Monday, April 20, 2015

ሰማዕታተ ሊቢያና የሲኖዶሱ መግለጫ

click here for pdf

የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡ 

ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ከበዳችሁ? እረኛ በጎቹን በሪሞት ይጠብቃል እንዴ?
እጅግ ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር ደግሞ ክርስቲያን በመሆናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን የምጠብቀውን ሦስት ነገር ከመግለጫው ማጣቴ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመታሰቢያ ጸሎት ሊደረግ ይገባው ነበር፡፡ በምንም ለማናውቃቸውና ለማያውቁን የኢንዶኔዥያ ዜጎች ሱናሚ መታቸው ብለን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ያደረግን ሰዎች ለሚያውቁንና ለምናውቃቸው ክርስቲያን ወገኖች ጸሎት ለማድረግ ለምን እንደከበደን እንጃ፡፡ ለመሆኑ ከአንድ አባት ከጸሎት በላይ ምን ሊገኝ ይገባ ነበር?
‹ማንነታቸው ተረድተን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን እናድርጋለን› ይላል መግለጫው፡፡ ለመሆኑ ከክርስትና በላይ ምን ማንነት አለ? የብሔር፣ የብሔረሰብ ማንነት ነው የምታጣሩት? ከዚያ ይልቅ ሁኔታውን የሚከታተል፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኝና ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊም ቀኖናዊም ተግባር ነገሮችን የሚያመቻች ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ምነው በአንድ አጥቢያ ገንዘብ ተወሰደ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋም የለምን?
ሦስተኛው ያሳዘነኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ የሚደርሰውን ኀዘን የምትገልጥበት ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሥነ ሥርዓት የሌላት ይመስል ኀዘንን በሴኩላር መንገድ ስትገልጥ ማየቴ ነው፡፡ እኔ የጠበቅኩት ለአንዳንድ ክርስቲያን ላልሆኑ ‹ታላላቅ ሰዎች› ቀብር እንኳን የሚከፈተው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከፍቶ፣ ለቢዮንሴ እንኳን ያልተነፈጋት ማኅሌት ተቁሞ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ጳጳሳቱ የሚገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ፣ መግለጫው በጸሎቱ ፍጻሜ ይሰጣል ብዬ ነበር፡፡ የመግለጫው አሰጣጥ ግን የዕለት ተዕለት ተግባርን በተመለከተ የሚሰጥ ሳምንታዊ መግለጫ ነበር የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ አይሸትም፡፡ የተወካዮች  ምክር ቤት እንኳን የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ሊያውጅ መሆኑን ሲገልጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የጸሎት ሳምንት አለማወጇ የታሪክ ትዝብት ውስጥ የሚከታት ነው፡፡
እኔ የሲኖዶሱ መግለጫና አገላለጡ ወርዶብኛል፡፡ ሲኖዶሳዊም መስሎ አልታየኝም፡፡ ሊቃውንቱ ያዩት፣ ጳጳሳቱ የተወያዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያሹት፣ ቀኖናዎቹ የዳሰሱት፣ ትውፊቱ የነካው፣ ባሕሉ ያጠነው አልመስልህ አለኝ፡፡ ‹ወይ እንደ እስክንድ ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ› አለ ታላቁ እስክንድር፡፡

36 comments:

 1. ሲኖዶሱ መንግስትን ‘እንዴት ያለ መግለጫ እንስጥ’ ብሎ ጠይቆና ‘እንዲህ በሉ’ ተብሎ ተነግፘቸው ሀይማኖትና ፖለቲካ ሊጠቀማቸው የሚገቡ አገላለጾችን እንኳ ሳያገናዝቡ መግለጫው መሰጠቱን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ሲኖዶሱ መንግስትን ‘እንዴት ያለ መግለጫ እንስጥ’ ብሎ ጠይቆና ‘እንዲህ በሉ’ ተብሎ ተነግፘቸው ሀይማኖትና ፖለቲካ ሊጠቀማቸው የሚገቡ አገላለጾችን እንኳ ሳያገናዝቡ መግለጫው መሰጠቱን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 2. ወይ ዲያቆን ዳኒ, ወንበሩ ላይ ሰጋቸው በቻ እኮ ነው የተቀመጠው. ነፍሳቸወ ይህንን ማሰብ አይችልም.እግዚኦ መሐርነ ክርሰቶሰ!እንደ ቅዱሰ ዳዊት ማቅ ለብሰው መሬት ወርደው ሰማዕትነት ሰለ ተቀበሉ ልጆቻቸው የሚያለቅሱበት ልቦና ይሰጣቸው. እነርሱ እንደሆኑ የሰማዕትነት ዋጋ ከተቀበሉት ከነ ቅዱሰ እሰጢፉኖሰ, ፓውሎሰ ,ጴጥሮሰ, .. ጋር ተቀላቅለዋል. ሰማዕታት ደማቸውን ሰለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ይህን መራራ አለም ጥለውት አልፉዋል. ሰለ እራሳችን እናልቅሰ እንፀልይ.ዲያቆን ዳኒ መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 3. ተቃጠልን … አይደለም የመኖር የሞት እንኳን ክብር አጣን ፡፡ ለምን ? የበደላችን ጽዋ ሞልቶ ይሆን ?
  ነገን ፈራው- ዛሬን ጠላው// እግዚአብሔር ይማረን ፡፡
  ̎ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ̎
  አባካችሁ እንጸልይ ?

