ታኅሣሥ 19 ቀን 2007 ዓም በቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከታወቁት ሊቃውንት
መካከል አንዱን አጥተናል፡፡ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየን፡፡ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመቆርቆር፣ በማስተማርና በመጻፍ
የምናውቃቸው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያገለገሉ፤ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ ጥያቄዎቹን በመመለስና አስረግጠውም በማስረዳት
የምናደንቃቸው ነበሩ፡፡
ዜማ፣ አቋቋም፣ የአማርኛ ሰዋስው፣ ቅኔና የግእዝ አገባብ፣ ብሉይ፣ ሐዲስ፣ ነገረ መለኮት፣
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በዘመናዊ ትምህርት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን ስናይ፤ በአንባቢነታቸው ጥንታውያንና
ዘመናውያን መጻሕፍትን የሚያገላብጡ ብቻ ሳይሆኑ በላዔ መጻሕፍት እንደነበሩ በሌሎቹ ሊቃውንት ሲመሰከርላቸው፤ በምሥራች ድምጽ ሬዲዮ
ትምህርት በመስጠት፣ በታሪክና ድርሰት ክፍል ለዐሥር ዓመታት በማገልገል፤ የመዝሙር ክፍልን በመምራት፣ የዜና ቤተ ክርስቲያንን በምክትልና
በዋና አዘጋጅነት በማገልገል፣ እንዲያውም ጋዜጣውን የጋዜጣ መልክ
በማስያዛቸው በ1962 ዓም መሸለማቸውን እያዘከርን የተጓዙበትን የዕውቀት
ጎዳና ስንመረምር ያጣነው አንድ ሰው ብቻ ባለመሆኑ፡-
አራት ሰው ሞተ ተቀበረ ዛሬ
ድጓ ጾመ ድጓ መዋሥዕት ዝማሬ
ተብሎ ለሊቁ የተገጠመው ሙሾ ለእርሳቸውም ይስማማቸዋል እንላለን፡፡
የየረርና ከረዩ አውራጃ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ጸሐፊ፣ የቀበና አቦ አስተዳዳሪ፣
የካህናት አስተዳደር መምሪያ ጸሐፊ፣ የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ የከፋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ የትምህርትና ማሠልጠኛ
መምሪያ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ የአስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣ የቁጥጥር አገልግሎት ኃላፊ፣ የበጀትና
ንብረት መምሪያ ኃላፊ፣ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ፣ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህት ቤት ምክትል
ዲን፣ እየሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን ማገልገላቸው ስንመለከት፡-
ቀባሪዎቹን
አፈር መልሱ እንጂ ድንጋይ ለምናችሁ
የቀለም ቀንድ ነው ትሰብሩታላችሁ
እንላቸዋለን፡፡
በ1977 በምዕራብ ጀርመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ ለማሳየት ከተጓዘው
ልዑክ አንዱ ነበሩ፤ በ1995 የዓለም አብያተ ክርስቲያናት በእስክንድርያ ከተማ ባደረገው ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንን ወክለው ነበር፣
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ በአዲስ መልክ ሲዘጋጅ በብርቱ ካገለገሉት ሊቃውንት አንዱ ነበሩ፣ የመንና ጅቡቲ የሚገኙ ምእመናንን ለማስተማር
በየዓመቱ ይጓዙ ነበረ፡፡ የሊቃውንት ጉባኤ አባል ሆነው ለብዙ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ይህንን ስንመለከትም
እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር
ዕውቀት ተሸክሞ መጣልህ መምር
እንለዋለን፡፡
ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሚያዘጋጁት ጉባኤ ልጆችን
ሳይንቁ፣ ክፍለ ሀገር በሚዘጋጅ ጉባኤ ለመንገዱ ሳይሰቀቁ በመጓዝ ያስተማሩ የዘመናችን ሐዋርያ ናቸው፡፡ ክህነትን፣ ትምህርትንና
ጽሕፈትን አንድ አድርገው የያዙ፤ በተለይም ‹‹ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን›› እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ ሆኖ እንዲወጣ በብርቱ የደከሙ
