Monday, April 20, 2015

ወደ ባሕላችንና እምነታችን ስንመለስ


በሊቢያ ምድር እምነታቸው ወንጀል ሆኖባቸው በአይሲስ የተሠዉትን ሰማዕታተ ሊቢያ በተመለከተ መንግሥታዊና የሃይማኖት ተቋማት ሊያደርጉ ስለሚገባው ነገር ስንለው ስንለው ቆየን፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ባሕላችንና እምነታችን እንመለስ፡፡
እነዚህ ወገኖቻችን ስማቸውንና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን የምታውቁ ንገሩን፡፡ በባሕላችን መሠረት ልቅሶ እንድረሳቸው፡፡ ኀዘናቸው እነርሱ ብቻ አለመሆኑን እንንገራቸው፤ መከራቸውን እንካፈላቸው፡፡ እንደ ባሕሉ ማድረግ ያለብንን እናድርግ፡፡ ይኼ ከዘወትሩ ኀዘን ይለያል፡፡ የተሠዉበት ምክንያት፣ የተሠዉበት ሁኔታ፣ ለመሥዋዕትነት ያቀረቧቸው አሸባሪዎች ማንነት ከዘወትሩ ይለያቸዋል፡፡ ኀዘኑ የወላጅ፣ የዘመድ የመንደር፣ የዕድር ብቻ አይደለም፡፡ ከፕሬዚዳንቱ እስከ እኔ ላለነው ሁሉ ኀዘን ነው፡፡ ስለዚህም እንደየአመቺነቱ ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ በየደረጃው ያለን እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ልቅሶ እንድረስ፤ ሰውነታችንን፣ ለዜጎቻችን ያለብንን ኃላፊነት፣ ለቤተሰቦቹ ያለንን የመጽናናት ምኞት በመግለጫ ብቻ ሳይሆን በባሕሉ መሠረት እንግለጠው፡፡ ፖለቲካዊ ዲስኩሩን፣ ነጥብ ለማስቆጠር መጨቃጨቁን፣ የተለመደ ቢሮክራሲያዊ አሠራሩን ትተን ወደ ባሕላችንና እምነታችን እንመለስ፡፡ ባሕል የሌለን እምነት የሌለን አንምሰል፡፡ ለእንደዚህ ያለ ወቅት የሚሆን ወግና ሥርዓት አለን፡፡  ያለ ወግ የመየጣውን ዕዳ በወግ እንክፈለው፡፡

