Friday, February 20, 2015

ሦስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተጀመረ

ለሁለት ተከታታይ ጊዜ የተካሄደው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት የ2007 የምርጫ ሂደት የካቲት 12 ቀን 2007 ዓም በካፒታል ሆቴል በተዘጋጀ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተጀመረ፡፡  

ጋዜጠኞች፣ የቀድሞ ተሸላሚዎችና እጩዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተከናወነው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ስለ በጎ ሰው ሽልማት ያለፉት ዓመታት ክንዋኔዎችና ያመጣቸውን በጎ ተጽዕኖዎችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል፡፡ የሽልማት ኮሚቴው አካላት እንደገለጡት 2007 ዓም የሽልማት ሂደት ካለፉት ዓመታት በተለየ በ10 ዘርፎች የሚከናወን ሲሆን ሂደቱ ተጠናቅቆ ሽልማቱ የሚሰጠው በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከጥቆማው በኋላ የእጩዎችን ዝርዝር መግለጫ የማዘጋጀት ሥራ የሚሠራ ሲሆን፣ በመቀጠልም በየሞያው ዕውቀትና ብስለት ባላቸው ሰዎች በተቋቋ ቡድኖች የመጀመሪያ አላፊዎች የመረጣ ሥራ ይከናወናል፡፡ በመቀጠልም ማጣሪያውን ላለፉት የሕይወት ታሪክ ዝግጅት ሥራ ይከናወናል፤ በማስከተልም ቦርዱ የመጨረሻዎቹ ተሸላሚዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

ለጠቋሚዎች የተሻለ ዕድል ለመፍጠር የኢሜይል፣ የስልክ፣ የፖስታና የገጸ ድር የመጠቆሚያ መንገዶች የተዘጋጁ ሲሆን፣ የበጎ ሰው ገጸ ድር እዚያው በእዚያው(አውቶማቲክ) የሆነ የእጩ መጠቆሚያ ቅጽ ዝርዝር መረጃዎችን ይዟል፡፡

ለሀገራቸውና ለወገናቸው የሠሩ፣ አኩሪ ገደል የፈጸሙ፣ ለትውልዱ አርአያ የሚሆኑና የሀገራቸውን ክብር ከፍ ያደረጉ ዜጎችን በመጠቆም ሕዝቡ እንዲሳተፍ፤ ጋዜጠኞችና በማኅበራዊ ሚዲያ የላቀ ተሳትፎ ያላችሁ ዜጎች መረጃውን በማዳረስ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙም አትሞ በመስጠት ሁሉም እንዲተባበር ቦርዱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

 

የዕጩ መጠቆሚያ ዘርፎች
1.      ሰላም፡- በዚህ ዘርፍ ለሀገራዊ ሰላም፣ ለሕዝቦች መግባባት፣ ለግጭቶች መፈታት፣ ማኅበረሰቡ ላቅ ያለ ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ የሠሩ ይሸለማሉ

2.     ሳይንስ፡ በሕክምና፣ በቴክኖሎጂ፣በፊዚክስ፣ በኬሚስሪ፣ በምሕንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ ወዘተ የሠሩ ይሸለማሉ

3.   ኪነ ጥበብ በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች በአዲስ መንገድ፣ በልዩ አቀራረብ፣ የሥነ ጽሑፍን ደረጃ ከፍ ያደረጉ፣ በማኅረሰቡ ዘንድ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሥራ የሠሩ፣ ለኪነ ጥበባችን ዕድገት የተጉ ዜጎች ይሸለማሉ

ሀ. ፊልም
ለ. ሙዚቃ
ሐ. ሥነ ጽሑፍ
መ. ቴአትር
ሠ. ሥዕልና ቅርጻ ቅርጽ

4.     የበጎ አድራጎት ሥራዎች፡- በርዳታና ሰብአዊ አገልግሎት የሠሩ ይሸለማሉ

5.     ግብርና ንግድና የሥራ ፈጠራ፡- በንግድ(ቢዝነስ)፣ በግብርና እና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሥራዎች በመፍጠር፣ አዳዲስ የሥራ ሐሳቦችን በማመንጨት የሠሩ ይሸለማሉ

6.     ስፖርት፡- በስፖርቱ መስክ አርአያነት ያለውና በጎ ተጽዕኖ የሚያመጣ ሥራ የሠሩ ይሸለማሉ

7.     መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን መወጣት፡- በተመደቡበት መንግሥታዊ የኃላፊነት ዘርፍ አርአያ የሚሆን ለውጥ ያመጡና ተገቢውን ሕዝባዊ አገልግሎት የሰጡ

