ከቀናት በፊት ሬዲዮ ማዳመጥ እስኪሰለቸን
ድረስ ሁሉም ጣቢያዎችና ፕሮግራሞች ስለ ‹ቫላንታይን ደይ› ነበር የሚወተውቱን፡፡ ልክ ፍቅር በዚህች ሀገር እንዳልተወለደ፣ ድኾ
እንዳላደገ፣ ለወግ ለመዓርግ ደርሶ ጎጆ እንዳልቀለሰ ይመስል ነበር፡፡ ቀይ ልብስ ያልለበሰ፣ አበባ ያልያዘ፣ በምሽት በሚደረጉት
ጭፈራዎች ያልተገኘ፣ ማታም ጥንድ ሆኖ አልጋ ያልያዘ ሰው ሁሉ ፍቅርን እንደማያውቅ ተደርጎ ነበር የሚተረክልን፡፡
ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ያመሻል፣
አፌ ፈራሽ እንጂ ልቤስ ከጅሎሻል፤
ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ካመሸ
ከፈራህኝማ ነገር ተበላሽ፡፡
ተብሎ ያልተገጠመ፤
አቡኪ ወእምኪ ኢይፈቅዱ እንግዳ
ሰዐምኒ ንሑር በሳንቃው ቀዳዳ፤
ምዕራባውያን በአንድ ነገር ጎበዞች
ናቸው፡፡ ባሕላቸውን ወደ ሸቀጥነት መቀየርና የገበያ ማሟሟቂያ ማድረግ ይችሉበታል፡፡ የካፒታሊስት ሥርዓት አንዱ መገለጫውም ሁሉን
ነገር ሸቀጥ ማድረግ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ለእነርሱ ሃይማኖት እንኳን ቢሆን ሲታመንበት ሳይሆን ሸቀጥ ሆኖ ሲሸጥ ነው የሚያዋጣው፡፡
‹የቫላንታይን ደይ›ን በዓል ከፍቅረኞች በላይ ባለ ሆቴሎችና ባለ ጭፈራ ቤቶች፣ አበባ ሻጮችና የስጦታ ካርድ አምራችና አከፋፋዮች፣
ቸኮሌትና ወይን አምራቾች ይፈልጉታል፡፡ እነርሱ ፍቅርን በእሴትነቱ ሳይሆን በሸቀጥነቱ ነው የሚፈልጉት፡፡ የሚሞቱለት፣ የሚሠዉለት
ዓይነት ፍቅር ሳይሆን የሚያተርፉበት ዓይነት ፍቅር፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የሚዲያ ባለቤቶች ስለ ቫለንታይን ሂስ ለማቅረብ የሚነሡ
የፕሮግራም አዘጋጆችን ‹‹ስፖንሰሮቻችን ይቀየማሉ› በሚል ሲከላከሉ እንደነበር ውስጥ ዐዋቂዎች ይናገራሉ፡፡
ፍቅር እንደ ሸቀጥ ስለታየ ‹ቀይ
ልብስ ለብሳችሁ ከመጣችሁ የክብር ሥፍራ አለን፣ ጥንድ ሆናችሁ ከመጣችሁ ቅናሽ እናደርጋለን፣ እኛጋ ጥንድ ሆናችሁ አልጋ ከያዛችሁ
ግብዣ ላይ ዋጋ እንቀንሳለን› የሚሉ ዓይነት ማስታወቂያዎች ነበሩ አየሩን የሞሉት፡፡
ኢትዮጵያውያን ከውጭ መልካም ሐሳብ
የያዙ በዓሎችን ሲያመጡ ሐሳቡን እንጂ ሙሉ ቅርጽና ይዘቱን አያመጡትም፡፡ ገና ኢትዮጵያዊ መልክ ነው ያለው፤ ግን ዓለም ዐቀፋዊ
በዓል ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በሌሎችም ክርስቲያን ሕዝቦች ዘንድ አለ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ኢትዮጵያዊ ቁመና፣ መልክና ባሕል አለው፡፡
የደብረ ታቦር በዓል በሌላውም ዓለም ይከበራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ቡሄ ሆኗል፡፡
ይህ መሆኑ በሦስት ነገር ሲጠቅመን
ኖሯል፡፡ በአንድ በኩል የራሳችን መገለጫ፣ የማንነታችን ማነጫና መግለጫ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ ለዚህ ነውኮ መስቀልን አዲስ
