በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ
ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ
ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ
ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣
ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን
በወጉ መግለጥ ነው፡፡
ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን
ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት
ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ
ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡
የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?
ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ
በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው
ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን›
ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት
አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡
የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን
ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው
‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤
ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን
የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው
የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም
ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ
ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን
ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?
ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ
ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ
የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን
በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ
ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው
‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ
‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት
ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው?
አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና
በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ
ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም
ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?
ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ
የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም
በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም
ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን
ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው
ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት
ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡
እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡
አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ
ይማር› አንልም፡፡
አሜን በረከታቸዉ ይደርብን! ቀሪዎቹንም እ/ር ይድረስላቸዉ
ReplyDeleteአስመሳይነትና እበላ ባይነት የነገሰበት ትውልድ ያስነገሰ አረመኔ መንግስት
Deleteበረከታቸው እንዲያድርብን መመኘት መልካም ነው፡፡
የተሻለው ግን እንደ እነርሱ በክርስትናችን ልበ ሙሉ ሆነን እውነትን ተናግረን ሌባውን ሌባ ብለን የተበላሸው ይስተካከል ብለን በግልፅ መናገር ስንጀምር ብቻ ነው፡፡ ይህን አረመኔ መንግስት በቃህ ብለን በራሳችን ፍትህ ስናቆመውና ስንፈርድበት ነው፡፡ ዋጋ የሚገኘው በመመኘት ሳይሆን ሆኖ በመገኘት ብቻ ነው፡፡
ሳንጃው
We shall consider and sit as if we don't have leaders. We better pray.
ReplyDelete‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡ dani Be Ethiopiawian mehounu Betam yasazenal.
ReplyDeleteበረከታቸው ይደርብን
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ለኛም የአቅማችን ሰማዕትነት እግዚአብሔር ይስጠን
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ለኛም የአቅማችን ሰማዕትነት እግዚአብሔር ይስጠን
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ለኛም የአቅማችን ሰማዕትነት እግዚአብሔር ይስጠን
ReplyDeleteDear Dani,
ReplyDeleteMany thanks for your Article.I was unable to write a comment the moment i saw this post. I must take enough time to cry.......Anyways....GOD is always with us....will help us soon.
ቃለ ህይወት ያሰማልን ለኛም የአቅማችን ሰማዕትነት እግዚአብሔር ይስጠን
ReplyDeleteበሆነው ነገር እጅግ በጣም አዝኛለሁ በውነት ይሄ ጊዜ ከልባችን ወደ እግዚያብሄር ልንፀልይ የሚገባን ወቅት አመላካች ነው ....''እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስይማር› አንልም፡፡''
ReplyDeleteአሜን በረከታቸው ይደርብን
ReplyDeleteStatement by National Security Council Spokesperson Bernadette Meehan on Murders in Libya
ReplyDeleteThe White House
Office of the Press Secretary
For Immediate Release
The United States condemns in the strongest terms the brutal mass murder purportedly of Ethiopian Christians by ISIL-affiliated terrorists in Libya. We express our condolences to the families of the victims and our support to the Ethiopian government and people as they grieve for their fellow citizens. That these terrorists killed these men solely because of their faith lays bare the terrorists’ vicious, senseless brutality. This atrocity once again underscores the urgent need for a political resolution to the conflict in Libya to empower a unified Libyan rejection of terrorist groups.
Even as terrorists attempt through their unconscionable acts to sow discord among religious communities, we recall that people of various faiths have coexisted as neighbors for centuries in the Middle East and Africa. With the force of this shared history behind them, people across all faiths will remain united in the face of the terrorists’ barbarity. The United States stands with them. While these dehumanizing acts of terror aim to test the world’s resolve – as groups throughout history have – none have the power to vanquish the powerful core of moral decency which binds humanity and which will ultimately prove the terrorists’ undoing.
Source: The White House
I wish this statement comes from 'OUR' government
What national security council?