8.     ማኅበራዊ ጥናት፡ በማኅበራዊ ጥናት መስክ ተሠማርተው የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ ችግሮች የሚፈቱና አዳዲስ ግንዛቤ የሚያመጡ፣ ዕውቀት የሚጨምሩ ላቅ ያሉ ሥራዎችን የሠሩ ይሸለማሉ

9.     ሚዲያና ጋዜጠኝነት፡ በሚዲያና በጋዜጠኝነት መስክ ለውጥ አምጭና በጎ ተጽዕኖ አሳዳሪ ሥራ የሠሩ ይሸለማሉ

10.   ቅርስና ባሕል፡- ቅርስና ባሕልን በመጠበቅ፣ በማስተዋወቅ፣ በመሰነድና ዓለም ዐቀፍ ዕውቅና እንዲያገኝ በመሥራት ለውጥ ያመጡ ይሸለማሉ፡፡


የመጠቆሚያ መመዘኛዎች
1.      የሚጠቆመው እጩ በሕይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ሰው ወይም ተቋም መሆን አለበት
2.     የምንጠቁማቸው ኢትዮጵያውያን በጎ ለውጥ አምጭ የሆነ ሥራ የሠሩ መሆን አለባቸው፣
3.     የዜጎችን ሕይወት በማሻሻልና ሀገርን በማሳደግ ሊጠቀስ የሚችል ነገር ያከናወኑ መሆን አለባቸው፣
4.     አንድ ሰው በተለምዶ ሊሠራው ከሚገባው ወይም ከሚችለው ሥራ ላቅ ያለ ሰብእና የሚታይበት ተግባር የፈጸሙ መሆን አለባቸው፤
5.     በአሠራር፣ በአስተዳደር፣ በጥናትና ምርምር፣ በኪነ ጥበብና በማኅበራዊ አገልግሎት አዲስ መንገድ ያመላከቱ፣ አዲስ አሠራር የዘረጉ መሆን አለባቸው፣
6.     የሀገርና የሕዝብን ችግር የፈታ ተግባር የከወኑ መሆን አለባቸው
7.     በተሠማሩበት መስክ መሥዋዕትነት ጠያቂ ግዳጅን የተወጡ፣ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን የሰጡ መሆን አለባቸው
8.     ይሁነኝ ብለው የሀገርንና የወገንን ስም የሚያስጠራ፣ ታሪካችንን፣ ባሕላችንን፣ ቅርሳችንን አጉልቶ የሚያወጣ የዜጋ ሥራ የሠሩ መሆን አለባቸው
9.     የማኅበረሰቡን ሞራላዊና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን ለሌሎች መጥፎ ምሳሌ በሚሆን መንገድ ያልጣሱና  ለትውልዱ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው
10.   በተቻለ መጠን ከዚህ በፊት ሥራቸው ሊነገር፣ ሊዘከርና ሊታወቅ ያልቻለ
11.      ለሀገሪቱ ዕድገትና ሥልጣኔ ለውጥ አምጭ አስተዋጽዖ ያደረጉ
12.    ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ብቁ አመራሮችን የሰጡ፣ በአመራሮቻቸውም አካባቢያቸውን፣ ድርጅታቸውንና መሥሪያ ቤታቸውን የለወጡ፣
13.    አዲስ፣ የራሱ ወጥነት ያለውና ያልተደፈረ የሚመስለውን ሥራ ያከናወኑ፣
14.   የሀገሪቱን ክብርና ደረጃ ያስጠበቁ፣ የሀገሪቱንም መብት ያስከበሩ፣
15.    ሀገራቸውን በዓለም አደባባይ በበጎ ያስጠሩ፣ ስሟን ከፍ ያደረጉ

የመጠቆሚያ አድራሻዎች
              ስልክ፡- 0941615252
              ኢሜይል፡- begosew2007@gmail.com
              ገጸ ድር     www.begosew.com
             ፖስታ፡- 150035  
የመጠቆሚያው ጊዜ
ከየካቲት 13 እስከ መጋቢት 12 ቀን፣ 2007 ዓም ድረስ

