click here for pdf
በተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነት
መሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸው
ተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡
አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉት
አሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባት
ያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን ሰምተን ነበር፡፡ አይሲስ አገር የለውም፡፡
እነዚህ ወንድሞቻችንማ ማተብ የሚያደርጉበትን
አንገት ለእምነታቸው ሲሉ የሰጡ ቅዱሳን ሰማዕታት ናቸው፡፡ እኛ በቃል ብቻ የምንናገረውን ሰማዕትነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን በተግባር
ያሳዩ የተግባር ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ምናልባት ባለ ሥልጣናቱና ሚዲያዎቹ ይህንን ለመናገር የከበዳቸው ሌሎች አማኞችን እናስከፋለን
ብለው አስበው ይሆናል፡፡ እውነት ለመናገር ግን በግድ ሃይማኖታቸውን ወደ እስልምና (ያውም አይሲስ ወዳጣመመው የእስልምና አመለካከት)
መቀየር ነበረባቸው ብሎ የሚከራከር ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡ ቢኖርም አመለካከቱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንጂ እርሱን
ላለማስቀየም እውነቱን መካድ አያስፈልግም፡፡
የአይሲስን ሐሳብ ተቀብለው፣ እምነቱን
አራምደው፣ ከእርሱ ጋር ተቀላቅለው ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን እድሜ ለማራዘም ቢፈልጉ መንገዱ ነበረ፡፡ ወላዋዮች፣ ለእምነት ግድ የለሾ፣
እምነታቸው እንደ ሸሚዝ ለመቀያየር የሚፈልጉ አቋም የለሾች ቢሆኑ ኖሮ ሞት ሩቅ ነበረ፡፡ እነ ኢያሱ፣ እነ ባልቻ፣ እነ ተስፋየና
እነ ዳንኤል ግን እንደዚያ አልነበሩም፡፡ በእምነታቸው ጸኑ፤ በክርስቲያንነታቸው ታረዱ፣ ሰማዕትነትንም ተቀበሉ፡፡
ይኼንን እውነታ መካድ ሰማዕታቱን
ሁለት ጊዜ መግደል ነው፡፡ ከሞታቸው በላይ የሞቱበትን ክቡርና ቅዱስ ዓላማ መካድ አብልጦ ይገድላቸዋል፡፡
ደግሞም ስደተኛነታቸው ለአደጋው
ምክንያት ሆነ እንጂ የተሠዉት በስደተኛነታቸው አይደለም፡፡ ስደተኞችም ሆነው እምነታቸውን ለመለወጥ ቢፈልጉ ኖሮ ይችሉ ነበር፡፡
የተሠዉት በክርስትናቸው ነው፡፡ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አንገታቸውን የሰጡት ለክርስቶስ ነው፡፡ እንደ አግናጥዮስ ምጥው
ለአንበሳ አነጋገር ‹እንደ ንጹሕ መገበሪያ ስንዴ ሆነው› ለአምላካቸው ነው በመሥዋዕትነት የቀረቡት፡፡
እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና
እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?
ሰለ ሃይማኖታችን መፍራትና ማፈር እንደሌለብን አሰተምረውን አለፉ. የኢትዬጵያ ጀግኖች መሀተቤን አልበጥሰም አሉ !በታሪክ የሰማነውን በኛ ዘመን ተደገመ በአይናችን አየነው.መድሃሂያሐም ይብቃችሁ በለን ቃል ከቤተ መቅደሰህ ይውጣ !ዲያቆን ዳኒ እሰኪ በወንጌሉ አፅናናን. መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜነ!
ReplyDeleteenersu aniget yesetuletin kiristina egna le menager lemin feranew? hodachew amlakachew emnetebis sile tekonenewa
ReplyDeleteእነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?
ReplyDeleteእዉነት ነው፡ እነሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው፡፡ መግለጫ የሚሰጡ አካላት በትክክል ሊገልፁት ይገባል፡፡
ReplyDeleteEwnet new lemen feran.
ReplyDeleteሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ስለእግዚአብሔርም ደማቸውን አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ
ReplyDeleteሞትን ታገሱ›› ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ
እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው???!!!
ደግሞም ስደተኛነታቸው ለአደጋው
ReplyDeleteምክንያት ሆነ እንጂ የተሠዉት በስደተኛነታቸው አይደለም፡፡ ስደተኞችም ሆነው እምነታቸውን ለመለወጥ ቢፈልጉ ኖሮ ይችሉ ነበር፡፡
የተሠዉት በክርስትናቸው ነው፡፡ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አንገታቸውን የሰጡት ለክርስቶስ ነው፡፡ እንደ አግናጥዮስ ምጥው
ለአንበሳ አነጋገር ‹እንደ ንጹሕ መገበሪያ ስንዴ ሆነው› ለአምላካቸው ነው በመሥዋዕትነት የቀረቡት፡፡
እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና
እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?
ewnt alk leg yzhalme gaze dablow ytsnawetw bnkaezw ynagaral ynzhen legwec sedetach kementach gar slhonw egezabher amelak lansw ysmatatnt keber satachw wa!!wa!! leza leza!! ewentwen snawk ytsatann ader ttan lmenkabatrew egzew maharani crestos!!!
ReplyDeleteqale hiwet yasemalin
ReplyDeleteእነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው? This is also my question.
ReplyDeleteEwnet gin lemen lemenager feran?
