Thursday, April 16, 2015

የሳይንቲስቱ ልጅ ጥያቄ

ባለፈው እሑድ፣ የትንሣኤ ዕለት ማልዳ ነው ከዕንቅልፏ የተነሣቺው፡፡ እናቷ ቤተ ክርስቲያን አድራ፣ አባቷ ደግሞ ሌሊት ከውጭ ሀገር ገብቶ ደክሟቸው እንደተኙ አልተነሡም፡፡ እርሷም በጠዋት የተነሣቺው ጓደኛዋ አደራ ስላለቻት ነው፡፡ ‹‹የቴሌቭዥን የትንሣኤ ፕሮግራም የተቀረጸው እኛ ቤት ነው›› ብላ አጓጉታታለቺ፡፡ የተነሣቺው ጓደኛዋን በቴሌቭዥን ለማየት ስትል ነው፡፡ ደግሞ ‹ዘፈን ምናምን አቅርቤያለሁ› ብላታለቺ፡፡ የጓደኛዋ አባት ‹ፍቅር እዚህም እዚያም›፣ ‹ትሄጅብኛለሽ› እና ‹ፍቅር በኪችን ውስጥ› የተሰኙ ሦስት አስቂኝ የፍቅር ፊልሞች ላይ የሠራ ‹ታዋቂ አርቲስት› ነው፡፡ ጓደኛዋ እንደነገረቻት ከሆነ የበዓሉ ፕሮግራም እነርሱ ቤት ሲቀረጽ የቀረ አርቲስት የለም፡፡ በዓሉ ራሱ ሕዝቡን ሊያዝናና ስለማይችል ‹ዘና እንዲያደርጉት› ተብሎ ቀልደኞቹ ሁሉ እነርሱ ቤት መጥተው ነበር፡፡ 

