Tuesday, November 18, 2014

‹ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ›

‹ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ› የተሰኘውን መጽሐፍ በተመለከተ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ(እድሜያቸውን ያርዝምና) ከመልካም ሐተታ ጋር አዘጋጅተውታል፡፡ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ማን ጻፈው? ዘርአ ያዕቆብ ማነው? ትውልዱስ የት ነው? ፍልስፍናው ከየት መጣ? እውነት ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ የውጭ ሰው? ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ ለመከራከር በመጽሐፉ ውስጥ ማስረጃዎች አሉን? የሚሉትንና ሌሎች ጥያቄዎችን አንሥተው ይተነትናሉ፡፡ መጽሐፉንም ተርጉመውና አትተው አቅርበውታል፡፡ የሚከተለውን ሊንክ ተጫኑና በነጻ አንብቡት፡፡


32 comments:

 1. I'm always grateful to the work of Professor Getachew Haile. Thank you for linking and presenting it in your blog. Thank you Professor!

  ReplyDelete
 2. Thank you so much ዳንኤል ክብረት, for transferring knowledge, however I am very disappointed because we didn’t buy the book or help the writer. Please give us his contact address or bank account to appreciate him. God bless you ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks for your positive unlike many pismistic folks

   Delete
 3. Dani, this is really confusing and philosophical for Christians like me.
  I do not recommend to place this book in your blog

  ReplyDelete
 4. Danni, I don’t think so you read it. It is not support or helps our Christianity. When I read this kind of book, my conclusion will be God is not exist. Please remove it from your blog and my message for Ethiopian orthodox follower don’t read it but if anybody don’t believe in God, it is ok to read it. God bless you Danni. Lapiso Bocchca from Welayta Sodo.

  ReplyDelete
  Replies
  1. The Anonymous person on November 19. I like your comment. I have a question for you, what is the meaning of your name in Amharic. I never heard this kind of first name and father name.

   Delete
  2. Lapiso = Bereket
   Bocchca = Love
   Shame on you, how you don't know your leader languche?

   Delete
 5. I agree this Anony,
  Please remove this book. The conclusion purely leads to God does not exist.

  ReplyDelete
 6. Thank you Daniel and I am grateful to Dr. Getachew for his noble work. However, the reading is against Christianity and may not be sponsored by this blog. Further what Dr. Getachew said about the origin of the writer is not convincing because. The writer by him self mentioned that he is from Axum. there is no strong justification to say that he was form Gondar.

  ReplyDelete
 7. እኔ እንደተረዳሁት ይህ መጽሀፍ እግዚአብሄር የለም የሚል መደምደሚያ የለውም፡፡ እንደውም የሰው ልጅ የፈጠረውን ለማወቅ ብዙ በመመራመሩ የፈጣሪውን ድንቅ ጥበበኝነት እንዲያስተውል አድርጎታል፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስም ሰዎች የፈጠራቸውን ለማወቅ ሲጥሩ ሀያላን የመሰሏቸውን ፀሀይ፣ ነፋስ ወዘተ… ቢያመልኩም እነሱም ፍጥረታት መሆናቸውን ሲገነዘቡ እንደገና የፈጠራቸውን ለማወቅ ብዙ ተመራምረዋል፡፡ አብርሀምም የፀሀይ አምላክ ተናገረኝ ብሎ ሲለምን እግዚሀብሔር አምላኩ እንደሆነነና ፀሀይንም ሆነ አለማትን ሁሉ የፈጠረ መሆኑ ተገልፆለታል፡፡
  ስለዚህ ዘርያቆብ ፈጣሪውን ለማወቅ ቢመራመር ምንም አይደንቅም፡፡ በመጨረሻም የደረሰበት እግዚአብሄር እጅግ ጥበበኛና ወሰን የሌለው ንፁኅና ቅዱስ አምላክ እንደሆነ ነው፡፡ ነገርግን የሰው ልጅ ለሚያደርገው የተሳሳተ ተግባር የእዚአብሔርን ፍቃድ እንደፈለገው እየተረጎመ የተፈጠረበትን አላማ ትቶ ክፋት በሞላበት ተግባር ምድርን ሲያረክሳት ይታያል፡፡
  አባቶቻችን ግን እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ጥበበኛና አስተዋይ አዕምሮ በበጎ ተግባርና ፈጣሪያቸውን በማመስገን ተጠቅመውበት ኖረዋል፡፡ እኛስ ?