ታዋቂ ሰዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት መሪዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሞያ ማኅበራት መሪዎች፣ ባለ ሀብቶች፣ በባሕሉ መሠረት ወደ ቤተሰቦቹ ሄደን ኀዘናችንን እንግለጥ፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ኀዘናችንን እንካፈለው፡፡ ልዩነታችንን ኀዘን አንድ ሊያደርገው ካልቻለ ከእንግዲህ ምን አንድ ያደርገዋል፡፡
እንደ እምነታችን ለሰማዕታቱ ተገቢውን ሥፍራ እንስጥ፤ የጸሎት ሥነ ሥርዓት በየአጥቢያው ይዘጋጅ፤ ፎቶዎቻቸው በየአጥቢያው ይለጠፉ፤ የተሠዉበት ክቡር ዓላማ ይነገር፤ በየአጥቢያው የሚዘመረው መዝሙር፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ምዕዳን ነገሩን ያገናዘበ ይሁን፤ ቢቻል በየ ቤተ እምነቱ ልዩ መርሐ ግብር ይዘጋጅ፡፡ ስለ ሰማዕታቱ የሚያወሳ፣ሽብርና ሽብርተኛነትን የሚያወግዝ፣ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር፤ በሐሳብ፣ በርእዮተ ዓለም፣ በአካሄድ ብንለያይም በሀገራዊ ጉዳይ አንድ መሆናችንን የሚያበሥር፣ የሰማዕታቱን ሰማያዊ ዋጋ የሚዘክር፤ ነገ ተመሳሳይ ነገር እንዳይደገም  መንገድ የሚቀይስ፣ ጉባኤ ይዘጋጅ፡፡
ይሄንን ነገር ያደረጉት አሸባሪዎች ናቸው፡፡ ይህንን ነገር ያደረጉት ኢሰብአውያን በመሆናቸው እንጂ ሙስሊም በመሆናቸው አይደለም፡፡ አንዱም ፍላጎታቸው እንዲህ ስሜት በሚነኩ ድርጊቶች ልዩነታችንን ማስፋት ነው፡፡ እኔ የብዙ ሙስሊም ወገኖቼን ስልክ ዛሬ ስቀበል ነበር፡፡ እጅግ ያዘኑ፣ የተነኩ፣ በእስልምና ስም በተፈጸመው ድርጊት ልባቸው የበገነ ሙስሊሞች፤ አማኞች እንጂ አሸባሪዎች ያልሆኑ፡፡ ሰው በእምነቱ የተነሣ መገደሉን በምንም መልኩ የማይቀበሉ ሙስሊሞች ኀዘናቸውን ሲገልጡ ነበር፡፡
ይኼንን ሰማዕታቱ የሰጡንን ዕድል ለአንድ ዓላማ ለመቆም እንጠቀምበት፤ የሰማዕታት ዓላማ ማስታረቅ ነው፤ ማግባባት ነው፡፡ ይኼንን የኢትዮጵያዊ መተዛዘንና መረዳዳት ጉዳይ ሙስሊም ወገኖቼ በእምነታቸውና በባሕላቸው አጉልተው ያሳዩናል ብዬ አምናለሁ፡፡ አንዳችን በሌላችን የኀዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተን ከእኩዩ ተግባር በተቃራኒ በጋራ መቆማችንን እናሳይ፡፡  
ያ ከሆነ የደሙ ልቦች ይድናሉ፣ የተጎዱ ቤተሰቦች ከልብ ይጽናናሉ፤ አራጆቻችንም የፈለጉትን ማግኘት እንዳልቻሉ ያያሉ፡፡ አሸባሪዎቹ በሰማዕትነት እንዳከበሩን ሁሉ እኛ ደግሞ የሰማዕታቱን ዓላማ በማጽናት እናዋርዳቸዋለን፡፡ ማን ያውቃል፣ የሰማዕታቱ ደም አልግባባ ላለው ልዩነታችን ሥርየት ይሆነን ይሆናል፡፡

22 comments:

 1. lega tre blhale !! yha hazen yulacenm new crhestanaw gedatam aleben yazanna masnnat yegabal haznachw lksachaw layshnem new ysametat betasebewech egezabher amelek mesnatwen yestachw endat btasdgachw new abatwech yferweten smetatent ensew bahwnew zemen ytkebalewe zare teznalach howela gen blegwechach meswetent keber kegzabher tagazalech bleez yech alem kent nat lhymant tamen memot metadal new ksmatw kedws gwergs kmebetachen kess gabez asgb bgent nebsatch endarefec altreterm amen!!