DeleteThe so called council
Arab affiliate council. Down with woyane collection
FUCK OFF
Amen bereketachew yiderbin
ReplyDeleteDaniel,
ReplyDeleteThank you for your comments which questioned our political and religious leaders at the time of crisis. To be human is enough to express the outrageous and evil act of ISIS. I also expect the Muslim leaders to come out and condemn this atrocities and show their solidarities with the rest of Ethiopians.
Again, we very much appreciated your timely and honest observation, and our fathers say "Eyehadga Lehager Zenbele Ahado Hare Bahtita"
Haileluel
Oh amlake ere minteshalen? Erigit New yenesu hasab Ethiopian yenesu gizat mareg New be 5 amet wust !
ReplyDeleteEre gobez berititen entseliy ere min teshalen?
Dn Daniel egzaber yakibirilin
Amen Bereketachew yidiresen
Yamal Betam Yamal
ReplyDeleteYamal Betam Yamal
ReplyDeleteAbetu yehonebinin asib!!!
ReplyDeleteበረከታቸው ይደርብን !!
ReplyDelete‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡
ReplyDeleteAmen bereketachw yideribin
ReplyDeleteAmen Bereketachew yederbin !
ReplyDeleteWhat inhuman act it is. I think they read Koran, the book where Muslim brothers bases on. Which part of the book leads them to act inhumanly.
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ የምትጽፋቸውን ጽሁፎች በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ አነባቸዋለሁ፡፡ ሌሎችም እንደዚህ የሚያሳዝኑ ነገሮች ነበሩ ይህኛው ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ከልቤ በጣም አዝኛለሁ፡፡ የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደርብን፡፡ የትምወርቅ
ReplyDeleteአብዮታዊ ዲሞክራሲ አራማጅ ማለት እኮ የሰይጣን ባሪያና አገልጋይ ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteለመሆኑ እዚህ ሀገር መንግስት አለ እንዴ?
በውስጡ የተሰገሰገው የሆዳም ስብስብ አይደል እንዴ? የሲአይኤ ተላላኪ አይደል እንዴ?
አንድ እውነታ ሳስብ ግን ደስ እሰኛለሁ፡፡ ከጎን የነፈሰው የነፋስ ሽውታ መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፍታ የሚለው የአባባ ከበደ ሚካዔል ስንኝ
ኢትዮጵያ ላይ የበቀለውንና አሁን ግን ከስሩ ሊቆረጥ የደረሰው የአይሲስ ተባባሪ፡ የወንበዴና የባንዳን ስብስብ መንግስት ነኝ ባይ ሊመነገል ቀኑ ደርሳEል፡፡ ለዚች ሀገር ድንበርና ለህዝባE የሚያስብ ደገኛ አስተዳደር ይመጣል፡፡
ወያኔ አይኑ ይጥፋ
አሜን በረከታቸው ይደርብን
ReplyDeleteአሜን በረከታቸው ይደርብን
ReplyDeleteEgeziyabehere libona yesetene wedete eyamerane endehone alawekeme Egeziyabehere yetadegene.
ReplyDeleteEGEZIYABEHERE LIBONA YISTENE WEDETE EYAMERANE ENDEHONEM AYETAWEKE EGEZIYABEHERE ETHIOPIAN YETADEGATE.
ReplyDeleteEdihinew metamen yihenew haimanot
ReplyDeleteአይሰስ የተባለን መንጋ ከምድረ-ገፅ ማጥፋት ጥሩ ነው። በታላቁና በገናና አፄ ዘርዓያቆብ ጊዜ ምን ያህል የኛ አገር እንዴት አንቀጥቃጭ እንደነበረች ከዚህ በውጭ አገር መነኩሴ የገጠመኝ ዘገባ መገንዘብ ይቻላል። ከዛም አፄ ዘርዓያቆብን ደንበኛ መጥፎ ሰው ተደርጎ የሚነገርበትን ካሁኑ ዘመነ ትግሬ/ዘመነ ዓረብ ዘመን ጋር እናስተያየው። አድሃኖም ያረብነት ካባ ለብሶ ሲገልፍጥ ተመልከቱት http://www.geezonline.org/2013/11/ethiopias-foreign-relations-then-and-now.html
ReplyDeleteThank you. In the near future everything will be cleared.