  ReplyDelete
 8. መጽሃፉ እንዳይነበብ አንሳው ማለት ምን ማለት ይሆን?

  በዲክታተር ተረገጦ መኖር የለመደ ትውልድ ፡ ዳሩ ሌላ ምን ሊል ይችላል! አስወግደው ግደለው…ሌላ ነገር በየት አርጎ ጭንቅላታችን ውስጥ ጠብ ይበል።

  ዳኒ በግድ አንብቡ አላለም። የፈለገ ያነባል ፡ ያልፈለገ የማንበብ ገዴታ የለበትም፡፡
  አልኮል የማይጠጣ ሰው ፡ አልኮል ቢቀዳለት ፡ መጠጣት አለበት?
  ግልጽ ለማረግ ይህል ፡ ቀጂው የሀበሻ መንግስት አይደለም።

  ReplyDelete
 9. Hi, Dani as you know that our children read your blog so why you post that express God doesn’t exist. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ may not believe in God but it is not our culture to write this kind of philosophy. Please remove this idea from your blog. Thank you. Belay Kumma from Merkato.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "It is not our culture to write this kind…"

   ሞባይል ስልክ መጠቀም ፥ መኪና መንዳት፡ ፓስታ መብላትና ባዕላችን ይሆኑ?

   Delete
 10. Are you guy’s crazy? I read the all book but it doesn’t say God doesn’t exist. In addition that we have to read all the fact not what we are looking for only. Shame on you all negative feedback writers.

  ReplyDelete
 11. The Pholosopher believed in the existence of God but in advance he researched , questioned and explored.
  He asked "What is real/Truth"? , Who could listen me in my pray? Is there God?
  After proving the existence of G
  od, Zara Yacob questioned whether every thing that is written in the Holy Scripture is true or not.
  So he was in search of the TRUTH as Socrates did.
  So appreciate how he philosophises.

  ReplyDelete
 12. I read the book. There is nothing different from the previous translations; if any, it is the lame claim that "Zera-Yacob is not from Axum but from Gonder". This is a frustrating claim given that Professor Getachew is one of the towering figures in writings related to Ethiopian Orthodox church.
  One, Zera Yacob himself firmly declares on two counts that he is from Axum. Two, it is not the first time professor Getachew read this book. I just cannot understand why he is presently claiming that Zera Yacob is from Gonder. Three, the claims he mentioned are too weak that one is tempted to undermine Professor Getachew's contribution.
  Look at the claims:
  1. "Axum is very far from Denbia and his opponents cannot accuse him many times going there". BUT, how many is MANY? And why not?
  2. "He cannot escape from the king unless he had some insiders". To escape, even people who bought his ideas could help him.
  3." Rulers MOSTLY appoint people in their localities, Welde Yohannes, his accuser was appointed in Dembia; therefore, the accused (Zera Yacob is from Dembia)". You are not serious, are you? Ethiopian history does not show this.

  ReplyDelete
 13. ብዙዎቻችን በዘርዓ ያዕቆብ ላይ ያለንን አናሳ ዕውቀት በመጠቀም፡ ጌታቸው ኃይሌ…የዚህን ፋላስፋ እትብት ከተቀበረበት ቆፍረው… ቢሆንልኛ ባሉት ቦታ ሲቀብሩት በዚህ መፅሃፍ እናያለን፡፡ በጠባብነት ስሪንጅ፡ ዘረኝነት ያልተወጋ ሰው በውኑ በዚህ ዘመን ይገኝ ይሆን?!

