(ያሬድ ሹመቴ)
አያልቅበት ስንታየሁ ሱዳን ውስጥ ለ3 ዓመት ያህል የኖረ የብርሀኑ ጌታነህ ወዳጅ ነው። የሚናፍቃቸውን እና ያላባት ብቻቸውን ያሳደጉትን፤ ለስደቱ ምክንያት የሆኑትን እናቱን ለማየት የዛሬ ዓመት ገደማ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
ሱዳን በነበረበት ወቅት ከራሱ ተርፎ እናቱን ለመርዳት የሚልካት ጥቂት ገንዘብ በስተርጅናቸው ሰው ቤት ተቀጥረው የጉልበት ስራ ከመስራት አላዳናቸውም።
ወይዘሮ አለሚቱ በላይነህ ልጃቸው ሱዳን ሳለ የሚልክላቸው ገንዘብ ከቤት ክራይ ክፍያ ውጪ የማይሸፍንላቸው ቢሆንም፤ ችግራቸውን ለልጃቸው ነግረው ከማሳቀቅ፤ በስተርጅናቸው የጉልበት ስራ ውስጥ ገብተው ኑሮዋቸውን በመከራ ተያይዘው ቆዪ።
የእናቱ ነገር የማይሆንለት አያልቅበት፤ በናፍቆቱ ምክንያት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ግን ሱዳን እያለ ይልክ የነበረው ገንዘብ ምን ያህል የእናቱን ህይወት ፈቅ ማድረግ እንደተሳነው ተረዳ።
የዚያን ጊዜ ታድያ ከሱዳን አድማስ ማዶ፤ እናቱን ለመጦር ይችልበት ዘንድ ተስፋ የጣለበትን የባህር ላይ ጉዞ ህልም ሰነቀ።
ለልጆቹ ህይወት በእጅጉ ከሚጨነቀው የረዥም ጊዜ ወዳጁ ብርሀኑ ጌታሁን ጋርም ሀሳባቸው ገጠመ። ወደ ሊቢያም በጋራ ሊሻገሩ ተቃጠሩ። ልጆችን ለማሳደግና እናትን ለመጦር።
አያልቅበት በሀምሌ 5፣ 2007 ዓ.ም ወደ ሱዳን ለመመለስ በሚሸኝበት ጊዜ፤ ከዚህ ቀደም በሰላም ደርሶ የተመለሰው ልጃቸው ተመልሶ የሚመጣው መርዶው መሆኑን ፈፅሞውኑ ባይገቱም ካይናቸው ልጃቸው ከሚርቅ በርሀብ ቀድመውት ቢሞቱ መርጠው ነበር።
የብርሀኑ እና አያልቅበት ቀጠሮ ቀን ሲደርስ፤ ብርሀኑ ሚስቱን "ድሬዳዋ ለስራ መሄዴ ነው፤ ስልኬ ግን አይሰራም" ብሎ ሀገሩን ለቆ ወደ ሱዳን አመራ።
በተቀጣጠሩ በስድስት ወራቸው ሱዳን ላይ የተገናኙት እኒህ የልብ ወዳጆች፤ አንዳቸው ስለ ልጅ አንዳቸው ስለ እናት ፍቅር ምስክር ሆነው። ልጆቹን ለናታቸው አደራ ሰጥቶ የተሰደደው፤ ለእናት የሚሰጥ ፍቅር ሀያልነት በአያልቅበት ሲማር፤ ለልጆቹ ሲል የተሰደደው ብርሀኑ ደግሞ በተራው የአባት ፍቅር ምሳሌው ነበር።
ወይዘሮ አለሚቱ፤ አያልቅበት ከሄደ በጝላም ቢሆን የዘወትር ፀሎታቸው የሚወዱት ልጃቸው መንከራተት በቅቶት ከእቅፋቸው ዳግም እንዲገባ ነበር።
የሀገራችን ሰማይ ጠቁሮ፤ ኢትዮጵያም አምርራ በልጆችዎ የግፍ ሞት ስታለቅስ፤ እንደ ብርሀኑ ባለቤት ብርቱካን እና መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአያልቅበት እናትም እንባቸውን ይዘረግፉት ነበር። ሊቢያ የማን ሀገር ጎረቤት እንደሆነች እንክዋን የማያውቁት እናት እንዲሁ በደፈናው ልጆቼ ለሚልዋቸው የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሁሉ ያነቡ ነበር።
ከሚወደው ወዳጁ ብርሀኑ ጎን በሊቢያ በርሀ አንገቱን ለሰይፍ የሰጠው አያልቅበት ሰማዕትነቱ የተሰማው ዘግይቶ የሁሉም ቤት ሀዘን በመብረድ ላይ ሳለ ነበር።
የእኒህን እናት አይን ለማየት በውነቱ ማን ይደፍር ይሆን? የሀዘናቸውንስ ጥልቀት ምን ይገልፀው ይሆን? በምንስ አይነት መንገድ....?
