(በብዙ አንባቢያን ጥያቄ በድጋሚ የታተመ)
የገና
እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን እና መሰል የሕዝቡን
የዘወትር ጥያቄዎች መልስ የያዘ የማያዳግም ጥራዝ ማውጣት ከሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው፡፡ አብዛኞቹ ጉዳዮች አበው
ቀድመው ሥርዓት የሠሩባቸው እና ማብራርያ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ናቸውና፡፡ ለዛሬ ሦስቱን ብቻ እንመልስ፡፡
ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?
ፍትሐ ነገሥት፡ ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር /ዐንቀጽ 15፣ ቁ566/
የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 603/
የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?
ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 595/
ልደት ጋድ አለው?
ፍትሐ ነገሥት፡ የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 566/
ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡
40 ጾመ ነቢያት
3 ጾመ አብርሃም ሶርያዊ
1 ጋድ
ድምር 44
የገና ጋድ ከጾሙ ተያይዞ የተቀመጠ እንጂ ለብቻው
የተቀመጠ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት ለብቻው የሚቆጠር ጾም ነው፡፡ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 565/ ነገር ግን
አንድ ሰው ዐቢይ ጾምን ሳይጾም ከርሞ ሕማማትን ለብቻው መጾም አይችልም፡፡ የገናም ጋድ እንዲሁ ነው፡፡
ይህንን ጋድ የልደትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች እንዲጾሙት የተሠራ ነውን?
መልስ፡
በቤተ ክርስቲያን ላልተጠመቁ፣ ለማይቆርቡ፣ ንስሐ ለማይገቡ፣ ለማያስቀድሱ፣ ለማይጾሙ ሰዎች ተብሎ የተሠራ ልዩ
ሥርዓት የለም፡፡ በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ
ናቸው፡፡ ስለዚህም የገናን ጾም ክርስቲያን ሁሉ ጾመው በበዓለ ልደት ሊገድፉ ይገባቸዋል፡፡ ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና
ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/፡፡ ይህም
ከገና ጾም ተሸርፎ የሚጾም ነገር እንደሌለው ያሳያል፡፡
መልካም በዓል
ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡
ReplyDelete40 ጾመ ነቢያት
3 ጾመ አብርሃም ሶርያዊ
1 ጋድ
ድምር 44
3ቷ ቀን የስምኦን ጫማ ሰፊው ለማለት ይሆንን?? ተሳስቼ ከሆነ እባክህ አርመኝ:: ከሆነስ አብርሐም ሶሪያዊው ማነው?
እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፣ መልካም መረጃ ነው
ReplyDeleteDicon Danel E/r yestelen .God bless u and yr family.
ReplyDeleteእግዚአብሔር የስጥልን፡፡ በአቅሚ ለማውቀው አደርሳለው፡፡ መልካም በዓል ላንተም ከቤተሰቦች ጋር፡፡
ReplyDeleteThank you very much edemane tena yesteline
ReplyDeleteመልካም በዓል for you and your family!!
ኣሜን ለሁላችን መልካም በኣል ዪሁንልን። ቃለ ሂወት ያሰማልን። እግዚኣብሔር ይባርክህ። ኣንድ ተጨማሪ ጥያቄ ልጠይቅህ ወንዲማችን ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት። ጾመ ጋሓድ እሁድ እና ቅዳመ ሲውል ይጾማል ወይ? .
ReplyDeletekal Hiwot yasemalin.
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin. I wish if you a discussion of such issues in the future- as many of us have poor understanding of our church doctrines
ReplyDeleteThanks Dn. Daniel.
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን። ለእርስዎና ለቤተሰቦችዎ እንዲሁም ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን መልካም በዓለ ልደተ ክርስቶስ (ጌና) ይሁን።
ReplyDeletedany selezi beaunu erobe selwale yebelale malte new?
ReplyDeleteDanie Egziabher Yistih
ReplyDeleteNice description GOD bless you
ReplyDeleteNice description God bless you
ReplyDeleteThanks Dani, it is good explanation.