ከቀረፃው ማግሥት ጓደኛዋ ትምህርት ቤት ስትመጣ የታዋቂ አርቲስቶችን ፊርማ በየደብተሯ ሰብስባ መጥታ ጓደኞቿን ሁሉ ስታስቀናቸው ነበር፡፡ በርግጥ ክፍል ውስጥ እርሷና ጓደኞቿ ትምህርታቸውን ረስተው የአርቲስቶችን ፊርማ ሲያደንቁ ያዩዋቸው መምህራቸው እንደ መገሰጽ ቢያደርጉም፣ እንደመስማት ያላቸው ተማሪ ግን አልነበረም፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ታዋቂ አይደሉማ፡፡ ደግሞ መምህር ከመቼ ወዲህ ነው ታዋቂ የሚሆነው፡፡ ይኼው ስንቱ አርብቶ አደርና አርሶ አደር ሲሸለም መምህር መቼ ተሸልሞ ያውቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ብዙዎችን ተማሪዎች ያናደዳቸው ‹‹የዘፈነም፣ የተወነም፣ ፊልም የሠራም፣ ማስታወቂያ የሠራም አርቲስት አይባልም›› ያሉት ነገር ነው፡፡ ‹‹አርቲስት የሚለው ስም ለሰዓሊዎች የሚሰጥ ስም ነው፡፡  ያውም ስካልፕቸርና ፔይንቲንግ ለሚሠሩት ብቻ፡፡ እርሱም ቢሆን እንደ ደጃዝማችና ግራ አዝማች ማዕረግ ሳይሆን የሞያ መጠሪያ ነው፡፡ እስኪ አሁን አርቲስት ማይክል ጃክሰን፣ አርቲስት ቢዮንሴ ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ሰው ማዕረግ የሚያበዛው ስሙ ብቻውን ለመቆም ዐቅም ስለሚያጣ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቱ፡፡ ዳቪንቼ፣ ሼክስፒር፣ ሞዛርት፣ ፒካሶ የሚለው ስምኮ ብቻውን የሚቆም ነው፡፡ ዕዝል ቅጽል አያስፈልገውም፡፡›› ያሉትን ነገር ተማሪዎቻቸው ‹‹እርሳቸው ከቴሌቭዥን ሊበልጡ ነው እንዴ›› ብለው ሙድ ያዙባቸው፡፡
ለነገሩ እርሳቸውም አብዝተውታል፡፡ ‹አርሶ አደርና አርብቶ አደር፣ ሠልጣኝና የትራፊክ ፖሊስ፣ ታራሚና ፍርደኛ፣ ጋዜጠኛና ጎዳና ተዳዳሪ ማዕረግ ሆነው ከስም በፊት በሚቀጸሉባት ሀገር ‹አርቲስት› ማዕረግ አይደለም ብለው ተማሪን ማሸበር በአሸባሪነት የሚያስከስስ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ እንዲያውም ኢቲቪ ቢሰማቸው ‹በአሸባሪነት ሊያስከስስ ይገባል ሲሉ አንዳንድ የሕግ ምሁራን አስገነዘቡ› ብሎ ለዜና ጥብስ ያውላቸው ነበር፡፡
እርሷ ሶፋ ወንበር ላይ ተቀምጣ ይኼንን ሁሉ ስታስብ ጓደኛዋ በቴሌ ቭዥን ዘገየች፡፡ እስኪጀመር ድረስ ያቺ የ12 ዓመት የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ማሰቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹ቆይ ግን አባዬ ምንድን ነው? አንድም ቀንኮ በቴሌቭዥን ታይቶ አያውቅም፡፡ ይኼው ኤልዳና እንኳን ስንት ጊዜ በቲቪ ልትታዪ ነው፡፡ አባዬ ግን ዶክተር ምናምን ከሚሆን አርቲስት ቢሆን ነበር ጥሩ፡፡ እርሱ ዶክተር ሆኖ ምንም አልጠቀመንም፡፡ አንዴ አሜሪካ አንዴ ጃፓን፣ አንዴ ጀርመን ለወርክ ሾፕ መሮጥ ብቻ ነው፡፡ በርግጥ የኤልዳናም አባት ውጭ ይኼዳል፡፡ ግን እርሱ ሲሄድም ሲመጣም በሚዲያ ይነገርለታል፡፡ ሊሄድ ነው፣ እየሄደ ነው፣ ሊደርስ ነው፣ ደረሰ ይባልለታል፡፡ የኔን አባት መሄድና መምጣት ግን እኛና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ነን የምናውቀው፡፡
ደግሞ የኤልዳና አባት ውጭ ሲሄድ ሰው ይከበዋል፣ ጉርድ ቀሚስ ያደረጉ ሴቶች፣ ቁጥርጥር የተሠሩ ወንዶች፣ አጅበውት ፎቶ ይነሣሉ፡፡ የኔ አባት ግን ፎቶዎቹን ሁሉ ሳይ ወይ ከራሰ በራ ሰው ጋር ወይ ድክምክም ካሉ ሴቶች ጋር ነው የሚነሣው፡፡ ደግሞኮ የኤልዳና አባት ሁልጊዜ የአበባ ጉንጉን ሲቀበል ነው የሚታየው፡፡ የኔ አባት ግን ሯጭ ይመስል ሜዳልያ ሲቀበል ነው የምናየው፡፡ ኤልዳና ቪዲዮውን በስልኳ ስታሳየን ሰው ሁሉ ኡኡ እያለ አዳራሽ ውስጥ ለአባቷ ይጨፍርለታል፡፡ የኔ አባት ግን አንድ ጠረጴዛ ነገር አጠገብ ይቆማል፤ የሆነ ነገር በፓወር ፖይንት ያሳያል፤ አንድ ጊዜ ይጨበጨብለታል፡፡ በቃ፡፡ አንድም የሚጨፍር ሰው አይታይም፡፡ አባዬ ግን ምንድን ነው?
