Monday, March 23, 2015

የአድዋ ዘማቾች
የጉዞው መሥራቾች
ትናንት(እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓም) በጨጨሆ የባሕል ምግብ አዳራሽ በተደረገ አንድ መርሐ ግብር ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር፡፡ ‹ጉዞ አድዋ› ይባላል መርሐ ግብሩ፡፡
 ከዛሬ 119 ዓመት በፊት ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓለም ታሪክ ያልተለመደ አዲስ ታሪክ ለመሥራትና ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የማይደረስበት ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ሲሉ ከመላዋ ሀገሪቱ አንድ ሆነው ወጥተው፣ አንድ ሆነው ወደ አድዋ ዘምተው ነበር፡፡ ያኔ ብዙዎቹ የተጓዙት በእግራቸው ጋራ ሸንተረሩን፣ አረሁን ገደሉን እየተሻገሩ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሀገራዊ ፍቅር ነበር፡፡ ያ አንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ነበር ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችንን ሊደግሙት እንጂ ሊረሱት የማይገባ ታሪክ እንዲሠሩ ያደረጋቸው፡፡
ይህንን የአድዋ መንፈስና ዝና፣ ክብርና ላቅ ያለ ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ፤ አድዋ እንደ አንድ ተራ ሥነ ሥርዓት በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ከማስቀመጥና ‹አስቦ ከመዋል› የዘለለ ትውልዳዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለማድረግ፤ አድዋ እንደ ባለሞያ ጠጅ በየጊዜው ከጥንስሱ እየተቆነጠረ በየትውልዱ እንዲጠጣ ለማስቻል፤ እንደ ሰራፕታ ዱቄት በየዘመናቱ ቡኾ ውስጥ እንደ እርሾ እየተጨመረ እንዲበላ ለማብቃት፣ አድዋ ላይ የታየው የላቀ ኢትዮጵያዊነት አንደ ሜሮን ቅብዐት ከትውልድ ትውልድ ሳይቋረጥ እየፈላ የሁሉ ማጥመቂያ እንዲሆን የተነሡ ወጣቶች ያዘጋጁት መርሐ ግብር ነበር፡፡ እንደ አድዋ ዘማቾች ወኔ እንጂ ሌላ ሀብት የሌላቸው ወጣቶች፡፡ 

እነዚህ ወጣቶች አንድ አስደማሚ ተግባር ጀምረዋል፡፡ በየዓመቱ የአድዋ በዓል ከመከበሩ ቀደም ብለው ከአዲስ አበባ በመነሣት በእግራቸው ወደ አድዋ መዝመት፡፡ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በእግራቸው የተጓዙትን መንገድ እነርሱም በእግራቸው መከተል፡፡ የቀድሞ የአድዋ ዘማቾችን ስሜት  እየተጋሩ፣ ታሪካቸውን እያጠኑ፣ በየደረሱበት ለሚያገኙት ሁሉ የአድዋን የላቀ ኢትዮጵያዊነት እየሰበኩ፣ የትውልድን ቃል ኪዳን ማደስ፡፡