DeleteAmen bereketachew yideribin
ReplyDeleteWhat do you expect from Redwan Hussien? He is one of them. Who knows what Redwan Hussien's and his friends agenda for Ethiopia is ? Personally I am disappointed to hear that someone who has the same faith as the killers is speaking on behalf of Ethiopia. May God bless Ethiopia
ReplyDeleteIn the name of all Fellow Ethiopians who stand for Human right respect, for peaceful coexisting around the world, for human life dignity & respect for freedom of faith what we are forced to witness from Libya, South Africa & Yemen on our innocent fellow Ethiopians massacre over the past week was a disgrace & unimaginable. These coward so called terrorists they achieve nothing they might kill innocent civilians hiding their face behind their mask they are cowards who can't fight in the open
ReplyDeleteAmen
ReplyDeleteAmen berketachew yidresen
ReplyDeleteThat's true, Berketachew yiderben
ReplyDeleteAmen Bereketachew Yideribin
ReplyDeleteእውነት የሀዘን ቀን ነው.በኢትዮጵያ ቲቪ ዘፈን ይዘፈናል ይገርማል. ዘማሪ ሀብታሙ ሽብሩ የሀዘን ቀን ዛሬ ነው የጨለማ ቀን ዛሬ ነው ብሎ ለመለስ ዜናዊ ዘመረ ለዚህ ሁሉ መከራ ለአበቃት ሰው. በውነት ዛሬ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ወጥቶ ደረቱን መድቃት እያለበት የጨለማ ቀን ዛሬ ነው የሀዘን ቀን ዛሬ ነው.የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ደወል መደወል ያለበት ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ብአንድ ላይ እግዚኦ ማለት አለብን። ያ የረገጥነውን ባንዲራችንን አንስተን ኡ ኡ ኡ የአምላክ ያለህ ብለን መጮህ ያለብን። እነዚህ ሰማእታት ለኛ እኮ እንደ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮሶች ናቸው.ወደፉት የነዚህ ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮሶች ሀውልት የግፈኛው አቡነ ጳውሎስ ሀውልት ፈርሶ የነዚህ ሰማእታት ሀውልት መተካት አለበት ለሀገራቸው ለሀይማኖታቸው የሞቱ ጀግኖች ናቸው። አንጀቴ ግን ተቃጠለላቸው እግዚአብሔር ሁሉን ይመልከት
ReplyDeleteአስመሳይነትና እበላ ባይነት የነገሰበት ትውልድ
Deleteእግዚአብሔር ሁሉን ይመልከት
ReplyDeleteእውነት የሀዘን ቀን ነው.በኢትዮጵያ ቲቪ ዘፈን ይዘፈናል ይገርማል. ዘማሪ ሀብታሙ ሽብሩ የሀዘን ቀን ዛሬ ነው የጨለማ ቀን ዛሬ ነው ብሎ ለመለስ ዜናዊ ዘመረ ለዚህ ሁሉ መከራ ለአበቃት ሰው. በውነት ዛሬ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ወጥቶ ደረቱን መድቃት እያለበት የጨለማ ቀን ዛሬ ነው የሀዘን ቀን ዛሬ ነው.የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ደወል መደወል ያለበት ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ብአንድ ላይ እግዚኦ ማለት አለብን። ያ የረገጥነውን ባንዲራችንን አንስተን ኡ ኡ ኡ የአምላክ ያለህ ብለን መጮህ ያለብን። እነዚህ ሰማእታት ለኛ እኮ እንደ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮሶች ናቸው.ወደፉት የነዚህ ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮሶች ሀውልት የግፈኛው አቡነ ጳውሎስ ሀውልት ፈርሶ የነዚህ ሰማእታት ሀውልት መተካት አለበት ለሀገራቸው ለሀይማኖታቸው የሞቱ ጀግኖች ናቸው። አንጀቴ ግን ተቃጠለላቸው እግዚአብሔር ሁሉን ይመልከት
ReplyDelete‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡ቀሪዎቹንም የኢትዮጵያ መንግስት ሳይሆን የኢትዮጵያ አምላክ ይታደግልን።
ReplyDeleteሰማዕታተ ሊቢያ በጸሎታችሁ አስቡን፤ አሜን፡፡
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ የምትጽፋቸውን ጽሁፎች በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ አነባቸዋለሁ፡፡ ሌሎችም እንደዚህ የሚያሳዝኑ ነገሮች ነበሩ ይህኛው ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ከልቤ በጣም አዝኛለሁ፡፡ የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደርብን፡፡ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አራማጅ ማለት እኮ የሰይጣን ባሪያና አገልጋይ ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteለመሆኑ እዚህ ሀገር መንግስት አለ እንዴ?
