Tuesday, January 20, 2015

ቁስል ተራ

click here for pdf
የመርካቶ ግርግር

ዛሬ ወደ ቢሮ እየመጣሁ በሬዲዮ ስለ አጭበርባሪ ልመናዎች እየሰማ ነበር፡፡ ራሳቸውን በሽተኛ አስመስለው ስለሚለምኑ ሰዎች፡፡ እጃቸውን አጣምመው፣ ሰውነታቸው አቁስለው፣ ዓይናቸውን  የጠፋ አስመስለው፤ ጀርባቸውን አጉብጠው ስለሚለምኑ ሰዎች፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሚታየው የጉዳት ምልክት ምንም ዓይነት ጥርጣሬን የማያመጣ ነው፡፡ 

በሰማነው ነገር ላይ እየተወያየን ስንመጣ መርካቶ ‹ቁስል ተራ› የሚባል ቦታ አለኮ አለኝ አንድ ሰው፤ ‹‹ምን የሚደረግበት›› ብዬ ጠየቅኩ፡፡ ‹‹ቁስል የሚሠራበት›› አለኝ፡፡ ‹‹እዚያ ትሄድና ገንዘብ ከፍለህ የምትፈልገውን ዓይነት ቁስል ይሠሩልሃል›› አለኝ፡፡ አይ መርካቶ! አለ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፡፤ እስኪ የበለጠ የምታውቁ አካፍሉን፡፡   

26 comments:

 1. ልክ አሜሪካ እንደ ሚደረግ tatoo ማለት እኮ ነው ይገርማል!!!

  ReplyDelete
 2. ልመና የአብዛኛዉ ዓለም ባህል ነዉ:: የመንግስታት ሲሆን ስሙ ተሽሞንሙኖ ባዛር: ቴሌቶን : SMS መላኪያ : የብድርና እርዳታ ስምምነት ወዘተ ይባል እንጂ ያዉ ልመና ነዉ:: ቁስል ተሰራለትም ወጣበትም አንዱ የመኖሪያ መንገድ ነዉ:: ምናልባት አስገራሚዉ ነገር መንግስታት የልመና ማህተም ሲመታላቸዉ ግለሰቦችም የቁስል ማህተም የሚሰራላቸዉ ማግኘታቸዉ ነዉ

  ReplyDelete
 3. I feel shame about you when I read this article especially you mentioned the source. As you know that election is coming so this government wants destroy the homeless people so they started blaming the poor people. When the election time approach, the government will take all the homeless people to jail. At the movement they are working hard to change an Ethiopian mind. I don’t mean there is not cheater but the government social media play the game to attack the homeless people. If you remember before last election all media were talking about the countryside immigrant then they took them by force from Addis to other location. All Ethiopian have the same right to live in Addis Ababa.

  ReplyDelete
 4. Your topic has negative message and not proved. You just heard from news and you posted. I am ok that but you should change the photo instead of posting people photo for negative comment, you can post Merkato building photo. What do you feel for this topic if I post your mother photo? Please change the photo to respect other people mother, father, sister and brother. Thank you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What kind of comment this is my friend? You've completely missed the idea, so I urge you to read it again. As a heads-up though, here are a few corrections. First, Daniel didn't say he'd heard the info from the news, but someone who was with him at the time he heard the radio program told him. He's just telling us what he'd heard. Second, what is the "negativity" of this message? The post is about Merkato, and people are always part of Merkato. What's wrong with that? And your statement, "What do you feel for this topic if I post your mother photo?,"is irrelevant to the topic. So once again, please read the post thoroughly!

   Delete
  2. I am amazed how on earth your understanding of the content of the article lead to such a comment! አለቅናታ አለ ሰውየው....ከአንተን መሳይ ገልቱ ጋር ተቀላቅለን!!

   Delete
 5. I don’t like the title.
  Some Tigray people may want takeover Merkato so they want blame other before the fire start. You will see soon, fire will start in Merkato. Dani, you know that they say something before they destroy the place.

