Tuesday, December 9, 2014

ራትን ቁርስ ላይ

አፍሪካውያን ቀደምት አያቶቻችን እንዲህ የሚል ትንቢት አዘል አባባል ነበራቸው፡፡ ‹‹የዚህ ትውልድ ትልቁ አደጋ ራታቸውን በቁርስ ሰዓት ለመብላት መፈለጋቸው ነው››፡፡ ሰው እንደ መላእክት አይደለምና በሂደት እየበሰለ፣ በሂደት እየተገነባ፣ በሂደትም የበለጠ እየተማረ የሚሄድ ፍጡር ነው፡፡ ይኼ ደግሞ የመንፈስ፣ የአካል፣ የስሜትና የአእምሮ ዕድገትና ለውጥን ይጠይቃል፡፡ ሰው ሲወለድ ለማደግና ለመለወጥ ከሚያስችል ዐቅም ጋር ነው፡፡ ይህንን ዐቅም ተጠቅሞ ለማደግና ለመለወጥ ግን ልምድ፣ ትምህርትና የሰውነት ግንባታ ያስፈልጉታል፡፡ ልምድ የሚባለው ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ በሕይወት ውጣ ውረድ የሚደርስበት ተሞክሮ ነው፡፡ ይህም የሕይወት ተጋድሎ ይባላል፡፡ ትምህርት ከሰዎች፣ ከትምህርት ቤት፣ ከመጻሕፍት፣ ከአካባቢውና ከሌሎችም የዕውቀት ምንጮች የሚያገኘው ጥበብ ነው፡፡ የሰውነት ግንባታ የሚባለው ደግሞ በምግብና በእንቅስቃሴ የሚያበለጽገውን አካል ነው፡፡

እነዚህ ነገሮች የሚመጡትና የሚከናወኑት በሂደት ውስጥ በመሆኑ ሰዎች ለተለያዩ የኑሮ ደረጃዎች የሚበቁበት ጊዜ ይለያያል፡፡ በልጅነት፣ በወጣትነት፣ በዐዋቂነትና በአረጋዊነት ጊዜ የሚከናወኑት ተግባራት በዚያው በየዘመናቸው እንዲከናወኑ የሚያስገድዱት ሰዎች እነዚህን ነገሮች ለማከናወን የብስለታቸው ደረጃ እንደ ዕድሜያቸውና በዚያ ዕድሜ የተነሣ እንደሚያገኙት ልምድና ዕውቀት ብሎም አካላዊ ዝግጁነት ስለሚለያይ ነው፡፡ የልጆች ጋብቻንና የልጅነት ጊዜ ወሊድን የምንቃወመው፣ ጋብቻም ሆነ ወላጅነት የሚፈልጓቸው የመንፈስ፣ የአካል፣ የስሜትና የአእምሮ የዕድገት ደረጃዎች ስላሉ ነው፡፡


የመንፈስ ዕድገት የምንለው በመንፈሳዊው ዓለም ሰው የሚኖረው ዕድገትና ለውጥ ነው፡፡ በእምነት፣ በአመለካከት፣ በመርሕና በአተያይ የሚኖረው የብስለት ደረጃ፡፡ የስሜት ዕድገት ለነገሮች የሚኖረንን ፍቅርና ጥላቻ፣ ቀረቤታና ርቀት፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ ስበትና ግፊት የምንለካበት የዐቅም መጠን ማደግ ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ለመቆጣጠር፣  ሕጋዊ፣ ሰላማዊ፣ ትክክልና ተገቢ በሆነው መንገድ ለመምራት ያለን ዐቅም ማለት ነው፡፡ የአእምሮ ዕድገት ስንል ደግሞ በዕውቀት ማደግን ነው፡፡

በትምህርት፣በልምድና በሰውነት ግንባታ እያደገና እየተለወጠ የሚሄደው ሰው፣ ሕይወቱ ተከታትለው በሚመጡ ሦስ ነገሮች  የሚዘወር ነው፡፡ ዐሉላ ጥላሁን ‹‹የሕይወት ሙሻዙር›› ይለዋል፡፡ እነዚህ ሦስቱ ጉጉት፣ ተጋድሎና ስኬት ይባላሉ፡፡ በሰው ሕይወት ውስጥ የሚያጓጓ፣ ይደረስበታል ተብሎ የሚታሰብ፣ የሚናፈቅና ተስፋ የሚደረግ ነገር ከሌለ ተጋድሎ የሚባለው የሕይወት ዋነኛ አጣፋጭ፣ ሰውንም ወደ ሙሉ ሰውነት የሚያደርሰው ታላቁ ድልድይ ተሰብሯል ማለት ነው፡፡ እርሱ ከተሰበረ ደግሞ ስኬት የሚባለው  ነገር አይታሰብም፡፡ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ሥልጣኔ የተመዘገበባቸው ሀገሮችና ዘመናትን ታሪክ ብናጠና እነዚህ ሦስቱ ነገሮች ገንዘባቸው የነበሩ መሪዎችን፣ ሊቃውንትንና ሕዝቦችን እናገኛለን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በኋላ ቀርነት ይሰቃዩ የነበሩና አሁንም የሚሰቃዩትን ሕዝቦች ስናይም እነዚህ ነገሮች ሲያጥሯቸው እናስተውላለን፡፡