  ReplyDelete
 2. በመጀመሪያ ቸሩ ፈጣሪ ለእምነታቸው የተሰወትን የእነዚህን ወንድሞቻችንን ሰማዕታት ነፍስ ይማርልን!በገነት ያኑርልን አሜን።
  Dear Daniel,
  We're living in an a 24hr news cycle era, where the average citizen consumes a vast volume of information every day, which sometimes force our brain to plunge the previous chronicles just to accept the new one.
  Today while I’m with such a heavy heart to the suffering of my fellow brothers all of the world. Yet, this incident brings back the memories of the mass shooting of the 2012, 20 innocent Newtown, Massachusetts kids with their teachers by a 20yr old Adam Lanza. On that very day the discussion was split in to two sides on every media outlets…One says…let’s take time to comfort the victims families today is not the day to talk about gun control …..And the other side takes a fierce opposite side...No! As a matter of fact the time to discuss about gun control is not today, it was YESTERDAY! So that we could avert today’s massacre. Till this day, it is an ongoing battle with the gun manufacturers, but yet society has made a tremendous progress in regards to violence, mental illness, early detection and recovery.. Etc. and I think we can learn a bit of a lesson here…before this incident vanish in thin air from our quick volatile memory, and shelved in to ‘nothing new’! I think we can take this catastrophic incident and use it as a strategy to address the root causes of our people so as to help us to see a better tomorrow.
  As much as they deserve it, I’m convinced that, condemning the already failed and corrupt government, or the already frail religious establishments all day long produce too late too little OR no results nor changes that we all want to see in Ethiopia. However, we all can campaign for breaking some society taboos and misnomers regarding to immigration /migration in our society.
  Apart from the emotions and out-cries for our fellow brothers and sisters …I feel a mighty inside pressure that the following issues needs to be tackled!
  - A National campaign has to be initiated to denounce migration!
  o Musicians , Art and Media all needs to preach about the reality of immigration
  o Immigration needs to be stopped being taken as a shortcut to prosperity.
  o Pay values and respect to those working low-class jobs within the country celebrate their success and make them an example…
  - As much as taboo to criticize our parents, it’s time to tell them to stop pushing their children to leave their country looking for better life risking their precious life.
  - The real truth about what our sisters do in the Middle East to show off artificial life needs to be told, as shameful it is, it is still better than getting thrown out the window or burned by flamed oil.
  - It’s time to expose and tell the truth about the brothers and sisters, who live in South Africa do to the locals, and the expense of the naivety of the South African black people.
  - An overall moral renascence is absolutely necessary, and we can’t get it from the government or officials let’s look for other avenues to restore our dignity. Society has gone too low on moral values, time to wake up and asses who we are, and what can we do to ourselves and our society.
  - We can ask and push government through it’s embassies to make a national ‘exodus’ type of travel initiatives with the help of the host countries.. to bring back to people to the motherland , so as to exemplify going back is possible.
  - Etc…
  I’m open to your thoughts!

  .. I have a disclaimer to state: I my self is an immigrant , but before I decided to come to the U.S to live I’ve traveled dozens of other countries back and forth to Ethiopia and it was a life choice decision for the most part, So please forgive me if I sound hypocrite. My intention is not, rather it is to help my fellow compatriots to reconsider the realities in the not so suitable parts of the world.
  Best Regards,
  Ghion


  ReplyDelete
 3. ሰላመ እግዚአብሔር ህዝባችንን ወገናችንን ሀገራችንን ያጽናናልን። እንግዲህ ምን ይባላል? ለቅሶ መድረሱ ስለአንድነት ዋጋ ይኖረው ይሆናል። ያስለቀሱንን ግን መሰረታዊ ምክንያታቸው ምን ቢሆን ነው ብሎ መጠየቅና ስለመነሻ ጉዳዩ በግልፅ መወያየትና መነጋገር ያስፈልገናል።

  አንድ ነገር በቅድሚያ ልበል ስለሰማዕትነት። ሰማዕትነት ላመኑት እግዚአብሔር " አንተ ከሁሉም ትበልጥብናለህና ከምድራዊ ነገር ይልቅ ያንተ ቸርነት የተትረፈረፈበትን ሰማያዊውንና ዘላለማዊውን መንግስትህን መርጠናል። እስከ ስጋዊ ሞትም ድረስ ታምነናል" ማለት ነውና... ከእውነተኛው ጌታ እሱም ያለበደሉ ስለኛ መስዋዕት ከሆነው ጋር ይከብራሉ። በመንግስቱም ያስባቸዋል።

  የኔ ጥያቄ... አንገት ቆራጮቹ ጋር ነው። ማለቴ አራጆቹ። ወይም የነዚህን አይነት እምነት ተከታዮች ወይም የእኩይ ድርጊታቸው በሃሳብና በገንዘብ ደጋፊዎች።

