Monday, February 16, 2015

የአማርኛ ሞክሼ ሆሄያት
በአማርኛ ቋንቋ ዕድገትና ብልጸጋ ጎዳና ላይ ከሚገኙት ተግዳሮቶች አንዱ ተገቢ የሆነ፣ ሁሉም የሚቀበለው፣ በቀላሉ የሚገኝና ደረጃውን የጠበቀ የአማርኛ ሥርዓተ ጽሕፈት አለመኖር ነው፡፡ የአጻጻፍ መንገዶችን፣ መልክዐ ፊደልና ሥርዓተ ፊደልን፣ በቃላት አጻጻፍ የሆሄ መረጣን፣ የፊደል መጠንን፣ የስያሜ ቃላት አሰጣጥን፣ የትርጎማ መንገድን፣ ወዘተ የተመለከተ ሥርዓተ ጽሕፈት ያስፈልገናል፡፡ ለዛሬው ግን ብዙዎቻችን የምንስትበትንና የምንምታታበትን የሞክሼ ሆሄያት (ሀ፣ ሐ፣ ኀ፣ ኸ፤ ሠ፣ሰ፣ አ፣ ዐ፤ ጸ፣ ፀ) አጻጻፍን በተመለከተ ታዋቂው ሊቅ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ(ነፍሳቸውን ይማርና) አዘጋጅተውት ሻማ ቡክስ ያሳተመውን ‹‹የአማርኛን ሞክሼ ሆሄያት  ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ›› የሚለው መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ፡፡
መጽሐፏ የኪስ መጠን ብትሆንም እስከዛሬ በጉዳዩ ከተዘጋጁት የተሻለች፣ በአመክንዮ የቀረበችና በጥናት ላይ የተመሠረተች ናት፡፡ በተለይም ለደራስያን፣ ለቢሮ ጸሐፊዎች፣ ለፖለቲካ ሰዎች፣ ለጋዜጠኞች፣ ለማስታወቂያ ባለሞያዎች፣ ለአርታዕያን፣ ለፌስ ቡክ ደንበኞችና ለሌሎቻችንም በሞክሼ ቃላት ዙሪያ መመሪያ የምትሆን ናት፡፡ እባካችሁ ነገራችን ወጥ እንዲሆን በሊቁ መንገድ እንሥራ፡፡ ዋጋው 25 ብር ነው ገዝተን በጠረጴዛችን ላይ እናስቀምጥና እንመራባት፡፡
ከምር ሁላችንም ቤትና ቢሮ መጥፋት የሌለባት ናት፡፡

6 comments:

 1. ሁሉን አሟልታ የሰጠችን አገር እድገቷን ያሳየን! አባቶቻችን ብዙ አሰቀምጠውልን አልፈዋል፠ አንብበን እንጠቀምበት፠ዲያቆን ዳኒ መድሃኒያለም ይባርክህ!
  አሜን!!!


  ሁሉን አሟልታ የሰጠችን አገር እድገቷን ያሳየን! አባቶቻችን ብዙ አሰቀምጠውልን አልፈዋል፠ አንብበን እንጠቀምበት፠ዲያቆን ዳኒ መድሃኒያለም ይባርክህ!
  አሜን!!!


  ሁሉን አሟልታ የሰጠችን አገር እድገቷን ያሳየን! አባቶቻችን ብዙ አሰቀምጠውልን አልፈዋል፠ አንብበን እንጠቀምበት፠ዲያቆን ዳኒ መድሃኒያለም ይባርክህ!
  አሜን!!!


  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ አስተያየትህ ጥሩ ነው። ግን ፬ ነጥቡ ትክክለኛው አይደለምና ወደፊት ባትጠቀምበት ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም አባቶቻችን(ያንተኑ አገላለጽ ወስጄ)ያስቀመጡልን ይሄንን (።) ነውጂ ይሄኛውን (፨) አይደለምና። ርዕሱስ ሞክሼን ለመዋጋት አይደል?!

