Tuesday, February 24, 2015

ዝቋላ ሀገሩ የት ነው?click here for pdf

የዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንም ካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ነገሥታቱ የሚገዙትን ሀገር ሕዝቦች ስም ይዘረዝራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካና የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የምንሻኮተው ብዙዎቹ ጎሳዎች/ነገዶች ስማችን የለም፡፡ ሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከተለያየ ቦታ መጥተን የሠፈርንበት ላይ ረግተን ነው ዛሬ የምንገኘው፡፡ የሕዝብ የሥፍራ ንቅናቄ የታሪኳ አንዱ መገለጫ በሆነቺው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ሌላውን ሀገርህ አይደለም፣ ክልልህ አይደለም፣ መሬትህ አይደለም እንደማለት ያለ ታሪካዊ ኃጢአት የለም፡፡ ትንሽ በታሪክ ወደኋላ ስንጓዝ ዛሬ ክልልና መንደር በመሠረትንበት ቦታ ሌሎች ሲኖሩበት እናገኛለን፡፡ አሁን የያዝነው ቦታ ከምእተ ዓመታት በፊት የሁላችንም አልነበረም፡፡ ሁሉም ሠፋሪ ነው፡፡ ነባር መሬቱ ብቻ ነው፡፡  

ኢትዮጵያ የምታዋጣን የሁላችን እንድትሆን አድርገን ከሠራናት ነው፡፡ እንደ አጥር ሠሪ እንስሳት(territorial animals)  ከዚህ በመለስ ማንም አይገባብኝም፡፡ እኔን ያልመሰለውን በዚህ አካባቢ ላየው አልፈልግም የሚለው ሂደት መጨረሻው መበጣጠስ ነው፡፡ የልዩነትን ያህል ተመሳሳይነት ሰፊ አይደለም፡፡ ተመሳሳይነት እጅግ ጠባብ ነው፡፡ አንድ ነኝ ብሎ በሚያስብ ‹ብሔርም ሆነ ብሔረሰብ› ውስጥ አያሌ ልዩነቶች አሉ፡፡ የጎሳ፣ የቤተሰብ፣ የአካባቢ፣ የእምነት፣ የፍላጎት፣ የርእዮተ ዓለም፣ የጾታ፣ የሀብት ደረጃ፣ የሥልጣን፣ ምኑ ቅጡ፡፡ ሁሉም ተመሳሳዩን ፍለጋ ከሄደ መጨረሻው ግለሰብ ነው፡፡ በሰውነት ክፍላችን እንኳን ተመሳሳያቸውን ከሚያገኙት ይልቅ የማያገኙት ይበልጣሉ፡፡ ሰው እንኳን በግለ ሰብእነት ሕልው የሆነው ልዩነትን በአንድ ኑባሬ ውስጥ በማስተናገድ ችሎታ ነው፡፡ አንድን አካባቢ ‹በተመሳሳይነት ሚዛን› አንድነቱን ጠብቆ ማቆየት አይቻልም፡፡ 


ያማ ቢሆን ኖሮ ሶማልያን የመሰለ ጠንካራና የማይናወጥ መንግሥት አይኖርም ነበር፡፡በእምነትና በቋንቋ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ይሄ ተመሳሳይነታቸው ግን አንድነታቸውን ሊጠብቅላቸው አልቻለም፡፡ ትኩረታቸው ‹ተመሳሳዩን ብቻ ፍለጋ› በሚለው ላይ ስለነበር ወደ ነገድ፣ ወደ ጎሳ፣ ወደ ጎጥ፣ ወደ ቤተሰብ እየወረዱ ነው በጦርነት ሲታመሱ የኖሩት፡፡ ለሶማልያ ችግር መፍትሔው ተመሳሳይን መፈለግ አይደለም ልዩነትን ለማስተናገድ መቻል ነው፡፡ ተመሳሳይነት ጠባብ ነውና፡፡ ጠባብነት ከሚመነጭባቸው ምንጮች አንዱም ‹ተመሳሳይን ብቻ ፍለጋ› ነው፡፡

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬ በሚታወቅበት ቦታ ላይ ከተገደመ ከ700 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ በዚያ አካባቢ አያሌ መንግሥታትና ሕዝቦች ተፈራርቀዋል፡፡ ገዳሙ ግን መከራ ሲገጥመው እየቀዘቀዘ፣ መከራውን አሸንፎ ደግሞ እንደ ፍግ እሳት እንደገና እየጋመ ከእኛ ዘመን ደርሷል፡፡ ወደዚያ ገዳም የሚገቡ መነኮሳት ሰማያዊቷን ሀገር የሚናፍቁ፣ ጾምና ጸሎትን ገንዘባቸው ያደረጉ፣ የጻድቁን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ ናቸው፡፡ የመነኩሴ ሀገር የለውም፡፡ መነኮሳት እንኳን ከእናትና አባታቸው በተወለዱበት ሀገር ቀርቶ ስማቸውና ታሪካቸው በማይታወቅበት ሀገርም ‹ሀገርህ የት ነው?› አይባሉም፡፡ 

ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ግብጽ ውስጥ ኖረዋል፣ ሊባኖስ ውስጥ ኖረዋል፣ ሶርያ ውስጥ ኖረዋል፤ ግሪክ ውስጥ ኖረዋል፣ ሮም ውስጥ ኖረዋል፡፡ አርመን ውስጥ ኖረዋል፡፡ ‹ሙሳ አል ሐበሽ› ሶርያ ውስጥ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ነው፡፡ የሶርያ ድርሳናት እንደሚነግሩን ሙሳ (ሙሴ) የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ ነው፡፡ ዛሬ ከኢትዮጵያ በላይ ሀገሩ ሶርያ ናት፡፡ በቅርብ ዓመታት የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ገዳም በሊባኖስ ውስጥ በቁፋሮ ተገኝቷል፡፡ ቫቲካን ውስጥ የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ማረፊያ ለታሪክ ቆሞ ይታያል፡፡ አርመን ውስጥ ኤቺሚዚን የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ገዳም ዛሬም አለ፡፡ 

እንዲያውም ዛሬ የዝቋላ መነኮሳት እንደገጠማቸው ያለ ‹ሀገርህ አይደለም› የሚል ሰውነት ያልገባው ፈተና ሲገጥማቸው ራሱ ፈጣሪ ነበር ይገሥጽላቸው የነበረው፡፡ በተአምረ ማርያም ላይ የተጻፈውና ኢየሩሳሌም በጦርነት ምክንያት በተዘጋች ጊዜ በ13ኛው መክዘ አካባቢ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው ኢትዮጵያዊ ታሪክ ለዚህ ማሳያ ሆኖ ይኖራል፡፡ ይህ በኢየሩሳሌም ተሳላሚዎች ሁሉ የታወቀውና ዛሬም ድረስ በጎልጎታ መግቢያ በር ላይ ምልክቱን ትቶ ያረፈው ታሪክ እንዲህ ነበር የተፈጸመው፡፡

ከዛሬ 700 ዓመታት በፊት አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛል፡፡ ከአፍሪካ ምድር የሄደ ብቸኛ ሰው ነበር፡፡ የትንሣኤ በዓል ሲከበር የትንሣኤውን መብራት ከመቃብሩ የሚያወጡት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ያን ጊዜ ግን ብቻውን ስለነበር ማንም ከቁም ነገር አልቆጠረውም፡፡ እንዲያውም  በመልኩ ምክንያት ተንቆ ‹ያለ ሀገርህ ለምን መጣህ፣ ውጣ› ተባለ፡፡ እርሱም ወጥቶ መግቢያው በር ላይ ሲያለቅስ በላዩ ላይ የብርሃን ዓምድ ተተክሎ ታየ፡፡ ተሳላሚው ሁሉ እምነቱንና ታላቅነቱን አደነቀ፡፡ ብርሃኑ የወረደበት ቦታም ተሰንጥቆ እስከ ዛሬ ድረስ ይታያል፡፡ ወደ ጎልጎታ የሚገባም ሁሉ ይሳለመዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በሌሎች ሀገሮች ሄደው በኪደተ እግራቸው የባረኩት ሁሉ ሀገራቸው ሆኖ መኖራቸው ብቻ አይደለም የሚገርመው፡፡ ከመላው ዓለም የመጡ መነኮሳትም በዚህች ሀገር ውስጥ ‹ከየት መጣችሁ? የማንስ ወገን ናችሁ?›› ተብለው ሳይጠየቁ እንደ ሀገሬው ዜጋ ኖረዋል፡፡ አባ መጣዕ(ሊባኖስ)፣ ተሰዓቱ ቅዱሳን፣ አርባ ሐራ፣ አምስቱ የመንዝ ቅዱሳን፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እጨጌ ዕንባቆም፣ ማኅበረ ጻድቃን፣ እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ መጥተው ኖሩ፡፡ እዚህችም ሀገር ዐረፉ፡፡ ገዳማቸው ገዳማችን፣ ታሪካቸው ታሪካችን ሆነ፡፡ 

ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ ነው የዝቋላ ገዳም መነኮሳት ዝቋላ ‹ሀገራችሁ አይደለም›› የተባሉት፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያውያን አይደሉምን? እዚህ ቦታኮ ከ700 ዓመታት በላይ ኖረዋል፡፡ እዚህ አካባቢ ከ700 ዓመታት በፊት የነበሩ ዜጎች አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲመጡ ‹ኦቦ› ብለው ተቀበሏቸው እንጂ ‹ሀገርዎ አይደለም ይውጡ› አላሏቸውም፡፡ ዛሬ በሥልጣን ላይ ካሉትና ገዳሙን በኢሬቻ መተካት ከሚፈልጉት ሰዎች ይልቅ ያኔ የነበሩት ሰዎች ልበ ሰፊዎች፣ አስተዋዮች፣ የሰውነት ክብር የገባቸው፣ የሀገርን ትርጉም የተረዱ፣ ከዘር ይልቅ ለሰውነት ታላቅ ቦታ የሚሰጡ፣ ሰውን በምግባሩ እንጂ በቋንቋውና በቀለሙ፣ በዘሩና በአጥንቱ የማይለኩ ነበሩ፡፡ 

የአንድ ክልል የቱሪዝም ቢሮ አንድን ገዳም ነጥቆ በገዳሙ ሥርዓት የማይፈቀድ ሌላ እምነትን ለመተካት ማነው ሥልጣን የሰጠው? በዚያ ገዳም ክልል ውስጥ ሊከበሩ የሚገባቸው ሃይማኖታዊ በዓላትንስ በምን ቀኖናዊ ሥልጣኑ ነው የሚወስነው? ለምንስ ነው እነዚህን መነኮሳት እየጠራ የሚያስፈራራው? ይኼ ገዳምኮ ዘመናትን ሁሉ ተሻግሮ እዚህ እንዲደርስ ያደረገው በእምነቱ ጽኑ የሆነው የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጅ ነው፡፡ ሕዝቡ እዚያ ገዳም ለጸሎት የተጉ መነኮሳት እንደሚገኙ፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቃል ኪዳን ቦታ እንደሆነ የሚያምን ነው፡፡ በየዓመቱ በጥቅምትና በመጋቢት 5 ወደ ቦታው በመሄድ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ከሚያከብረው ሕዝብ አብዛኛው የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጅ ነው፡፡ ታድያ እነዚህ አካላት ይህንን አስተሳሰብ ከየት አመጡት? 

