Friday, April 24, 2015

እየተስተዋለ


እነዚህ ወገኖቻችን ሰማዕታት ናቸው፡፡ ሃይማኖታቸውን አንለውጥም ብለው የተሠዉ፡፡ ‹ስደተኛ ኢትዮጵያውያን› የሚለውን አገላለጽ ነፍሴ ትጸየፈዋለች፡፡ ከአኩሪው የሰማዕትነት ተግባራቸው በላይ ስደተኛነታቸው ለማጉላት ስለሚያኮበኩብ፡፡ ሰው በሀገሩ ቢኖር፣ ቢሠራና ቢከብር የመጀመሪያ ምርጫው ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያውያን፡፡ ነገር ግን ‹እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል› ይባላልና የቸገረው ቢሰደድ ምን ይፈረድበታል? በርግጥ ስደቱ በሰላም፣ በሕግና በጤና ቢሆን የማይወድ የለም፡፡ ግን ሁል ጊዜ ይቻላል ወይ? ምቹ ሁኔታስ አለ ወይ? ዛሬ ከአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራልያ፣ ከአፍሪካና እስያ ገንዘባቸውን እየላኩ አንዳንዴ ከቡና በላይ አንዳንዴም ከቡና ቀጥሎ የውጭ ምንዛሬውን የሚያስገኙልን ወገኖች አብዛኞቹ ዛሬ ‹ሕገ ወጥ› በምንለው መልኩ የሄዱ አይደለም ወይ? እንዲያ እንዲሆኑ ያደረጋቸውን መሠረታዊ ምክንያት መፍታት እንጂ የሆኑበትን መንገድ ማውገዝ ምን ይጠቅማል? 
 