አበባ፣ ገናን ላሊበላ፣ ጥምቀትን ጎንደር ላይ ለማየት የአገር ፈረንጅ የሚጎርፈው፡፡ እዚያ የሚሄደው ኢትዮጵያዊውን መልክ ለማየት
እንጂ ጌታ መወለዱን፣ መጠመቁንና መስቀሉ ከተቀበረበት መገኘቱን እንደ አዲስ ለመማር አይደለም፡፡ ይህን ሐሳብ ወደ ሕልው ባሕል
የቀየርንበትንና ያንንም የጠበቅንበትን መንገድ ለማየት እንጂ፡፡ አንድን ሐሳብ የሕዝብ ባሕል ማድረግ በሰው ልጅ ጉዞ ውስጥ ወሳኙና
እጅግ አስፈላጊው የሰብእና ክፍል ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከኢትዮጵያዊ
ማንነት ጋር የተዋሐደ በመሆኑ ገጠር ከከተማ፣ ሰሜን ከደቡብ ሳያነቅፈው ተጣጥሞ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ከደኻ እስከ ሀብታም፣ ከማይም
እስከ ምሁር፣ ከደቂቅ እስከ ሊቅ እንደ ዐቅሙ ያከብረዋል፡፡ ሦስተኛው ደግሞ በዓሉ ቤተኛ መሆኑ ነው፡፡ ቤተኛ በዓል ማለት ቤተሰብን
የሚመለከት፣ ሁሉም የሚሳተፍበት፣ የሀገር ቤቱን ሰው ተሳትፎ የሚጠይቅ ማለት ነው፡፡ ለገና ዳቦ የሚሆነውን እህል፣ በግና ዶሮውን
ገበሬ ያመጣል፤ ነጋዴ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ነገር ያከፋፍላል፡፡ የሴቶች ሞያ በጠላው በዶሮው፣ የወንዶቹ ሞያ በእርዱ በሥጋው
ይታያል፡፡ እንኳን አደረሰህ የሚለው ዘመድ አዝማድ መልእክቱን ይልካል፡፡ ከጉልት ገበያ እስከ ‹ሱፐር ማርኬት› አገሩ ሸብ ረብ
ይላል፡፡ በዓል መሆኑን አካባቢውም ይናገራል፡፡ ልጅ ዐዋቂው፣ ያገባው ያላገባው፣ ነባሩና አዲስ መሽራው፣ መናኙና ከተሜው፣ ሁሉም
ይሳተፋል፡፡ ለዚህ ነው እነዚህ ሀገርኛ በዓላት የመከራ ዘመናትን ሁሉ አልፈው በየጊዜው እየበለጸጉ እዚህ ዘመን የደረሱት፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የ‹ቫለንታይን
ደይ› ኢትዮጵያኛ ሆኖ ቢሆን ኖሮ በየካቲት አበባዉ ሁሉ ረግፎ ባለቀበት በየካቲት ወር አልነበረም መከበር የነበረበት፡፡ በጥቅምት እንጂ፡፡ አበባ መስጠት ያለባችሁ
የግድ ገዝታችሁ ነው ካልተባልን በቀር፡፡ አገሩ በሙሉ በአበባ የሚያሸበርቅበትን የጥቅምትን ወር አሳልፎ የአበባን በዓል በመከር
ጊዜ ማክበር ምን ያህል በዓሉ ኢትዮጵያዊነት እንደሚጎድለውና ተገንጥሎ ብቻውን እንደቆመ የሚሳየን ነው፡፡
ምንም እንኳን ቀይ ሽብር፣ ቀዩ
ጦር፣ የቀይ ኮከብ ጥሪ፣ የሚሉ መጥፎ የቀይ ቀለም ትዝታዎች ቢኖሩብንም ያ ሁሉ ቀይ ወይን፣ ቀይ ምንጣፍ፣ ቀይ መብራት፣ ቀይ አበባ፣
ለጦርነት፣ ለሽብርና ለጠብ አይደለም፤ ለፍቅር ነውና ኩነቱን ሳይሆን ምክንያተ ክዋኔውን ተመልክተን ስለ ፍቅር አምላክ ስንል ይሁን
ብለን እዚህ ላይ እንለፈው፡፡
ግን እስኪ ልክ እንደ ቫላንታይኑ
ሁሉ ለራሳችንም ጉዳይ ትኩረት እንስጥ፡፡ አሁን ነገ የካቲት 12 ቀን ለዚህች ሀገር ሕይወታቸውን የገበሩ፣ በፋሽስቶች የተጨፈጨፉ፤