ቆይ ግን እኛ ቤት ኢቲቪዎች የማይመጡት ለምንድን ነው? አባቴ አርቲስት ስላልሆነ ነው አይደል፡፡ የኔ አባትኮ እንኳን ለፋሲካ ለአርሂቡ ቀርቦ አያውቅም፡፡ እውነታቸው ነው፡፡ በአርሂቡኮ አርቲስቶች ሲቀርቡ ‹እንትናዬ አድናቂህ ነኝ፣ እወድሃለሁ፤ ቀጣዩ አልበምህ መቼ ነው የሚወጣው? ምን ፊልም ልትሠራልን ነው?›› የሚል ሰው ይደውልላቸዋል፡፡ አሁን አባዬ አርሂቡ ላይ ቢቀርብ ምን ሊባል ነው? ምን ተብሎ ሊጠየቅ ነው? ደግሞ ማንም አድናቂ አያገኝም፡፡ አልበም የለው፤ ፊልም የለው፣ ሰዎች በምን ያውቁታል፡፡
አባዬ ግን አርቲስት መሆን ነበረበት፡፡ ዶክተርነት ምን ያደርግለታል፡፡ አርቲስት ቢሆን ኖሮ በኋላ ሲያረጅ ‹የክብር ዶክትሬት› ተብሎ ይሰጠው ነበር፡፡ ‹የክብር አርቲስት› ብሎ ግን ማንም አሁን አይሰጠውም፡፡ ዶክተርነት ይደረስበታል፡፡ አርቲስትነት ግን አይደረስበትም፡፡ እንዲያውም እነርሱ ሲጠሩ ‹ክቡር ዶክተር› ነው የሚባሉት የኔ አባት ግን ‹ዶክተር› ብቻ ነው፡፡
እርሷ ይህንን ስታወጣና ስታወርድ የቴሌቭዥኑ ፕሮግራም ጀመረ፡፡ ጋዜጠኛውም ‹እያዝናናን እናስተምራለን› ብሎ የጓደኛዋን ቤት አሳየ፡፡ ምንም እንኳን የተቀረጸው በጾም ጊዜ ቢሆን ዶሮው፣ በጉ፣ ክትፎው፣ ቅቤው፣ ዕንቁላሉ ይታያል፡፡ ለነገሩ እንደ ኢቲቪ አቆጣጠር ጾሙ አንድ ሳምንት ሲቀረው ያልቃል፡፡ ከዚያ በኋላ ቀረጻ ይቻላል፡፡ ጓደኛዋን አየቻት፡፡ ቤታቸው እየታየ ነው፡፡
እየሮጠች አባቷን ቀሰቀሰቺው፡፡
‹‹ጓደኛዬ በቴሌቭዥን እየታየች ነው›› ስትለው ድካሙ ባይለቀውም እርሷን ለማስደሰት ተነሥቶ ዓይኑን እያሸ ወደ ሳሎን መጣ፡፡ ‹እያት ኤልዳናን› አለቺው፡፡ ኤልዳና እየተጠየቀቺ ነው፡፡ ቃለ መጠይቁ ሲያልቅ ‹አባዬ አንተ መቼ ነው በቲቪ የምትቀርበው› አለቺው ልጁ፡፡
‹‹ሚዲያችን ከታዋቂ ይልቅ ለዐዋቂ ቦታ ሲኖረው›› አላት አባቷ፡፡
‹‹አንተ ግን ለምን ታዋቂ አልሆንክም››
‹‹ልጄ እኔኮ ታዋቂ ነኝ፡፡ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ግን አያውቁኝም፡፡ የቢቢሲ፣ የሲኤንኤን፣ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ያውቁኛል፡፡ እኔ አንድ ነገር ስለ ግብርና ከተናገርኩ ወይም ከጻፍኩ ያ ዜና ይሆናል፡፡ እዚህ አገር ግን ዕውቀት ዜና አይሆንም ልጄ፡፡ እዚህ ሀገር ዜና የሚሆነው ፖለቲካና ቀልድ ነው፡፡››
‹‹እሺ ለምን አርሂቡ ላይ አትቀርብም››
‹‹ያማ ጋዜጠኛውን ማሰቃየት ነው ልጄ››
‹‹ለምን ይሰቃያል?››
‹‹ምን ይጠይቀኛል? ጥናታዊ ጽሑፎቼን ማንበብ ሊኖርበት ነው፡፡ ምርምሮቼን መቃኘት ሊኖርበት ነው፡፡ ስለ እኔ የተሰጡ የሌሎች ሳይንቲስቶችን ምስክርነት ማገላበጥ ሊኖርበት ነው፡፡ ይሰቃያል ልጄ፡፡ ቀልድ የለመደን ሰው ዕውቀት ያሰቃየዋል፡፡በቀለላሉ የመጀመሪያ አልበምህ መቼ አወጣኸው? የመጀመሪያው ፊልምህ ምን ነበር? ገጠመኝህ ምንድን ነው? እያለ ሰዓቱን መሙላት ሲችል ምን በወጣው ሳይንቲስ አቅርቦ ይሰቃያል፡፡ ጋዜጠኞቹ መዘጋጀት ስለማይችሉም ስለማይፈልጉም አይደል እንዴ ‹እስኪ ራስሽን ለአድማጮች አስተዋውቂ› የሚሉሽ፡፡ ይኼኮ የጋዜጠኛው ሥራ ነበር፡፡ አንብቦ፣ ፕሮፋይል ሠርቶ ቢመጣ ኖሮ እንዲህ አይልም፡፡ ደግሞም አለቆቹም ላይወዱለት ይችላሉ፡፡ ዕውቀት የመለወጥ ኃይል አለው፡፡ ሕዝቡ ደግሞ እንዲዝናና እንጂ እንዲለወጥ አይፈለግም፡፡››
‹‹ተዪው እኔን፡፡ አንድ ገበሬ በዓል እንዴት ነው የሚያከብረው? ድንበር ላይ ባሉ ወታደሮች ዘንድ እንዴት ይከበራል? ተረኛ ሆነው ሆስፒታል ወይም እሳት አደጋ መከላከያ ውስጥ ባሉ ባለሞያዎች ዘንድ ፋሲካ ምን ዓይነት በዓል ነው? በዕለቱ አየር ላይ በሚሆኑ የአውሮፕላን አብራሪዎችና አስተናጋጆች፣ መርከብ ላይ በሚሠሩ ኢትዮጵያውያን፣ ሆስፒታል በተኙ ሕሙማን፣ በዓል እንዴት ይከበራል? የሚለውን እንኳን መች ያሳዩናል፡፡ ለምን ይመስልሻል?
‹‹እነርሱ ታድያ አርቲስት ናቸው እንዴ?››
››ልጄ የኑሮ አርቱማ ያለው እዚያ ውስጥ ነበር፡፡ የኛነታችንን ሌላ ገጽታ የምናየውማ እዚያ ውስጥ ነበር፡፡ ግን ይኼ ማሰብ ይጠይቃል፤ መመራመርን፣ ማንበብን፣ መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡ ማሰብ፣ ማንበብና መዘጋጀት ደግሞ እዚያ ቤት የሚወደዱ አይመስሉኝም››
‹‹እሺ ታድያ መቼ ነው የኛ ቤት በቴሌቭዥን የሚቀርበው?››
‹‹ወይ እኔ መቀለድ፣ ወይ እነርሱ ማወቅ ሲጀምሩ››
  