  ReplyDelete
 4. እኔ ዝም በዬ ሳስበው መንገስት እነዲህ ማለት ነበረበት ቤተክርስቲየን ደግሞ እንደዚህ ማለት በራሱ ደካም ነው የሚመስለኝ፡፡ እንዴት እንደዘነጋቸሀት በለውቅም በተከሰቱት እየተከሰቱ ባሉት ነገሮች ሁሉ በመንገስትና በቤተክርሰቲያን ተስፋ ከቆረጥን ቆየት ብለናል፡፡
  እምነት እንጂ የሀይማኖት መሪ የለንም ዝግጁ እመቤት ተብረላ የተጠራች የስርአት ሁሉ ቁንጮ የሆነች እንጂ ሰርአት አስፈጻሚ የሌለባት ቤተክርስቲያን ከሆነች ቆየት በላለች፡፡
  ታደያ ስለራሳቸው ብቻ በሚጨነቁ መሪዎች፡ ዛሬ ከተከሰተው ሀዘን ይልቅ የነሱ ምርጫ ከሚያሳስበው መንግስት፡ ቅዱሳነን ከመዘከር ይልቅ የስልጣን ህልውናቸው ከሚያሳስባቸው የሀይማኖት መሪዎች ምን ትጠቅቃላቸሁ፡፡ እነሱ ሁልጊዜ በተመዘኑበት ሚዛን ቀለው ነው የሚገኙት ፡ ለተገባረቸው የማያፈሩ ፡ በሀገሩ ዋና የተለቪዥን ጣቢያ በየቀኑ ነው የሚዋሹት ምን አዲስ ነገር አለው፡፡
  አንድ ነገር ግን እናውቃለን ማንም ምንም ቢል ያለቁት ወገኖቻችን አንድም ኢትዮጵያውያን ናቸው አንድም ክርስቲያኖች ናቸው አንድም ሰማዕታት ናቸው፡፡ ማንም ክብር በምድር ባየሰጣቸው የምናምነው አምላክ ነብሳቸውን በዕልልታ ይቀበላል ከቀደሙት አባቶቻችን ሰማዕታት ጋርም ይደምራቸዋል፡፡
  እነሱ አንደኛውን ይዘውታል ይብላኝ ለእኛ እዚህ ቆመን በሀገራቸን የውርደት ሸማ ለተከናነብነው፡ ይብላኝ በእምነታቸን ስም ኪሳችሁን እየሞላቸሁ ልጆቻችሁን በጠራራ ፀሐይ ለካደችሁ ፍርዱ የርሱ ነው፡፡