በውስጡ የተሰገሰገው የሆዳም ስብስብ አይደል እንዴ? የሲአይኤ ተላላኪ አይደል እንዴ?
አንድ እውነታ ሳስብ ግን ደስ እሰኛለሁ፡፡ ከጎን የነፈሰው የነፋስ ሽውታ መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፍታ የሚለው የአባባ ከበደ ሚካዔል ስንኝ
ኢትዮጵያ ላይ የበቀለውንና አሁን ግን ከስሩ ሊቆረጥ የደረሰው የአይሲስ ተባባሪ፡ የወንበዴና የባንዳን ስብስብ መንግስት ነኝ ባይ ሊመነገል ቀኑ ደርሳEል፡፡ ለዚች ሀገር ድንበርና ለህዝባE የሚያስብ ደገኛ አስተዳደር ይመጣል፡፡
ወያኔ አይኑ ይጥፋ
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡
ReplyDeleteሌላ ምን አይነት ቃላት ይህንን ድርጊት ይገልፀዋል ወጐኖቼ
AMEN. MAY THEIR PRAYERS AND BLESSINGS BE WITH US ALL. WE ARE SO PROUD OF THEM
ReplyDeleteAMEN!
ReplyDelete@ Daniel kibret,
ReplyDeleteyou criticise the Holy Synod Fathers as if they haven't felt any sorrow by the horrefic tragedy,by saying, "Some Archbishops are abroad,at this time they should have come back,if not they should have done a Prayer Service for our fellow Ethiopian Christian who have been brutally slaughtered" but They have done what they have to do as a Father!Here is the evidence.
A Special Prayer service was led by Archbishops,His Grace Abune Gebriel and His Grace Abune Kewistos,on Monday(April 20,2015)
Here is the video of the Special Prayer Service that was held at Re'ese Adbarat St Mary of Debre Tsion,London,NW Europe Diocese of EOTC, on Monday(April 20,2015)in memory of our fellow Ethiopians who have been brutally murdered and massacred by ISIS in Libya,Yemen and the victims of xenophobia in South Africa.
https://youtu.be/Ls2MhLp4j2w
https://youtu.be/tjJRHijiXd4
May the Lord God rest their soul in the bosom of our Holy fathers,Abraham,Isaac and Jacob.
May God,the Ultimate Master give courage and strength to their families and communities in this difficult time.