  ReplyDelete
 6. ጤና ይስጥልኝ ወዳጄ ዲ/ን ዳንኤል በእውነቱ ይህ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ የማህበረሰባችን ጠንቅ ነው። ይሄ የዛሬው ርእስህ አንድ በቀይ ሽብር ዘመን ተመሳሳይ ነገር እያደረጉ ወጣቱን ይታደጉት የነበሩን ግለሰብ አስታወሰኝ። በዚያን ጊዜ የታሰሩ ወጣቶችን የገረፉ ለማስመሰል እግራቸውን በግራሶ ቀብተውና በፋሻ አሽገው ከእስር ቤት ይፈቱ በነበሩ ነውና ለልመና ይህን በሚያደርጉ ሰዎች መካከል ያለውን የስብእና ልዩነት እንዴት የሰው ልጅ የዚህን ያህል......

  ReplyDelete
 7. እኔ የማውቀው መርካቶ እንዲህ አይነት ሰም አልነበረውም፠ማን ይሆን ይህን የሚያደርግ?ለምን? የሀገሬ እዝብ እኮ ደግ ነው፠ለመስጠት ቁሰል ማየት አይፈልግም፠አምላከ ቅዱሳን የኢትዬጸያን ትንሳሔ አሳየን አሜን አሜን!!!

  ReplyDelete
 8. ስለእዉነት ለመናገር እንዲህ የሚባል ነገር ስለመኖሩ ያነበብኩት ዛሬ ነዉ፡፡ ግን እንዲህ ዓይነቱ ነገር ቢኖርም አይገርመኝም፤ምክንያቱም በእየመንገዱ ዳር በልመና ስራ የተሠማሩ ወገኖቻችን ላይ የምንመለከተዉ ነዉ፡፡ በእዉነት ለእኔ ግን የተሰማኝ ስሜት የሚደብር ነዉ፤ያለዉን እዉነታ ለመቀበል ተቸግሬም ቢሆንም፡፡ ነገሩን ልብ ብሎ ለተመለከተዉ ግን እንዲህ ዓይነቱ ተግባር ከአሻባሪነት የማይተናነስ ወንጀል ነዉ…….

  ReplyDelete
 9. This is not new for me.....although i don't remember the exact date,but i have heard such things from sheger fm presented by Wondimu Hailu......if i am mistaken sorry for all.....

  ReplyDelete
 10. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 11. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውJanuary 25, 2015 at 12:48 AM