  ReplyDelete
 5. ‘መልእልተ ኩሉ’ ብትባልስ ከስሟ ኋላ “የኢትዮጵያ…” የሚል ቅጽል መኖሩን ስታውቅ፣መንግሥት እንጅ ቤ/ክ በየሀገሩ ኤምባሲ እንደሌላት እየተረዳህ፣ቤ/ክ ቤተሰባዊ መረጃ የምትይዝበት መንገድ ያን ያሕል እንዳልተጠናከረ ስታውቅ፣“በሪሞት በባትሪ” እያሉ መሳለቅ ለምን? የባዕድ ተመልካች መሰልክብኝ ወንድምዓለም፡፡
  ለሱናሚው ጸሎት የተደረገው የነፍስ አድን ዘመቻው ሲጠናቀቅ እንጅ ሰቆቃው እንደተሰማ በግብታዊነት አይደለም፡፡ተው እንጅ ወንድማችን፡፡በኮሞሮስ ለተከሰከሰው አውሮፕላን ጸሎት ሲደረግስ አባቶችና ሊቃውንት ተሰብስበው በወጉ በሥርዓቱ እንጅ ድንገት በሰዓታት እድሜ ተሰብስቦ አልተደረገ፡፡ምናለበት አባቶቻችንንም እንደኛ ሰብዓዊነት የሚሰማቸው ፍጡራን ስለመሆናቸው እንኳ ብናስብ? የኃዘኑ ውርጅብኙ ለእነሱም እኮ እንደሁላችንም የከበደ ነው፡፡ቢዮንሴን እየጠራህ ማላገጥህ የደረስክበትን ተዐብዮ እንጅ ተቆርቋሪነትህን አይገልጽም፡፡አንተም እንደ ባዕድ ታነውረን!!
  እረ ተው አንተ ልጅ፡፡በየትኛው አጥቢያ ነው ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ለገንዘብ ማጣራት ሲሰየም ያየኸው?እረ እንዲያ የሚባል አጥቢያ የደረሰ ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ አያውቅም፡፡ተው ያልኾነ ጸያፍ ቅኔ ለመቀኘት አትሞክር፡፡
  እንደምታየው በግብጻውያን ስናየው ሩቅ የመሰለን ሰቆቃ ድንገት ሲደርስ ሁላችንም ተወዛግበናል፡፡ተቋማቱም ሰብዓዊ ፍጥረታት የሚመሯቸው ናቸውና እንዲያ ሆኑ፡፡በዚህ ላይ እኛ እንደ ዐረባውያኑ ግብጻውያን በጂኦግራፊም ሆነ በቋንቋ ቅርርብ ከሊብያ የተሻለ መረጃ ስለሰማዕታቱ የምናገኝበት እድል ጠባብ እንደሆነ አትስተውም፡፡ይሄን ሁሉ አስበህ ከተቋምህ እና ከመራሕያኑ ጎን ቆመህ በቀና ልቡና ከአንድ ምሑር የሚጠበቀውን መንገድ የማሳየት ስራ መስራት ሲገባህ ኀዘኑ ከተሰማ ጀምሮ “ቤተክሕነት እንዴት ሊኾን ይኾን?” በሚል የሟርት መንገድ ጀምረህ ሂደቱን ሁሉ እየተከታተልክ ማጠልሸትህ አንድም የኖረ ቂም ነው፣ወይም ከጋራ ቁስላችን ለማትረፍ የምታካሂደው ርካሽ እወደድባይነት ነው፡፡
  ባሏ የሞተባትን ሴት ዐይንና ዕንባ አወራረድ እየተመለከቱ እንደሚሳለቁ የሟች ቤተሰቦች የአባቶቻችንን እንቅስቃሴ እያሳደዱ ማነወር ርኵሰት ነው፡፡የቅን ልጅ ስራ ተግባር አይደለም፡፡ትናንት ስለግብጻውያን…እስመ ዘኢይትመወት ሞተ፡ሞተት እስክንድርያ…ሲሉ የነበሩ ኅዙናን አባቶቻችን ስለ መንፈስቅዱስ ልጆቻቸው ሞት እንደማይገዳቸው አድርጎ ማቅረብ ያማል፡፡ተው፡፡ካንተ መንገድ ጠቋሚነትን እንጅ ተሳልቆን አንጠብቅም፡፡
  ተው፡፡የጋራ ሕመማችንን በቅጡ የምንወጣበትን መንገድ ማሳየት እንጅ ከኀዘናችሁ ኀዘናችን ስለበለጠ ሲኖዶስ አይደላችሁም አይነት ሰድቦ ለሰዳቢ የመስጠት ስሜታዊ ጎዳና የሚያንጽ አይደለም፡፡ይሕን በመሰለ የጋራ ሰቆቃ ላይ ታዝሎ በሌላው መሳለቅ ጸያፍ ነው፡፡
  አቤቱ የወንድሞቻችንን ደም ከደም ሰማዕታት ደምርልን!!አሜን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ አንተ ለኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ነው እንጂ ቂርቆስ ላይ ለቅሶው የተጀመረውኮ እሑድ ዕለት ነው፡፡ ምን የተለየ መረጃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስሕተቱን በስሕተት መከላከል የባሰ ስሕተት መሥራት ነው፡፡ ደግሞስ እነርሱ ሲሳሳቱ ያላፈሩትን እርሱ ሲጽ ለምን ያፍራል፡፡ ኢየሩሳሌም ገዳም ገንዘብ ጎደለ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ተሰይሞ ማጣራቱን ዜና ቤተ ክርስቲያን ሲዘግብ አላነበብክምን፡፡ በሃይማኖቱ ምክንያት የሞተን ሰማዕትና በአደጋ ምክንያት የሞተን እኩል ነው የምታየው ማለት ነው፡፡ አሰቃቂነቱ ላንተ ሁለቱም እኩል ነው፡፡ እባክህ መጀመሪያ ሰው ሁንና ከዚያ በኋላ ጻፍ፡፡

   Delete
  2. አየህ በሽታህ፣ ለማዳመጥ፣ ለመታረም አለመቻላችን ነው፡፡ ሕዝቡ እኮ ከአባቶቹ ብዙ ብዙ ቀድሟል፡፡ ዲ/ዳንኤል በሕዝቡ የታዘበውን ነው የጻፈው፡፡ እርሱ ብይጽፈውም እኛ እያልነው ነውኮ! ባንተና በርሱ መካከል ያለ ችግርህን ለጊዜው ትተኸው ምናለ የብዙኃኑን ሕዝብ ስሜት የሚያዳምጥ ልብ ቢኖርህ? ይኸው ሕዝቡ ሰልፍ እየወጣ ነው፡፡ ነገም ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል፡፡ የሚባለውን ስማ፡፡ እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብና ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናን መሪ አላቸውን? ከሞቱት ወገኖች እኩል ሐዘናችንን ያጸናብን ይኸው ነው፡፡ ነገን ተስፋ እንዳናደርግ፡፡ ሕዝብ መምራት እንኳን ቢያቅታችሁ ሕዝቡን ከስር ከስር እየተከተላችሁ፣ ምዕመኑ ምን አለ እያላችሁ መልስ መስጠት እንዴት ያቅታችሁ ይህንንስ እንዴት ትክደዋለህ? ለምን ወጣ ብለህ አትጠይቅም? አትታዘብም?