ተጓዦቹ ከመልስ በኋላ
በድንኳን እያደሩ፣ ያገኙትን እየቀመሱ፣ ከአራዊት ጋር እየታገሉ፣ ከተራራና ገደል ጋር እየተገዳደሩ፣ እየወደቁ እየተነሡ፣ እየታመሙ እየተፈወሱ፣ እየደከሙ እየጀገኑ፣ እያዘገሙ እየፈጠኑ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር ማቆራረጥ፡፡ አድዋ ላይ ተጉዘው የታሪክ ማርሽ በዘወሩ ጀግኖች ስም ራሳቸው እየሰየሙ፣ የመንፈስ ወራሽታቸን ማረጋገጥ፡፡  
የዘንድሮ ተጓዦች ስድስት ናቸው፡፡ ከስድስቱ አንዷ ሴት ናት፡፡ ጽዮን ትባላለች፡፡ በጉዞው ስሟ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ፡፡ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግሯ አቆራርጣ እንደ እቴጌ ጣይቱ አድዋ ላይ ሰንደቋን ተክላለች፡፡ መድረኩ ላይ ወጥታ የእቴጌን ታሪክና የጉዞውን ትዝታ ስትተርክ የሆነ የሚንፎለፎል ትኩስ ወኔ ከውስጧ እየወጣ ይገርፈን ነበር፡፡ እናለቅሳለንም፣ እንገረማለንም፣ እናጨበጭባለንም፡፡ የማትነጥፍ ሀገር፡፡
ከጉዞ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው መሐመድ ስለ ጉዞው ዓላማና ሂደት ሲገልጥ እርሱ ራሱ ከዐፄ ምኒሊክ ሠራዊት ጋር የዘመተ ነበር የሚመስለው፡፡ መቼም መሐመድ ስለ ኢትዮጵያ ሲያወራ መስማት በባለሞያ ካህን የተከሸነ ቅዳሴ እንደመስማት ያለ ነው፡፡ ያወጣዋል፣ ይተርከዋል፣ ያውም ከዕንባና ከስሜት ጋራ፡፡
እነዚህ ወጣቶች የዛሬ ዓመት በ2008 ዓም አንድ ታላቅ ታሪክ ሊሠሩ አስበዋል፡፡ የአድዋ አንድ መቶ ሃያኛ ዓመት ሲከበር አንድ መቶ ሃያ ተጓዦችን ይዞ ወደ አድዋ በእግር ለመዝመት፡፡ ወጣቶች ናቸው፡፡ ግን ልባቸው ሸምግሏል፤ ብዙ ሊስቧቸው የሚችሉ  ብልጭልጭ ነገሮች ነበሩ፤ ነገር ግን ሀገራዊውን ታሪክ መርጠዋል፡፡ ከሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር አቆራርጠው፣ የሀገራችንን ባንዴራ ከፍ አድርገው ፣ በየደረሱበት አድዋ ላይ የተገለጠውን ያንን ሁላችንንም የሚያኮራ ኢትዮጵያዊነት እየተረኩ በእግራቸው ሊጓዙ ተነሥተዋል፡፡

ጽዮን - እንደ እቴጌ ጣይቱ
እንደ እኔ እንደ እኔ አንድ ትውልድ ታሪኩን ሲያነሣ፣ በማንነቱ ሲኮራ፣ ታሪክም ለመሥራት ሲቆርጥ መደገፍ ይገባል እላለሁ፡፡ ወጣቶች ከሥነ ምግባር ሲወጡ፣ ማንነታቸውንና ታሪካቸው ሲረሱ፣ ለሀገራዊ ነገሮችም የእኔነት ስሜት ሲያጡ እንደምንወቅሰውና እንደምናዝነው ሁሉ፤ በሀገር ፍቅር ስሜት ሲነሡና ታሪካችንን ከፍ አድርገው በአዲሱ ትውልድ አዲስ መንፈስ ውስጥ ሊጽፉት ሲተጉም አብረናቸው መሥራት ይገባናል፡፡ ታሪካችንና ማንነታችን እንደማይዘነጋ ማረጋገጥ የምንችለው ተተኪው ትውልድ የእኔ ነው ብሎ በራሱ መንገድ ሊገልጠው ሲሞክር ካየን ብቻ ነው፡፡

የጉዞው አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ
እናግዛቸው፣ አብረናቸውም እንቁም፤ የቻልን የጉዟቸውን ወጭ እንጋራ፣ ያልቻልን በሚደርሱበት ቦታ ሽሮ ሠርተን ውኃ ቀድተን በማስተናገድ የጥንት አያቶቻችን የአድዋ ዘማቾችን የሸኙበትን ታሪክ እንድገመው፡፡ በሚደርሱባቸው ቦታዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወጣቶቹ ከተጓዦቹ  ጋር ስለ ታሪካቸው እንዲወያዩ መርሐ ግብር ያዘጋጁ፡፡ የእምነት ተቋማት ደግሞ በሚደርሱባቸው ቦታዎች በመቀበል ለታሪካችንና ማንነታችን ያለንን የከበሬታ ሥፍራ እናሳይ፡፡ በየቦታው የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም በየደረሱበት ቦታ እየተቀበልን ባንዴራውን ከፍ አድርገን በማሻገር የታሪክ ተረካቢነታችን እናረጋግጥ፡፡ አንድ መቶ ሃያኛውን የአድዋ በዓል፣ በ2008 ዓም ከአበባ ማኖር በዘለለ በማይረሳ የወጣቶች ታሪካዊ ጉዞ እናክብረው፡፡  
ጠቢብ አስቦ ይሠራል
ጎበዝ ደግሞ ከሚሠሩት ጋር ያብራል፡፡     