ዛሬ እኛ ዘና ብልን በቀይ ወይንና በቀይ ምንጣፍ የ‹ቫላንታይን ቀንን› እንድናከብር ያደረጉ ሰማዕታት በዓል ይከበራል፡፡ ከቫለንታይን ይልቅ የካቲት 12 የራሳችን ጉዳይ ነው፡፡ ለዛሬ
ማንነታችን ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡ እንዲህ በነጻነት ቀና ብለን እንድንሄድ ዋጋ ከከፈሉ ሰዎች መካከል ናቸው የየካቲት 12 ሰማዕታት፡፡
ይኼው ዛሬ ዋዜማው ነው፡፡ ማንም ግን ስለ ነገው በዓል እየተናገረ አይደለም፡፡ ነገም ከአንዲት ዜና በቀር ማን ስለ ጉዳዩ ጣል
እንደማያደርግ እገምታለሁ፡፡
የትናንት ታሪኩን በሚገባ የማያውቅ፣
የማይተነትንና የማይገነዘብ የትናንቱን ስሕተቱን በከፋ መንገድ ለመድገም የተረገመ ነው፡፡ ከትናንት የተሻለ ለመሥራት በትናንቱ መሠረትም
ላይ ለመገንባት ትውልድ የተሠራበትን የታሪክ ጡብ ማወቅ አለበት፡፡ በርግጥ እንደ ቫለንታይን ቀን በስፖንሰር አያንበሸብሽም፣ በርግጥም
ቀይ ወይንና ቀይ ምንጣፍ የለውም፡፡ አበባ ለመሸጥና ጭፈራ ለመጨፈር አይመችም፡፡ ግን ከቫለንታይን ቀን ይልቅ የካቲት 12 ቀን
እኛነታችን ነው፡፡ መነሻ የሌለው መንገድ፣ መንገድ የሌለውም መድረሻ የለም፡፡ ለመንገዱ ዋጋ ነሥቶ፣ ለመድረሻው ተስፋ ማድረግን
የመሰለ ዕብደትም የለም፡፡ ለመንገድ ሠሪው ዋጋ ነሥቶ በመንገዱ ላይ ለሚሄደው መኪና ምስጋና ማዥጎድጎድን የመሰለ ክፉ ዐመል የለም፡፡
በትናንቱ ላይ ለመግባባት አለመቻላችን ነው በዛሬውም ላይ ሊያግባባን ያልቻለው፡፡
እናም እናንት ‹ሚዲያዎች›፣ እናንት
በዓለ ሚዲያዎች
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ
ኢትዮጵያዊ ለሆኑ በዓሎችና ጉዳዮች
እንደ ቫለንታይን ቀን ሁሉ አገሩን በሚዲያ ስታውዱት፣ እንደ ቅዱስ ቫለንታይን ሁሉ ስለ የካቲት 12 ሰማዕታት፣ ስለ አድዋ ጀግኖች፣
ስለ ማይጨው ዘማቾች ስትተርኩ እንስማችሁ፡፡
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ፣ ባሕሎች
ላይ፣ ታሪኮች ላይ፣ በዓሎች ላይ፣ ጀግኖች ላይ፣ ቦታዎች ላይ አጥንታችሁ፣ አንብባችሁ፣ ስታቀርቡ እስኪ እንያችሁ፡፡
ርግጥ ነው ዊኪፒዲያ ላይ አይኖር
ይሆናል፣ ኢንተርኔት ላይ በክሊክ አይገኝ ይሆናል፣ ጎልጉል ሲጎለጎል በቀላሉ አይመጣ ይሆናል፡፡ ግን የራሳችን ጉዳይ ነው፡፡ ‹ራሴን
በራሴ ካላንቆለጳጰስኩት ማን ያንቆለጳጵስልኛል› ነውና እኛ ለእኛ እንሥራ፡፡ ሌሎችም ስለ ሠሩ ነው ዛሬ ስለ እነርሱ በቀላሉ የትም
የምናገኘው፡፡ እኛም ብንሠራ የኛ ጉዳይ በቀላሉ እንዲደረስበት ማድረግ እንችላለን፡፡
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ፤
እኔም የማስበውን ነው የተናገርከው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ጣልያን አሁንም የገዛን ያክል ነው የሚሰማኝ ፡፡ እኔ እንደውም የምጠረጥረው ጣልያን ስለ የካቲት 12 ሰማእታት ስ አድዋና ማይጨው ሚዲያው እንዳያወራ ስፖንሰር ሆና ፕሮግራም እንዳይወራ ያደረገች ይመስለኛል ከሸገር ኤፍ ኤም በስተቀር፡፡ ለሸገር ኤፍ ኤም ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል፡፡ ማስተላለፍ ያለባቸውን ያስተላልፋሉና፡፡ ሁሌም ጀግንነትን እንሰማበታለን፡፡