በሀገራችን ኢትዮጵያ እየኖሩ በአክራሪዎችና አሸባሪዎች ሕይወታቸው የተሠዉ ክርስቲያኖች አልነበሩም ወይ? በ1980ዎቹ መግቢያ በአሰቦት ገዳም የታረዱት መነኮሳት፣ በአርሲ ኮፈሌ የተገደሉትን ምእመናንና በ1998 ዓ.ም. በጅማ በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተሠዉት ምእመናንና ካህናት ስደተኞች ሆነው አልነበረምኮ? ክርስቲያን ስለሆኑ እንጂ፡፡ በአይሲስ እጅ ወደቀው ከነበሩት መካከልኮ እነርሱ የእስልምና እምነት ይከተላሉ ብለው ያሰቧቸውን ሱዳናውያንና ሶማልያውያንን ያለ ምንም እንግልት ይለቋቸዋል፡፡ የቁርዐን ጥያቄ የሚጠየቁት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ናቸው፡፡ ከእነርሱም መካከል ሙስሊም አይደለም ብለው ያሰቡትን ነው በኮንቴይነር አስገብተው ወደ አልታወቀ ሥፍራ የሚወስዱት፡፡ እነዚህም ቢሆኑ ምርጫ ይቀርብላቸዋል፡፡ ‹እስልምናን ወይንም ሞትን መቀበል› እምነታችንን አንለውጥም ሲሉ ይገደላሉ፡፡ አይሲስ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ክርስቲያኖችን ሲያርድ በግድ እንዲመለከት የተደረገው ኤርትራዊው የ16 ዓመት አዳጊ ወጣት ናኤል ጎይቶም ከእጃቸው አምልጦ ከወጣ በኋላ ለኢንተርናሽል ቢዝነስ ታይምስ የነገረውም ይሄንኑ ነው፡፡ ለቪኦኤ ቃሉን የሰጠው ከሞት ያመለጠ ወጣት ይህንኑ ያረጋገጠ ነበር፡፡ አይሲስም በአድራሻ ‹ጠላታችን ለሆነቺው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን› ብሎ ተናግሯል፡፡ አይሲስ ራሱ ሀገራዊ ብሔርተኝነትን ሳይሆን ሃይማኖታዊ ብሔርተኝነትን ማስፈን ነው  ዓላማው፡፡ ሊመሠርትም የተነሣው ‹የእስልምናን መንግሥት› ነው፡፡
ይኼ ሁሉ የሚያሳየው እነዚህ ወንድሞቻችን የተሠዉት ክርስቲያን በመሆናቸው እንደሆነ ነው፡፡ በንግግራችንም ሆነ በመግለጫችን ልንናገረው የሚገባን እውነትም ይኼው ነው፡፡ ሕገ ወጥ ስደትን እንኳን እኛ ስደተኛው ራሱም አይፈልገውም፡፡ የሞታቸው ዋና ምክንያት ግን ስደት አይደለም፡፡ ያ ቢሆን አብረዋቸው የተሰደዱት ሶማልያውያንና ሱዳናውያንም ይገደሉ ነበር፡፡ ምክንያቱ ክርስትናቸው ነው፡፡ እነርሱን ‹ባይሄዱ ኖሮ አይገደሉም ነበር› በሚል ዓይነት ጥፋተኞች ለማድረግ ለምን እንደክማለን፡፡ እነርሱ የአቋም ሰዎች ናቸው፡፡ ዘላቂውን አቋም ለጊዜያዊ ጥቅም መቀየር ያልፈቀዱ፡፡
ስለ እነዚህ ወንድሞች ክርስትና መናገር ሌሎች አማኞችን ያስቀይማል ወይም ያገላል ብለን ከሆነ ስሕተት ነው፡፡ ሙስሊሞችና ሌሎችም ወገኖቻችን ‹ማንም በእምነቱ ምክንያት መገደሉን እናወግዛለን› እያሉኮ ነው፡፡ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ርእሰ መንበር ‹በዲናችን አስተምሮና አሳምኖ እንጂ አስገድዶና ገድሎ እምነት ማስቀየርን አንቀበልም› ነው ያሉት፡፡ ይኼ ነገር እነዚህ ወገኖቻችን በግድ እምነታችሁን ቀይሩ ተብለው በአረመኔዎች መገደላቸውን እየነገሩን ነው፡፡
ከአይሲስ እጅ በእግዚአብሔር ቸርነት ለወሬ ነጋሪነት ያመለጡ ወገኖች እንደሚናገሩት አይሲስ ትልቁ ትኩረቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ ስደተኞች ላይ ነው፡፡ ሱዳናውያንንና ሶማልያውያን ወዲያው ነው የሚለቀው፡፡ በተለይ ደግሞ የመስቀል ምልክት በሰውነታቸው ላይ የተነቀሱና ሌሎች ሃይማኖታዊ ምልክቶችን ያደረጉትን ወዲያው ያለምንም ጥያቄ ክርስቲያን መሆናቸው አረጋግጦ ለብቻ በኮንቴይነር ያስቀምጣቸዋል፡፡ ከአይሲስ ጋር የሚደረግ ውይይት፣ ድርድር፣ ክርክር የለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የለበሱት የሊቢያ ወታደሮችን ልብስ ስለሆነ እነማን እንደሆኑ የሚታወቀው በኋላ ነው፡፡ የሰዎችን ጥያቄና ልመና ለማስተናገድ ዕድል የሚሰጡ አይደሉም፡፡
ከዚህ አንጻር ከኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ጋር ጀማል የተባለ ሶማልያዊ ሙስሊም ‹ክርስቲያኖችን እረዳለሁ ብሎ› አብሮ ተሠውቷል የሚለውን መረጃ ለመቀበል ይቸግራል፡፡ በመጀመሪያ ሶማልያውያንን ለጥያቄ አያቀርቧቸውም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ጓደኞቼን ትቼ አልሄድም ስላለ አይሲስ ‹ና አብረሃቸው ሂድ› ብሎ አስተያየት የሚያደርግ ቡድን አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ተጓዦቹ ሲያዙ የሊቢያ ወታደሮች እንደያዟቸው እንጂ አይሲስ መሆናቸውን የሚያውቁበት ዕድል የለም፡፡ የለበሱት የወታደር ልብስ ነው፡፡ የመጀመሪያው መለያየት የሚፈጠረው ደግሞ እምነትን ሳይሆን ዜግነትን መሠረት አድርጎ ነው፡፡ ሶማልያውያንና ሱዳናውያን ወዲያው ያስኬዳሉ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን ይይዛሉ፡፡ ሶማልያውያንና ሱዳናውያን የሚይዙት የተለየ እምነታቸውን የሚጠራጥር ነገር ካገኙባቸው ብቻ ነው፡፡ እንደ ማተብ፣ የመስቀል ንቅሳት፣ የአለባበስ ለውጥ ወዘተ፡፡ ክርስትና ጥያቄ ሆኖ የሚመጣው ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዘንድ፡፡
በዚህ ሁሉ ነገር ጀማል ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ለመርዳት ዕድል የሚያገኝበት መንገድ የለም፡፡ ቢፈልግ እንኳን፡፡ እርሱ ከሶማልያውያን ጋር መጀመሪያ ተለይቶ ወይ ሄዷል፤ ወይ ሌላ ቦታ ተቀምጧል፡፡ እስካሁን ለማምለጥ ዕድል ያገኙ ወገኖችም ይህንን ታሪክ አያውቁትም፡፡ መረጃውን ሰጡ የተባሉት የሶማልያ ምንጮች ናቸው፡፡ ተርፈው የወጡ ወገኖች የሚጠራጠሩት ሁለት ነገር ነው፡፡ አንድ ጀማል እምነቱን ቀይሮ ክርስቲያን ከሆነና ይህንንም ከመሰከረ፤ ሁለት በሰውነቱ ላይ የመስቀል ንቅሳት አሠርቶ ከሆነ፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ሶማልያዊ ሙስሊም ሆኖ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚታረድበት በቂ ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ እንኳን ለመታረድ አብሮ ለመቆየት ዕድል የለውም፡፡  
ይኼ ማለት ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን አይወዱም ወይም አይረዱም ማለት አይደለም፡፡ በሊቢያ ተደብቀው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መረዳዳቱን በሚገባ መስክረዋል፡፡ ይኼ የማይታበል ሐቅ ነው፡፡ ይኼ ነገር በራሱ ቆሞ ሊናገር የሚችል ስለሆነ ሌላ ነገር መፍጠር የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡
ጀማልን በተመለከተ የተሠራጨውን ዜና መቶ በመቶ አይሆንም ማለት አይቻልም፡፡ በቦታው የለንምና፡፡ ከዓይን ምስክሮችና በሊቢያ ምድር ከሚገኙ ምንጮች፣ ተርፈውም ለመገናኛ ብዙኃን ምስክርነት ከሰጡ ሰዎች ተነሥተን ስናየው ግን ‹ተረጋግጦ ያለቀ እውነት ነው› ብሎ ለመቀበል የበለጠ መረጃ የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡   
እነዚህን ወገኖች ለማሰብ፣ ቤተሰቡን ለማጽናናት በቀጣይም ተመሳሳይ ነገር እንዳይከሰት ለመሥራት ቤተ መንግሥት፣ ቤተ ክህነት፣ ሚዲያዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የንግድ ተቋማትና ሌሎችም እያደረጉ ያለው ነገር ነገሩን በኢትዮጵያዊ ባሕልና ወግ መሠረት ለማከናወን የሚደረገውን ጥረት ያሳያል፡፡ በየእምነት ተቋማቱ ጸሎት እየተደረገ ነው፡፡ በየ አጥቢያው ምሕላ እየተከናወነ ነው፡፡ በኀዘንተኞቹ ቤት ሕዝቡ በነቂስ እየተገኘ ኀዘኑን እየተካፈለ ነው፡፡ ኀዘንተኞቹም በሕዝቡ አጋርነት እየተጽናኑ ነው፡፡ ፓርላማው ያወጀው የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን እየተተገበረ ነው፡፡ የሚስመሰግን ነው፡፡
የምናደርጋቸው ነገሮች ግን እምነቱንና ትውፊቱን፣ ወጉንና ባሕሉን፣ ኅሊናንና ሰብእናን የጠበቁ ቢሆኑ መልካም ይሆናሉ፡፡ ርዳታችን፣ ኀዘናችን፣ ማጽናናታችን፣ ችግሩን ለመፍታት መሯሯጣችን እምነት፣ ኅሊና፣ ባሕልና ወግ አስገድዶን እንጂ ለተወዳጅነትና ለገጽታ ግንባታ ባይሆን ይመረጣል፡፡ የወገኖቻችንን መሥዋዕትነት ለፖለቲካ ጥቅም፣ ለሚዲያ ፍጆታ፣ ሩኅሩኅነታችንን ለማሳያ፣ ለጋስነታችንን ለማስመስከሪያ እንድንጠቀምበት ኢትዮጵያዊ ባሕልና ወግ አይፈቅድልንም፡፡ የምንሰጠው ገንዘብ፣ የምንወስደው የእዝን እንጀራ፣ የምንደርሰው ልቅሶ ሁሉ እየተቀረጸ፣ በፎቶ እየተነሣ፣ በሬዲዮ እየተላለፈ የሚደረግ ከሆነ ለራሳችን ገጽታ ስንል እንጂ አዝነን ያደረግነው መሆኑን ያጠራጥራል፡፡ ሌሎች ስለ እኛ ይናገሩ እንጂ እንዴት ‹ይህን አድርገናል፣ ይህን ሰጥተናል› እያልን ራሳችንን ራሳችን እንቀርጻለን፣ ራሳችንንስ እንዴት ራሳችን እናስተዋውቃለን? ነውር ቀረ ማለት ነው? የንግድ ድርጅቶችና ‹ታላላቅ ሰዎች› ይህንን ለራስ መክበሪያነት ሲያውሉት ማየት ግን ያማል፡፡
አንዳንድ ሰዎችን አይተናል ረድተዋል፣ ልቅሶ ደርሰዋል፣ አጽናንተዋል፣ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ነጋሪት እየጎሰሙ አይደለም፡፡ በርግጥ በተራራ ላይ ያለች መብራት ልትሠወር ስለማይቻላት ሌሎች አይተዋቸው ስለ እነርሱ ዘግበዋል፡፡ እነርሱ ግን ‹እዩልን ስሙልን› አላሉም፡፡ ‹አምስት ሺ ብር ሰጠሁ፣ ዐሥር ሺ ብር ሰጠሁ› ሲሉ አልተሰሙም፡፡ ድርጊቱን የተደረገለትና ዋጋ ቆጣሪው አምላክ ያውቀዋል፡፡ በሚዲያ ገብተውም ‹እገሌ ይህንን ያህል ሺ ብር ስለሰጠዎት አመስግኑት› ብለው የኀዘንተኛ ምስጋና አልሰበሰቡም፡፡
ጎበዝ እየተስተዋለ እንጂ፤ አንገቱን ለሰጠ ገንዘብ ሰጥን ብለን ይሄ ሁሉ ነጋሪት?
  