   Delete
  3. ወዳጄ ምናልባት የቤተክህነቱ የቅርብ ሰው እንደምትሆን እንገምታለን ከላይ የጠቀሰው አንባቢ እንዳለው ስህተን ለመሸፈን የሚደረግ ሥራ ሌላ ስህተት መሥራት መሆኑን እንዳትዘነጋ እረ ለመሆኑ ቤተክነቱ ቋንቋ አጥቶ ነው እንዴ በቀጥታ ከመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የወጣውን ቋንቋ ቃል በቃል የወሰደው?
   ቤተክርስቲያናችን እኮ ስንዱ እመቤት፣ የቋንቋሆች ባለቤት የሆነች መሆኗን አንተም ታውቀዋለህ እኛም እንገነዘባዋለን ነገር ግን የእኛ ቤተክርስቲያን መሪዎች እነ አባይ ጸሐዬ ወይም ሬድዋን ሁሴን የሰጧቸውን ማኅተም አድርገው የሚያስነብቡን ምናለበት በረጋ መንፈሥ መንፈሣውያን አባቶች ተነጋግረውበት ቋንቋውንም አጠይመው እንደ ወረደ ተገልብጦ የሚወጣው እንደው ትንሽ ማፈር እንኳ የለም ሰው ይታዘበናል ምዕመናኖቻችን ምን ይሉናል የምንመራቸው የምንጠብቃቸው መንጋዎች ይታዘቡናል የሚባል ነገር ጭራሽ ቀረ እንዴ። ለነገሩ ቤተክርስቲያናችን ካሏት 18 የሚገመቱ የተለያዩ መምሪያዎች 16 የሚሆኑት የተያዙት ወይም የመምሪያዎቹ ሃላፊዎች እንእንትና አይደላችሁም እንዴ እንደው ምዕመን ዝም ሲል የማያውቅ ይመስላችኃል እንዴ እረ ተው . .. ተው ይሄ ጽዋ ይሞላል እንደዚህ በምዕመናን ብሎም በሃገራችን ይኽው አሁን ደግሞ በሰማዕታት ኢትዮጵያውያን ላይ ታላግጣላችሁ እንደው አፍስ አለን ብላችሁ ታወሩልናላችሁ እንዴ? ተው ግድ የለም የዛሬውን እንለፍ ነገም ይመጣል በዚህች አገር ላይ እኮ አብረን ነው የምንኖረው
   አለማፈርህ ነው እንጂ የኛ መሪዎች እኮ ባለፈው ግፃውያኑ በግፍ በሃገራቸው በሙስሊም ወንድማማቾች በተገደሉ ጊዜ እኮ የቤተክርስቲያን መሪዎች ነን ባዮች ቀደምት ነበሩ የሐዘን መግለጫ ለመላክ ከምሥራቃውያኑ አብያተ ክርስቲያናት ቀደምት ነበሩ ታዲያ ዛሬ ለእራሳችን ሰማዕታት ለዚያውም ቤተሰቦቻቸው በልቅሶ ተቀምጠው ባሉበት ጊዜ እኮ ነው ዜግነታቸውን አጣርተን እንጸልያለን የሚሉን? እንዴት እንዲህ አይነት ጊዜ ላይ ደረስን ወገን አቶ ሬድዋን (እስላም) የተናገሩን ቃል በቃል ሰውየው ሲጀመር እራሱን መሆን ያቃተው ሰውን ለመምሰል ሲሞክር ይኽው እስካሁን ይዳክራል የሰው መሳለቂያ በዛ ላይ የአራጆቻችን የበኩር ልጅ ስለምን ቢባል ከዚህ ሰው ቃል ይዋሳሉ?? ?
   መልሱ ለራስህ ይሁን እና ሲመስለኝ ካህን ተመስላለህ እውን እግዚአብሔር በሚወደው እና በሚፈልገው መንገድ ነው እረኞችን እየጠበክ ያለህው ወይንስ የምትጠብቀው እነእንትናን ብቻ ነው? ወይስ ስለሌላው አይመለከትህም ሲጀመር ጀምሮ የእኛ አባቶች ጥላሸት በራሳቸው መቀበት የጀመሩት እኮ እራሳቸው ናቸው እነ አባይ ጸሐዬን ሲከተሉ ነገር ልጆቻቸው ሰማዕትነት አሳዩአቸው ይህ ሰማዕትነት ለአባቶች ነበር አባይ ጸሐዬ መጥቶ እንዲህ አርጉ እንዲህ አታርጉ ሊላቸው ተቀብለው ከመፈጸም የለም ቤተክርስቲያናችን እንዳንተ ያለውን ጉግማንጉግ አትሰማም እኛ የክርስቶስ ወታደሮች (እንደራሴዎች) ነን ብለው በመለሱት ነበር ፖትርያሪኩም አባይ ጸሐዬ እኮ ነው እዚህ መንበር ላይ ያወጣኝ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአባይ ጸሐዬ፣ እግዚአብሔር እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን በሚጠይቀኝ ሳይሆን አባይ ጸሐዬ በሚያዘኝ ብለው የተቀመጡ መሆናቸውን እረሳነው እንዴ?? እንደዛማ ባይሆን ትላንት የዋልድባ መነኮሳት እረ የፈጣሪ ያለህ እረ የወገን ያለህ ቤተክርስቲያናችሁን ጠብቁ፣ ቅርሶቻንን እንጠብቅ፣ ገዳማችን አይፈርስም እያሉ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ እኮ በቴሌቭዥናችን መስኮት መጥተው "ማርያምን" የማውቀው ነገር የለም ያሉን አባቶች የሞሉበት ሲኖዶስ እኮ ሆኗል።
   ዛሬ ዛሬ የሲኖዶሱ አባቶች ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሳይሆን ዓለማዊ ሥርዓቶችን አይደለም እንዴ እያስተማሩን ያሉት? እስቲ መልስ ዛሬ ስንቶቹ የሲኖዶስ አባላት ናቸው በገዳም የሚኖሩ ወይም ቅዱስ ሲኖዶስ ባዘጋጀው ማረፊያ የሚያርፉ? እማናውቅ ሆነን ነው እንዴ ስንቶቹ የሲኖዶስ አባላት ከአንድም የሦስት ትላልቅ የቪላ ባለቤቶች አይደሉም እንዴ? ታዲያ ዛሬ እንዲህ ሲባሉ ምነው ኮረኮረህ እራሳቸው አይደሉም እንዴ ጥላሸት መልካም ስማቸውን የቀቡት ምን ያስገርማል ዛሬ ወሬያቸው ሁሉ ምን አገኛለው ነው እንጂ እግዚአብሔር በምን ይደስትበታል ብሎ የሚሉ በጣት የሚቆጠሩ አረጋውያን አባቶች አይደሉም እንዴ ስለዚህ ወዳጄ እኔም በዲ/ን ዳንኤል እስማማለው እንኳን ቤተክህነትን ሊሸት እንደው እረ ተወኝ እባክህ የእነሱን ነገር መድኅኒዓለም ፍርዱን ይስጥ
   ትላን እኮ ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቦ ገዳም ሲቃጠል "ምን አዲስ ነገር አለ? የስንቱ ቤት ይቃጠል አይደለም ወይ" ብለውን ያሉት እነማን ናቸው እግዚአብሔር ይደሰትበታል ወይ ይከብርበታል ወይ፣ደዓዳ የሆነውን ሥብሃት ከማቅረብ ዛሬ ምድራውያኑን ተመልክተው ሥብሐታቸውም ምድራዊ ሆኗል እኮ ምዕመን አይናገርም እንጂ ብዙ ታዝቧል ብዙ ቆስሏል በሃገራችን መሪዎች እና በቤተክርስቲያናችን መሪዎች ተስፋ ቆርጧል እግዚአብሔርም ከራማ ይሄንን ሁሉ ያያል ይሰማል በመንበሩ ቁጭ ብሎ እድሜ ለንሰሃም ይሰጣል፣ ነገር ግን ያ የሞላ ለት ወየውልን መድረ አሸርጋጅ ሁላ ወየውልን ሰማያዊ ጅራፉ የተነሳች እለት የምጽዓት ቀን ናት ያቺ ሁላችንንም ከዛ መዓት በረደኤቱ ይጠብቀን ለመሪዎቻችንም ልቦናውን ይስጣቸው ለምድራውያኑ አደለም እነሱ ልቦና የታላቸውን እና ለእረኞቻችን ማለቴ ነው
   የሰማዕታቱ በረከታቸው በሁላችንም ላይ ይደርብን ቀድሶ የሚያቆርበን ንሰሃችንን የሚቀበል አባት አያሳጣን እላለሁ