ሰው ይህንን የሕይወት ሙሻዙር ዘውሮ ሕይወቱን ወደ ልዕልና እንዳያደርሳት የጉጉት፣ ተጋድሎና ስኬትን መሥመር የሚሰብሩ አራት ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ዋናን የሚያጠፋ ርዳታ ነው፡፡ ርዳታ ወይም እገዛ መልካም የሚሆነው ዓሣ ሊያሰግር የወጣውን ሰው በቀላሉ ብዙ ዓሣዎች እንዲያሰግር የሚያስችለውና እርሱም የተሻለ ማስገሪያ እንዲሠራ የሚያበቃው ዓይነት ርዳታ ከሆነ ነው፡፡ ሰውዬው ቁጭ ብሎ ዓሣ እንዲያገኝና ምንም እንዳያስብ የሚያደርገው ርዳታ ግን ርዳታ ሳይሆን ግድያ ነው፡፡ መጀመሪያ ብዙ ዓሣ ለማስገር የነበረውን ጉጉት ይገድልበታል፡፡ ቀጥሎ ያንን ጉጉት ለማሟላት እንዳይጋደል ያሰንፈዋል፡፡ በመጨረሻም ስኬት አይኖረውም፡፡ ስኬት ማለት የጥረት ውጤት ነውና፡፡ ያለ ጥረት በዱብ ዕዳ የተገኘ ነገር ሁሉ ስኬት አይደለም፡፡ ዕድል፣ ዕጣ ወይም ስጦታ ይሆናል እንጂ፡፡ ሰውን ወደ ዕድል፣ ዕጣና ስጦታ ደረጃ ማውረድ ደግሞ ከሰውነት አሳንሶ ‹መትኅተ ሰብእ መልዕልተ እንስሳት› ማድረግ ነው፡፡ ራቱን ቁርሱ ላይ እንዲበላው ማድረግ፡፡ ነገ ልታገኘው የምታስበውና የምትለፋለት አዲስ ነገር ከሌለህ ‹ነገ› ለምን ይምጣ? ‹ነገ› ስ  ከአንድ ተጨማሪ ቀን ውጭ ሌላ ምንድን ነው?

ሁለተኛው ሰባሪ አደጋ ደግሞ በወንጀል የተገመደ አቋራጭ መንገድ ነው፡፡ በስርቆት፣ በጉቦ፣ በማስመሰል፣ በሥልጣን በመባለግ፣ የሰዎችን ዕድል በማበላሸት፣ ትውልድን በመግደል፣ ሀገርን በማጥፋት፣ ወዘተ በኩል የሚገኝ አቋራጭ መንገድ፡፡ በቀላሉ ሥልጣን፣ ገንዘብ፣ ክብር፣ ስምና ዝና የሚገኝበት፡፡ ይህ መንድ ምናልባት ገንዘብ፣ ስምና ክብር፣ ሥልጣንና ዝና ያስገኝ ይሆናል፡፡ ውስጣዊ ደስታ ግን አያስገኝም፡፡ ደስታ ከስኬት የሚገኝ ነውና፡፡ ሌሎቹን ነገሮች ማስመሰል ቢቻልም ውስጥን ማስመሰል ግን አይቻለም፡፡ ደስታ ውስጣዊ ስለሆነ ነው አስመስሎ መሥራት የማይቻለው፡፡

እንዲህ ባደረገ ሰው ውስጥ የሚፈጠረው ጦርነት የትም ቦታ የማይፈጠር ነው፡፡ የሕግ መውጣት፣ የሥርዓት መለወጥ፣ የዳኝነት ሥርዓት መጠንከር፣ የሚዲያ ምርመራ መጀመር፣ የሰዎች ዕውቀት መጨመር፣ እርሱ የፈጸማቸውን ነገሮች የሚቃወሙ አሠራሮች መምጣት፣ የዓለም አስተሳሰብ እየተቀየረ መሄድ ያሳስበዋል፡፡ ያስጨንቀዋል፡፡ ለዚህም ነው እውነተኛውን ደስታ የማያገኘው፡፡ ድሮ ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን›› የሚለው መግቢያ ለተረት የሚያገለግል ነበረ፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ለሰዎችም ያገለግል ጀምሯል፡፡ ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን እገሌ ድንገት ኢንቨስተር ሆነ፣ ድንገት ባለ ሀብት ሆነ፣ ድንገት ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሆነ፣ ድንገት ባለ ሥልጣን ሆነ፣ ድንገት ባለ ኩባንያ ሆነ፣›› ከየት ተነሥቶ፣ በየት በኩል ሄዶ፣ ምንም አድርጎ? መልስ የለም፡፡ ‹‹እንዴው ከዕለታት በአንድ ቀን›› ነው መልሱ፡፡ በዚህ መንድ የሚመጡ ሰዎች ስኬታማ አይደሉምና ደስተኛም አይደሉም፡፡ ደስተኛ ግን ይመስላሉ፡፡ ራታቸውን ቁርሳቸው ላይ ስለበሉት ምንጊዜም የራት ነገር ሲያሳስባቸው ይኖራል፡፡ ራት ያልበላ ሰው የሚተኛውን የረሃብ ዕንቅልፍ ስለሚተኙ፤ አልጋ እንጂ ዕንቅልፍ አይኖራቸውም፡፡ ቅዠት እንጂ ሕልም አይታያቸውም፡፡

ሦስተኛው ሰባሪ አደጋ ዕድል፣ አጋጣሚና የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥሩት ግሽበት ነው፡፡ የማስተማሪያ ዐቅምና ዕድል ስላገኘን ብቻ ልጃችንን ያለ ዕድሜው ወደ ትምህርት ቤት ብንልከው ልጁ እየተማረረ እንጂ እየተማረ አይመጣም፡፡ በኋላም ከፍ ሲል ትምህርት ጠል ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንዱ ያለ ዕድሜ ወደ ትምህርት ቤት መግባትና መደበኛ ትምህርት መጀመር ናቸው፡፡ ዕድልና አጋጣሚ አገጣጥሞላቸው ያለ ከዕድሜና ከዕውቀት በፊት ገንዘብ ማግኘት ያቻሉ አንዳንድ ሰዎች ገንዘቡ መጥፊያቸው ሲሆን አይተናል፡፡ አካባቢያቸውን ለማስተዳደር መጀመር ባለባቸው ጊዜ አገር ማስተዳደር የሚጀምሩ፣ ቤተሰባቸውን መምራት ከመጀመራቸው በፊት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት መምራት የጀመሩ ሰዎች ዕድሉን ለስኬት ከመጠቅም ይልቅ ሀገር ለማጥፋት የሚጠቀሙበት በዚህ ስኬት ሰባሪ አደጋ የተነሣ ነው፡፡ ራታቸውን ቁርስ ላይ በልተውት፡፡ 

ዛሬ ዛሬ በጋብቻ ውስጥ ብቻ ሊደረጉ የሚገባቸው ነገሮች ከጋብቻ በፊት፣ በበሳል ዕድሜ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ጾታዊ ግንኙነቶች በሚዲያ፣ በፊልም፣ በማኅበራዊ ድረ ገጾችና በአንዳንድ አቀንቃኞች ምክንያት በሚፈጠሩ የስሜት መመቻቸቶች የተነሣ በልጅነት ዕድሜ እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ሰዎች ራታቸውን ቁርስ ላይ በልተው የሚጓጉለት ነገር እንዳይኖር አድርጓቸዋል፡፡ ልጆች ተምረው ሊያገኙት የሚገባውን ነገር የድመት ፍቅር በያዛቸው ወላጆች ምክንያት ሳይማሩ ስለሚያገኙት ለትምህርት ሊያውሉት የሚያስፈልግ ጉጉትና ጥረት ተሟጥጦባቸዋል፡፡ በምዕራቡ ዓለም ታላላቅ ሰዎች ልጆቻቸውን በኩባንያቸውና በፖለቲካ መሥመራቸው መተካት የቻሉት፣ ልጆቹ መሥመሩን ተከትለው በመጋደል መሥመሩ የሚያስገኝላቸውን እያገኙ እንዲያድጉ በማድረጋቸው ነው፡፡ የአባታቸው ሀብት ስለሆነ ብቻ አያገኙትም፤ ተምረው፣ ሠርተው፣ ከሌሎቹ ጋር ተወዳድረው፣ ከታች እስከ ላይ ያለውን የዕድገት መሰላል በመንፈስ፣ በትምህርት፣ በልምድና በአካላዊ ዕድገት እየዳበሩ አልፈው፣ በተወዳዳሪነትና በአሸናፊነት ተጋድሎ ተፈትነው ሲደርሱ፤ ያን ጊዜ ወላጆቻቸው ‹ተቀመጥ በወንበሬ፣ ተናገር በከንፈሬ› ብለው ያስረክቧቸዋል፡፡ ሳንቲሞች እንዴት እንደመጡ ሳያውቁ ብሮችን አያስነኳቸውም፡፡ ነገ ሊደርሱበት የሚገባውን ራት ዛሬ በቁርስ ሰዓት አያበሏቸውም፡፡ ልጅ ምንም ያህል ቢፈለግ በሦስት ወር ይወለድ አይባልምና፡፡

አራተኛው ሰባሪ አደጋ የሚመጣው በጋሸበ አድናቆትና ግፊት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች የሚሰጠንን አስተያየት፣ ድጋፍ፣ ተቃውሞ፣ ክብር፣ ዝና፣ ስምና ታላቅነት ከውስጣችን ዐቅም ጋር መዝነን ካላስተናገድነው አደጋ ያስከትላል፡፡ ሰዎች ትችላላችሁ፣ ያለ እናንተ ሰው የለንም፣ ጀግና ናችሁ፣ ስላሉን ያሉንን ሁሉ አንሆንም፡፡ ጭብጨባውን፣ ሙገሳውን፣ አድናቆቱን ለችሎታ መመዘኛነት ከወሰድነው ከራሳችን ጋር እንጣላለን፡፡ ቀስ በቀስ በዕድገትና በልምድ፣ በትምህርትና በተጋድሎ ልንደርስበት የሚገባንን ገፋፍተው ሲያወጡን ከተቀበልንና ‹ሕዝብ ከመረጠኝ፣ ሕዝብ ካለ፣ ሕዝቡ ከደገፈኝ› ካልን ራታችንን ቁርስ ላይ ያስበሉናል፡፡ እላይ ከወጣን በኋላም የምናደርገው ይጠፋናል፡፡ በውጫዊ ግፊትና አድናቆት ‹ነህ› የሚሉንን ከመቀበል በውስጣዊ ዕውቀት ‹አይደለህም› የሚለንን መቀበሉ ያዋጣናል፡፡ ዛሬ ዓለምን ለበሽታ የዳረጓት ዕንቁላል ሳይሆኑ ዶሮ የሆኑት ናቸው፡፡

ሰው በሂደት የሚሟላ ፍጡር ነው፡፡ የሚያሟሉትም ትምህርት፣ ልምድና የሰውነት ግንባታ ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ የሚፈጸሙት በጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ አንድን ነገር ዕድል ስላገኘን፣ ነገሮች ስለተመቻቹ፣ አቋራጭ መንገድ ስላለው፤ በአድናቆትም ሆነ በተቃውሞ ስለተገፋፋን፣ ጊዜ የሰጠው ቅል ስለሆንን ወይም ደግሞ በምናያቸው ፊልሞች፣ በምናነባቸው ስሜት ቀስቃሽ ጽሑፎች፣ ከጓደኞቻችን በሚፈጠሩብን ግፊቶች ተስበንና ተገፍተን ራታችንን ቁርስ ላይ መብላት የለብንም፡፡ ጉጉት የሌለው ነገ፣ የማይጋደሉበትም ሕይወት ስኬትን አያመጣምና፡፡ ስኬትን የማያጣጥም ሰውነት ደግሞ ምንጊዜም ውስጡ ክፍተት ይኖረዋል፡፡ ያ ክፍተት ነው ተስፋ መቁረጥን፣ ትካዜን፣ ራስን መጥላትን፣ የበታችነትን፣ ወራዳነትንና ራስን መጥፋትን የሚፈጥረው፡፡   

52 comments:

 1. ድሮ ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን›› የሚለው መግቢያ ለተረት የሚያገለግል ነበረ፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ለሰዎችም ያገለግል ጀምሯል፡፡ ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን እገሌ ድንገት ኢንቨስተር ሆነ፣ ድንገት ባለ ሀብት ሆነ፣ ድንገት ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሆነ፣ ድንገት ባለ ሥልጣን ሆነ፣ ድንገት ባለ ኩባንያ ሆነ፣›› ከየት ተነሥቶ፣ በየት በኩል ሄዶ፣ ምንም አድርጎ? መልስ የለም፡፡ ‹‹እንዴው ከዕለታት በአንድ ቀን›› ነው መልሱ፡፡ በዚህ መንድ የሚመጡ ሰዎች ስኬታማ አይደሉምና ደስተኛም አይደሉም፡፡ ደስተኛ ግን ይመስላሉ፡፡ ራታቸውን ቁርሳቸው ላይ ስለበሉት ምንጊዜም የራት ነገር ሲያሳስባቸው ይኖራል፡፡ ራት ያልበላ ሰው የሚተኛውን የረሃብ ዕንቅልፍ ስለሚተኙ፤ አልጋ እንጂ ዕንቅልፍ አይኖራቸውም፡፡ ቅዠት እንጂ ሕልም አይታያቸውም፡፡
  አቤት እንዴት አንጀት የሚያርስ ጽሁፍ ነው፡፡ ትክክልኛው አሁን እያየነው ያለው ሁኔታ ነው ፡፡ እውነትም ‹‹አራትን ቁርስ ላይ›› አቤት አራት ሳይበሉ አንቅልፍ አይጣል ……

  ReplyDelete
 2. Kale hiwote yasemalin!!! May God bless you and your family Amen!!!!

  ReplyDelete
 3. God bless you Dakon Dani.

  ReplyDelete
 4. ራታቸውን ቁርሳቸው ላይ ስለበሉት ምንጊዜም የራት ነገር ሲያሳስባቸው ይኖራል፡፡ ራት ያልበላ ሰው የሚተኛውን የረሃብ ዕንቅልፍ ስለሚተኙ፤ አልጋ እንጂ ዕንቅልፍ አይኖራቸውም፡፡ ቅዠት እንጂ ሕልም አይታያቸውም፡፡

  ዛሬ ዓለምን ለበሽታ የዳረጓት ዕንቁላል ሳይሆኑ ዶሮ የሆኑት ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 5. በዕለት ተዕለት ኑሮአችን የምናየዉ ነገር ግን አስተዉለን ልናስተካክለዉ የተሳነን እዉነታን ስላሰነበብከን ምስጋና ይገባኃል።

  ReplyDelete
 6. ድሮ ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን›› የሚለው መግቢያ ለተረት የሚያገለግል ነበረ፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ለሰዎችም ያገለግል ጀምሯል፡፡ ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን እገሌ ድንገት ኢንቨስተር ሆነ፣ ድንገት ባለ ሀብት ሆነ፣ ድንገት ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሆነ፣ ድንገት ባለ ሥልጣን ሆነ፣ ድንገት ባለ ኩባንያ ሆነ፣›› ከየት ተነሥቶ፣ በየት በኩል ሄዶ፣ ምንም አድርጎ? መልስ የለም፡፡ ‹‹እንዴው ከዕለታት በአንድ ቀን›› ነው መልሱ፡፡ በዚህ መንድ የሚመጡ ሰዎች ስኬታማ አይደሉምና ደስተኛም አይደሉም፡፡ ደስተኛ ግን ይመስላሉ፡፡ ራታቸውን ቁርሳቸው ላይ ስለበሉት ምንጊዜም የራት ነገር ሲያሳስባቸው ይኖራል፡፡ ራት ያልበላ ሰው የሚተኛውን የረሃብ ዕንቅልፍ ስለሚተኙ፤ አልጋ እንጂ ዕንቅልፍ አይኖራቸውም፡፡ ቅዠት እንጂ ሕልም አይታያቸውም፡፡የድመት ፍቅር በያዛቸው ወላጆች ምክንያት አሁን በደንብ ነው ያቀረብከው ተባረክ ኑሮአችን ከድመት ጋር በመሆኑ

  ReplyDelete
 7. ውድ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ፣ እየመገብከን ያለው ጥበብ ድንቅ ነው፡፡ እንድንጠቀምበት ፈጣሪ ይርዳን፡፡ እስኪ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ የተከሰተውን የመሬት ሽያጭ ዋጋ አስመልክተህ አንድ በለን፡፡ አንድ ካሬ መሬት ከ ሶስት መቶ ሺህ ብር በላይ መሸጡ አስደንግጦኛል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ዋጋ በአለም ላይ የመጀመሪያ ውዱ እንደሆነ ልብ ይባል፡፡ እውነት ሀገራችን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሳለች? በሀረሪቱ ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው ገንዘብ ጤነኛና ተሰርቶ የተገኘ ይሆን? እንዲህ አይነቱ ውድድር መንግስትን ሊያሳስበው አይገባም? ቅን፣ ጀማሪ ተስፈኞችንስ ተስፋ አያስቆርጥም? እይታህን እጠብቃለሁ፡፡ ---ዳዊት ተሸመ - ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማለት የምትችለው ካለ ማለት ነው እንጂ እንዲት ስሜትህን በሌላ ሰው ምለስ እንዲነገር ትፈልጋለህ ወንድሜ እራሳችንን እንሁን ምን መማለት ነው አንተ የተሰማህን እርሱ እንዲናግርልህ ለምን ትፈልጋለህ