   Delete
 2. በጣም ጥሩ ጥቆማ ነው ወዳጄ ዲ/ን ዳንኤል አመሰግናለሁ። በሆሄያታችን ዙሪያ እኔም ብዙ የሚከነክነኝ ነገር አለ። በየኔታ የትምህርት ዘመን ፊደል ስቆጥር ያላየኋቸው ፊደላት አሁን ከየት እንደሚመነጩ ሊገባኝ አልቻለም። ለምሳሌ ፦ ኯ፣ ዯ፣ ጟ፣ ጏ ፣ ቝ ፣ ኌ ወዘተ ከየት መጡ? ያኔ አንቀላፍቼ ያመለጡኝ ይሆኑ ወይስ ያኔ ሀ ሁ፣ አቦጊዳና መልዕክተን ጨርሼ ወደ ወንጌል ስዛወር የኔታ የሚሸጡት ወንጌል ባለቀባቸው ሰሞን አባቴ ከመርካቶ ገዝቶልኝ ስሄድ ለምን ከውጪ ገዛህ ብለው ባለንጋ ገርፈው ካባረሩኝ በኋላ ያመለጡኝ?
  እስኪ እባክህ በዚህና አማርኛ እየተናገሩና እየጻፉም እንግሊዝኛ ለሚደነቅሩት መልዕክት አስተላልፍልን።
  ሰሞኑን በቪኦኤ በዚህ ዙሪያ ከ፫ የቋንቋ ምሁራን ጋር ግሩም የሆነ ውይይት ሳዳምጥ አንተም በነበርክበት እያልኩ ነበር። ይህ ዓይነት የውይይት ርዕስ ሲነሳ ሁሌም የሚታወሰኝ በአንድ መ/ቤት ውስጥ ለወይይት የቀረበ "የማናጅመንት መመሪያ" የሚል መጽሐፍ ነው። እንዲያው እውነት ለመናገር ማናጅመንትን የሚተካ የአማርኛ ቃል ታጥቶ ነው???? የተማሩና የሰለጠኑ መሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርጉት ሙከራ ከንቱ የከንቱ ከንቱ መሆኑን ንገርልን እባክህ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. http://patft.uspto.gov/netacgi/nph-Parser?Sect1=PTO1&Sect2=HITOFF&d=PALL&p=1&u=%2Fnetahtml%2FPTO%2Fsrchnum.htm&r=1&f=G&l=50&s1=9000957.PN.&OS=PN/9000957&RS=PN/9000957

   Delete
 3. ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል፤ የጻፍኩት ነገር ከላይ ካለው መልእክት ጋር ባይገናኝም አስፈላጊ ሆኖ ካገኘከው ት ጽፍበት ዘንድ ይህን ጽሁፍ ለጥፌያለሁ፡፡
  እንደሚታወቀው በሶሪያ በርካታ ክርስቲያኖች በአይኤስአይኤስ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል እየተፈጸመባቸውም ይገኛሉ፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ በርካታ የግብፅ ክርስቲያኖች አንገታቸው ተቀላ፡፡ ከአምስቱ እህት ቤተክርስቲያኖች (Oriental Churches) በሁለቱ አሁን ጥቃት እየተፈጸመ ነው፡፡ ነገ በሌሎቹም ሆነ በኛ ላለመፈጸሙ እርግጠኞች አይደለንም፡፡ ይህ ነገር ደግሞ በጉልበት እንደማይቀለበስ ጉልበተኞቹ ሞክረው የተሳካላቸው አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን አባቶች አስተባባሪነት ጸሎተ ምህላ ቢያዝ መልካም አይመስላችሁም? እዚህ ቀደም ስለመደረጉ ወሬ ስላሰማሁ ነው፡፡ አባቶቻችን የግብፅ ክርስቲያኖች ሲነኩ እንዴት ይንገበገቡና አጸፋውን ይመልሱ እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል፤ የጻፍኩት ነገር ከላይ ካለው መልእክት ጋር ባይገናኝም አስፈላጊ ሆኖ ካገኘከው ት ጽፍበት ዘንድ ይህን ጽሁፍ ለጥፌያለሁ፡፡
   እንደሚታወቀው በሶሪያ በርካታ ክርስቲያኖች በአይኤስአይኤስ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል እየተፈጸመባቸውም ይገኛሉ፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ በርካታ የግብፅ ክርስቲያኖች አንገታቸው ተቀላ፡፡ ከአምስቱ እህት ቤተክርስቲያኖች (Oriental Churches) በሁለቱ አሁን ጥቃት እየተፈጸመ ነው፡፡ ነገ በሌሎቹም ሆነ በኛ ላለመፈጸሙ እርግጠኞች አይደለንም፡፡ ይህ ነገር ደግሞ በጉልበት እንደማይቀለበስ ጉልበተኞቹ ሞክረው የተሳካላቸው አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን አባቶች አስተባባሪነት ጸሎተ ምህላ ቢያዝ መልካም አይመስላችሁም? እዚህ ቀደም ስለመደረጉ ወሬ ስላሰማሁ ነው፡፡ አባቶቻችን የግብፅ ክርስቲያኖች ሲነኩ እንዴት ይንገበገቡና አጸፋውን ይመልሱ እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል፡፡   Delete