   Delete
 6. ዲ/ን ዳንኤል፣ እግዚአብሔር ያክብርህ፡፡ ሲኖዶሱ በጭራሽ አልተሰበሰበም፣ አባ ማትያስ የዶ/ር ሽፈዉ ተክለማርያምን መልእክት ነዉ እኮ የቤተክርስቲያን ብለዉ ያስነበቡ፡፡ በገዳማት ያሉ ደጋጎች እነዲጸልዩ መንገር ነዉ፣ ቤተክርስቲያኑአ መደበኛ /ፎርማል/፣ የሚቆረቆርላት፣ ለመንጋዉ የሚያስብ አስተዳዳሪ ስለሌለ፣ የጠበቅነዉን ነዉ ያየነዉ፡፡ እግዚአብሔር የግበጻዉያንን አይነት አባቶች/ፓትርየርክ፣ጳጳሳት/ ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 7. enes endenesu behaimanot yetsenahu negn erasachinin enimermir tilik timihirt setewinal behaimanot metsinat eskemot dires metamenew

  ReplyDelete
 8. Dani,
  this is an article that all christians will agree on. I DON HAVE AN ADDITIONAL COMMENT......THIS IS MORE THAN ENOUGH.
  Abdul mejid hussen'n hedew yikberu....

  ReplyDelete
 9. TheAngryEthiopian/ቆሽቱ የበገነውApril 20, 2015 at 6:48 PM

  የገናናውና የታላቁ ንጉሰነገሥታችን አፄ ዘርዓያቆብ ጊዜ http://www.geezonline.org/2013/11/ethiopias-foreign-relations-then-and-now.html

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንኤል፣ እግዚአብሔር ያክብርህ፡፡ ሲኖዶሱ በጭራሽ አልተሰበሰበም፣ አባ ማትያስ የዶ/ር ሽፈዉ ተክለማርያምን መልእክት ነዉ እኮ የቤተክርስቲያን ብለዉ ያስነበቡ፡፡ በገዳማት ያሉ ደጋጎች እነዲጸልዩ መንገር ነዉ፣ ቤተክርስቲያኑአ መደበኛ /ፎርማል/፣ የሚቆረቆርላት፣ ለመንጋዉ የሚያስብ አስተዳዳሪ ስለሌለ፣ የጠበቅነዉን ነዉ ያየነዉ፡፡ እግዚአብሔር የግበጻዉያንን አይነት አባቶች/ፓትርየርክ፣ጳጳሳት/ ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ዳንኤል፣ እግዚአብሔር ያክብርህ፡፡ ሲኖዶሱ በጭራሽ አልተሰበሰበም፣ አባ ማትያስ የዶ/ር ሽፈዉ ተክለማርያምን መልእክት ነዉ እኮ የቤተክርስቲያን ብለዉ ያስነበቡ፡፡ በገዳማት ያሉ ደጋጎች እነዲጸልዩ መንገር ነዉ፣ ቤተክርስቲያኑአ መደበኛ /ፎርማል/፣ የሚቆረቆርላት፣ ለመንጋዉ የሚያስብ አስተዳዳሪ ስለሌለ፣ የጠበቅነዉን ነዉ ያየነዉ፡፡ እግዚአብሔር የግበጻዉያንን አይነት አባቶች/ፓትርየርክ፣ጳጳሳት/ ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 12. ክሲኖዶሱ ምንም አንጠብቅ። ምናልባት ከሃይማኖት አርበኞች ጥቂት የሲኖዶሱ አባላት እንጂ። ክርስቲያኑ በቢቱ እና በአጥቢያው በጸሎት ያስብ እንጂ። የአለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ግን ሊመሰገኑ ይገባል።