   Delete
  2. እሱ የሚለውንማ አለኮ!
   ባይሆን አያስደንግጥህ ዋጋው በለው። ለመግዛት አቅም ካለው ፥ ነገ ቀን ሲዞር ፡ ብሩ ከየት እንደመጣ ማሳውቅም ይኖራልና ይታሰብበት። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ፡ ሰው ከገቢው ላይ ፡ ቀረጥ ይከፍል ይሆን ;-)

   Delete
  3. Please don't be mean for your country. These people they can invest any country but they want invest their country and they created many jobs for your brother and sister. You have to thank them. Most of Ethiopian invest other country so we have many unemployeed people. Do you know Bereket Smone hired more than 2000 people because of his investment. In other hand Meles Zenawi dauter deposit five billion dollar in New York bank , but she dosen't invest single birr in Ethiopia. Do you know her money can finish " Abay Gdbe" so please incurage all the people that invest in Ethiopia.

   Delete
 8. ሦስተኛው ሰባሪ አደጋ ዕድል፣ አጋጣሚና የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥሩት ግሽበት ነው፡፡ የማስተማሪያ ዐቅምና ዕድል ስላገኘን ብቻ ልጃችንን ያለ ዕድሜው ወደ ትምህርት ቤት ብንልከው ልጁ እየተማረረ እንጂ እየተማረ አይመጣም፡፡ በኋላም ከፍ ሲል ትምህርት ጠል ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንዱ ያለ ዕድሜ ወደ ትምህርት ቤት መግባትና መደበኛ ትምህርት መጀመር ናቸው፡፡ ይህ ሀሳብ እኔም ሁልግዜ በዉስጤ የሚመላለስ ጉዳይ ነበር፤በጣም አመሰግናለሁ ዳኒ፡፡ ከዚህ ከትምህርት ጋር በተገናኘ ልጆቻችን እንዲማሩ የምንፈልገዉስ ምን ይመስላል? አንደኛ እኛ የምንፈልገዉን እንጅ ልጆች መማር የሚፈልጉትን አይደለም፡፡ ሁለተኛ ነገር እዉነት ልጆች ከምንም በላይ መማርና መመራመር እንዲሁም ማወቅ ያለባቸዉ ስለራሳቸዉ ታሪክ፣ባህል፣ቋንቋ እንዲሁም ኦኮኖሚ አይደለምን፤ይሄም እየሆነ አይደለም፡፡ ወደ ራስ እንመልከት፤ሁሉም ነገር ዉብ ነዉ፤ ምንም ነገር ለእኛ እግዜር ከሌላዉ አሳንሶ ወይም ያልሰጠን ነገር የለም፡፡ የኛ ነገር ይገርመኛል……እንቆቅልሽ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 9. በጊዜአችን ከፍ በለን የምንመለከተው ተምሳሌት ሰው ነህ በይበለጥ ደግሞ ለእኛ ለተዋህዶ ልጆች
  አዎ ከምንግዜም በላይ በክርስትና ሰነምግባር የታነጰ እውቀት ያለው ሰው እጅጉን ያስፈልገናል ስለዚህም ብዙ ዳንኤሎች እንዲፈጠሩ እንመኛለን እግዛብሄርም በነዚህ በተመረጡ ሰወች አድሮ በመጥፋት ላይ ያለውን ትውልድ ያድን ዘንድ መልካም ፍቃዱ ይሁን.
  ወንድም ዳንኤል እግዛብሄር ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ የመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እረድኤት እና በረከት አይለይህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. misgana new weys amlikot?????????????
   በጊዜአችን ከፍ በለን የምንመለከተው ተምሳሌት ሰው ነህ በይበለጥ ደግሞ ለእኛ ለተዋህዶ ልጆች

   Delete
 10. ዲያኮን ዲኒ እግዚሃብሔር ይባርክህ! እኛንም ሰሚ እና አንባቢ ብቻ አያድርገን.


  ዲያኮን ዲኒ እግዚሃብሔር ይባርክህ! እኛንም ሰሚ እና አንባቢ ብቻ አያድርገን.


  ReplyDelete
 11. nice idea dani. Weldebrhan mekele

  ReplyDelete
 12. ከአራተኛ ክፍል ጄኔራል በሚኮንበት፡
  ከስምንተኛ ክፍል ማስትሬት በሚወሰድበት፡
  ጥንታዊ መጽሃፎች ከብሔራዊ መጽሃፍት ቤት ፡ በኪሎ በሚሸጡበት አገር፡

  አንተ እራት ቁርስ መሆኑ ገረመህ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከላይ ያልከወው ናያልተዘረዘረሩ ጭምር ሦስተኛው ሰባሪ አደጋ ዕድል አጋጣሚና የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥሩት ግሽበት ነው፡፡ሰባሪ አደጋዎቹ በቅደም ተከተል ተቀምጠው ከሆነ እኔም በእኛ ሐገር ተጨባጭ ሁኔታ ግን 1ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥያለበት ይመስለኛል፤፤፡፡ ከፅሁፍ መንደርደሪያ ሀሳብ ጋርም ተዛማጀነት ያለው የሕይወት ሙሻዙር›ን ጠብቆ ባልመጣ ክስተት የሚከሠት አደጋ

   Delete
  2. ጥሩ ታዝበሃል ወዳጄ፡፡
   እኔ የሚያሰጋኝ በመሰረተ ትምህርት የተደራጁ አነስተኛና ጥቃቅን ሃገር ላለመምራታቸው ዋስትና ያለመኖሩ ነው፡፡

   Delete
 13. እናመሰግናለን!!!!!!!

  ReplyDelete
 14. I always liked ur point of view in both religious and political situation I always am the first to read ur articles but I will always hope long achievement in ur career god bless you

  ReplyDelete
 15. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 16. The book says " it is enough a word for a wise person" but there is no wise now , so please keep going to teach us in every way. thank you.

  ReplyDelete
 17. Tsihufochih betam astemariwoch nachew, gin lenezia eratachewun bekursachew gizie lebelut endiet adrgo masnebeb ychalal? Minalbat wedefit biastewulu, mechem yalefewus alfual.

  ReplyDelete
 18. Min enlalen, tiru astemarina yemigerim tsihuf new. Egziabiher edimehin yarzimilin.

  ReplyDelete
 19. እጠቅሳለሁ “ዛሬ ዓለምን ለበሽታ የዳረጓት ዕንቁላል ሳይሆኑ ዶሮ የሆኑት ናቸው፡፡“
  ዛሬ ኢትዮጵያን ለበሽታ የዳረጓት ከከረፋ የዶሮ ዕንቁላል የተፈለፈሉት ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 20. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 21. Diakon Daniel Egziabher Ybarkeh Edmena tena yesteh

  ReplyDelete
 22. I think most of your follower affected by this idea so they don’t give that much feedback. Please tell us how we can bet this bad habit? I asked myself and failed 2/4. However it is so difficult for me to lose my position even if I got it before dinner time. It never bothering me and I sleep very well and I am one of the happiest person in this planet.

  ReplyDelete
 23. It is not bad idea as long as they spend the money in Ethiopia. Most of the people they put the money in other country bank so we don't get any benafit. As we all know that we are the poorest country so we need more investor. We have to support all Ethiopian to invest in Ethiopia. There is not perfect person and all everybody want to be rich so we have to work togeter evenif we don't know the money where come from. At the movement the goverment has bad bolicy such as if you have more than 250,000 in bank, he will investgate you so our economy slow down since this policy approved by goverment.

  ReplyDelete
 24. Ezi hunta wust yale sew endat yewuta? Maleta Eratun kuris liy yebela.

  ReplyDelete
 25. "ቤተሰባቸውን መምራት ከመጀመራቸው በፊት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት መምራት የጀመሩ ሰዎች..." Check it, intellectuality doesn’t depend on ones age. In general, I always admire your point of view. God bless you!!!

  ReplyDelete
 26. Nice reflection on the very serious problem we are facing at every corner of our life nowadays. May God bless you and your family Amen!!!!

  ReplyDelete
 27. Thank you Dani. I always apreciste you b/c of ur view.

  ReplyDelete
 28. kala hiwat yasamalem dakon danal

  ReplyDelete
 29. Dear Dn Daniel, I always read your instructive writings. I'd like to express my heartfelt gratitude! Nowadays, some individuals become wealthy by illegal means; it retards the country's economic development endeavor. They are criminals and they need to be punished!

  ReplyDelete
 30. " Zare alemin lbeshita yedarguat enkulal sayhonu doro yehonut nachew". Really amazing expression. GOD bless u.

  ReplyDelete
 31. Egziabiher Yiselen. I hope could be posted to some other medias as well.

  ReplyDelete
 32. Egzer Edmena tena yestelin.