 ዕጩዎችን በሚጠቁሙበት ጊዜ
1.      የተጠቋሚዎችን ሙሉ ስም ይጻፉ
2.     የሚገኙበትን ልዩ ቦታ ይግለጡ
3.     የሠሩትን ሥራ በአጭሩ ይግለጡ
4.     ስለ ተጠቋሚው ተጨማሪ መረጃ ሊገኝ የሚችልበትን ምንጭ ይጠቁሙ
5.     ከተቻለ የስልክና የኢሜይል አድራሻቸውን ይግለጡ
6.     የራስዎንም አድራሻ ይግለጡ(ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ)
7.     ስለሚጠቁሙት ዕጩ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጡን ከቻሉ በኢሜይል ወይም በገጸ ድራችን ያያይዙልን

18 comments:

 1. ጤና ይስጥልኝ

  ይህ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የበጎዎች ሁሉ በጎ ተግባር ነውና በርቱ ማለት እወዳለሁ። ለመሆኑ ዲያቆን ዳንኤል ከዚህ በፊት ተሸላሚ የነበሩትን መጠቆም የሚቻልበት አሰራር ይኖር ይሆን?
  ይህን እየተጠራጠርኩም ቢሆን ለመጠየቅ የቻልኩት ሽልማት በባህሪው ለበለጠ ስራና ሃላፊነት እንደማነሳሳቱ ከቀድሞ ተሸላሚዎች መካከል የላቀ በጎ ተግባር ያስምዘገቡ ዜጎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገመት ነው።

  ቸር እመኛለሁ!!!

  ReplyDelete
 2. መምህራችን ዲያቆን ዳንኤል በአብዛኛዎቹ ዘርፎች ግለሰቦችንና ተቋማትን መሸለሙ ለህብረተሰቡ ካለው ፋይዳ አንፃር ፣ ወደፊት የበለጠ መስራት ይችሉ ዘንድ ማበረታቻ ስለሆነ መልካም ነው፣ ግን ከዘርፎቹ አንዱ ዘፈንን ይጨምራል፣ ዲያቆን አንተ የቅዱስ ወንጌል መምህር ነህ፣ በጥኡም አንደበትህ እጅግ ብዙ ክርስቲያኖችን ወደ ህይወት መንገድ አምጥተሀል፣ እናም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች አንተን ፣መልካም የሆነውን የክርስትና ህይወትህን አርአያ አድርገው በዚህ ፈተና በበዛበት አለም ይኖራሉ ፣ ስለዚህ ዘፋኞችን መሸለሙ ዘፋኝነትን ማበረታታት ስለሆነ ከክርስትና አንፃር ሲታይ መልካም እንዳልሆነ ይታወቃል፣ ክርስቲያኖች ዲያቆን ዳንኤልን የሚያዩት መንፈሳዊ መሆኑን ነው ፣ ስለዚህ ከዚህ አንፃር የዘፈን ዘርፍ ሽልማት እንደገና ቢታሰብበት???

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጤና ይስጥልኝ ወንድሜ ማሩ! የመንፈሳዊ አስተሳሰብህ ጥሩ ነው። ነገር ግን እኔ እንደሚገባኝ ይህ የበጎ ሰው ሽልማት በግለሰብ የሚመራ ሳይሆን በቡድን (በቦርድ) ስለሆነ አገራዊ እንጂ መንፈሳዊነትን ማነጻጽር የሚቻል አይመስለኝም። እኔ ይህን ብልም የዲ/ን ዳንኤል ምላሽ ምን እንደሚሆን እጠባበቃለሁ በዚያውም ግምቴ ምን ያህል ትክክል እንደሆነ ለማወቅ ይረዳኛል።

   ቸር እመኛለሁ!!!

   Delete
  2. Wondime Maru: Do you know that there are lots of Non spiritual singers who built more number of churches that we can't? help the poor? go for mahlet and kidasse?