  ወዳጆቼ አንሞኝ አሁን የተሰለፍነው ወጣም ወረደ በሁለት ጎራ ነው።

  1ኛ. ሀይማኖትን ለማስፋፋት የሚደረግ መግደል ያጸድቃል የሚል "ቅዱስ" መጽሐፍ ተከታዮችና...
  2ኛ. ለሀይማኖት ሲባል መሞት ያጸድቃል የሚል ቅዱስ መጽሐፍ ተከታዮች።

  ስለዚህ ከሁለት አንዱ ሊኖር ሌላው ሊከስም ግድ ነው። በእኔ እይታ መግደልን የሚደግፈው እምነት ተጠየቅ ውስጥ ገብቶ ሊያብራራልን ይገባልና እጠይቃለሁ ።

  ሰውን በማንኛውም መንገድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መግደል ወንጀል ነው። ማንም በማንም እምነት ላይ ጣልቃ አይገባም። እነዚህን የመሳሰሉ የህግ ማዕቀፍ ያስቀመጥን ህዝቦች እንዴት ከህገመንግስቱ ለሚቃረን፣ ያውም እንደዚህ አይነት ተግባሮች እንዲፈጸሙ እርሾ የሆነውን የ"ቅዱሱን" መጽሐፍ ተከታዮች ይህንን በመግደል መስፋፋት የሚለውን ህገ አራዊት ሳያወግዙ ወይም ከቁራናቸው ሳይሰርዙ እንዴት እንደ አንድ በሀገሪቱ ህግ ውስጥ በሰላም የሚንቀሳቀስ እምነት ድርጅት ፈቃድ ተሰጣቸው (በተለይ በእኛ ሀገር)? የፀረ ሽብር ህጉስ ለምን በዚህ ጉዳይ አይፈተንም? ለምን ጋዜጠኞችን ብቻ?

  በኔ አመለካከት ከዚህ በኋላ አንድ ሙስሊምን ሰላማዊ ነው፣ ወይም ጊዜና ሁኔታዎች ሲመቻቹለት ጠብቆ ለመጽደቅ ሲል ክቡር ሰው እንደማይገድል የማምነው ይህ በመግደል የመስፋፋትና የመጽደቅ መልዕክት ከቁራን ውስጥ እንዲሰረዝ ሲደግፍና ሲያስተባብር ብቻ ነው። ያለበለዚያ... ዛሬ ለሊቢያው ሲገርመን ነገ ሙስሊም ጎረቤታችን ለሀይማኖቱ ሲል ጎራዴ ስሎ ላለመጠበቁ ምን ማረጋገጫ አለን? በተደጋጋሚ የምንሰማው "አንድ አይሱዙ ጎራዴ እንትን ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች ሲያስገቡ በፖሊስ ተያዘ" የሚሉ ወሬዎችን ስንሰማ ለማን አንገት እየተዘጋጁ እንደሆነ ይገባናል። በተጨማሪም በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ ጥናት የአካል ቅልጥፍና ስልጠናዎችን ከሚከታተሉ ወጣቶች ውስጥ 78 ከመቶው ሙስሊም መሆናቸውስ ዝግጅቱ ለማነው ማለት አይገባንም? ነው ወይስ ኑ አንገታችንን ቀሉን አገራችንንም ፈንጩባት እኛ ግባችን ሰማዕት መሆን ብቻ ነው ሌላ አላማ የለንም እንበላቸው?

