Tuesday, March 17, 2015

አዳቦል


በምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች ባሕል የኑግ ክምር አዳቦል ይባላል፡፡ የኑግ ክምር ቀላል በመሆኑ ነገረ ቀላል የሆነውን ሰው አዳቦል ይሉታል፡፡ እነርሱ አዳቦል የሚሉት ነገረ ቀላል ሰው ሦስት ነገሮች የሌሉትን ነው፡፡ ወይ ሲናገር አዲስ መረጃ የማይሰጠውን፣ ወይም ዕውቀት የማያዳብረውን ወይም ደግሞ ለሁኔታው የማይመጥን ነገር የሚናገርውን፡፡ 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሐዲስ ዓለማየሁ የባሕል ማዕከል ዓመታዊ በዓል ምሽት ላይ በኛ ጠረጲዛ ዙሪያ የነበሩ ምሁራን ይህንን የገበሬውን ነገር ሲሰሙ አዳቦልነት በሦስት ነገሮች የተነሣ ሊመጣ ይችላል ሲሉ ሐሳብ ሠነዘሩ፡፡ የመጀመሪያው ለንግግርና ለጽሑፍ ካለመጠንቀቅ ነው፡፡ ለማን፣ ምን፣ እንዴት ልናገር ብሎ የማያስብና እንዳመጣለት ብቻ የሚናገር ወይም የሚጽፍ ሰው ንግግሩ ወይም ጽሑፉ አዳቦል ይሆናል፡፡ ቃላት ይደረደራሉ፤ ዐረፍተ ነገሮች ይሰካካሉ፤ ዐናቅጽ ይሰደራሉ እንጂ አእምሮን ያዝ ወይም ልብን ስልብ የሚያደርግ ፍሬ ነገር አይገኝበትም፡፡ በውስጡ ንጥረ ነገር የሌለው ሆድ የሚሞላ ምግብ እንደመብላት ነው፡፡ ሆድን ይሞላል እንጂ ለሰውነት ድጋፍ አይሆንም፡፡ ሰምተው ወይም አንብበው ሲጨርሱ የሚይዙት ነገር አይኖርም፡፡ ወፍጮ ቤት ደርሶ የመጣ ሰው ቢያንስ ጥቂት ዱቄት ሳይነካው እንደማይመጣ ሁሉ አንድን ነገር የሰማ ወይም ያነበበ ሰውም ጥቂት ነገር ሳያገኝ መቅረት የለበትም፡፡

ለሰው የሚገባው፣ ግልጽ የሆነና ፍሬ ያለው ነገር ለመናርና ለመጻፍ የቋንቋ ችሎታም ያስፈልጋል፡፡ ቡናን እንዲጠጣ የሚያደርገው ቡናነቱ ብቻ ሳይሆን አፈላሉና አቀዳዱም ጭምር ነው፡፡ ሳይሰክን የተቀዳ ቡናና መግለጫ ያጣ ሐሳብ አቅራቢ አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱም የሚሰጡን ነገር እያላቸው አሰጣጡን አያውቁምና፡፡ የቋንቋ ችሎታ ማለት ጉዳዩን እስከ ጥግ ድረስ በመናገሪያው ቋንቋ አልቆ ለመናገር መቻል ነው፡፡ አልቆ ሲልም ይዘቱ በሚፈልገው ደረጃ ለማለት ነው፡፡ ጉዳዩን በምሳሌ፣ በዘይቤ፣ በከሳች ቃላትና ነገሩ እንዳይረሳ በሚያደርግ አገላለጥ ለማቅረብ መቻል፡፡ ሰሚና አንባቢ ሊገባው በሚችል መጠን እንዲረዳው ሆኖ ያልቀረበ ነገር ቃላትን መስማትና ማንበብ ብቻ ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ በአንድ ጠረጲዛ ላይ ምግቡን ሁሉ እንደ ተራራ ከምሮ እንደማቅረብ ያለ፡፡ ምንም እንኳን ምግቡ ጣፋጭና በባለሞያ የተሠራም ቢሆን ከክምር ውስጥ ምግብ እየጎረጎሩ ማውጣት ግን አማራጭ ላጣ ሰው ብቻ የሚሆን ነው፡፡ ያልረታን ንግግር የሚያዳምጠውና ያልበሰለን ጽሑፍም የሚያነበው አማራጭ ያጣው ሰው ብቻ ይሆናል፡፡

