Thursday, April 2, 2015

ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤትበግእዝ የተጻፉ ጥንታውያን መዛግብት ከተጻፉበት ዓላማ በተጨማሪ ሌሎችንም አገልግሎቶች ሲሰጡ ኖረዋል፡፡ አብዛኞቹ የተጻፉት ለሃይማኖት ማስተማሪያነትና ለታሪክ መመዝገቢያነት ቢሆንም በየዘመናቱ የተፈጠሩትን ማኅበራዊ ክስተቶች ተከትለው ሌሎችንም አገልግሎቶች ሰጥተዋል፡፡
በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ አንደኛውን እንመለከታለን፡፡ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች  ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ሆነው ሲያገለግሉ የኖሩበትን አሠራር፡፡
በጥንታውያን የግእዝ የብራና  ጽሑፎች  ላይ ከሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘቶች በተጨማሪ በመጻሕፍቱ መጀመሪያና መጨረሻ በሚኖሩ ባዶ የብራና ቅጠሎች፣ በኅዳጎች፣ በራስጌና  በግርጌ ክፍት ቦታዎች ላይ ውሎችን፣ ቃል ኪዳኖችንና ስጦታዎችን ሲመዘግቡ ኖረዋል፡፡ እነዚህ ምዝገባዎች በተዋዋዮቹ፣ በገዥዎቹና  ሻጮቹ፣  በስጦታ ሰጭዎቹ ወዘተ መካከል የሚኖሩትን ስምምነቶች በማስፈር እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት እየሆኑ ማገልገላቸውን ያሳዩናል፡፡

( ጥናታዊ ጽሑፉን ቀጥሎ ካለው የፒዲኤፍ ፋይል ይመልከቱ)


16 comments:

 1. I don't understand how this could be a research article. It is simply collected information.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you know what research is?

   Delete
 2. እግዚአብሔር ይስጥልን ዲያቆን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. First thing it has a methodology and procedure to do it.............. Gebre Medhin

   Delete
 3. እግዚአብሔር ይመሰገን እሰካሁን በመኖራቸውም! በአቀማመጥ የተጉዱ ይመሰላሉ. ብንጠቀምባቸው ይጠቅሙናል. ዲያቆን ዳኒ ,ቸር ያሰማህ አሜን!

  ReplyDelete
 4. Dear Diakon Dani,

  Is it a research or provoking idea for conducting research regarding the issue raised? Difficult to accept it as a research or am I confused....
  Anyway keep it up your strong useful and valuable work. I always appreciate yours supper eagle eyed. Long-live for you forever here and there.

  ReplyDelete
 5. Dani enda Matusal edimhn yarzimew

  ReplyDelete
 6. Dn Daniel, I don't whether you have said something about these "Brana" Books before. But this is one of the issues i was always worrying about- Keeping our precious manuscripts properly. Specially how they should be kept securely and confidentially. So please say something, so that we can have some idea. Thank you!

  ReplyDelete
 7. Dani edmena tena yisth .

  ReplyDelete
 8. Deacon Daniel edmena tena yisth.

  ReplyDelete
 9. There is difference in writing a biography and a scientific letter. Scientific journals should be written in passive form or if necessary to write in active the subject should be plural ("We", in this case).
  "የብራና መጻሕፍት ይህንን አገልግሎት መስጠት የጀመሩት ከየትኛው ከዘመን አንሥቶ እንደሆነ ርግጠኛ መረጃ አላገኘሁም፡፡"

  ReplyDelete
  Replies
  1. አላገኘሁም አላገኘሁም አላገኘሁም አላገኘሁም አላገኘሁም

   Delete
 10. Dear Dani

  It is a great article but I think there is error in the paper which I noticed and needs correction i.e. the date of the Garima Gospel which is stated in the 8th C but on the contrary they are dated to be from late 4th C to early 7thC.

  A short explanation about this situation is provided in Amharic with relevant references.

  I hope you make this useful correction. Thank You.

  እነዚህ የወንጌል መጽሐፍትበተለያዩ ወቅቶች በተደረጉ ሳይንሳዊ ምርምሮች ዘመናቸው በአክሱም ዘመን መሠራታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ለምሳሌ በ2000 እ.ኤ.አ. በጃክየስ መርስዬር የተጠና ራድዮ ካርበን ውጤት እንደሚያሳየው ለአውሳብዮስ ቀኖና ለያዘ የብራና ክፍል 430-650 ዓ.ም. እና ከወንጌላውያኑ ሥዕሎች ለአንዱ 330-540 ዓ.ም. አመላከተ፡፡ ከዚህ በመቀጠለም በ2010 እ.ኤ.አ. በሳይንቲስቶች በድጋሚ የተደረገ ተመሳሳይ ጥናት ውጤቱ ከ300 ዓ.ም. እስከ 650 ዓ.ም. የመጽሐፍቱን ዕድሜ አስቀመጠ፡፡ ዳግመኛም የኦክስፎርድ ዩኒቨርሰቲ ጥናትና ምርመር ቡድን (The University of Oxford’s Research Laboratory for Archaeology and the History of Art) ተጨማሪ ናሙና ወስዶ ተመሳሳይ ውጤት አገኘ፡፡ በቅርቡም በ2013 እ.ኤ.አ. ማብቂያ ላይ በኢትዮጵያ ሄሪቴጅ ፈንድ (Ethiopian Heritage Fund) አዘጋጅነት በኦክስፎርድ በተደረገ ኮንፍረንስ ላይም የአባ ገሪማ ወንጌል ‹‹ገሪማ ፩›› ከ390 -570 ዓ.ም. እና ‹‹ገሪማ ፪›› ከ530 -630 ዓ.ም. ዕድሜያቸውን አስቀምጧል፡፡ በዚህ ኮንፍርንስ ላይም ጃክየስ መርስዬር መጽሐፍቱ በዘመነ አክሱም መጻፋቸው ብቻ ሰይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሥዕሎቹንም ጨምሮ ነው የተሰሩት በማለት ያስረዳል፡፡

  Alessandro Bausi. Ethiopia and the Mediterranean World in Late Antiquity: The Garimā Gospels in Context.

  Alessandro Bausi, “The ‘TrueStory’ of the Abba Gärima Gospels”, COMSt Newsletter 1, 2011, p. 17–20.

  Earliest Christian Manuscript: Illuminated Art in Garima Gospels http://www.decodedpast.com/garima-gospels-earliest-christian-manuscript /4358 .

  THE ART NEWSPAPER. Research uncovers lost African school of painting፡ Analysis of illuminated gospels suggests that first Christian manuscript art may have come from Ethiopia. Number 252, December 2013.

  ReplyDelete