34 comments:

 1. ዳኒ ሀሳቡ ግሩም ነው መደምደምያክ ላይ ያነሳህውም ሀሳብ መልካም ነው ግን ተግሳጽ ከራስ ይጀምራል አንተም ለቅሶ እንደሄድክ እና እንዳለቀስክ ጭምር በገዛ ጡመራህ ጽፈህ አስነብበህናል ስለዚህ ልክ ካልሆነ ያንተም ነው መነሳት የነበረበት ብዬ አምናለሁ

  ReplyDelete
 2. ዳኒ እግዚአብሔር ይሥጥህ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ፡፡ አምላከ ሰማዕታት ቤተሰብህን፤ እውቀትህን ይባርክልህ ፡፡
  ለምን እውነታውን ለመደበቅ እንደተፈለገ እኔም አይገባኝም ፡፡ ቤተክርስቲያንን ይበልጥ የሚያደማት የሰማዕታት እናት እዳትባል የቤተክርስቲያን ልጆች የሊብያን ሰማዕታት እያዩ እምነታቸውን እንዳያጠበክሩ የሚደረግ ፕሮፐጋንዳ ነው ፡፡ ስለሆነም በሊቢያ ሰማዕትነትን የተቀበሉት ህገ ወጥ ስደተኞች ሳይሆኑ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ፤የቤተክርስቲያን አበቦች ፤የቤተክርስቲያን እውነተኛ አገልጋዮች ፤ የቤተክርስቲያን የ21 ክፍለ ዘመን ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 3. ሃይማኖታቸውን አንለውጥም ብለው የተሠዉ፡፡ ‹ስደተኛ ኢትዮጵያውያን› የሚለውን አገላለጽ ነፍሴ ትጸየፈዋለች፡፡

  Thank you!!!

  ReplyDelete
 4. ዳኒ በእውነት ውስጤ ሲብሰለሰል የነበረውን ነገር ነው የተናገርከው ይህንን የሀዘን ሳምንት ከመንግስት ጀምሮ ብዙ ሰዎች ለሌላ አጀንዳ ሲጠቀሙበት ማየት ያሳፍራል በእውነት ለስንቱ እንዘን ለአይ ኤስ የግፍ ስራ፣ ለፌደራል ፖሊስ ዳግማዊ አይኤስነት ወይስ ለነዚህ ጥቅመኞች አይ እማማ ኢትዮጵያ ምነው መከራሽ በዛ ትንሳኤሽን ያሳየን

  ReplyDelete
 5. ዳኒ የፅሑፉ ሃሳብ ጥሩ ይዘት ተደስቼ ሳላበቃ መደምደሚያ ላይ ያነሳከው አቀራረብ በጣም ደስ አይልም facebook ላይ ሲያበሳጨን የዋለውን ፅሁፍ አይነት ይዘህ መቅረብህ አስከፍቶኛል። ለቅሶ ለመድረሱ አንተም ደርሰካል መሔድክንም አንተ ነግረከን ነው ያወቅነው፤ ማልቀስክንም እንደዚያው፤ ታዲያ ሌለው ሰው አደረገ ያልከውን ነገር ቢያደርክ ምንድን ነው ጥፋቱ አንተ ካደረከው ጋር ምንድን ነው ልዩነቱ በርግጥ የተነሳችሁበት አላማ አንተ ትምህርትን ወይም እይታህን በፅሑፍ ህዝብ ጋር ማድረስ ሌላኛው ደግሞ በፎቶ ወይም በቪዲዮ ቀርፆ ማስተላለፍ በተላለፈው መረጃ ለተጎጂዎች የሚሆን እርዳታ ማሰባሰብ ወይም አንተ እንዳልከው ራሳችን ገጽታ ለመገንባት አንድ ያልተረዳነው ነገር በጎ አድራጎት ከስብዓዊ ስሜት ወይም ከመንፈሳው ምግባር ከየትኛው የሚለውን ነገር ማጥራት ይኖርብናል። ከስብዓዊ ስሜት የሚመጣ ከሆነ ነጋሪት ማስደጎሙ ምንድን ነው ችግሩ እንደውም ሌላው መስጠትን እንዲማር ያደርጋል። ከመንፈሳዊ ምግባር አንፃር ከሆነ የምታደረጉትን በድብቅ አድረጉ እኔ አምላካችሁ የሰራችሁተን አያለሁ ብሎ አስተምሮናለ ስለዚህ እኛም እንደዚያው ብናደርግ ብለህ ልትል ትችል ይሆናል ግን ይሄ ይለያል። ደግሞስ ወደ ባህላችን እንመለስ ብለህ አስተምረክ ባህላችን የሚያሳይ ነገር ለማየት ቻልን መቼም አንድ ነገር ሙሉ በሙሉ እንከን አይወጣለትም ማለት ይከብዳል ደካማውን ነገር ሰዎች በአፋቸው እንዳይቀባበሉበት አድርገህ እንዲስተካከል አድርገህ መምከር ሲቻል ለምን ወቀሳን መረጥክ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ማለፍ እንደሌለብህ ይገበኛል ይሄን ግን በሂደት ማስተካከል የሚቻል ነገር ይመስለኛል። ለሁሉም ልብና ኩላሊትን የሚመረምር እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይለግሰን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርሱኮ ሄድኩ አለህ እንጂ ሄዶ ያደረገውን እንኳን አልነገረህም፡፡ ለፎቶ የሚሆን ሞባይልም አያጣም ነበር፡፡ ሀዘኑን ነገረን፡፡ እኔ እዚያው ልቅሶ ቤት ነበርኩ፡፡ እርሱ ያልፈለገውን አላነሳም ብየ እንጂ እነግርህ ነበር፡፡

   Delete
  2. በቦታው ላይ የነበረውን እና ያየውን ነገር ሲፅፍ የሚፅፈው ነገር ከሰዎች ሰምቶ ሳይሆን በትክክል እራሱ በቦታው ተገኝቶ ያየው ነገር መሆኑን ለመግለፅ ይመስለኛል "እዛ ተገኝቼ ነበር...እንደዚህ እይተደረገ ነው ..." እያለ የተናገረው እንጂ እንደሌሎቹ እንዲወራለት ፈልጎ አይመስለኝም።
   May the spirit of God be with u Dani, Amen!!!

