Thursday, January 8, 2015

ተዋሕዶ በተዐቅቦስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በሚነሡ መድረኮች ላይ አንድነትና ኅብር ዋና መከራከሪያዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቻችን የብሔረሰቦች ተናጥላዊ መብትና ማንነት እየጎላ መምጣት፣ ሰዎችም ለአካባቢያዊ ማንነታቸው፣ ቋንቋቸውና ባሕላቸው ይበልጥ እያሳሱ መሄድ ኢትዮጵያዊ የሚባለውን ማንነት እንዳያጠፋውና ቆይቶም ኢትዮጵያ የምትባለውን አንዲት ሀገር እንዳይበታትናት እንሰጋለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሚባለው ባሕል፣ ማንነት፣ ታሪክና ግዛት በውስጡ የሚገኙትን ልዩ ልዩ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ታሪክ፣ ማንነት፣ያላቸውን ብሔረሰቦች እንዳይውጣቸው፣ ህልውና እንዳይነፍጋቸው፣ መብታቸውን እንዳይነፍጋቸው እንፈራለን፡፡
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድነትንና ልዩነቶችን(ኅብርን) አስታርቆና አስማምቶ እንደመጓዝ ያለ ፈታኝ የቤት ሥራ የለም፡፡ ሁለቱም የሀገሪቱ እውነታዎች ናቸውና፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሁላችንንም እንደሰበዝ ያያያዘችና የያዘች ሀገር አለችን፡፡ ከነ ልዩ ታሪኳ፣ ማንነቷ፣ ባሕሏና ስሜቷ፡፡ ደግሞም እያንዳንዳችን ቀየ፣ ጎጥ፣ ጎሳ፣ ነገድ፣ ብሔረሰብ አለን፡፡ ከነ ልዩ ታሪኩ፣ ባሕሉ፣ ቋንቋው፣ ልማዱና ወጉ፡፡
ጥያቄው እንዴት ሳይጣሉና ሳይጠፋፉ እናስኪዳቸው ነው፡፡