   Delete
  3. አማተሩ ማሩ ከበደ(እና መሰሎቹ)፡- ወፈ - ገዝት አትሁኑብንማ፡፡ወደ ዝሙትና ሥጋዊ ፈቃድ የሚጎትት ዘፈን እንጅ ዘፈን ብሎ ነገር በጭራሽ አትስሙ አልተባለም፡፡እንደመናፍቅ ደረቅ ንባብ ይዛችሁ አትመጻደቁብን፡፡አስተውሉ!! የሀገሪቱን ባሕልና ወግ ተሸክመው ካሻገሩልንና ከሚያሻግሩልን ድልድዮች አንዱ ሙዚቃ ነው፡፡ጎንደር ፋሲለደስ፣ላሊለበላና አክሱም ከማንም በላይ እውቅና ያገኙት በባህላዊ ሙዚቃዎቻችን ነው፡፡በማስታወቂያ አይደለም፡፡ሙዚቃ ውስጥ ባሕል፣አለባበስ፣ማንነት፣ቋንቋ፣መሳሪያዎች አሉ፡፡እንደውም የደቡቡ የሐገራችን ክፍል በፕሮቴስታንት ጫና ካጣቸው የማንነት መገለጫዎች አንዱ ሙዚቃ ይመስለኛል፡፡በበኩሌ እንደሰሜናዊ ሰው ከጎጃምና ከወሎ ወይም ከጎንደርና ከትግራይ ሕዝብ ማንነት ውስጥ ሙዚቃን መነጠል ግማሽ ማንነትን እንደመግደል እቆጥረዋለሁ፡፡መተከዣችንን ምን የቆረጠው ግልብ አማተር ነው በሃይማኖት የሚነጥቀን፡፡ባይሆን ዝሙታዊ መንፈስ እንዳይኖረው በቅጡ ማድረግ እንጅ ዘፈንና ዘፋኝነት ኃጢኣት ነው እያሉ በጅምላ ሙዚቃን ማውገዝ መመጻደቅ ነው፡፡የፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ባጓጉል መመጻደቅ ማሲንቆውን በኦርጋን ተክቶ፣የባሕል አለባበሱን በሱፍና በከረባት እንዲሁም በታይት ተክቶ ነባር ትውፊታችንና ዘፋኝን ማሽሟጠጥ ሳያንሰን የራሳችን ልጆች ባጓጉል አዋቂነት አትበጣጠሱብን፡፡እነ አቡነ ጎርጎርዮስና አቡነ ገሪማ ሳይቀሩ የአዝማሪ ዘፈን እየጠቀሱ የቤ/ክ ታሪክ ጽፈዋል፡፡ዓረብ-ዓርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም የሚለው የአዝማሪ ዘፈን የኢኦተቤክ ታሪክ በሚለው የአቡኑ መጽሐፍ ሰፍሯል፡፡አንብብ፡፡ጠይቅ፡፡ትውፊቱን ገጠር ከከተማ ተመልከት፡፡በገጠር ትውፊቱን ሳይለቅ ከባሕሉ ተጣጥሞ ታቦት ባገር ባህል ዘፈን ይታጀባል፡፡ወጣ ብለህ እይ፡፡በሰንበት ኮርስ አታምቧትርብን፡፡ኤጭ!!አዲስ እረኛ፣ከብት አያስተኛ!!ለነገሩ አምናም የሽልማት ሥርዓቱ ለምን በቢራ ፋብሪካ ስፖንሰር ተደረገ ባዮች ነበሩ!!የማኅበራዊው ሚዲያው መንጋ ትውልድ እንከን ለመንቀስ ማን ብሎት!!ለእኔ ይሕ ሽልማት በማኅበራዊ ሚዲያ ገንቢ ተግባራትም ሊከናወኑ እንደሚችሉ ማሳያ ነው፡፡የእናንተን ስድብና ፍረጃማ በየኅቡዕ ሚዲያችሁ ቋቅ እስኪለን እየተጋትነው ነው፡፡ሰልችቶናል፡፡ስድብ ሰልችቶናል፡፡መመጻደቅ ታክቶናል፡፡ተውንማ!!
   ውድ ዘፋኞቻችን፡- ላገር ክብር፣ለተፋቅሮ፣ለሥነ - ምግባር እና ለሰብዓዊነት እሴት የሚጨምር ዘፈን ዝፈኑልን፡፡እናከብራችኋለን፡፡ላገር ሉዓላዊነትና ለሰብዓዊነት ከማንም በላይ ያደረጋችሁትን እናውቃለንና በእኛ አማተሮችና እንደ ወረደ ፕሮቴስታንቲዝምን ተቀብለው ካቀባዮቻቸው አህጉራት በተለየ መልኩ ዘፈንን በጅምላ ነውርና ኃጢኣት በሚሉ ተመጻዳቂዎች አትሸማቀቁ፡፡ከማንኛውም ሚዲያ በበለጠ ትውልድ ቀረጻ ላይ አሻራችሁን የማስቀመጥ አቅም እንዳላችሁ ተገንዝባችሁ ሙያውን በክብር ይዛችሁ ስሩበት፡፡እንወዳችኋለን!!እናከብራችኋለን!!
   ወንድማችን ዳኒ፡- ከተመጻዳቂዎች ጫና ወጥተህ በዘፋኝነት ሕይወት ውስጥ ላለው ሀገራዊ አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ባንተ የተመሰረተውና አሁን ላይ ተቋማዊ ቅርጽ የያዘው የሽልማት ድርጅት ዓድማሱን በማስፋቱና ውድ ዘፋኞቻችንን በማካተቱ ምስጋናችንን ውሰድ!!እናመሰግናለን!!ወደ ኋላ እንዳትል!!

