Tuesday, April 7, 2015

ግብረ ሕማማት

click here for pdf
በቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሕይወት ውስጥ ታላቅ ቦታ ካላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ‹መጽሐፈ ግብረ ሕማማት› ነው፡፡ ሊቃውንቱ ‹ግብር› የሚለውን ‹አገልግሎት› ብለው ይተረጉሙትና ‹ግብረ ሕማማት› ማለት ‹በሕማማት ወቅት የሚፈጸም አገልግሎት› ማለት ነው ይላሉ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹እርሱ ሕመማችንን ተሸከመ›(ኢሳ 53÷4) በማለት የገለጠው ኃይለ ቃል ለሰሙኑም ሆነ ለመጽሐፉ ስያሜ መነሻ መሆኑንን ሊቃውንቱ ይገልጣሉ፡፡ ሐዋርያትም በሥርዓት መጽሐፋቸው ‹ወአንትሙሰ ተዐቀቡ ወግበሩ ተዝካረ ሕማማቲሁ - እናንተ ግን ተጠበቁ፣ የሕማማቱንም መታሰቢያ አድርጉ› ብለው ደንግገዋል (ግብረ ሕማማት፣ 1996፣9)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ‹ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሐተ - የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ይመስገን› ብሎ ገልጦ ነበር፡፡ (ዝኒ ከማሁ፣10) 

ግብረ ሕማማት ከበዓለ ሆሳዕና እስከ በዓለ ፋሲካ የሚከናወነውን ሥርዓት የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው፡፡ የመጽሐፉ የተወሰነ ክፍልና ሥርዓቱ ከ8ኛው መክዘ ቀደም ብሎ ጀምሮ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነበረ፡፡ አሁን ያለውን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሰሙነ ሕማማት መጽሐፍ (ፓሻ) ያዘጋጁት አቡነ ገብርኤል 2ኛ(1131-1145) የተባሉት የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው፡፡ ፓትርያርክ ገብርኤል አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስና የሊቃውንት ትርጓሜ ዕውቀት ያላቸው ሊቃውንት በማሰባሰብ ለየሰዓቱና ለየኩነቱ የሚነበበውን ሥርዓትና ንባብ አዘጋጁ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በሰላማ መተርጉም ጊዜ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡(ዝኒ ከማሁ፣ 9) ከጎንደር መድኃኔዓለም ተወስዶ በብሪቲሽ ሙዝየም በሚገኘው ግብረ ሕማማት ላይ ከአባ ሕርያቆስ ድርሳን መጨረሻ ላይ ‹‹ዘንተ መጽሐፈ ዘተርጎመ ብፁዕ ወርቱዕ ሃይማኖት አቡነ አባ ሰላማ ይጽሕፍ ስሞ እግዚአብሔር ውስተ መጽሐፈ ሕይወት› ይላል፡፡ (catalogue Ethiopian manuscripts in British Library, 140) 

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንደሚሉት ከሆነ ግብረ ሕማማትን አሁን ባለው መልክ ያዘጋጁት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ናቸው፡፡ እስከ 14ኛው መክዘ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሰሙነ ሕማማት የሚሆኑ የጸሎት ሥርዓት ሳይኖሯት ቆየች ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ አቡነ ሰላማ መተርጉም የተወሰነውን የመጽሐፈ ግብረ ሕማማት ድርሳናት በመተርጎም ቀድሞ በነበረው የሰሙነ ሕማማት የጸሎት ሥርዓት ውስጥ መጨመራቸውን ይገልጣሉ፡፡ አሁን ባሉን የግብረ ሕማማት ቅጅዎች የአቡነ ሰላማን ስም የሚያነሣው ከሊቃውንቱ ደርሳናት መጨረሻ ላይ የሆነውም ለዚህ ሊሆን ይችላል፡፡ አቡነ ሰላማ መተርጉም ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን አሰባስበው የትርጉም ሥራ ይሠሩ የነበሩት በደቡብ ጎንደር ስማዳ በምትገኘው ደብረ ዕንቁ ማርያም ነበር፡፡ አቡነ ሰላማ የግብጹን ግብረ ሕማማት ይዘውት የመጡ ይመስላል፡፡ በደብረ ዕንቁ የነበሩ ሊቃውንት መጽሐፉን መነሻ በማድረግና ከቀደመው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ጋር በማስማት አሁን የምናውቀውን ግብረ ሕማማት አዘጋጅተውልናል፡፡ 

