Tuesday, April 21, 2015

የሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ታወጀየኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ባወጣው ባለ ዘጠኝ ዐንቀጽ መግለጫ ለሰማዕታቱ ተገቢውን ቀኖናዊ ክብር እንደሚሰጥ ገልጧል፡፡ ለዚህም የሰማዕታቱን ቤተሰቦች የመረጃ ትብብር ጠይቋል፡፡ ‹‹የጀግና እናት አታለቅስም›› ያለው መግለጫው የሰማዕታቱ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ሰማዕትነት በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ስላለው በዚህ እንዲጽናኑ አደራ ብሏል፡፡ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ከመንግሥት ጋር አብሮ የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ እንደሚያቋቁምም ገልጧል፡፡
መግለጫውን ቀጥሎ ያንብቡት


በተያያዘ ዜና ዛሬ ከሰዓት ዐሥር ሰዓት ላይ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ ሰማዕታቱ ቤተሰቦች በመሄድ ጸሎት እንደሚያደርጉና እንደሚያጽናኑ ተነግሯል፡፡  


ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ ሲሠራ ‹ሲኖዶስ ሲኖዶስ› ይላል፡፡

6 comments:

 1. አሃ ማንነታቸው ስለተረጋገጠ እንዴ ምህላ የተወሰነው?
  ምነዋ ለማሊ ሃገር በቅድስት ስላሴ ካትድራል ለኢቦላ ስጋት ማስወገጃ በአምባሳደሩ ጥያቄ ፀሎት ሲደረግ ማንነታቸውን አውቀው ነበር?
  ማሊ ማለት እኮ እስላም የበዛበት ነው እኮ፡፡ ክርስትና ግን ቀኝህን ለሚመታ ግራህን ስጥ ትላለች ለዛም ነበር ፀሎቱ የተደረገው
  ዛሬ ነው እንዲህ የምታስቡት ያውም ደግሞ ከአረመኔ መንግስት ጋር በመተባበር፡ አረመኔ መንግስት ስለ ክርስትና ምን አገባው ምን ያውቃል፡፡ ክርስትና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሰረተ እንጂ በአረመኔዎች የስለላ መዋቅር የተዋደደ አይደለም፡፡ የሲኖዶስ አባላት ምዕመኑን ያዙ እንጂ የአረመኔዎችን ይሁንታ አትጠብቁ፡፡
  በቁጣ የነደደውን የህዝብ ቁጣ ለማብረድ፡፡ የዛሬው ጩኸት ምንም እንካን ከህዝብ ወጥቶ ህዝቡን እንደ አይሲስ በሚበላ አውሬ የወታደር ሆዳም እንዳይሳካ ቢደረግም በሃሙሱ የህዝብ ጩኸት ላይ እንገኛኝ
  እግዚአብሄር እንደ ሰው አይደለም፤ አይዘበትበትም፡ ስለሲኒዶስ ማንም ሊነግረው አይሻም
  ብሎገር ዳንኤል ሚዛን ደፋም አልደፋ መረጃ ማቀበልህ አይከፋም፡፡ ግን ለመኮነንም ለማመስገንም አትቸኩል፡ ዙሪያ ገባውን አጢን
  OFF COURSE IT’S GOOD TO BE CRITIC
  ሳንጃው

  ReplyDelete
 2. አንገታችንን ደፉን!መድሃሂያለም ቀና አድርገን.ምን ልበል ለእናቶቼ እንዴት ልግለፅ አዘኔን? ምን ዓይነት ቃል እንጠቀም? እመብርሀን አንቺው አረጋጊያቸው.በቃ በይን

  ReplyDelete
 3. Jesus Christ is Lord. John 3:16

   For God so loved the world that he gavehis one and only Son, that whoever believes in him shall not perish but have eternal life.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰው ሆኖ ከመፈጠር በፊት የሚቀድም ምን አለ? ሃይማኖት ነው፣ ቋንቋ ነው፣ ጎሣ ነው ወይስ ምንድንነው?