57 comments:

 1. Yes......., nice view as usual. keep it up!!!

  ReplyDelete
 2. ወደድኩት በቃ ወደድኩት
  ‹‹እሺ ታድያ መቼ ነው የኛ ቤት በቴሌቭዥን የሚቀርበው?››
  ‹‹ወይ እኔ መቀለድ፣ ወይ እነርሱ ማወቅ ሲጀምሩ››

  ReplyDelete
 3. Dn. Daniel anjetene new yareaskelegne. Tebarek Bro

  ReplyDelete
 4. የጋዜጠኞቻችንን ዓይነ ልቦና ወደ እውቀት ይመልስልን!

  ReplyDelete
 5. ዳኒእይታዎችህ ምርጥ ናቸው ግን ይሄ ከ ኢህአዲግ ጋር የምትሳፈጠው ነገር አሸባሪ አክራሪ ምናምን አስብሎህ አነዚህን የሚጣፍጡ ፅሁፎች እንዳናጣ

  ReplyDelete
 6. እኔኮ ታዋቂ ነኝ፡፡ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ግን አያውቁኝም፡፡ የቢቢሲ፣ የሲኤንኤን፣ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ያውቁኛል፡፡ እኔ አንድ ነገር ስለ ግብርና ከተናገርኩ ወይም ከጻፍኩ ያ ዜና ይሆናል፡፡ እዚህ አገር ግን ዕውቀት ዜና አይሆንም:: Long live Diacon Daniel