   Delete
  4. ከላይ ያለውን እደግፋለሁ፡፡ዘፋኝንት ኃጢአት ነው፡፡ሙዚቃም ብትለው ሌላም ስም ብትሰጠው ያው ነው፡፡ለመንፈሳዊ ሰው ማለቴ ነው፡፡ ለስጋዊ ሰው ሜዳው ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ የማሩን ሃሳብ እጋራለሁ፡፡ጨለማና ብርሃንን ለማስተባበር እንሞክር፡፡

   Delete
 3. Well, this is more of "social" than "spiritual" and thus need to address all professional fields regardless of religious denomination or professions (that's why Music is also included, and members of other religion were also awarded for that they did for the country).

  My concern is - if Daniel has a strategy to "institutionalize" this. Please institutionalize this, then you can ensure its sustainability. Otherwise, it will stop if Daniel stops. Thanks

  ReplyDelete
  Replies
  1. I strictly disagree ! If it was Dn Begashaw who did this you would kill him for sure. Our church should not have a diakon that awards musicians in any context !

   Delete
  2. Music yemilew sem rasu ye greek taot sem endehone takalachu lemehonu.....alsmamam. music lishelem aygebam. wede grea wede kegne yelem.

   Delete
 4. ሰላም ዲየቆን ዳኒ, በኢትዬጵያ ለይ ጥሩ ሰራ ሰርቶ ለሚገኝ ማመሰገን,ማበረታታት ተገቢ ነው. ኢትዬጵያን ከማሰጠራት በለይ ምን ጥሩ ሰራ አለ? ? ምናልባት ከኮሚቴዎችው ውሰጥ በሙዚቃ ሰራ የሚለውን የሚደግፉ ሊኖሮ ይችላሉ. ሌሎቻችን ግር እንዳይለን ወይንም እንዳንሰናከል እዛ ቦታ ላይ ያለህን የሰራ ድርሻ ግለፅልን፠ መልካም አሰተያያት ካልሰጠሁ ይቅርታ እጠይቃለው፠እመቤታችን ትባርክህ አሜን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Amen yebarek. Yehunena yesera dersha milew neger aygebagnem.....musikan lemeshelem yesera dersha yalachewen hulu mekawem alebet.

   Delete
 5. 1/ የነፃነት ታጋይ
  እነ ቼ ማንዴላ …የጠሩ ኮከቦች
  ለፍትህ ተጋዳይ ለነፃነት ሟቾች
  መለኪያ የሆኑት ለሌሎች ታጋዮች
  ህዝቦች በአርያነት የተከተሏቸው
  ክብርና ዕውቅና ዓለም የቸራቸው
  የግል ጥቅማቸው ሳያሣስባቸው
  የጎሳ የቀለም ድንበር ሳይኖራቸው
  ከጥላቻና ቂም ፀድቶ ስሜታቸው
  ሰውን ያለምክንያት እኩል ማክበራቸው
  በተራማጅ ሃሳብ ህዝብን በማራመድ
  የመተማመን ፀር ትዕቢትን በመናድ
  ሁሉ እንዲመላለስ እንቅፋት ሳይገጥመው
  ዋጋ እየከፈሉ ስለጠረጉት ነው
  ሃውልት የማይተካው ስም የተሰጣቸው
  ማነህ ባለተራ ታጋይ ነኝ የምትል
  ይገባህ ይሆን ወይ ኩርፊያ ጋር እያለህ
  ቂምን በይቅርታ መለወጥ ተስኖህ
  ሃሳብ ከማሸነፍ ስጋ ላይ ያተኮርህ
  ሂሳብ ማወራረድ ምንጊዜም እያለምህ
  ርቀህ ሳትሄድ ላለው ካጠገብህ
  ስቃይ የሆነከውን ለወንድም ለእህትህ
  ቋንቋ ወንዝ ጎጡን መሻገር ላቃተህ
  ታጋይ መባል መቼም ከቶም አይመጥንህ
  ከተባለም ይሁን ህገ-ቅብ ሽፍታ ነህ