  ሌላው ጉዳይ ሞት ለእኛ ኢትየጵያዊያን እንደማይደንቀን "ዘጠኝ አይነት አሟሟት አለ" ቢሉን ሳንደነግጥ አንዱን ግባ የምንል እንደሆንን፣ ሞት የማያስፈራን ከሞት በኋላ ላለው ዘላለማዊ ህይወት የምንጨነቅ እንደሆንን አምናለሁ። ግና ዘጠኙ ሞት ውስጥ ይህ አንገት መቀላት ቢኖርም ባይኖርም አንገት መቅላት ወይም ሰውን ማረድ ለምን አስፈለገ ብዬ ግን እጠይቃለሁ። በማረድ የሚቀጣ ዘመናዊ መንግስት እንደሌለ ልብ በሉ። እንደውም በአብዛኛው የሞት ፍርድ መቅረት አለበት የሚሉ አለማዊ መንግስታት ብዙ ናቸው። ምክንያታቸው የሰው ልጅ ህይወትን ስላልሰጠ ህይወትን መንጠቅ አይችልም ነው። በሀይማኖት ስም ሰውን ለሚያርድ ከአለማዊ መንግስት እንኳን ላነሰ እምነት የሚከተለውን እላለሁ።

  የሚታረድ የሚበላ ሲሆን ነው። ስለዚህ ሰው አራጆች ሆይ ሰው በላ ናችሁ!!!
  የክቡር ሰውን ደም ለመሬት ገዢ መናፍስት እየገበራችሁ ነውና ሰይጣኖች የዲያብሎስ ሎሌ ናችሁ።

  መልዕክት ለዲያቆን ዳንኤል።
  ምንም እንኳን የፃፍኩትን የማምንበት ጉዳይ ቢሆንም በዘመኑ ካለው አስመሳይ የሀይማኖት መከባበር የሚል አታላይና አስጠቂ አጀንዳ ምክንያት... የሌላ እምነት ስለተነካ ብለህ ሃሳቤን ባታስተላልፈው ደስ ባይለኝም ቀናነትህን ስለማውቅ ግን ቅር አይለኝም። ብትለጥፈው ግን መልካምነበር። ነውም። መልስ ካላቸው ቁራኑን ካነበቡት...

  ReplyDelete
  Replies
  1. An Appreciable idea.....Let somebody from the religion give response to this nice idea.....come on ....let's discuss

   Delete
 4. መድሃሂያለም ያዘኑትን ያፅናናልንአሜን! አዎ እራሳችንን ዝቅ አድርገን የሚጠበቅብንን እናድርግ!መድሃሂያለም በምህረተህ አይንህ ተመልከተን.ትንሣሔዋን አሳየን አሜን!!!

  ReplyDelete
 5. Please open this link.
  http://www.ethiotube.net/play/?p=5863

  ReplyDelete
 6. Dani?? Gelametuh endie? Ayizon, Akafawun Akafa,Domawun doma blo lemenager eskeferan dres be-akafam be-domam anat anatachinen eyeteqeteqetn 1 band maleqachin ayiqerm. Be-1net meqom yalchale hizb yemanm mechawecha endemihon yetaweqe newu! Lemin bilu tebetnowalaa! Btn mingiziem btn newu.

  ReplyDelete
 7. egziabher yestelen.Dni. leyu eyeta new.lesryet yadergelen.

  ReplyDelete
 8. Dear Dani

  Excellent idea we all have to share their grief, May GOD rest their soul, I am deeply saddened.
  Daniel You are doing great Job brother keep it up. May God bless you and your family.

  ReplyDelete
 9. ኦ እናንተ አይሲሶች ሆይ ምስጋና ይገባችኋል፤ በክፋታችሁ የመንግስተ ሰማያትን በር ከፍታችሁልናልና!
  ኦ እናንተ አይሲሶች ሆይ ምስጋና ይገባችኋል፤ ሀይማኖት የለም እግዚአብሔር የለም የሚል ከንቱ ትውልድ በበዛበት በዚህ ዘመን ለሀይማኖታቸው የፀኑ ከዋክብትን አሳይታችሁናልና!
  ኦ እናንተ አይሲሶች ሆይ ምስጋና ይገባችኋል፤ መካሪ አስተማሪ በጠፋበት ዘመን እምነትን እና ጽናትን በተግባር ኖረው ሚያስተምሩ መምህራንን አሳይታችሁናልና!
  ኦ እናንተ አይሲሶች ሆይ ምስጋና ይገባችኋል፤ የቆማችሁለትን ሀይማኖት ከንቱነት ለዓለም መስክራችኋልና!
  በመጨረሻ ግን ለናንተ ሀዘን ይገባችኋል ለብዙዎች መዳን ምክንያት ስትሆኑ ለራሳቸሁ ግን ዘላለማዊውን ሞት ተሸክማችኋልና በፈጠራችሁ ፊት ምህረትን የሚያሰጥ ስራ አታችኋልና

