Tuesday, April 21, 2015

ቂርቆስ በኀዘን ማቅclick here for pdf
ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከፖኤቲክ ጃዝ አባላትና ከሌሎች የኪነ ጥበብ ሰዎች ጋር ወደ ቂርቆስ ሄጄ ነበር፡፡ ያቺ ሳቂታዋና ተጫዋቿ ቂርቆስ ኀዘን ወርሯታል፡፡ የቂርቆስን ልጆች አውቃቸዋለሁ፡፡ ማልታ፣ ግሪክ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ስዊዘርላንድ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ መሳቅ ነው፣ መጨዋት ነው፡፡ መቀለድ ነው፡፡ ችግር እነርሱ ጋር የለም፡፡ ካገኙ ተካፍለው ካጡ ተሳስቀው ያልፉታል፡፡ መተዛዘን፣ መረዳዳት፣ ነገር ማቅለል ማን ይችላቸዋል፡፡ እንግሊዝ ሀገር የደረሱት በመንገድ ያለቁትን የሚያስቡበት ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀን አላቸው፡፡
ከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ
ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱ
ይላሉ የማልታ ልጆች፡፡

ዛሬ ያ ሁሉ ሳቅና ጨዋታ በኀዘን ተቀይሯል፡፡ የልጆቻቸውን መሞት በቪዲዮ በተመለከቱ ወላጆች፣ ማንነታቸውን ከቪዲዮው ለመለየት አቅቷቸው በሰቀቀን ውስጥ በሚገኙ ወላጆች፣ የልጆቻቸውን መረጃ ፈልገው መልስ ባጡ ወላጆች ቂርቆስ ተሞልታለች፡፡ ትጠይቃለች፤ መልስ ግን አላገኘችም፡፡ እንዴት ያለው ትምህርት፣ እንዴት ያለው ጥበብ፣ እንዴት ያለው ብልሃት እንደሚያጽናናት እንጃ፡፡  
እኔ በልቅሶ ቤት ሄጄ ብዙም አላለቅስም፡፡ ዛሬ ግን አለቀስኩ፡፡ በተለይ የባልቻ እናት ‹ፍቅር እስከ መቃብር› እያሉ ሲያለቅሱ ስሰማ ዕንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ኢያሱና ባልቻ ሲበሉም፣ ሲጠጡም፣ ሲሄዱም፣ ሲቀመጡም የማይለያዩ አብሮ አደጎች ናቸው፡፡ ሲሰደዱም አብረው ነው የተሰደዱት፤ መሥዋዕት የሆኑትም አብረው ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹ፍቅር እስከ መቃብር› የሚሉት የባልቻ እናት፡፡ እናቱን ሊረዳ እንደሄደ፣ ድሮም በእምነቱ ቀልድ እንደማያውቅ፣ ብዙ ተስፋ ሰጥቷቸው እንደነበረ እያነሡ ያለቅሳሉ፡፡ ‹‹እኔ ሲሞት እንዳላየው ብሎ አንገቱን ዘንበል አደረገ››  ይላሉ፡፡
 አያሌ የከተማው ሕዝብ ለእግር መቆሚያ እስኪጠብ ድረስ ሠፈሩን አጨናንቆታል፡፡ ኡኡታ፣ እሪታ፣ ሰቆቃ፣ ቁጭት፣ ሰቀቀን፣ ይነበባል፡፡ የባልቻ እናት ከልጃቸው ሞት በላይ አሁንም በሊቢያ የሚገኙ ሌሎች ወገኖቻችን ያሳስቧቸዋል፡፡ ስለ እነርሱም ያለቅሳሉ፣ ይወዘወዛሉ፡፡ አይ ኢትዮጵያዊት እናት፡፡  

16 comments:

 1. WE ALL ETHIOPIANS CRY ALOT...especially ''orthodox'' may GOD help us.......ewnet fetari zem aylem but we have to PRAY alot with out hesitation

  ReplyDelete
 2. ዳኒ፡ ዕድሜ ለፌስ ቡክ አድራሻዉን ስለነገረኝ እኔም በጡዋት ሄጄ አልቅሼ ወጥቶልኝ ነዉ ሥራ የገባሁት፡ እኔን እንዲህ ያቃጠለኝ እናት ምን ትሆን አልኩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በጌታችን አዳራሽ ተሰብስበዉ ሲደሰቱ ከናፈቃቸዉ አባታቸዉ ጋር የሚሆኑትን በዓይነ ሕሊናዬ እየተመለከትኩ ቀናሁ፡ ድብልቅ ስሜት፡፡ ነፍስ ይማር አልልም ነፈሳቸዉ ተምሮአል፡፡ ለኛስ ምን አስበናል፡ትልቁ ጥያቄ፡፡