ይኼ ተልዕኮ ሃይማኖታዊ ተልዕኮ አይደለም፡፡ የጠብ ጫሪነት ተልዕኮ ነው፡፡ በሰላም የኖረውን ሕዝብ የማበጣበጥ ተልዕኮ ነው፡፡ መጋቢት 5 ቀን በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ‹ኢሬቻን በጠበሉ ቦታ እናከብራለን፣ ሐውልት እናቆማለን› ብሎ በሕዝብ መገናኛ ማወጅ ጠብ ያለሽ በዳቦ እንደማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ያጸድቀኛል ብሎ ያሰበው እምነት ሊከተል ይችላል፡፡ ሁለት እምነቶች ግን በአንድ ቤተ መቅደስ ሊመለኩ አይችሉም፡፡ ሁሉም የየራሱን ነው መከተል ያለበት፡፡ ‹ከባልሽ ባሌ ይበልጣልና አልጋሽን ልቀቂለት› የሚለው ብሂል ግን ዛሬ የሚያዋጣ አይመስልም፡፡ የሃያ አንደኛው መክዘ ኢትዮጵያንም በጤና አውሎ አያሳድራትም፡፡ በዝቋላ ገዳም ላይ የተጀመረው ርስትን የመንጠቅ ሥራም በዝቋላ የሚያበቃ አይሆንም፡፡ ‹መንግሥታዊ ሃይማኖት የለም› ከተባለ መንግሥታዊ መዋቅሮች አንድን እምነት ደግፈው ሌላውን እምነት ለመጫን እንዴት ቻሉ? 

ስለዚህም
1.      ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁኔታውን በተመለከተ ለሚመለከታቸው ድብዳቤ  መጻፋቸው የሚገባ ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶስ ግን ይህንን ነገር በዕንቁላሉ ለመቅጨት መወሰንና መሥራት ያለበት ጊዜ ዛሬ ነው፡፡ መነኮሳቱና ሀገረ ስብከቱ የጻፏቸው ደብዳቤዎች በገዳሙ ስለደረሰው መከራ ብዙ የሚናገሩት ነገር አለ፡፡ በስብሰባዎች የደረሰባቸው ጫና፣ በየጊዜውም የሚደርስባቸውን እንግልት ገልጠውታል፡፡ ሲኖዶሱ ገዳማትን ከመጠበቅ የሚቀድም ሌላ ኃላፊነት የለውም፡፡  

2.     ምእመናንም ገዳሙን በንቃት መከታተልና በተለይም በመጋቢት 5 ቀን በክብረ በዓሉ በመገኘትና በዓሉን በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት በማክበር ለቅዱሱ ሥፍራ ያለንን ፍቅር፣ ለመነኮሳቱ ያለንን የዓላማ አንድነት፣ ሁላችንንንም ለሚያቅፈው ኢትዮጵያዊነት ያለንንም ክቡር ሥፍራ ማሳየት አለብን


3.     መንግሥትም በጥባጭ ካለ ጥሩ ለመጠጣት አይቻልምና በሚዲያ የተሳተው በሚዲያ፣ በአሠራር የተበላሸውም በአሠራር እንዲታረም ማድረግ ይገባዋል፡፡ 
                  

80 comments:

 1. የፈ ጣ ሪ ያለህ ኧረ ምን ዓይነት ጊዜ ነው እባካችሁ ሌላው ሳያንስ ደግሞ በዚህ? እውነት ሊከሰት የሚችለውን መንግስትስ አጥቶት ነው ወይስ እንደልጅ ጨዋታ የራሳቸው ጉዳይ ብሎ ተመልካች ሊሆን? ይህ ከመቼውም በላይ አሳሳቢ የሆነ ጉዳይ ነውና በየትኛውም መልኩ ወደ አላስፈላጊ ነገር እንዳይገባ ህዝቡ በተለይ ደግሞ የገዳሙ አካባቢ ህብረተሰብ ቆም ብሎ ጉዳዩን ማጤን ያለበት ይመስለኛል።
  ቸሩ መድሃኒዓለም ክፉውን ያርቅልን!!!
  ፈጣሪ አምላክ የነዚያን ደጋግ አባቶቻችንን ጭንቀትና ስጋት አስውግዶ ቤተ ክርስቲያንንና ምዕመናኑን ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
 2. አይ ዳኒ ይሄ መንግስት እኮ ገና እየጀመረ ነው አማራን እና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ከልማት አጀንዳው ቀዳሚ ነው ዋልድባ ፤ ዝቋላ ከዛማ ተረኛ ይቀጥላል ያው ሲኖዶሱ butorphanol ተወግቶ ተኝቷል ግን ዳኒ ሃገር ውስጥ ያሉት በመሄድ የራሳቸውን ግዴታ ይወጣሉ ከሃገር ውጭ ያለነውስ ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ እንድታሳየን እንፈልጋለን ነገ በእግዝአብሄር እና በትውልድ ተወቃሽ እንዳንሆን አባቶቻችን በብዙ መከራና እንግልት ያስረከቡንን ገዳማት እኛ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን።
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወሬኛ፣ መርዛም፣ ዘረኛ ይልቁስ ወደ ቁም ነገሩ አትገባም ፡፡ እንዴት ባለ ዲፕሎማሲ ጉዳዩን እንጨርሰው እንዴትስ ቤ/ክቱ ክልሏል ታስጠብቅ ለሚለው ሰፊ ውይይት እንዲደረግበት መሰለኝ ዳኒ ያቀረበው እንጂ እንደ አንተ ለመሳደብ ፈልጐ አይደለም

   Delete
 3. My parents are from Oromo background but never had this type of complete and utter hate for other people or their religion. This comes from their bosses - woyane- and their dictatorial, tyrant rule. This drives me crazy and believe me this is not going to end well for the "menekosat" in the gedam. They will not hesitate to massacre anyone who stands in their way.
  Is there anything we can do as EOTC members?

  ReplyDelete
 4. Not only this
  Non oromo Ethiopian living in the so called " Oromia region" are suffering a lot thanks to the racist EPRDF ( OPDO) and OLF
  God Bless Ethiopia

  ReplyDelete
 5. የመጨረሻው ዘመን አስጨናቂ ይሆናል የተባለው እየደረሰ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከምንሰማው መልካም ዜና ይልቅ አስጨናቂው ዜና ይበዛል፡፡ ለዋልድባ ያለቀስነው እንባችን ሳይደርቅ ደግሞ በዝቋላ በኩሉ ዞሩ!? ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ለአገሪቱ ወደ ኋላ መቅረት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂናት ሲሉ ተደምጠዋል ምናልባት ለዚህ ይሆን የሃይማኖታችን አምድ የሆኑትን ገዳማት ለመድፈርና ለማፍረስ የተነሱት፡፡ እግዚአብሔር የሰይጣንን ሐሳብ ያፍርስልን፡፡

  ReplyDelete
 6. Thanks for sharing. Is there NOone with little wisdom in the government?

  ReplyDelete
 7. God bless u,eagle eye Daniel!---every one has to understand that making a kios in Eth Orthodox church has been started since the inception of TPLF. By cracking down the unified religion, this group is calculating its eternal power on this nation!---Pray and unification are the two weapons to stop this junta!

  ReplyDelete
 8. ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳምዎትን ጠብቁ። ይሄንን ሃሳብ ላመጡት ሰዎች ልቦና ስጡልን።

  ReplyDelete
 9. Ye pootika siltanachewun tegen be madireg yelelawun imnet lemashemakek ina yerasachewun lemasfafat yemitiru be andand birowoch yitayalu Egziabher libona yistachew letefeterewum neger meftihe yist ignam be haymanotachin ina be migbar ke kedimow beteleye initsina

  ReplyDelete
 10. አይ ዳኒ ይሄ መንግስት እኮ ገና እየጀመረ ነው አማራን እና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ከልማት አጀንዳው ቀዳሚ ነው ዋልድባ ፤ ዝቋላ ከዛማ ተረኛ ይቀጥላል ያው ሲኖዶሱ butorphanol ተወግቶ ተኝቷል ግን ዳኒ ሃገር ውስጥ ያሉት በመሄድ የራሳቸውን ግዴታ ይወጣሉ ከሃገር ውጭ ያለነውስ ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ እንድታሳየን እንፈልጋለን ነገ በእግዝአብሄር እና በትውልድ ተወቃሽ እንዳንሆን አባቶቻችን በብዙ መከራና እንግልት ያስረከቡንን ገዳማት እኛ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን።
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ


  ReplyDelete
 11. አሁን ነገሮች እየተፋፋሙ መጥተዋል፡፡ የግብጽን ክርስቲያኖች ኑሮ ሳስብ እንዴት እንደሚጸኑና እነደ በግ በተኩላ እየተበሉ መኖራቸው ይገርመኛል፡፡እነርሱ በሃይማኖት አይቀልዱም፡፡እኛም ወደዚያው እየሄድን ነው፡፡የአሕዛብ ዘመን መጥቶአል፡፡ በአሕዛብ እየተዋጥን ነው፡፡ ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁ የበራ ይሁን፡፡ ክርስትና በደም ላይ ነው የተመሠረተው፡፡ ለዚች ሃይማኖት ለመሞት የሚዘጋጁ ብጹአን ናቸው፡፡ የአባቶችን ርስት ለማስከበር የሚሞቱ ብጹአን ናቸው፡፡ዝÌላ የኢትዮጵያ ዓይን ነው፡፡ በዓይን ደግሞ ቀልድ የለም፡፡እ/ር የፈቀደለት ይዘጋጅ፡፡ ያለርሱ አጋዥነት ሰማዕትነትን መቀበል ስለማይቻል፡፡አቡነ ጴጥሮስ በጣልያን የተገደሉት ለዚች እምነት ብለው ነው፡፡ አቡነ ተ/ሃይማኖት ጣዖት አምልኮን ለማጥፋት ብዙ መከራን የተቀበሉት፤ አቡነ ገ/መ/ቅዱስ መቶ ዓመት የጸለዩበት ሐይቅ በጣዖታውያን ይደፈራልን ይህ እ/ር የእኛን አÌም ለመለካት ያመጣው እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡የብሔር ነገር ከተነሳ እኔም ኦሮሞ ነኝ፤ ግን ሁሉም አሮሞ በእሬቻ፤በገዳ ስርዐት፤በጫጩ፤በከለቻ፤በአቴቴ፤በቦረንቲቻ፤በመልካ፤በቃሉ፤ወዘተ.ያምናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ የእኛ አያቶች በዚያ መንገድ ተጉዘው ሊሆን ይችላል፡፡ የኔ አያት በወንዝ ታመልክ ነበር(ባለማወቅ)፡፡ አሁን ደግሞ ሰለጠንን የሚሉ በውሃ አናመልክም፤ውሃውን በፈጠረ እንጂ እያሉ ሞዲፋይ እያደረጉ በ40 በ80 ቀን የተጠመቀውን ሕዝብ ግራ ያጋቡታል፡፡ ስለዚህ የጭንቁ ቀን ብቅ እያለ ስለሆነ እንዘጋጅ፤ሃይማኖታችንን ነቅተን እንጠብቅ እላለሁ፡፡እነዚህ የአክሱም ነገስታት ልጆች ምንም አይሰማቸውም?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም የደማ ልጅ ኦሮሞ ብሆንም ቤተሰሶቼ በእሬቻ ቢያምኑም ያንተን ሀሳብ ነው የምጋራው፡፡ በነገራችን ላይ የኔ ቤተሰቦች እራሱ ምን እንዳሉ ታውቃለህ ይህን የያዘዘ ወይም የጠየቀ ባለስልጣን አጀንዳው መጠናት አለበት ስለዚህ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ሁሉም በእሬቻ የሚያነው ሰው ይህንን ሀሳብ ላይቀበለው እንደሚችልም ማሰብ ጥሩ ነው፡፡
   የአባቶቻችን አምላክ ከኛ ጋር ይሁን፡፡

   Delete
  2. አንተ ደደብ ስለ ኦሮሞ ህዝብ ባህልና ሃይማኖት ስርኣት ኣንተ ብቻ ኣይደለህም በዚህ መልኩ የተነተንከዉ፡ቅድመ አያትህ አባ ባህረም ያንተው አይነት አቋም ነው የነበረው፡ኤና ያንኑ አራውታዊ ትችት ነው ኢየበረቀስክ ያለሀው፡የጣኦት ባለ ሀብቶች ማን አንደሆኑ ራስክ ታቀዋለህ፡፡ You z evil-mided!