ReplyDeleteኢትዮጵያ ትልቅ ናት መከራውም ትልቅ ነው
ReplyDelete“ከማኅተባችሁ መበጠስ የአንገታችሁ መበጠስ የቀለላችሁ የክርስቶስ ሙሽሮች”
ከግብጽ ቀጥሎ ጵጵስናን የተቀበለች ሀገር ሰማዕትነትን በእነዚህ ሰላሳ ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን ተቀበለች፡፡ይህ እድል _ብንፈልገውም አናገኘውም ምክኒያቱም መመረጥ ያስፈልጋል፡፡ ሰማዕት መሆን ታላቅ ክብር ነው፡፡ ክርስቶስ ስለመረጣቸው ሰማዕት ሆኑ፡፡ሰማዕትነታችው ጥርጥር የለውም ምክኒያቱም ስለክርስቶስ ሞተዋልና ክርስቶስ ያለፈ ኃጢያታቸውን በአንዲቷ ቀን መስዋዕት ክብርን ይሰጣቸዋል ስለሰሙ ሞተዋልና ታድለናል በህይወታችን በታሪክ የምናቀውን ሰማዕትነት በዓይናችን ስለእምነታችውና ስለክርሰትናቸው ሲሰዉ ማየት መታደል ነው፡፡ “
_ከማኅተባችሁ _መበጠስ _የአንገታችሁ _መበጠስ _የቀለላችሁ _የክርስቶስ _ሙሽሮች _ሆይ፡- ማኅተቤን_ _አጠበቃችሁት፣ከብራችሁ_አስከበራቸሁኝ፣አንገታችሁን_ደፍታቸሁ ቀና_አረጋችሁኝ ፣ስለክርስቶስ ሞታችሁ የሃይማኖቴን ትክክለኛት ለዓለም አስታወቃችሁልን፣ተንበርክካቸሁ አቆማችሁኝ፤ ምን ብላቸሁ እረካለሁ እ እ እ ፡፡ለእናንተ እኔ ባከብራችሁ ምን ሊረባችሁ እርሱ ክርስቶስ አክብሯችኋል፡፡ ስንቱ በተለያየ በሽታ ስም ሲሞት እናንተ ግን በክርስቶስ ስም ሞታችሁ……………
ባልቻ ስለሚ ባለው ልጅ ኢቢስ ላይ እህቶቹ ሲጠየቁ የአመት ፈቃድ ወስዶ ነው የሄደው ወንድሜ የሰባት ሺ ብር ደሞዝተኛ ኦቨር ታይም ከሰራ እስከ አስር ሺ ይከፈለዋል አለች፡፡ሁሉ አለው፣ የኢያሱ ደሞ ከ ከኳዋታር መቶ ነው መመለስ ስላለቸሃለ ወደ እንግሊዝ ለመሃድ ነበር ለዚሁም ለሁለቱም ዘጠና ሺ ብርታዋል…ታዲያ ይሄ ሁሉ እያላቸው እንዴት በበረሃ ለምን ሄዱ ልንል እንችላለን…. ክርስቶስ መርጧቸዋልና ጠራችው በ..ቃ..አ.. መረጣቸው ፈለጋቸው….
በመጨረሻም ለሲኖዶስ አባቶች ጥያቄ አለኝ እነዚህን ሰማዕታት ብላ ማወጅ እና ማረጋገጥ ማክበር የለባት ከማውገዝ ብቻ???? ከ ግብጽ እሰቲ እንማር
ከሰማዕታቱ ፅናት እና ክብር በረከት ይስጠን፡፡
Egziabher nefsachewn be Genet yanurelen. Bewnet hilinan yakoslal Egziabher yenagerlachwal engna sewech Ema ye kentu kentu nen.
ReplyDeleteደግሞም ስደተኛነታቸው ለአደጋው
ReplyDeleteምክንያት ሆነ እንጂ የተሠዉት በስደተኛነታቸው አይደለም፡፡ ስደተኞችም ሆነው እምነታቸውን ለመለወጥ ቢፈልጉ ኖሮ ይችሉ ነበር፡፡
የተሠዉት በክርስትናቸው ነው፡፡ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አንገታቸውን የሰጡት ለክርስቶስ ነው፡፡ እንደ አግናጥዮስ ምጥው
ለአንበሳ አነጋገር ‹እንደ ንጹሕ መገበሪያ ስንዴ ሆነው› ለአምላካቸው ነው በመሥዋዕትነት የቀረቡት፡፡
እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና
እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?
Daniel yalew neger tilikl new. yetaredut bekrstnachew enjo besdetegnanetachew aydelem. Haymantocahewn eko bikeyru metref ychlu neber. lene enezih wondmochachin kdusan semaet nachew. Bemitaredubet woym bemigedelubet seat andach enkua yefirhat woym yemedenaget smet aytaybachewm. ene betam yegeremegn yih new. Lik ende estifanos fit neber fitachew yemiyaberaw. Ewneten new. esti balchan, eyasunm hine lelochun eyiachew. minm firihat alneberebachewm. Fitachew betam new des yemilew. Amlak nefsachewn begent yanurln. Enesu jeginoch nachew. yezih zemen semaetat. Egziabiher talak new. Ye Ethiopia Amlak enezihn gfegnoch degmo yketachewal. ende tbiya new beninew yemitefut. Aremenewoch. Enes bewondmoche sematenet korchalehu. Amen!!!. Amlak Bdrun ykeflal.
ReplyDeleteKale Hiwot yasemalin.Kesemaitatu bereket yasatfen.Ergit new bezih alem ewunetin menager kebad hunual.Hulum kerasu astesaseb astegto menagerin metsafin new yemimertew.melkam belehal ehuye.bertalin.Lebego eyedekemik new.
ReplyDeleteEgziabher ke_semaetatu bereket ayinfegen. Endenesu besime Silasse yatsinan.
ReplyDelete