እንደ እኔ እንደ እኔ ኢትዮጵያዊ የምንለው የሁላችንም የሆነው፣ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባሕል፣ ሀገር፣ ዜግነትና ክብር ብሔረሰባዊ ማንነትን፣ ታሪክንና ባሕልን ሳይድጠው፣ ሳይውጠው፣ ሳያጠፋውና ሳይመጠው፣ ሳይጨፈልቀውና ሳይጠቀልለው፤ የብሔረሰብ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባሕልና ልማድም ኢትዮጵያዊ አንድነትን ሳይከፋፍለውና ሳይበታትነው፤ ሁለቱም ያለ መነጣጠልና ያለ መጠፋፋት፣ በተዐቅቦ ተዋሕደው፤ አካባቢያዊ ባሕል፣ ቋንቋ፣ ልማድና ማንነት ለኢትዮጵያዊነት ውበቱ፣ ጌጡ፣ ሀብቱ፣ ሰበዙና አክርማው ሆኖ፤ ኢትዮጵያዊነትም ለአካባቢያዊ ማንነት ኩራቱ፣ የጋራ መገለጫው፣ መዋሐጃውና መግባቢያው፣ በጋራም የሚገነባው የተግባቦት ቤቱ ሆኖ፤ የአንዱ መኖር ሌላውን ሳያጠፋው፤ የአንዱ መኖርም ሌላኛውን ሳያስክደው፤ አካባቢያዊ ማንነት ለኢትዮጵያዊነት መጋቢው ጅረቱ፣ ኢትዮጵያዊነትም ለየአካባቢያዊ ማንነት መሰባሰቢያው፣ መታያው፣ ዓባዩ ሆኖ፤ አካባቢያዊነት ግብዐቱ፤ ኢትዮጵያዊነት ወጡ፤ አካባቢያዊነት ድርና ማገሩ፣ ኢትዮጵያዊነትም ጋቢና ቀሚሱ፤ አካባቢያዊነት ፊደሉ፤ ኢትዮጵያዊነት ጽሕፈቱ፤ አካባቢያዊነት ቃሉ፣ ኢትዮጵያዊነት ድርሰቱ፣ አካባቢያዊነት ብሎኬት፣ ኢትዮጵያዊነት ሕንጻ፤ አካባቢያዊነት ብልት፣ ኢትዮጰያዊነት አካል ሆኖ መኖር ያለበት ይመስለኛል፡፡
ኢትዮጵያዊነት የሁላችን ድምር ውጤት፣ የሁላችንም የጋራ ቤት፣ የሁላችንም ማንነት ውሕደት ያስገኘው ልዩ የሆነ ማንነት ነውና ከአካባቢያዊ ማንነቶች ሁሉ ይሰፋል፣ ይበልጣልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአካባቢያዊ ማንነት የሰፋ ለየት ያለ ማንነት ያላቸው፤ እንዲያውም አካባቢያዊ ማንነትም የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ከተለያዩ ጎሳዎች፣ ነገዶችና ማንነቶች ከመጡ ቤተሰቦች የተገኙ፤ አንድ ብቻ የሆነ ማንነት የሌላቸው፤ ሦስትና አራት ማንነቶችን ያዋሐዱ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ እነዚህን የዚህ ጎሳ፣ ነገድ፣ አካባቢ ሰዎች ማለት አንችልም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሌላ ሀገር ተወልደው፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን አግኝተው፣ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ከአንዱ ያልተወለዱ ኢትዮጵያውያንም አሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ የሚጠቀልል ነው ኢትዮጵያዊነት፡፡  
ኢትዮጵያዊና አካባቢያዊ ማንነት ተጣጥሞ የመሄጃው መንገድ የተዐቅቦ ተዋሕዶ ይመስለኛል፡፡ ተዐቅቦ ማለት ሁለቱም በየራሳቸው ራሳቸውን እያሳደጉ፣ አንዱ አንዱን ለማጥፋት፣ ለመደፍጠጥና ለመጨፍለቅ፣ ለመበታተንና ለመሰነጣጠቅ ሳይሠራ፣ ሂደቱን ለተፈጥሯዊ ሂደት ትቶ ነገር ግን ዕውቅና ተሰጣጥቶ መኖር ማለት ነው፡፡ ተዋሕዶ ስንል ደግሞ አካባቢያዊ ማንነት ኢትዮጵያዊነትን ገንዘቡ አድርጎ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አካባቢያዊ ማንነትን ገንዘቡ አድርጎ፤ በተቃርኖ ሳይሆን በተዋሕዶ መኖር ነው፡፡ በተዐቅቦ ምክንያት መለያየት እንዳይመጣ ተዋሕዶ እያረቀው፤ ተዋሕዶ  መጠፋፋትን እንዳያስከትል ተዐቅቦ እያቀናው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሲባል የአካባቢያዊ ማንነቶች ድምር ውጤት ብቻ ሳይሆን በሂደት ተጣጥመውና ተገናዝበው የፈጠሩት የላቀ አንድ ውሑድ ማንነት ሆኖ መጓዝ ነው፡፡ 
ይህንን ሂደት ውጤታማ ለማድረግ ሦስት ነገሮች የሚያስፈልጉ ይመስለኛል፡፡ ማከም፣ መተዋወቅና ነጻነት፡፡ በታሪክ ሂደት ውስጥ ሕዝቦችን እንወክላለን የሚሉ አካላት ተጋጭተዋል፡፡ መቼም ሕዝብ ለሕዝብ መክሮና ወስኖ አይጋጭምና፡፡ እነዚህ ግጭቶች በአንደኛው ወይም በሁሉም ላይ ትተውት የሚያልፉት ቁስል አለ፡፡ ይህንን ቁስል እንዲያመረቅዝ በየጊዜው ኮምጣጤ ከመጨመር ይልቅ ወደ ማከም ብናደላ መልካም ነው፡፡ በነበሩት ችግሮች ላይ በይፋ ተወያይቶ፤ በችግሮቹ ላይ ተግባብቶ አብሮ መፍትሔውን መፈለግ፡፡ ትናንትን ምንም ልናደርገው አንችልም፡፡ አልፏል፡፡ ልናክመው ብቻ ነው የምንችለው፡፡ ነገን ግን እንደምንፈልገው አድርገን መቅረጽ እንችላለን፡፡ አሁን እንደሚታየው ቁስሉን እየገላለጥን ታማሚውን አካል ይበልጥ እንዲያመው አድርገን ከመተው ይልቅ፣ ቁስሉን ገላልጦ ትክክለኛውንም ሕክምና ሰጥቶ ማዳን ያስፈልገናል፡፡
በርግጥ ሕመም የህልውናቸው መሠረት የሆኑ አካላት አሉ፡፡ ልክ አንዳንድ ነዳያን ቁስላቸውን ለልመና እንደ ሚጠቀሙበት፤ ከቁስል መዳናቸውን ሳይሆን ራሱን ቁስሉን ለገበያ እንደሚፈልጉት ሁሉ የሕዝቦችን ቁስልም ለገበያ የሚፈልጉት አካላት ይኖራሉ፡፡ የሚያተርፉት ከቁስሉ በመሆኑ ምንጊዜም ስለቁስላችንና ማን እንዳቆሰለን እንጂ እንዴት ልንድን እንደምንችል አይነግሩንም፡፡ መድኃኒቱን አያሳዩን፡፡  ቁስለኞቹ ግን መዳኑን እንፈልገዋለን፡፡ ለዚህ ነው ማከም አለብን የምለው፡፡ አንድ በሽተኛ የሕመሙን ዓይነትና ምክንያት ማወቁ ብቻ ለድኅነት አያበቃውም፡፡ እንዴት ሊድን እንደሚችል ማወቅ፣ መድኃኒቱንም ማግኘት ይበልጥ ይጠቅመዋል፡፡ በኢቦላ በሽታ ያለቁ የምዕራብ አፍሪካ ወገኖቻችን፣ የበሽታውን መነሻና አስተላላፊ ዐውቀውታል፡፡ የቸገራቸው መድኃኒቱ ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ መተዋወቅ ነው፡፡ አጥር ከመሥራት ድልድይ መሥራት፤ ድንበርተኛ ከመሆን በረኛ መሆን የተሻለ ሕይወት ይሰጠናል፡፡ ሁሉም በአካባቢው ቋንቋ መማሩና ቋንቋውን ማደሳደጉ መልካም ነው፤ መብትም ነው፡፡ ቋንቋ ግን በራሱ ሰዎች ብቻ አድጎ አያውቅም፡፤ እንግሊዝኛ ያደገው በእንግሊዞች ብቻ አይደለም፡፡ ከጃፓን እስከ አሜሪካ ያሉት ሁሉ ተሳትፈውበት ነው፡፡ ተምረውት፤ ዐውቀውት፤ ተጠቅመውበት ነው፡፡ አማርኛን ያሳደጉት ‹አማሮች› ብቻ አይደሉም፡፡ እንዲያውም ከጥንት ጀምሮ የአማርኛን ሥነ ጽሑፍ ያሳደጉት ‹አማራ› ከሚባለው የተለምዶ አካባቢ ውጭ ያሉ ሊቃውንት ናቸው፡፡ አማርኛ የኢትዮጵያ ጎሳዎች፣ ነገዶችና ወገኖች ሁሉ ተሳትፈውበት ነው ያደገው፡፡
ዛሬም የሌሎችን ወገኖቻችንን ቋንቋዎች እናሳድግ ካልን መፍትሔው አጥር ሠርቶ ለብቻ መነጋገር ሳይሆን ሌሎችም እንዲያውቁት፣ እንዲጠቀሙበትና ገንዘብ እንዲያደርጉት ማብቃት ነው፡፡ አሁን የምንከተለው የአንድ ቋንቋ ፖሊሲ የሚያዋጣ አይመስለኝም፡፡ አንድ ሰው ኦሮምኛን ለመቻል ኦሮሞ፣ ሶማልኛን ለመቻል ሶማሌ፣ ትግርኛን ለመቻል ትግራዊ የመሆን ግዴታ ሊኖርበት አይገባም፡፡ ከዚህ ይልቅ በአንድ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከክልላቸው ቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችን የሚያውቁበት መንገድ መፈጠር አለበት፡፡ ቢያንስ ሶማልኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሲዳምኛ፣ ወላይትኛ በሁሉም ክልሎች በአማራጭነት ቀርበው፤ አንድ ተማሪ ከክልሉ ቋንቋና ከፌዴራሉ ቋንቋ በተጨማሪ ቢያንስ ሁለቱን ጨምሮ እንዲማር መደረግ አለበት፡፡ ቋንቋ መለያያችን ሳይሆን መግባቢያችን መሆን እንዲችል፡፡ ቋንቋ አጥር ሳይሆን ድልድይ እንዲሆን፡፡
ዛሬ ዛሬ በአንዳንድ ክልሎች ከሌሎች ክልሎች ከሚመጡ ወገኖቻችን ይልቅ የውጭ ሀገር ሰዎች የተሻለ ነጻነት ይሰማቸዋል፡፡ ከክልላቸው ውጭ የሥራ ዕድል ለማግኘት(መያድ ካልሆነ በቀር) የማይችሉ የአንዳንድ ክልሎች ሰዎች አሉ፡፡ ይኼ ሁኔታ በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን፣ አለመግባባትንና በጠላትነት መተያየትን ይፈጥራል፡፡ እየቆየ ደግሞ ቂምና በቀልን ለትውልድ ያኖራል፡፡ እያንዳንዱ በሌላው ክልል የደረሰበትን በራሱ ክልል ሲበቀል አገሪቱ የማያልቅ አዙሪት ውስጥ ትገባለች፡፡ የወደፊቱን እያሰበች ከመጓዝ ይልቅ ትናንት የተፈጠሩትንና ዛሬ የሚያገረሹትን ችግሮች በመፍታት ላይ ትጠመዳለች፡፡ ለዚህ ነው ኢትዮጵያውያን በየትኛውም ክልል ተዘዋውረው ሲኖሩና ሲሠሩ ነጻነት እንዲሸታቸው፤ ደኅንነት እንዲሰማቸው ማድረግ የሚያስፈልገው፡፡ ኢትዮጵያውያን ነጻነትና ደኅንነት የሚሰማቸው በክልላቸው ውስጥ ብቻ ከሆነ ዐውቀንም ይሁን ሳናውቅ በአንዲት ሀገር ውስጥ ሊግባቡ የማይችሉ ብዙ ሀገሮች እየፈጠርን ነው ማለት ነው፡፡   
ለዚህ ነው የተዐቅቦ ተዋሕዶ ይሻለናል ያልኩት፡፡ መጠፋፋትን በተዐቅቦ፣ መለያየትን በተዋሕዶ፤ ማጠቃለል ዝርዝሮችን ያስረሳል፤ መዘርዘር ደግሞ ጠቅላላን ነገር ያጠፋል፡፡ ዝርዝርን በተዋሕዶ፤ ጥቅለላን በተዐቅቦ፤ የከረረ አካባቢያዊነት ብሔራዊነትን ይንዳል፤ የተለጠጠ ብሔራዊነትም አካባቢያዊነትን ይጨፈልቃል፣ ስለዚህም ብሔራዊነትን በተዐቅቦ፣ አካባቢያዊነትን በተዋሕዶ እያረቅን ኢትዮጵያን ወደ ልዕልና እንውሰዳት፡፡ መገናዘብ(አንዱ ሌላውን ገንዘቡ ማድረግ) እንጂ መጠፋፋት ለዚህ አይበጀንም፡፡36 comments:

 1. ዛሬም የሌሎችን ወገኖቻችንን ቋንቋዎች እናሳድግ ካልን መፍትሔው አጥር ሠርቶ ለብቻ መነጋገር ሳይሆን ሌሎችም እንዲያውቁት፣ እንዲጠቀሙበትና ገንዘብ እንዲያደርጉት ማብቃት ነው፡፡ አሁን የምንከተለው የአንድ ቋንቋ ፖሊሲ የሚያዋጣ አይመስለኝም፡፡ለዚህ ነው ኢትዮጵያውያን በየትኛውም ክልል ተዘዋውረው ሲኖሩና ሲሠሩ ነጻነት እንዲሸታቸው፤ ደኅንነት እንዲሰማቸው ማድረግ የሚያስፈልገው፡፡ ኢትዮጵያውያን ነጻነትና ደኅንነት የሚሰማቸው በክልላቸው ውስጥ ብቻ ከሆነ ዐውቀንም ይሁን ሳናውቅ በአንዲት ሀገር ውስጥ ሊግባቡ የማይችሉ ብዙ ሀገሮች እየፈጠርን ነው ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 2. Please see for yourself how your articles contradict each other at times. For example, how are you going to reconcile this article with your previous article titled "Mejemeria Sew Negn"?

  ReplyDelete
 3. Nice view.Thanks dani. የሕዝቦችን ቁስልም ለገበያ የሚፈልጉት አካላት ይኖራሉ፡፡

  ReplyDelete
 4. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳኒ፠ለገና በሀል የተቸጋጀው ፕሮግራም ላይ የሰጠሀቸው መልሶች በጣም ያኮራ ነበር፠መድሀኒያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 5. "Ze bo ezn semi'a leysma!" Joro yalew mesmatin ysma! Liul Egziabher tenahn ystih, mastewalun ayaguadlibih.

  ReplyDelete
 6. what an article Dani!!! readers of this article please share the link of article or the article itself by mentioning the source at least for 15 people. and if possible please discuss your friends also.

  Thank you Dani

  ReplyDelete
 7. Hi, Dani I love your idea but at this time it looks like difficult because this government think if Amhara and Oromo come together; it will be hard to continue on the leadership chair. For the past ten years when people asked me about my region I said I am an Ethiopian. Some people don’t like my idea then they didn’t want to be my friend. I don’t have any problem when I spend my time in Addis but when I go all other region except Amhara region. Life will be difficult to me because I don’t speak their languche. I born in Addis Ababa, my mom is from Oromo and my father is from Gurage but I speak only Amharic. My wife from Tigray so I fell I am an Ethiopian not from this or that region. God bless you for your hard work.

  ReplyDelete
 8. በርግጥ ሕመም የህልውናቸው መሠረት የሆኑ አካላት አሉ፡፡ ልክ አንዳንድ ነዳያን ቁስላቸውን ለልመና እንደ ሚጠቀሙበት፤ ከቁስል መዳናቸውን ሳይሆን ራሱን ቁስሉን ለገበያ እንደሚፈልጉት ሁሉ የሕዝቦችን ቁስልም ለገበያ የሚፈልጉት አካላት ይኖራሉ፡፡ የሚያተርፉት ከቁስሉ በመሆኑ ምንጊዜም ስለቁስላችንና ማን እንዳቆሰለን እንጂ እንዴት ልንድን እንደምንችል አይነግሩንም፡፡ መድኃኒቱን አያሳዩን፡፡ ቁስለኞቹ ግን መዳኑን እንፈልገዋለን፡፡ ለዚህ ነው ማከም አለብን የምለው፡፡ አንድ በሽተኛ የሕመሙን ዓይነትና ምክንያት ማወቁ ብቻ ለድኅነት አያበቃውም፡፡ እንዴት ሊድን እንደሚችል ማወቅ፣ መድኃኒቱንም ማግኘት ይበልጥ ይጠቅመዋል፡፡ በኢቦላ በሽታ ያለቁ የምዕራብ አፍሪካ ወገኖቻችን፣ የበሽታውን መነሻና አስተላላፊ ዐውቀውታል፡፡ የቸገራቸው መድኃኒቱ ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. Thanks Dn. Daniel
  የሚሰማ ካለ ሁሉን ብለህዋል
  This 'government' is running people relationship on propose. And there are other groups trying to benifit from the chaso. God is above all our problems. He isn't gonna let us down.