ReplyDelete... ኢንተርኔት ላይ በክሊክ አይገኝ ይሆናል፣ ጎልጉል ሲጎለጎል በቀላሉ አይመጣ ይሆናል .... betikikil ye hagerachin ye midiya sewoch ke internet wuchi be rasachew afliko sile hagerachew metsafi yemichilu iymesilegnim. ye adegut hagerat merejachew bekelalu ke internet sile migegni yitsifutal ye igna gin silelele minim mallet iychilum. and ande internet ina bbc, cnn,... le and samint bikuaret irgitegna negn sport zena ina yeteleyayu programoch yidegemalu weyim be muzika yizelelalu
ReplyDeleteበጣም የሚገርም ትዝብት ነው እውነትም የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ እንኪ እንያችሁ፡፡
ReplyDeleteእኔን ግን በጣም የሚገርመኝ የኢትዮጵያ ኮርፖሬሽን፡ የኢትዮጵያ ሚዲያ፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር እያላችሁ በግልፅ ግን የውጭ የሆናችሁ ኤፍ ኤም ራዲዮኖቻችን ወይ ስማችሁን ቀይሩልን ወይ ስለ ኢትዮጵያ አውሩልን ልብ ካላችሁ፡፡
እውነትም
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ
Ya we should talk about akafaw Michael moges asgedom abriham deboch & z sacrifice on that day.
ReplyDeleteእውነት ነው ዛሬ ቀይ አበባ ይዘን ቀይ ልብስ ለብሰን ሰንጓዝ አባቶቻችን በከፈሉልን መሰዋትነት ነው. እንደ አባባ እረግፈውልን ነው ያቆዮት ይህችን አገር እምዬን. እጅ ለእጅ ተያይዘን አበባውን ይዘን ማበርከት ያለብን ለእነሱ ነው. ይገባቸዋል! ይህ ነው ፍቅር ማለት! ማንነታችንን አንርሳ!እራሳችንን እንሁን ! ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማህ በርታ !ለሁላችንም የሚያሰተውል ልቦና ይሰጠን አሜን!!!
ReplyDeleteእውነት ነው ዛሬ ቀይ አበባ ይዘን ቀይ ልብስ ለብሰን ሰንጓዝ አባቶቻችን በከፈሉልን መሰዋትነት ነው. እንደ አባባ እረግፈውልን ነው ያቆዮት ይህችን አገር እምዬን. እጅ ለእጅ ተያይዘን አበባውን ይዘን ማበርከት ያለብን ለእነሱ ነው. ይገባቸዋል! ይህ ነው ፍቅር ማለት! ማንነታችንን አንርሳ!እራሳችንን እንሁን ! ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማህ በርታ !ለሁላችንም የሚያሰተውል ልቦና ይሰጠን አሜን!!!