   Delete
 6. ዲያቆን ዳኒ እግዚአብሔር ያክብርልኝ
  በእውነት ውስጤ ሲብሰለሰል የነበረውን ነገር ነው
  የምንሰጠው ገንዘብ፣ የምንወስደው የእዝን እንጀራ፣ የምንደርሰው ልቅሶ ሁሉ እየተቀረጸ፣ በፎቶ እየተነሣ፣ በሬዲዮ እየተላለፈ የሚደረግ ከሆነ ለራሳችን ገጽታ ስንል እንጂ አዝነን ያደረግነው መሆኑን ያጠራጥራል፡፡ ሌሎች ስለ እኛ ይናገሩ እንጂ እንዴት ‹ይህን አድርገናል፣ ይህን ሰጥተናል› እያልን ራሳችንን ራሳችን እንቀርጻለን፣ ራሳችንንስ እንዴት ራሳችን እናስተዋውቃለን? ነውር ቀረ ማለት ነው? የንግድ ድርጅቶችና ‹ታላላቅ ሰዎች› ይህንን ለራስ መክበሪያነት ሲያውሉት ማየት ግን ያማል፡፡
  አንዳንድ ሰዎችን አይተናል ረድተዋል፣ ልቅሶ ደርሰዋል፣ አጽናንተዋል፣ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ነጋሪት እየጎሰሙ አይደለም፡፡ በርግጥ በተራራ ላይ ያለች መብራት ልትሠወር ስለማይቻላት ሌሎች አይተዋቸው ስለ እነርሱ ዘግበዋል፡፡ እነርሱ ግን ‹እዩልን ስሙልን› አላሉም፡፡ ‹አምስት ሺ ብር ሰጠሁ፣ ዐሥር ሺ ብር ሰጠሁ› ሲሉ አልተሰሙም፡፡ ድርጊቱን የተደረገለትና ዋጋ ቆጣሪው አምላክ ያውቀዋል፡፡ በሚዲያ ገብተውም ‹እገሌ ይህንን ያህል ሺ ብር ስለሰጠዎት አመስግኑት› ብለው የኀዘንተኛ ምስጋና አልሰበሰቡም፡፡
  ጎበዝ እየተስተዋለ እንጂ፤ አንገቱን ለሰጠ ገንዘብ ሰጥን ብለን ይሄ ሁሉ ነጋሪት?

  ReplyDelete
 7. The arguments and the analysis you made on Jemal are a bit nebulous and contradicting. We do not know Jemal. Probably he was intimate with the victims and regardless of his religious faith he decided to follow them until death. ለነሱ ያለው 'ፍቅር' ከስደቱ 'ተስፋ' ከሐይማኖታዊ 'እምነቱም' ሊበልጥበት እና እስከሞት ሊከተላቸው ስለሚችል። ፍቅር ይበልጥ የለ ከሁሉም!? ሰብአዊ ፍጡር ማለት ደግሞ ይህ ነው። አስተሳሰብንም እምነትንም እንደጥበቁ ለሚወዱት መሞት። ይኽ ከሆነ ደግሞ ለአይ ሲስ ጀማል ሶማሌ መሆኑ፥ ወይም ሙስሊም መሆኑ ዋጋ ቢስ ነው። የጀማልን ሞት ከኢትዮጵያዊ/ሶማሊያዊ/ ወይም ኤርትራዊ ከሚል የብሔራዊ ብሔርተኝነት ወይም ደግሞ ፥ ወደ ክርስቲያን ከመለወጥነት ለይተን በሰባዊነት ብናስበው መልካም ነው።

  በሐዘን ላይ ሲቀለድ እና አድር ባይነት ማሳየት ግን እንሆ በመለስ ሞት ተጀመረ ይሔው አሁንም እንደ ባህል ቀጠለ።

  እንዲህ አይንት ነገር ሲፈጠር ግን ሶስት አይነት ይህዝብ ባህሪያት ይወጣሉ። አንዳንዱ ከልቡ ያዝናል ይረበሻል፥ አንዳንዱ ምንም የማይሰማው ይሆናል። ከነዚህ የባሰው ደግሞ እራሱን የማያዳምጥ፥ ስሜቱን የማያውቅ፥ ያዘነ እየመሰለው ዝምብሎ በነገሩ ድራማነትይዝናናል። የኢትዮጵያ አብዛኛው ታዋቂ ሰው በሶስተኛው ጎራ ነው የምናገኛቸው።

