Friday, November 21, 2014

መጀመሪያ ሰው ነኝ

አንድ ወዳጄ በየገጸ ድሩና በየውይይት መድረኩ የሚሰማውን ‹መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፣ መጀመሪያ ትግሬ ነኝ፣ መጀመሪያ አማራ ነኝ› የሚል ክርክር አየና ‹አንተ መጀመሪያ ምድንነህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ 

እኔ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ የተፈጠርኩትም ሰው ሆኜ ነው፡፡ አምላክም የፈጠረው ሰውን ነው፡፡ ቡድን፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ጎሳ፣ ነገድ የሚባሉ ነገሮችን ፈጠረ የሚል መጽሐፍም ትምህርትም አላገኘሁም፡፡ ክብርም፣ ሥልጣንም፣ ጥበብም፣ ፈጣሪውን መምሰልም የተሰጠው ለሰው ነው፡፡ መላእክት ሲፈጠሩ በማኅበር ነው የተፈጠሩት፡፡ አንድ ላይ ነው የተገኙት፡፡ ሰው ግን ሲፈጠር በየተራ ነው፡፡ መጀመሪያ አዳም፣ ከዚያ ሔዋን፣ ከዚያ ቃየል፣ ከዚያ አቤል እያለ ተራ በተራ፡፡ ቡድኖቹን ሰው በኋላ ራሱ ፈጠራቸው እንጂ አብረውት አልተፈጠሩም፡፡

መጀመሪያ ሰውነቴ ነበረ፡፡ በኋ ቡድኔ መጣ፡፡ በኋላ የመጣው ቡድኔ በፊት የነበረውን ሰውነቴን ከዚህ አትለፍ ከዚህ አትውጣ፣ ከዚህ አትዝለል ከዚህ አትሻገር አለው፡፡ ቡድኔ በእኔ መጠራት ሲገባው እኔ በቡድኔ ተጠራሁ፡፡ ለእርሱ ህልውና ሲል እኔን ሰዋኝ፡፡ እርሱ ሳይመጣ በፊት ግን እኔ ሰውዬው ነበርኩ፡፡

መጀመሪያ ሰው ስለነበርኩ መጀመሪያ ሰው ነው መከበር ያለበት፣ መጀመሪያ ሰውነቴ ነው መብት የሚያስፈልገው፣ ሰውነቴን አሥረህ፣ ገርፈህ፣ ገድለህ፣ ነጥቀህ፣ ቀምተህ ቡድኔን ከየት ታገኘዋለህ? እኔን ትተህ እንዴት እኔ ለፈጠርኩት ቅድሚያ ትሰጣለህ? እኔን ንቀህ እንዴት እኔነት ተሰባስቦ ላቋቋመው ቡድን ክብር ትሰጣለህ? ይኼማ ሐሰት ነው፡፡ ሴሎቹን ገድለህ ሰውየውን ማኖር ትችላለህ? ገጾቹን ገንጥለህስ መጽሐፉን ታኖራለህን? ከብቶቹን አርደህ ስለ መንጋው መጨነቅስ ምን ማለት ነው?

ሀገር ይቀየራል፣ ቋንቋ ይቀየራል፣ ባሕል ይለወጣል፣ እምነት ይለወጣል፣ ጎሳ ይለወጣል፤ ሰውነት ግን እኔ ነኝ፡፡ እነዚህን ሁሉ መቀየር የቻልኩት ሰው ስለሆንኩ ነው፡፡ ሰው ሆኜ ስለተፈጠርኩ ከሰዎች ጋር እኖራለሁ፡፡ ለብቻዬ የማልችላቸውን  ነገሮች በጋራ ለመከወን፡፡ ያን ጊዜ የጋራ መግባቢያ ያስፈልገኛል፡፡ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ልማድ፣ ወግ፣ ሥርዓት ይመጣሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎችን በጋራ ለማኖር፣ ሲኖሩም ተግባብተውና የጋራ የሆነ እሴት ኖሯቸው እንዲኖሩ ለማድረግ በእኔ በሰውየው የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ሊተውኝ አይችሉም፤ ልተዋቸው ግን እችላለሁ፡፡ ያለ እነርሱ መኖር እችላለሁ፤ ያለ እኔ መኖር ግን አይችሉም፡፡ እኔ ነኛ ዋናው፡፡