እውነት ነው ዳኒ እኛስ መጤውን አደነቅን አከበርን እውነተኛ አኩሪ በአሎቻችንን ግን ቅርፁን እየጠበቅንለት ይሆን?
ReplyDeleteፈረንጆቹ ለትውልድ ትውልዳቸው እንዳይጠፋ እየጠበቁት ነው እኛስ ፈረንጅ ናፋቂዎች እነሱ ከነመኖራችን ትዝ የማንላቸው ለልጆቻችን ምን አለን???
በእጅ የያዙት እንዳይመስልብን።
Lib yalew libyibel specialy those who works on ethiopian media please choice the right way.
ReplyDeleteጤና ይስጥልኝ
ReplyDeleteዛሬም በጣም ጥሩ ጉዳይ ነው የመዥረጥከው። የኢትዮጵያዊነት ባህል፣ ልማድና ወግ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ መሸርሸሩና መቀየጡ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የሚከነክን ጉዳይ ነው። በየትኛውም የኢትዮጵያዊነት ዙሪያ መገናኛ ብዙሐን ብዙ መስራት ሲጠበቅባቸው ጭራሽ ያለንንና የያዝነውን እየበረዙ በማንነታችን ላይ ይቀልዳሉ።
ይህ ለግልና ለቡድን ጥቅም ሲባል የሚደረግ እሩጫ እንደ ዜጋ ለአገር እሴት ያለመቆርር ነው። ህሊና ያለው ሰው ከህሊናው ጋር ለመኖር ሆዱን ሞልቶ ህሊናውን ማስራብ አይገባውም። ይሄ ከሰው ፍጡር በታች ሊያደርገን የተነሳብንን ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ማስወገድ እንኳን ቢሳነን መቀነስ ካልቻልን ማንነታችን አጠያያቂነቱ ይቀጥላል።
ስለዚህ ለህሊና እየኖሩ ባህልንና ማንነትን ጠብቆ የመኖር ጥበብና ጥንካሬ ሊኖረን ይገባል ለማለት እወዳለሁ።
ኢትዮጵያዊ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ!!!???
ጤና ይስጥልኝ ዳኒ ! ለመሆኑ የቢታንያ ድንጋዮች ኢትዮጵያ የሉምን? ሰሚ የት ተገኝቶ ወዳጄ ።ውጤቱንማ ከየካቲቱ ሰማዕታት ቀን ይልቅ ቫላንታይን ሚድያውን ተቆጣጥሮታል ያልከውን በማግስቱ የንጉሴ አክሊሉ ትዝብት በVOA ያሰማውን ልብ ይልዋል። ወይ ዘመን!
ReplyDeleteImpressive!
ReplyDeleteአይ ዳኒ የዛሬ ወላጅ ለልጁ አባታችን ሆይ በል የሚል ይመስልሀል
ReplyDeleteአይደለም አድገህ አሜሪካ እልክሀለው ነው የሚለው ታዲያ ማን ይመከር ፣ማን ታሪክ ይናገር
ብቻ እግዚአብሄር ይጠብቀን
መነሻ የሌለው መንገድ፣ መንገድ የሌለውም መድረሻ የለም፡፡ ለመንገዱ ዋጋ ነሥቶ፣ ለመድረሻው ተስፋ ማድረግን የመሰለ ዕብደትም የለም፡፡ ለመንገድ ሠሪው ዋጋ ነሥቶ በመንገዱ ላይ ለሚሄደው መኪና ምስጋና ማዥጎድጎድን የመሰለ ክፉ ዐመል የለም፡፡ በትናንቱ ላይ ለመግባባት አለመቻላችን ነው በዛሬውም ላይ ሊያግባባን ያልቻለው፡፡
ReplyDeleteGreat God bless you!!!