ዛሬም ቢሆን ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቶአል። ገርጂ ከጊዮርጊስ ቤ.ክርስቲያን ጀርባ በምትገኘው ሰማዕቱ ልጃቸው በተከራየላቸው ጠባብ ቤት ውስጥ፤ በብቸኝነት ተኮራምተው፤ አንድያ ልጃቸው ተመልሶ እንደማያዪት ከተረዱ ሳምንት ሳይሞላቸው ያለ አስተዛዛኝ ብቻቸውን የተቀመጡት እናት፤ የሚያነጋግራቸው ዘመድ፣ ሲቦርቁ እያዪ የሚፅናኑባቸው ህፃናት የሌሉበት ጠባብ ቤት ያለመጠን ሰፍቶ ፍርሀት ሲያነግስባቸው፤ ቤታቸው የተሰቀለው ልጃቸውን ከነገዳዩ የሚያሳይ ምስል እያባነነ እንቅልፍ ሲከለክላቸው፤ ይህንን ሁሉ እየሰማን እና ይህን ሁሉ እያየን ዝም የምንል መሆናችን ያሳፍራል። (በእርግጥ ለህዝቡ ማን ነገረው? የመንግስት ሚድያዎች በሌሎች ጉዳዮች ተጠምደዋል።
ሀላፊነታቸውን በብርቱ ይወጡ የነበሩ ጋዜጦች እና መጵሄቶች ዛሬ በስራ ላይ የሉም) ዛሬስ እኔም እፍረት በዝቶብኝ አንቆ ሊደፋኝ ደርሶዋል።
አያልቅበት እኮ "የሞተው ሁላችንንም ተክቶ ነው። እሱ እኮ አንገቱን የደፋው የናቱን አንገት ቀና ሊያደርግ ነው።"
በኢትዮጵያ አምላክ እለምናለው አዛውንት እናትና ህፃናት ልጆች አንድ ናቸው። ስደቱም የመጣው ለማሳደግና ለመጦር ነው። እኚህን እናት አጠገባቸው ሄደን እናጽናናቸው። ቀሪ ህይወታቸውንም ወድቀው እንዳይቀሩ እንደግፋቸው።
የሰማዕቱ አያልቅበት ድምጽ ግን ይሰማል። ብቸኛዋን "እናቴን አደራ"።
ለሰማዕቱ አያልቅበት ነፍስ ይማርልን!! እንፀድቅባቸው ዘንድ እናቱንም ትቶልን ከሱ ሰማዕትነት
በረከት እንድንሳተፍ እነሆ "እናቴን አደራ" ይለናል።
ከቻሉ በአካል ተገኝተው እናታችንን ያፅናኑ፤ ካልቻሉ ይህን መልዕክት share በማድረግ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች መሆናችንን (እንግለጥ።)
አሁንም በድጋሚ እናገራለው። ከብዙ ቃል መግባት ጥቂት ቃልን መፈፀም ዋጋው የላቀ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን!!

እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ ያጽናልን።
ReplyDeleteThanks for sharing the information
ReplyDeleteI will do my best Dn. Daniel cry cry . . . E/R yakibirih nurilin . . .