  ReplyDelete
 10. This is what i always expect from Dani to write up on! This is my believe on Nationalism and Regionalism. you have written the issue clearly and briefly, Thanks Dani!
  I wish most Ethiopian should keep this attitude if we want to live together long and in peace!

  ReplyDelete
 11. ይህ አሳብ የአንተ ብቻ እና የጥቂቶቹ ነው፡፡ ችግሩ ቁስሉ እንዳይድን የሚፈልጉ አካሎች አሉ፡፡ በቁስሉ ለመኖር የሚፈልጉ፣ ለቁስለኞች የማያስቡ ሁሌ እንዲጠዘጥዛቸው ጨው የሚጨምሩ….፡፡ እግዚአብሔር ይጠብቃት እንጂ፡፡ ተዋሕዶ በተዐቅቦ ግን ከባድ ነው- ለወልደ እግዚአብሔር ብቻ የተቻለ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 12. ኢትዮጵያን ወደ ልዕልና እንውሰዳት

  ReplyDelete
 13. ....2. “የአንድነት ፓርቲዎች (በተለይም አማራዎች) ትንሿን የፌደራሊዝም መብታችንን እንኳን ሊቀበሉ ዝግጁ አይደሉም” ጀዋር መሃመድ ብሄርተኝነት አይንን እንደሚከልል ቢታወቅም ይሄን ያህል ግን እንደሚያሳውር እና አንድ የማሰቢያ አእምሮን ቆርጦ እንደሚያወጣ በጀዋር እና መሰሎቹ መረዳት ችያለው። እንዴት ነው ነገሩ እነሱ (ትህነግ፤ኦነግ ወዘተ) ያሉትን የብሄር ፌደራሊዝም (ያውም የአማራውን ብሄር መብት ያላካተተ የብሄር ፌደራሊዝም) አለመቀበል ማለት አጠቃላይ የፌደራሊዝምን ስርአት አለመቀበል ነው ያለው ማነው? በድሮው ስርአት አልተወከልንም ድምፃችን አልተሰማም የሚል ወገን እንዴት ነው 1/3 የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አማራው ባልተወከለበት የተካሄደ የመሬት ሽንሸና ያለማመንታት ተቀበሉ የሚሉን? ሲጀመር ድሮም አሁንም እኮ አማራው ደሃ ነው ጥቂት የአማራ ልሂቃን ናቸው አገሪቱን ከሌላው ብሄር ልሂቃን ጋር ሆነው የጨቆኑት ያደሞ የኦሮሞ ልሂቃንንም ይጨምራል ሲባሉ የለም እነኛ ኦሮሞዎች ኦሮሞን አይወክሉም ይሉናል። እኔምለው መቼ ነበር አማራው ታዲያ ይወክሉኝ ብሎ ልሂቃኑን ልኮ የተወከለው በቃ የተደራጀ ጉልበት ያለው ያሻውን አድርጎ አለፈ እንጂ። ከቀደሙት መሪዎች መልካም ነገራቸውን ተምረን ጥፋታቸውን እንዳይደገም አድርገን እንለፍ ሲባሉ የለም መጀመሪያ ይሄንን ተቀበሉ ይላሉ አለበለዚያ በደፈናው ስም ይሰጥሃል። ስታስቡት በሰሜን ትግራይ በምስራቅ አፋር በምዕራብ ቤኒሻጉል በደቡብ ደሞ ኦሮሚያ እያላቹ አጎቶችህ ኦነግ ከትህነግ ጋር ተስማምቶ አማራንም ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ህዝበ ውሳኔ ሳይጠይቅ የተፈጠረ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ባንቱስታን ስታይል አከላለል ተቀበሉ ስትሉ አታፍሩም? አዲስ አበባን ጨምሮ ቁጥራቹ ያነሰበት ቦታ የለም በታሪክ የኛ ነበር ትላላቹ ልክ ምድር ስትፈጠር ጀምሮ እዛ ቦታ የኖራቹ ይመስል (ታሪክ የ 200 አመት ብቻ ሳይሆን 500 ከዛም 1000 ከዛም 3000 እያለ ይቀጥላል ቅንጭብ አድርጋቹ አትውሰዱ)። ያውም እንደኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሲቪል ዋር ውስጥ ባለፈች ህዝብ ከቦታ ቦታ በጦርነት በረሃብ በተለያየ ምክንያት በሚሰደድባት በሚቀላቀልባት ሃገር ይሄ ቦታ የኛ ብቻ ነው ሲባል እንዴት ሰው አያፍርም። እህ በአማራ መካከል በዛ ያለ ኦሮሞ ሲኖር ደሞ አማራ ብላቹ ቁራጭ ከሰጣቹት መሬት ላይ ልዩ ዞን ምናምን ተብሎ ለብቻ ይከለላል። ምነው ኦሮሚያ የተባለው ክልል ውስጥ በርካታ አማራ ያለበት ቦታ ልዩ ዞን አልተፈቀደም? አማራው የመምረጥ የመመረጥ መብት አለው ኦሮሚያ በተባለው ቦታ ሁሉ ነው ያልከው ሳታፍር በዛውም የትህነግን የምርጫ ድራማ እያፀደክላቸው ማለት ነው? እስቲ ሃረር ድሬዳዋን እንመልከት አማራም ኦሮሞም ሃረሪም ሶማሌም ሌላውም አለ ነገር ግን ተለይቶ አማራው መብቱ እንዳይከበር እና በሌሎች መልካም ፍቃድ እንዲኖር የተደረገበትን ስርአት ነው እንግዲህ ልክፍተኞቹ ያለድርድር ተቀበሉ የምትሉት? አሳፋሪ ነው። የሁሉንም መብት የሚያከብር ሁሉን አቀፍ የሆነ ስርአት ማሰብ አትፈልጉም። አገሪቱ ብሄራዊ ቓንቓ ሳይኖራት የተለያየ አገር ከምትሆን (አሁን አማርኛ ፌደራል ቓንቓ ብቻ ነው) ቢሆን ህዝቡ ከመረጠ ሁለት ብሄራዊ ቓንቓ ይኑራት እና አንድ ሰው ሌላ የሃገሪቱ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሃገር የሄደ ይመስል አዲስ ቓንቓ ያውም ብሄራዊ ቓንቓ ያልሆነ ማጥናት ሊገደድ አይገባም ቓንቓ ማወቅ መልካም ቢሆንም ሲባል የድሮ ስርአት ናፋቂዎች ትላላቹ እንዲህ ያለ ቢቻል ሁለት ብሄራዊ ቓንቓ ይኑረን የሚል ሃሳብ ድሮ ያለ ይመስል።...