ሊቅ ናቸው፡፡ ድካማቸው ፍሬ አግኝቶ በየጊዜው ያዘጋጇቸው መጣጥፎችና መጻሕፍት ዛሬ ከኮሌጆች እስከ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ድረስ
የማስተማርያ ዋና መሣሪያዎች ሆነዋል፡፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንድ የትምህርት ዘርፍ ሆኖ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ሚያዝያ 19 ቀን 1929 ዓም ይፋት ውስጥ ደብረ ምሥራቅ ሾተል አምባ በኣታ አጥቢያ ተወልደው፣ በ1941 ዓም ከብጹዕ
ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዲቁና፣ በ1959 ዓም ቅስና ተቀብለው፤ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ወልደው፣ አሥር የልጅ ልጆች አይተው
በ78 ዓመታቸው የተለዩን ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ በዕለተ ዕረፍታቸውና ቀብራቸው ብዙዎችን ያስደነቁ ሁለት ነገሮች ተከስተዋል፡፡
የመጀመሪያው ክንፈ ገብርኤል ተብለው ተጠርተው በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል(ታኅሣሥ 19 ቀን) ወደ ፈጣሪያቸው መጠራታቸው
ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሲከናወን የሕይወት ታሪካቸው በሚነበብበት ጊዜ ከትልቅ ዋርካ
ላይ ማንም ሳይነካው አንድ ትልቅ ቅርንጫፍ ተገንድሶ መውደቁ ነው፡፡
ቦታው የነበሩ፣ ይህንንም ነገር የተመለከቱ ሁሉ ታሪኩን በካሜራቸው ሲቀርጹና ከታላቋ ዋርካ
ከቤተ ክርስቲያን ብዙዎችን የያዘው አንዱ ታላቅ ቅርንጫፍ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል ዛሬ መሰናቱን በኀዘን ሲተረጉሙ ነበር፡፡ የቅርንጫፉን
ቅጠልም ብዙዎቹ ተሻምተው ወስደውታል
በረከታቸው ይደርብን፡፡
Meches Taamir Neew! Warkam Hazen Gebaw!?
ReplyDeleteWho is going to replace such ye-Betekirstian Maaezen?
Nefsachewn Be-Genet Yanur!
Thank you Dani!
RIP
ReplyDeleteBetam azignalewu
EGZIABHER nefsachewin bedegagochu abatoch ekif yanurlin.
ReplyDelete.I am truly sorry to hear the loss of such a big father.May God give him the comfort and peace that he seek and may his soul rest in peace.. May our Lord bless and comfort his family and all Christians during this time of grief
ReplyDeleteክቡር ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል በረከታቸው ይደርብንና ከላይ መምህራችን ዲያቆን ከገለጽው በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ወደ የመን ከተላኩት እና በየመን መስቀለ ብርሐን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ወንጌል በመስበክ ንስሐ በመቀበል ቀድሶ በማቁረብ እና ተጋቢዎችን በተክሊል እና በስጋወደሙ በማጋባት ምዕመናንን በማጽናናት ለመስቀለ ብርሐን ባለውለታ ከሆኑት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች አንዱ ነበሩ። አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን።ለቤትሰባቸው መጽናናትን ይስጥልን።
ReplyDeleteበጣም የገረመኝ ደግሞ እኒህ ታላቅ ሰዉ የተወለዱትም ሆነ የሞቱት የመልዕኩ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ-በዓል መሆኑና መጠሪያ ስማቸዉም ክንፈ-ገብርኤል መሆኑ አስገርሞኛል፡፡ ነፍሳቸዉን በገነት ያኑርልን፤በእሳቸዉ እግር የሚተካ አገልጋይና ጠባቂ ይስጠን፡፡
ReplyDeleteነፍሳቸውን ይማርልን የሚለው እንደ እርሳቸው አይነት ሊቃውንትን ስለማይመጥን በረከታቸው ይደርብን በማለት ሃዘን ሳይሆን ደስታየን እገልጣለሁ፡፡ ተዘጋጅቶ ለሄደ ሃዘን አይገባውምን!