ReplyDeleteእኔም የማስበውን ነው የተናገርከው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ጣልያን አሁንም የገዛን ያክል ነው የሚሰማኝ ፡፡ እኔ እንደውም የምጠረጥረው ጣልያን ስለ የካቲት 12 ሰማእታት ስ አድዋና ማይጨው ሚዲያው እንዳያወራ ስፖንሰር ሆና ፕሮግራም እንዳይወራ ያደረገች ይመስለኛል ከሸገር ኤፍ ኤም በስተቀር፡፡ ለሸገር ኤፍ ኤም ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል፡፡ ማስተላለፍ ያለባቸውን ያስተላልፋሉና፡፡ ሁሌም ጀግንነትን እንሰማበታለን፡፡
ReplyDeleteበጣም የሚገርም ትዝብት ነው እውነትም የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ እንኪ እንያችሁ፡፡
ReplyDeleteእኔን ግን በጣም የሚገርመኝ የኢትዮጵያ ኮርፖሬሽን፡ የኢትዮጵያ ሚዲያ፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር እያላችሁ በግልፅ ግን የውጭ የሆናችሁ ኤፍ ኤም ራዲዮኖቻችን ወይ ስማችሁን ቀይሩልን ወይ ስለ ኢትዮጵያ አውሩልን ልብ ካላችሁ፡፡
እውነትም
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ
ግዜክስ
Dani,
ReplyDeleteMany Thanks. Egziabher Astesasebihin, Haymanotihin Yitebikilin.
YEHUALAW KELELE YELEM YEFITU
ጥሩ አልክ ዳኒ…..እኔ ደግሞ በጣም የገረመኝ ሁሌ አብረው እኖሩ ቀን መስጠት፡ ብናውቀው ለተፈቃቃጆች ሁሌም ቫላንታይን ዴይ ነው፡፡ ብዙ የሚወራለት አይደለም ለማለት ነው፡፡ ልክ እንደእኔ…..በውስጤ ያለው እኔነቴ የሚኖረው በጸጥታ ቤቱ ውስጥ ነው፡፡ በ ሀገሬ ያለው ታሪክ በሀገሬው ካልታወቀ ማን ሊያውቀው ይችላል፡፡እስከዘለአለሙ ሳይታወቅና ሳይደረስበት የሚኖረውም እዚያ ነው ያለንን አውቀነው ካላሳወቅን የታወቀው ሣይታወቅ እንዳልታወቀ ይቀራል፡፡ ይህም እንዳይሆን ሚዲያዎች ከሁሉ በፊት ስለ ራስ ከራስ ሲተርፉ አይደል ለሰው የሚኮነው፡፡ ዳኒ በርታጥሩ አልክ ዳኒ…..እኔ ደግሞ በጣም የገረመኝ ሁሌ አብረው እኖሩ ቀን መስጠት፡ ብናውቀው ለተፈቃቃጆች ሁሌም ቫላንታይን ዴይ ነው፡፡ ብዙ የሚወራለት አይደለም ለማለት ነው፡፡ ልክ እንደእኔ…..በውስጤ ያለው እኔነቴ የሚኖረው በጸጥታ ቤቱ ውስጥ ነው፡፡ በ ሀገሬ ያለው ታሪክ በሀገሬው ካልታወቀ ማን ሊያውቀው ይችላል፡፡እስከዘለአለሙ ሳይታወቅና ሳይደረስበት የሚኖረውም እዚያ ነው ያለንን አውቀነው ካላሳወቅን የታወቀው ሣይታወቅ እንዳልታወቀ ይቀራል፡፡ ይህም እንዳይሆን ሚዲያዎች ከሁሉ በፊት ስለ ራስ ከራስ ሲተርፉ አይደል ለሰው የሚኮነው፡፡ ዳኒ በርታ
ReplyDeleteዳጊ
Good idea
ReplyDeleteኢትዮጵያ ካላቹሁ እስኪ እንያቹሁ
ReplyDeleteእግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህ ይባርክል ሥራክ ለጽድቅ ይሁንልክ አሜን
yekatit 12 endaytawes yekattit 11ne derbubet aydel endi !!!
ReplyDeleteየኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ፤
EGIZIABIHERE YISTLIN,BEDMENA BE TSEGA YITEBIKILIN!!!!!!