ስለዚህ ነው መጀመሪያ ሰው ነኝ ያልኩት፡፡ ሰው ስለሆንኩ የሰው ሁሉ ነገር ይመለከተኛል፡፡ የሰውም ሁሉ ነገር ያሳስበኛል፡፡ ያ ሰው ማንም ይሁን፣ ምንም ዓይነት ቋንቋ ይኑረው፤ የትኛውንም ዓይነት ባሕል ይከተል፡፡ እርሱ እኔና እርሱን አያገናኘንም፡፡ መገናኛችን ሰውነት ነው፡፡ የእሥረኛው ነገር ይመለከተኛል፤ ምክንያቱም ሰው ስለታሠረ፤ የሟቹ ነገር ይቆረቁረኛል፤ ምንያቱም ሰው ስለሞተ፤ የተገፋው ልቅሶ ይሰማኛል፤ ምክንያቱም ሰው ስለተገፋ፤ የተቀማው ዕንባ ያርሰኛል፤ ምክንያቱም ሰው ስለተቀማ፡፡
እንደሰው በፈጠረው ነገር መልሶ የሚጠፋ፣ በሠራው ነገር መከራ የሚያይ፣ ባመጣው ነገር የሚሄድ፣ ባስገኘው ነገር የሚታሠር ፍጡር የለም፡፡ ራሱ ያመጣቸው ጎሳዎች፣ ነገዶች፣ ቡድኖች ራሱን እንዳያይና የተፈጠረበትን እንዲረሳ አድርገውታል፡፡ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሰውነትን እንዲረሳ፡፡  ‹እገሌ እንዲህ ሆነ› ሲሉት ‹ሀገሩ የት ነው፣ የማን ወገን ነው፣ የኛ ሰው ነው፣› ጎሳ ነገዱ፣ ወንዙ ጎጡ እያለ እያጠበበ ይጠይቃል፡፡ የሰውየው ማንነት ከእርሱ ቡድን እየራቀ በሄደ ቁጥር ጭንቀቱ ይቀንሳል፡፡ አንዳንዴም እንደ ድል ይቆጥረዋል፡፡ ‹የራሱ ወገን› የተጠቃ ሲመስለው ግን አራስ ነበር ሆኖ ይነሣል፡፡ ራሱ በፈጠረው አጥር ራሱን አጥሮ፤ መገናኛውን ሰውነትን ሰብሮታል፡፡ ያም ሰውኮ ሰው ነው፡፤ መጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ሰው ስለሆነ ነው እንደዚያም የሆነው፡፡ ሃይማኖት የኖረው ሰው ስለሆነ ነው፣ ባሕልም የኖረው ሰው ስለሆነ ነው፣ በቋንቋም ያወራው ሰው ስለሆነ ነው፡፡ የተለየ አመለካከትም የያዘው ሰው ስለሆነ ነው፡፡ የሚቃወምህም ሰው ስለሆነ ነው፡፡ መጀመሪያ ሰው ነው፡፡

ያኛው ባሕል፣ ያኛው እምነት፣ ያኛው ቋንቋ፣ ያኛው አስተሳሰብ፣ ያኛው ልማድ፣ እንዲከበር፣ መብቱም እንይደፈር፣ ዋጋም እንዳያጣ የምፈልገው - የሰው ስለሆነ ነው፡፡ እዚያ ውስጥ ሰው ስላለበት ነው፡፡ የዚያኛው ፓርቲ፣ የዚያኛው ማኅበር፣ የዚያኛው ቡድን መብትና ክብር እንዲጠበቅ የምሟገተው ስለማምንበት፣ ስለምቀበለውና ስለሚስማማኝ አይደለም - ሰው ስላለበት ነው፡፡ የሰው ስለሆነ ነው፡፡ በተለየ መንገድ የተደራጀው፣ በተለየ መንገድ ያሰበው፣ በተለየ መንገድ የሄደው፣ በተለየ መንገድ ያመነው፣ በተለየ መንገድ የተፈላሰፈው ሰው ስለሆነ ነው፡፡

ልዩነቱን እንኳን መፍጠር የቻለ - ሰውኮ ነው፡፡ ሌሎቹ ፍጡራን ልዩነታቸው ተፈጠረላቸው እንጂ ልዩነትን አልፈጠሩትም፡፡ ሰው ግን ባሕል፣ ቋንቋ፣ ልማድ፣ ሥርዓት፣ ሀገር፣ አመለካከት፣ አስተሳሰብ የሚባሉ ነገሮችን አምጥቶ የገዛ ልዩነቱን ራሱ የፈጠረ ነው፡፡ ለምን? ቢሉ ሰው ስለሆነ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚከብሩት ሰው ሲከብር ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ህልው የሚሆኑት ሰው ህልው ሲሆን ነው፡፡ አማራ ሆኖ፣ ኦሮሞ ሆኖ፣ ሶማሌ ሆኖ፣ ሕንድና ቻይና ሆኖ፣ እንግሊዝና ጣልያን ሆኖ የተወለደ የለም፡፡ ሁሉም ሰው ሆኖ ነው የተወለደው፡፡ ባሕሉን ለመደው፣ ቋንቋውን ለመደው፣ አለባበሱን ለመደው፣ ሀገሩን ለመደው እንጂ ራቁቱን፣ ቋንቋ ሳያውቅ፣ ወገን ሳይኖረው ነው የተወለደው፡፡

አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡ 
88 comments:

 1. yemigerm eyita new ene bizu timirabetalehu
  kale hiwote yasemalin

  ReplyDelete
 2. አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 3. Yes Danni, you are human being. However when people born and grow up with human then they will think like a human. As you know that some people they didn’t get this chance, they born in the forest and grow up with wild animal then they start working with human. It is so difficult for them to agree or work with human being because when the grow up they learn everything from wild animal such as Animal kill other animal, Animal take other people place, Animal never talk or work with other animal, Animal never learn from his/her mistake, Animal always scare other animal. Animal think he/she smarter than other. In conclusion they will never agree with your idea because when they grow -up their family told them, they are ትግሬ so they think they are ትግሬ. At the movement they force us to think, speak, read, write, eat, work like them because wild animal think this way.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wise thinking, God bless you. I was wondering why they think like this now you solved my question. Wild animal is Wild animal.

   Delete
  2. You didn't go to school. you need schooling

   Delete
 4. አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 5. አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 6. This is great. This is wonderful. And most of all, it is True and Human.
  Somehow, it reminds me of Tolstoy saying, "Christ Himself was not Christian!"

  ReplyDelete
  Replies
  1. No much wisdom in that saying. "Christ is Christ"

   Delete
 7. Thank you Dn.Daniel, it is very interesting article.

  ReplyDelete
 8. ለዚህም ነው ንጉስ ዳዊት ለልጁ ለንጉስ ሶሎሞን ሲመክረው ሰው ሁን ያለው።
  ሰው መሆን ታዲያ ዲን ዳንኤል እዳስተዋለው ነው መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 9. "እኔ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ የተፈጠርኩትም ሰው ሆኜ ነው፡፡ አምላክም የፈጠረው ሰውን ነው፡፡ ቡድን፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ጎሳ፣ ነገድ የሚባሉ ነገሮችን ፈጠረ የሚል መጽሐፍም ትምህርትም አላገኘሁም፡፡!!!"

  Dani, EGZIABHER yitebkh!!!

  ReplyDelete
 10. ''እኔ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ የተፈጠርኩትም ሰው ሆኜ ነው፡፡ አምላክም የፈጠረው ሰውን ነው፡፡ ቡድን፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ጎሳ፣ ነገድ የሚባሉ ነገሮችን ፈጠረ የሚል መጽሐፍም ትምህርትም አላገኘሁም፡፡!!!''


  ReplyDelete
 11. ገጾቹን ገንጥለህስ መጽሐፉን ታኖራለህን?

  ReplyDelete
 12. ዳኒ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ፡፡ በእውነት መማር ማለት እንደዚህ ነግሮችን አርቆ ለማሰብ እንጂ ለዕለት ትርፍ ባለመመሆኑ፡፡

  ReplyDelete
 13. ይች ጽሁፍ ጣም አላት! በተለይ ለዘር ድርጂት መሪዎችና ለመንግስት ባለስልጣናት ተብራርታ በሴሚናር መልክ ብትቀርብ ፡ ጥቅሟ ለትውልድ ሁሉ ይተርፋል፡

  ReplyDelete
 14. እኔም ከናቴ ማህጸን ወጥቼ ይህቺ ምድር ስትቀበለኝ መሬቱ ኣንተ ጉራጌ ነህ ኣላለኝም

  ReplyDelete
 15. Man kind has lost the knowledge.

  ReplyDelete
 16. Dani indimen ke muluteninet gar yistih tiru iyita new betele ahun yalenibet kifu "gize". አማራ ሆኖ፣ ኦሮሞ ሆኖ፣ ሶማሌ ሆኖ፣ ሕንድና ቻይና ሆኖ፣ እንግሊዝና ጣልያን ሆኖ የተወለደ የለም፡፡ ሁሉም ሰው ሆኖ ነው የተወለደው፡፡ ባሕሉን ለመደው፣ ቋንቋውን ለመደው፣ አለባበሱን ለመደው፣ ሀገሩን ለመደው እንጂ ራቁቱን፣ ቋንቋ ሳያውቅ፣ ወገን ሳይኖረው ነው የተወለደው፡፡ Lib lalew lib yist beteley fidel kotern lemilu sewun be wenz lemekefafel letenesu.