  ReplyDelete
 14. In Amhara, the constitution also provides for the establishment of aConstitutional Interpretation Commission. However, as opposed to
  the Oromia constitution, the Amhara constitution does provide for a guaranteed representation of ethnic minorities in this commission.
  The Commission consists not only of members nominated fromeachWereda
  council, but also from each Nationality Council (this is
  the legislative council of the Nationality Administration).
  Amhara constitution provides for the establishment of a NationalityAdministration for three ethnic minority groups in the region: theOromo, Himra and Awi. As such, the representation of these three
  ethnic minority groups in the regional organ for constitutional
  interpretation is guaranteed!

  ReplyDelete
 15. You raised the most critical problem of our country. Because of bad incidence in the past, there are still problems associated to self determination. I some regions of our country, the concept of self determination was extended beyond limit and affecting the life of money people. I agree with most of the solutions you proposed. But, when we come to language, it is very difficult and to costly to select a language to be used as a working language or to be given in a school. In Ethiopia, there are more than 80 languages spoken..If we agree that all languages are equal as far as they serve for communication, how do we select one language and leave the other. For instance, You have included Welayita in your list, but Guragigna was spoken by money people than Welayita did. This kinds of issues will lead to so many problems. My proposal for our country is to use International language ( English) as working or school language through out the country uniformly and on top of this each regional states or nations and nationalities can also develop their own mother tongue language if they wish. of course their might be some inconvenience until English is adopted at least for 20 years. But this is temporary. I think this will avoid inferiority complex which is the cause for most the problems in our country.

  ReplyDelete
  Replies
  1. do not seek and love foreign language keep your and try to empower yours and continue to find how to compromise our challenges

   Delete
  2. English as a national language??that is NOT a solution and CANNOT be a solution.yihe tilik widket new mihonew.kuaun eyetetekemin masadeg engi belea eyeteku megdel meftihe ayhonim::

   Delete
 16. Melktu. Ejiig bizegeyim tiru naw . Bene emnet gin it is too late

  ReplyDelete
 17. ውድ ዳኒ ይህን አስተውለከዋል?
  ምክንያት ካለክ ጥሩ እኔ ግን ፈራው በጣም ታስፈልገናለአ
  2014-78
  2013-96
  2012-119
  2011-148
  2010-123
  መልካም ጊዜመልካም ጊዜ

  ReplyDelete
 18. Dn, Daniel , Thank you so much God bless you. This is really fabulous current views.thi s is what our country and people ( We Ethiopian ) needs to admire our difference and believe in unity. None of us can't be a part without the whole. The party who benefitted with the isolation of the part from the whole whistle as if they feel the pain , while the truth is that ,they want to destroys the name Ethiopia and Ethiopian nation from the dictionary and the world map that is why in the name of autonomous region what is going on currently in our country . We should think in unity by respecting the dignity of regions , culture, norm, language and all customs of individual. GOD BLESS THE LAND OF ETHIOPA AND THE PEOPLE NATION AND NATIONALITY OF ETHIOPIA.YE KIDUSAN AMELAK YERDAN,

  ReplyDelete
 19. Here is an issue you should bow out b/c it is way beyond your intellectual capacity!

  ReplyDelete
 20. Thank you Dn ,
  I think lots of countries wants to have bilateral relationship, which indicates by being closure is better for their interest. Also what a great idea to have knowledge of at least two Ethiopian languages. as a requirement if everyone agrees.

  ReplyDelete
 21. A t thi s point we ca n already se e difference s betwee n th e Amhara and th e Oromi a constitutions in the ways they handle ethnic diversity . The first significant provisions are in the preamble . Th e preamble of th e Amhara constitution refers to the peoples of the region , whereas the Oromia constitution refers to the Oromo people . This illustrate s different constitutional attitudes towards diversity : a positiv e attitude in Amhara , a negative one in Oromia . The constitutional provision so n sovereignty reinforce this attitude . In the Amhara constitution , sovereign power in the region is exercised by the different peoples but in Oromi a by th e Oromo people . The sam e attitudes ca n b e found in the provisions for the composition of the respective regional parliaments . The Amhar a constitutin recognises that the first past the post electoral system in an ethnically organised state carries dangers for the representation of ethnic minorities , hence its provision for the guaran - teed representation of ethnic minority groups . The Oromi a constitution pays no attention to the representation of minority groups ; the association of the region with the Oromo people leaves no room for it . Th e Oromi a constitutio n o f 1995 , jus t lik e othe r regiona l constitutions , als o provide d fo r a ver y specia l mechanis m o f constitutiona l interpretatio n unde r whic h th e powe r t o interpre t th e constitutio n wa s give n t o th e regiona l parliament . This was a clear infringement of the nemoiudex in suacausa principle . However , the constitutiona l amendment o f 2001 created a new institution fo r constitutional interpretation : the Constitu - tiona l Interpretation Commission . This Commission consists of a representativ e nominate d from each district council. Since the districts in Oromia are not ethnically based , there is no guarantee that member so f ethnic minoritie s (non Oromo ) will be represented in this commission . In Amhara , the constitution also provides for the establishment of a Constitutional Interpretation Commission . However , as opposed to the Oromia constitution , the Amhara constitution does provide for a Art . 6 7 (1 ) guarantee d representation of ethnic minorities in thi s commission! http://www.gap.ugent.be/africafocus/pdf/07-20-12-Vanderbeken2.pdf

  ReplyDelete
  Replies
  1. I did not even know we have all kinds of constitution in my poor beloved country. What a disaster for waiting. EGZIER YETADEGEN