ReplyDeleteአነጋጋሪ ጉዳዮች ናቸው
ReplyDeleteእዚህ አሜሪካን አገር በዓላት ሁሉ ሸቀጥ ከሆኑ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡ በዓሉ ሲደርስ ፍሬ ነገሩ ሳይሆን ተስፋ የሚደረገው፡ በበዓሉ የሚገኘው ስጦታ ነው።
እስኪ ታዘቡት ነዋሪ የሆናቹህ፡ ልደት፤ ቫለንታይን፤የናቶች ቀን፡ ያባቶች ቀን፤ ወዘተርፈ።
አሁን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ዓለማት፡ ተመሳሳይ ነገሮች እየተከሰቱ ነው። የበዓሉን ፍሬ ነገር ወደጎን አድርጎ ሸቀጡ ላይ ማተኮር። እኛም በዓላቶቻችን በሸቀጥ እንዳይበረዙ ወይም እንዳይለወጡ፡ ፍሬነገሩን ለትውልድ በየዓመቱ ማሳሰብ ይረዳ ይሆናል።
ሌላው፡ የሰው ባሕልን የራስ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው። የጎደለን፡ የቀረብን አለ ወይ በሰው ባሕል ልንሞላው የምንፈልገው? ግን እኛ ኢትዮጵያውያን፡ ባለን ታሪክና ባሕል ይኼ ቀላዋጭነት፡ የማያዋጣ መሆኑ ብቻ ሳይሆን አያምርብንም።
መገናኛ ብዙኀን የጎላ ድርሻ ቢኖራቸውም ዜጎችም ፈጻሚ አስፈጻሚ በመሆናችን ኃላፊነት አለብን።
long live dn .dany i cant write in amharic due to some problem but i feel sth different when i read your script god bless u
ReplyDeleteAy Ayin yenisir ayn eko new yaleh Deacon Dani. egziabher Yibarkih.
ReplyDeleteEwunetihin eko new FM Radio sisema nege bezih hotel ke ezih se'at jemiro liyu program tezegajtual ye valentines dayin mikniyat be madreg yilal, lela FM Radio tabiya sitkeyir hulet gazetegnoch honew mismer lay admach iyetekebelu sile Valentines Day yaweralu. keza kuch biye min ale Deacon Daniel silezih neger bitsef ( biketib) biye lebichaye asebku.keza and FM Radio Tabiya Lay and (1) sew dewulo min ale Valentines day Bilen Ke minakebir Ye Misgana (Thank You Day) Ken bilen bInakebir bilo asteyayet sete. ante tishalaleh alkugn be wuste keza Radion zegawut. keza yihew kibr misgana yigbawuna amlakachin ye tekeshene tsuf (Writing) akerebkilin Dani.
Betam astemari tsuf new Fikir malet eko le sew lij asfelagi neger silehone fikiregnamoch be eyekenu, be eyeeletu me faker new yalebachew. kezih bashager ye fikiregnamoch ken bilew makber yale bachew huletu fikiregnamoch yetegenagnubetin ( fikir) yejemerubetin ken new enji endew zim bilo media ye fikiregnamoch ken be ezih elet yikeberal silale makber yelebnim be eletu fikir yejemernbet ken ke hone eseyew yanin ken mastawes tiru new fikir le rakachew fikirin be mestet kal hone gin <> ?.
kibir ethiopian ke telat werera le tadeguat jegnoch.
በጣም ደስ የሚል ገንቢ ትችት ነው። አንጀቴ ቂቤ ጠጣ አሉ፥ቃለ ሂዎት ያሰማልን።
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚል ገንቢ ትችት ነው። አንጀቴ ቂቤ ጠጣ አሉ፥ቃለ ሂዎት ያሰማልን።
ReplyDeleteWaaaaaw betam yamral.......