   Delete
 12. ዲ/ን ዳኒኤል በጣም እናመሰግናለን፡፡ በታም ጥሩ እይታና አስተያየት ነው፡፡ አንዳንድ የመንግስ ባለስልጣናት ያለ አግባብ የሚሰሩትን እኩይ ተግባር ማጋለጥ አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ዝም ብለን ከተመለከትን በኋላ ቤተ ክርስቲያን አፍርሰን ለሌላ የዕምነት ተቋም እንሰጣለን ማለታቸው አይቀርም፡፡ ለታሪካዊቷ ቤተ ክርስቲያን እየተሰጠ ያለው ግምት ዝቅ ከማለቱም በተጨማሪ ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ መብቷ እየተገፈፈ ነው፡፡ ይሄ መቼም ፖለቲካ ነው ማለት አይቻልም፡፡-አላዋቂነት እነጂ!
  ለማንኛውም የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያን አካላት አስቀድመዉ ባይሠሩም ዛሬ ከእንቅልፋቸው ከነቁ የሆነ ነገር ቢሉ፡፡ እርግጥ እነርሱን ይሄ ያሳስባቸዋል ወይ የሚለው ይያቄ ነው፡፡ ---የሌላ እምት ተከታዮች ስለወረሩት ምን ይደረግ፡፡… አይ ቤተ ክህነት…ቤተ ትክነት ከሆነ ዋለ አደረ!
  ከዚህ በተጨማሪ አስተያየጥ የምንሰጥ አካላት ልሎች ነገሮችን ባንቀላቅል፡፡ አማራዉን….ምናምን የሚሉ ነገሮች ከተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ጋር አብረው የሚሄዱ አይደሉም፡፡ ያኛው በሌላ የፖለቲካ መድረክ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ እርግጥ የፖለቲካ ጉዳይ ሆኖ ቤተ ክርስቲያኗን የሚመለከት ሲሆን ዝም ማለት ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ቢሆንም ግን ቤተ ክርስቲያን የምታራምደው የአማራን፣ የኦሮሞን፣ የሀረሪን፣ የአፋሩን፣ የትግሬውን፣ የወላይታውን፣ የጉሙዙን፣ የልሎችብሔር ብሄረሰቦች (በአሁኑ አባባል) ክርስትና ሃይማኖትን ነው፡፡ ኦርዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በብሔር ብሐየረሰቦች የተገነጣጠለች አይደለችምና! ስለዚህ አማራ፣ ኦሮሞ ….ወዘተ የሚል ፍረጃ ውስጥ ሳንገባ ገዳሙ የሁላችን ነውና አብረን እረፉ እንበላቸው፡፡

  ReplyDelete
 13. ሲጀመር ምን ያህል እንጭጭና በዐእምሮ የበሰለ እንዳልሆነ የምታውቀው ለችግሩ እልባት ከመፈለግ ይልቅ አንተንና መሰል ለእምነታቸው ተቆርቋሪ ምዕመናን ላይ ሃሳብ ሲሰጥ ነገ እንሰማለን በመገናኛ ብዙሃን ዳኒ ችግሩ የቱ ጋር እንዳለ እናውቀዋለን፡፡ ሆን ተብሎ ቤ/ክኒቱን የኢሬቻን በዐል ከማያከብሩት ጋር ለማናከስና ፖለቲካዊ ትርፍ መሰብሰብ ነው፡፡ ሌላው የቤታችን ችግር ነው፡፡ የኃይማኖት መንበር ላይ ቁጭ ብለው ፖሊሲ ሙሉ የሚያስፈጽሙ አካላቶቻችን አልጸዱም፡፡ ከገዳሙ እና ከሃ/ስ ደብዳቤ ይልቅ ለመጣው ሲጨነቁ ጀንበር ትጠልቃለች ያሳዝናል••••••••••••

  ReplyDelete
 14. its very sad to hear this story. when we close one door they will wait us on another one just to attack. i don't understand the difference between politics and faith. may GOD give us all the courage and strength to overcome this terror.

  ReplyDelete
 15. Great Job Your Holiness Abune Mathias!!ማኅበረ - መነኮሳቱና ቅዱስነታቸው ያሳዩት ቁርጠኝነትና ችግሩን በሰለጠነ መንገድ ለማስወገድ የሄዱበት አካሄድ የሚመሰገን ነው፡፡ድርጊቱ ቢያናድድም እኛ ድርጊቱን ከወጠኑት መሻል አለብን፡፡በአስተየያታችን ውስጥ ፖለቲካዊ አድሏዊነት አይንጸባረቅ፡፡አጀንዳውን የኖረ የፖለቲካ ሂሳብ ማወራረጃ አናድርገው፡፡ከተቋማችን ጋር እንቁም፡፡ኤሬቻ ላይ እንደተቋም ተቃውሞ እንደሌለን በስራ አስኪያጅ ደረጃ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሃይማኖት አባቶችን ጭምር በመላክ ገልጸናል፡፡ያ ማለት ግን በዐሉ በኢኦተቤክ ቅድስና የተሰጠው ነው ማለት አይደለም፡፡ሌሎች ሃይማኖችም ቢሆኑ ስለኢሬቻ ከእኛ የተለየ አቋም የላቸውም፡፡አይቃወሙትም፡፡አያከብሩትም፡፡ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ነጥሎ መፈታተን አጓጉል የአክራሪ ብሔርተኛነት መገለጫ እየሆነ ሀገራዊ መግባባትን እንዳያውክ መንግሥት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ይሰማኛል፡፡ሰላም!!!!

  ReplyDelete
 16. ‹መንግሥታዊ ሃይማኖት የለም› ከተባለ መንግሥታዊ መዋቅሮች አንድን እምነት ደግፈው ሌላውን እምነት ለመጫን እንዴት ቻሉ?

  ReplyDelete
 17. ጥሩ ብለሀል ዲያቆን ዳንኤል፤ እይታህን ከማስነበብ ባሻገር ግን መፍትሄ ውስጥም አስተዋጽኦ ማድረግ ከቻልክ እባክህ ተሳተፍ፡፡

  ReplyDelete
 18. Really, are they Humans? this time is not different from the time of Yodit Gudit and Gragn Mohamed!! wey wayane (EPDRF) menew melkam neger alerjik honebachu!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 19. የኢትዮጵያ መንግስት ISIS ን መደገፍ ጀመረ እንዴ?

  ReplyDelete
 20. This issue is not passed as a previous ones . The govt part and the church should work to alleviate the problem and also the political parties pls inform your members that " democracy is not about a place . But it is all about people and diversity "

  ReplyDelete
 21. የመጨረሻው ዘመን አስጨናቂ ይሆናል የተባለው እየደረሰ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከምንሰማው መልካም ዜና ይልቅ አስጨናቂው ዜና ይበዛል፡፡ ለዋልድባ ያለቀስነው እንባችን ሳይደርቅ ደግሞ በዝቋላ በኩሉ ዞሩ!? ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ለአገሪቱ ወደ ኋላ መቅረት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂናት ሲሉ ተደምጠዋል ምናልባት ለዚህ ይሆን የሃይማኖታችን አምድ የሆኑትን ገዳማት ለመድፈርና ለማፍረስ የተነሱት፡፡ እግዚአብሔር የሰይጣንን ሐሳብ ያፍርስልን፡፡

  ReplyDelete
 22. ይኼ ተልዕኮ ሃይማኖታዊ ተልዕኮ አይደለም፡፡ የጠብ ጫሪነት ተልዕኮ ነው፡፡ በሰላም የኖረውን ሕዝብ የማበጣበጥ ተልዕኮ ነው፡፡ መጋቢት 5 ቀን በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ‹ኢሬቻን በጠበሉ ቦታ እናከብራለን፣ ሐውልት እናቆማለን› ብሎ በሕዝብ መገናኛ ማወጅ ጠብ ያለሽ በዳቦ እንደማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ያጸድቀኛል ብሎ ያሰበው እምነት ሊከተል ይችላል፡፡ ሁለት እምነቶች ግን በአንድ ቤተ መቅደስ ሊመለኩ አይችሉም፡፡ ሁሉም የየራሱን ነው መከተል ያለበት፡፡ ‹ከባልሽ ባሌ ይበልጣልና አልጋሽን ልቀቂለት› የሚለው ብሂል ግን ዛሬ የሚያዋጣ አይመስልም፡፡ የሃያ አንደኛው መክዘ ኢትዮጵያንም በጤና አውሎ አያሳድራትም፡፡ በዝቋላ ገዳም ላይ የተጀመረው ርስትን የመንጠቅ ሥራም በዝቋላ የሚያበቃ አይሆንም፡፡ ‹መንግሥታዊ ሃይማኖት የለም› ከተባለ መንግሥታዊ መዋቅሮች አንድን እምነት ደግፈው ሌላውን እምነት ለመጫን እንዴት ቻሉ?

  ReplyDelete
 23. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 24. Closely working with the surrounding community to consider institutions like the one under discussion as its own institutions shall be considered as one of the strategies to overcome such problems in the long run. Here, to closely work with the community, working on the notion that relates the EOTC to the totalitarian monarchy system and means of oppression particularly in the South needs serious attention along with respecting rights of people in the area that follow the traditional beliefs through assigning well educated, multilingual and matured Scholars of the church in such sensitive areas.

  ReplyDelete
 25. ጎበዝ ይህ የሃይማኖት እንጂ የብሔር ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህም እንዴት አድርገን ይህን ታላቅ የጸሎት ቅዱስ ቦታ በመንፈሳዊ ቅንዐት ፡ እንደባላደራ፡ እንደ እምነት ሰው እንታደገው ነው ብለን መዘጋጀት ያለብን፡፡ እንታደገዋለን ስንል በኃይለ እግዚአብሔር ፡ በቅዱሳን ምልጃ እና ጸሎት ነው፡፡
  መንግሥት የጥንት ጠላታችን ፡ዲያብሎስ መሳሪያ ከሆነ ቆየ፡፡ ፖለቲካ ምናምን እየተባለ.......ፖለቲካም ከሆነ ፡ ቤ/ክ የሁሉም ናት እንጂ የአንድ ሠፈር አልነበረችም፡ አይደለችም፡፡
  ስለዚህ "ፖለቲከኞቹ" ባሰመሩልን ሳይሆን እምነታችን በሚያዘን ና ቀደምት ባቆዩልን ነው መሔድ ያለብን የሚመስለኝ፡፡

  ReplyDelete
 26. Egzier hzbachinen yiTebQ,

  Guys, please read this intersting article from Abune Gebremenfes Qidus.