  ReplyDelete
 7. እኔኮ ታዋቂ ነኝ፡፡ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ግን አያውቁኝም፡፡ የቢቢሲ፣ የሲኤንኤን፣ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ያውቁኛል፡፡ እኔ አንድ ነገር ስለ ግብርና ከተናገርኩ ወይም ከጻፍኩ ያ ዜና ይሆናል፡፡ እዚህ አገር ግን ዕውቀት ዜና አይሆንም:: Long live Diacon Daniel

  ReplyDelete
 8. እኔኮ ታዋቂ ነኝ፡፡ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ግን አያውቁኝም፡፡ የቢቢሲ፣ የሲኤንኤን፣ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ያውቁኛል፡፡ እኔ አንድ ነገር ስለ ግብርና ከተናገርኩ ወይም ከጻፍኩ ያ ዜና ይሆናል፡፡ እዚህ አገር ግን ዕውቀት ዜና አይሆንም

  ReplyDelete
 9. በጣም የሚገርም ጽሁፍ ነው። ጨምሮ ጨማምሮ ጥበቡን ፈጣሪ ይስጥህ!!!
  "ማሰብ፣ ማንበብና መዘጋጀት ደግሞ እዚያ ቤት የሚወደዱ አይመስሉኝም››"

  ReplyDelete
 10. Ohh Dani

  You touched my heart. If you see most of ETV/EBC program, more than 75% are focused on 'Artist'. I am not hate artist, they are the valuable asset for the country. But we need Engineers, Doctors, lawyers, economist, soldiers,teachers, farmers, etc who are the corner stone for our country. The kids can learn a lot from these professionals, they use them as model.... By the way why not the private media start this? Any way Ant Chuh Chuh....

  ReplyDelete
 11. ዲያቆን ዳኒ እንኳን አደረሰህ ከነመላው ቤተሰብህ!ዕውቀቱን የሰጠህ እግዚሃብሔር ይመሰገን!ግሩም የሆነ እይታ! ትልቅ አሰተምሮ ያለውና ግሩም የሆነ መልዕክት ነው ያሰተላለፍክልን. ቢነበብ ቢነበብ የማይሰለች. ልብ ያለው ልብ ይበል ነው የሚባለው.ማወቅ, መሰማት ,ማድነቅ, ማየት,ያለብንን ሳናውቅ ጋዘጤኛዎቻችንና ኢቲቪ ጌዜዎን ሲያባክኑ ዘመናት አለፉ ጥሩ ጊዜ መጥቶ ይሔንን የምናይበት እነመኛለን ለታላቋ አገራችን. እኛም የድርሻችንን እናድርግ! የኢትዬጽያን ትንሳሔ ያሳየን አሜን.ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማህ መድሃሂያለም ጥበቡን ይጨምርልህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 12. Oh amilake E/R yisitih Dn. Daniel , when I was @ AAU one of our instractor told us this issues frequintly I hope he will read it " pls Dr. Husien kedir read it !"

  ReplyDelete
 13. ሰው ማዕረግ የሚያበዛው ስሙ ብቻውን ለመቆም ዐቅም ስለሚያጣ ነው፡፡ dink new Dn. dani. Tebarekilin.

  ReplyDelete
 14. Ewnthn naw dany
  I ETV mach naw kum nager emqarbaw
  la wadfet beyasbubat akrarbun beyastkakelut malkam naw.

  ReplyDelete
 15. menew alawakiwochen beeweket asekayehachew

  ReplyDelete
 16. ሰላም ዳንየ! በጣም የሚገርም እይታ ነው ተደስቼበታለሁ፡፡አሁን ይህንን አይቶ የሚከፋን እንኖራለን ነገር ግን ስንት ሂሶችን ስንውጥ እየዋልን ከዚህችም ትንሽ እንውሰድላት ታሽረናለች፡፡

  ReplyDelete
 17. እግዚአብሔር ይስጥህ ሁሌ አንጀቴ የሚያርበት ጉዳይ ነው።
  ‹‹ወይ እኔ መቀለድ፣ ወይ እነርሱ ማወቅ ሲጀምሩ››

  ReplyDelete
 18. ኡፍ . . . . አንጀቴን አራስከው! እድሜውን ከጤና ጋር ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥህ!