ReplyDeleteምን አይነት እምነት ነው? ምን አይነት ጽናት ነው? አያልቅበት የታተመበት የመንፈስ ቅዱስ ማእተብስ ምን አይነት ነው? እሱ በአርባ ቀኑ በጥምቀት ዳግም ሲወለድ የታተመበት የልጅነት ምልክት ማእተቡ እንዴት ያለነው? እኔን በሱ ተክቸ ሳስበው፤ እናቱንም የኔ አድርጌ ስስላት እንሿን ስለት ባንገቴ ሆኖ ይቅርና ገና በንግግር ማተብህን በጥስ የሚለውን ስሰማ የማረግድ የታዘዝኩትን ከመፈፀም ሆኘ ነው የሚሰማኝ። ወንድማችንም ሆነ አብረውት ሰማእትነትን የተቀበሉት በዘመኑ አለመኞች እምነታችን በልባችን ነው እንደሚሉት አስመሳዮች ማተባችን በልባችን ነው ብለው የሰይጣንን መሸንገያ ቋንቋ ሳይጠቀሙ እንደ ሰለስቱ ደቂቅ አንገታችንን በኀይፋችሁ ቅሉት ግንባራችንን በመትረይሳችሁ በትኑት እንጂ እኔስ ተዋህዶ እምነቴን የክርስቶስኔቴን ማእተቤን አልበጥስም ሞቶ ያዳነኝን ህይወት የሰጠኝን አልክደም ብለው በተግባር የመሰከሩ የክርስቶስን መስቀል የተሸከሙ ናቸው። እናም እንደተባለው የሰማዕቱ እናት የኑሮ እሳት ከሐዘኑ ጋ ተደምሮ እንዳይሰብራቸው፤ በእምነት እንዳያደክማቸው ፤ ክፉዎች ገብተው እንዳይጥሏቸው ማጽናናት መደገፍ በመንፈሳዊ ህይወታቸውም ማጠንከር ተገቢ ነው። ስለሆነም በሩቅ ያለነውም እንዳቅማችንና ፍላጎታችን የበረከቱ ተካፋይ የምንሆንበት መንገድ ቢዘጋጅና ቢገለጽልን መልካም ነው እላለሁ። ዲያቆን ዳንኤል አንተንም እግዚአብሔር ይባርክህ የቅዱሳኑ ምልጃና ፀጋም አይለይህ።
ReplyDeleteእናት ሆኖ ልጄ ልጄ እንደ ማለት የሚከብድ ነገር የለም. እንዴት ይሆን ሀዘናቸውን ሊረሱ የሚችሉት? የሚያቃጥል ሀዘን! ዲያቆን ዳኒ ,እንዴት ነው መርዳት የምንችለው? እንደ እግዚሃብሔር ፈቃድ ወደ ኢትዬጵያ ከመመለሥህ በፊት የገንዘብ እርዳታ ተደርጎ ይዘህ የምትሄድበትን መንገድ ቢፈለግ? ወይንም የተከፈተ የባንክ አካውንት ካላቸው?እንዴት እንደምናገኞቸው ብትነግረን መልካም ነው. ይህ የሁላችንም የኢትዬጵዬን ግዴታ ነው. መድሃሂያለም ፅናቱን ለእናታችን ይሰጥልን አሜን! የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን አሜን! አንተንም መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!
ReplyDeleteበገንዘብም ቢሆን መርዳት እንድንችል እርሳቸው የሚገኙበትን ስልክ ወይም አድራሻ ብትተውልን።
ReplyDeleteትክክለኛ መረጃ የሚያደርስ ለህዝብ የቆመ መገናኛ መንገድ ጠፋ እኮ፣ምን ይሻለን ይሆን?
ReplyDeleteየሰማዕታቱ በረከት ይደርብንና የእነርሱን ቤተሰብ ለመርዳት ህዝቡ ቢፈልግ የተደራጀ የገንዘብ አሰባሰብና ኃለፊነት ወስዶ የሚንቀሳቀስ ተአማኒ ኮሚቴ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ መንገዶች ገንዘብ ማሰባሰብ ይቻላል(sms-text፣ ዝግጅቶችን በመሥራት፣ ወዘተ.)፡፡ ይህን በማድረግ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማሳተፍ ይቻላል፡ ጥቁር ሱፍ ለብሶ በቲቪ መታየት በቂ አይደለም፡፡ መንግስትም፣ድርጅቶችም፣ ህዝቡም አስተዋጽኦ ማድረግ የጠበቅባቸዋል፡፡
ReplyDeleteየሰማዕቱ አያልቅበት ድምጽ ግን ይሰማል። ብቸኛዋን "እናቴን አደራ"።
ReplyDeleteOur mother's phone no.pls
ReplyDeleteDn. Daniel, thank you for your follow-up on the families of the Martyrs. We need to seriously discuss and organize how to help their families. It should not be a onetime help. We need to see who needs education, who needs help to make himself/ herself productive, and who needs month to month help depending on their age and health. We should not be emotional always. We need to be reasonable. We need to put ourselves in their families’ shoes. Also, we need to be Thankful to Almighty God, that we are in a position of giving.
ReplyDelete1ኛ ዮሐ: 3: 17-18 ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።
Medhanialem metsenanatun yistahew! hey danel i live in canada how cwn i help
ReplyDeletehurry up let us know the address
ReplyDeletekalehiwet yasemaln diaqon ende semaetu birhanu enatachn yemnredabet menged btamechachln
ReplyDelete"...በእርግጥ ለህዝቡ ማን ነገረው? ... አዛውንት እናትና ህፃናት ልጆች አንድ ናቸው። ስደቱም የመጣው ለማሳደግና ለመጦር ነው። እኚህን እናት አጠገባቸው ሄደን እናጽናናቸው። ቀሪ ህይወታቸውንም ወድቀው እንዳይቀሩ እንደግፋቸው።"
ReplyDeleteእግዚአብሔር መፅናናቱን ይላክላቸው፡፡
ReplyDeleteDear Ethiopians,
ReplyDeletelet us cooperate and support these two families.If we have one heart and thought it will be easy!God be with us.
ዳኔ ልርዳባይ ሳይጠፋ በምን መልኩ ይድረስ? ያው መላው ይፈለግና በግዜ እንድረስላቸው ።
ReplyDeleteእድሜና ጤና ላንተ ይሁን ።አሜን
bank account binegeren
ReplyDeleteሰላም ዲ, ዳንኤል ሰሞኑን ድምፅህ ጠፋብኝ መቼም የጠፋህበት ለኛው መልካም ድግስ አዘጋጅተህ ብቅ ለማለት እንደሆነ አምናለሁ ።
ReplyDeleteእናትነት ማለት ለወለዱት ልጅ ብቻ የሚንሰፈሰፍ አንጀት ብቻ እንዳልሆነ የሰማዕቱ አያልቅበት እናት ምስክር ናቸው። የልጃቸውን ሞት ከመስማታቸው በፊት ሌላውን ሲያሰተዛዝኑ፤ በጎን ደግሞ ያ የወላድ አንጀት የልጄ እጣስ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ ሲሞግት፤ ልጅ በስደተ ሰማዕት ሆኖ መርዶ ሳይደርሱ መቆየት፤ ቆይቶ መርዶ በር ሲያንኳኳ፤ ኦ አምላኬ ይህች እናት ምን ያክል ተጎዱ? እስኪ እናስበው! ዳኒ ከቻልክ( ዲያቆን ዳንኤል) ከቻልክ ለዚች ክብርት ኣናተ ሁሉም እንደየአቅሙ እንዲረዳ የባንክ ቡክ ቢከፈት እና ቁጥሩ ይፋ ቢሆነ ጥሩ ነው ባይ ነኝ! እርግጥ ከፍቅር በላይ ምንም የለም፤ ማዕናናት ትልቅ ነገር ነው! እናቱን የሚወድ ተየጎዱ፤ ያዘኑትን እና የተከፉትን ከመርዳት እና ከማዕናናት ይጀምራል! እማማ እግዚአብሔር ያዕናሽ! አሜን!................................የሰማዕቱ አያልቅበት ድምጽ ግን ይሰማል። ብቸኛዋን "እናቴን አደራ"።
ReplyDeletee/r yasinalin....zts all i wanna say!!! ye semaitatu bereket yederibin.
ReplyDeleteI want to help how can I get her contact information
ReplyDeleteእግዚአብሔር አምላክ ፅናት ይሁናቸው። የአበልን ደም የተበቀለ እግዚአብሔር ለዚህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ደም መፍሰስ ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በጊዜው ይበቀል አሜን።
ReplyDeleteእግዚአብሔር አምላክ ፅናት ይሁናቸው። የአበልን ደም የተበቀለ እግዚአብሔር ለዚህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ደም መፍሰስ ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በጊዜው ይበቀል አሜን።
ReplyDelete