  ReplyDelete
 27. Sorry, here is the link.

  http://www.tigraionline.com/articles/ethiopian-church-miracle.html

  ReplyDelete
 28. የሚያሳዝን ጊዜ ደረሰን. እንግዲ ሁላችንም ሰምተናል ሥሜታዊ ባልሆነ መንገድ መፍትሔ መፈለግ አለብን.ወቅቱ የአብይ ፆም ወቅት ነው . መድሃኒያለምን የመጣውን እሳት እንዲያበርደው ተግተን እንፀልይ. በመቀጠልም ቤተ ክህነት ከሚመለከተው ክፍል ተነጋግሮ ጊዛዊ ሳይሆ ቂሚ የሆነ ወይንም ድጋሚ እንደዚ ዓይነት አሳብ እንዳይነሳ ማድረግ መቻል አለበት. በቅዱሳኑ ፀሎት እኮነው ዛሬ ያለነው. የሚመካ ቢኖር በእግዚሃብሔር ይመካ ነው የሚለው ቅዱሰ ወንጌል. ሰለ ኢትዬጵያ አንድ ሆኖ ማሰብ ነው ያለብን. በዘር, በገንዘብ,በሰልጣ ....መመካት ውጤቱ ባዶነት ነው. መጨረሻውም አያምርም. ወደ ልባችን ተመልሰን የተቀደሰ ሥራ ሰርተን እንለፍ. ዲያቆን ዳኒ ከአገር ውጭ ላላን በምን መልኩ መርዳት እንዳለብን የሚመስልህን አሳብ እባክህን ጠቁመን. አሁን ነው ዝምታ ወርቅ አይደለም ማለት. አምላከ ቅዱሳን ቤተክርሥቲያናችችንና,ኢትዬጵያን ጠብቅ! እመብርሐን አሥራት አገርሽን ኢትዬጵያን አስቢ አሜን!!!ዲያቆን ዳኒ እመብርሐን አትለይህ አሜን!

  ReplyDelete
 29. እዚያው ከአሰለመዱት አጅሬው ከበዛበት በራቸው ትተው ወደተቀደሰው ቦታ ሒዶ ለማርከስ ማሰብ ጠብ ጫሪነት ብቻ አይገለጸውም ደፋሮች ለእግዚአብሔር. ከብር የማይሰጡ ቢሆኑም. 21 ግብጻውያን ከገደሏቸው አረሜኔና ጨካኞች ጋር. ተመሳሳይ መሆን ነው። እዚያው ከአጅሬው ጋር ከተለማመዳችሁበት ቦታ ወዴት ወዴት ጦር ሞልቶኛል አብዶን አውርጅ ከሆነ መድሃኒታችን አለን። ቅዱሳንም አሉን። ወይ መንግሥታችን¡¡¡!!!"!¡

  ReplyDelete
 30. ለመሆኑ ዲ/ን ዳንኤል ይህንን ዕኩይ ጸባጫሪነት ከዚህ ባለፈ ለመቃወም ለመጋቢት አቦ ክብረ በዓል ያሰብከው እንደተጠበቀ ሆኖ ምናልባት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብና ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ያስፈልግ ይሆን?

  ፈጣሪ ክፉውን አርቆ ቸር ወሬ ያሰማን!!!

  ReplyDelete
 31. ግድየለም አምላክ ሀያል ነው በምርጫ ሰሞን የህብረተሰቡን አመለካከት ለመሳብ የማይደረግ የለም ግን አንዘንጋ አምላክ ቅርብ ነው ጎልያድም ወድቆ ነው የታየው ታሪካችን መለያችን እንጂ መጠቂያችን አይደለም በልልን ዳኒ
  እግዚአብሄር ከመጣብን መአት ይሰውረን
  ላመጡብንም ልቦና ይቸራቸው

  ReplyDelete
 32. መስዋእትነት እስከ ደም ጠብታ ይከፈላል እንጂ ማንም ዝም ብሎ አያይም፡፡ ኦሮሚያን ሲያሰኛቸው የሙስሊም ክልል አድርገው የሚያዩ አሉ፡፡ ኢሬቻን የሚያከብሩት ደግሞ ሙስሊሙም አህዛቡም ነው ስለዚህ ይህየተቀደሰ ቦታ ደግሞ የኦርቶዶክስ ነውና እወቁልን፡፡ አይ ኤስ አይ ኤስ ሃገራችን አለ የሚባልበት ደረጃ ላይ ነን ያለነው ማለት ይቻላል፡፡ መንግስት ምርጫ በመጣ ቁጥር የህዝብን ጥቅምና መብት አሳልፎ በመስጠት የተለየ ነገር ለማግኘት ሲደክም ይስተዋላል፡፡ መንግስት ሃገር እያስተዳደረ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን እንድንጠይቅም ያደርገናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ የጥምቀት ቦታን ለመስጊድ መስሪያ ሲሰጥ መስዋእትነት ተከፍሎም ቢሆን ዝም እንደተባለው እንዳይመስልህ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አለም አቀፍ ታሪካዊም ቦታ ነው ለማን ለኢትዮጵያ በባለቤትነት ደግሞ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፡፡ አሁን እንደሚታየው ከሆነ ሃይማኖታዊ መንግስት በተለይ ኦሮሚያ ላይ እየተንሰራፋ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ መንግስት ቸልተኝነትን ትቶ እንደዚህ የሚያደርጉትን ጠራርጎ ሊያስወግድ ይገባዋል፡፡ ያለበለዚያ እራሱም ላይኖር ይችላል የሚያኖር እግዚአብሔር ነውና፡፡ ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት ብሎ የነጋዴዎችን እቃ ገለባበጠባቸው ከቦታውም አስወጣቸው አባረራቸው፡፡ ስለዚህ እጣችሁን እያወቃችሁት፡፡

  ReplyDelete
 33. ተመሳሳይነት ጠባብ ነው፡፡ ጠባብነት ከሚመነጭባቸው ምንጮች አንዱም ‹ተመሳሳይን ብቻ ፍለጋ› ነው፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ ሶማልያን የመሰለ ጠንካራና የማይናወጥ መንግሥት አይኖርም ነበር፡፡በእምነትና በቋንቋ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ይሄ ተመሳሳይነታቸው ግን አንድነታቸውን ሊጠብቅላቸው አልቻለም፡፡ ትኩረታቸው ‹ተመሳሳዩን ብቻ ፍለጋ› በሚለው ላይ ስለነበር ወደ ነገድ፣ ወደ ጎሳ፣ ወደ ጎጥ፣ ወደ ቤተሰብ እየወረዱነው በጦርነት ሲታመሱ የኖሩት፡፡ ለሶማልያ ችግር መፍትሔው ተመሳሳይን መፈለግ አይደለም ልዩነትን ለማስተናገድ መቻል ነው፡፡
  ዳንኤል፣ እዚህ ላይ ትክክል ብለሃል። የአገርቷ ግንባታም የከሸፈውና አሁን ላለንበት ውጥንቅጥ የበቃነው ልዩነትን በመደፍጠጥ አንድ ህዝብ፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ አገር፣ … በሚል መርህ ተመሳሳይነትን ፍለጋ ከመነሻው የተሳሳተ አካሄድ በመከተላችን ይመስለኛል። መፍትሄው ልዩነትን አክብሮ ለጋራ አገር ግንባታ በጋራ መስራት ነው።

  ReplyDelete
 34. ምን ያድርጉ የ ሆራው ሾላ ዛፍ መለመላውን ቆሞ ሲያሳጣቸው? ለ ነገሩ የእሬቻ አምልኮ ተከታይዎች ሌላም ቢቃጡ አይደንቀኝም። ከ ዛፍ ቁመት ያለፈ ማመዛዘን አላቸው ብየ ስለማልጠብቅ። «ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ» ነው ነገሩ።

  ReplyDelete
 35. ዲ/ን ዳንኤል፣ ትክክል ብለሃል፤ ተመሳሳይነት ጠባብ ነው፡፡ ጠባብነት ከሚመነጭባቸው ምንጮች አንዱም ‹ተመሳሳይን ብቻ ፍለጋ› ነው፡፡ የኛ አገር ግንባታስ የከሸፈውና አሁን ላለንበት ውጥንቅጥ የበቃነው ልዩነትን በመደፍጠጥ አንድ ህዝብ፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ አገር፣ … በሚል መርህ ተመሳሳይነትን ፍለጋ ከመነሻው የተሳሳተ አካሄድ በመከተላችን ነው፡፡ አሁን ግን በልዩነት ተከባብሮና ተቻችሎ ለጋራ አገር ግንባታ በጋራ መስራት ጊዜውም የግድ ይላል። እንደዝቋላ ያሉ የእምነት ተቋማትን ከአደጋ ለመከላከል ከመስተዳደር አካላት ጋር ደብዳቤ መለዋወጡ ችግሩን ለጊዜው መፍታት ያስችል ይሆናል፡፡ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ግን በዋነኛነት ከአካባቢ ኅ/ሰብ ጋር በመነጋገር የጋራና ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ኅ/ሰቡ ተቋሙን እንደራሱ አካልና ሃብት እንዲያያው ማድረግ የተቋሙን ህልውና በአደጋ ጊዜም እንኳ ከአደጋ እንዲጠበቅ ሊያደርግ የሚችል ስለሆነ እንደ አንድ አማራጭ ዘዴ ተወስዶ በሚመለከተው አካል በሰፊው ሊሰራበት ይገባል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ቤ/ክርስቲያንቷ ካለፋት ሥርዓቶች ጋር የነበራትን የተዛባ ግንኙነት መነሻ በማድረግ የሚደረገውን አሉታዊ ቅስቀሳ መቀልበስ ሌላው ትኩረት ተሰጥቶት በሚገባ ሊሰረባት የሚገባው ጉዳይ ነው። ለዚህም ቤ/ቷ ያሏትን በሃይማኖት እውቀታቸው የበሰሉ፣ ቢቻል የየአካባቢውን ቋንቋና ባህል የሚያውቁና ምራቅ የዋጡ አዋቂዎቿን ያቀፈ ግብረ-ኃይል አቋቁሟ በፕሮጀክት መልክ ቢትሄድበት ይመከራል፡፡

  ReplyDelete
 36. We all believe , you are our voice. Please push hard to make this stupid idea get rid off. We cant blame the government for everything happen back home, but we the people have to team up and change the difference. Thank you Daniyee.