  ቦለቲከኛው/ መምህር/ ዲያቆን/ ጋዜጠኛ/ ጦማሪ/ ደራሲ ዳንኤል ክብረት እንደምን አለህ ? እኛ ሰፈሮች ሁሌም ቆሽጣችን ከመብገኑ በስተቀር የኢትዮጵያችን አምላክ ይመስገንና ከመጠን በላይ ደህና ነን። ግን የበግነት ፀባይ ከቶ የሌላቸው፣ በንቃትና በአንክሮ ነገሮችን ማየት የሚመርጡ፣ አንተንም በደንብ አድርገው በጎሪጥ የሚታዘቡ ሰፈርተኞች እንዳሉ ብታውቅ ጥሩ ነው። አንድአንዴ ፈሪሃ እግዚአብሄር በናንተ ሰፈር በኩል ዝር የሚል እንኳን አይመስለንም። ብዙውን ጊዜ የአንድን ማህበረሰብ አመለካከት የማነፅ፣የመሞረድና የመበረዝ ችሎታና፤ ባጋጣሚ የሃላፊነትም ቦታ ላይ የተኮፈሱ ግለሰቦች የፈሪሃ እግዚአብሄር ውሃ-ልካቸው ሲመዘን፤ በውስጣቸው ትንሽ ቅንጥብጣቢ እንኳን የማይገኝ ሆኖ እናገኘዋለን። ይኼ ደግሞ በሃይማኖት ስም በሚቅበዘበዙ ሰዎች ላይ ጎልቶ ይታያል። ምክንያቱም አድማጮቻቸውና ተከታዮቻቸው ልባቸውን ከፍተው፣ ጆራቸውን ቀስረው፣ አይኖቻቸውንም አተኩረው ያልዋቸውን ሳያጣጥሙና ሳያኝኩ ስልሚሰለቅጡት ነው። አሁን በገብርኤል እንዴት አንተ ራስህ በዓይንህ ያላየኸውን ነገር አምነህ፣ ተንደገና ደግሞ አንባቢዎችህን ደግሞ እንደዚህ አይነት ወሬ ካላችሁ አካፍሉኝ ብለህ ትጠይቃለህ ? የአየር ሞገድ ዜና ስርጭት አቀናባሪዎችም እኮ መርሆ ይዘው እኮ ነው የወሬ ዘመቻቸውን የሚነዙት። ይሄኔኮ ራሳቸው በአሁን ሰዓት በመቅረፀ-ምስል የተቀዳ ትዕይንት እያቀናበሩ ሊሆን ይችላል - ከነመረጃው እጅ ከፈንጅ ያዝናቸው ለማለት። ከተቻለ ደግሞ አንተው ራስህ ሠርጎ ገብ ጋዜጠኛ ሆነህ፣ድሪቶ ልብስ ተከናንበህ አገልግሎታቸውን ለመቀበል፣ መርካቶ እዛው የተባለው ሰፈር ሂድና ዘገባውን አቀናብረህ አካፍለን። "እንደዚህ እኮ ተባለ" - "እንደዚህኮ አሉ ጎበዝ" ብሎ ወሬ ማሰራጨት በቤተክርስትያናችን ውስጥ ባለህ የሃላፊነት ቦታና፣ ለምስኪን በግ ተከታዮችህ ስትል እንኳን ከንደዚህ አይነት የቡና ሃሜት ተግባር ብትቆጠብ ጥሩ ነው። ያልከው ነገር እውነት ሆኖ ቢገኝስ ምንድን ነው የሚያስደንቀው ? መንግስት ተብየው አካል ራሱ በልመና የሚተዳደር የበድኖች ጥርቅም አይደል ?!?! ሊበሏት ያሰቧትን ጅግራ ቆቅ ናት እንደሚባለው ሁሉ - መርካቶ ውስጥ ያጠቆሩት ቦታ ወይም ግለሰቦች አሉ እንዴ ? ወይስ ራሱ መርካቶን ነው በጠቅላላው ያጠቆሩት? በተረፈ ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ ለምትለው የእንቆቅልሽ ጥያቄ መልሱ ሁሌም ክብሪት ካልሆነም እሳት ነበር። መልሱ ግን ውሸት ወይንም ሃሜት መሆን ነበር የሚገባው ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰላም ወዳጄ በመጀመሪያ የሃሳብ ነጻነትን የማምን ሰው መሆኔን መግለጽ እወዳለሁ። ይሄንንም ያሰኘኝ አንተነህን ሳልነካ ሃሳብህን ለመቃወም መፈለጌን እንድትረዳልኝ ነው። የማንም ደጋፊና ተቃዋሚ አይደለሁም ነገር ግን ሃሳብ ወይም አጀንዳ ላይ ለመወያየትና ብሎም ለመማማር እወዳለሁ።

   ታዲያ ወዳጄ አንተ ዲ/ን ዳንኤል ያነሳውን ሃሳብ ለመቃወም የሄድክበት መንገድና አጻጻፍ ትንሽ ወጣ ያለ አይመስልህም? እስኪ ከሌላ ሌላ ስሜት ነጻ ሆነህ እንደገና የጻፍከውን አንብበው። እውነት ለመናገር እንደ ግለሰብ ለግለሰቡ ጥሩ ስሜት ከሌለህ ለራስህ ትክክል ልትሆን ትችላለህ። ነገር ግን ይህ ልመና ከማንነታችን፣ከባህላችንና እምነታችን አኳያ ሊወገዝና ሊወገድ የሚገባው ስለሆነ ትኩረታችን በነጥቡ ዙሪያ ቢሆን ጥሩ ነው የሚል እምነት አለኝ።

   Delete
  2. you wrote all this nonsense for what, are you going to say what Daniel written is wrong. This scam by the beggars is an old aged tradition that has been going on...it doesn't relate to politics, race, religion. It is just a selfish activity that is done by few to get easy money without doing anything