እስካሁን ባሉን መረጃዎች ረጅም እድሜ ያስቆጠሩት የግብረ ሕማማት ቅጅዎች በ15ኛው መክዘ የተጻፉት ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ሦስቱ በኢትዮጵያ ማይክሮ ፊልም ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ (EMML 1765, 4434, 4752) EMML 1765 የሐይቅ እስጢፋኖስ ቅጅ ሲሆን በዚህ መጽሐፍ ላይ ልዩ ልዩ ድርሳናትን የተረጎሙት አባ ሰላማ መሆናቸውን ይገልጣል፡፡ EMML 4434 የእንዳፍሬ ማርያም(ሞረት) ሲሆን EMML 4752 ደግሞ ሰሜን ሸዋ የሚገኘው የሙሽ ዜና ማርቆስ ንብረት ነው፡፡

በግብረ ሕማማት ውስጥ ከጾመ ድጓና ምዕራፍ የተወሰዱ ጸሎቶች መኖራቸው፤ በግብጹ መጽሐፍ ላይ የሌሉ ከተአምረ ማርያምና ክተአምረ ኢየሱስ የሚነበቡ ምንባባት መገኘታቸው፤ እንዲሁም የቀረቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በቅርጽ ካልሆነ በቀር በብዛትና በዓይነት የተለዩ መሆናቸው ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የመጽሐፉን መነሻ ከግብጽ ወስደው ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንዲሆን አድርገው ማዘጋጀታቸውን እንደሚያሳይ የሚገልጡ አሉ፡፡ ለብዙ ዘመናት ግብረ ሕማማት በግእዝ ብቻ የሚገኝ መጽሐፍ ነበር፡፡ በ1990(?)ዓም በሊቀ መዘምራን ላዕከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ(ዘአሰላ) ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ታትሟል፡፡

በግብረ ሕማማት ውስጥ ሦስት ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ጸሎት ሲሆን ‹ዐማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም› እየተባለ የሚጸለየውና ካህናትና ምእመናን በየመካከሉ የሚደግሙት ዳዊት የዚሁ መገለጫ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ስግደት ነው፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት፣ በሦስት፣ በስድስት፣ በዘጠኝና በ11 ሰዓት ከጸሎት ጋር የሚደረግ ስግደት አለ፡፡ በዕለተ ዓርብ ደግሞ የ12 ሰዓት ጸሎትና ስግደት አለው፡፡ ከግብረ ሕማማት ትልቁን ቦታ የሚይዘው ሦስተኛው ክፍል ንባቡ ነው፡፡
በሰሙነ ሕማማት በመጽሐፈ ግብረ ሕማማት መሠረት የሚነበቡ ብዙ ምንባባት አሉ፡፡ እነዚህንም በአራት መድበን መመልከት እንችላለን፡፡
1.      መጽሐፍ ቅዱስ፡- በተለይም በዋናነት ከብሉይ ኪዳን ከኦሪት፣ ከጥበብ መጻሕፍት(ምሳሌ፣ መኃያ መኃይ፣ ጥበበ ሰሎሞን፣ ሲራክ፣ ኢዮብ)፣ ከመጽሐፈ ኢያሱ፣ ከመጽሐፈ ሩትና ከሌሎችም የሚቀርቡ ከሰሞኑ ጋር የሚሄዱ ምንባባት አሉ፡፡
2.     ትርጓሜ፡- የልዩ ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ትርጓሜ ይነበባል፡፡ በተለይ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያን ትርጓሜ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከእርሱም ጋር የኤጲፋንዮስ፣ የአትናቴዎስ፣ የቄርሎስና የያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜያት ይሰማሉ፡፡
3.     ምዕዳን፡- በግብረ ሕማማት የክርስቲያንን ልዩ እሴቶች የሚመለከቱ ምክሮች ይቀርባሉ፡፡ ስለ ፍቅር፣ ይቅርታ፣ ወገንን መርዳት የተመለከቱ ምንባባት አሉ፡፡
4.     መጻሕፍተ ሊቃውንት፡- በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከተዘጋጁና እምብዛም ከማናገኛቸው ድርሳናት መካከል በግብረ ሕማማት ውስጥ የምንሰማቸው አሉ፡፡ መጽሐፈ ዶርሖ፣ ላሃ ማርያም ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ ከተለመዱት ምንባባት ደግሞ ስንክሳር፣ ተአምረ ኢየሱስና ተአምረ ማርያም ይጠቀሳሉ፡፡
   በተለይ በአሁኑ ጊዜ መጽሐፉ በአማርኛ የሚነበብ በመሆኑ ምእመናን ሁላችን በማስተዋል ብናዳምጥ በሌላ ጊዜ የማናገኛቸውን የቤተ ክርስቲያን ታሪኮች፣ ምሥጢራትና ምንባባትን የምናዳምጥበት ዕድል ይሆናል፡፡ የኛን ግብረ ሕማማት ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማነጻጸር ይኼን መሥመር በመከተል የእነርሱን ግብረ ሕማማት በእንግሊዝኛ መመልከት ይችላል፡፡ http://ixoyc.net/data/Fathers/118.pdf
መልካም ሰሙነ ሕማማት፡፡