   እኔ እንደተረዳሁት ፈጣሪ በቅድሚያ ሰውን ፈጠረ ከዛም ለሰው ልጅ መተዳደሪያ ህግ ወይም ትእዛዝ ሰጠው። በመሆኑም አዳምና ህይዋን ከተፈጠሩ በሁዋላ እጸበለስን አትብሉ ወይም በሙሴ ህግ ደግሞ አትስረቅ፣ አትግደል፣ አትዋሽ፣ እናትህንና አባትህን አክብር ወዘተ የሚለው ትእዛዝ ሰጠው። ጎሣና ብሔር፣ ባህልና ቋንቋ ከመፈጠራቸው ወይም ከመስፋፋታቸውና ከመከፋፈላቸው፣ አሁን በዓለማችን የሚገኙት የሃይማኖት ድርጅቶች ከመከሰታቸው በፊት የሰው ልጅ በዚህች ምድር አስቀድሞ ነበር።

   ስለዚህ ከሁሉም በፊት የሰውን ልጅ በሰውነቱ እንጂ በዘሩ፣ በቋንቋው በሃይማኖቱ ወይም በአመለካከቱ ወይም በሌላ መንገድ መመዘን አይገባንም። ይህን ካደረግን ግን ያሳስተናል። ሰብአዊነትን ወደጎን ትተን አንዱን ጫፍ ይዘን ካከረርን ISIS የሚባሉት የእስላም አክራሪዎች በሊቢያ በሚገኙ በዜጎቻችን ላይ እንደፈፅሙት አይነት አሰቃቂ እልቂት ይከሰታል።

   ተጨባጭ ምሳሌ ለመስጠት ያህል በህውሃት የሚመራው የኢህአዲግ መንግሥት በጎሳ ላይ የተመሠረተ መንግሥት በሃገራችን ከመሠረተ በሁዋላ በአንድ ወቅት ሟቹ ጠ/ሚ የአአ ዩኒቨርስቲ መምህራንን ሰብስበው በጎሳ ላይ የመሠረቱት ፌዴራል መንግሥት የሃገራችችንን ችግር እንደሚፈታ ሲያብራሩ አንድ ወጣት ምሁር ሃሳባቸውን በመቃወም እናንተ የዘርን ጉዳይ እንዳከረራችሁ ሌላው ደግሞ የሃይማኖት ወይም የሌላ ችግርን አክሮ ጫፍ በማድረስ በሃገራችን ብጥብጥ ሊያስነሳ ይችላል በማለት በለሰለሰ አንደበት ለጠ/ሚኒስትሩ መግለፁን አስታውሳለሁ።

   አንድን ነገር መዞ በማውጣትና በማጋነን ወይም በማካበድ የተወሰኑ ሰዎችን በማነሳሳት ጥቂቶች ብዙሃኑን ሊያተራምሱ ይችላሉ። በዚህ የአንድን ነገር ጫፍ ይዞ ማክረር የተለከፉ ሰዎች በአርሲ፣ በሀረርና በሌሎች አካባቢዎች ካህናት ሳይቀሩ በርካቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገለዋል። በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ይኖሩ በነበሩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ ተወልደው ባደጉበት በሃገራቸው ላይ የደረሰባቸው ማንገላታት፣ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ እድሜልካቸው ያፈሩትን ንብረታቸውን ነጥቆ ማባረር በአጠቃላይ የተፈፀመባቸው ኢሰብአዊ ድርጊቶች ነገሮችን አጥቦ ከማየት ጠባብ የአስተሳሰብ ችግር የወለደው በሽታ ነው። እኔ ፓለቲከኛ ሳልሆን ለህሊናዬና ለእግዚአብሔር የምመሰክር በወሬ ሳይሆን ክፍለ ሃገር ሥሰራ ይህንን የመሳሰለ የድሃ ወገኖቼን እንግልት በአይኔ ያየሁ ህያው ምስክር ነኝ። በጋራ ሃገራችን በጋራ ተስማምተን መኖሩ ይሻለናል። ተስማምተን በመኖር ሃገራችንን ብናሳድግ ኖሮ ወንድሞቻችንም ነገ ያልፍልናል ብለው በረሃ ለበረሃ ሲንከራተቱ ሰብአዊነት በጎደላቸው አሸባሪዎች እጅ ወድቀው እንደከብት ባልታረዱ ነበር። የሚሰማ ይስማ።

   Delete
 4. Deacon Daniel Emebete Mariyam Tirdah, Kante gar tihun.

  ReplyDelete