  ReplyDelete
 37. TheAngryEthiopian/ቆሽቱ የበገነውFebruary 26, 2015 at 9:46 AM

  በአሁን ጊዜ ያሉት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አስተማሪ ነን ባዮች ትልቁ ስራቸው ህዝቡን ሽንታም ማድረግ ነው፣ከዛም ማደንዘዝ ለጥቆም ቤተክርስትያኒቱን ለጴንጤ ማስረከብ ነው።
  ትግል ከመደንዘዝ በፊት ነው፤ ከደነዘዙ በኋላ መነቃነቅ ውጤቱ ምንም አያምርም። እነሆ የወያኔ ዘመን (ዘመነ ትግሬ/ ዘመነ አረብ) በጠቅላላ የድንዘዛ ዘመን ነው። ቤተክርስትያናት
  ይቃጠላሉ፣ይዘረፋሉ፣ቤተክርስትያን ትቦረቦራለች ትከፋፈላለች፣ አጥፊዎችዋ በላይዋ ላይ ይሾማሉ፣ ማንነቱን ከዚች ቤተክርስትያን ጋር አጣምሮና የሙጥኝ ብሎ ለዘመናት
  የተከተላት እና የሞተላት፣ አገሩንም የጠበቀው የአማራው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብም ይዋከባል፣ በዕቅድ እንዲጠፋም ይደረጋል። ምንም የለም ጭጭ ነው። ቤተክርስትያኒቱ
  የመተንፈሻ ቱቦዋ በእርሷ ባልሆኑ በቡድን በሚንቀሳቀሱ የባዕድ አካላቶች ቁጥጥር ስር ነው ያለው። በፈለጉ ጊዜ ጭብጣቸውን ማላላት ወይም ማጥበቅ ይችላሉ። በኢትዮጵያችን ላይ
  እንደአገርነቷ በሷ ላይ የሚነጫነጩባት፣ በቤተክርስትያኒቱ ላይም ሆነ በአማራው ማህበረሰብ ላይ የሚዶልቱትና ጥቃት የሚፈፅሙት የምናምንቴ ጥርቅሞች፤ የሚነቃነቁት በታመቀ
  የእልህ ቁጣ፣ፍፁም ጨለምተኝነትን ያማከለ፣ቦለቲካዊ አላማም አንግበው፣ፀረ-ኢትዮጵያ ከሆኑ አገሮች ጋር በተጣመረ ትስስር ነው። በሌላ አንፃር ደግሞ የእኛው ጎራ ሲገመገም ደግሞ፣ ዱላ በተሰነዘረበት ቁጥር እግዚኦ ማለት፣ እሱኑ ለማዳከምና ለማጥፋት ለተቋቋመው መዋቅር አቤቱታ ማቅረብ፣ ቤተክርስትያንና ቦለቲካ መገናኘት የለባቸውም የሚል መርዘኛ
  አይሁዳዊ ፀረ-ቤተክርስትያን አመለካከት ማራገብ ነው። እዚህ መድረክ ላይ ከተለጠፉት የአቤቱታ ማመልከቻ ውስጥ አንዱ እንደሚነግረን ከሆነ፣ በእሬቻ ዙሪያ ላይ ያለ የዝቋላ ጉዳይ በ፪ሺ፬ ዓ.ም. ግንቦት ፳፰ እና ሰኔ ፰ ቀን ለቀድሞው ፀረ-ቤተክርስትያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆነው "ፓትርያርክ" ተብዬ ግለሰብ ቀርቦ እንደነበር ነው፤ ግለሰቡም በግብርም በአላማም ፀረ-ቤተክርስትያን ስለነበርና ነገሩን ከቁምነገር ስላልቆጠረው ዘለቄታዊ መፍትሄ አልተሰጠውም። አንድ ነገር መረዳት ያለብን ደግሞ ሁለት ወር ቀደም ብሎ መጋቢት ላይ ዝቋላ አካባቢ ያለው ደን እሳት ተለኩሶበት ነበር - የእሬቻዎች ቅድመ-ዝግጅት ይሆን ? በዚሁ በመጋቢት ወር በአሰቦት ገዳም ያለው ደንም ተመሳሳይ እጣ ደርሶበት ነበር። የዝቋላና የአሰቦት ደን የተቃጠለበት ጊዜ ደግሞ፣ የዋልድባ ገዳም ፈተና የምዕመናኑን ትኩረት የሳበበት ወቅት ነበር። ሶስት ዓመት ወደፊት እንፈነጠር - አሁን ደግሞ የቤተክርስትያን ቁንጮ እንዲሆን እስራኤል ቀብታ የላከችው ግለሰብ በዝቋላ ገዳም ይዞታ ላይ ሊደረግ የሚታሰበውን የእሬቻ ግርግር በተመለከተ ሁኔታ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ እንደተፃፈለት እዚህ ያሉት ማስረጃዎች ያሳያሉ። አንደኛው በመስከረም ፳፩ ቀን የገዳሙ አባቶች የፃፉት ሲሆን፣ የመጨረሻው ገፅ እዚህ ለማስረጃ አብሮ አልቀረበም። ለምን ? ደብዳቤው የ፪ሺ፬ቱን ጉዳይ ያስታውስና እንደገና በዚህ ዓመት በመስከረም ፲፭ ቀን በኢቢሲ የተላለፈውንና መጋቢት መጨረሻ ላይ እሬቻ በገዳሙ ንበረት ላይ እንደሚከበር የተላለፈውን ዜና አሳሳቢነት ይገልፃል። የመጨረሻው ገፅ እዚህ ድህረ-ገፅ ላይ ስለሌለ መደምደሚያውን ነጥብ ልናውቅ እንችልም - ግን ግልፅ ነው። ሁለተኛው ደብዳቤ የተፃፈው ደግሞ ታህሳስ ፲፬ ቀን ሲሆን፤ አቡነ ጎርጎርዮስ "ለፓትርያርኩ" ፅ/ቤት የላኩት ደብዳቤ ሲሆን ግልባጩም ለዝቋላ ገዳም አበው ተልኳል። የነገሩን አሳሳቢነት አበክረው ገልፀዋል፣ በታህሳስ ፲፬ ቀን ከገዳሙ የተፃፈላቸውን አንድ ገፅ ደብዳቤም ብዢውን አብረው "ለፓትርያርክ" ፅ/ቤቱ መላካቸውን ጠቁመዋል። መስከረም ፲፭ ቀን በኢቢሲ የተለቀቀው ዜናና መስከረም ፳፩ ቀን "ለፓትርያርኩ" ፅ/ቤት
  የተላከው ደብዳቤ ምንም ዓይነት አፀፋ መልስ አላገኘም። በድጋሚ ታህሳስ ፲፬ ላይ ከአቡነ ጎርጎርዮስ የተላከው ደብዳቤ ምንም መልስ አላገኘም። "የፓትርያርክ" ተብየው ግለሰብ ድህረ-ገፅም ምንም ትንፍሽ አላለም። ጭራሹኑ ዜናው ለመጀመሪያ ጊዜ ሽፋን ያገኘው የማህበረቅዱሳን ድህረ ገፅ የካቲት ፲፬ ቀን በለቀቀው ዘገባ ነው። ሃተታውም "ፓትርያርኩ" ለ"ኦሮሚያው" መሪ ሙክታር ከድር ነገሩ እርማት እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቃቸውን ይጠቅሳል። ነገር ግን ዘገባው ውሸትና ማዘናጊያ ነው የሚመስለው - ሲጀመር ጉዳዩ በኢቢሲ መስከረም ፲፭ ቀን ከተስተዋወቀና የገዳሙ አባቶችም ደብዳቤያቸውን በመስከረም ፳፩ ካስገቡ ፤ እንዴት ከአምስት ወር በኋላ ጉዳዩ እንደ አዲስ ዜና ይቀርባል ? እሬቻ የሚባለው ግርግርም ካልጠፋ ቦታ ገዳሙን ሊያረክስ አንድ ወር ቀረው ማለት ነው። ጉዳዩ ሲራገብ የነበረው ግን ከ፪ሺ፬ ጀምሮ ነው። እንግዲህ በአመት ሁለት ጊዜ እንዲከበር የሚታቀድለት እሬቻ የሚከበረው መስከረም ፳፭ ቀን በደብረዘይት ከተማ በሆራ ሃይቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ዙር ግን በደፈና መጋቢት መጨረሻ በዝቋላ ገዳም ይዞታ ስር ባለው ቦታ ላይ ነው ተብሎ ተወስኗል። ይህቺ መጋቢት "መጨረሻ" ለምንድነው ቀኗ ያልተወሰነው ያው የመጋቢት መጨረሻዋቹ ደግሞ የሁዳዴ ፆም ማገባደጃ ቀናት ይመስላሉ። ይኼ ነገር አንድ የድሮ ነገር አስታወሰኝ በመካከለኛው ክፍለ ዘመናት ወቅት አረቦች ያገራችንን ህዝብ ያጠቁት የነበረው ይህችኑ የፆም ወቅት ጠብቀው ነበር። በአፄ ናኦድ ዘመነ መንግስት የፆም ወቅትን እየጠበቀ በኢትዮጵያ ላይ ጅሃድ ሲያካሂድ የነበር ማህፉዝ የተባለ የዘይላ ገዢ ነበር። አባ ገብረ እንድርያስ የተባለ አርበኛ መነኩሴም በፆም ጊዜ ለውጊያ ለሚዘጋጁት ወታደሮች ፆማቸውን ለጊዜው አፍርሰው ፍልሚያቸውን ከጨረሱ በኋላ ንስሃ መግባት እንደሚችሉ ሰብኮ፤ ውጊያቸውን በድል ፈፅመውት ማህፉዝም በሽሽት አምልጧል። ይሄው አርበኛ መነኩሴም በዕድሜው ልጅ በነበረው አፄ ልብነድንግል ጊዜም ጀብዱ ሰርቶ ነበር። እንደተለመደው ማህፉዝ ለዘመቻ በሚዘጋጅበት ጊዜ ሳይታሰብ አጣብቂኝ ውስጥ ስለገባ፣ ወደ ንጉሱ ሰፈር
  መልእክተኛ ልኮ አንድ ለአንድ ከንጉሱ ጋር ለመጋጠም አማራጭ በሚሰጥበት ጊዜ፤ አባ ገብረ እንድርያስ ለግብግቡ ራሱን መርጦ ከማህፉዝ ጋር የከረረ ክትክት አካሂዶ፤ የማህፉዝን ጭንቅላት ለንጉሱ ግዳይ የጣለበት ጊዜ ነበር።አባ ገብረ እንድርያስ እስከለተ ሞቱ ድረስ በንጉሱ ችሎት ዙርያ የተከበረ፣የተፈራና የተወደደ ነበር። እንግዲህ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን የቆየችው እንዲሁ በእግዚዖታ ብቻ አይደለም፤ ጠላቶችዋን እየሰባበርች እንጂ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስመኘው ሙንዬFebruary 26, 2015 at 2:27 PM

   መምሬ ቆሽቱ፡- ቅድስት ተዋሕዶ እየተፈተነች ያለችው በወያኔ ብቻ ሳይሆን እንዳንተ ባሉ ያልበሰሉ የአማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ያልተገባ ቱሪናፋና እምቧከረዩ ባይነት ጭምር ነው፡፡የተሸፋፈነ ዘረኝነትህን እዛው!!አጀንዳችሁን ለብቻው አስኪዱ!! ኦና አጀንዳችሁን ከኦርዶክሳዊት ቤ/ክ ጋር እያጣበቃችሁ ለአክራሪ ብሔርተኞች መፈልፈያ አትሁኑብን፡፡ራሳችሁን ቻሉ፡፡ማኅበረቅዱሳንን ተገን አድርጋችሁ ፖለቲካውን እያንቦጫረቃችሁ ማኅበሩን ጥርስ ውስጥ ከተታችሁት፡፡ቅድስት ተዋሕዶን የአንድ ብሔር ብቻ አስመሰላችሁብን፡፡ያላዋቂ ሳሚ ሁላ!!ራሳችሁን ቻሉ፡፡ያረጀና ያፈጀ የትምክህት ፖለቲካችሁን ሃይማኖት አትቅቡት፡፡አክራሪ ብሔርተኛ ከአክራሪ ትምክህተኛ በምታደርጉት ምውት የፖለቲካ እንካሰላንቲያ ቤ/ክ አይመለከታትም፡፡የዐውደምሕረቱ ሕግ አንዱን እንድትወግን አይፈቅድም፡፡
   ዐይንህን ክፈት እስኪ!!አቤቱታውን ለፓ/ኩ ያደረሱት አቡነ ጎርጎርዮስ ትውልዳቸው ትግራይ ነው፣የአቡነ ማትያስንም ታውቀዋለህ!!ሃይማኖቱን የአማራ ብቻ አስመስለህ ያላዋቂ ሳሚ አትሁንብን!!ስንትና ስንት ተቋማትንና ደቀመዛሙርትን ያፈሩትና በደርግ እጅ ከመጋዝ ጀምሮ ከሀገር-ሀገር እስከመሳደድ የደረሰ ሕይወት ገፍተው በክብር ያረፉት አባታችን አቡነ ጳውሎስ ደግሞ በእንደ አንተ አይነቱ አማተር አፍ ስማቸው ሊዘነጠል አይገባም፡፡ይከብዱኃል!!ዳሩ ምን ታረጉ "ስማችሁ የለም" እያሉ አባቶችን ደፍረው የሚያስደፍሩ እነ ዳንኤል ክብረት ናቸው!! ህም!!መድረኩን አንቦርቅቀው አባቶችን መዛበቻ ማድረግን ጌጥ አድርገውታል!!ህም!ተቆርቋሪነት በስድብ የሚገለጽበት ሃይማኖት የእኛ ብቻ ሳይሆን ይቀራል!!ባለንጀራው ቢያሸንፈው እልሁን በሚስቱ እንደተወጣው ባል ምድረ-ትምክህተኛ ፖለቲካው ሲያቅትህ ቤ/ክ ተጠልለህ ትቦጠልቃለህ፡፡ቆይ!!
   ስማ!!አባ ገብረ እንድርያስ የተፋለመው አማራጭ ስላልነበረው ነው፡፡እኛ ደብዳቤያችንን ጽፈን በክብር የተቀበለን ኃይል አለ፡፡የእሱን መልስ ሳንሰማ ካልተሰዋን-ካልተቀላን ማለት ጦር አውርድ መሆን ነው፡፡ዝም ብላችሁ አጋጣሚ እየጠበቃችሁ ተደብቆ የማይደብቅ ዘረኝነታችሁንና ፖለቲካችሁን አትደርድሩብን፡፡የትግራይ ኦርቶዶክሳዊነት ከአማራም ሆነ ከሌላው ብሔር ኦርቶዶክሳዊነት ያነሰ አይመስለኝም፡፡ወያኔ የወጣው ከዚህ ጽኑ አማኒ ማ/ሰብ ነው፡፡ደርሳችሁ ለሃይማት አልባው ደርግ እንኳ ያልሰጣችሁትን ስያሜ አትስጡ፡፡እስኪ ሰው ምን ይለናል በሉ!!
   እባካችሁ!!ተቋሙ በሰከነ መንፈስና በኃላፊነት የያዘውንና በንግግር ሊፈታ መንገድ የያዘውን አጀንዳ እየጠለፋችሁ የፖለቲካችሁ ማጩዋጩሂያ አታድርጉብን!!ባልተገራ ልሳን ለአክራሪ ብሔርተኞች ጭድ አቀባይ አትሁኑብን!!መጠለያና ደወል ስር ተቀምጣችሁ እየቦጠለቃችሁ ቅጽራችንን አታስደፍሩ!!ከቻላችሁ ሜዳው ሰፊ ነው!!ሀገሩ ትልቅ ነው!!ታገሉ!!ተዋጉ!!ቤቱ ግን የጸሎት ቤት እንጅ የጸብ አይደለም!!የእሬቻ ማክበሪያም አይደለም!! ሁልሽም ለቀቅ!!ልቀቁን!!ተፋቱን!!