  ReplyDelete
 17. በእርግጥ በአሁን ጊዜ የሀገራችንም ዋነኛው ችግር ይሄ የጠባብነት አመለካከት ነው ብሄር ከብሄር ሀይማኖት ከሀይማኖት ጎሳ ከጎሳ መንደር ከመንደር አልፎ ተርፎ ቤተሰብን ከቤተሰብም እየከፋፈለ ያለ የአለማችን ዋነኛው የአመለካከት በሽታ ነው። አሁንማ እህት ወንድሞቻችን በአለማችን የተለያዪ አገሮች ኑሮዋቸውን አድርገው ባሉበት ጊዜ በማያውቁት ባህል ስራ ቀለም ተስማምተው እየኖሩ ባለበት ጊዜ እኛ ግን ፠እከሌ የወንዜ ልጅ ነው፠ እንባባላለን
  ሁላችንም እራሳችንን እንፈትሽ የጠባብነት በሽታ ውስጥ ያለን በቅድሚያ እራሳችን ከበሽታው እንፈወስ ቀጥሎ ይህን አስተሳሰብ ለማጥፋት የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል። ጠባብነትን ከራሳችንም በማስወገድ ቀድመን በመለወጥ ከዛ ሌሎችንም እንለውጥ እላለሁ

  ReplyDelete
 18. እውነት ነው፤ ሰው መጀመሪያ ሰው ሆኖ ተፈጠረ፡፡ቀጠለና በእርሱ ውስጥ ያሉት ስሜቶች እና ፍላጎቶች እነደ እርሱ ካሉ ሰዎች ጋር ተደምረው ባሕል እና ስርዓትን ሲያድግም ብሔርተኝነትን ፈጠሩ፡፡እውነት ነው፤ሰው ፍላጎቶቹንና ስሜቶቹን ከገዛቸው በእነእርሱም ላይ የበላይ ከሆነ፡፡በእውነትም ሰው ሰው ይሆናል፡፡
  ወንድማችን እግዚአብሔር ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 19. dani, egziabher ystlin, endih astemren engi
  tiliku hatiat zeregn net newna!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 20. ጥሩ ነገር እየነገርከን ነው ዳንኤል ሌሎቹ ፍጡራን ልዩነታቸው ተፈጠረላቸው እንጂ ልዩነትን አልፈጠሩትም፡፡ ሰው ግን ባሕል፣ ቋንቋ፣ ልማድ፣ ሥርዓት፣ ሀገር፣ አመለካከት፣ አስተሳሰብ የሚባሉ ነገሮችን አምጥቶ የገዛ ልዩነቱን ራሱ የፈጠረ ነው፡፡ ለምን? ቢሉ ሰው ስለሆነ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚከብሩት ሰው ሲከብር ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ህልው የሚሆኑት ሰው ህልው ሲሆን ነው፡፡ አማራ ሆኖ፣ ኦሮሞ ሆኖ፣ ሶማሌ ሆኖ፣ ሕንድና ቻይና ሆኖ፣ እንግሊዝና ጣልያን ሆኖ የተወለደ የለም፡፡ ሁሉም ሰው ሆኖ ነው የተወለደው፡፡ ባሕሉን ለመደው፣ ቋንቋውን ለመደው፣ አለባበሱን ለመደው፣ ሀገሩን ለመደው እንጂ ራቁቱን፣ ቋንቋ ሳያውቅ፣ ወገን ሳይኖረው ነው የተወለደው ታዲያ ችግሩ ይህንን መረዳት የሚችል አይምሮ ማግኘት ነው ስለዚህ አንተም መፃፍን እኛም ማንበባችን ህዝቡ መረዳት እንዲሰጠው እግዚያብሄር ይርዳ ፡፡

  ReplyDelete
 21. Thank you.God bless You.

  ReplyDelete
 22. It is an interesting article. May God bless you Dn. Daniel.

  ReplyDelete
 23. መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 24. Dn.dany egzer edmehin yibarkileh beahun seat yetemarewim yaltemarewim sew chigir yihie new

  ReplyDelete
 25. መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 26. በጣም ትክክል ነው ወንድም ዳንኤል እግዚአብሔር አይለይህ፡፡ በሙሉ ከሰውነት በኋላ የተጨመሩት ሁሉ የሰው መጠቀሚያ ቁሳቁሶች ናቸው፡፡ በቁሳቁስ ደግሞ የሰው ልጅ ህይወቱን እስኪጠላ ድረስ መጣላት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ወንድሙን ሳይወድ ቅጥያ (ተገድራ) ሰው ሰራሽ ሀብቶቹን መውደድ እንደሌለበት መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ሌሎች የማህበራዊና የፍልስፍና መጻሕፍት ይነግሩናል፡፡

  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 27. It is interesting, we have ears,eyes but not want to listen and to look at thoroughly and understand deeply.Moreover even those who teach the public in the spritual matter don't have the morale to teach in the way you express.May God give us the patience to listen not to hear!!!

  ReplyDelete
 28. Really nice article ! thank you Dani!

  ReplyDelete
 29. ሰው ደግሞ ክቡር ነው! ሰው ዕዖብ ድንቅ ፍጡር ነው!
  ክቡርነታችንን አውቀን መኖር ሌላውንም ማክበር እንግዲህ የኛ ድርሻ ነው::

  ReplyDelete
 30. እግዚአብሄር ይባርክህ! ጊዜውን ዋጅተህ በአሁኑ ሰዓት ለእኛ አስፈላጊውን እና አንገብጋቢውን ነገር ስለመከርከን እግዚአብሄር አመሰገንኩት ለአንተም ለወንድሜም ረዥም እድሜ ተመኘሁ ... ኢትዮጵያ ያጣችው ፍቅርን ና አውነቱን ለፍርሃት እሚሰበኩትን ነው... አሁንም ሰው ነኝ!!!

  ReplyDelete
 31. መጀመሪያ ሰውነቴን አክብሩት! ሰው ስሆን የተሰጠኝን ሰብአዊ መብት አክብሩት! ሌላው እኔ ስከበር ይከበራል! ማ/ክ

  ReplyDelete
 32. የሰው አእምሮ መልካምነት ሲጎለው ዘረኛና ሀሜት ይበዛበታል። ተጠያቂው ማን እንደሆነ መናገር በከብድም እኛ ግን በዘር በሽታ ተወረናል። ማለቂያ የሌለው ችግር ሳይከተን በትውልዱ ላይ ዘረኝነትን እንዳስተማርነው መልሰን በትምህርት ክትባት ማከም ይኖርብናል። እንደ ዳንኤል ያሉ አስተማሪዎች ብዙ ያስፈልጉናል

  ReplyDelete
 33. Thanks D. Daniel
  yes all from Adam
  we are all from one

  ReplyDelete
 34. አሜን! እውነት ነው - መጀመሪያ ሰው ነኝ! መጨረሻዬንም አምላክ በሰውነት ይጠብቀኝ፡፡

  ReplyDelete
 35. እንደሰው በፈጠረው ነገር መልሶ የሚጠፋ፣ በሠራው ነገር መከራ የሚያይ፣ ባመጣው ነገር የሚሄድ፣ ባስገኘው ነገር የሚታሠር ፍጡር የለም፡፡

  ዲ/ን ግን ምን ይሻለናል?

  አዎ፣ በተለይ አሁን ለኢትዮጵያ 'ከቡድን' በፊት 'ሰው' ነታችን ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ የጋራ ጉዳያችን ነው፡፡

  ReplyDelete
 36. መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 37. Interresting saying as usaul. thank you for all your efferts....

  ReplyDelete
 38. የተረጋገጠ መነሻና መድረሻያለው ሀሳብ ነው፡፡

  ReplyDelete
 39. ለትውልዱ የክፋት ዘርን የሚዘሩ የእግዚአብሄርን መልካም ፍጥረት ሰውን ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል በዘር፤ በጎሳ፤ በብሄር፤ በጎጥ፤ በመንደር መከፋፈል ለግዜው ይሆን እንደሆን እንጂ መቼም አይቀጥልም ፤ በመጀመሪያ እግዜር አንድ አድርጎ ፈጥሮናልና፡፡

  ReplyDelete
 40. zeregna sew haymanot yelewm!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 41. "አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡"

  ReplyDelete
 42. ዲ/ን ዳንኤል፡ የአሁኑ መከራከሪያህ ፋይዳ ብዙም አልታየኝም፡ እንደው ብለዋል ለማለት ካልሆነ በስተቀር፡፡ እርግጥ ነው ሁላችንም ሰው ነን፡፡ ማንም፣ ምንም ከሰውነት በላይ አይደለም፡፡ ግን ከሰውነት በታችም ሌሎች ማንነቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ማንነቶች የሚዳሰሱም ጭምር ናቸው፡፡ እነዚህ ማንነቶችም ክብር ይገባቸዋል፡፡ ለእነዚህ ማንነቶች ክብርና እውቅና ካልሰጠን ሰውነትንም መጉዳት ይመጣል፡፡ በእነዚህ ማንነታቸው ብቻ የተጎዱ፣ ህይወታቸውን ያጡም እንዳሉ በደንብ ታወቃለህ (ጉዳዬ አይደለም ካላልክ በስተቀር)፡፡ ካልዋሻችሁ በስተቀር (ወይም ለፖለቲካ ካልሆነ በስተቀር) ሁላችሁም ቢያንስ ብሄራችሁን ታምናላችሁ (አንተን ጨምሮ ማለት ነው)፡፡
  ስለዚህ እንደኔ እንደኔ እነዚህን ማንነቶች በሰውነት ሸፍነን ለመክዳት ከመሞከር ክብር እና እውቅና መስጠት ይሻላል፡፡ ጠባብ ወዘተ ማለትም አያዋጣም፡፡ ችግሩ ያለው በእነዚህ ማንነቶች መኖር ሳይሆን በእነዚህ ማንነቶች ምክንያት ራሳችንን ከሰው በላይ ሌሎቹን ደግሞ ከሰው በታች አድርጎ ማሰባችን ይመስለናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ራሳችንን "ከሰው" በላይ ...... "ከሰው" በታች Can you see the point?
   ተዘበራረቀብዎት እኮ! ይህንን "በላይ" "በታች" የሚሉትን 'ሰውነት' አስቀድመን እናግኝ እኮ ነው የተባለው፡፡ ገና "ሰው" ሳይባሉ ሌላውን አላገኙትም፡፡

   Delete
  2. Dear Anonymous November 24, 2014 at 5:23 PM
   I did not see a conceptual difference with the writer. What I see is way of explaining it.

   Delete
 43. E/re yetebkehe Ame, Ame, Amen

  ReplyDelete
 44. I love your comment, however I love this government too so it is difficult for me to apply your suggestion. We were poor before this government came to power. At the movement my family are the richest people in Ethiopia so we support this government.

  ReplyDelete
 45. Eski berta ayzo and sew hibretesebin meqeyer yichila and sew demo hager yatefal ena EGZABIHER LIBONAHINAEWUQETIHIN
  EMINETIN YIKENAKENILIN.

  ReplyDelete
 46. dani we need this type issue GOD with you write, i am ready to read

  ReplyDelete
 47. Thanks Dani
  Jesus Christ, our Lord, did not sacrifice himself for ONLY Israeli; even if he is from those people.

  ReplyDelete
 48. It is fine article, but It could have been well articulated. yeteshale articulate madreg techil neber

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please you try!
   Why not pectoral article to help beautify it.
   A R T I C U L A T E !!!! I don't need that.... I got the message fine and clear.

   Delete
 49. it is good explanation thank u

  ReplyDelete
 50. Hi, Dani, you went so far from our world fact. It is not logic this kind of thinking. You have to write that meaningful for us. My name is Aster Tadesse, nationality Ethiopian and region Amhara so it is Logic for me. I strongly objected discrimination but it doesn’t change my name, nationality and my ancestor. We are Ethiopian but we have different name, religion and culture. If you go Oromia you will hear Kebede, Challa, Chaltu. If you go Amhara region Dawit, Henok, Mekdes, if you go Welayta Bula, Fura, Calaca, if you go Tigray region Kill him, take his money, eat human being flush and take his land. So we are an Ethiopian but we have different languche, name, religion and region. God bless Ethiopia except Tigray.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Retarded. you need to work out on your way of thinking

   Delete
  2. I will pray to God that you will not die until you visit Tigray and its people and understand every thing!!! May God keep us all from evil things!!! Amen!!!

   Delete
 51. Tilish tadiya ''Sew kesew yile'yal'' sil min maletu new?

  ReplyDelete
 52. Tadiya Tilish "Sew kesew yile'yal" sil min maletu new?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you think that singers or lyrics writers have a knowledge in everything? If he/she knows, in my opinion, will not sing a song. He/she praise God through hymns.
   Please Dn. Daniel, don't extract songs lyrics to ascertain what you meaning. Such types of quotations may be the cause of these types of comments.
   By the way, your articles and opinions really transform generation. So keep it up, and may God bless all human beings; since, from the beginning we are human!!! (Addis M.)

   Delete
 53. Thank you so much D/N Daniel .. may God bless you
  .. amen

  ReplyDelete
 54. lib Yalew lib yibel

  ReplyDelete
 55. አሜን! እውነት ነው - መጀመሪያ ሰው ነኝ! መጨረሻዬንም አምላክ በሰውነት ይጠብቀኝ፡፡

  ReplyDelete
 56. Sew yemyanebwen meredat tewe enda?

  ReplyDelete
 57. seifemichael zeejereNovember 29, 2014 at 7:36 AM

  መጀመሪያ ሰው ነኝ
  ሁሉም ነገር ቢነሱልኝ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ እውነቱን ሸሽቶ የምን ጥግ ጥጉን መሄድ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ ያለ በሙሉ ሰው ነው፡፡ በጣም ትክክል ነው፡፡ ሁሉም የአዳም ልጅ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ የሞተውም ለዚህ ሰው ለተባለ ፍጡር ነው የትም ቦታ ላለ፡፡ ለጥቁሩም፣ ለቢጫውም ለነጩም ሞተ፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳው ሰዎች በሃጢያታቸው ምክንያት ተለያዩ፡፡ ቋንቋቸው ተለያየ፣ ሃይማኖታቸው ተለያየ፣ አስተሳሰባቸው ተለያየ፡፡ ይህ የቋንቋ መለያየት፣ የሃይማኖት መለያየት፣ የጎሳ መለያየት፣ የሀገር መለያየት ተፈጠረ፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ በስፋት እውቅና ተሰጥቶት ተፃፈ፡፡ ለሀዋርያት ጌታ ቋንቋን ሲገልፅላቸው አንድ ቋንቋ ሳይሆን ብዙ ቋንቋ እንዲያውቁ ገለጠላቸው፡፡ በቋንቋቸው ተማሩና ተረዱ፡፡ በመጀመሪያ ሰው ስለነበሩ እና መዳን ስላለባቸው ለዚያ ክብር ተሰጥቶ ግን በቋንቋቸው ተነገራቸው፡፡ የአካባቢቸው የመጡበት ሁሉ እየተጠቀሰ ተጠራ፡፡ እናንተ ሃጢያተኞች በቋንቋ በአካባቢ የተለያያችሁ ዞር በሉ አልተባሉም፡፡ አሁን መኖር ያለብን በእውነት ውስጥ ነው እንጂ እውነትን አዳፍነን አይደለም፡፡ ይልቅ መነጋገር ያለብን እኔ ኦሮሞም ልሁን አማራ፣ ትግሬም ልሁን ጉራጌ፣ ወላይታም ልሁን ከንባታ፣ ጋምቤላም ልሁን ሺናሻ ..... እንደ ሰው ማሰብ፣ እንደ ሰው መኖር እና ማሰብ ያለብኝ መሆኑን ነው፡፡ እንደ ሰው ማሰብ እና መኖር ማለት ሰብአዊ መሆን ነው፡፡ የትኛውንም ሃይማኖት ላምልክ፣ የትኛውም አይነት ፆታ ልሁን፣ የትኛውንም ሃይማኖት ልከተል፣ ከየትኛውም ብሄር ልሁን ሰብኣዊ መሆን ግድ ነው፡፡ ይህ መሆን ካልቻለ ችግር ነው፡፡ ይህ መሆን ካልቻለ እንደ ሰው ካልሆነ ሰው ወደ አውሬነት ይቀየራል፡፡ አሁን ባለንበት አለም ሰው ምንም ያህል በቋንቋ ቢከፋፈል፣ የተለያየ ሃይማኖትና ብሄር ቢኖርም ሰብኣዊነት አይሎ በመገኘቱ አለም አልጠፋችም፡፡ ይህ የተናደ ቀን ሁሉም ይጠፋል፡፡ በኛም ሀገር በየገጠሩ የተለያየ ቋንቋ ቢናገሩም፣ የተለያየ ሃይማኖት ቢያመልኩም፣ ትምህርታቸው ቢለያይም በጣም ብዙ ሰዎች እንደ ሰው የሚኖሩ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎችን ወደ አውሬነት የምንቀይራቸው ግን አንድ አይነት ቋንቋ ተናገሩ፣ አንድ አይነት ሃይማኖት አምልኩ፣ በአንድ አይነት ባህል ኑሩ የተባሉ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ እንዴት በሰላም እንኑር ብሎ ማሰብ እንጂ አሁን ባለንበት ሁኔታ እና አሁን ባለንባት ሀገር ሰው የሚባል ቋንቋ፣ ሰው የሚባል ሃይማኖት፣ ሰው የሚባል ፆታ፣ ሰው የሚባል ባህል፣ ሰው የሚባል አገር፣ ሰው የሚባል ፕሮፌሽን የለም፡፡ ሰው እንደፈለገው ከሀገር ሀገር መዘዋወር ሳይችል በሀገሩ ተወስኖ አለ፡፡ ሰው የሚባል ፍጡር እና ሰብአዊ የሚባል ህግ ግን አለ፡፡ የዳንኤልን ጽሁፍ ተረድቼው በአድናቆት አነበብኩት ከሚለው ውስጥም ሰውን ወደ ጫካ ወስዶ አራዊት ያለ፣ ‘’God Bless Ethiopia Except Tigrian’’ ያለም አለ፡፡ እባክህ እንደ ሰው ሁንና አስብ እለዋለሁ፡፡ ምናልባት ከዚህ አለም በሞት ስንለይ ሁላችን ወደ ነበርንበት ንፁህ ሰውነት እንመለሳለን፡፡ በአንድ ቋንቋም እንናገራለን፡፡ እስከዚያው ግን በባቢሎን ዘመን በተፈጠረው የቋንቋ መለያየት፣ ከብዙ ሺህ አመት በተከፋፈለው ሀገር፣ እኛን ተጠያቂ ማድረግና እና ለዚህ ዘመን ማስረዳት ፋይዳው ምንድነው፡፡ ይልቅ ከተቻለ እንደ ሐዋርያት የሁሉንም ቋንቋ እንዲገልጥልንና ተነጋግሮ መግባባት እንዲቻል መጸለይ አይሻልም፡፡ ሐዋርያት ተግባብተው የሚፈልጉትን ማስተማር ችለዋልና፡፡ ዳንኤል እውነቱን ተጋፈጥና ፃፍ፡፡ ትምክህቱንም ጠባብነቱንም ተዋጋቸው፡፡ አላስቀምጥ ያሉት እነርሱ ናቸውና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው እንዋጋቸው ብትል ኑሮ! ዳነኤል ብቻውን የሚጋፈጠው ፡ በምን ምክንያት ይሆን?
   ድግስ ቢሆን ኑሮ ፡ ተሰብስቦ ለማላመጥ ፡ የሚደርስብን የለምኮ!

