ መልካም እይታህን አበረከተክልን ዕድሜና ጤና ፈጣሪ ያድልልህ ትንሽ ጠፋ ስትል እንዴት ይርበናል መሰለህ ግን ቆይታህን ሁሉ አምላክ የበለጠ አድርጎ የተሻለ ያሳየናል ብየ ሁሌ ተስፋ አደርጋለሁ።

  ReplyDelete
 12. ተወልጄ ባደግሁበት አካባቢ ጥንታዊ የአቦ ቤተ ክርስቲያን አለ፣ ከቤተክርስቲያኗ አጠገብ በቅዱስ አባታችን ስም ፀበል አለ፣ ፀበሉ እጅግ የሚገርም ተአምረኛ ነው፣ የፀበሉ ጣእም ጨዋማ ሲሆን የአካባቢውን ህብረተሰብ ብሎም ራቅ ካሉ አካባቢዎች ለሚመጡ ሰዎች ለዘመናት የፈውስ አገልግሎት ሰጥቷል፣ እየሰጠም ይገኛል፣ እዚህ ፀበል ዘንድ መጥቶ ሳይፈወስ የሚሄድ የለም፣ ፈዋሽነቱ ለሰው ብቻ አይደለም ፣ ለእንስሳትም ጭምር እንጅ፣ በተለይ ለብዙ ጊዜ ሳትወልድ የቆየች ላም ፀበሉን ከጠጣች በአጭር ጊዜ ትወልዳለች፣ የታመመ ከብትም እንዲሁ ፣ ለቅዱስ አባታችን የተሰጣቸው ቃል ኪዳን በህብረተሰቡ ዘንድ እጅግ ሰርጾ የገባ ነው፣

  እንደምናውቀው በተለይ በገጠሩ የሚኖረው ኦርቶዶክሳዊ ምእመን ማህበር የሚመሰርተው በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን በተሰየመ ቅዱስ ስም ነው ፣ አንዳንድ ጊዜ የሁለት ማህበር አባል ይሆናሉ፣ በአብዛኛው ማለት ይቻላል ሁለተኛው የፅዋ ማህበር የአቦ ነው የሚሆነው፣ ለምሳሌ የወላጆቼ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ በአለ ወልድ ሲሆን በአምላካችን ስም የበኣለ እግዚአብሄር መደበኛ ወርሃዊ የፅዋ ማህበር አላቸው፣ ሁለተኛው ደግሞ የፃድቁ የአቦዬ ማህበር ፣ እውነትም ፃድቁ በህብረተሰባችን የእለት ተእለት ሀይማኖታዊም ሆነ ባህላዊ ህይወት ውስጥ እጅግ የተዋሃደ ስም አላቸው፣ የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ማለት ይህ ነው!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Maru, would you tell where this miraculous Church with its holy water is found? You didn't mention where your locality is. Thanks!

   Delete
 13. ዲ/ዳኒ ጽሁፎችህን በተቻለ መጠን ተከታትዬ አነባለሁ በጣም አስተማሪዎች ናቸው በርታ ፈጣሪ ጸጋውን ያብዛልህ
  ማጠቃለያህ ላይ የጻፍኸው ነገር ሰሞኑን የማውቀውን ነገር ግን ያላስተዋልሁትን ነገር አስተዋል" ቤዛዊተ ዓለም" የሚል ከድንግል ማርያም ስዕል ስር የተጻፈ በጣም ገረመኝ እኔ እንደገባኝ የአለም ቤዛ ሆኖ ነፍሱን ስለእኛ የሰጠ ልጇ እየሱስ ክርስቶስ ነው ታድያ ይህ አባባል ባህላዊ ነው ወይስ መንፈሳዊ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ እንደሚል የማይገባ ክብርስ መንፈሳዊነት ነው? ወይስ እኔ ያልገባኝ ነገር ካለ በዚህ አጋጣሚ ብታስረዳኝ፡፡

  ReplyDelete
 14. Thank you so much!

  ReplyDelete
 15. ጻድቁ በትግራይ አቡዬ ????????????????????????????
  NOOOOOOOOOOOOOOO
  ጻድቁ በትግራይ እና በ ኤርትራ አባ ጋብር ወይም ጋብር ይባላሉ እንጂ “አቡዬ” አይባሉም:: ዬ እኮ የኣማርኛ የኔነት ነው እንጂ የትግርኛ አይደለም፡፡ የ “አቡዬ” ትገርኛ “አቦይ” ነው ወደ ግእዝ ለማስጠጋት ከሆነ “ አቡየ ” ነው፡፡

  ReplyDelete
 16. ሰላም ዲያቆን ዳንኤል፤
  መልካም ዕይታ ነው። ግን እኔ ያስተዋልኩት አንድ ነገር አለ። በጽሁፍህ መግቢያ አካባቢ እንደጠቀስከው፤ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ግን የማይራራቁ መጠሪያዎች አሉኣቸው።

  ነገር ግን አንዱ መጠሪያቸው ይኸውም አቦ የሚለው መጠሪያቸው ብቻ ነው በብዙ ማሳያዎችህ ምሳሌ ያደረከው። ምናልባት ይኼ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ በኦሮሞው ማኅበረሰብ የበለጠ ቅርበት ወይም ተወዳጅነት አላቸው ብዬ እንድገምት አድርጎኛል፤ ልክ አባታችን አቡነ አረጋዊ በትግሬው እና በ ኤርትራው ማኅበረሰብ አንዳላቸው ተወዳጅነት።
  አንተ በዚህ መልኩ ተመልክተኸዋል ወይ? ይኽስ የሆነበት ታሪካዊ ክስተት ወይም አጋጣሚ አለ ወይ?
  እግዚአብሔር ይስጥህ፤ ሌላ እስክታስነብበን በተስፋ እጠብቃለው።

  ReplyDelete
 17. Very interesting which revises both spiritual and cultural views and nicely summarised. Please write similar articles sometimes

  ReplyDelete
 18. በ ጠበል በ ልጅነቴ ከ ሕማሜ የ ፈወሱኝ ናቸው:: በ ጥቅምት ፭ ከ አደጋ የተበቁኝ
  የማከብራቸው ፃድቅ ናቸው ::

  ReplyDelete
 19. be tyake amekagnnet yekerebut tshufoch mels btsetachew?