የሀገሬ ሰው ጎመን ብቻ መብላት ዐቅምም ጤናም እንደማይሰጥ ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል›› የሚለው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ንግግር የሚያደርጉ ወይም የሚጽፉ ባለሥልጣናት፣ ምሁራን፣ ጸሐፍትና የእምነት መሪዎች ሰው የሚሰማቸው ወይም የሚያነባቸው አማራጭ ስለሌለው ነው ወይስ ገብቶት ነው? የሚለውን የሚለዩበት መንገድ ቢኖር መልካም ነበር፡፡ ‹‹እኛስ ይህቺን ክረምት ወጣናት በመላ
                                   በኩርማን እንጀራ ጎመን ተጠቅልላ› እንዲል ገበሬ፡፡ ሌላ አማራጭ አጥቶ ክረምቱን በጎመን ብቻ እንዳለፈው ሁሉ፣ ሰምቶን እየሄደ ያለው አማራጭ ከማጣት ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ባለሞያዎችና ባለ ሥልጣናት ለንግግራቸውና ለጽሑፋቸው ተገቢውን የቅድሚያ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው፡፡ እነርሱ ነገሮችን የሚጠሩበት ስያሜ ቃል (terminalogy) በኋላ የሚዲያው ትርክት ሆኖ ስለሚቀጥል እንዳመጣ መሰየምን ልማድ ማድረግ የለባቸውም፡፡ ያለበለዚያ ንግግራቸው ለሕዝቡ አዳቦል ይሆንበታል፡፡ አንገቱን እየነቀነቀ የማያደምጠው፡፡ ቢነቀንቅም ለትዝብት ያህል የሚነቀንቀው፡፡ መናገራቸው እንጂ ንግግራቸው የማያስታውሰው፡፡  

ሁለተኛው የአዳቦል መነሻ ደግሞ የማያውቁትን ወይም ያላመኑበትን ነገር ሊጽፉ ወይም ሊናገሩ ሲሞክሩ ነው፡፡ እንዲያውም በሀገራችን አንዳንድ ባለ ሥልጣናት እ- እ- እ- እያሉ አንጀት የሚጎትት ንግግር የሚናገሩበት ምክንያት፣ አንድም ያላመኑበትን ወይም የማያውቁትን አለያም ያልተረዱትን ነገር ሊናገሩ ስለሚፈልጉ ነው የሚል ምሳሌ ቀረበ፡፡ አንድን መረጃ አንብቦ ወይም ሰምቶ፣ ከዚያም ተረድቶ፣ በመጨረሻም ቅርጽ አስይዞ ለማውጣት የሚጠይቀው አእምሯዊ ሂደት አለ፡፡ በጉዳዩ ላይ ማሰብ፣ ለራስ መተንተን፣ በራስ ቋንቋ መረዳትና ለማቅረብ መቻልን ይጠይቃል፡፡ እህል ያገኘ ሁሉ ምግብ አይሠራም፣ ምግብ የሠራ ሁሉ ምግብ አያቀርብም፡፡ እህል ያገኘ ምግብ ለመሥራት፣ ምግብ ሠሪም ምግብ ለማቅረብ ሦስቱ ሞያዎች ያስፈልጉታል፡፡ እህሉን ማወቅ፣ ምግብ አሠራሩን ማወቅና ምግብ አቀራረቡን ማወቅ፡፡ ንግግርና ጽሑፍም እንዲሁ ነው፡፡ ጉዳዩን አስልቶ መስማት ወይም ማንበብ፤ አጥልቆ መረዳትና አሣምሮ ማቅረብን ይጠይቃል፡፡ 