  ReplyDelete
 8. ሰማዕታት ማለት እኔን በሰው ፊት ያመነኝን ሰው እኔም በሰማያዊ አባቴ ፊት አምነዋለሁ ብሎ ክርስቶስ ስለእነርሱ የተናገረላቸው ናቸው፡፡ እነዚህን በመከራቸው ጊዜ ብትመስሏቸው ስለ ቁርጥ ሓሳባችሁ ሰማዕትነት ይቆጠርላችኋል፡፡ የተባለላቸው ናቸው፤ሰማዕታት ለሃይማኖታቸው ታማኞች ለመድኅኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ደማቅ ምስክሮች ናቸው፤
  ሰማዕታት በቅዱሳት መጻሕፍት ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ፤(ማቴ 10÷28) የሚለውን ቃል ተቀብለው ምርጫቸው እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ ያሳዩ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡
  ሰማዕታት የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው በተባለው መሠረት የመንግሥተ ሰማያትን የክብር አክሊል በጥበብ ጀምረው በደማቸው ምስክርነት የተቀዳጁ ናቸው፡፡
  ክብራቸውም አቡቀለምሲስ ዮሐንስ በራእዩ ምዕ 20 ቁጥር 4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእርሱ ላይ ለተቀመጡትም ዳኝነት ተሰጣቸው፣ ስለኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቆረጡባቸውን ሰዎችአየሁ ብሎ እንደተናገረው በእግዚአብሔር መንግሥት የማያልፍ አክሊልና የፍርድ ዙፋን የተዘጋጀላቸው ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 9. እውነትን መናገረ እራሱን የቻለ ሰማዕትነት ነው.እውነቱን እውነት ሐሰቱን አሰት እንበል . ክቡራን ወንድሞቻችን ይህንን አሰተምረውን ነው ያለፎት.እኛ ባንናገር ባንመሰክር አየነው እኮ ደማቸውን ሰጥተው መሰከሩልን.ለምን ሁሉ ነገር ፖለቲካ ይሆናል? ሃይማኖቴን መሰቀሌን መዐተሜን ኢትዬጵያውነቴን አልቀይርም ነው ያሉት. ክብር ለነሱ ይሁን! ምንም ያልተቀላቀለበት ምንም ጥርት ያለ እውነት. ሁሌም ሰው አለው መድሃሂያለም እውነቱን ሳያፍር ሳይፈራ የሚመሰክርለት ማየት ማመን ነው. አሳዬን !!! እምዬ ኢትዬጵያ ትንሳሔሽን ያሳየን አሜን!!! በእምነታችን ያፅናን !!!ዲያቆን ዳኒ, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 10. ጉዳዩ ግን መነጋገሪያ ርዕስ ነው። ዛሬ ይኼ የሃዘን አጋጣሚ ምክንያት ሆነ እንጂ፤ በየአብያተክርስቲያናቱ፤ በየልግስና ጣቢያዎች ረዳሁ/ረዳን ብሎ ማስነገር ክርስቲያናዊ አይደለም። በመንፈሳዊ ዓይን አንየው ብለን ብንልም በግለሰቡ ላይ የሚንፀባረቀው የራስወዳድነት ባሕርይ ማኅበረሰቡ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
  በአንፃሩ ደግሞ፤ ሲለግሱ ላለመታየት የሚደረግ ክልክ ያለፈ ጥረት ደግሞ ተገቢው ርዳታ ለተረጂው በወቅቱ እንዳይደርስ ያደርጋል።
  ልግሥና ሲዘወተር እነዚህ ጉዳዮች ቦታ ያጣሉ። እግዚአብሔር ዘወትር እጆቻችን ለልግሥናና ለምጽዋት የተዘረጉ ያድርግልን።
  ለሰማዕታቱ ቤተሰቦችም እግዚአብሔር ኀዘናችሁን ያሰስልላቹህ። ናዛዚትነ እምኅዘን ትናዝዛችሁ።

  ReplyDelete
 11. በሀገራችን ኢትዮጵያ እየኖሩ በአክራሪዎችና አሸባሪዎች ሕይወታቸው የተሠዉ ክርስቲያኖች አልነበሩም ወይ? በ1980ዎቹ መግቢያ በአሰቦት ገዳም የታረዱት መነኮሳት፣ በአርሲ ኮፈሌ የተገደሉትን ምእመናንና በ1998 ዓ.ም. በጅማ በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተሠዉት ምእመናንና ካህናት ስደተኞች ሆነው አልነበረምኮ? ክርስቲያን ስለሆኑ እንጂ

  ReplyDelete
 12. leg ega legachacten hymanotachawe ankedem blaw ytsstchwe merch embe blaw mswatenten end keds gwerges tkablew enge bsdtgantache mech honena hulem neg egezabher amlek ewentwen yferedal endhw bkentw ysmettoch dam aykerm!! derom leg stcger ymredh ymtaggw kteket egezabher kbarekachw new stmot gen wendmw serab ylabelaw setema ylatataw semat yezwez lekakh yelal me hnena now legachatchnee ysadatwe ayzachw ymelena salam ymestach legach ymeleach atew ywlegechcewn rhab chegr llmayt sertw lered eng lhyment mlewet sllhedw meleswn bsmetnt asatwe ynswe dem medetranyen bher yfssaw ysmetat dem alemen ydares lhlem ymastenkekey talk ymswetent dem new leb yl leb yebe ydengl mareyem ysret legwech smetent bkent aydelem egzabhern medelel aychalm mengawen mtbk zgawen menkebake yers!! wa!! wa!!ymzh smatat dem eych new!!leb ylew leb yebel!! lega egezabher ytabkh!!

  ReplyDelete
 13. ሰላም ጤና ይስጥልኝ። አንዳንድ የዘመኑ የፖለቲካ ሰዎች ይሀን የክርስትያኖች ሰማእትነት በመጠቀም፤ በተለይም "ጀማል" የተባለ እስላም አበሮ ተሰውቷል አያሉ እስልምናን ከፍ ከፍ ሲያደርጉ ይሰማሉ። ክርስቲያኖች ነን እያሉ "አይሲስ አሰልምናን አይወክልም" ይላሉ። ይህ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። አይሲስ እራሱ ወኪል ነኝ እያለ እነሱ ምን ቤት ናቸው? አይሲስ ግራኝ መሀመድ ያላደረገውን አደረገ እንዴ? ዐረቦች አፍሪካን ሲያሰልሙና ኢትዮጵያን ሲገነጣጥሏት ያላደረጉትን አደረገ እንዴ? ምነው ኢትዮጵያዊ እየተጃጃለ መጣ እንዴ? ጥንት አያቶቻቸው እምቢ ያሉት ታርደው፤ ሰይፍ አንገታቸው ላይ ሲውል እሺ ያሉት ደግሞ ሙሰሊሞች እንደሆኑ አሁን ያሉት ሙስሊሞቸ ተረድተው ወደ ቀደመችው ርቱእ ሀይማኖት ወደ ተዋሕዶ የሚመለሱበት ጊዜ አሁን ተከፍቶላቸዋል። አኪያሄዳቸውን ማየት እንጂ ክርስቲያን ሆኖ ለነሱ ማጨብጨብ አሳፋሪ ምግባር ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. kensu yebask atela ras neh bakih, Minilik ye Harar muslim maredun tawq yihon? ISIS meskid wust bomb yemiyafeneda naw. christian lemehon ISIS Muslim naw malet ayasfeligihim, eyetestewale!!