  ReplyDelete
 20. ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማልን! ለእኔ ትልቅ ቦታ አላቸው አባታችን. ሥዕላቸውን መመልከት በራሱ የተሥፋ መልዕክት ነው የሚያሰተላልፉልን. ከምንወዳቸውና ከምናከብራቸው ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈሰ ቅዱሰ ምልጃቸውና በረከተቸው, እንዲሁም እረድኤታቸው አይለየን. አሜን!!!

  ReplyDelete
 21. ዲያቆን ዳንኤል የእናቴን ነፍስ ይማር እና እናቴን ጨምሮ 65 የሰፈር እናቶች በአባታችን ስም የጽዋ ማእበር አላቸው በ 5አመት አንዴ ይደርሳቸዋል ደግሞ ለሀዘንም ግዜ እንደመረዳጃም ነው አባታችንን በጣም በየውሩ ሲዘክሮቸው አውቃለሁ በጣም የሚገርመው ደግሞ የእናቴ አባት ስም አቦ መሆኑ በኦሮሞ ብሄር አቦ ተብለው እንደሚጠሩ እኔም ላረጋግጥልእ እወዳለሁ እግዛብኤር ጸጋውን ያብዛልክ ወንድማችን ጽሀፍእ ሀሌም አስተማሪ እና ተናፋቂ ነው።

  ReplyDelete
 22. ሌሎች ሰዎች የፃፎትን comment, (copy paste)አናድርግ፠ጥሩ ልምድ አይደለም


  ReplyDelete
 23. ‹አቦ› እግዚአብሔር ይባርክህ።

  ReplyDelete
 24. በእርግጥ አዲስ ታሪክ አዲስ ትምህርት ነው የተማርኩት ዳንኤል አግዚአብሔር እድሜህን ያዝርምልህ!!

  ReplyDelete
 25. ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥህ በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው፡፡ የአቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክ አገራችን ኢትዮጵያን ህዝቦቿን ይጠብቅልን በረከታቸው ይደርብን!!

  ReplyDelete
 26. betam des yemil eyita new , EGZABIHER TSEGAW YABZALI . yegeremenge neger kale gn be @maru kebede yetesetew comment lay , hagerachin eritrea wust be (mendefera) yemibal sefer YE TSAEDIQ ABATACHIN SEBEL BOTA ALE (HOLYWATER) wndimachin endegelesew sebelu chewama new bzu sewoch demo yitatebalu moslim bebizat yemitatebulet sefer new eza bota demo bzu yefewsi agelgulot ena tamirat yitayal . tsebelu yehuletu sefer and mehonu gin geremenge rasu ehe tamirat new . YEABATACHIN TSELOTINA REDIET YITEBIQENGE .EGZABIHER YIMESGHEN .

  ReplyDelete
 27. በእርግጥ አዲስ ታሪክ አዲስ ትምህርት ነው የተማርኩት ዳንኤል አግዚአብሔር እድሜህን ያዝርምልህ!!

  ReplyDelete
 28. Des Yilal, YeAbune Gebremenfes kidus bereket, redietachaw beigna yideribin.

  ReplyDelete
 29. GOD bless you. Thanks.

  ReplyDelete
 30. Deacon Daniel please tell us about history of st.george i need to more information in amharic
  Thank you

  ReplyDelete
 31. ቅዱሱ አባታችን' ከሕግዚአብሔር ከራሱ ከሌሎች ስዎች በተለየ አይነት ሁለት አስደናቂ ጸጋዎችን ሲወለዱ ጀምሮ የተሰጣቸው አለ ማንም ክርስቲያን ሊያውቀውና ሊያምነው የሚገባ ነው ። እነርሱም =
  1ኛ- 'ቅዱሱ አባታችን' ከተወለዱ ጀምሮ እስከ ሚሞቱ ድረስ የናታቸውን (የጡት ወተትን) ጨምሮ ምንም አይነት ምድራዊ (ምግብና - የሚጠጣ) ነገርን ያልቀመሱ ናቸው።
  2ኛ- 'ቅዱሱ አባታችን' ሲወለዱ ጀምሮ ሁሉም ስውነታቸው በሙሉ ከስው በተለየ መልኩ በጸጉር የተሽፈነና የተመላ በመኦኑና አብርዋቸው ከእድገታቸው ጋር በተአምር ስለሚያድግ ምድራዊ ልብስ አላስፈለጋቸውም። ይህም በገድላቸው መጽሐፍ ላይ ትጽፎ ይገኛል። በረከታቸው ይደርብን፡ አሜን።

  ReplyDelete
 32. He is one of remarkable Ethiopian legend.

  ReplyDelete
 33. እንዳንተ አይነት ሰዎችን እግዚአብሔር ያብዛልን አሜን

  ReplyDelete