32 comments:

 1. Deacon Daneal, GOd Bless you and give you more time and energy for doing more such spiritual service. Amen!!!
  Welde Gebreal - Bahir dar.

  ReplyDelete
 2. በተለይ በአሁኑ ጊዜ መጽሐፉ በአማርኛ የሚነበብ በመሆኑ ምእመናን ሁላችን በማስተዋል ብናዳምጥ በሌላ ጊዜ የማናገኛቸውን የቤተ ክርስቲያን ታሪኮች፣ ምሥጢራትና ምንባባትን የምናዳምጥበት ዕድል ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 3. እንደሁልጊዜውም መልካም ነገር ነው ያስተማርከን፣አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት ይባርክህ።

  ReplyDelete
 4. እንደሁልጊዜውም መልካም ነገር ነው ያስተማርከን፣አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት ይባርክህ።

  ReplyDelete
 5. በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
  በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
  ኪርያላይሶን
  ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
  ናይናን
  የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
  እብኖዲ
  የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው
  ታኦስ
  የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
  ማስያስ
  የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው
  ትስቡጣ
  «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
  አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
  Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so
  የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
  አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
  Em-nees the-tee mo-a-geh-e enti vasilia so
  የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው
  አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
  Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so
  የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

  ከዲያቆን ዳንኤል የ2012 ጹሑፍ የተወሰደ

  ReplyDelete
 6. ዳኒ ላንተም መልካም ሰሞነ እማማት
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን
  አጋጣሚውን ተጠቅመ ስለ ወቅቱ በጥያቄ እና መልስ የተወሰነ ነገር ብትጽፍልን መልካም መሰለኝ ምክንያቱም አንዳንዶቻችን ትክክል ነን ብለን የምናስበውና ትክክል የሚሆነው ስለሚለያይ ማለቴ ነው፡፡ በጣም ትልቅ ጉዳይ ነው ብዬ ሳይሆን አጋጣሚውን ተጠቅመን ትክክለኛወንም ነገር ብናውቅስ….. ለምሳሌ ሰላምታችን፣ በግዝት ቀኖች ይሰገዳል አይሰገድም፣ የሚጸለይ የማይጸለይ ጸሎት ከነ አመክንዬ እና ሌሎች አንተ ያስፈልጋሉ የምትላቸውን ጉዳዮች
  ከተቻለ በዚህ ሳምንት ከተፈጸመው ነገር በመነሳት…….. ለመንፈሳዊ፣ለማህበራዊ፣ለአገራዊ ጉዳዬች ብትመክረን ልክ እንደ ጲላጦስ አይነቶች፣ ልክ ህለቱ አርብ ነው አይነት
  በድጋሚ መልካም ሰሞነ እማማት ከቤተሰቦች ጋር