   Delete
 22. The fact that article 2(1 ) o f the regional constitution recognises that Oromia is populated by "people of the Oromo nation and other peoples", article 8 stipulates that "Sovereign power in the region resides in the people of the Oromo nation. " The fact that "people of the Oromo nation" refers exclusively to people of the Oromo ethnic grou p ca n b e deduce d fro m articl e 39(6 ) o f th e Oromi a constitution : "For the purpose of this constitution, the expression 'the people of the Oromo nation' shall be construed as meaning those people who speak the Oromo language, who believe in their common Oromo identity, who share a large measure of a common culture as Oromos and who predominantly inhabit in a contiguous territory of the Regional State. " Thus , th e sovereig n powe r i n Oromi a doe s no t resid e i n th e variou s ethni c group s o f th e region , bu t i n th e Orom o ethni c group . Fro m her e i t follow s tha t th e regiona l parliament , th e Caffee, shoul d no t b e perceive d a s th e representativ e institutio n o f th e populatio n o f Oromia , bu t a s th e representativ e institutio n o f th e Orom o ethni c group . Severa l othe r element s suppor t thi s conclusion . First , unlik e th e Amhar a constitution , th e Oromi a constitutio n contain s n o provision s fo r th e guarantee d representatio n o f ethni c minorit y group s i n th e regiona l parliament . Second , w e ma y not e tha t th e Caffee elect s exclusivel y Orom o representative s t o th e federa l Hous e o f th e Federation . Consequently , th e Amhar a livin g i n th e Oromi a regio n ar e represente d i n th e Hous e o f th e Federatio n onl y b y member s electe d b y th e Amhar a regiona l parliament . Finally , w e ma y not e th e regiona l constitutiona l provision s o n th e righ t t o secession . Articl e 3 9 (4 ) o f th e federa l constitutio n stipulate s tha t a deman d fo r secessio n mus t b e approve d b y th e legislativ e counci l o f th e nation , nationalit y o r peopl e concerned . Thi s provisio n ha s bee n include d i n articl e 3 9 o f th e Oromi a constitution . Articl e 3 9 (5 ) o f th e latte r constitutio n stipulate s tha t th e "Demand for secession is approved by a two thirds majority vote of the members of the caffee. " No r d o Oromia' s constitutiona l provision s o n th e regiona l executiv e an d judicia l organ s contai n provision s fo r guarantee d representation . Ethni c minorit y group s i n Oromi a hav e n o righ t t o territoria l self - administration . Th e Zona l administrativ e leve l i s no t a n ethnic-base d territoria l entity , bu t a n executiv e orga n o f th e regiona l administration .

  ReplyDelete
 23. ሰላም ዳንኤል መልካም ሀሳብ አንስተሀል በአንደኛው ላይ ግን በግሌ አልስማማም እሱም ‹‹አንድ ተማሪ ከክልሉ ቋንቋና ከፌዴራሉ ቋንቋ በተጨማሪ ቢያንስ ሁለቱን ጨምሮ እንዲማር መደረግ አለበት›› በሚለው ነው ያልተስማማሁበትም ምክንያት በእውነት ቋንቋ መቻል ዘረኝነትን ሊያጠፋ ይችላልን? በርግጥም እንደኔ ዘረኝነት ከቋንቋ በዘለለ አመለካከት ነው፡፡ ሰዎች ከዘረኝነት አስተሳሰብ ሳይወጡ የሌሎችን ቋንቋ ቢችሉም ባይችሉም ምንም ለውጥ የለውም ነገር ግን ከዘረኝነት አስተሳሰሰብ የወጣ ማህበረሰብ ካለ ቋንቋውን ባያውቅ እንኳ በፍቅር መግባባት ይችላል፡፡ ፍቅር ካለ ደግሞ አደለም መግባቢያ የሆነውን ቋንቋ ሌሎችንም በቀላሉ ያለ ትምህርት ቤት መልመድ ይቻላል፡፡ ሌላው አዋጭ መፍትሄ አይደለም ያልኩበት ምክንያት አዲስ አበባ ዙርያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ላይ ያለው ተሞክሮ ነው የክልሉ ቋንቋ ስለሆነ በግድ እንደ አንድ ትምህርት ይሰጣል የብሄሩ ተወላጅ ያልሆኑት ግን በጥናት የተረጋገጠ መረጃ ባይሆንም አብዛኛዎቹ ከትምህርት በዘለለ የአካባቢው መነጋገርያ ቋንቋ ሆኖ እንኳን ቋንቋውን አይለምዱትም ወይም ለመልመድ አይፈልጉም በአጠቃላይ የነጮች እና የጥቁሮችን የዘረኝነት ታሪክ ብናይ አንድ ቋንቋ እየተናገሩ እንኳን መቀረፍ አልቻለም ስለዚህ መፍትሔው እና ቀዳሚው ስራ እንደ አንድ ልብ መካሪ አንድ ሀሳብ ተናጋሪ የሚያደርግ ህብረ ልቦናን እንዲሰጠን መለመን ነው

  ReplyDelete
 24. ጥሩ ፅሁፍና ፣ተወያይቶ ለመግባባት፣ የሚያስችል ዕውነታን የያዘ ነው ጥሩ ልብ ካለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የሰፈነው የግፍ ስርዓት ይህን አይፈቅድም፡፡ ሲጀመርም ኢትዮጵያን ከፋፍሎ ለማጥፋትና አሻራዋም ከምድር እንዲፋቅ የዚህ የግፍ ስርዓት አጀንዳ ስለሆነ ስለኢትዮጵያዊነት ማውራት ሞኝነት፣ከሃዲነት፤አሸባሪነት፣ወዘተ….. ነው፡፡ እንደኔ ኢትዮጵያዊነትን ማጉላት በዘመኑ አነጋገር አናሳ (አናሳ ብሎ የለጠፈባቸው ስርዓቱ ነው ቃሉንም ስጠቀመው ያመኛል) ማጥፋት ወይም ማንነታቸውን ማደብዘዝ አይደለም፡፡ ለሚገባውና ጥሩ ልብ ላለው ኢትዮጵያዊነት አንድ ያደርጋል፡፡በቁጥር ትንሽ መሆንን ለመግለጽ አናሳ ከሚለው (በብዛት ትንሽ) አጅግ ይሻላል፡፡
  ተንኮለኞቹ ጣልያንና እንግሊዝ ጀምረውት ያልተሳካላቸው የከፋፍለህ ግዛ ቅኝት በወያኔ ተግባራዊ እየሆነ ሰውን ከሰው እያባላ ነው፡፡ በስራ አጋጣሚ በ2000 ዓ.ም. ጋምቤላ ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር የደረሰብንን መንገላታት አስታውሳለሁ፡፡ እኛ እስከሚገባን ይህ መሬት የሚገኘው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ሱዳን ውስጥ የሰው መሬት የረገጥን ፣ለስራ ሳይሆን ዳረጎት ልንለምናቸው የሄድን እስኪመስለን ድረስ ተሳቀናል፡፡አበሻ ናችሁ የሰው መሬት ላይ ምን ታደርጋላችሁ ተብለናል፡፡ በእግዚአብሄር ቸርነት ወደ ከተማችን ተመለስን እንጂ በፖሊስ ዱላ ከመደብደብ አልተረፍንም፡፡ ቅርጹ ይለያል እንጂ ተመሳሳይ አደጋ በ1998 ነቀምት ላይ ገጥሞኛል፡፡የቆዳ ቀለም ይህን ካስከተለ እንግዲህ አይፋቅ፡፡
  ሁሉም በቀEንቀEው ቢማር፣ቢግባባ ራሱን ያሳድጋል ሀገር ይጠቅማል እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ገና ለገና አማርኛን በመጥላት ብቻ (Over ambitious) መሆን ግን እርባና ቢስ ያደርጋል፡፡ ልብ እንበል ጥልያን አድዋ ላይ በትግራይ መሬት ድል ሲደረግ እኮ ኢትዮጵያውን ናቸው በንጉሰ ነገስታቸው እየተመሩ የዘመቱትና አኩሪ ገድል ያስመዘገቡት፡፡ ክልል፣ብሄር፣አናሳ፣ብዙ፣አማራ፣ትግሬ፣ወላይታ፣ጉራጌ፣ሀመር፣እዚህ ላይ አይሰራም፡፡ አሉታዊ ውጤቱም በዜሮ ይባዛል፡፡ፖለቲከኞች ለጥቅማቸው ሲያባሉን መሳሪያቸው አንሁን፡፡ ሞኛችሁን ፈልጉ እንበላቸው፡፡ ያኔ ኢትዮጵያ ትለወጣለች፡፡ አለበለዚያ የምናውቃቸው እንደሚሉት ልዩነታችን ውበታችን ሳይሆን -- ልዩነታችን ነቀርሳችን ሆኖብናል፤፤ ነቀርሳ ደግሞ አይድንም፡፡

  ReplyDelete
 25. በርግጥ ሕመም የህልውናቸው መሠረት የሆኑ አካላት አሉ፡፡ ልክ አንዳንድ ነዳያን ቁስላቸውን ለልመና እንደ ሚጠቀሙበት፤ ከቁስል መዳናቸውን ሳይሆን ራሱን ቁስሉን ለገበያ እንደሚፈልጉት ሁሉ የሕዝቦችን ቁስልም ለገበያ የሚፈልጉት አካላት ይኖራሉ፡፡

  ReplyDelete
 26. Hulachin kezi melketa memar alebin. Deacon Dani, Emebete Mariyam Aimrohin ene Ejochin Degagma Tibark.

  ReplyDelete
 27. ከእሾህ ወይን አይለቀምም፡፡ ከስጋዊያን ሰዎች መንፈሳዊ ፍሬ አይገኝም፡፡ ዛሬ አንዳንዶች ብሔረተኝነትን እደሃይማኖት እየቆጠሩ ዓይናቸው ታውሮ ስለ ነፍሳቸውና ስለእግዚአብሔር ስለ ሰማያዊ ህይወት አያስቡም፡፡ ስለዚህ የምድሩ መንፈስ የተቆጣጠራቸው ናቸው፡፡ በእርግማን የመጣውን የÌንÌ መለያየት እንደ መባረክ(ብሌሲነግ) ቆጥረው ልዩነታችን ውበታችን ነው ይላሉ፡፡

  ReplyDelete
 28. አይነኬውን ከነካኸው ዲያቆን ዳንኤል ምን ይደረግ ልጠይቅ ነው።

  ልሂቃኖች÷ታላላቆች÷ ገብቷችሁ ሃገር እየመራችሁ ወይም ፓርቲ አቋቁማችሁ ሀገር ለመምራት ለምትሰናዱ ሁሉ....እባካችሁ ጥያቄዬን በሚገባኝ ቋንቋ (አማርኛ) መልሱልኝ ይግባኝ ልረዳው...... መቼም ሌላውም ትውልድ ተጋሪዬም ተበረታቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም ጥያቄ እንዲጠይቃችሁ

  እኔ የደርግን ስርአት የምሬን ነው አላውቅም (ያው አራድኛው ይገባችኋል ወጣትነቴን ለመግለጽ ነው ÷ ያንኛውን ስርአት... ምናምን... ናፋቂ ተብሎ ጥያቄዬ ሳይመለስ እንዳይድበሰበስ ብዪ እኮ ነው)። በዚህ አጋጣሚ ጠያቂ እንዳልጠፋ ህያው ምስክር እንደ ዲያቆን ዳንኤል (መቸም እድሜ ከጤና ይስጥህ ሌላ ምን ይባላል) አስቴር በዳኔ ደግሞ መጥታለች። "የጥበብ ሰዎች" ሁሉም ስለ ገንዘብና ዝና ሲባል ዘመኑን ሲመስሉና ሲሸጎጡ እሷ ግን ባለስልጣናትን (ሪፓርተር ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ) የጠየቀችው ጥያቄ ዋዋዋዋው .... ብቻ ምስጋና ይድረስሽ። መላሽ ባይገኝም! ለካ የአንድ እጅ ጣት አትሞሉም እንጅ ለካ ሰው አለን። ደግሞም ከባረካችሁ ትበቁናላችሁ። ዲያቆን ዳንኤል ስለሁሉ ነገር አብዝቼ በቅድሚያ አመሰግንሃለሁ።

  "ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ ዕለት" ብሎ የለ ገጣሚው...

  ወደ ጥያቄዬ÷
  "ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች" የሚል ሃረግ በተደጋጋሚ ጆሮዬ ጠግቧል። ህገመንግስቱንም ውስጥ አለ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስቱ ራሱ ይሄ ሀረግ በጣም ተደጋግሞ በመጠቀሱ ምክንያት የህገመንግስቱ መገለጫ ጭምር መስሎ ይታየኛል ።

  ጥያቄዬ ታዲያ ብሔር ስትሉ ምን ማለት ነው? ኢትየጵያ ውስጥ ካለነው ማንን ይወክላል? ብሔረሰቦች ስትሉስ? የእንግልጣሩ ፍቺ Nationality ብሔረሰቦች ለሚለው አማርኛ ቃልስ እንዴት ልኩ ሆኖ አገኛችሁት? ዜግነትን በእንግልጣር አፍ ተርጉሙልኝ እስኪ? Nationality ማለት አይደለም ወይ? ብሔራዊ ቡድናችን ሲባልስ? የትኛው ብሔርን ነው የሚወክለው? ህዝቦች ሲባልስ ማንን ለመግለጽ ነው? ለህዝብ ደረጃ ያልበቁ እንዲሁም ህዝብ ያልሆኑስ አሉ እንዴ?

  ሌላው ጥያቄ ከማብራሪያ ጋር ስለ ቋንቋና ዘር (ዘረኝነት) ኧረ አንድ በሉኝ... በተለይ የዘር ልዩነት አለ ብላችሁ የምታስተምሩን...