  ReplyDelete
 10. ኢትዮጵያ ትናንት በዐረብ ምድር

  ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ የ ፌስቡክ ቡድን የተወሰደ

  መጽሐፈ ስንክሳር በአይሁድ ንጉስ ፊንሐስ የተፈፀመውን የሀገረ ናግራንን ክርስትያኖች እልቂት ካወሳ በኋላ እንዲህ ይቀጥላል
  ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ፊንሐስም ወደ ሀገሩ በሄደ ጊዜ ወደ ነገስታቱ ሁሉ በሀይል እየተመካ ላከባቸው፡፡ የሮም ንጉስ ዮስጥንዮስም ሰምቶ ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ ጢሞትዮስ ላከ፡፡ በሀገረ ናግራን ናግራን ለሚኖሩ የክርስትያን ወገኖች ደማቸውን ይበቀል ዘንድ ለኢትዮጵያ ንጉሥ ለካሌብ መልእክት እንዲልክ ነው፡፡
  የኢትዮጵያው ንጉሥ ካሌብም መልእክት በደረሰው ጊዜ ፈጥኖ ተነሳ በዋሻ ከሚኖር ከአባ ጰንጠሌዎን በረከትን ተቀብሎ ከብዙ ሰራዊት ጋር መርከቦችን ተጭኖ ሔደ፡፡ በደረሰም ግዜ የሳባን ንጉስ ፊንሐንስን ሀገር አጠፋ ሰውም ሆነ እንስሳት ሆነ ሸሽቶ የሚያመልጥ እንኳ ምንም ምን ሳይቀር አጠፋቸው፡፡ የናግራንን ከተማ ህንፃዋን አደሰ፡፡ የሰማዕታትንም መታሰቢያ አቆመ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ሮም ንጉስ ዮስጢኖስ ፣ ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ አባ ጢሞትዮስ መልእክትን ላከ እነርሱም ሰምተው እጅግ ደስ አላቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡
  ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር 26
  ይህን ታሪክ ሰፋ አድርጎ አብራርቶ ያስነበበን ዲን ዳንኤል ክብረት ደግሞ እንዲህ ያስቀምጠዋል
  ‹‹ናግራን ከኢትዮጵያ መንግስት የደቡብ ግዛቶች አንዷ ነበረች የምትገኘውም በዐረቢያ ልሳነ ምድር ነው፡፡ አፄ ካሌብ መልእክቱ ከደረሰው በኋላ ከ 120 ሺ በላይ ወታደሮች ከሀገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች ፤ 60 መርከቦች ከሮም፣ ከፋርስ ፣ ከህንደኬ ተሰባሰቡ፡፡ ይህም የኢትዮጵያን መንግስት ወታደራዊ አቅም ያመለክተናል፡፡ ከእነዚህም መርከቦች በተጨማሪ 15 ከአይላም፣ 20 ከቁዝልም(ግብጽ) 7 ከእምጣንዮስ፣ 30 ከባርኒኮስ ፣9 ከላርሴን በድምሩ 81 መርከቦች በተጨማሪ ተገዙ፡፡ እነዚህ ሁሉ የጦር መርከቦች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የጦር ጥበበኞች ደግሞ 70 ታላላቅና 100 ታናናሽ መርከቦችን ሰሩ፡፡ የመርከቦቹ ስራ አንድ አመት ብቻ መፍጀቱን ስንመለከት ኢትዮጵያ ሀገራችን የነበራትን ጥበብና የስልጣኔ ደረጃ ያመለክተናል፡፡ ለዚህ ጦርነት በጠቅላላው 311 መርከቦች ተዘጋጁ፡፡
  ንጉሥ ካሌብ ከዚህ ሁሉ የጦርነት ዝግጅት በኋላ ወደ አክሱም ጽዮን ገብቶ ጸሎት አድርሷል፡፡ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ ወደሆኑትና ከአክሱም አጠገብ በበአት ወደሚኖሩት አባ ጰንጠሌዎን በመጓዝም ቡራኬያቸውን ተቀብሏል፡፡ ከጦርነቱ ከተመለሰ በኋላም መንግስቱን ለልጁ ገብረ መስቀል አስረክቦ ሰኔል እና የውሀ መጠጫ ቅል ብቻ በመያዝ ወደ አባ ጰንጠሌዎን ገዳም ገብቶ በዝያው በምናኔ ነው ያረፈው፡፡
  ምንጭ፡- የናግራን ሰማዕታት ገጽ 6-7
  ዲ.ን ዳንኤል ክብረት 1998 ዓ.ም