27 comments:

 1. በጣም ደስ የሚል ነገር ነው እግዚአብሔር አምላክ ይርዳቸው ያሰቡትን ለመፈፀም ያብቃቸው። ከእግር ጉዞ ውጪ በአድዋ ድል በዓል አከባበር ሊታሰብበት የሚገባ ነው ከዓመት ዓመት እየቀዘቀዘ ያለ ነው የሚመስለኝ የዘንድሮ ደግሞ የባሰ ነው ትንሽ ህጻናት ልጆች በዓሉ ማክበሪያ ቦታ ላይ ያሳዩት ነገር ተስፋ ሰጪ እና የሚያስደስት ሆኖ አግኝቼዋለው ራሴንም እንድጠይቅ አድርጎኝ አድርጎኛል። እናም ሁሉም ኢትዮጵያው አልፎም ሁሉም አፍሪካው ሊያከበረው የሚገባ በዓል መሆኑን የማንክደው ሃቅ ስለሆነ እናስብበት የቻለ እዛው አድዋ ላይ ያልቻለ ደግሞ አራዳ ጊዮርጊስ አፄ ምንሊክ አደባባይ ላይ ለማክበር የዓመት ሰው ይበለን።

  ReplyDelete
 2. አደዋን!
  እንዳለ የቋንቋ የሃይማኖት የዘር-ሐረግ ልዩነት፣
  ለጋራ ዓላማ፣ ለሀገር ነፃነት በጋራ መሞት፣
  መኖሩን ማስተማሪያ ሕያው እውነት፣
  ሊያደርገው ይገባል የዛሬ ወጣት፡፡
  እግዚአብሔር የወጣቶቹን ልቦና አይለውጥብን፡፡

  ReplyDelete
 3. እግዚሃብሔር ይመሰገን! ይህንን ማየታችንና መሰማታችን. በአባቶችሰ ፈንታ ልጆችሽ ተተኩልሸ ልንልነው . ታሪክ ሰሚ ብቻ ላንሆን ነው ተመሰገን! የምችለውን አደርጋለሁ እባክህን ዲያቆን ዳኒ ሙሉ አድራሻቸውን ሰልካቸውን ላክልን. ያባቶቻችን አምላክ አይለያቸው አሜን!ዲያቆን ዳኒ ቸር ያሰማህ!!!

  ReplyDelete
 4. Menew Dani!!! Betam Betam Yaganenekew Aymeselehem??? Masaregiawen Eredu/Awatu/Tebaberu Lemalet Yehan Yakel KeLek Yalefa Mugesa Menden New !!! Le 'Media' Sayehon Betegebar Be Eger Megwaz Be Geteru Ethiopia Ahunes Yale Aydel Enda (Be Egerachew Yehadut Bidemer ke 1000 KM Aybeletem TeLaLeh???) :: Tadya Ahun "Ye Gwadegniochih" Be Eger Mehad Le Ethiopia Hezeb Menden New Yemitekemew ??? Alemehadachewes Men Yegodanal???

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን ሰይጣን የያዘህ ሰው ነህ እባክህ፡፡ እንዴት አድርገህ ብትረዳው ነው ይህንን የጻከው ለእርዳታ ነው ብለህ የገመትከው፡፡ ደግሞስ እንዲህ ላለው በጎ ሥራ ርዳታ መለመንስ ነውር ነው እነዴ፡፡ እነዚህን የመሰሉ ልጆች መርዳት ካልቻልንኮ ነገ ድራግ ወስደው ጋንጃህን ብለው ብሩን ይቀበሉሃል፡፡ ከዚያ ሲለምኗት ትታ ሲጎትቷት ይሆናል፡፡ እነዚህ ልጆች የዳንኤል ጓደኞች መሆናቸውስ በምን ዐወቅክ፡፡ የጠባብነት መንፈስ ስለተዘራብ ነገሮችን ሁሉ ከሥጋ ዝምድና ከአጥንትና ጉልጥምት ባለፈ ለማየት አቃተህ፡፡ ከዚህ በላይ ም ልክፍት አለ፡፡