  ReplyDelete
 33. I agree with you. This message for Ethiopian Prime Minster Please change the school policy from grade 10 to 12. Our children must eat their dinner on time not on breakfast time. God bless you Dani.

  ReplyDelete
 34. ርዳታ ወይም እገዛ መልካም የሚሆነው ዓሣ ሊያሰግር የወጣውን ሰው በቀላሉ ብዙ ዓሣዎች እንዲያሰግር የሚያስችለውና እርሱም የተሻለ ማስገሪያ እንዲሠራ የሚያበቃው ዓይነት ርዳታ ከሆነ ነው፡፡

  ReplyDelete
 35. daaqon daani'eel ilaalchi ati waantota itti ilaaltu baay'ee nama ajaa'iba. namoota hundumaaf barnoota olaanaa kenna.waaqayyoon umurii dheeraa siif haa kennu.eyyeen akkasi malee manni amantaa ortodoksii tawaahidoo namoota hundaallee ija tokkoon ilaaluushee atuu ilmi ishee hojii keetiin mirkaneessiteetta. jlaalala dhugaa kiristoosirraa waan baratteef jaalala dhugaa hundarra ni qabda.amantaan osoo osoo hindaanga'iin namooni hedduun hojiikee ni dubbisu.irraa baratu. KANAAF ITTUMA FUFI.HUMURII DHEERAA SIIF HAA KENNU.( ayele,tekleamanu'el,afar region).

  ReplyDelete
 36. are dani rabenko mendenew koyehko are chegru mendenew? blogehen hulle sekeftew akumehal serahen mendenew beselam new gen?

  ReplyDelete
 37. kala hiwot yasemalen deakon daniel

  ReplyDelete
 38. ENDAT SHARE LARGEW BENATACHU NICE VIEW AS USUAL

  ReplyDelete
 39. ዛሬ ዛሬ በጋብቻ ውስጥ ብቻ ሊደረጉ የሚገባቸው ነገሮች ከጋብቻ በፊት፣ በበሳል ዕድሜ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ጾታዊ ግንኙነቶች በሚዲያ፣ በፊልም፣ በማኅበራዊ ድረ ገጾችና በአንዳንድ አቀንቃኞች ምክንያት በሚፈጠሩ የስሜት መመቻቸቶች የተነሣ በልጅነት ዕድሜ እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ሰዎች ራታቸውን ቁርስ ላይ በልተው የሚጓጉለት ነገር እንዳይኖር አድርጓቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 40. Tilik melikit new hulum neger kedimo tasibobet kaltesera fitsamew iyamirim le hagerim iytekimim. indezihum chinawoch yemilut ababal alachew 'Teach friends fishing, donot give a fish' le hagerachinim melkam neger yemiyasasib le meriwochachin e/her yistilin

  ReplyDelete
 41. ''ጉጉት የሌለው ነገ፣ የማይጋደሉበትም ሕይወት ስኬትን አያመጣምና፡፡ ስኬትን የማያጣጥም ሰውነት ደግሞ ምንጊዜም ውስጡ ክፍተት ይኖረዋል፡፡ ያ ክፍተት ነው ተስፋ መቁረጥን፣ ትካዜን፣ ራስን መጥላትን፣ የበታችነትን፣ ወራዳነትንና ራስን መጥፋትን የሚፈጥረው፡፡ '' Dn Daniel,God bless u,am so excited.It changed ma thought.

  ReplyDelete
 42. ርዳታ ወይም እገዛ መልካም የሚሆነው ዓሣ ሊያሰግር የወጣውን ሰው በቀላሉ ብዙ ዓሣዎች እንዲያሰግር የሚያስችለውና እርሱም የተሻለ ማስገሪያ እንዲሠራ የሚያበቃው ዓይነት ርዳታ ከሆነ ነው፡፡
  this is z only fact!!!
  tnx indeed!!

  ReplyDelete
 43. I really appreciate your view.It is better we all see ourselves and find an improvement opportunity to develop ourselves in the fare way in the way to be a good figure head for the next generation. I have learned a lot from your writing.God bless you and your family.

  ReplyDelete
 44. ዲ/ን ዳንኤል
  በቃ ምን ልበል? ብቻ በቃላት አልገልፀውም፡፡ እግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን፡፡

  ReplyDelete
 45. በቃ ምን ልበል? ብቻ በቃላት አልገልፀውም፡፡ እግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን

  ReplyDelete
 46. Egezabeher kedezih ayenet meker ena temeheret sayeleyen hiwotachenen yemneqagnebet yaderegen

  ReplyDelete