አንዳንድ ጋዜጠኞቻችንና አሠልጣኞቻችን ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎችን ወስደው  ሲያቀርቡ የሚያጋጥማቸው ችግር ከዚህ ይመነጫል አሉ ሊቃውንቱ፡፡ አንዳንዴ በሰላ ሁኔታ አይቃርሙትም፣ ወይም በሚገባ አይረዱትም፣ አለበለዚያ ደግሞ እንዴት ማቅረብ እንዳለባቸው አያስቡበትም፡፡ ምናልባት ያገኙት መረጃ አሳዝኗቸዋል፣ አስደስቷቸዋል፣ አስገርሟቸዋል፣ ወይም ደግሞ ከፕሮግራማቸው ጋር ሄዶላቸዋል፡፡ ነገር ግን በውስጣቸው አላመነዥኩትም፡፡ ጥሬውን እንደሆነ ነው ያስቀመጡት፡፡ እናውጣህ ሲሉት ቃል ያጥራቸዋል፡፡ እነርሱ ያገኙትን መረጃ ያህል ለኛ ማስተላለፍ ይከብዳቸዋል፡፡ ያኔ ነው ‹ቃላት ያጥሩኛል፣ ልዩ ነበር፣ ፐ፣ ጉድ ነው፣ አሪፍ ነው፣ ነፍስ ነው፣ የጸዳ ነው፣ አስደናቂ ነው› የሚሉ ነገሩን ከመግለጥ ይልቅ ስሜትን ብቻ የሚገልጡ ቃላት የሚበዙባቸው፡፡  አንዳንዴ ደግሞ ‹እንትን፣ ምን መሰለህ፣ ያ ነገር፣ እና፣› የሚሉ ቃላትን በመደጋገም መረጃ ሳይሰጡን ይቀራሉ፡፡ ወይም ደግሞ አንዱን ነገር ሰባት ጊዜ ይደጋግሙትና ያሰለቹናል፡፡  

ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ዕውቀት አጠር ከመሆን የሚመጣ ነው፡፡ ስለምትናገረው ወይም ስለምትጽፈው ነገር በንባብ፣ በትምህርት፣ በልምድ ወይም በሌላ መንገድ የተገኘ የተከማቸ ዕውቀት ከሌለህ ያላስገባህውን ልታስወጣ አትችልምና ነገርህ ሁሉ አዳቦል ይሆናል፡፡ ከነጠፈች ላም ወተት እንደመጠበቅ ያለ፡፡ ስለ አንድ ነገር በልዩ ሁኔታ ያጠኑ፣ በዚያ መስክ የሠሩ ወይም ያነበቡና የሠለጠኑበት ሰዎች ይጻፉ ወይም ይናገሩ የሚባለው ወደ አእምሯቸው ባስገቡት መጠን ውኃ ያዘለ ነገር ሊያወጡ ስለሚችሉ ነው፡፡ ‹የምትናገረው ነገር ከሌለህ ዝም በማለት እርዳኝ› የሚባለው በዚህ ምክንያት ነው አሉ አንደኛው ሊቅ፡፡ ‹ከራበው በሬ ሥጋ አይጠበቅም› ይላሉ አፍሪካውያን› አሉ ሌላኛው፡፡ ዕውቀት ሲያጥርህ ንግግርህና ጽሑፍህ ትርጉም በሌላቸው ቃላት የታጀቡ ይሆናሉ፡፡ ከልክ በላይ የሆኑ አጎላማሾች ይታጨቁባቸዋል፡፡ ‹‹ከተማዋ በአንጸባራቂ ድል ታጅባ በፈጣን እድገት ላይ ትገኛለች› ዓይነት ይሆናል፡፡ ‹አንጸባራቂ› ና ‹ፈጣን› ምን ያህል ናቸው? እዚህ ውስጥ መጠኑን መለካት አትችልም፤ ሥራህ እንደ በቀቀን ማስተጋባት ብቻ ይሆናል፡፡ ሐሳቡን በራስህ መንገድ ማቅረብ ስለማትችል በአሰልቺ ቃላት(ጃርገን) ትሞላዋለህ፡፡  

አዳቦልነት በትምህርታችን፣ በንግግራችን፣ በዜናዎቻችን፣ በጽሑፎቻችንና በመግለጫዎቻችን ውስጥ እየበዛ በሄደ ቁጥር የመልዕክት ልውውጡ የተሰበረ፣ አንጆ አንጆ የሚል፣ ችክታ የበዛበት፤ ተግባቦት የሚያጥረውና ሐሳቡ የነጠፈ ይሆናል፡፡ ይኼ ደግሞ የዕውቀት ሽግግርን፣ የሐሳብ ምይይጥን፣ የመልእክት ዝውውርን ይጎዳል፡፡ ‹በተለይም ደግሞ ባለሥልጣናት፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የእምነት መሪዎች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ ጸሐፍት፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችና ሥልጠና ሰጭዎች በአዳቦል በሽታ እንዳይጠቁ ለዕውቀት፣ ለአቀራረብና ለምናቀርብበት ማኅበረሰብ ተገቢውን ቦታ መስጠት ይገባናል› ሲሉ ምሁራኑ ውይይቱን ዘግተውታል፡፡