  2/ኢ-ምርጫ
  በራስ እጅ ሲቆረጥ
  እንዲህ ይሆን መቅበጥ
  ምርጡ እንዳይመረጥ
  ውድድሩ እንዳይጦፍ
  ሜዳውን በማንቀፍ
  ዳኛውን በማቀፍ
  ታዛቢን ማግባባት
  ተመልካችን መርሳት
  ማስመሰል ማምታታት
  እውነት ለመቀባት
  የሌለን ማበርታት
  ቅጥረኞችን ማምረት
  ድርጎውን በመስጠት
  ጠጣሩን ማላላት
  የቆመን ማጉላላት
  የተኛን ማስነሳት
  የራቀን በመጥራት
  ሲመጡ በር መዝጋት
  ሰበብ ፈጥሮ ማገት
  አንዳንዱንም እሽት
  አስቀድሞ በስጋት
  ወኔን በማሟሟት
  በፎርፌ ለመርታት
  ባሸባሪ ቅርጫት
  ቆንጆም ብትሆን መክተት
  ከብትም ሆነ ኩበት
  ቀድሞም በሌለበት
  ይገርማል ሲባክን
  የድሃ ህዝብ ሀብት
  ጊዜም ሆነ ጉልበት
  በዕብሪትና ትዕቢት
  መቼም ላይቀይሩት
  ፍጥጥ ያለን ውሸት
  ምን ቢያሰማምሩት
  ሃሰት ላይ ቢደረት

  ReplyDelete
 6. የሌሎች ሀገር ተሞክሮ ወደ እኛ ሀገር አምጥቶ መልካም የሠራን በሕይወት ሳለ ማበረታታት መለካም ነው፡፡ እኔ በቤተሰቤ ፣ በሥራ ቦታዬ፣ በአካባቢዬ በሕይወት ሳለሁ ጅምር በሆነ በመልካም ሥራቸው ማበረታታት የሚገባኝ እንዳሉ አምናለው፡፡ ከዚህ መጀመር አለብን እና፡፡
  የበጎ ሰው ሽልማት የሚያስመሰግን የቅን ሰዎች ተግባር ነው፡፡ ለሁለነታዊ ሀገራዊ እድገታችን አውንታዊ ተጽህኖ እንደሚሳድር ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ሥራውን ከግለሰቦች ወደ ተቋም ማሳደግ ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርጋል እና የሁላችን ድርሻ ነው፡፡ አዘጋጆችም በዚህ ረገድ እየሰሩ መሆኑን አምናለው፡፡ “መልካም ሥራ አንድ ውይም ጥቂቶች ይጀምሩታል ብዞዎች ይከተሉታል” አደለ የሚባለው፡፡
  በስተመጨረሻም 3ኛው ዙር የበጎ ሰው ሽልማት በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ መልካም ምኞቴ ነው፡፡ ለአዘጋጆቹም ብርታቱን ይስጣችሁ እላለው፡፡
  ሰይፉ አበበ

  ReplyDelete
 7. ለሰው ልጅ እጅግ አኩሪ ስራ የሰሩና ምሳሌ የሆኑ ነገር ግን በህይወት የሌሉ( ስራቸው ለብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልተገለጠ) በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት ይህን ውድድር መወዳደር ይችላሉ?????

  ReplyDelete
 8. ከቀረቡት ዘርፎች ሙዚቃ ቢወጣ መልካም ነው እላለሁ

  ReplyDelete
 9. አዝማሪው ተባረክ፡፡ አንጀቴን አራስኸው፡፡ እነ ጎርፉ በተቀደደላቸው ቦይ እንጂ የራሳቸዉ መንገድ ስለሌላቸው አልፎ አልፎ መታረቅ ይሻሉ፡፡ ሲሆን ሰሆን የላወቁትን ጠይቆ ወይ አንብቦ ማወቅ ፣ የራስ ንብረት ማድረግ፤ አልያም ለአዋቂዎች ዕድል ሰትቶ ራስን ዝቅ በማድረግ በዕውቀት ፀበላቸው ታጥቦ ካለማወቅ ዕድፍ መፅዳት፡፡
  በኃይማኖተኛነት ሰበብ ሙዚቃን የኮነንከው ወንድሜ የ ሊቁ ያሬድን መዚቃ እንዴት ታየው ይሆን ? impress me ባክኽን!!

  ReplyDelete
 10. የሽልማቱ outcome የሚታይበት ሁኔታ ቢኖርህ መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete