ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡
አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢው ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል
አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ
የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ
ተቀምጦ እየዞረ ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ
ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም ተቀየረሳ›› እያለ ዝም
ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ እንዳይነበብ አሳስባለሁ)
ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር እየጨመረ ሄደ፡፡ እየቆየም
በግመልና በግመል ወተት ከሚታወቁት የሀገሩ ነጋዎች በላይ እኔ ነኝ ያለ፣ ቢጠሩት የማይሰማ ሀብታም ሆነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም
‹‹ይኼ ሰው ትናንት ምንም አልነበረውም፡፡ የጠፋ ግመል ሊፈልግ ጫካ ገባ፤ ተመልሶ መጣ፤ ከተማ ገባ፤ በአንድ ጊዜ ተመነደገ››
እያሉ ይገረሙ ነበር፡፡ ወተት ብቻ ተሽጦ እንዴት በሁለት ዓመት ሦስት መቶ ግመል ሊገዛ ቻለ፡፡ የሚለው የሕዝቡ ሁሉ ወሬ ሆነ፡፡
ሰውዬው ግን ምንም አልመሰለው፤ በወተቱ ውስጥ ውኃውን እየጨመረ ቀጠለ፤ እንዲያውም እበላ
ባይ ቱልቱላዎችን ቀጠረና የእርሱ ወተት ሰው ጠጥቶት የማያውቅ መሆኑን እንዲለፍፉ አደረ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ወተቱን ለመልኩ ብቻ ይጨምርበትና የቀረው ውኃ ያደርገው
ነበር፡፡ ‹‹ኧረ ሕዝቡ እያማረረ ነው፤ በአንድ በኩል በድንገት ተነሥህ፤ ከተማ ገብተህ ቢጠሩህ የማትሰማ ሀብታም ሆንክ፤ ይኼንን
ስንታገሥህ ደግሞ ወተቱን ቀንሰህ ውኃውን እያበዛህ መሸጥ ጀመርክ፡፡›› ሲሉት ‹‹ተውት ባካችሁ፣ ለመሆኑ የእኔን ወተት ከመግዛት ውጭ ሕዝቡ ምን አማራጭ አለው፤›› ይል ነበር፡፡
በወተቱ ውስጥ የሚጨመረው ውኃም እየበዛ፣ ግመሎቹም እየበዙ ሄዱ፡፡ ግመሎቹም ሀገሩን ሞሉት፡፡ የሚያድሩበትና የሚግጡበት
ልዩ የከተማ መሬት ተሰጣቸው፡፡ ወንዝ ዳር የሚገኝ ለም መሬት፡፡
አንድ ቀን ሸበሌ ወንዝ አጠገብ ግመሎቹን አሠማርቶ እርሱ አንድ ዛፍ ጥላ ሥር ሻሂ ከልጁ ጋር ይጠጣ ነበር፡፡ በዚህ
መሐል ከደጋ የዘነበ ዝናብ ወንዙን ሞላውና በግራ በቀኝ ሲግጡ የነበሩትን ግመሎች ጠራርጎ ወሰዳቸው፡፡ የጎርፉን ድምጽ ሰምተው አባትና
ልጅ ከጥሻው ሲወጡ ግመሎቻቸው ሁሉም ተወስደዋል፡፡ እሪታውን ሰምተው የተሰበሰቡ የሀገሩ ሰዎችም በአግራሞት የሆነውን ነገር ይመለከቱ
ነበር፡፡
‹‹አየህ›› አሉት አንድ አዛውንት ‹‹ያ በወተቱ ላይ እየጨመርክ የሸጥከው ውኃ ተጠራቅሞ፣ ተጠራቅሞ ጎርፍ ሆኖ ግመሎቹን
ወሰዳቸው፡፡ ግፍ እንደዚህ ነው፡፡ ሲሠራ ቀላል ይመስላል የተጠራቀመ ዕለት ግን ጎርፍ ሆኖ ይወስዳል፡፡ ተው ብንልህ አልሰማ ብለህ
ነበር፤ አንተ በግፍ ግመል ስትሰበስብ የግፉ ውኃ ሌላ ቦታ እየተሰበሰበ መሆኑን ረስተህዋል፡፡ ቀን ጠብቆ ግን ይሄው ጎርፍ ሆኖ
መጣ›› አሉት፡፡
ግፍና ጎርፍ፡፡
ይህ በጣም ደስ የሚልና አስተማሪ ነው፡፡ ነገር ግን ማን ያስተውላል?
ReplyDeleteአየህ›› አሉት አንድ አዛውንት ‹‹ያ በወተቱ ላይ እየጨመርክ የሸጥከው ውኃ ተጠራቅሞ፣ ተጠራቅሞ ጎርፍ ሆኖ ግመሎቹን ወሰዳቸው፡፡ ግፍ እንደዚህ ነው፡፡ ሲሠራ ቀላል ይመስላል የተጠራቀመ ዕለት ግን ጎርፍ ሆኖ ይወስዳል፡፡ ልቦና ይስጠን! ዳኒ እናመሰግናለን
ReplyDeletegood
ReplyDeleteok dani thanks
ReplyDeleteደስ የሚል ጽሑፍ ነው ዲያቆን ዳንኤል!
ReplyDeleteእንደ አረዳዳችን ልንጠቀምበት እንችላለን::እኔ ወደ ሃገራችን ግፈኞች ወስጄ ተመለከትሁአትና ጥሩ ምክር እንደሰጠሃቸው አሰብሁ::ወደ ጫካ ገብተው ያገኙትን ሥልጣን(ግመል) እንዴት እንደሚጠቀሙበት ግፉን በዚህ ፅሁፍ ቢማሩ በማለት...
ይህ ግን የራሴ የጽሁፉን አረዳድ እንጅ የአንተን ዕይታ ላይገልጥ ይችላል::
እግዚአብሔር ይስጥልን!
i like it
ReplyDeletevery nice
ReplyDeleteበተለይ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አመራር ቦታ ላይ ተቀምጠው ግፍ የሚሰሩ ሰዎች አንድ ቀን ፅዋው የሞላ እለት ተጠራርገው መጣላቸው አይቀርም፣ እስከዚያ ግን በዚህ ምስኪን ክርስቲያን ላይ ይጫወቱበት።
ReplyDeleteI am surprised that Maru sent this comment. He wants to give you a big blow if you talk about such things. He would lable you Tehadiso!! Mesenbet tiru newu, Maru! I am tired and scared of your illuminati eyes, though. Titenequlaleh libel?
Deleteሰሚማ ቢኖር! አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንዲሉ፤ አንድ ቀን ጽዋዉ ሲሞላ ፤ ከጫካ የመጡት ግፈኞች ገዥዎቻችን ተጠራርገው ይጠፋሉ!!! ዝም ብሎ ይገዛ የነበረው ሕዝብ ሰብዓዊ መብቱን ይጎናፀፋል( ይገዛ የሚለው ቃል በደንብ ጠብቆ ይነበብልኝ)!!!!
ReplyDeleteግሩም ተረተ ተምሳሌት ነው። ተረትና ምሳሌዎቻችንን ልብ ብሎ ላስተዋለ ብዙ መማር ይችላል። ችግሩ የተሰጠንን ልብ እንዲያስተውል አለመፍቀዳችን ላይ ነው።
ReplyDeleteጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም
ይባል የለ?!!!!
ልቦና ይሰጠን፠እውነተኛ ፍርድ መፍረድ የሚችለው መድሃኒያለም ብቻ ነው፠ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳኒ እመብርአን ትጠብቅህ አሜን!!!
ReplyDeleteye ehidigen gef egzir eyekoter yehon. yeeeee
ReplyDeleteይሕ ግመል ፈላጊ የእናንተ ስብስብ ይመስለኛል፡፡ወጣቱ ደግሞ ግመል፡፡ፈላጊው ግመሏን ፍለጋ ብሎ በቅንነት ወጣ፡፡ሲነሳ ቅን ነበር፡፡አገኛት፡፡ወተቷ ጣመው፡፡አለባት፡፡ማለት በሥሟ እየማለ በጥቂት በጥቂት እየረዳ በብዙ በብዙ እየነገደና ንግዱ ሲሞቅለት አክሲዮን እየሸጠ ከበረ፡፡ግመሏን የግሉ አስመሰላት፡፡በ5 ኪሎ፣በራጉኤል፣በለቡ፣በኡራኤል፣በየክልሉ ሱቅ ከፈተ፡፡ነገደ፡፡አተረፈ፡፡ከበረ፡፡ታበየ፡፡ባለቤቱን ናቀ፡፡አቃለለ፡፡አጥፋፋ፡፡ማንም እንዳይናገር ሥም እየሰጠ አሸማቀቀ፡፡መንታ ልሳን ፈጠረ፡፡የገሐዱን ልሳን ለማርገጃ፤የስውሩን ማሳደጃ አደረገ፡፡መደበ፡፡ተኮሰ፡፡ጳጳሳቱ ከፓትርያርኩ እንዳይስማሙ አናከሰ፡፡ምዕመናን ካሕናትን እንዳይሰሙ ሰበከ፡፡ሁሉን አጥላላ፡፡ራሱን ብቻ ሰበከ፡፡ብቻውን ተንጎማለለ፡፡ከእኔ በላይ ለቤ/ክ ላሳር አለ፡፡ገና በ20ዎቹ እድሜ ክልል ሆኖ ባለሺህ ዘመናቱ ቤተክሕነት ከእኔ ውጭ አማራጭ የለውም አለ፡፡አሁንም ቅ/ሲኖዶስ በመጣ ቁጥር ጥቅምትና ግንቦትን እየጠበቀ ነገር እያቀጠነ ነው፡፡ውሃው አያልቅበትም፡፡ጎርፉና ግፉ እስኪሞላ ማቅጠኑን የሚያቆም አይመስለንም፡፡ሆኖም ስለየዋሐን ግመሎች ስንል አቁርር መዐተከ እምኔነ ማለታችንን አንተውም፡፡በከንቱ ውዳሴ የታወረ ልቡን ወደ ቀልቡ እንዲመለስለት ዱዐ እናደርጋለን፡፡እንጸልያለን--ጎርፉ ሳይሞላ እንዲገኝ መላ!!እንጸልያለን--እንደ ሱማሌ አርብቶ አደር ባካሄዱ ወሰን ለማያውቀው ስብስብ!!እንጸልያለን--በግመሎቹን ብዛትና ሰልፍ ነኁልሎ ከድንበሩ የወጣው በቅጡ እንዲሆን--ወደ መስመሩ እንዲገባ!!ከጸሎት በመለስም መዋቅር ያልጠበቀ እንወቅራለን--በትሕትና የዕቡያንን አናት እንወቅራለን--ቋ!!ቋ--ዮሴፍ ነኝ፣አባ አኖሬዎስ፣አባ ፊልጶስ…..እረ እኔ ነኝ፣እንትን የሰራሁ፣እንትን የጀመርኩ፣አማሳኝ በላኝ፣መንፈስ ልሆን ነው፣ቅንአት ይዞኝ ነው……ላላላ እስኪል ቋ!!ቋቋ!!ቋቋቋ!!በልክህ ተራመድ!!ግራቀኝ ተመልከት…ጎርፉ…ግፉ….ቋ…ለብው…አስተውል…አማተር…የምን እምቡር-እምቡር…የምን ውጥር-ውጥር…ገና በ20 አመት….ቀስስስ…ቋ…ኮርኮም…ቋ…
ReplyDelete"ዱዐ እናደርጋለን" አልክ ወንድሜ ከአነጋገራቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዲል ማንነትህን በግብርህ አሳየህ የጽሁፉ ሀሳብ ራስን ምናይበት ሆነእንጂ እንዳንተ ሌሎችን ምናይበት ቢሆን ኖሮ በዚህ ከታማስ በ 1 ቀን ጉባኤ 15000 እና ከዛ በላይ ከገጠር አብያተ ክርስትያናት እየተቀበለ ግፍ ለሰራው ወንድምህ እና ላንተ እውነትን ለመቀበል ልብህ ለደነደነ በተተረጎመ ነበር ግና የመከሩ ጌታ እሱ ይፍረድ በለን እንተወዋለን
Delete"ዱዐ እናደርጋለን"
Deleteበቀላሉ ወንድሜ ጥቅማቸው ከተነካባቸው የእነ አባ እገሌ ወገን ትመስላህ በዚሁ ከቀጠልክ እራስህን ታጠፋለህ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ፡፡
Deleteሊያፈላልግ ሄዶ ... ግመል የተሰወረ
ReplyDeleteሲያገኘው ሰረቀ ... ሊከብር ሞከረ
ቤተሰቡን አሰራ ... አወረሰ ንብረት
በላቡ እንዳመጣው ... ልክ እንደደከመበት
ግና...
የሌላን ሰው ንብረት ሰርቆ .. ሲያደርገው ለራሱ
ጠያቂዎች የሉም ወይ .. ለፍትህ የሚነሱ?
ምርቱን ግሳንግሱን የሚገዛው እሱ ነው
እንዳሻውእንዲፏልል የልብ ልብ የሰጠው።
ሰራቂው ሲከብር ሸጦ ... ውሀ በወተት ስም
ፍትህ ባይጠይቀው አድልቶ ... ለዘራፊው ሃብታም
ጎርፉ የግሳንግሱ ገዢ ... ህዝቡ ቢመስልም ያልገባው መሃይም
ጠርጎ ሊወስደው ነው ... ያፈራው ንብረትም ለማንም ላይጠቅም
ዋይ ኢንደውመንት ...
(ይህ የኔ መረዳት ነው እንጂ እንደ ትንቢት አይወሰድብኝ)
ልቦና ሰጥቶን ወደ መተሳሰብ ይመልሰን።
ሃሳባችንን እንድናንሸራሽር አጋጣሚውን የፈጠረውን ድንቁን ዲያቆን ዳንኤልን ከክፉ ይጠብቅልን።
"የግፍ ፅዋ ሲሞላ መመለሻ ዋጋው የስንት ህይወት ነው?"
ከፊንፊኔ ነኝ
በተለይ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አመራር ቦታ ላይ ተቀምጠው ግፍ የሚሰሩ ሰዎች አንድ ቀን ፅዋው የሞላ እለት ተጠራርገው መጣላቸው አይቀርም፣ እስከዚያ ግን በዚህ ምስኪን ክርስቲያን ላይ ይጫወቱበት።
ReplyDeletedaikon danale egzaher kant gare yhone tarek sqay tareat yhonL ahon bzemanatchen eytay ylaw yhanaw ant bazit kulw amlK kant gare thown amen
ReplyDeleteThanks D/n Daniel. God bless u
ReplyDeleteጥሩ ተረት ነው ግን ወያኔ ምን አንደሚልህ ታውቃለህ አማራ ተረት ብቻ
ReplyDeleteI like it
Delete"ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ "
ReplyDelete”የሚያድሩበትና የሚግጡበት ልዩ የከተማ መሬት ተሰጣቸው፡፡ ወንዝ ዳር የሚገኝ ለም መሬት፡፡” ልብ ያለው ልብ ይበል
ReplyDeleteየከተማ ቤት ያውም ወንዝ ዳር !!! እንዲህ ነው እንጂ
DeleteDiakon Dani bruk hun astemari new.
ReplyDeleteእንዴት እንማር? እንዴትስ እንመከር?
ReplyDeleteየተለለፈውን መልዕክት ወደ ሕይወታችን እየለወጥን ካልቀና መንገዳችን እንመለስ ዘንድ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ሲገስፀንና ሲያሰተምረን ያልተፃፈውን በግል ምኞታችን መነፅር እያነበብን ሌሎችን የምናታክት ያውም መንፈሳዊያን የምንመስል ወንድሞችም እንሁን አባቶች ራሳችንን ልንመረምር ቢገባ ጥሩ ነበር፡፡
ከሀገሬ ሰው ተረቶች አንዷም መሬት እንደማትወደቅ አምናለሁ የኚህ ሰው (Anonymous January 16, 2015 at 4:18 PM ) ፅሑፍ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ እንዲህ ሊገለጡ አንደሚችሉ እረዳለሁ፡፡ <> እልፍ ሲባልም <> ብሎ መግለጥ ይቻላል፡፡ ያልተፀፈ አንባቢና ተረጓሚ ንገሩኝ ባይ፡፡ እድሜ በመቁጠር ከሆነ በዙሪያዎ ያሉ ዛፍችና ድንጋዮች እንደሚቀድምዎት አይዘንጉ፡፡
በቤታችን እየኖርን የቤታችንን ጓዳ የማናውቅ የዋህ ምዕመን አንምሰሎት እኛ ምዕመናን <> በጥቂት እንደርስዎ ዘመን የሚቀምሩ የተግባር ድሆችና እበላባዮች ያልተፃፈም አንብበው በሚተረጉሙ ግለሰቦች ስትታመስ ልባችን ይደማል፡፡ ስለዚህ አባቴም ይሆኑ ወንድሜ እኛ መድረኩን እንመከርበት ዘንድ ሕይወታችንን እንቃኝበት ዘንድ እንሻዋላን እና ለቀቅ ያድርጉልን ማሳደሙን አዚያው ከመሰሎቾት ጋር ሲሰባሰቡ ይደርሱበታል፡፡
ደግሞ የማህበሩ አባል መስየዎት ንፁኃኑ ላይ ጣቶትን እንዳይቀስሩ፡፡ ይህ የማህበሩ መድረክም አይደለም አቅምና እወቀቱ ካሎት ደህረ ገጽ ይኑሮት፡፡
Aba Goshu awaki mesay alu. Meches bezemenu
ReplyDeletekit yata gimel lay yetekemtik ante nehi 'yebete kihinetu jagre'
gin ewunetunina melkam astedader lenafekew miskin hizb
beakison bitil bemin bitil kale lehizbu legeteru maskedesha lata bet kiritian new. 'bo gize lekulu' latem aymola yiker mektahin siwozd , behula nebabit nefs ewnet tinageralchna nsiha giba.-----kw....kw,,, dewel.
I usually do not see reciprocated judgment no a days. The oppressors are like survivors of the fittest. unfair world1
ReplyDeleteI usually do not see reciprocated judgment now a days. The oppressors are like survivors of the fittest. unfair world!
ReplyDeleteአልቆላቸዋል, ጎርፉ ተቃርብዋል
ReplyDeleteThanks! If some one wants to learn it is much about
ReplyDeleteTHAT IS FUNNY
ReplyDeleteግመል ሰርቆ፤አጎንብሶ….መዋቅር ጥሶ፤አድበስብሶ!!
ReplyDeleteመድረኩ ክፍት ነው፡፡ገባን ፡፡ተናገርን፡፡ዳኒ ለእነ እከሌ ብቻ ብሎ አልከፈተውም፡፡የጋራችን ነው፡፡ገና ወደ አክሲዮንነት አልተቀየረም፡፡እንናገራለን፡፡በየዋሕ ምዕመን ሥም “እኛ” እያሉ ማጭበርበር ይቅር፡፡ተነቃ!!ምዕመኑ በሰበካ ጉባኤና በልማት ኮሚቴ ከዚያም አልፎ በዕድርና በጽዋ ማኅበር ድምጹን ያሰማል፡፡ወጣቱም በሰ/ት/ቤቱ በኩል ይደመጣል!!በምእመኑ ሳይመረጥ ራሱን እንደ ምዕመን እንደራሴ የሚቆጥርና በጉባኤ ቤትም ሆነ በመንፈሳዊ ኮሌጅ ሳይታደም ራሱን በአዋቂነት የሚቆልል ግመል ፈላጊ አያሻውም፡፡ባይሆን ውሳኔ-ሲኖዶስ ለምኔ ብለሽ እዛው በማእከልሽ ያለ ሞዴላሞዴል በምትሰበስቢው ቁጥጥር የማያውቀው ገንዘብ ተንቀባረሪ፡፡
ቤ/ክ በእናንተ እጅ ብትሆን ገና ድሮ ለአራትና አምስት ትከፈል ነበር፡፡አክሲዮን ትሆን ነበር፡፡ተይ፡፡አማተር ተይ፡፡በልክሽ ሁኚ፡፡አባል ነኝ፤አይደለሁም እያልሽ በብልጣብልጥነት ራስሽ ከሳሽና ምስክር አትሁኝ፡፡የአይጥ ምስክር ድንቢጥ!!ተነቃ!!ባይሆን በተሰጠሸ ልክ በድርሻሽ አገልግይ፡፡ግመሉን የብቻሽ አድርገሽ ከድርሻሽ በላይ አትጩሂ፡፡አንቺ ራስሽ የቤተክሕነት አካል እንዳልሆንሽ ሁሉ ድክመቱን ለሌላ ጥንካሬውን ለራስሽ እያደረግሽ ቀኗ እንደ ደረሰ ማሽላ አንገትሽን አታስግጊ!!እጣሽ አንድም ለወፍ፣አንድም ለወንጭፍ እንዳይሆን!!በጥንካሬው ብቻ ሳይሆን በድክመቱም አለሽበት!! ግመል ሰርቆ አጎንብሶ!!ለድክመቱ ሲሆን አትደበቂ!!ከዘረኝነቱ እስከ ፖለቲካው ገብተሸበታል!!ታይተሻል!!እረፊ!!ወደ መዋቅር ግቢ!!በሕግ አምላክ ግቢ!!ብርድ ይመታሻል!!
አበሳሽን ዙረሽ አብሽው!!ከነድክመቱ ተቋሙን ለሺህ አመታት ተሸክሞ የኖረውን የቤተክሕነትን ኃጢኣት አሰምቶ በማጮህ ያንቺ አበሳ አይሸፈንም!!ከቻልሽ ድክመቱን እንደ ልጅ ቀርበሽ በፍቅር አስተካክይ፡፡የገሰጹሽን እየለየሽ በማሳደድ አበሳሽ የሚሰረይ ከመሰለሽ ግን ይቅናሽ፡፡እምቡርርርር በይ!!በምዕመን ሥም ነግጅ!!ይቅናሽ አማተር!!አክሲዮኑ ይድራልሽ!!ገበያው ነጻ ነው!!ትምክህትሽን በስስ ነጠላ ሸፍነሽ ተንቀባረሪበት!!ይቅናሽ!!በመንታ ልሳንሽ መመጻደቁን ቀጥይበት!!በዚህ አርግዶ በዚያ ማሳደዱ ይስመርልሽ!!ገና በውጥንሽ በአባላት ጭብጨባ ደንቁሮ፣እንደ ዶኪ ሂዎቴ ከግራቀኙ ተናክሶ ከኔ በቀር ማን አለ ማለቱ ከጠቀመሽ ቀጥይበት!!የመዋቅር ጥሰትሽንና ትምክህትሽን ግን ገና እንናገራለን፡፡በግልጽ ስለሚታይ፡፡ሺህ ብታሸማቅቂም ልትደብቂው አልቻልሽም፡፡ግመል ሰርቆ አጎንብሶ!!
May God bless you!
ReplyDeleteThis is a nice shot. Dani? Do you want to join zone 9? I am exausted to have demonstration every week in front of white house. Be safe! ( atdafer)��
ReplyDeleteIt is a good advise for the tplf government
ReplyDeletedakon daniel dessie yezare 18 amet newu yemakh silembetachn yastemarkewu timhrt eskahun dires ayresagnm betam newu yemwedh yemakebrh egziabeher edmena tena yisth
ReplyDeleteSo nice !!!!!!!!!!!