ReplyDeleteከታዘነስ ቦታውን ይዘው ሳይሰሩ በቁማቸው ለሞቱትና ጠንካራ ዕድርተኛ ስለሌለን ከመቃብር ስር ሳይገቡ ለሚባዝኑት ነው፡፡ ይብላኝ ትምህርታቸውን ሰምተን ለውጥ ላላመጣነው ሁሉ!
እውነት ብለዋል።
DeleteCopy and paste, what you said is what I have inside.
Deletebetkrstane zare telke abat atalche ........egzyabher nebschewn begent yanure berktachew yederben
ReplyDeleteRip
ReplyDeleteRip
ReplyDeleteበረከታቸው ይደርብን
ReplyDeleteEGZIABHER NEFISACHEWUN YIMARILIN IGNANIM KEBEREKETACHEW YASATIFEN!!!
ReplyDeleteሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ በዕለተ ዕረፍታቸውና ቀብራቸው ብዙዎችን ያስደነቁ ሁለት ነገሮች ተከስተዋል፡፡ የመጀመሪያው ክንፈ ገብርኤል ተብለው ተጠርተው በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል(ታኅሣሥ 19 ቀን) ወደ ፈጣሪያቸው መጠራታቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሲከናወን የሕይወት ታሪካቸው በሚነበብበት ጊዜ ከትልቅ ዋርካ ላይ ማንም ሳይነካው አንድ ትልቅ ቅርንጫፍ ተገንድሶ መውደቁ ነው፡፡
ReplyDeleteWeldebirhan Mekelle
I consider myself lucky to have had the good fortune of learning (though for a short time) from this Pillar of the Church.
ReplyDeleteHe truly was one of a kind who deserved the title of "Doctor of the Church."
He was a well rounded, learned, patient, understanding priest (that's what he considered himself to be first and foremost) who knew the why and how of every church sacrament. (The questions we asked him and the quick response he gives on every subject with ample and convincing explanation....lot's of good memories...)
May he rest in peace.
እውነት ብለሃል። በረከታቸው ይደርብን።
ReplyDeleteውዶቼ ፣ነፍስ ይማር የሚባለው እንደ እኔ አይነት ደካማ ሲሞት ነው፣ ብጹእ ክቡር አባታችን እድሜያቸውን በሙሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በታማኝነት፣ ያለመታከት ያገለገሉ በእውነት ዲያቆን ዳንኤል እንዳለው በረከታቸው ይደርብን ነው የሚባለው፣ አምላከ ቅዱሳን እሳቸውን የሚተካ አባት ይስጠን፣
ReplyDeleteYe Abatachen Bereket Tselote Ayleyene.