  ReplyDelete
 11. አሸባሪዎቹ በሰማዕትነት እንዳከበሩን ሁሉ እኛ ደግሞ የሰማዕታቱን ዓላማ በማጽናት እናዋርዳቸዋለን፡፡ ማን ያውቃል፣ የሰማዕታቱ ደም አልግባባ ላለው ልዩነታችን ሥርየት ይሆነን ይሆናል፡፡

  ReplyDelete

 12. በረከታቸው ይደርብን !!!!!!!!!ለ
  9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።

  10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።

  11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።

  ReplyDelete
 13. 9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።

  10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።

  11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው። ራዕይ ፮፥፱

  ReplyDelete
 14. Dear Dani,
  I hope people can open their eyes with your blessing words. It makes a huge difference in our life. It means a lot. Thank you very much.
  Thank you for making us think as one.

  ReplyDelete
 15. ለቅሶ ልንደርስ የሚገባንን የሞቱትን ወንድሞቻችንን ቤተሰቦች ቤት የምታውቁ እባካችሁ አድራሻቸውን ጻፉልን፡ ጠቁሙንለቅሶ ልንደርስ የሚገባንን የሞቱትን ወንድሞቻችንን ቤተሰቦች ቤት የምታውቁ እባካችሁ አድራሻቸውን ጻፉልን፡ ጠቁሙን

  ReplyDelete
 16. We really appreciate your views.We really touched with loss of our brothers in SA and Libya by inhuman people. Our leaders are not concerned on the loss of these innocent people but rather on the election to sustain the power. our church leaders have to look their position. May God Mercy on us.

  ReplyDelete
 17. The problem is the way we think...the generation is getting spoiled...selfishness...money...fame...by any means...selling the soul...cold blooded crimes...this how the elders do...the next will do worse to win over the former. Then the world will end!

  ReplyDelete
 18. አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።
  በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።
  ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።ራዕይ ፮፥፱