   Delete
  3. To The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነው,
   What is your matter? What Daniel is telling us what he heard. If it is not quite true, just ignore it. he did not say that he has seen the place.
   He did not say any negative thing about Merkato. Endeante jilajil yale sew yadegebat mehonun binager neber Tiruw.
   First learn how to read beyond the line and comment as professional as possible--- Lenegeruma Professional bithon nuro...አንድአንዴ ፈሪሃ እግዚአብሄር በናንተ ሰፈር በኩል ዝር የሚል እንኳን አይመስለንም Balak neber. Lemehonu Feriha egziabher Zir sil Ayteh tawukaleh... Yet sefer?
   Bel ebakih mejemeriya Yanten Sihitet Ewek.. Then you will comment him.
   Please do not say these words as if you are part of Gods decision making process: የፈሪሃ እግዚአብሄር ውሃ-ልካቸው ሲመዘን፤ በውስጣቸው ትንሽ ቅንጥብጣቢ እንኳን የማይገኝ ሆኖ እናገኘዋለን። Yet neberk ante ውሃ-ልካቸው ሲመዘን፤ Lemanigawum kemanbebih befit endet endeminebe Ewok, keziza you will learn how to make comments.

   Delete
  4. ለ ቆሽቱ የበገነው

   ምነው እባክህ ካልጠፋ ስም ይሄንን የብዕር ስም መረጥክ?
   በተነሳው ርዕስ ዙሪያ የጻፍከ አስተያየት በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። ዋናውን ነጥብ ትተህ ወደማይሆን አቅጣጫ ምነው መወነጫጨፍህ? እባክህ በጽሞና አንብቦ መረዳትንና ነጥቡን ያልሳተ አስተያየት ለመስጠት ሞክር ካልሆነም ይቅርብህ የበለጠ ቆሽት ህን አትምለጠው።
   ቅንነትንና አስተዋይነትን ያብዛልን!!!

   ድሬ ነኝ

   Delete
 12. አንብቦ ለመረዳት እግዚአብሔር ልቦናችንን ይክፈትልን፠አሜን!!!

  ReplyDelete
 13. ቁስልማ በደንብ ይሰራል፡፡በዋናነት በግራሶ ነው የሚሰራው፡፡ማቅለሚያዎችም ይጨመራሉ፡፡እረ ሞልቷል፡፡ዳኒ ያለው ትክክል ነው፡፡
  የልመና ዘዴማ ብዙ ነው፡፡
  ሳይታወሩ ጥቁር መነጽ ማድረግ፣ሳይሰናከሉ ክራንች መያዝ፣ልምሾ ሳይሆኑ በከመነዳሪ ታስሮ መንፏቀቅ፣የውሸት ሬሳ አጋድሞ መለመን፣የውሸት ታማሚ መስሎ መዞር፣የውሸት ስዕለት አለብኝ፣የውሸት የቤ/ክ ማሰሪያ፣የውሸት ባሌ ሞቶብኝ፣…በያይነቱ አለ፡፡ሆኖም ሰጭው አይጎዳም፡፡እዳው የተቀባዩ ነው፡፡እኛማ ቀኝ እጅህ የምትሰጠውን ግራህ አትየው ተብለናል፡፡መስጠት ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. If you give knowingly to liars and thiefs, I think you are responsible too.

   Delete
 14. በቅርብ ለጥምቀት በዓል ካጋጠመኝ ነገር ጋር ይመሳሰላል

  ReplyDelete
 15. ለጥምቀት ቀን ወደ አጥቢያዬ ወደሚገው ጥምቀተባህር ለማክበር እየሄድኩ መንገድ ላይ ሁለት ወንዶች ከፊቴ እያወሩ ይሄዳሉ በመሀል አንዱ ሞባይልህ እየጠራነው እንዴ? በብለሎ ይጠይቀዋል እንዳይረብሸኝ ቫይብሬት ላይ ነው ብሎ መለሰለት ከጥቂት ሰዓት በኃላ ታቦት አስገብቸ ሰመለስ በቤተክርስቲያን በር ላይ ስለወንድ ልጅ አምላክ ድንገት በወጣበት ነው የቀረው እያለ ሲለምን አንዱ ተሸፋፍኖ ተኝቶአል፡፡ ወይ ጉድ

  ReplyDelete
 16. ቆሽቱ የበገነው በዚሁ ከቀጠልክ ገና በደንብ ትበግናለህ

  ReplyDelete

 17. Thanks so much for a great post. I'd like to know more about these topics and hope that I can receive more insight into this topic.
  Click Here : Used excavator cat 320cl-eag00700 for sale in cheap price

  ReplyDelete