   Delete
 14. እኔ አሁን ሳስበው በህብረት ያበድን ይመስለኛል ነገሮችን እኛ በሚስማማን በኩል ተርጉመን ስናበቃ ከዛ" ይሄ ነው ትክክል ተቀበሉ" እንባላለን እኛም የነሡን ቃል በቀጥታ እንውጠዋለን አንዳንዶቻችን በየዋህነት ሌሎቻችን ሌላ ስም እንዳይሠጡን ፈርተን መቸም እኛ ሀገር በህብረት መስራት ከባድ ነው ግን በህብረት እናስባለን፣ በጅምላ እንናገራለን፣ በማህበር እንደግፋለን በአንጻሩም እንቃወማለን ከዛች ክበብ የወጣ ወዮለት ባልተፈጠረ ይሻለው ነበር እንዲል መፅሐፍ ሀበሻዊ እርግማን ሁሉ ይወርድበታል ደንደን ያለ ትከሻ ከሌለው ስድብና እርግማናቸው ውስጡ ገብቶ ያጠፋዋል፡፡
  ሠሞኑን በደረሠው አሳዛኝ ነገር በጣም እጅግ በጣም አዝኜያለው ያለኝ አቅም ለጊዜው እሡ ስለሆነ፡፡ሠሞኑን ከተነሡት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የወንድማችን የጀማል ጉዳይ ነው "ከክርስቲያን ጔደኞቼ አልለይም ብሎ ከነሡ ጋር ሠማዕት ሆነ" በረከቱ ይደርብን ግን እኔ የምለው እስቲ በዚያች ሠዓት እንደዛ ሲል ከየት ሠማችሁት የሚል ሠው አልነበረም ስለዚህ ተደጋግሞ ተወራ አሁን መረጃ ሲጠየቁ ድሮም አንተ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ልታፋጅ ነው ዱባ ፍሬ ገለመሌ ተባለ ለተጠየቁት ጥያቄ ቀጥታ መልስ መስጠት ነው ያለበለዚያ እንደ አዋቂ ሠው ጊዜ ወስዶ መረጃ መሠብሠብ እንጂ እኔ ያልኩትን ያልተቀበለ የማርያም ጠላት ነው አካሄድ የትም አያደርስም ደግሞም የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስትያኑ ዛሬ በጀማል ሞት አይደለም አንድ የሚሆነው ሙስሊሙ ከክርስትያኑ ፤ ክርስትያኑ ከሙስሊሙ ጋር አብሮ መኖርና መሞት የነበረ ነው ይህን ለማወቅ ወደኋላ ሄዶ ታሪክ ማገላበጥ ነው፡፡
  ሊቢያ ባለው ሁኔታ ግን አልለይም ብሎ የምትለዋ ቃል ለገዛ ፕሮፓጋንዳቹ መጠቀም ስለፈለጋቹ እንጂ አረጋግጣቹ ወይ ሠምታችሁ አይደለም፡፡ከተናገራችሁት ልጠይቃቹ
  1= ከክርስትያን ወንድሞቼ አልለይም አለ አላችሁ በምንድነው የማይለየው? ሀይማኖት እንጂ ዘር አልተጠየቁም በሊቢያ የነበርን ይሄ ሙስሊም ነህ ወይስ መሲህ( ክርስትያን) የሚለው ጥያቄ የዕለት ተዕለት ጥያቄ ነው ከስማችን በፊት ሀይማኖታችን ነው የምንጠየቀው ስለዚህ ይህን ጥያቄ ከሞት ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም ስለዚህ ማንም ሀይማኖቱን ይናገራል እንደውም እውነቱን ማወቅ ከፈለጋቹ ብዙ ክርስቲያኖች ፈርተን ሙስሊም ነን የምንል ነበርን ስማችንን ሁሉ የቀየርን ነበርን ሊቢያ የነበረ ሁሉ እርግጠኛ ሆኖ ይመሠክርላችኋል ይህን ጉዳይ፡፡ isis ሲጠይቁ የነበረው ሀይማኖት ነው ታድያ ጀማል እንዴት ክርስትያን ነኝ ይላል?
  2= "አልለይም አለ አላችሁ" ምን ማለት ነው አለመለየት?ከምንድነውስ የማይለየው? እርግጥ ነው በሀገር አንድ እንሁን እንጂ በሀይማኖት እንለያያለን ለዛ መሠለኝ የአምልኮ ቦታችን መስኪድ ወይ ቤ/ክርስትያን የሆነው መቼም ሁለቱም ጋር የሚሄድ ያለ አይመስለኝም ስለዚህ ጥያቄው ሀይማኖታዊ ስለነበረ እንለያያለን ስለዚህ ሊሆን የሚችለው ኢትዮጵያዊ ሲባል በህብረት ይሆናሉ፤ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከሙስሊም ኢትዮጵያኖች ወንድሞቻችን ጋር ይሆናል ግን በየትኛውም ነገር ያላችሁት ጉዳይ ገለባ ነው የሆነብኝ፡፡
  ጀማል ሠማዕት የሆነበት ምክንያት እንደ እ/ር አሠራር ጥሪ ወይም መመረጥ ነው፡፡
  በሠውኛ ደግሞ ከነበረው ሁኔታ (ከቅርብ ወንድም እንደሠማሁት) ዳኒ እንዳለው ወይ ሀይማኖቱን ቀይሯል ፣ ክርስትያናዊ ምልክት አለበት ወይም ቁርዓን መቅራት አይችልም አልፋቲሃን የማይችሉ ሙስሊም ወንድሞች አሉ ግን በምንም ምክንያት ይሁን ጀማል ከሠማዕታት አንዱ ነው ደሙ ከሠማዕታት ደም ጋር ተዋጅቷል፡፡በረከታቸው ይድረሠን

  ReplyDelete
 15. tiru zimi yale sinodosum ahun yinka mejemriaya endenzihi alem yalawokachew sematat bearusi,bejima.....yemotutim yitawku! anten Eizabher kebetesebhi gar yitebikihi.
  yaltsafkehewn yeminebum LIB yistachew.

  ReplyDelete
 16. መምህር ልክ ነው ቃለ ህይወትን ያሰማልን ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር ማስተዋልን ያድለን

  ReplyDelete
 17. Gad has reason for evtg.Let us stop blaming each other and pray and fasting to get relief form our almighty Gad

  ReplyDelete
 18. አቶ ዳንኤል ፅሁፍህን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ለማንበብና ለመረዳት ሞክሬለሁ።

  ነገር ግን ‹ስደተኛ ኢትዮጵያውያን› የሚለውን አገላለጽ ነፍሴ ትጸየፈዋለች፡፡ ብለህ የፃፍከው ምን ለማለት ፈልገህ እንደሆን ብታስረዳን። ምክንያቱም ብዙ ያነበቡ ሰዎች ቃሉን ነጥለው በማውጣት እንደሚመስለኝ ከሆነ አንተ ልትል ባልፈለከው መንገድ ትርጉም በመስጠት ፖስት በማድረግ ላይ ናቸው። ስለዚህ በዚህ ዙሪያ ወሬው ሳይደራ ማብራሪያ ብትሰጥበት ደስተኛ እሆናለው። ይሁንና የቃላቱን ትርጉም ፍቺ ካላስቀመጥክ የእነርሱ ትርጉም ትክክል እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል ማለት ነው።

  ሌላው ያልገባኝ ሱዳናዊና ሱማሊያዊ ከሆኑ ሙስሊም እንደሆኑ ስለሚያውቁ ይለቌቸዋል ብለሀል። ታዲያ ነገሩ እንደዚህ ከሆነ በኢራቅና በሶሪያ ያሁሉ ሰውን የጨረሱት ኢራቅና ሶሪያ የክርስቲያን ሀገር ስለሆኑ ይመስልሀል? እንጃ ለኔ ግን በፍፁም አይመስለኝም።