  ReplyDelete
 13. ይድረስ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት።

  እኔን ያልገባኝ ነገር፣ ነገሮችህ ሁሉ መንፈሳዊ መንፈሳዊ አልሸት አሉኝሳ?! ምንድነው ዋናው ዓላማክ??? ቤተክርስቲያንን ሰድቦ ለሰዳቢ አሳልፎ መስጠት ነው እንዴ??? ወይስ ብዙ በተናገርክ ቁጥር የቤተክርስቲያን ጠበቃ የሆንክ መስሎ ይሰማሃል? ይበልጥ እኔን ግራ ያጋባኝ አቋምህ ደግሞ, አንዴ "የኢትዮጵያ ክርስቲያን" ትላለህ፣ ሲልህ "ኢትዮጵያውያን ስደተኞች" ትላለህ፣ ሲያሰኝህ ደግሞ "የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት መግለጫ ይሰጣሉ ብዬ እጠብቃለሁ።" ትላለህ። በመሰረቱ ራሳቸውን"የኢትየጵያ እምነት ተቋማት" ብለው የሚጠሩ አካሎች ምን የሚመለከታቸው ነገር አለና ነው መግለጫ የሚሰጡልህ??? የተነካባቸው አባል ወይም አካል አለ??? ለመሆኑ የታረዱት ((የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች???)) ወይስ "የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች???" አንተ እነዚህን ሰማእታት ማን ብለህ ነው 'ምጠራቸው??? እንዴ! ለምን እንደ ኦርቶዶክሳዊነትህ "የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሊቢያ ሰማእትነት ተቀበሉ።" ብለህ ደፍረህ አትናገርም? ሌሎች ራሳቸውን "የኢትዮጵያ ክርስቲያን ነን" ብለው እንደሚጠሩ ተቋማት አንተም "የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች" እያልክ ታስተጋባልናለህ እንዴ??? በየትኛውም ዓለም እግርህ እስኪቀጥን ብትዞር መከራ እየተቀበለ ያለው "የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ(የኦርቶዶክስ ክርስቲያን) እንጂ፣ የካቶሊክ ወይም የፕሮቴስታንት አሊያም የሌላ ራሳቸውን "ክርስቲያን" እያሉ የሚጠሩ አካላት "አማኝ ነን" ባዮች አይደሉም። ((በመላው ዓለም ኦርቶዶክሳዊ ብቻ ነው እየታረደ ያለው።))

  እኔ ግን ዝም ብዬ ሳይህ ሌሎች የእምነት ተቋማት(ራሳቸውን እንደሚሉት) እንዳይቀየሙክ የማቻቻል ንግግሮችን ይመስላል የምትናገረው። በቃ አንተ 'ምትወክለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ነው። ስለዚህ አንዴ "የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች", "አንዴ የኢትዮጵያ ስደተኞች" እያልክ በጅምላ አትጻፍ። "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልጆች ታረዱ።" ስትለን ነው ኦርቶዶክሳዊ መልእክት የሚሆነው። አለበለዚያ ንግግርህ ስለሃይማኖት መቻቻል የምትሰብክ ነው የሚያስመስልብህ(የሆነ አካል እንዳይቀየምህ።)

  #ስለዚህ "ወይ እንደ ኦርቶዶክስ ጻፍ ወይ የኦርቶዶክስን ስም መልስ።"

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይይ በጣም ታሳዝናለህ ትንሽ ሰፋ ያለ አመለካከት ቢኖርህ…..…

   Delete
  2. ወንድሜ በስሜታዊነት አትነዳ፤ ዲ/ዳንኤን ኦርቶዶክሳዊም ኢትዮጵያዊም ነው፡፡ ብሔራዊም ኦርቶዶክሳዊም ጉዳይ እንኳን እርሱ እኛ እያንዳንዳችን ይመለከተናል፡፡ አንተ ላያገባህ ይችላል፡፡ ሌላው አንተ ዲ/ዳንኤልን በስሜታዊነት እንጂ በእውቀት አትበልጠውምና ምህርህን ለጊዜው አዘግየው፡፡ በኔ እይታ የማላተም ስትራቴጂ ያላት ትመስላለች፡፡ ዲ/ዳንኤል እንዲ አለ ብሎ ለመሮጥ ምችመች መፈክር የመሰለች ምክር፡፡ የመለያየትና የማላተም ምኞት ያላት ምክር፡፡ ካድሬ ካድሬ ምችሸት ምክር፡፡

   Delete
  3. ከመጻፍህ በፊት አንብብ ሰዎቹ እኰ ኦርቶዶክስ ካቶሊክ ፕሮቴስታንት..... ብለው አልጠየቁም ምነው ልዩነታችንን ወደ ጐን በመተው ልብ ብንገዛና ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን ብንፀልይ ምናልባትም እግዚአብሔር ይቅር ይለን ይሆናል ፀሎታችንንም ይሰማናል። ወንድሜ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጥህ።

   Delete
  4. stupid ppl always draw a wrong conclusion from the right article. leave the guy alone, at least he can write what the general ppl feel about the where our religion & government stand which is the lowest point in History (every body is a cadre not religious leader including urself).

