Monday, January 5, 2015

ከሳምንታት በኋላ ይወጣል

8 comments:

 1. የሰውን ልጅ ከእንሰሳ የሚለየው ዋነኛው ነጥብ መጻፍና ማንበብ መሰለኝ። ሆድን መሙላት ፡ መተኛት መነሳት ፡ ጎጆ መስራትና ፡ መራባትማ ፡ ድምቢጥ ወፍም ትችላለች እኮ። የማያነብ ሰው ያለው ግንዛቤ አናሳ ነው። በመሆኑም ዓለምን የሚለካት በሆዱ ይሆናል ፡፡ የራሱ ከርስ ከሞላ ፡ ዓለም ሙሉ ነች። የጭንቅላቱ ባዶነት አያሳስበውም።
  በበዳይ መንግስት የሚገዙ ሕዝቦች እኮ ፡ የሚሰቃዩት ፡ የገዥው ጭንቅላት አርቆ ማሰብ የማይችል ሰለሆነና ፡ ተገዥዎቹ ደግሞ ፡ ችግርን የመሸከሚያ ጫንቃቸው ፡ ባለማወቃቸው ምክንያት ፡ አድማስ ዓልባ ፡ ሆኖ ነው። የዚህ አይነት ሕዝብ እራሱ እስካልተነካ ድረስ ለሌላው ግድ የለውም።

  አንድ ቀን ፊልም ላይ ፡ አራት አንበሶች ፡ ጎሾቹን አድነው አንዱን ጣሉት ፡ ከዛ ግን ገና የጣሉትን መብላት ሳይጀምሩ ፡ ጎሾቹ ቀንዳቸውን አሹለው አንበሶቹ ላይ መጡ ፡ ደፈር ያለው አንበሳ በመጀመሪያው ጎሽ ቀንድ ፡ ሆዱ ተበሸርከ ፡ ሌሎቹ ፡ አንበሶች ነፍሴ አውጭኝ አሉ። የወደቀው ጎሽ ፡ መበላቱ ቀርቶ ተነሳ፡፡ እኔም እራሴን ታዘብኩት! ወገኖቼንም ታዘብኳቸው።

  ReplyDelete
 2. ዳንኤል ክስረት አንተን ዲያቆን ያደረገህ ማን እንደሆነ ባይገባኝም እኔ እስከማዉቅህ ድረስ የሰዎችን ስም በማጥፋትና ጥላሸት በመቀባት ጥርስህን የነቀለክና ሃይ ባይ በማጣትህ ምክንያት ራስህን እንደምሁር እየቆጠርክ ያለህ ጅል ሰዉ ነዉ ነህ፡፡ በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን እንደተናገሩት አንተ የምትጽፈዉ ስላወቅህ ሳይሆን ያዉቃል ለመባል ስለሆነ ከአንተ ዝባዝንኬ ተረት ቁምነገር ይገኛል ብለን ያንተን ድሪቶ አናነብም፣ ያንተን የማይጠረቃ ኪስም አናደልብም፡፡ ልብ ካለህ እና አዉነተኛ የቤተከርስቲያን ልጅ ከሆንክ ትክክለኛዉን የክርስቶስ ወንጌል ሰብከህ ከመሸበት ታድር ነበር አንተ ግን ዲያቆን የሚል ማደናገሪያ ደርበህ የተረት መጻህፍትን እየደረትክና ባገኘኸዉ አጋጣሚ ሁሉ እያሻሻጥክ ኪስህን ታወፍራለህ፡፡ መጨረሻህ ሲኦል ስለሆነ ቢያንስ በዚህ ምድር ቢደላህ የሚቃወም የለም፡፡ በእኛ ብር ግን አይደረግም!

  ReplyDelete
 3. እንዳንተ አይነት ሰዎች ትገርሙኛላችሁ፡፡ ሰው ነገር አለሙን ትቶ ወነጌል ብቻ ያስተምር ትላላችሁ፡፤ እናንተ ራሳችሁ ግን እንጀራ የምትበሉበትን ወይም የተማራችሁበትን ሥራ ትሠራላችሁ፡፡ ዳንኤል በየቦታው ያስተምራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይጽፋል፡፡ ምንድን ነው አንተን ሆድህን የቆረጠህ፡፡ ደግሞኮ የርሱ መጽሐፍ ለአንተ አይነቱ አይደለምና፡፡ እባክህ አታንብበው፡፡

  ReplyDelete
 4. እኔ እምለው ቤተክርሰቲያን እያገለገለ መጽሐፍ ቢጺፍ ምንድነው ችግሩ ?
  በማስታዋል ብንናገር ጥሩ ነው፡፡


  ReplyDelete
 5. woregna.....ante lehayimanotih, le hagerih, letiwulidu min serah?

  ReplyDelete
 6. “አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል” የሚል አባባል አለ፡፡ አንድ ሰው አስተያየት የሚሰጥበት መንገድ ያለበትን የበሳልነትና የአስተሳሰብ ደረጃን ያመለክታል፡፡ የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ አስተያየት ለሰው ስንሰጥ “ጨዋነት” የተሞላው ቁም ነገር ቢሆን ይመረጣል፡፡ ለሁላችንም ፈጣሪ ማስተዋልን ይስጠን! ቃሉ በኢዮብ 38፡2 ላይ “ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው?” ይላል፡፡ ለምንናገረው ነገር እንድንጠነቀቅ ፈጣሪ ልቦናን ይስጠን! ዳኒ መጽሀፉን በጉጉት ከሚጠብቁት አንዱ ነኝ!

  ReplyDelete
 7. ዳኒ እግዚአብሄር ያበርታህ ቀጥልበት የቀና ምንም ያልተሳካለት ብዙ ያወራል

  ReplyDelete
 8. እንዳንተ አይነት ሰዎች ትገርሙኛላችሁ፡፡ ሰው ነገር አለሙን ትቶ ወነጌል ብቻ ያስተምር ትላላችሁ፡፤ እናንተ ራሳችሁ ግን እንጀራ የምትበሉበትን ወይም የተማራችሁበትን ሥራ ትሠራላችሁ፡፡ ዳንኤል በየቦታው ያስተምራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይጽፋል፡፡ ምንድን ነው አንተን ሆድህን የቆረጠህ፡፡ ደግሞኮ የርሱ መጽሐፍ ለአንተ አይነቱ አይደለምና፡፡ እባክህ አታንብበው፡፡ ዳኒ እግዚአብሄር ያበርታህ ቀጥልበት የቀና ምንም ያልተሳካለት ብዙ ያወራል

  ReplyDelete