  ስለዚህ እዚ ጋ ያስቀመጥከው ሎጂክ እንኴን አሳማኝ ሊሆንልኝ አልቻለም። ይሁንና አንተ እንዳልከው ገዳዮችም እንዳሉት እነዚህ ሰማእት ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖች መሆናቸው እርግጥ ነው። ታዲያ እንደምታውቀው ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ሲባል ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ ብቻ ነው ለማለት አያስደፍርም። ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የክርስትና ሀይማኖት ተቌማት አሉና። ለምሳሌ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እና የመሳሰሉ ይገኝበታል።

  ስለዚህ ገድላቸው እንደሆን ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዩ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሆን ይመስለኛል። ስለሆነም የታሪክ ቅሚያ ውስጥ የሚያስገባን ባይሆን መልካም ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሆነ ታሪኩን እንዲሁም ሀዘኑን መጋራት መብቱ ነው። ምክንያት አንዱ የተገደሉበት ነጥብ ኢትዮጵያዊነት ስለሆነ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. don't you hear the oppening statement of ISIS " nations of the cross" i.e. they were killed because of thier chrstianity not by their origin/ethiopia/.
   most of you elaborations are not logical, ISIS killed citizens of iraqe and syria because of thier idiology and to triiger frustration across all populations of these countries, but ISIS is ajihadist against chrstianity all over the world! please read more!!

   Delete
 19. የተሻለ አመለካከት የተሸለ አስተውሎት፡፡ የተሻለ የሽምግልና አዕምሮ የተሻለ ትንትናኔ፡፡ በቃ ይሄ ነው አመለካከት ካሉ ላይቅር ሊቀርብ የሚቻለው፡፡

  ReplyDelete
 20. እኔ አሁን ሳስበው በህብረት ያበድን ይመስለኛል ነገሮችን እኛ በሚስማማን በኩል ተርጉመን ስናበቃ ከዛ" ይሄ ነው ትክክል ተቀበሉ" እንባላለን እኛም የነሡን ቃል በቀጥታ እንውጠዋለን አንዳንዶቻችን በየዋህነት ሌሎቻችን ሌላ ስም እንዳይሠጡን ፈርተን መቸም እኛ ሀገር በህብረት መስራት ከባድ ነው ግን በህብረት እናስባለን፣ በጅምላ እንናገራለን፣ በማህበር እንደግፋለን በአንጻሩም እንቃወማለን ከዛች ክበብ የወጣ ወዮለት ባልተፈጠረ ይሻለው ነበር እንዲል መፅሐፍ ሀበሻዊ እርግማን ሁሉ ይወርድበታል ደንደን ያለ ትከሻ ከሌለው ስድብና እርግማናቸው ውስጡ ገብቶ ያጠፋዋል፡፡
  ሠሞኑን በደረሠው አሳዛኝ ነገር በጣም እጅግ በጣም አዝኜያለው ያለኝ አቅም ለጊዜው እሡ ስለሆነ፡፡ሠሞኑን ከተነሡት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የወንድማችን የጀማል ጉዳይ ነው "ከክርስቲያን ጔደኞቼ አልለይም ብሎ ከነሡ ጋር ሠማዕት ሆነ" በረከቱ ይደርብን ግን እኔ የምለው እስቲ በዚያች ሠዓት እንደዛ ሲል ከየት ሠማችሁት የሚል ሠው አልነበረም ስለዚህ ተደጋግሞ ተወራ አሁን መረጃ ሲጠየቁ ድሮም አንተ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ልታፋጅ ነው ዱባ ፍሬ ገለመሌ ተባለ ለተጠየቁት ጥያቄ ቀጥታ መልስ መስጠት ነው ያለበለዚያ እንደ አዋቂ ሠው ጊዜ ወስዶ መረጃ መሠብሠብ እንጂ እኔ ያልኩትን ያልተቀበለ የማርያም ጠላት ነው አካሄድ የትም አያደርስም ደግሞም የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስትያኑ ዛሬ በጀማል ሞት አይደለም አንድ የሚሆነው ሙስሊሙ ከክርስትያኑ ፤ ክርስትያኑ ከሙስሊሙ ጋር አብሮ መኖርና መሞት የነበረ ነው ይህን ለማወቅ ወደኋላ ሄዶ ታሪክ ማገላበጥ ነው፡፡
  ሊቢያ ባለው ሁኔታ ግን አልለይም ብሎ የምትለዋ ቃል ለገዛ ፕሮፓጋንዳቹ መጠቀም ስለፈለጋቹ እንጂ አረጋግጣቹ ወይ ሠምታችሁ አይደለም፡፡ከተናገራችሁት ልጠይቃቹ
  1= ከክርስትያን ወንድሞቼ አልለይም አለ አላችሁ በምንድነው የማይለየው? ሀይማኖት እንጂ ዘር አልተጠየቁም በሊቢያ የነበርን ይሄ ሙስሊም ነህ ወይስ መሲህ( ክርስትያን) የሚለው ጥያቄ የዕለት ተዕለት ጥያቄ ነው ከስማችን በፊት ሀይማኖታችን ነው የምንጠየቀው ስለዚህ ይህን ጥያቄ ከሞት ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም ስለዚህ ማንም ሀይማኖቱን ይናገራል እንደውም እውነቱን ማወቅ ከፈለጋቹ ብዙ ክርስቲያኖች ፈርተን ሙስሊም ነን የምንል ነበርን ስማችንን ሁሉ የቀየርን ነበርን ሊቢያ የነበረ ሁሉ እርግጠኛ ሆኖ ይመሠክርላችኋል ይህን ጉዳይ፡፡ isis ሲጠይቁ የነበረው ሀይማኖት ነው ታድያ ጀማል እንዴት ክርስትያን ነኝ ይላል?
  2= "አልለይም አለ አላችሁ" ምን ማለት ነው አለመለየት?ከምንድነውስ የማይለየው? እርግጥ ነው በሀገር አንድ እንሁን እንጂ በሀይማኖት እንለያያለን ለዛ መሠለኝ የአምልኮ ቦታችን መስኪድ ወይ ቤ/ክርስትያን የሆነው መቼም ሁለቱም ጋር የሚሄድ ያለ አይመስለኝም ስለዚህ ጥያቄው ሀይማኖታዊ ስለነበረ እንለያያለን ስለዚህ ሊሆን የሚችለው ኢትዮጵያዊ ሲባል በህብረት ይሆናሉ፤ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከሙስሊም ኢትዮጵያኖች ወንድሞቻችን ጋር ይሆናል ግን በየትኛውም ነገር ያላችሁት ጉዳይ ገለባ ነው የሆነብኝ፡፡
  ጀማል ሠማዕት የሆነበት ምክንያት እንደ እ/ር አሠራር ጥሪ ወይም መመረጥ ነው፡፡
  በሠውኛ ደግሞ ከነበረው ሁኔታ (ከቅርብ ወንድም እንደሠማሁት) ዳኒ እንዳለው ወይ ሀይማኖቱን ቀይሯል ፣ ክርስትያናዊ ምልክት አለበት ወይም ቁርዓን መቅራት አይችልም አልፋቲሃን የማይችሉ ሙስሊም ወንድሞች አሉ ግን በምንም ምክንያት ይሁን ጀማል ከሠማዕታት አንዱ ነው ደሙ ከሠማዕታት ደም ጋር ተዋጅቷል፡፡በረከታቸው ይድረሠን