  ReplyDelete
 7. Thanks Decon, when I saw Egypt book one question came to my mind . First thanks our father like mezmeran la'ek MARIAM translated to amharic. My question is when will be our book came by pdf like Egypt Coptic church?

  ReplyDelete
 8. ሁላችንም ሰምተን በሰራ ላይ ለማዋል የቅዱሳን አምላክ ይርዳን አሜን!ሁል ጊዜ ጥሩ ነገር እንድታቀረብ ጥበቡን የሰጠህ እግዚሃብሔር ይመሰገን !ዲያቆን ዳኒ መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!

  ReplyDelete
 9. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 10. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 11. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 12. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 13. Thank you for the insight.My computer couldn't open it and it warns it has virus with it

  ReplyDelete
 14. ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
 15. Kalehiwot Yasemalin Mengist Semayat Yawursilin. D.n Daniel.

  ReplyDelete
 16. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 17. Kalheywot yasmalen egzabhar yebrekh

  ReplyDelete
 18. It is also my question to get it in PDF.

  ReplyDelete
 19. መልካም አደረክ ዳኒ መናፍቃኖች ግብፅ ለኢትዮጵያ ወሩን በሙሉ በአል ነው በማለት አስተምራ እንዳይሰሩ አደረገችና እራስዋ ግብፅ ግን ግድቡን ሰርታ ጨረሰች ብለው ያወሩትንና ያሳመኑትን ህዝብ እራሳችን የሀይማኖት ሊቃውንት እንዳሉንና የራሳችን ህግ እንዳለን አስረግጠህ ገልፀህልናል
  እግዚአብሄር ይባርክህ መልካም በአል በየትኛውም አለም ላለነው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ይሁንልን።

  ReplyDelete
 20. ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
 21. Egziabher yistln amlak zemenhin yibark.

  ReplyDelete
 22. Kalheywot yasmalen egzabhar yebrekh
  addis nagn

  ReplyDelete
 23. ዳኒ የእንግሊዘኛውን ሶፍት ቅጂ አስቀመጠ ሌሎች ደግሞ የኛን ግብረ ህማማት መጽሐፍ ጭነውልናል http://ethiopianorthodox.org/amharic/holybooks/gibre%20himamat%20-%20Gunda%20Gunde.pdf

  ReplyDelete
 24. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 25. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 26. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 27. Memihir,Gibre hmamate sinebeb hizibu min eyaderege endehone astewilet yawikalu biye egemitalehu.ene rasen chemiro minalbat yetewesenu kalatin kalhone besteker betikikil gibre himamatu min eyetebal endeminebeb mesimat ayichalim bekunkua chiger mikniyat.kahinatu yenibab chilotachewn lemasayet enji bewnet sile mekera ena sikaye yemiiyanebu ayimesilum.egna binesemam banisemam gid yelachewim ejig betam befitnet gobez anibabi lemebal(andandie ende fukara yemikataw ale) bemimesil melku yanebalu.kekahinatu wchi yalew hizib ketikitoch besteker geez ayichilim ena kuch bilo yerasun lela mestehaf yanebal wey behasab befeterew alem yibazinal....Enam ke 10 amet belay himamatun semiche and mulu paragraph mesimat alchalkum ..minale be amaregna binebeb min chiger alew bezih zuria tinesh bitsfu lewit yenor yihonalna ebakiwet yemefithae haseb yitekumun.

  ReplyDelete
 28. ምነው ወደ አማርኛ የተረጎሙትን ሊቅ ምንም ሳትላቸው የግድ……… መሆን አለባቸው።

  ReplyDelete