   Delete
  2. Brother you are not uderstand the context of the srticles or you are outside the circle. Ready again and sgain or do not to attack personally. Zelabediki, sorry to say!

   Delete
  3. Aha Semegnew, menew TPLF sineka amemeh, Egna eskemnawkew ye Ethiopian Hizb zeregnet yastemarew, bezer yemiyabalaw, Betechristianen selam yasataw TPLF new, musegneten ena lebeneten yemiyaberetata new. Ene kemotku serdo aybekel new! Abo lekek Adergen!!!!!!

   Delete
  4. Mr. Simegnew: You go and tell this rubish idea to your protestant and Tehadiso followers.

   Delete
  5. ምነው ወንድም ሃሳብን እንጂ ሰውን አትቃወሙ እያልክ አንተው ሰውን ከመቃወም አልፈህ ዘላበድክ ማለትህ?! ከላይ ከጻፉት ከሁለቱ ለየትኛው እንደጻፍክ እንኳን ግልጽ አይመስለኝም ለማንኛውም ወንድሜ ይሄ ድህረ ገጽ መማማሪያና ሃሳብን በነጻነት ማንሸራሸሪያ መሆኑን ብትረዳው ጥሩ ነው። የሰውን ክብር መንካት የራስን ያስነጥቃል ሲባል አልሰማህም እስኪ አንተም ደጋግመህ አንብበው እርግጠኛ ነኝ እራስህን ትታዘበዋለህ። በመጨረሻም ለአባባልህ ይቅርታ መጠየቅህም ያዋቂ አጥፊነትህን አይመሰክርብህ ይሆን?
   ማስተዋሉን ይስጠን!!!
   ቸር እመኛለሁ!!!
   ብላቴናው

   Delete
  6. ይህንን ያኽል ነገር የተጠናወተው ጽሑፍ መጻፍ ከቻልክ እንዴት ቁልጭ ብሎ የተጻፈን ነገር መረዳት አቃተህ? እኔ ግን አይመስለኝም? የሰው ልቦና ስለ አንድ ነገር መረዳት ከደነደነ ላም ባልዋለበት ኩበትን ይለቅም ዘንድ ይሻል …………. ምናልባትም ወንድሜ ሆይ እውነት ሲነገራቸው ከሚሸሹ አልያም ስማቸው ከሌሉት ወገኖች ትኾንን? ……. ለኹሉም ግን የመጣውን ፈተና አምላከ ቅዱሳን በቸርነቱ ይመልስልን የምናስተዉልበትን ልቦና ይስጠን ፡፡

   Delete
 38. ዳኒ በእዉነት በጣም የሚያሳዝን ድርጊት የዋሁን ወገኔን ክፉ ሀሳብ ይዘዉ ወደማይፈለግ ጥፋት ለመግፋት
  የሚንቀሳቀሱትን የወቅቱ የክፋት አራማጆች በአስተዋይ ልቦና ልንከላከላቸዉ ያስፈልጋል ይህ አካሄድ ለመንግስትም
  የማይጠፋ እሳት እንዳያስነሳ ሊያስብበት ያስፈልጋል

  ReplyDelete
 39. ይህን ፈተና ለመወጣት በስሙ ሳይሆን በግብሩ ሙሉ የሆነ አንድ ክርስቲያን ካለ በቂ ነው :: / በቅርቡ ራሱን ለሰይፍ እንደ ሰጠው የ ቻድ ዜጋ ማለቴ ነው/ "በመሰረቱ የአማኒያን ልመና መሆን ያለበት ወደ አለሙ መንግስትና አሰራሩ ሳይሆን ወደ ሰማያዊው መንግስትና አሰራሩ ነው::" ግብራችን ብቻ ሊያወጣ ባለበት በዚህ ዘመን የቅዱሳን አምላክ ጽናቱን ይስጠን::

  ReplyDelete
 40. እዚህ አካባቢ ከ700 ዓመታት በፊት የነበሩ ዜጎች አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲመጡ ‹ኦቦ› ብለው ተቀበሏቸውእንጂ ‹ሀገርዎ አይደለም ይውጡ› አላሏቸውም፡፡ ዛሬ በሥልጣን ላይ ካሉትና ገዳሙን በኢሬቻ መተካት ከሚፈልጉት ሰዎች ይልቅ ያኔየነበሩት ሰዎች ልበ ሰፊዎች፣ አስተዋዮች፣ የሰውነት ክብር የገባቸው፣ የሀገርን ትርጉም የተረዱ፣ ከዘር ይልቅ ለሰውነት ታላቅ ቦታየሚሰጡ፣ ሰውን በምግባሩ እንጂ በቋንቋውና በቀለሙ፣ በዘሩና በአጥንቱ የማይለኩ ነበሩ፡፡

  ReplyDelete
 41. የዚህ ዘመን ፈተና - እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን::

  ReplyDelete
 42. እዚህ አካባቢ ከ700 ዓመታት በፊት የነበሩ ዜጎች አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲመጡ ‹ኦቦ› ብለው ተቀበሏቸውእንጂ ‹ሀገርዎ አይደለም ይውጡ› አላሏቸውም፡

  ReplyDelete
 43. ebakachu those TPLF gorella fightres , ebakachu amhara/neftegna/ bemalet hezbun ketweldu yatefachut yibekal....betam asgeraminegernew!!! we know the agenda of MAH
  LELET program of TPLF, i think its better to pray to God.

  ReplyDelete
 44. ውንድም ዳንኤል፡ ምንም እንኳን የምሰጥህ ሃሳብ የመጨረሻ አንስተኛ እና እዚህ ግባ የማትባል ብትሆንም ፣ ያው በድፍረት ልወረውራት ደፈርሁ። ቢቻል ትጠቅምህ ይሆናል ባይቻል ግን ለትዝታ ስትል ብቻ አንብብልኝ…

  እንደ አንድ የቤተክርስቲያኗ ልጅ ፣ በአገሬ እና በቤተክርስቲያኔ ላይ የሚደርሰው ጥቃት ፍጹም ያንገበግበኛል። በኢትዮጵያ ምድር ላይ ፣ በዚህ ዘመን ፣ የጥቃቶች ሁሉ ከባድ መከራ እየወረደበት ያለው ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክስነት ነው ብየ አምናለሁ። ጥቃቱ ሁሉ ተቀምሞ የሚለቀቀቅው ከወቅቱ ገዥ ፖለቲከኞቻችን ቢሆንም ፣ ትልቁ የአጀንዳቸው ፈጻሚና አስፈጻሚዎች ግን እኛው “በኢትዮጵያዊነት እንኮራለን” ብለን የምንምል የምንገዘት ኦርቶዶክሶች ነን።

  ብዙዎቹ የመከራው ተባባሪዎቹ ተራ ኢትዮጵያውያን መጠለፊያ ምክንያቶችም ለጊዚያዊ ጥቅም መደለል ፣ የግንዛቤ ማነስና የርስበርስ መመቃቀኝ ሲሆን ፤ የተራ አጥፊ ዜጎችን እንዲባባስ እያደረገ ያለው ግን ፣ አንተን ጨምሮ ፣ ሰፊ የመድመጥ እድል ያላችሁ የቤተክርስቲያኗ ሰባኪያን ፣ ዘማሪያን ፣ ቀሳውስት ፣ አስተዳዳሪዎችና ጳጳሳት የያዛችሁት ያልጠራ ሃሳብ ነው።

  ዛሬ ይህን የምጽፈው ግን ለአንተ ነውና እራስህን የምትጠይቅበት ሃሳቤን ልሰንዝር። በተለያዩ ማህበረሰባዊ ዝቅጥታችን እና የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መጣመምን አስመልክቶ ፣ በልዩ ጸጋህና በሞላህ እውቅትህ ተደግፈህ ብዙ አስነብበኸናል። አንድ ግን ትልቅ የሳትህኸው ሃቅ አለ። የአንድ አገር ዜጋ ላይ የሚነበቡ ማህበራዊ ቀውስን ተከትሎ ፣ ቅዱሳንንን የትግሬዎች ወይም የጎንደሮች … ከመባባል አንስቶ ፣ ቀኖናን በመናድ ሃውልት በህይወት እያሉ ማሰራትን ስትተች ፣ ሁላችንም ደስ ብሎን አንብበን አመስግነንህ አልፈናል።

  ዋልድባ ታረሰ ፣ አውደምህረት ተደፈረ ፣ ሰው በዘር ተባላ ፣ ማህበረ-ቅዱሳን አላግባብ ተወነጀለና ተፈረደበት ፣ ዝቋላ … እያሉ በዜና ዙሪያ መድከም ፣ የሸረርሪትን ድር እየጠረጉ መኖር ነው። ዋናው ቁምነገር ያለው ግን ፣ የኢትዮጵያዊነትና የኦርቶዶክስነት የጥፋት ምንጭ የሆነውን ስርዓት በአንድ ጎን እየደገፉ በሌላ በኩል ስራውን ለመንቀፍ መሞከሩ ላይ ነው። ለምሳሌ አንተ ቀጣይ ሶስት ወሳኝ የሆኑ አገራዊ አጀንዳዎችን አስመልክቶ ፣ ግልጽ በሆነ መንገድ ስትደግፍ ይስተዋላል… ግን ሶስቱም እርስ በ እርስ ይጣረሳሉ።