   Delete
  2. Ahunem Degema Elalehu (YeGel Asteyayeta new)... Ye Lejochi Be Eger ke A/A- Adwa Deres Mehad Le Ethiopia Hezeb Menden New Yemitekemew ??? Alemehadachewes Men Yegodanal??? ... Degemo Beyet Bekul New Wetatun Ke Snemgbar Blshunet Yemitadegut (Drug ena be Eger Megwazen Men Agenagnew ???) ... Be Mknyat/Masreja Mekeraker Kechalk Asredan ??? Le enya Tebabnet Malet... Be Chifnu Medegefem/Mekawemem New ... Tyakayen Masredat Kalchalk Zem Belo Afen Be Sideb/Zacha['ሰይጣን የያዘህ ሰው'/ጋንጃህን ብለው/ጠባብነት) Mekfet ... Le enya Yeham Tebabenet New

   Delete
  3. ወንድሜ- ምን ለማለት እንደፈለግህ ባይገባኝም……. እስኪ ልጠይቅህ
   1. ታሪክ ለአንተ ምን አይነት ትርጉም ይሰጥሀል?
   2. የዳንኤል ጥፋት ምንድን ነዉ?
   3. መድሀኒት እና ጉዞ ምን አገናኘዉ ላልከዉ….. በ መደሀኒት የነፈዘ ትዉልድ ምን ታሪክ የሰራል… ?
   አስተያየት፡
   ከብዙሀኑ በተለየ መንገድ ማየትህን ብቀበልም…. ምንም አመክንዮ የሌለዉ ጭፍን ተቃዉሞ መሆኑን ሳየዉ…. በአስተሳሰብ ብስለትህ ላይ እንድጠራጠር አደረግኸኝ›››› ….. ሚኒሊክን ሳይዘክሩ/ጠሐይቱን ሳያዉቁ እና ሳያወሱ ታሪክ መስራት ከባድ እንደሆነ ልብ በል…. ትንታግ የሆነ ሐሳብ ይዘህ በልዩነት ብትቆም ደስ ባለኝ… አስተያየትህን ለማንበብ ጓጉቸ ነብር……ግን ቢከፍቱት……. ሆነብኝ
   በርታ
   ሰላም ሁን!!!

   Delete
  4. I fully agree with this Anony,
   What is the significant of their march? why they select Adewa, why they did not select Meqdela? are they from that region and promoting their hidden mission?
   We need to ask all these questions, Dani ofcourse has right to give his comments too. But for me it is not so significant for the Ethiopian people.

   Delete
  5. የታሪክ ሽርሙጥና….. የአድዋ ድል በተነሳ ቁጥር ልባችሁ የሚርድባችሁ አንተና መሰሎችህ እናውቃችኋለን!!!! ለጦርነት ልትማግዱን ስትሹ ብቻ ነው እኛም ኢትዮጵያም አድዋም ትዝ የሚላችሁ፡፡ ባለፈው ታሪካችን ብዙ ጊዜ እርስ በርስ ተጫርሰናል፤ አሸንፈንም ተሸንፈንም እናውቃለን፤ ነገር ግ አድዋ ሁሉን ኢትዮጵያዊ ለጋራ አላማ ያቆመ እንደሆነ የምናውቅ ማካበድ ሲያንስበት ነው…… የአድዋ ዘማቾቹን በሙሉ መሐመድን ጨምሮ አላህ ለሚቀጥለው ጉዞ በሰላም ያድርሰን ያድርሳችሁ