ReplyDeleteMKR SENAYT. LEKULU. ZEYGEBRA !
ReplyDeleteBetam Astemari Tshuf new.
Been menfes yalteredu demo AMLAK mastewalu ysttln.
D Dani
Amlake Qdusan Kante Gar Yhun.
Rejm Edme Ystln Ayzoh.
ገዢ ፓርቲ የመንግሰትን መዋቅር ተጠቅሞ ፐሮግራሞቹን ማራመድ የይችላል ብለው የለ፡፡ ህግ እና ትርጉሙ ለየቅል የሆነባት ሀገር
ReplyDeleteጥሩ ነው
ReplyDeleteጥሩ ነው
ReplyDeletewhat A nice lesson is! thanks A lot
ReplyDeleteካላስፈላጊ ኮመንት ሰውረን
ReplyDeleteዳኒ አስተያየት ሰጥቼ አላውቅም ግን አስተያየት ወይም ኮመንቶችን ብዙ ግዜ አነባለሁ. ከአስተያየቶች ብዙ ነገር ተምሬአለሁ. አላስፈላጊ ማለት ስድብ የሆኑ፣የማያስተምሩ ወይም በአንተም ለኛ በነሱም በኩል ለነሱ ገንቢ ያለሆነ አሰተያቶቸን ባታወጣ የተሻለ ነው እላለሁ፡፡
ካላስፈላጊ ኮመንት ሰውረን
ዳኒ አስተያየት ሰጥቼ አላውቅም ግን አስተያየት ወይም ኮመንቶችን ብዙ ግዜ አነባለሁ. ከአስተያየቶች ብዙ ነገር ተምሬአለሁ. አላስፈላጊ ማለት ስድብ የሆኑ፣የማያስተምሩ ወይም በአንተም ለኛ በነሱም በኩል ለነሱ ገንቢ ያለሆነ አሰተያቶቸን ባታወጣ የተሻለ ነው እላለሁ፡፡
Amlake Qdusan Kante Gar Yhun.
ReplyDeleteRejm Edme Ystln Ayzoh.
አይ የኛ ነገር! ደስ ይላል: ሁሉም ለፈለገው ነገር ተረጎመው: ለማንኛውም ዲን ዳንኤልን ቃለ ህይወት ያሰማልን :እድሜውን ይስጥልን::
ReplyDeleteከጽሑፉ ይልቅ አስተያየቶቹ አስተማሪ ይመስላሉ፡፡ ከኔ ጀምሮ ሁላችንም ግፍ ሠርቻለሁ/እየሠራሁ ነውና መመለስ አለብኝ መልእክት አንድ ሰው አለመጻፉ ያለንበትን የአስተሳሰብና የመንፈሳዊነት ደረጃ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አስተማሪ ነገር ነው፡፡ ሁሉም የሚወነጅለው አካል አለው፡፡ ራሳችንን መውቀስ መች ይሆን የምንጀምረው!
ReplyDeleteወንድሜ አንተም የፃፍከው ስለሰዎች ነው
DeleteThank you it is helpful.
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚልና አስተማሪ ተረት ነው ፡፡ እ/ር ይባርክህ!
ReplyDeleteቤት አከራዮቻችንንስ የምን ግፍ ጠራርጎ ይወስዳቸው ይሆን?
ReplyDeleteI am so sorry! for those of you who gives non sense comments, but the message of the document is very nice for who is wise and learn from ....
ReplyDeleteበተለይ በዚህ ዘመን ላለን ሰዎች በጣም አስተማሪ መካሪ ነው እናመሰግናለን ዲያቆን
ReplyDeleteበተለይ በዚህ ዘመን ላለን ሰዎች በጣም አስተማሪ መካሪ ነው እናመሰግናለን ዲያቆን
ReplyDelete