  ReplyDelete
 21. ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ ብቻ ነው ለማለት አያስደፍርም። ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የክርስትና ሀይማኖት ተቌማት አሉና። ለምሳሌ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እና የመሳሰሉ ይገኝበታል።›› እኔ በበኩሌ ፕሮቴስታንት ማህተም/ማተብ/ና ከአንገት የሚያሰር መስቀል ማጥላላት እና ልክ እንደ አይ ኤስ አይ ኤስ በሰይፍ ሕይወትን ማጥፋት ሳይሆን በቃላት ነብሳትን በየጊዜው የሚገድሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ናችው ታዲያ እንዴት ብለው ነው ስለ ማተባቸው ይምሰውት መቼ የያዙት ማተብ ነው አንበጥስም የሚሉት? /ጣሰው ፀሃየ ረዳ ነኝ/ አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 22. Interesting article. We also need to ask why our younger generation are feeling from our country. If we really care for our church and our people we need to analysis the current political situation in our country.
  Why are we scared of politics?

  ReplyDelete
 23. There is no compulsion where the religion is concerned.” (Holy Quran: 2/ 256) በሃይማኖት ማስገደድ የለም (ቁር አን 2/256)

  ይህ የቁር አን አንቀጽ ከእስልምና መሰረታዊ አስተምህሮቶች ዋነኛው ነውና፡ በአረቡ አለም በርካታ ሚሊዮን ክርስቲያኖች ዛሬም ድረስ አሉ፡፡ ሙስሊሞች በታሪካቸው አስገድደው ያሰልሙ እንዳልነበር ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ ነገር ግን አስገድዶ ማስለም ቢኖር ኖሮ አንድም ክርስቲያን እንዳይቀር ማድረግ በቻሉ ነበር፡፡ ለዚያም ነው ምንም እንኳን ሙስሊሞች እስይፔንን ለ736 አመት ተቆጣጥረዋት የነበረ ቢሆንም በዘመኑ አይሁድ እና ክርስትና እምነት ተከታዮች በዚያ ግዛት ኖረዋል. እንዲያውም አይሁድ ያንን ዘመን ወርቃማው ዘመን ይሉታል ( The golden age of Jewish culture in Spain coincided with the Middle Ages in Europe, a period of Muslim rule throughout much of the Iberian Peninsula. During intermittent periods of time, Jews were generally accepted in society and Jewish religious, cultural, and economic life blossomed).
  ሙስሊሞች ህንድንም ከአንድ ሺህ አመት በላይ ሲገዟት ቆይተዋል፡፡ ነገር ግን አስገድደው ሰዎችን ወደ ኢስላም እንዲገቡ አላደረጉምና አሁንም ድረስ ሙስሊሞች ቁጥራቸው ከጠቅላላው ህዝብ አንፃር ሲታይ እጅግ አነስተኛ ናቸው፡፡ በአለም ላይ ትልቁ የሙስሊም ህዝብ ያለባት ሀገር ኢንዶኔዢያ ነች፡፡ ነገር ግን አንድም የሙስሊም ወታደር እግር አልረገጣትም፡፡ ማሌዢያ ብዙሃኑ ህዝቧ ሙስሊም ነው፡፡ ነገር ግን አንድም የሙስሊም ወታደር እግር አልረገጣትም፡፡ የፀረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ ከፍቶ የሁዶች ከአውሮፓ ምድር ሲፈናቀሉ በብዛት ወደ ሙስሊሙ አለም ሲጎርፉ ነበር፡፡ እምነታቸውን በግድ ሊቀይሯቸው ቀርቶ ተቀብለው ነበር ያስተናገዷቸው፡፡ ሙስሊሞች ይህን ሁሉ ሲያደርጉ የነበረው “በሃይማኖት ማስገደድ የለም!” የሚለውን ቁርኣናዊ መልእክት እየተገበሩ ነበር፡፡

  አሁን አሁን ግና ለገዛ እምነታቸው ባይተዋር በሆኑ፤ ብሄራዊና ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም እስላምናን መጠቀሚያ በሚያደርጉ፤ ቡድኖች ይህ በሃይማኖት ማስገደድ የለም የሚለው መሰረታዊ የ’ስልምና አስተምህሮ እየተጣሰ ማየት የማይደንቅበት ዘመን ላይ ደርሰናል.

  ReplyDelete
 24. kemenfasawi saw antar lek neh d.n. gen sawn mared bemenfasawi bech sayhon sebeawinetenm yemigafa naw menfasawi yalhonu sawoch endalum mezengat yelbenem endesebawi sawentachaw gen azenawal hazenachewen megelecham adergewal tekertawal 3 ayenet saw al endani
  1,sabawi (bechawn sebawi naw)
  2,menfasawi(yesaw sebawinet bewestu al)
  3,kehultum yalhon (ensesawi benlow yesalal by asebalhu)
  selazih enazih sawech yadergut neger bemenfasawi eyeta klmzanut tekekel naw
  mengest gen ortodox selhonu endetaredu yefa mawetat neberbet. betkerstiyanm ldersahwan mewesad neberbat by assebalhu

  ReplyDelete
 25. ዳኒ እንዲያው እግረ መንገድህን ከአመታት በፊት በጅማ ስለተሰዉት ወገኖቻችን ምን ትለናለህ እስከማውቀው የተደረገላቸው ነገር የለም እስቲ በዚህ ጉዳይ እይታህን አስቀምጥልን

  ReplyDelete
 26. there are a number of thousands of ortodox tewahido christians in iraq iran and the arab world.In Iraq only50000!!

  ReplyDelete
 27. A while ago i read an article about what happened to some Syrian Armenians when IS took over a town in Syria. These Armenian Christians were kidnapped and were given the choice of converting to Islam or abandoning all their possessions and leaving the town or death.The Armenians chose conversion to save their lives and possessions.But IS still executed them by bullets knowing their conversion was not genuine.When people asked for their bodies IS replied that they were Muslim martyrs and were given Muslim burials.

  I think in the video the ones who refused to convert were beheaded while the ones who converted were shot execution style.

  ReplyDelete
 28. please inante blogeroch zim bilachu ware atinzu hule kiristina kiristina iyalachu ye Ethiopia muslimina kirstian machem inante ware silanafesachu yimilayew nager yelem sila Jemal atarachum alatarachu......ye fetari bereketina selam hagerachinin yigobgn

  ReplyDelete
 29. Misgun new, misgun: esu bewazegnoch : bekifuwoch menged yalhede. berta D.N Daniel.<< Higih leegre mebrat lemengedem birhan new>>.

  ReplyDelete