   Delete
  6. ጎበዝ በዚህ መስኮታችን አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ ሆን ብለው ያልተገባ አስተያየት የሚሰነዝሩት የስንዴ እንክርዳዶች ናቸው። መቼም ቢሆን ጊዜያችንን ከማባከናቸውና ገጹን ከማጣበባቸው ባለፈ ምንም አሉታዊ ነገር መፍጠር አይችሉም።
   ምክንያቱም ታሪክን የማኮሰስና የመበረዝ አካሄዳችቸው ከንቱ የከንቱ ከንቱ መሆኑን እንኳን እኛ እነሱም አሳምረው ያውቁታልና ነው።
   ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው፥ ለኛም ማስተዋሉንና ጥበቡን ያብዛልን አሜን !!!
   ከብላቴናው

   Delete
  7. እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ነገሮች ባለሀብት ነች፡፡ ከእነዚኽ ነገሮች አንዱ ደግሞ ተዝቆ የማያልቀው የታሪክ ሀብቷ ነው ፡፡ ይኽንን ጣፋጭ እዉነታ ለመቀበል ከእሬት የሚያይል ምሬት የሚመርራቸው ልጆቿንም በጉያዋ አቅፋ ይዛለች ፡፡ ….. የቅኝ ግዛት ፍቅር የተጠናወታቸው ዛሬ የዓድዋ ድል ሲነሳ ጉረሮአቸውን የአንቃር ስሜት የሚታገላቸው ብዙዎች ናችው፡፡ …… አሁን ባለው የሉላዊነት ምሥጢራዊ ሤራ ማንነታችን ተድጦ ወደ አልኾነ መንገድ ከመሄድ በጥንት አባቶቻችን የአለምን ታሪክ እና አስተሳሰብ የቀየረ ታላቅ አኩሪ ገድል በቦታው ላይ ተገኝቶ ማዘከሩ ጥፋቱ ምን ላይ ነው? እኛ የማናውቃቸው እነሱም የማያውቁን ሰዎች በቡድን ተቧድነው ቅሪላ ሲቆራቆሱ ጊዜ ሰጥተን የሥራ ጊዝያችንን አጥፍተን በቴሌቭዥን መስኮት እነሱን ፍጥጦ ከማየት እና የምናዉቃችው የወለዱንን የአባቶቻችንን አኩሪ ድል ሥራ ከማዘክር የቱ ይሆን የሚሻል? ለሀገራችንስ ሕዝብ የሚጠቅመው የቱ ይኾን? …… ትውልድ ማንነቱን እንዲያውቅ ስለማንንቱ እንዲያስብ ማድረግ ከጥፋት አለመታደግ ይኾንን? …… ሀገረን ሕዝብን በጉልህ አይጠቅም ይኾንን? … በእርግጥ ዓድዋ ድረስ ተጉዘን አባቶቻችን ድል እንዳድረጉት ያለ በጉልህ የምንገጥመዉ ጠላት ባናገኝም ታግለን ልንጥለው የሚገባ ጠላት ግን አለ ያንን ፈልጎ ማቸነፍ የእያንዳዳችን ኃላፊነት ነው፡፡ (ጠላት ያልኩት …… ድህነትን፤ ሙስናን፤ ብሔርትኝነትን …… የመሳሰሉትን መኾኑን ልብ ይሏል)፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት የምታብብበት ዘመን እንደመኾኑ መጠን (ያሉ ችግሮች እንዳሉ ኾኖ) ወደፊት ለሚመጣ ፍሬዋ ገና በማለዳው ዋግ የሚመታውና አራሙቻ የበዛበት አዝመራ አያስፈልጋትም ፡፡ …… ዓድዋን ብቻ ሳይኾን ሌሎች ብዙ የታሪክ ቦታዎች (መቅደላ ፤ ጉንደትና ጎራ፤ መተማ፤ ዶጋሊ… የመሳሰሉት )እና ሥራዎች ሊዘከሩ እንደሚገባ ባምንም ከከዋክብት ኮኮብ ሊልቅ እንደሚገባም አምናለኍ፡፡ ከ "ሀ" ካልተነሱ እንደምን "ፐ" ላይ ይደረሳል ፡፡ደግሞ እኮ "…. ለኹሉም ጊዜ አለው …" ፡፡ ማን ያውቃል እንደ ዓድዋው ኹሉ ሌሎችን የሚያስብ ትዉልድ ጽንሰቱ በዚኽ ታሪካዊ የዓድዋ ጉዞ ይኾናል፡፡ አኹን በወጣቶቻችን የተዠመረዉ የጉዞ ታሪክ ወደ ሌላ ቀጣይ ታሪካዊ ጉዞ ሊያመራ ስለሚችል ጉዞው ላይ በሚኖረው ማንኛዉም አይነት እንቅስቃሴ ሱታፌ ብናደርግ መልካም ይመስለኛል፡፡