27 comments:

 1. ዕውቀት ሲያጥርህንግግርህና ጽሑፍህ ትርጉም በሌላቸው ቃላት የታጀቡ ይሆናሉ፡፡ ከልክ በላይ የሆኑ አጎላማሾች ይታጨቁባቸዋል፡፡ ‹‹ከተማዋ በአንጸባራቂድል ታጅባ በፈጣን እድገት ላይ ትገኛለች› ዓይነት ይሆናል፡፡ ‹አንጸባራቂ› ና ‹ፈጣን› ምን ያህል ናቸው? እዚህ ውስጥ መጠኑንመለካት አትችልም፤ ሥራህ እንደ በቀቀን ማስተጋባት ብቻ ይሆናል፡፡ ሐሳቡን በራስህ መንገድ ማቅረብ ስለማትችል በአሰልቺ ቃላት(ጃርገን)ትሞላዋለህ፡፡


  Enamesegnalen dani amlak edmehn yarzmew ...

  ReplyDelete
 2. This works not only for Journalists, Writers and Speakers but also for teachers. There are Adobal teachers. Some Adobal teachers know the subject they are teaching very well but are not fluent enough to express the concepts. Other Adobal teachers do not know the subject but are fluent in convincing students. Teachers having both the good qualities are limited in number. This is one of the factors for the low quality graduates we are having right now. Anyway, it is a good observation and keep it up teaching us.

  ReplyDelete
 3. ከቃልህ የተነሳ ትጸድቃለህ ከቃልህም የተነሳ ትኮነናለህ ይላል ቅዱስ መጽሐፍ።

  ReplyDelete
 4. በአንድ አቅጣጫና በራስ ሃሳብ ብቻ ነገሮችን መመልከትም አዳቦልነት ነው፥ አሁን አሁን ብዙዎች የተለከፉበት በሽታ ይሄ ይመስለኛል፡ በራሳቸው የትምህርት ዘርፍ እይታ ብቻ፣ በራሳቸው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ብቻ፣ በራሳቸው የእምነት ወይም የጎሳ አስተምህሮና ግንዛቤ ብቻ ሌላም ሌላም የተጠመዱ ከሆነና በተሰጣቸው አንገት ተዟዙረው የሌላውን ባይኖሩበትም መልከት ማድረግ እንኳን ከተሳናቸው እኚህ ታዲያ ቀላል የኑግ ክምር አይደሉምን::
  መምህራችን ዲን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ብርታትና ጥበቡን ደርቦ ደርቦ እንደ ጎበዝ ገበሬ ክምር ያድልልን፤ ጥቅመኞቹና ተመጋቢዎቹ እኛ ነንና!!!

  ReplyDelete
 5. Hi Dn Daniel, you raised very interesting issue which invites all of us to assess the way we write, speak and discus with others. Thank you so much!!

  ReplyDelete
 6. Hi Dn Daniel, you raised very interesting issue which invites all of us to assess the way we write, speak and discus with others. Thank you so much!!

  ReplyDelete
 7. i appreciate your view am adabol

  ReplyDelete
 8. ዲ. ዳንኤል ፣ በማናቸውም መልኩ የምታቀርባቸው ጽሁፎች እጅግ አስተማሪ ለመሆናቸው መናገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል ፡፡ ለእኔ ግን የሚገርመኝ እና ዘወትር የአንተን ጽሁፍ ለማንበብ የሚያስገድደኝ ዋናው ምክንያት፣ እያንዳናዱን ነገር የምትመለከትበት አግባብና ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫ በመመርመር የምትሰጠው ጆሮ ገብ ትንታኔ ነው፡፡
  ወደ ዛሬው ሃሳብ ልመለስና ‹‹ አዳቦል›› የሚለው ቃል በአራት ፊደላት የሚያስተላልፈው መልእክት እጅግ ጠንከር ያለና በአላዋቂ ሳሚነት . . . መንፈስ የሚደረገውን ሂደት በሚገባ የሚገልጥ ነው ፡፡ በማናቸውም መልኩ ቢሆን የሰው ልጅ በሚሰራው ስራ፣ በሚናገረው ንግግርና በሚያቀርበው ሀሳብ ላይ በቂ እውቀት፣ ማራኪ የአቀራረብ ስልትና የሚተላለፈው መልእክት ለአድማጩ ( ለተጠቃሚው ) የሚኖረው ፋይዳ በሚገባ መጤን እንዳለበት ሰፊና አስተማሪ የሆነውን ፅሁፍህን ወድጀዋለሁ፡፡
  እንድን ሀሳብ ተናጋሪው እንደፈለገውና የራሱን ስሜት ብቻ መሠረት በማድረግ የሚያቀውበው ከሆነ እንደተባለው በአማራጭ ማጣት ሰበብ የሚነበብ ቢሆንም በሂደት ግን የንባብ ፍላጎትን ከማኮላሸቱም በላይ አንባቢው የተሳሳተ አቅጣጫ እንዲከተልና የተዛባ አመለካከተን እንዲያዳብር በማድረግ በህብረተሰቡ ውስጥ የሀሳብና የአመለካከት ግጭት ( ideology conflict) ስለሚያሰፍን በዚህ ረገድ ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ግንዛቤ መውሰድ እንዳለብን በሚገባ ተምረናል ፡፡
  ስለአንድ ነገር ለመጻፍ (ሃሰብ ለማቅረብ) በመጀመሪያ ርእሱን መምረጥ፣ በርእሱ ዙሪያ ማለት ስለተፈለገው ሀሳብና ሊተላለፍ ስሚፈለገው መልእክት በቂና በመረጃ ላይ የተመሠረተ እውቀትና የተሸለ ግንዛቤ መያዝ የመጀመሪው ምዕራፍ ሲሆን በቀጣይነት ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ደግሞ መልእክቱን ለማስተላለፍና አንባቢው በተረጋጋ መንፈስና በፍቅር እንዲያነበው ለማድረግ የቃላት አጠቃቀም፣ የሃሳብ አወራረድ(ቅደም ተከተል)፣ ማብራሪያና መደምደሚያው በሚገባ እና በተሳካ ሁኔታ ተጽፎ እስተማሪና ገንቢ መልእክት መተላለፉ መረጋገጥ ይኖርበታል ፡፡ ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ቃላቶችን በመጠቀምና በተገለባበጠ የሀሳብ እንሽርሽሪት መልእክትን ለማስተላለፍ መሞከር የ ‹‹ አዳቦል›› ስብስብ አባል ስለሚያደርግ ጠንቀቅ ማለቱ አይከፋም ፡፡ ቸር ይግጠመን ፡፡
  እግዚአብሔር በቸርነቱ ለ‹‹ዳኒ›› ረጅም እድሜ ከመልካም ጤንነት ጋር ይስጥልን ፡፡

  ReplyDelete
 9. Hi Dani, you make a choice very interesting title. As you discussed with lovely words and smart ways of interpretation, the word that you chosen can transmit very sensitive message. In this era it is a very vital and burning issue. I think so; some writers have not that much idea, what they do. That is why; some books and literatures which are published under some newspapers and magazines could not attract readers, even a lot. Some speakers of the government and private sector also done as a similar manner while they held discussion with others and they make speech to publics. .
  You had given well enough expression, what the concerned bodies follow while they held discussion, write any literature and communicate with others. It is up to them. If they want to attract a reader and listener as what they want, they should follow an appropriate way of expression as Dn. Daniel argued. Thanks Dani. GOOD bless you!

  ReplyDelete
 10. የምትናገረው ከሌለህ ዝም በማለት ተባበረኝ
  ተመቸኝ !!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. እግዚአብሔር ይስጥልኝ ዲ ዳንኤል ሁሌም ጽሑፎችህ አነባቸዋለሁ…….እማርባቸዋለሁ አስተምርባቸዋለሁም….አንተን ዓይነት ሰው አምላክ ያብዛልን፡ አንተንም በጤና ይጠብቅህ ፡፡ ነገር ግን አንተን እንዲህ አድርግ ማለት እንደ ድፍረት አይቆጠርብኝና አዳቦል ከሆኑ ሰዎች ንትርክ ባትገጥም( በ ዘሀበሻ ስለ አንተ የሚጽፉትን ማለቴ ነው) አይመጥኑህምና………አትውረድ እንዳልከው

  ReplyDelete
 12. Lega Dakon danile yleban hasab negerkz egezabher ytabekh amen!!

  ReplyDelete
 13. ጤና ይስጥልኝ

  ማንኛውም ሰው ከመናገሩና ከመጻፉ በፊት ቆም ብሎ ማሰብና ማሰላሰል ያለበትን ጉዳይ ነው ያሰመርክበት። ይህ ባለአራት ፊደላት "አዳልቦ" ርዕስህ አራት ነጥቦችን አስታወሰኝ፤ ይህም የሰው ልጅ ከሚከተሉት በአንዱ እንደሚመደብና ከዚህ ውጭ እንደማይሆን ቆየት ሲል ያነበብኩት መጽሃፍ እንዲህ ይላል፥
  ፩/ ማወቁን የማያውቅ
  ፪/ ማወቁን የሚያውቅ
  ፫/ አለማወቁን የማያውቅ
  ፬/ አለማወቁን የሚያውቅ
  ታዲያ ዲ/ን ዳንኤል ምን ያህል ትክክል ነው ትላለህ/ትላላችሁ?

  በቸር ያሰንብተን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Besufekad Siyabara ምን ለማለት እንደፈለግህ እኔ አልገባኝም? እራስህ ፀሐፊው ደግመህ አንብበህ እራስህን መርምር የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ ምክንያቱም ለማለት የፈለከው ግልጽ አልሆነልኝም፡፡ ስለራሴ ነው የጠየኩህ፡፡ እየተሳደብክ ይሁን እያመሰግንክ ስላልገባኝ ነው፡፡ ጥያቄህን ለመመለስ ተቸገርኩኝ፡፡ ማንን እንደጠየክም እንደሆነም አልገባኝም፡፡ ፀሐፊውን ነው ወይስ አስተያየት ሰጪውን? የሰው ልጅ ግን የምንገርም ፍጥረት ሆነናል ፡፡ እያነበብን እንዳላነበብን ለመሆን የምንፈጥነው ነገር በራሱ ይገርመኛል፡፡ እራሴን ጭምር ነው፡፡ በዚህ ከምንፈጥን አንብበን እራሳችንን ማንበብ ልማድ ብናደርግ መልካም ይመስለኛል፡፡

   Delete
 14. ሰላም ዲያቆን ዳኒ, ግሩም የሆነ እይታ ነው! ሁላችንም እየወደቅነበት ያለው አካኤድ ነው.በተለይ አሁን ላይ የሚወጡት መፅሀፎች ሽፉናቸውን አሳምረው ምንም ፍሬ ነገር የሌላቸወና እና ተፅፎ ለመውጣት ብቻ የሚቸኮልባቸው, በጣም ማሰተዋል የጎደላቸው እየሆኑ መተዋል. ሁላችንንም የሚመለከት መልእክት ነው ያሰተለለፍክልን. ለመናገር, ለመፃፍ አንቸኩል. ለማዳመጥ ቦታ እንሰጥ . ሰሚና አንባቢ ብቻ ሆነን አንቅር!!! እግዚሃብሔር ልቦና ይሰጠን አሜን!!! ዲያቆን ዳኒ እመብርሐን እውቀትህን ታብዛልህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 15. Dn. Dani, Very interesting idea, that we all of as should follow and implement and take care off for what we write; speak and communicate to others.....Thank you so much!!

  ReplyDelete
 16. It is good but oyane will say ''Amhara - only talk''

  ReplyDelete
 17. ዳንየ! አንድ እንግሊዝኛ መምህራችን 3ኛ ክፍል እያለን 'the man has two saks of potatos' በሉ በማለት ሲጠይቅ አንድ ልጅ ብቻ ትንሽ ሲሞክር ሁላችንም ያንን ጽሁፍ ከጥቁር ሠሌዳ ላይ እያየን መናገር አልቻልንም በዚህም ምክንያት ሁላችንም ተንበረከክን ያልጅ ብቻ ቀረ መምህሩ ግን አንድ ነገር ተናገረን አዳቦል፡፡ አለን ምንም እንኳን እንግሊዝኛ 3ኛ ክፍል ላይ ብንጀምርም እያነበብን አለመናገራችን አስቆጥቶት ይመስለኛል አዳቦል ያለን፡፡ዛሬም ብዙ አዳቦል አለ እያነበበ እንኳን በልምድ ብቻ ተጠምዝዞ እውነቱን ሐሰት ብሎ መሠረቱን እየናደ ያለ አዳቦል ሞልቷል፡፡እይታህን ወድጀዋለሁ ብዙ አዳቦል ማውጣትም ይቻል ነበር ለሁሉም ልክ ስላለው እንጅ፡፡ሰላም ሁንልኝ፡፡

  ReplyDelete
 18. ግሩም ነው። እባክህ ይህን ፅሁፍ ሰዓሊ አምሳሉ እንዲያነበው አድርግልን። የሚፅፈውን የማያውቅ፣ጭብጥ የሌለው፣ ፍሬ የማይገኝበት ገለባ ብቻ!
  ወይ ጉድ አዳቦል አሉ!
  ጥሩ ምሳሌ ሰአሊ አምሳሉ!

  ReplyDelete
 19. thanks for your adivce

  ReplyDelete
 20. ‹በተለይም ደግሞ ባለሥልጣናት፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የእምነት መሪዎች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ ጸሐፍት፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችና ሥልጠና ሰጭዎች በአዳቦል በሽታ እንዳይጠቁ ለዕውቀት፣ ለአቀራረብና ለምናቀርብበት ማኅበረሰብ ተገቢውን ቦታ መስጠት ይገባናል›
  ዳኒ በጣም ደስ የሚል ምልከታ ነው but they are already
  affected by jargon words

  ReplyDelete
 21. ‹በተለይም ደግሞ ባለሥልጣናት፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የእምነት መሪዎች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ ጸሐፍት፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችና ሥልጠና ሰጭዎች በአዳቦል በሽታ እንዳይጠቁ ለዕውቀት፣ ለአቀራረብና ለምናቀርብበት ማኅበረሰብ ተገቢውን ቦታ መስጠት ይገባናል› dani it is amazing but they already affected by jargon words

  ReplyDelete
 22. ‹‹ከተማዋ በአንጸባራቂድል ታጅባ በፈጣን እድገት ላይ ትገኛለች› kkkkkkk

  ReplyDelete
 23. "አዳቦል" ኑግ ከተወቃ በኋላ የቀረው ረዘም ያለና ውስጡ ክፍት አንዳንዴም እናቶች ለቀሰምየሚጠቀሙበት በቀላሉ የሚሰባበር አካሉና ጉልበቱ ፈጽሞ የማይመጣጠኑ በቀላሉ የሚጨፈላለቅ፣ ቅርጹን የሚለቅና ፍሬ የሌለው መሆኑን ልብ ይሏል!!!

  ReplyDelete
 24. ዳኒ የሚገርም እይታ ነው፡፡ በጣም ነው የገረመኝ የእኔ ባህሪ ብዙ ጊዜ አንተ የገለጽካቸውን ጽሁፎችና ውይይቶች መስማት ይሰለቸኛልና ለምን እንደሆነ አይገባኝም ነበር አሁን ተረዳሁት፡፡ ካዲያ ኑሮ ያደከመን ህዝብ ነን እንደዚህ ዓይነቱን አንብቡ እያሉ ልባችንን ትክን የሚያደርጉት በመጀመሪያ ጽሁፍ ሳይኖር ነው አንብቡ የሚሉን፡፡ ዶ/ር ምህርት ደበበ ስሙን ካልተሳሳትኩኝ የተቆለፈበት ቁልፍን የፃፈው ጸሐፊ ባለፈው ሳምንት በውይይት ላይ የሰጠው አስተያየት ደስ ብሎኛል ሀገራችን ውስጥ አንባቢ ሳይሆን የሌለው የሚነበብ ነው የሌለው ያለውን በእውነት ዛሬ ግልጽ ሆነልኝ፡፡

  ReplyDelete