Deleteendezi aynet ken be kerbu new wede agerachen memetat yejemerut valantin day degeme ke mahiberawi Nero Yetenesa Yemekeber Bail New Neger Gen Egna Ethiopia Yetegenagenebet Ken Belen Makiber Bail Yelenem Selezi Le Masetaos Bailu Asetewaso Alew Neger Gen Yetegenagubet(Fiker Yejemerubet Ken) Beyakeberu Tru New Endegena Degemo Wede Ethiopia Bahil Mametat Alebachew.Lelaw Neger Egna Ethiopia Ye Bail Abetamoch Nen Ye Semaitat Ken and Yeadewa Bahil Meresat Yelelebet new Media Beteley Uneta Shifan Lesetew yegebal.dani Sele valantine ken other view Etebekalew like you give explanation about Christmas tree in EBC on Christmas Holiday.d/n Daniel Kiberit as usual Thank you Very Much
ReplyDeleteI WISH LONG LIFE AND HEALTH TO U AND YOUR FAMILY
ReplyDeleteWE Started to see Amharich after 3 year in ethiopia media.
last year federal police denied selamai self of ADWA patrots
day and protesters of GRAZIANI recogination of italy in our
home. we already sold naw we r dirctly colnnized rather than neo-colonialism.
Tank you very very much
ReplyDeleteTHANK YOU DANI ! THEY ARE THE TOOLS OF eprdf /woyane/ MIN YEDEREG
ReplyDeleteስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ለማውራት ፡ መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ዜና ማሰራጫ ፡ መኖሩ ቀድሞ መሟላት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል።
ReplyDeleteያሉትን ውዥንብር (ዜናማ የላቸውም) ማሰራጫዎቹ ፡ ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ አውሩ ማለት፡ በራስ መቀለድ ነው።
Who dies in love s't valentine or Jesus Christ ? Guys think a moment !!!!!
ReplyDeleteእናንት ‹ሚዲያዎች› የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
ReplyDeleteእስኪ እንያችሁ
የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ፣ ባሕሎች ላይ፣ ታሪኮች ላይ፣ በዓሎች ላይ፣ ጀግኖች ላይ፣ ቦታዎች ላይ አጥንታችሁ፣ አንብባችሁ፣ ስታቀርቡ እስኪ እንያችሁ፡፡
ርግጥ ነው ዊኪፒዲያ ላይ አይኖር ይሆናል፣ ኢንተርኔት ላይ በክሊክ አይገኝ ይሆናል፣ ጎልጉል ሲጎለጎል በቀላሉ አይመጣ ይሆናል፡፡ ግን የራሳችን ጉዳይ ነው፡፡
You are truly understandable, strait forward ETHIOPIAN.
ReplyDeleteLet God keeps you for long to inform us facts as you always do
Yacob Lemma
Boston
Boston
የአገር ቤቱን አላውቅም እንጂ እዚህ ውጭ አገር ያሉ ቤተክርስትያኖች ውስጥ ካህናቱን ዛሬ የፍቅር ቀን ነውና ስለዚህ ቀን አንድ ነገር ይበሉን እያሉ በጆራቸው ሾክ የሚሉ የቤተክርስትያን ሰበካ ጉባዔ አባላትም ሆነ ዘመናዊ ዲያቆናት ከነደዚህ አይነት ተግባራት ቢቆሙ ጥሩ ነው። የአገር ቤት ሚድያዎች ጉዳይ ከተነሳ ግን - መጀመሪያ እነዚህ ሚድያዎች ማናቸው ? ማንስ ከጀርባቸው ሆኖ ያንቀሳቅሳቸዋል? ማንስ ኮትኩቶ እንፆዋቸዋል ብሎ መጠየቁ ጥሩ ነው። አገሪቱ በውጭ እርዳታ ተቅዋማት (ኤንጂዖ) መርሆ ጥንስስ የምትመራ ስለሆነ፤ሚድያዎቹም ከዛ አይወጡም።
ReplyDeleteየትናንት ታሪኩን በሚገባ የማያውቅ፣ የማይተነትንና የማይገነዘብ የትናንቱን ስሕተቱን በከፋ መንገድ ለመድገም የተረገመ ነው፡፡ ከትናንት የተሻለ ለመሥራት በትናንቱ መሠረትም ላይ ለመገንባት ትውልድ የተሠራበትን የታሪክ ጡብ ማወቅ አለበት፡፡
ReplyDeleteበትናንቱ ላይ ለመግባባት አለመቻላችን ነው በዛሬውም ላይ ሊያግባባን ያልቻለው፡፡
ReplyDeleteCultural imperialism... yebahl werera yemengst policy
ReplyDelete