   ዳኒ ቅንነትና መልካምነትን ለተመላ ሀገራዊ ስሜትን ለሚያንጸባርቁ፤ ትውልድን ለሚያንጹ ጽሑፎችህ ሳላመሰግንህ አላልፍም፡፡ በአምላከ ቅዱሳን ስም ምስጋናዬ የደርስኽ ዘንድ ተመኝቻለኹና ፡፡ በሊጦስትራ አደባበይ እውነትን ከፊታቸው አቁመው " እውነት ምንድን ነው? " ብለው ከሚጠይቁ ጠቢባን አምላክ ይጠብቅህ ………

   Delete
 5. እግዚያብሔር ይስጥልን

  For considering the copy right comment.
  Now we can enjoy the printed pdf files.

  Blessings!

  ReplyDelete
 6. ጤና ይስጥልኝ

  ጠቢብ አስቦ ይሠራል
  ጎበዝ ደግሞ ከሚሠሩት ጋር ያብራል፡፡ ድንቅ አባባል ነው፤
  በሚገርም ሁኔታ ታሪክን የመስራት መንገድ በአዲስ አቅጣጫ እየመጣ መሆኑ ይሰማኛል። በዚህ ወጣቱ በብዙ መንገድና በቀላሉ የሕይወት መስመሩን በሚስትበት ዘመን እነዚህን የመሰሉ ወጣቶች ማግኘት የሚታሰብ አይደለም። እውነት ነው የጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ገድል እንዲህ እየደበዘዘና ቦታ እያጣ በመጣበት ወቅት ይህ ዓይነቱ የወጣቶቹ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም አመርቂ ነው። በበኩሌ ወጣቶቹ የጀግኖቻችንን ትንሳኤ እየፈነጠቁልን እንደሆነ ያመላክታልና ከፈጣሪ ጋራ ሁላችንም ልናበረታታቸው ይገባል። ለማንኛውም ዲ/ን ዳንኤል አድራሻቸውን ቢገለጽ ጥሩ ይመስለኛል።

  ከብላቴናው

  ReplyDelete
 7. Menew Dani!!! Betam Betam Yaganenekew Aymeselehem??? Masaregiawen Eredu/Awatu/Tebaberu Lemalet Yehan Yakel KeLek Yalefa Mugesa Menden New !!! Le 'Media' Sayehon Betegebar Be Eger Megwaz Be Geteru Ethiopia Ahunes Yale Aydel Enda (Be Egerachew Yehadut Bidemer ke 1000 KM Aybeletem TeLaLeh???) :: Tadya Ahun "Ye Gwadegniochih" Be Eger Mehad Le Ethiopia Hezeb Menden New Yemitekemew ??? Alemehadachewes Men Yegodanal???
  Replyምን ሰይጣን የያዘህ ሰው ነህ እባክህ፡፡ እንዴት አድርገህ ብትረዳው ነው ይህንን የጻከው ለእርዳታ ነው ብለህ የገመትከው፡፡ ደግሞስ እንዲህ ላለው በጎ ሥራ ርዳታ መለመንስ ነውር ነው እነዴ፡፡ እነዚህን የመሰሉ ልጆች መርዳት ካልቻልንኮ ነገ ድራግ ወስደው ጋንጃህን ብለው ብሩን ይቀበሉሃል፡፡ ከዚያ ሲለምኗት ትታ ሲጎትቷት ይሆናል፡፡ እነዚህ ልጆች የዳንኤል ጓደኞች መሆናቸውስ በምን ዐወቅክ፡፡ የጠባብነት መንፈስ ስለተዘራብ ነገሮችን ሁሉ ከሥጋ ዝምድና ከአጥንትና ጉልጥምት ባለፈ ለማየት አቃተህ፡፡ ከዚህ በላይ ም ልክፍት አለ፡፡

  ReplyDelete
 8. አይ አንቺ እማማ አትዮጵያ

  ታሪሽ እንኳን ላንቺ ለሌላው የሚሞቅ … እንደዲህ ነው ጀግና

  የቻልን የጉዟቸውን ወጭ እንጋራ፣ ያልቻልን በሚደርሱበት ቦታ ሽሮ ሠርተን ውኃ ቀድተን በማስተናገድ የጥንት አያቶቻችን የአድዋ ዘማቾችን የሸኙበትን ታሪክ እንድገመው፡፡

  በሚደርሱባቸው ቦታዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወጣቶቹ ከተጓዦቹ ጋር ስለ ታሪካቸው እንዲወያዩ መርሐ ግብር ያዘጋጁ፡፡

  የእምነት ተቋማት ደግሞ በሚደርሱባቸው ቦታዎች በመቀበል ለታሪካችንና ማንነታችን ያለንን የከበሬታ ሥፍራ እናሳይ፡፡

  በየቦታው የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም በየደረሱበት ቦታ እየተቀበልን ባንዴራውን ከፍ አድርገን በማሻገር የታሪክ ተረካቢነታችን እናረጋግጥ፡፡  ReplyDelete
 9. የሚታየው እና የሚደገፈው ዓላማው ነው፡፡ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ እየደበዘዘ ያለውን የአባቶቻችንን ተጋድሎ በአዲሱ ትውልድ ዘንድ ግንዛቤው እንዲጨምር ለማድረግ ስለሚያግዝ ዓላማው የሚደገፍ ነው፡፡ ሆኖም ሁሉም ሰው ሊሳተፍ የሚችለው በአቅሙ ልክ ሊሆን ይገባል፡፡ “በጎመን የተደለለ ጉልበት” አይደለም 1000 ኪሎ ሜትር አንድ ዳገምት ለመውጣት ሊከብደው ስለሚችል በእግር ጉዞው ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 10. አያቶችህ የኢትዮጵ ያን አንገት ቆርጠው ለፋሺሽቲው ጣሊያን የሸጡበት አሳፋሪ ታሪክ መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃአለን።

  ReplyDelete
 11. Thank you Dani.
  I am always prod of them.Others should follow their suits too
  Worku

  ReplyDelete
 12. ከአድዋ ጦርነት በኋላ የኢትዮጵያኖች ሥም በዓውሮፓ ተከበረ ይልቁን በሩሲያ ገነነ።

  ከፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለማርያም መጽሐፍ ገጽ92
  የነ ምዩ ምንሊክና የእቴጌ ጣይቱ የአድዋ ጀግኖች አባቶችና እናቶቻች ታሪክ በዚህ ጊዜ ይቆማል እሚባል ታረክ ሳይሆን እውነትም ስለሆነ በተለያየ መልኩ ሊዘከርይገባዋል።

  ReplyDelete
 13. lega Adwa Ethiopian trek betch sehon lawekaw saw yafrekam tarek new marenatawetch endemelewt aedlem bahunew gza yhann ymysbew legwech bmgaztatche egezabher yemsgan amen!! marenatawech ynafekacehut mecedale sla haymanotachen basben keter ymanresachewen talakun yandent fer kadge tedresen yatanbet ymanersaw lelaw teleku tarekatch yaltres mahunwen letredut yegabal tareken ylmaweken e hulme gza alew atchkule sawen lemezlaf yha tarek yadwe new lmhonew inager tmelesach end egzabeher ktfatachu endemalesachuen ydengl marym yasret legewwech endethune yzeweter solet new marenatewch!!

  ReplyDelete
 14. ጽሁፉን አነበብኩት የተሰጡትንም አስተያየቶች ሁሉ አነበብኳቸው በጣም የሚገርመው ግን የልጆቹ ጉብዝናን ከሚገባው በላይ ሳደንቅ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ግን ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እንኳን እጠራጠራለሁ እባካችሁ ቸሩ እግዚአብሄር ፍቅርንና ልቦናን ይስጠንዲ/ን ዳንኤልን የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ

  ReplyDelete
 15. ዲን መምህር ብርሃኑ ሀዲስ ከማይጨው
  እኛ የማይው ልጆች ደግሞ ኣጤ ምኒሊክ ወደ ዓድዋ ለድል ሲያልፉ የፀለዩበትና የታመሙ ሰራዎትና ፈረሶቻቸውሳይቀር የተፈወሱበት የፃዲቁ ኣቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ደብረፀሃይ ኣቡነ ተክለሃይመኖት ማይጨው ገዳም ላይ ማረፍያ ለማዘጋጀት ድንኳን ተክለን ንፍሮ ቀቅለን ጉእጉዝ ሳር ጎዝጎዘን ለማስተናገድ ጠበሉን ለሚጠመቁ ተጠምቀው እንዲጓዙ ከኣባቶችና ከሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሃዋርያው ብፁእ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ በማስፈቀድ ታሪክን እንዲቆይ ለማገዝ እንጥራለን ። ያግኙን ልግዜው ይህንን ስልክ በመጠቀም ስለ ዓለማው መነጋገር ይቻላል።
  ዲ/ን መምህር ብርሃኑ ሓዲስ 0914849042/ሶስና ባራኪ ኣብርሃ 0928934364

  ReplyDelete
 16. most of the history ignorant groups are those which are held back by narrow ethnicity, which leveled themselves as history washers and cleaners by considering revenge through taking drugs and chat. they are trashes of western media propagating English football, BBC ... they don't have history rather than blaming and chanting against golden histories and great kings who fought for truth and for their country. Even, if you consider as if you are a narrow nationalist you will not get the present identity of your family and your country. Thanks Dani for your priceless motivational engagement!!!

  ReplyDelete
 17. የአድዋን ድል ፡ የአፍሪካ ጥቁር በሙሉ ይኮራበታል! ለነጮች ደግሞ የሰለጠነው የጣሊያን ጦር ፡ ከአውሬ አይሻልም በሚሉት የጥቁር ጦር መሸነፉ ፥ እራሱን የቻለ እንቆቅልሽ ነው።
  ዘርና ሐይማኖትና ሳይቆጥር ፡ በአንድነት የተሰለፈው ያ ጀግና ትውልድ ደግሞ እግረ መንገዱን ፡ በዛ ሰዓት ፡ ከኛ ከዛሬዎቹ ፡ የተሻለ ግንዛቤ ያለው ስልጡን ሕዝብ እንደነበረም ማስመዝገቡንም ፡ አንዘንጋ!

  ReplyDelete
 18. አድዋ...አድዋ... አድዋ...

  የአባቶቻችንና እናቶቻችን ደም ያለ ኃይማኖት፣ ያለ ቋንቋ፣ ያለ ባህል፣ ወዘተርፈ ልዩነት ስለዛሬዎቹ እኛ ማንነት ሲባል በተራሮችሽ ደረት ላይ ለነፃነት እንደ ውሃ ፈሰው አንድ ላይ የተዋሀዱብሽ ነሽና የኢትዮጵያችን አምሳያ ነሽ።

  በጉልበቴም ተንበርክኬ 1,000 ኪሜ ተጉዤ ብጎበኝሽ (እድሉ ጠፋ እንጂ) ሲያንስሽ ነው እማማ! ኢትየጵያ አድዋ። አድዋ ኢትየጵያ። ማንም የማንነትሽ መንፈስ ያልገባው ቢያጥላላሽ እናቴ ሆይ በፍፁም አትደነቂ።

  ዘላለም ኑሪ አድዋ! ዘላለም ኑሪ ኢትዮጵያ!

  ዲያቆን ዳንኤል ምስጋናዬ ይድረስህ። እሱ ሁሉን ሰጪው አትረፍርፎ በሙላት ይስጥህ። አሜን።

  አዲስ ነኝ።

  ReplyDelete
 19. የእናንተን መናኛ አመለካከት የማይደግፍ ሁሉ ኢትዮጵያዊ አአይደለም ማለት ነው? ኪኪኪ ሆዳም ማፈሪያዎች!

  ReplyDelete
 20. ጠቢብ አስቦ ይሠራል
  ጎበዝ ደግሞ ከሚሠሩት ጋር ያብራል፡፡

  ReplyDelete