  1) የውጭውን ሲኖዶስ ታወግዛለህ
  2) የአባይ ግድብ አገራዊ አጀንዳ ነው ብለህ ታምናልህ
  3) ማህበረቅዱሳን በሰጠው ተግባራዊ አስተዋጽኦ ተገቢውን ክብር ማግኘት አለብት ትላልህ

  እነዚህ ሶስቱም ግን እርስ በ እርስ ይጣረሳሉ። የውጭው ሲኖዶስ ህዝባዊ ይሁንታ በሌለው አገዛዝ ትዕዛዝ ከአገር ቤት የተባረረ እና በውጭው ያለውን ኢትዮጵያዊ ሸክፎ ያዳነ ሲሆን ፤ የአባይ ፕሮጀክትም ህዝባዊ ተጠያቂነት በሌለው የፖለቲካ ግሩፕ የተጠነሰሰ ቅዠት ሆኖ ማህበረቅዱሳን ደግሞ እራሱ አገዛዙ በሚያረቅቀው የማጥፊያ ወጥመድ እየተተበተበ ያለ መሆኑን ፣ ለማንም ድብቅ አይደለም።

  ታዲያ ፣ ማንም ሰው እንደ ተራ ዜጋ ፣ በማንኛውም አጀንዳ ላይ አስተያየቱን ቢያሰፍር ምንም ችግር የለውም። የአንተ አይነት ፣ በርካታ አንባቢ እና አድማጭ ያለው ሰው ግን ፣ የሚያሰፍረው ሃሳብ እና የሚያደርገው እንቅስቃሴ ጥንቃቄ ካልተላበሰ ፣ ዞሮ ዞሮ ጥፋት ነው። ለዚህ ነው ፣ ሌላው ተራ ሰው ጥፋቱን እንዲያበርክት እያደረገ ያለው የአንተ አይነት የመሪነት ሚና ላይ ያላችሁ ሰዎች ያላችሁ እርስ በ እርስ የሚጋጭ የሃሳብ ገጽታችሁ ነው የምልህ።

  ሰላም ሁን
  Michael Canda

  ReplyDelete
  Replies
  1. እስኪ የውጪው ሲኖዶስ አንዴት ተዋህዶን ኣስጠብቆ አንደኖረ ያስረዱን?
   ያባይ ጉዳይስ በማንም ዪታሰብ ይታቀድ ግን ለሃገር የሚጠቅም ነው ብለው ኣያስቡም?

   Delete
 45. amelak byeatkerstiyanene yetbekelen

  ReplyDelete
 46. ejig betam asafari new CHRISTIANNOCH maninetachin weyane siatefa zim anilim!

  ReplyDelete
 47. I wonder what the government wants to happen in the country. Are they fueling some kind of religious war andwant to come out as a hero after punishing both sides (or no matter how many factions will come out if this continues). The locals won't have any intention of overturning this historic monastery. this kind of inflammatory concept comes some Cadres in the local government looking for an opportunity to steal the hearts and minds of people in the name of 'ethnic patriotism'. I wish the locals (the people) could sit down and talk...iron out their difference and come up with a working solution ( Non politicized, practical solution).

  ReplyDelete
 48. አንብቦ ለመረዳት እግዚሃብሔር አይነ ልቦናችንን ይክፈትልን አሜን!!በተቻለን መጠን መልዕክቱን ደጋግመን ለማንበብ እንሞክር፠

  ReplyDelete
 49. ተግተን እንጸልይ....... አምላካችን ለቅዱሳን አባቶቻችን የገባላቸውን ቃል አይረሳም። ቤተክርስቲያናችን ብትናወጽ እንጂ አትወድቅ/አትጠፋ። ጸንተን እንቁም።
  ይህን እኩይ ተግባር ያሰቡትን ልቦና ይሥጥልን። የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን...አሜን!!!

  ReplyDelete
 50. oh!! this is a complete disregard of the right religion of the people,because the goverment is in a way to determine the place of worship for agiven religion in favor of the other.more over,this is the act of initiating a conflict between the peoples who are living together in good faith. how can the governement allienate the worship place of a given religios inistitution? this is the awkward of the government.so,it is better for the government to shorten its hand from intervininig in religious matter.

  ReplyDelete
 51. Be and(1) Bete Mekdes Hulet Amlak Ayimelekim. Deacon Dani, Libin yemiyasdest Melikit( Message) New: Lib Yalew Lib Yibel. Egziabher Bi Fekid Hedalew Megabit 5 Zikuala. Eziyaw Enigenagn Gobez

  ReplyDelete
 52. ABETU AMLAKACHEN ABETU ZEM ATBEL!!!! EMBREHAN AMALJETU EGZIO LIJESHEN ASASBILEN KIDANE MEHRET EGZIOOO!!!!!:(:(:( ye degaguchu ZEM ATEBEL:(:(:(

  ReplyDelete
 53. ሁሉም ተመሳሳዩን ፍለጋ ከሄደ መጨረሻው ግለሰብ ነው፡፡

  ReplyDelete
 54. Hello Daneil,
  The remedy forr the problem is removing Woyane Racist from the power. But, you are still (for the last 20 years) beating around the bush. This is your reallity!! What are you going to do? Continue to ignore the real source of the problem?

  ReplyDelete
 55. ውድ የወንጌል ሰባኪ ሆይ! ሉሲ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወዘተ… አይደለችም ብለሃል፡፡ ሳይንሱን ባለማወቅህ አንተ ተሳስተህ ምዕመናንን እያሳሳትክ መሆንክንና ከወንጌላዊ የማይጠበቅ ጥፋት እየፈጸምክ መሆንክን ላስረዳህ እሻለሁ፡፡ አገር ወዳድነት ሌላ በእምነት መቀለድ ሌላ፡፡
  ከቀደመ ነገር ሉሲ ሰው አይደለችም፡፡ She is an ape. ጦጣ ደግሞ ብሔረሰብ የለውም፡፡ ሉሲ ተበላ የተሰየመችው ሰው ስለሆነች ሳይሆን በግኝቱ ወቅት ፌሽታ ሲያደርጉ ይዘፈን የነበረው ዘፈን "Lucy in the Sky" ስለነበረ ነው፡፡ በኢቮሉሽን አማኞች ትንተና መሰረት ሰው ከጦጣ ዝርያ ወደሰውነት ሲለወጥ ያለፈበት Australopithecus afarensis በተባለችው የጦጣ ዘር በሉሲ ዓይነት ፍጡር ነው፡፡ Australopithecus afarensis ሌላ ፍጡር ነው፡፡ Homo sapien ሌላ ፍጡር ነው፡፡ እኛ Homo sapien ነን፡፡ እኛ ሰው ነን፡፡ ሉሲ ግን ሰው አይደለችም፡፡
  በቤተመቅደስ መድረክ ላይ ቆመህ እኛ በአርአያ ሥላሴ ተፈጠርን ብለህ ታስተምራለህ፡፡ እዚህ ደግሞ አገር ወዳድ ለመባል ሉሲ ሉሲ እያልክ ታደነቁረናለህ፡፡ እባክህ ታረም፡፡ ቲፎዞዎችህን ሳይሆን ሥላሴን አክብር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. u ediet forget about lucy and think about the real fact ante d\n danieln lemenager first ante man nek ? devil? protestant ? or what?

   Delete
  2. betam yemigerm ye lucy tintanie yihen silawerh Danieln beltkew! wondimie meyaz yalbihe mulu hasabun enge . ebakihe yemitsfewn ewoke. guregna neh bado

   Delete
  3. Good Observation!! Thank you!!

   Delete
  4. ጤና ይስጥልኝ!

   በመጀመሪያ ሁላችንም የብዕር ዓይነት ስም ቢኖረን በትክክል ለዕከሌ እያልን ለመጻፍ የሚያስችል ይመስለኛል።
   (ውድ የወንጌል ሰባኪ ሆይ) ብለህ ሃሳብህን የሰነዘርከው ወንድሜ፤ የሳፍከው መልዕክት ዘለፋ አዘል ባይሆን ምንኛ ጥሩ ነበር። ይህ ዓይነት ማህበራዊ ድህረ ገጽ መማማሪያና ሃሳብን ማንሸራሸሪያ በሆነ መልኩ ማየትና መገንዘብ ጥሩ ይመስለኛል። ማንኛችንም ብንሆን ከዚህ አሉታዊ (ኔጋቲቭ) አመለካከት የጸዳን ነን ለማለት አልደፍርም። እኔ ግን ከስሜት ነጻ በመሆነ መንገድ መጻፍ ቢያንስ ለህሊና እረፍት ስለሚሰጥ እራሳችንን መግዛት ብንጀምር ጥሩ ነው ለማለት እወዳለሁ። አንተ በስሜት በመጻፍህ ሌሎቹንም በስሜት እንዲጽፉ ያደረገ ይመስለኛል። ሰው ሃሳቡ እንጂ ማንነቱ አይነቀፍም በተጨማሪም ሰውን አለማክበር የራስን ክብር ባጣጣል አይሆንም ትላለህ?

   ቸር እመኛለሁ!

   ብላቴናው

   Delete
  5. መጽሐፍ ከተሰወረ ፍቅር የተገለጠ ዘለፋ ይሻላል ይላል፤ ምሳሌ 27፡5፡፡
   ቄሱ፣ መነኩሴው፣ ጳጳሱ፣ ሰባኪው ሁሉ ነገር አሳመርሁ ብሎ ሉሲ ሉሲ ሲል አያስቆጣምን?

   Delete
 56. ye eminetu teketayi ye honik be wuchim be hageri wusitim yalew betekiritiyan andi natina kitirin atasidefir betselot egiaberin teyik wede esu alikis lesu yemisanew yelemina
  hulachinim egizaber yirdan amen

  ReplyDelete
 57. bereget lucy sew ayedelechem gen mediawochachen Ysew zer megegnea eyalu sebekun. bereget ye Antropology professor Ethiopia the birth place of all human binges eyalu adekunune ayedel? danielem eko hulun awek ayedelem! melekotawim ayedelem! memerochu፣ mediaw Yastemarewun zeref enji.

  ReplyDelete
 58. ጤና ይስጥልኝ!

  በመጀመሪያ ሁላችንም የብዕር ዓይነት ስም ቢኖረን በትክክል ለዕከሌ እያልን ለመጻፍ የሚያስችል ይመስለኛል።
  (ውድ የወንጌል ሰባኪ ሆይ) ብለህ ሃሳብህን የሰነዘርከው ወንድሜ፤ የሳፍከው መልዕክት ዘለፋ አዘል ባይሆን ምንኛ ጥሩ ነበር። ይህ ዓይነት ማህበራዊ ድህረ ገጽ መማማሪያና ሃሳብን ማንሸራሸሪያ በሆነ መልኩ ማየትና መገንዘብ ጥሩ ይመስለኛል። ማንኛችንም ብንሆን ከዚህ አሉታዊ (ኔጋቲቭ) አመለካከት የጸዳን ነን ለማለት አልደፍርም። እኔ ግን ከስሜት ነጻ በመሆነ መንገድ መጻፍ ቢያንስ ለህሊና እረፍት ስለሚሰጥ እራሳችንን መግዛት ብንጀምር ጥሩ ነው ለማለት እወዳለሁ። አንተ በስሜት በመጻፍህ ሌሎቹንም በስሜት እንዲጽፉ ያደረገ ይመስለኛል። ሰው ሃሳቡ እንጂ ማንነቱ አይነቀፍም በተጨማሪም ሰውን አለማክበር የራስን ክብር ባጣጣል አይሆንም ትላለህ?

  ቸር እመኛለሁ!