ReplyDeleteNebsachewen Ke Kidusan Gara Yanurelene. Amen
እጅግ የማከብራቸውና የምወዳቸው የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ምሁርን ማጣታችን ያሳዝናል እኔም በጣም አዘንኩ፡፡ የስርዓተ ቤተክርስቲያን መጽሓፋቸው ለብዙዎች መሰረት የሆነ የመሰለንን በመሰለኝ ከመናገር ምላስን የገታ እጅግ የተከበረ መፅሐፍ አኑረውልን ሄደዋል፡፡ በእግዚአብሄር ስራ ገብቶ ማንም ፍርድ አይሰጥምና እንደ ሌሎችም ዛሬ ፀድቄያለሁ ብለን አንመጻደቅምና ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን በረከትና ረድኤታቸው ይደርብን እላለሁ፡፡እጅግ የማከብራቸውና የምወዳቸው የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ምሁርን ማጣታችን ያሳዝናል እኔም በጣም አዘንኩ፡፡ የስርዓተ ቤተክርስቲያን መጽሓፋቸው ለብዙዎች መሰረት የሆነ የመሰለንን በመሰለኝ ከመናገር ምላስን የገታ እጅግ የተከበረ መፅሐፍ አኑረውልን ሄደዋል፡፡ በእግዚአብሄር ስራ ገብቶ ማንም ፍርድ አይሰጥምና እንደ ሌሎችም ዛሬ ፀድቄያለሁ ብለን አንመጻደቅምና ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን በረከትና ረድኤታቸው ይደርብን እላለሁ፡፡
ReplyDeleteቅዱስ እግዚአብሄር ነብሳቸውን በገነት ያሳርፍልን፡፡
ReplyDeleteሀዋርያዊት ቅድስት ቤተክርስትያን እንደ እሳቸው ያሉትን ትሻለች፡፡
የሃይማኖት ዜግነት ቀይረው ግን በቤተክርስትያን ውስጥ መስለው ገብተው ግራ ተጋብተው ምዕመኑን ግራ ከሚያጋቡትን እግዚአብሄር ይጠብቀን፡፡
አምላከ ቅዱሳን ነፍሳቸውን ከአብሃም ከይስሐቅና ከደጋግ አጋቶች ጋር በቅኝ ያቁምልን፡
ReplyDeleteNefs yimar!
ReplyDeleteእግዚአብሄር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን
ReplyDeleterip mazene le ega new enje le esachew aydelem escwe ema wede abatchew adewale
ReplyDeleteegziabhere nefesachwen begenet yadergewe
ReplyDeleteበዘመናቸው መሥራት የሚገባቸውን ሰርተው አልፈዋል።ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን ሰው በራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም የእነርሱን አርአያ መከተልና ክርስትናን ለሚቀጥለው ትውልድ በመጠበቅ ማስረከብ ይኖርብናል።ዛሬ ምድሪቱን ሊወር የተዘጋጀውን መስቀል ቆራጭና ጨረቃ ተካይ ለመከላከል ተጋድሎውን ማጠናከር የእነዚህ አባቶች ተጋድሎ እያዩ መትጋት እንጂ በጊዜያቸው ተጠቅመው ያለፉ ሰዎችን እያደነቅን የራሳችንን ሃላፊነት ሳንወጣ እንዳንቀር አደራ እንላለን!!
ReplyDeletewe so lost the father.
ReplyDeleteAmen bereketachew yideribin
ReplyDeleteAMEN AMEN AMEN BEREKETACHEW YIDERIBIN . NEFSACHEW YIMAR LE ABATACHIN.
ReplyDeleteAmelake Kidusan Nebe.sachewune Berfet Wuha Belemelem Meseke Yanurlen. Le Betesebochachewu Metsenanaten. Kehulum Belay Yisetelen Yiseten. Endezihe Ayinete Abatochen Medere Tsetata Egiiyo , new Malete Yalebe Ezibe Chiristian Kutawun Bemeheretu Edimeleselen. Ye Abatachine Bereketache Kehulachine Gar Yihun, Yedekamochine chihote Yemayinek Amelake new ena Tegetet Seleemenetachi ena sela hagerachine Abet enbele wode fetari,. Dn ,Daniel edme ketene kene mela betesebehe cheru amelakachin Yadileh
ReplyDeleteበጣም አሳዝኖኛል! እውነት ነው ቤተክርስቲያናችን ትልቅ ሰው አጣች!!”
ReplyDeleteሰባዎቹ አጋማሽ ላይ በክረምት ወራት በታዕካ ነገስት በኣታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ባለው የመማሪያ ክፍል ስለ ሥርዓተ በተክርስቲያን ያስተማሩኝ ትምህርት ክረምት በመጣ ቁጥር አስታውሰዋለሁ፡ በእውነት በረከታቸው ይደርብን፡፡