   Delete
 58. ere ebakachehu endi eyetebalen enkan sew mehonachenne teten ene................ becha sew nene egzer yebrkhe!!!

  ReplyDelete
 59. D/N Daniel EGZIABHER beteshle lemagelegle tibebun yigletselh ."አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡"

  ReplyDelete
 60. አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡"

  ReplyDelete
 61. So nice and timely.article you wrote.
  Live long Dani

  ReplyDelete
 62. መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡

  ReplyDelete
 63. አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 64. አሁን አሉኝ የምላቸው ልዩነቶች በሙሉ ቢነሡ፣ ከልዩነቶቹ ሥር እኔ ሰውዬው ብቻዬን ቆሜ እገኛለሁ፡፡ ሰው ነኛ፡፡ መጀመሪያም ሰው ነኝ፤ መጨረሻ ሰው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 65. Dn, Daniel perfect views , God bless Ethiopia !!!. Please Our almighty God regardless of our evil doing and thinking give all of us peace and love. With the help and name of our Mother of Holly Virgin Mary, and in the name of All Holly Fathers and Mothers. The curse of land comes out of human being wrong doing. stop blaming each and let start reconcile our difference respect fist human being not its nation ( race) , world try to be united , we struggle to isolate and disappear by our creation evil doing and transmit for the Generation. We are living now at the expense of our fathers, they paid a lot to have the lovely Ethiopia. Let pray to see the united Ethiopia and Bright time. " God Bless Ethiopia" Ethiopia Ejochuan Wode Egiziabeher Tizeregaleche

  ReplyDelete
 66. ልዩነቱን እንኳን መፍጠር የቻለ - ሰውኮ ነው፡፡ ሌሎቹ ፍጡራን ልዩነታቸው ተፈጠረላቸው እንጂ ልዩነትን አልፈጠሩትም፡፡ ሰው ግን ባሕል፣ ቋንቋ፣ ልማድ፣ ሥርዓት፣ ሀገር፣ አመለካከት፣ አስተሳሰብ የሚባሉ ነገሮችን አምጥቶ የገዛ ልዩነቱን ራሱ የፈጠረ ነው፡፡ ለምን? ቢሉ ሰው ስለሆነ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚከብሩት ሰው ሲከብር ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ህልው የሚሆኑት ሰው ህልው ሲሆን ነው፡፡ አማራ ሆኖ፣ ኦሮሞ ሆኖ፣ ሶማሌ ሆኖ፣ ሕንድና ቻይና ሆኖ፣ እንግሊዝና ጣልያን ሆኖ የተወለደ የለም፡፡ ሁሉም ሰው ሆኖ ነው የተወለደው፡፡ ባሕሉን ለመደው፣ ቋንቋውን ለመደው፣ አለባበሱን ለመደው፣ ሀገሩን ለመደው እንጂ ራቁቱን፣ ቋንቋ ሳያውቅ፣ ወገን ሳይኖረው ነው የተወለደው፡፡10Q a lot dn dani...GOD Bless you

  ReplyDelete
 67. ልዩነቱን እንኳን መፍጠር የቻለ - ሰውኮ ነው፡፡ ሌሎቹ ፍጡራን ልዩነታቸው ተፈጠረላቸው እንጂ ልዩነትን አልፈጠሩትም፡፡ ሰው ግን ባሕል፣ ቋንቋ፣ ልማድ፣ ሥርዓት፣ ሀገር፣ አመለካከት፣ አስተሳሰብ የሚባሉ ነገሮችን አምጥቶ የገዛ ልዩነቱን ራሱ የፈጠረ ነው፡፡ ለምን? ቢሉ ሰው ስለሆነ፡፡

  ReplyDelete
 68. ምርጥ ሰው ያንስሃል ምን ልበልህ ከዚህ ውጭ አሁንም ምርጥ ሰው፡፡

  ReplyDelete
 69. ምርጥ ሰው ያንስሃል ምን ልበልህ ከዚህ ውጭ አሁንም ምርጥ ሰው፡፡

  ReplyDelete
 70. ምርጥ ህዝብ ይኑረን

  ReplyDelete
 71. It is a wonderful and very impressive view.God bless you!!!

  ReplyDelete
 72. ለእሀዴግ እንደዚህ እያልክ ንገርልኝ

  ReplyDelete
 73. "ሰው ግን ሲፈጠር በየተራ ነው፡፡ መጀመሪያ አዳም፣ ከዚያ ሔዋን፣ ከዚያ ቃየል፣ ከዚያ አቤል እያለ ተራ በተራ፡፡"
  ስህተት ነው ልክ ነኝ ካልክ ደግሞ ሃሳብክን ተንትነክ አስረዳኝ

  ReplyDelete