  "አባቴ ኦሮሞ ነው" ሲባል ኦሮሞ የሚባል የአይኑ ቀለም የተለየ ደም ግባትና መልኩ ከሌላው ኢትየጵያዊ የማይገጥም ዘር ያለው "ኦሮሞ" የሚባል ዘር ያለ አስመሰላችሁት እኮ።

  "አባቴ ኦሮሞ ነው" ማለት ለኔ "የአባቴ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ኦሮምኛ ነው" ማለት ነው። That much so simple. አባቴ ኦሮምኛ ተናገረ ማለት ደግሞ ሌሎች ኦሮምኛ ከሚናገሩ የአካባቢው ሰዎች ጋር እና ቋንቋውን ከሚችሉ ሌላ አካባቢ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ይግባባበታል ማለት ነው። Period. ኦሮምኛ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ አለባበሱ ÷ አኗኗሩ ወዘተረፈ ቋንቋውን ይምሰል ከሆነ... ይሄ ፍጹም አላዋቂነት ይመስለኛል። ሲጀመር ቋንቋ ሃሳብን መግለጫ ÷ መግባቢያ እንጂ ባህልን አይወክልም። ያ ቢሆንማ እንግልጣር ተናጋሪ ሀገር ሁሉ ባለ አንድ አይነት ባህል ባለቤት በሆነ ነበር። አውነታው ግን ሌላ ነው።

  አግዐዝያን (ግዕዝን እንደ መግባቢያ ሲጠቀሙ የነበሩ ህዝቦች) ተወካያቸው ለምን ምክር ቤት አልገባም? ምክንያቱም አሁን ግዕዝን የሚጠቀም አለማዊ ነዋሪ ስለሌለ። ያ ማለት አግዐዚያን ዘራቸው ከምድረገጽ ጠፍቷል ማለት ነው እንዴ? አይደለም በፍጹም አይደለም እነሱ እኛን ያስገኙን አባቶችን ናቸው እንጂ።

  በኢትዮጵያ ታሪክ የእንትን ቋንቋ ተናጋሪ ከእንትን ቋንቋ ተናጋሪ ጋር እንዳትጋባ ÷ እንዳትዋለድ ወይም ጉዲፈቻ እንዳትሰጣጥ ተብሎ የተነገረ አዋጅ አልነበረም ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ ኦሮምኛ በሚናገረው አባቴ ወገብ ውስጥ ስንት ቋንቋቸው የጠፋና ዛሬም ቋንቋቸው ያለ ሰዎች ዘረ መል (ጂን) እንዳለ ከፈጣሪ ሌላ ማንያውቃል? ሳይንሱም የሚያውቅ አይመስለኝም።ለዛስ አይመስላችሁም የኔን ፎቶ ተለጥፎ ብታዩ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬን መገመት የሚከበብዳችሁ።

  እንደው ፍቃዱ ሆኖ መልካችን ተመሳሰለ እንጂ እኛማ እንዳያያዛችን የአይናችን ወይም የፀጉራችን ቀለም ቢለያይልንማ ተቧድነን መጫረስ ነበር ስራችን የሚሆነው። (በሂደት የጠፋ እና የተዋሃደ አንድነት ያለው ዘር ሆነን ተገናኘን እንጂ ሂትለር ኧረ ይሻላል በስንት ጣዕሙ እንባባል ነበር)

  አባቴ ክትፎ በላ ማለት "ጉራጌ" የሚባል ዘር አባል ሆኗል ማለት ነው? ጉራጊኛ ተናጋሪ እንጂ ጉራጌ የሚባል ዘር አለ ወይ? መልሱልኝ አዋቂያን!

  አባቴ ኦሮምኛና አማርኛ አቀላጥፎ ስለሚናገር እባካችሁ ዘሩን ፈልጉልኝ ወረታውንም እከፍላለሁ ብዬ ላስለፍፍ ወይስ አባቴን ላስጨንቀውና ቀድሞ ከአፉ ያወጣትን ቃል አስታውሶ ከዛ ዘሩን ይንገረኝ? እኔም ከዛ "ኢትየጵያዊ ከመሆኔ በፊት አማራ ነኝ ወይም ኦሮሞ ነኝ ልበል?" እንዴት ነው የተቀለደዉ እባካችሁ?

  ኩራተኝነት ÷ ትምክህተኝነት ÷ ጎጠኝነት ÷ መናናቅ ሰይጣናዊ ምግባር ነው። ሰው ሰውን በስራው እንጂ በመጣበት አካባቢ ወይም በሚናገረው ቋንቋ ሰውን ከሰው ከለየ ÷ ከዛ ስራ ካስቀጠረ ÷ ካሾመ ÷ ካሸለመ ወይም ካሻረ ለእሱ ሱባኤ ሊያዝለት ይገባል (ክርስቲያን ከሆነ)። ዘመኑን አልዋጀማ... ድንቁርና ተጠናውቶታላ...

  ስታስተምሩን "ቋንቋ ይወለዳል ያድጋል ይሞታል" ብላችሁናል። እኛም አምነናል። ለምሳሌ ያህል እየተነጋገርንበት ያለው አማርኛ ተወልዷል ያድጋል ይሞታል በመጨረሻም በሌሎች ይዋጣል ወይም ይጠፋል። አማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ዘርና ትውልድ ግን ቋንቋው ተቀይሮ ሌላ ቋንቋ ይናገር ይሆናል እንጂ እንዴት ዘሩ ይጠፋል? ለምንስ በሚሞት ቋንቋ የማይሞት ዘርን እንወክላለን? የእውነት አልገባኝም...

  መፍትሔ
  1. ሁሉም በአካባቢው ያለውን ቋንቋ እንዲሁም ባህል ያክብር
  2. ሁሉም ዜጋ የፈለገውን ቋንቋ በፈለገበት ቦታ እንዲማር ሁኔታዎችን ማመቻቸት (ኢኮኖሚክ አቅማችንን ማሳደግ)
  3.የአፍ መፍቻ ቋንቋንና ማንነትን አለማደባለቅ (ማንነታችን ኢትዮጵያዊነታችን። በተረፈ ወንድሜን እንኳን መምሰል አልፈልግም እራሴን እንጂ let alone ብሔር ገለመሌ ... ማን እኔነቴን ይሆንልኛል እኔ ሌላ መስዬ?)
  4. እናንተ ጨምሩበት።

  አበዛሁ። ይቅርታ። ግራ ግብት ብሎኝ ነው።
  ዲያቆን ዳንኤል በርታ። አስተምረን። አምላክ ይርዳህ (መቸም የኃጥዕ ምርቃት..)
  አዲስ ነኝ

  ReplyDelete
 29. I read it 7 times. but i'm still in need of it. and i wish all ETHIOPIANS can get and read this interesting article.

  ReplyDelete