  ReplyDelete
 19. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  እውነት ነው የወንድሞቻችን ሰማዕትነት ለትምህርት እንጠቀምበት፡፡ ታላቅ ዓለም አቀፍ ዓውደ ምእረት አግኝተናል፡፡ ወንድሞቻችን የተግባር ትምህርት በዓለማቀፍ አውደ ምእረት አስተምረውናል፡፡ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በዚህ በወንድሞቻችን የደም ዋጋ ባሰናዱት አውደ መእረት እናስተምርበት፣ እንስበክበት፡፡ የክርስትናን ትምህርትና የሰማእታትን ክብር እንግለጽበት ሀገሬ ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚያአብሔር ህዝቦም ህዝበ እግዚአብሔር መሆኑን ለዓለም እናሰተምርበት፡፡ እኔ የሀገሬ ወጣቶች ለታቦቱ ክብር ምንጣፍ ሲያነጥፉ፣ አውደ መእረቱን ለትምህርት ሲያዘጋጁ ነበር ያሰተዋልኩት አሁን ደግሞ ለዓለም አቀፍ ስብከት በቀዩ ምንጣፍ በተመሰለው በደማቸው ዓለም አቀፍ አውደ ምህረት አዘጋጁ፡፡ በሉ ሊቃውንቱ ዝም አትበሉ በዚህ በደም ዋጋ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ዓውድ መእረት ላይ አስተምሩ ፡፡ ስበኩ ፤ የሰማእታቱን ክብሩት አውሱ፡፡ በወንጌል “ሥጋን መግደል የሚችሉትን ነፍስን ግን ማጥፋት የማይችሉትን አትፍሩ” የተባለውን አመስጥሩ፤ አብራሩ፡፡ ለእኔ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት ናቸው እላለው፡፡ ኮራውባቸው፣ እምነቴንም አጸናውባቸው፡፡ ወንድሞቼ ሰማዕታት እናንተስ በገነት ነብሳችሁ ከብሯል፡፡ የሰማዕታቱ የእነ ቅ/ጊዮርጊስ፣ የእነ ቀ/እስጢፋኖስ፣የሰማእቱ ቅ/ዮሐንስ፣ የሰማዕቷ ቅ/አርሴማ፣ የሰማዕቱ ቅ/ቄርቆስ፣ የእነ ቅ/ማርቆስ፣ የሰማእቱ ቅ/ጴጥሮስ ወዘተ… ልጆች መሆናችሁን በተግባር አስመሰከራችሁ፡፡ ቀናውባችሁ፡፡
  በእናንተ የሰማዕትነት ደም ክርስትና ትስፋፋለች፤ የአንገታችንን ክር አጥብቀን እናስራለን፡፡ ስለ ሃይማኖት ያፈሰሳችሁት ክቡር ደማችሁ እና የሰዋችሁለት ክቡር ሕይወታችሁ የከበረ ዋጋ አለው ፡፡ እኔ ዛሬ በእነዚ በወጣቶች ደም ቃሌን አድሻለው፡፡ ለሃይማኖቴ እና ለሀገሬ የምችለውን ሁሉ ላደርግ ቃል ገብቻለው፡፡ ታላቅ ብርታት እየተሰማኝ ነው፡፡ እናንተስ?
  የሰማዕትነት በረከታችሁ ይድረሰን፡፡ ለሰማእታት ቤተሰብ እና በአዘኑ ልቡ የተነካ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን መጽናናጽ ይስጥልን፡፡ አጽራረ ቤተክርስቲንን ያስታግስልን፡፡
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

  ReplyDelete
 20. ሠይፈገብርኤልApril 22, 2015 at 3:10 AM

  Selam Dn. Daniel,

  I enjoy reading most of your articles. However, you occasionally cross the red line. Please stop judging the Holy Synod (and anyone else for that matter). Leave that to the Real Judge! Please don't tell me that the Holy Synod took your advise and came up with a better wording of its declaration. Give me a break! እንዴ አቅማችንን፣ ልካችንን እንወቅ እንጂ ወንድሜ፤ ወደ ላይ መንጠራራት ለማንም አይበጅም። የግድ መታረም ያለበት ጉዳይ ካለ ደግሞ አባቶቻችን ጠጋ ብሎ በልጅነት ቢያማክሯቸው ያዳምጡናል እኮን! እንግዲህ በቅዱስ ሲኖዶሳችን አዋጅ መሰረት ሁላችንም በየአጥቢያችን ወደ ጸሎተ ፍታቱና ምህላው እንሂድ...(ስለ ጉራማይሌው ቋንቋ ይቅርታ፤ በሚቀጥለው አርማለሁ)።

  ReplyDelete