ReplyDeleteCan you pls put a refernce or any resouce material about why/how/when our calender is different from European calender? I am staying outside Ethio & I couldnt explain it to pro-Ethiopian collegues! pls
http://www.melakuezezew.info/2013/09/1.html
DeleteIf you want to know the history about ethiopian calendar go to youtube.com and search Megabe Hadis Rodas interview with sheger FM. You will learn a lot. It has 4 parts (1-4)
DeleteThank you very much! It could have been so easier to avoid mind wave if we were able to visit our books!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteዳኔ ኑርልን ከበቂ በላይ መልስ አግኝተናል ።መልካም በአል
ReplyDeleteAMEN KALE HIWET YASEMALIN!
ReplyDeletethank you D.n Daniel kibret. Happy Christmas
ReplyDeleteሁሌ ገና በመጣ ቁጥር አጨቃጫቂ ከሚሆን እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ሲኖዶስ ምላሽ ቢሰጥበት የተሻለ ይሆናል፤ አሳ በፆም ይበላል አይበላም የሚሉትን ጨምሮ ምንም እንኳን አሳ ፆም መሆኑ ቢታወቅም …
ReplyDeleteውድ ዲ/ን ዳንኤል ገናና ጥምቀትን አስመልክቶ እጥር ምጥን ላለችው አገላለጽህ ምስጋናዬ የላቀ ነው። እስኪ በዚሁ እግረ መንገድህን ከፈረንጆቹ ገናና የዘመን አቆጣጠር ጋር ያለንን ልዩነት በጥፋጩ ብዕርህ ዳስልን። ኦኦ ለካ በብዕርህ ሊባል አይችልም .... ታዲያ በምንህ ልበል...... በጣቶችህ.... በኪቦርድህ......
ReplyDeletethe pen is in the mind and the board is anything
DeleteI know my dear it is just to fun. Yalebotaw kelje kehone gin ykirta.
DeleteDejen Y.
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin, ke-tsomum bereket yikfelilin. Amen
Better if you answer some questions you think important well to fully take care your readers . Otherwise it has no use commenting .
ReplyDeleteሰላም
ReplyDeleteእኔ ሳስበው ለዘመን መለወጫ ጋድ ቢሰራ እላለሁ:: ምን ትላለህ?
አመሰግናለሁ::
ጥምቅት በዓል ዓርብ እና እና የረቡዕ በሚውልበት ጊዜ ማክሰኞ እና ሐሙስ ጋድ ስለሆነ ይጾማሉ:: ነገር ግን የገና በዓል በየትኛው ቀን ቢውል ከበዓሉ አንድ ቀን በፊት ሁሌም ጾም ነው:: ስለዚህ በገና ሁልጊዜ ጋድ ለምን ይሆናል? ጋድ ጾም ዓርብ እና እና የረቡዕ ምትክ ቢሆን ኖሮ ከዛውጭ በሆኑ ቀናት መበላት ነበረበት:: ለዚህ ምላሽ የሚሰጠኝ ሰው ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር....
ReplyDeleteይህን ጥያቄ እኔም እጋራለሁ። በዚሁም አጋጣሚ በገና በዓል የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በዓሉን አስምልክቶ ያቀረብከውን አስተያየት እጅግ በጣም ከማድነቄም በላይ አኩርተኽናልና በርታ ቃለ ህይወት ያሰማልን ለማለት እወዳለሁ ዲን ዳን ኤል።
Deleteወንድማችን ዲያቆን ዳኒኤል በግልጽ ኣስቀምጦታል።
Delete1ኛ) የመጀመርያዎቹ 40 ቀናት ጾመ ነብያት ይባላሉ።
2ኛ) ቀጥሎ ያሉት 3 ቀናት ጾመ ኣብርሃም ሶርያዊ ይባላሉ።
3ኛ) የመጨረሻው 1 ቀን(የገና ዋዜማው ዕለት) ደግሞ ጾመ ጋሓድ ይባላል።
ykirta be mezegite! "be tsom neger lay kirkir betenesa gize le tsome adlu" ye millew ye abatoch wisanes endet yitayal?
ReplyDeleteKale hiwot yasemalen rejem edime ketena gare yisteh.
ReplyDeleteDn Daniel kalehiwot yasemalin selizih lidet be 28 yemikeberebet gize 44 ken endihon tsom megbiaw hidar 14 new malet new?
ReplyDeleteMabraria betesetibet Egziabher yistelen