  ReplyDelete
 19. ሰው ማዕረግ የሚያበዛው ስሙ ብቻውን ለመቆም ዐቅም ስለሚያጣ ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. ሰው ከመሞቱ በፊት ሐውልት የሚያሠራው ከሞተ በኃላ እንደማይሠራለት ሲያውቅ ነው!

  ReplyDelete
 21. የጋዜጠኞቻችን ዓይነልቦና ወደ እውቀት ይመልስልን

  ReplyDelete
 22. የጋዜጠኞቻችን ዓይነልቦና ወደ እውቀት ይመልስልን

  ReplyDelete
 23. Really i am so so happy to read this article. thank you so much Dani. This article is one of those best ones!

  ReplyDelete
 24. Very Trueeeeeeeeeee

  ReplyDelete
 25. ‹‹ልጄ እኔኮ ታዋቂ ነኝ፡፡ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ግን አያውቁኝም፡፡ የቢቢሲ፣ የሲኤንኤን፣ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ያውቁኛል፡፡ እኔ አንድ ነገር ስለ ግብርና ከተናገርኩ ወይም ከጻፍኩ ያ ዜና ይሆናል፡፡ እዚህ አገር ግን ዕውቀት ዜና አይሆንም ልጄ፡፡ እዚህ ሀገር ዜና የሚሆነው ፖለቲካና ቀልድ ነው፡፡››

  ReplyDelete
 26. ‹‹እሺ ታድያ መቼ ነው የኛ ቤት በቴሌቭዥን የሚቀርበው?››
  ‹‹ወይ እኔ መቀለድ፣ ወይ እነርሱ ማወቅ ሲጀምሩ››

  ReplyDelete
 27. ማወቅ ወንጀል ሆኖማ ብዙዎች ያወቁ ኑሮዋቸው ከርቸሌ ከሆነ አመታት አስቆጠርን ፡ እኮ!

  ReplyDelete
 28. Good observation
  Thank you D/n Daneil

  ReplyDelete
 29. ሚዲያችን ከታዋቂ ይልቅ ለዐዋቂ ቦታ ሲኖረው

  ReplyDelete
 30. Ewnthn naw dany etv lay emqarbaw hebrtasabun la mastamarya sayhon hebrtasabun la mazenagn naw.
  gen ez lay tekurt madrg albat .median tataqeman ya hebrtasbun nuro malwat alben .

  ReplyDelete
 31. Very interesting. I agree with this scientist.

  ReplyDelete
 32. I am interested by this weeks post. I found it very educational if we are wise enough to understand it. And the point you mentioned about the teachers has touched me that teachers has never been given the right place in the society since the end of His Majesty Emperor Hailesilassie's regime. The media particularly focuses on frivolous, silly and trash comedy and waste of time rather than presenting important persons who can change the country and the world by their knowledge. Thank you Daniel! let us pray in order to get out of such darkness and ignorance. Because God enlightens us when we want to be changed, without our consent God does not help us.

  ReplyDelete
 33. lega ewnet tmagera abat llegw machme adametaw khone!!

  ReplyDelete
 34. በኤቤስ ተቪ ላይ የኩራዝ ቡና ቤት እንግዳ በሚል የሚጠይቃቸውን ሰዎች የስነፅሁፍ ስራዎችን፣የምርምር ፅሁፍቸውን፣ጆርናሎቻቸውን በደንብ አንብቦ ከሌሎች ፀኃፍት ጋር አንፃፅሮ ለነገሩ ልጁ /ጋዜጠኛው/ የማንበብ ልምድ እንዳለው ያስታውቃል በዙሁ መሰረት የሚቀርባቸው እግዶች እስኪገረሙ ድረስ ጥሩ ጥሩ ጥቄዎችን ያቀርባል እና ከእንደዚህ አይነት ወገኖች በጥቂቱ ብንማር፡፡