ወዳጄ የሃይማት አባቶችና የሃይማኖት መሪዎች ይለይ እንጂ፡፤ የሃይማኖት መሪዎች የሚባሉት በእመነቱ ቁንጮ ላይ ያሉት ናቸው፡፡ ፓትርያርኩ፣ የእስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ፣ የካቶሊኩ ካርዲናልና ሌሎች፡፡ አሁን የጠቀስሻቸው የሃይማኖት አባቶች ነው የሚባሉት፡፡ ወዴት ወዴት
Deleteዲያቆን ዳንኤል ስንት ቀን ሙሉ ሣስበውና ስነጋገርበት የነበረውን ነገር ነው የፃፍከው፡፡ የልቤን አደረስከው፣ እኛ ለማን እንናገር በምን እንተንፍስ፡፡ እግዚአብሔር እድሜ፣ ጤናና የሰው መውደድን አብዝቶ ይስጥህ፡፡ ይሄ ፖለቲካ ነው ወንድሞቻችንን ከአገር አስወጥቶ ለስቃይ የዳረጋቸው፡፡ ያለምንም ልፋት በሙስና አገርን በመበዝበዝ የሚከብሩ ፖለቲከኞችና የነሱ አጨብጫቢዎች ባሉበት አገር ወጣቱ ሰርቶ ማግኘትን እንዴት ተስፋ ያድርግ፡፡ የሚገርመው የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች እምነታቸው የዘቀጠ መሆኑን በተለያየ ጊዜ ማየታችን ነው፡፡ እኛ የምንጮኸው ወደ እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ ይሰማል፡፡ ከእርሱ መፍትሄን እንጠብቃለን፡፡
ReplyDeleteበረከታቸው ይደርብን፤ ዲ/ን ዳንኤል አንተም ከአስመሳይነት ተመልሰህ እንደዚህ እውነት በመናገርህ እናመሰግንሃለን። እውነት አርነት ያወጣችኃል ብሎናል እኮ ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ።
ReplyDeleteእነደው በዚህ አጋጣሚ አንድ ነገር ጠቆም ለማድረግ እውዳለው የሃገራችን መሪዎች ምን እንበላቸው እንደው ብቻ ዝም ነው እግዚአብሔር አምላክ ጽዋው የሞላ ቀን አይቀርላቸውም በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም አይደል የሚባለው? ሌላው ምልከታዬ በዚህ በአይ ሲስ አረመኔያዊ ግድያ የተሰውት ሰማዕታት ደማቸው ይጣራል በሃገራችን ያሉት የእስልምና ተከታዮች እውን ይህ ነገር አሳዝኗቸዋል እንዴ? ሃዘናቸውን ሲገልጹ፣ ድርጊቱንም ሲያወግዙ አልሰማንም ምናልባት ነገም እኮ ጊዜውን እና ቦታው ቢመቻቸው በሃገራችን እንዲህ አይነት እልቂት ሊያደርጉብ እንደማይችሉ ምን ማረጋገጫ አለን እነዚህም እኮ የአምላካቸውን ስም ጠርተው ነው እንዲህ ዓይነት የእንሰሳ ተግባር የፈጸሙት፤ ስለዚህ የነገው ያስፈራኛል ምክንያት አለኝ እንዲህ ያልኩበት
እነዚህ ሰማዕታት ዓለም ስላያቸው ነው በተለያዩ ማኅበራዊ መድረኮች ትላልቅ የዜና አውታሮች ብሎም በዓለማችን ትላልቅ የሚባሉት ሃገሮች ድርጊቱን በአደባባይ ወጥተው በማውገዛቸው ነገሩ ከፍ ተብሎ ሊታይ ብቅቷል (የሃገራችን መሪዎች ነን ባዮች ምንም ባይናገሩም) በጣም ስለዘገዩ የተናገሩ ያህል አይቆጠርም እንደኔ አስተያየት። ስለዚህ እኒህን ሰማዕታት ዓለም ተመልክቷል በየ ቴሌቪዥኑ መስኮት ወይንም በኮሚፒውተር መስኮት የሃገራችን እስምና ተከታይ መሪዎች ይህንን ኢሰብዓዊ ድርጊት የፈጸሙትን እነሱን በሃይማኖት የሚመስሏቸውን ሰዎች ሲያወግዙ አልተሰሙም፥ ቢያወግዙም አይገርመኝም በአደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸውን ቢገልፁም አይገርመኝም። የዛሬ ስድስት ዓመት አካባቢ ይመስለኛል በሻሾ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጂማ ዞን ክራችንን አንበጥስም ያሉ ካህናት እና ምዕመናን ሰማዕታት እኮ ደማቸው አይረሳም፥ በዛ አስከፊ ሰዓት የተናገረ የእስልምና መሪም ሆነ አማኝ አልሰማሁም የእስልምና መሪዎች ነን ብለው በአውሮፖ እና በአሜሪካ የሚኖሩት ሁሉ ድርጊቱን ሲያወግዙ አልተሰሙም ለምን? እንዲህ ዓይነት እምነት የለንም እስልምና ሰላም ነው ካሉ በዚያ ጊዜ የተሰዉትን ሰማዕታት ለምን በዝምታ አለፉ፣ ያው የነሱው እምነት ተከታዮች የእነሱን አምላክ ስም ጠርተው ልክ እንደ አሁኖቹ አይ ሲስ አንገታቸው ቀልተው ነው የተሰዉት ልዩነቱ በዚያን ወቅት የሃገራችንም ዜና ሰዓት ብቻ ነው በትክክል የሚናገረው በመሆኑም ምንም ነገር ሳይናገር ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት አባቶች በአግባቡ ጸሎት ሳያስደርጉ አለፈ ምናልባት እና አቡነ እስጢፋኖስ ሃገረ ስብከታቸው በመሆኑ በወቅቱ በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሲያስጸልዩ
አስታውሳለሁ ከዛ ውጪ በሌላ ቦታ ሲጸለይላቸውም አልሰማሁም ቤተክርስቲያንም የጸሎት ጊዜ አላወጀችም ለዚያውም ተወልደው በተከበሩበት ቀዬ በአክራሪዎች ቢላ ሲሰዉ መንግስትም ዝም ሕዝበ ክርስቲያኑም ዝም፣ የእስልምና ተወካዮችም ዝም የእነዚህ እንኳን የአላማ አንድነት ስላላቸው ሊሆን ይችላል ነውም እንጂ የእኛው ጠማማ ግን እግዚአብሔር በደላችንን ይቁጠርልን ይሄ ጽዋ ግን መሙላቱ አይቀርም እና ከወዲሁ አድርባዮች ቢያስቡበት ይሻላል እላለሁ አንድ ነገር ማለት በፈለኩ ነበር ነገር ግን በሌላ ጊዜ ብመለስ ይሻላል ለዛሬው የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደርብን አሜን።
ከሳሪስ ነኝ
Mr Daniel, I can't put it any better than that. The true statement i have ever seen ... "God bless Ethiopia" Many thanks
ReplyDeleteBereketachew yderbgnal
ReplyDeleteYekidusan Amelak Nebesachewun ,Keabereha Yesake,Yakob endihun kesemaetu Kidus Geiorgies, Kesematu Etstiphanos end Kesematu Aresema kidise ga yasarifilegn metadele new bezi balekebete zemen lesega ssyisasu enziayane yemeselu. Etsanate Angeten Enje Mesekele lebila altstem Bilewu. Le Amelakachew Bealem mederek sebeku. Cheru Feteriachine Yerhele enba yabese ye Ethiopia lijochine enba yabisele Enbachine kesemaye semayati yiderese. Demache ke Libeya mider Tichuy Egziabehe yizegeyale enji yimetale ena man Yawukal leneba chew , Le chrisetena emenatachewu enduhu Le hagerachi Ethiopia yetesewu " SEMAETATE" Nache Berketachi Yideriben.Bedemache yekoshesewu Maninetachinene Atibe Tensa Ethiopian Yasayen. Dn Danie kale Hiwot yasemalen
ReplyDeleteSEMAETATE nachew!!!
ReplyDelete