   Delete
 14. ዲ/ን ዳንኤል፣ እግዚአብሔር ያክብርህ፡፡ ሲኖዶሱ በጭራሽ አልተሰበሰበም፣ አባ ማትያስ የዶ/ር ሽፈዉ ተክለማርያምን መልእክት ነዉ እኮ የቤተክርስቲያን ብለዉ ያስነበቡ፡፡ በገዳማት ያሉ ደጋጎች እነዲጸልዩ መንገር ነዉ፣ ቤተክርስቲያኑአ መደበኛ /ፎርማል/፣ የሚቆረቆርላት፣ ለመንጋዉ የሚያስብ አስተዳዳሪ ስለሌለ፣ የጠበቅነዉን ነዉ ያየነዉ፡፡ እግዚአብሔር የግበጻዉያንን አይነት አባቶች/ፓትርየርክ፣ጳጳሳት/ ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 15. ዲያቆን ዳንኤል እ/ር ይባርክህ አንድ ጓደኛዩ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ምን ብሎ የሚጠራት መሰለ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊካን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይህንን ነው ዛሬ ያሁት

  ReplyDelete
 16. አሁንስ አበዛሀው!! ዝምብለህ መንቀፍ ነው እንዴ ስራህ የሆነው? ተናግረህ ሞተሃል አሁን አንተ ወደ ትዕቢት እያመራህ ያለህ ነው የመሰልከኝ!!

  ReplyDelete
 17. Perhaps it is time for countries with a Muslim minority population to start a mass removal of Muslims. Seeing the turmoil around the globe, Imagine how peaceful the world would be without Islam in any country, even their own, they kill each other. send them all back to the middle east and let them at one another. it would be Islam's problem and no longer the entire globe. There are far too many bad Muslims that come along with the good Muslims so all must go.
  Ayatollah Obama on Worldwide Jihad: "We Can't seem to Pin Point The Problem"....Really?

  The Shoe Bomber was a Muslim
  The Beltway Snipers were Muslims
  The Fort Hood Shooter was a Muslim
  The underwear Bomber was a Muslim
  The U.S.S. Cole Bombers were Muslims
  The Madrid Train Bombers were Muslims
  The Bali Nightclub Bombers were Muslims
  The London Subway Bombers were Muslims
  The Moscow Theatre Attackers were Muslims
  The Boston Marathon Bombers were Muslims
  The Pan-Am flight #93 Bombers were Muslims
  The Air France Entebbe Hijackers were Muslims
  The Iranian Embassy Takeover, was by Muslims
  The Beirut U.S. Embassy bombers were Muslims
  The Libyan U.S. Embassy Attack was by Muslims
  The Buenos Aires Suicide Bombers were Muslims
  The Israeli Olympic Team Attackers were Muslims
  The Kenyan U.S, Embassy Bombers were Muslims
  The Saudi, Khobar Towers Bombers were Muslims
  The Beirut Marine Barracks bombers were Muslims
  The Besian Russian School Attackers were Muslims
  The first World Trade Center Bombers were Muslims
  The Bombay & Mumbai India Attackers were Muslims
  The Achille Lauro Cruise Ship Hijackers were Muslims
  The September 11th 2001 Airline Hijackers were Muslims

  The complete list is literally endless and added to daily.

  Think of it, "pretty much" in today's world:

  Buddhists living with Hindus = No Problem
  Hindus living with Christians = No Problem
  Hindus living with Jews = No Problem
  Christians living with Shintos = No Problem
  Shintos living with Confucians = No Problem
  Confucians living with Baha'is = No Problem
  Baha'is living with Jews = No Problem
  Jews living with Atheists = No Problem
  Atheists living with Buddhists = No Problem
  Buddhists living with Sikhs = No Problem
  Sikhs living with Hindus = No Problem
  Hindus living with Baha'is = No Problem
  Baha'is living with Christians = No Problem
  Christians living with Jews = No Problem
  Jews living with Buddhists = No Problem
  Buddhists living with Shintos = No Problem
  Shintos living with Atheists = No Problem
  Atheists living with Confucians = No Problem
  Confucians living with Hindus = No Problem

  Muslims living with ANY Non-Muslims = BIG PROBLEM

  But they desire most to live in almost every country that is not Islamic! And who do they blame? Not Islam... Not their leadership... Not themselves...

  They blame their newly adopted country. And they want to change the countries they've adopted, to be like the countries they came from where they were unhappy.

  Islamic Jihad: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  ISIS : AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Al-Qaeda: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Taliban: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Hamas: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Hezbollah: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Boko Haram: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Al-Nusra: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Abu Sayyaf: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Al-Badr: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Muslim Brotherhood: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Lashkar-e-Taiba: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Palestine Liberation Front: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Ansaru: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Jemaah Islamiyah: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION
  Abdullah Azzam Brigades: AN ISLAMIC TERROR ORGANIZATION

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቀሽም! ከየትም ለቃቅመህ ዝምብለህ copy paste ታረግብናለህ እንዴ! የምትጨምረው ሀሣብ እንኳን ባይኖርህ ምናለ from google የሚለውን ብትጨምርበት ?