  ReplyDelete
 35. አሪፍ እይታ ነው በጣም ተመችቶኛል፡፡ እንዲህ ያለ ጠንከር ያለ ሀሳብ በመሰንዘር ልብ ያላቸውን ጋዜጠኞች ማንቃትና አዲስ ነገር እንዲሰሩ ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ለፍቶ እና ደክሞ ታሪክ እየሰሩ ያሉ ጀግኖቻችንንነ ግን ደግሞ ያልታወቁትን ምሁራኖቻችንን ማቆለጳጰስ ይገባል፡፡ ሌላው የውጭ ሀገር የዜና አውታር እስኪያከብራቸው መጠበቅ የለብንም፡፡ ነገር ግን እኔም የምስማማበት ከፊታው ያለውን ቀላል ነገር እንጂ ትልቁንና ልፋት የሚጠይቀውን የሚወዱት አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም በርታ ዳኒ፡፡

  ReplyDelete
 36. ye tsega hulu minch Egiziabiher yimesgen. Amilake kidusan be cherntu be edme ena tsega yitebikilin !!!!!!! Dn Daniel ebakih tolo tolo tsaflin,,,,enamesegnalen.

  ReplyDelete
 37. ማንን ለመንካት አስበህ እንደ ጻፍከው ገብቶኛል። በነገራችን ላይ ስራችሁ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ የሚሸት ግብራችሁ ግን ኢትዮጵያዊ ትህትና የጎደለው ግለሰቦች ብትኖሩ አንተ እና ቴዲ አፍሮ ናችሁ። እሱም የሚዘፍነው አንተም የምትቸከቸከው ኢትዮጵያዊነት ከአፋችሁ እና ከብዕራችሁ ውጭ በሂወታች የማይታይ የዘመኑ ፈሪሳውያን እናንተ ናችሁ። ስለ እትዮጵያዊንት፣ ስለእትዮጵያ እሴት እና ህዝቦቿ እሱም ሊዘፍን አንተም ልትጽፍ ትችላላችሁ እንጂ እራሳችሁን እንደ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ሞዴል እንዳትቆጥሩ። ለሞዴልነቱ እንደናንተ እዩን እዩን የማይሉ ሁነው ግን እያሳዩን ያሉ ምስጉን ኢትዮጵያውያን አሉ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኣንድ ጊዜ እንዳንተ ኣይነቱ ማስተዋያውን ጎርፍ የወሰደበት ደደብ ሰው ከያኒ(ኪነ ትበበኛ) ይርዳው ጤናን እሺ ይርዳው ለምን ኣይነ ስውር ሆንክ ብሎ ሲጠይቀው ምን ኣለው መሰለህ፡ "እንዳንተ ኣይነቱን ገልቱ ላለማየት" ኣለው። እውነት ገልቱ ነህ፡ ኣሁን እስኪ ባነበብከው ጽሁፍ ላይ ኣስተያየት መስጠት እየቻልክ እንደ ኣርሂቡ ጋዜጠኛ ላለማንበብ ወደ ስድብ ትገባለህ? ብቻ ይሁን ግን ዪሄ ማኛ የሆነ ጽሁፍ ነው ከቻልክ ተማርበት

   Delete
  2. Where is the insult? There is no insult in my comment. Could you take a moment and look back your comment? Afehen endet ante lesideb endekefet? This is the problem of blind supporters. I am not against Daniel. I am against to some of his actions. That is why I am commenting. ሰውን ከማምለክ እግዜር ያትርፍህ። ሌላ ምንም አልልህም። ከአጉል እምባ ጠባቂነት እግዜር ይጠብቅህ።

   Delete
 38. very interesting, i hope they can learn something from this.


  ReplyDelete
 39. ‹አባዬ አንተ መቼ ነው በቲቪ የምትቀርበው› አለቺው ልጁ፡፡
  ‹‹ሚዲያችን ከታዋቂ ይልቅ ለዐዋቂ ቦታ ሲኖረው››

  ReplyDelete
 40. TheAngryEthiopian/ቆሽቱ የበገነውApril 19, 2015 at 1:18 PM

  እስላሞቹ በዓላቸውን ሲያከብሩ ቀጥታ ከመካ የሚተላለፍ ክፍለዝግጅት በቲቪ ይተላለፋል፤ የዝግጅቱ መርኻ ግብርም ሃይማኖት ተኮር ይሆናል እንጂ እንደኛ ትርኪ ምርኪ አይሆንም። ከሞላ ጎደል በአገሪቱ ሁለንተናዊ ፀባይ ላይ አሻራዋ ያለበት ቤተክርስትያን ሃይማኖታዊ በዓልዋን ስታከብር ግን ከቤተክርስትያን የሚተላለፍ ሙሉ ዝግጅት በማረግ ፋንታ ከያኒዎች ጅላጅል፣ ከሃይማኖት በዓሉ ጋር ያልተገናኘ ጨዋታ ሲጫወቱ ማሳየት፤ካልሆነም ራስን ለማዋደድና ለማስተዋወቅ ራስ ተኮር የሆነ ክፍለዝግጅት ካንዱ ከያኒ ተብየው ቤት
  ዝግጅቱ ይተላለፋል። አሁንም አንድን ጠቃሚ ግለሰብ ተመራማሪም፣ አስተማሪም፣ ዘፋኝም ሆነ ከያኒ፣ ወታደርም ሆነ ማንም በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያየ ድርሻ ያለውን ግለሰብ በተለያየ ጊዜ በቲቪ ሌላ ክፍለጊዜ ውስጥ ማስተዋወቅ ይሻላል እንጂ፤ የሃይማኖት በዓሉን ለሃይማኖት ተኮር መርኻ ግብር መተው ነው የሚገባው።

  ReplyDelete
 41. "My people are destroyed for lack of knowledge."

  ReplyDelete
 42. My people are destroyed for lack of knowledge.

  ReplyDelete
 43. ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ

  ReplyDelete
 44. Good observation ችግሩ ያለው ቴሌቪዥን ላይ ብቻ አይደለም። The whole journalism lacks professionalism. In my view, there is no journalist in that country. May be we have reporters.

  ReplyDelete
 45. እንዲያውም ኢቲቪ ቢሰማቸው ‹በአሸባሪነት ሊያስከስስ ይገባል ሲሉ አንዳንድ የሕግ ምሁራን አስገነዘቡ› ብሎ ለዜና ጥብስ ያውላቸው ነበር፡፡

  ReplyDelete
 46. WOW......NICE VIEW..I LOVE IT.

  ReplyDelete
 47. I should admit that this is a perfect portrayal of the unjust side of the earthly life.... good job. But i have one comment... i think the government has started to award best performing teachers, at least in the area of science and mathematics....in case if you don't have the information. Thank you!

  ReplyDelete
 48. Where the problem lays? On the journalist or on the institution?

  ReplyDelete
 49. Great view!!! Thank u for sharing. I agree 100% with you.

  ReplyDelete
 50. ‹አባዬ አንተ መቼ ነው በቲቪ የምትቀርበው› አለቺው ልጁ፡፡
  ‹‹ሚዲያችን ከታዋቂ ይልቅ ለዐዋቂ ቦታ ሲኖረው›› አላት አባቷ፡፡

  ReplyDelete
 51. ‹‹ጓደኛዬ በቴሌቭዥን እየታየች ነው›› ስትለው ድካሙ ባይለቀውም እርሷን ለማስደሰት ተነሥቶ ዓይኑን እያሸ ወደ ሳሎን መጣ፡፡ ‹‹እሺ ለምን አርሂቡ ላይ አትቀርብም››
  ‹‹ያማ ጋዜጠኛውን ማሰቃየት ነው ልጄ››
  ‹‹ለምን ይሰቃያል?››
  ‹‹ምን ይጠይቀኛል? ጥናታዊ ጽሑፎቼን ማንበብ ሊኖርበት ነው፡፡ ምርምሮቼን መቃኘት ሊኖርበት ነው፡፡ ስለ እኔ የተሰጡ የሌሎች ሳይንቲስቶችን ምስክርነት ማገላበጥ ሊኖርበት ነው፡፡ ይሰቃያል ልጄ፡፡ ቀልድ የለመደን ሰው ዕውቀት ያሰቃየዋል፡፡

  ReplyDelete
 52. wow it is amazing way . i like it .I hope they learn some thing .
  unless they are blind to see the truth . may God be with you

  ReplyDelete
 53. I like it so much.

  ReplyDelete