  ReplyDelete
 3. GETA HULUNM ENDWODED YADREG

  ReplyDelete
 4. እኔ ሲሞት እንዳላየው ብሎ አንገቱን ዘንበል አደረገ›› ይላሉ፡፡
  አያሌ የከተማው ሕዝብ ለእግር መቆሚያ እስኪጠብ ድረስ ሠፈሩን አጨናንቆታል፡፡ ኡኡታ፣ እሪታ፣ ሰቆቃ፣ ቁጭት፣ ሰቀቀን፣ ይነበባል፡፡ የባልቻ እናት ከልጃቸው ሞት በላይ አሁንም በሊቢያ የሚገኙ ሌሎች ወገኖቻችን ያሳስቧቸዋል፡፡ ስለ እነርሱም ያለቅሳሉ፣ ይወዘወዛሉ፡፡ አይ ኢትዮጵያዊት እናት፡፡

  ReplyDelete
 5. ለቅሶ ቤት ያለሁ ያህል ተሰማኝ፡፡ ባለሁበት ለቅሶውን ተጋራሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. የእምዬን አይን ላለማየት አንገቱን ዝንብል አደረገ! የእኔ አንገት ይደፋ ምናባቴ ልበል, አቤት እንዴት ያማል . እንግዲ ዲያቆን ዳኒ በተሰጠህ ዕወቀት በወንጌሉ አፅናናቸው አደራ! መድሃሂያለም ኢትዬጵያን ይጠብቅ አሜን!

  ReplyDelete
 7. ለዚህ መልሱ ዝም ነው በቃ ዝም ብሎ ማልቀስ የሊቢያን ነገር ሊቢያ የነበረ ያውቀዋል ግን ለዛሬ ኡፍፍፍፍ እያሉ እየተቃጠሉ ዝም እስቲ ሁላችንም ዝም እንበል፡፡አንገት ሲቀላ ፣ ጭንቅላት በጥይት ሲበተን እያየን በቃ ዝም ጭጭ ፀጥ እንበል ፤ አብረን በአንድነት ዝምምምም እንበል፡፡

  ReplyDelete
 8. Egiziabiher metsinanatun yistachew

  ReplyDelete
 9. lega egezabher ybarkh hedah hasnewn bmkafele yethiopian ent lekeso machy yekmal bleh new hulgezam bskeken blekso new ymetnorew legach blow ymenkebakb ayzwesh ymelat mer keswe eskeshmelat hulew shomet ksaw hon kegzabher ymeshom taf bzyet kule wledet amelak klegew amaled slasrtw klasmerechn abat!!egzow bkach balen legachcen ytkablewt smetatent lethiopians tnesa lenswm mtasabach honew mechew toweled ymzkerachw yaderglen ksmatw kedws gwergs gare smach szkara ynoral ysmat enatwech bertw egezabher ytnecu himanota alwetem lsetan algeberm blow smetent mkeble begzabher mmret now abatwech ykatacewn legwech tkablewt abate yant sera !! leb yalew leb yebel leza mechresaten men yowen endhew mengawen ytsatenn ader tlen lalawe mengest snagbedd wo!! lerase!!

  ReplyDelete
 10. They should leave or take out that idiot article out of their book. that is when we really trust them from now on. caution to Ethiopia, its people and government. Of course there has been enough cautions in Ethiopia's land too. This is just extra and serious caution for somebody caring for Ethipia.

  ReplyDelete
 11. Lekiso Lekiso Lekiso . . . . Lela minlarg hazenen yemigaraw enkuan wegen yelegn kegone lekiso Lekiso . . . Yaum yecherkos lijoch . . .

  ReplyDelete
 12. እኔ ያደኩት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ አካባቢ ነው፡፡ ስናድግ የቅ/ቂርቆስን ገድል እየሰማን ነው እናም ክርስቶስን መካድ አይሆንልንም፡፡

  ReplyDelete
 13. ይድረስ በሊቢያ ለታረዱ ወገኖቼ
  ምነው በበረሀው
  ወገን እንደሌለው
  አንገታችሁ ታርዶ
  ተመታችሁ አሉኝ በመአት በረዶ
  ምን ጨካኞች ናቸው አረመኔዎች
  ሰው አልላቸውም እነዚህን ፍጥረቶች
  እናንተስ አገኛችሁ ሰማእትነት
  አምላክ ሊያኖራችሁ በገነት
  አራጆች አለባቸው ወዩታ
  ነፍሳቸው የሚኖረው በእሳቱ ቦታ

  ReplyDelete
 14. አይ ኢትዮጵያዊት እናት!!!
  ‹‹የጀግና እናት አታለቅስም››!!!

  ReplyDelete
 15. Egziabher kesemeatat bereket yakaflen

  ReplyDelete