   Delete
 18. ዲ/ን ዳንኤል፣ እግዚአብሔር ያክብርህ፡፡ ሲኖዶሱ በጭራሽ አልተሰበሰበም፣ አባ ማትያስ የዶ/ር ሽፈዉ ተክለማርያምን መልእክት ነዉ እኮ የቤተክርስቲያን ብለዉ ያስነበቡ፡፡ በገዳማት ያሉ ደጋጎች እነዲጸልዩ መንገር ነዉ፣ ቤተክርስቲያኑአ መደበኛ /ፎርማል/፣ የሚቆረቆርላት፣ ለመንጋዉ የሚያስብ አስተዳዳሪ ስለሌለ፣ የጠበቅነዉን ነዉ ያየነዉ፡፡ እግዚአብሔር የግበጻዉያንን አይነት አባቶች/ፓትርየርክ፣ጳጳሳት/ ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 19. ሁሉም የየስሜቱን ይፅፋል፣ እኔም ታዘብኋችሁ!!!

  ReplyDelete
 20. አዬ...... ምን ዘመን ላይ ደረስን ምንስ መልካም ዜና እንሰማ ይሆን?
  እግዚአብሄር ሰዉን በመልኩ ፈጠረ ........ ዛሬ ሰዉ በአገሩ ሆኖ መስራት ካልቻለ ምን ምርጫ አለዉ ..... መሰደድ በአገር መሰደድ፤ ከክልል መሰደድ ከንግድ ቦታ መሰደድ ታዲያስ .... ሌላ ቦታ ሄዶ መስራት እና መብላት፤ መኖር .... በዘመናዊ ባርነት መኖር፡፡ ታዲያ ቤተክርስቲያንን የሚያዉቅ እኮ ድምፁአን ያዉቃል፤ ቃናዋን ያዉቃል፤ ሽታዋን ያዉቃል፡፡ በዕዉነት ይህ ድምፅ ያ ድመፅ ነዉ?

  ReplyDelete
 21. ዲ/ን ዳንኤል፣ እግዚአብሔር ያክብርህ፡፡ ሲኖዶሱ በጭራሽ አልተሰበሰበም፣ አባ ማትያስ የዶ/ር ሽፈዉ ተክለማርያምን መልእክት ነዉ እኮ የቤተክርስቲያን ብለዉ ያስነበቡ፡፡ በገዳማት ያሉ ደጋጎች እነዲጸልዩ መንገር ነዉ፣ ቤተክርስቲያኑአ መደበኛ /ፎርማል/፣ የሚቆረቆርላት፣ ለመንጋዉ የሚያስብ አስተዳዳሪ ስለሌለ፣ የጠበቅነዉን ነዉ ያየነዉ፡፡ እግዚአብሔር የግበጻዉያንን አይነት አባቶች/ፓትርየርክ፣ጳጳሳት/ ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 22. Oh hapen "AnonymousApril 21, 2015 at 1:43 AM"
  Atekatele enje leyunetu Yeweket enje yesewenet aydelem
  Dani tebarek

  ReplyDelete
 23. dani egizabher tsinatun yisitih.....le ethiopia endate chigiruan yemiyawik tiwilid yasifeligal....lemauch beteseboch metsinanatin medihanialem yistilin

  ReplyDelete
 24. ኢትዮጵያውያን ፣ሙስሊም ክርስትያኑ፣ በዜጎቻችን ላይ በደቡብ አፍሪካና በሊብያ በደረሰው ግፍና ሰይጣናዊ ግድያ በጥልቅ ሀዘን የምንገኝበት ወቅት ነው፡፡ አንድነታችንን ከማንም ጊዜ በላይ ያሳየንበት፣ እንደ አንድ በአንድ ልብ ሀዘናችን የገለፅንበትም ወቅት ነው፡፡ይሁንና አንዳንድ ለርካሽ ግላዊ/ፖለቲካዊ ትርፍ እንጂ ለዜጎች ደንታ የሌላቸው ግለሰቦችና የፖለቲካ ቡድኖች ይህን ጥልቅ ሀዘናችን ለርካሽ አላማቸው መጠቀምያ ለማድረግ ሽርጉድ ሲሉ ይታያሉ፡፡ ይህ ድርጊታቸው ተረድተን ካላስቆምናቸው ካለፈው የበለጠ ዋጋ እንከፍላለን፡፡

  ReplyDelete
 25. you have very good view relly you are wonderful l!!!

  ReplyDelete
 26. empty,killin sb is not being terrerrosim,

  ReplyDelete
 27. ጎሽ ዳንኤል! ልክ እንደዚ ወደ እውነታውን ስታንፀባርቅ ለውስጣዊ ሰላምህም ሆነ ለህዝባዊ ቅቡልነትህ አንድ ቀን ማስረጃ ይኾንሀል፡፡ ዳኒ አቅም/potential እንዳለህ ግልፅ ነው፡፡ ግና ሁሌም መዘንጋት የሌለብህ ነገር እቅም ካለ አቋም ባዶ ነውና፡፡ የህዝባችንን ብሎም የሀይማኖታችንን ስሜት without fear and favour ግለፅለት፡፡ ያኔ እመነኘኝ ህዝባችን ለታመነለት ሟች ነው ይክስሀል፡፡
  ephraim

  ReplyDelete