  ብላቴናው

  ReplyDelete
 59. seifemichael zeejereMarch 9, 2015 at 9:04 PM

  ሁሉንም ፅሁፍ አየሁት፡፡ ኢትዮጵያውያን እንዲህ አይነት የተዘበራረቀ አመለካከት ያለን አይመስለኝም ነበረ፡፡ ያውም በአንድ ሃይማኖት ኦርቶዶክሳዊነት ስር ያለ፡፡ ሰውን ዘረኛ እያለ እርሱ ግን ሌላውን ዘር ከኢትዮጵያ ምድር ሊያጠፋ የተነሳ፡፡ የእኔን ልግለፅ፡፡ እኔም አማራም ኦሮሞም ነኝ፡፡ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወገኔ ነው ብዬ የማምን ነኝ፡፡ በፖለቲካ እምነቴ ኢሕአዴግን በፅናት እደግፋለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ልማትም ሰላምም ያመጣል ብዬ አምናለሁ ደግሞም እያመጣ ነው፡፡ እያንዳንዱን ነገር አንብቤ እና አምኜ እንጂ ለመለጠፍ አይደለም፡፡ በሃይማኖቴ ኦርቶዶክስ ስሆን ሁለት ሲኖዶስ እንዳለን አላምንም፡፡ የሚመራን ሲኖዶስ በሀገር ቤት ያለው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በኮሌጅ ህይወቴ ማህበረ ቅዱሳን ሃይማኖቴን እንዳውቅ ያሰባሰበኝ፣ ለቤተክርስቲያን ብዙ መልካም ስራ እንድሰራ ያገዘኝ እስከዛሬም በጊዜዬና በገንዘቤ የምደግፈው በመንግስት ስልጣን ስር ተጠልለው ሌላ ስም በመስጠት ሊያስወግዙና ሊያስጠፉ የሚሞክሩት እነሱ እንደሚሉት እንዳልሆነ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ማህበሩን ለተለያየ ፖለቲካዊ አጀንዳ ለማዋል ሲሞከር አላማውን በትክክል በተረዱ ወንድሞች ጥረት መስመሩን ሳይለቅ እስከዛሬ ያለ ነው፡፡ አንድ ግርግር በተነሳ ቁጥር ማህበረ ቅዱሳኖች ናቸው እንዲህ የሚያደርጉት እየተባለ ባልሆነው ሲወቀስ፣ አንዳንዱም እውነታውን ሳያጣራ እርምጃ ለመውሰድ ሲንደረደር ሁሉ የታየበት ነው፡፡ ማህበር እንደ ማህበር የመንግስትን ስርዓት ስላከበረ የኢሕአዴግ ደጋፊ፣ አንዳንድ አባላቱ ደግሞ መንግስትን ስለሚቃወሙ የተቃዋሚ ደጋፊ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፡፡ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ያለን የፖለቲካ መስመራችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ሃይማኖታዊ መስመራችን ግን አንድ ነው፡፡ እኔ ኢሕአዴግ ነኝ፡፡ ሌላው ከተቃዋሚ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ አይንህን አልየው መባባል አይቻልም፡፡ በማህበሩ ያሰባበሰበን አጀንዳ ማህበሩ የያዛቸው አላማዎች እንጂ ሌሎች አይደሉም፡፡ ስለዚህ ይህን የኔን አመለካከት እንዲከበርልኝ እፈልጋለሁ፡፡ የጨዋ ተቃዋሚ አስተያየትም አከብራለሁ፡፡ ይሰቀል ይወገር አልልም፡፡ ወደ ዝቋላ ገዳም ጉዳይ ስመጣ ዝቋላ ታሪካዊ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሃብት ነው፡፡ ይህንን የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ሊጠብቁት እንጂ ሊያፈርሱት አይገባም፡፡ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በፅሞና ተመልክተውት ለህዝብና ለሀገር ሰላም ሲባል፤ ለሀገር ቅርስ ደህንነትም ሲባል እስከዛሬ ያለውን ታሪክ ሊጠብቁት የጎደለውንም ሊያሟሉለት ይገባል፡፡ የማይመች መንገዱንም ቢቻል በጀት መድበው ሊሱለት ልማቱንም ሊደግፉት ይገባል እንጂ እውቅና ነፍጎ ለሌላ እምነት እንዲውል መፍቀድ ትክክል አይደለም፡፡ ከአፍ እስከአፍንጫቸው ርቀት ብቻ ከሚያስቡ እንጂ ከአስተዋይ መሪ አይጠበቅም፡፡ እስኪ ፍልስጥኤምና እስራኤልን እንመልከት፡፡ የፍልስጥኤም መንግስት እምነቱ ክርስትና አይደለም፡፡ ነገር ግን ቅድስት ኢሩሳሌምን ያከብራል፡፡ መሀሙድ አባስ ለፋሲካ እየተገኙ አብረው ያከብራሉ እንጂ የናንተ አይደለም አይሉም፡፡ እስራኤልም እምነታቸው አይሁድ ቢሆንም ታከብራለች፡፡ ታዲያ ዝቋላ ገዳምን በዚህ ልክ ማክበር እና ማሳደግ ብዙ ህዝብ ወደዚያ እንዲመጣ ማድረግ ሲገባ ለጠብ መዘጋጀት ምን ይባላል፡፡ ይህ የጤንነት አይደለም፡፡ ይህ በፍጥነት ይታረማል ብዬ አምናለሁ፡፡ አጋጣሚውን ጠብቀህ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የተዘጋጀህ ግን ታፍራለህ ሁሉም መልክ መልክ ይይዛል፡፡ ይህ ለምርጫ ፍጆታ የሚውልም አይደለም፡፡ የኦሮሞ ብሄርን ከሌላው ኢትዮጵዊ ጋር የምታገናኘውን እያንዳንዷን ክር አልሞ በመበጠስ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ለማሰኘትና ለማለት ቀን ከለሊት የሚሰራ፣ ይህም አካል መንግስትም ውስጥ የተደበቀ ከውጭም ያለ ማን እንደሆን ስለሚታወቅ ታግለን እንወጣዋልን፡፡ አምላካችን ሀገራችንን ይባርክ፣ ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጤና ይስጥልኝ ሰይፈስላሴ

   እጅግ በጣም ሚዛናዊና በሳል አስተሳሰብ ያለህ ሰው ነህ ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ሚዛናዊነት የትም ፣ መቼም ፣ ለማንም ፣ ለምንም ወዘተ እጅግ ጠቃሚና ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚችል አስተሳሰብ ነው። ይህም ከቀናነትና ከበጎ አመለካከት የሚመነጭ ይመስለኛል። በተለይ ይህ አገላለጽህ ሁሉንም የሚያግባባ ይመስለኛል፥
   1. "*ማህበር እንደ ማህበር የመንግስትን ስርዓት ስላከበረ የኢሕአዴግ ደጋፊ፣ አንዳንድ አባላቱ ደግሞ መንግስትን ስለሚቃወሙ የተቃዋሚ ደጋፊ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፡፡ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ያለን የፖለቲካ መስመራችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ሃይማኖታዊ መስመራችን ግን አንድ ነው፡፡ እኔ ኢሕአዴግ ነኝ፡፡ ሌላው ከተቃዋሚ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ አይንህን አልየው መባባል አይቻልም፡፡ በማህበሩ ያሰባበሰበን አጀንዳ ማህበሩ የያዛቸው አላማዎች እንጂ ሌሎች አይደሉም፡፡ ስለዚህ ይህን የኔን አመለካከት እንዲከበርልኝ እፈልጋለሁ፡፡ የጨዋ ተቃዋሚ አስተያየትም አከብራለሁ፡፡ ይሰቀል ይወገር አልልም፡፡
   2.*"ዝቋላ ታሪካዊ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሃብት ነው፡፡ ይህንን የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ሊጠብቁት እንጂ ሊያፈርሱት አይገባም፡፡ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በፅሞና ተመልክተውት ለህዝብና ለሀገር ሰላም ሲባል፤ ለሀገር ቅርስ ደህንነትም ሲባል እስከዛሬ ያለውን ታሪክ ሊጠብቁት የጎደለውንም ሊያሟሉለት ይገባል፡፡ የማይመች መንገዱንም ቢቻል በጀት መድበው ሊሱለት (ቢሰሩት) ልማቱንም ሊደግፉት ይገባል እንጂ እውቅና ነፍጎ ለሌላ እምነት እንዲውል መፍቀድ ትክክል አይደለም፡፡*"

   ፈጣሪ እንዲህ ዓይነት ሚዛናውያን ሰዎችን ያብዛልን!!!

   Delete
 60. ጤና ይስጥልኝ Seifemichael zeejere

  እጅግ በጣም ሚዛናዊና በሳል አስተሳሰብ ያለህ ሰው ነህ ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ሚዛናዊነት የትም ፣ መቼም ፣ ለማንም ፣ ለምንም ወዘተ እጅግ ጠቃሚና ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚችል አስተሳሰብ ነው። ይህም ከቀናነትና ከበጎ አመለካከት የሚመነጭ ይመስለኛል። በተለይ ይህ አገላለጽህ ሁሉንም የሚያግባባ ይመስለኛል፥
  1. "*ማህበር እንደ ማህበር የመንግስትን ስርዓት ስላከበረ የኢሕአዴግ ደጋፊ፣ አንዳንድ አባላቱ ደግሞ መንግስትን ስለሚቃወሙ የተቃዋሚ ደጋፊ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፡፡ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ያለን የፖለቲካ መስመራችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ሃይማኖታዊ መስመራችን ግን አንድ ነው፡፡ እኔ ኢሕአዴግ ነኝ፡፡ ሌላው ከተቃዋሚ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ አይንህን አልየው መባባል አይቻልም፡፡ በማህበሩ ያሰባበሰበን አጀንዳ ማህበሩ የያዛቸው አላማዎች እንጂ ሌሎች አይደሉም፡፡ ስለዚህ ይህን የኔን አመለካከት እንዲከበርልኝ እፈልጋለሁ፡፡ የጨዋ ተቃዋሚ አስተያየትም አከብራለሁ፡፡ ይሰቀል ይወገር አልልም፡፡
  2.*"ዝቋላ ታሪካዊ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሃብት ነው፡፡ ይህንን የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ሊጠብቁት እንጂ ሊያፈርሱት አይገባም፡፡ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በፅሞና ተመልክተውት ለህዝብና ለሀገር ሰላም ሲባል፤ ለሀገር ቅርስ ደህንነትም ሲባል እስከዛሬ ያለውን ታሪክ ሊጠብቁት የጎደለውንም ሊያሟሉለት ይገባል፡፡ የማይመች መንገዱንም ቢቻል በጀት መድበው ሊሱለት (ቢሰሩት) ልማቱንም ሊደግፉት ይገባል እንጂ እውቅና ነፍጎ ለሌላ እምነት እንዲውል መፍቀድ ትክክል አይደለም፡፡*"
  ታዲያ ምን ያደርጋል እንዳንተ አይነት ቅን አስተሳሰብና በጣም ጥቅቶች ናቸው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hello D/n Daneal,betem ewunet new..gin tiwuldu minyarg bileh new..EPRDF..MEKEFAFEL bemigaba astemarun..EGIZABHER libona yistachew elalehu..betinish adebete,,Thank you

   Delete
 61. የመጨረሻው ዘመን አስጨናቂ ይሆናል የተባለው እየደረሰ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከምንሰማው መልካም ዜና ይልቅ አስጨናቂው ዜና ይበዛል፡፡ ለዋልድባ ያለቀስነው እንባችን ሳይደርቅ ደግሞ በዝቋላ በኩሉ ዞሩ!? ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ለአገሪቱ ወደ ኋላ መቅረት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂናት ሲሉ ተደምጠዋል ምናልባት ለዚህ ይሆን የሃይማኖታችን አምድ የሆኑትን ገዳማት ለመድፈርና ለማፍረስ የተነሱት፡፡ እግዚአብሔር የሰይጣንን ሐሳብ ያፍርስልን

  ReplyDelete