  ReplyDelete
 14. ስኮትላንዳዊያን በእንግሊዛውያን፡ ፍልስጥኤማዊያን በእስራኤላዊያን፡ ኩርዶች በኢራቃዊያን መገዛት እንደማይወዱት ሁሉ እኛ አማሮችም በትግሬዎች መገዛትን አንወድም ብለው በይፋ ከተናገሩ ወዲህ ለእሳቸው የነበረኝ ክብር በእጅጉ ቀነሰብኝ፡፡ የማይረጥቡ ዓሳዎች የሚለውን የሪፖርተር ጋዜጣ ርእሰ አንቀፅ (ከ 4 ዓመት በፊት??) ማየት ይቻላል፡፡

  ReplyDelete
 15. ትንሽ ስለ ፈላስፋው ዘርአ ያዕቆብና ስለ ጌታቸው ኃይሌ ተባራሪ ሃሳብ(wide speculation)
  በምን ተአምር ነው ሰውየው እንዲህ ብሎ የደመደመ,”ወርቄና ጠላቱ ወልደ ዮሐንስ ሁለቱም ያንድ አካባቢ (የደምቢያ) ሰዎች መሆን አለባቸው። ወርቄ/ዘርአ ያዕቆብ በጌምድሬ፥ በዛሬው አነጋገር፥ ጎንደሬ ነበር።”

  የታሪክ ሽሚያ፣የማንንት ፍለጋ ትግል ይኖራል ብየ አስባለው፡፡ እንዲህ ዓይነት ዓይን ያወጣ ዝርፊያ ግን ኣልገመትኩም፡፡ ማንስ ሊገምት ይችላል፡፡ ዘርአ ያዕቆብን ኣማራ በማድረግ ኢትዮጵያወነቱን በደንብ ለማረጋገጠ የተደረገ ጥረት ይገርማል፡፡ ከትግራይ ሰለ ሆነ ወያኔ የሆነ ሰለ መሰላቸው እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ለማደረግ መጀመርያ ላይ ኣማራ ማደረግ ኣለብኝ ብሎ ያሰቡ ይመስላሉ፡፡ ወይ ደግሞ ኣከሱም አካባቢ ሰለ ተወለደ ለኤርትራ ቅርብ ነው ብሎ ፈርቶ ከሆኑ በግልፅ ይንገሩን፡፡ የፑሽኪን እጣ እንደይደርሰባቸው ከፈሩም እንስማቸው፡፡ ያባ ጊርጊሰ ዘጋስጫ ማንነት ገደል ኡራኤል እኔ ከኣክሱም እንድያውም ከያሬድ የተውልደ ቤተሰብ ነኝ የሚል እንዳይነሳ ከፈሩም ኣንድ ቀን ኣይቀርም፣ ይሀው ዛሬ አነሳሁት፡፡ ሰለ ገናና መፅሃፍ ክብረ ነግስት ደራሲ ወይም ተረጓሚ ሰለ የትግራይ ሰው ነቡርእድ ይሳቅስ ምን ማለት ይቻላል፡፡ መቸም ሌላ ሊሆን አችልም፡፡ ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ሰውየው በደንብ ያውቃል፡፡ እስጢፋኖስ ራሱ የዓዲ ግራት ኣከባቢ እንደሆነ ገደሉ ላይ ይገኛል፡፡ እስኪ ወደ ፈላስፋው ዘርአ ያዕቆብ እንመለስ፡፡
  ፈላስፋው ዘርአ ያዕቆብ ራሱ እንዲህ ይላል”ጥንተ ትውልዴ ከአክሱም ካህናት ነው። ሆኖም እኔ የተወለድኩት በአክሱም አካባቢ ከአንድ ደኻ ገበሬ፥ በነሐሴ 25 ቀን፥ በያዕቆብ መንግሥት በ3ተኛው ዓመት፥ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ1592 ዓመት ነው። ክርስትና ስነሣ ዘርአ ያዕቆብ ተባልኩ፤ ሰዎች ግን ወርቄ ነው የሚሉኝ።” (ገፅ13-14)፡፡ትምህርት ሲማር ከቆያ በኋላ ወደ ትወለድ ሀገሩ ሲመለስ እንዲህ ይላል “ከዚያ በኋላ ወደ አክሱማዊት ሀገሬ ተመልሼ 4 ዓመት መጻሕፍት አስተማርኩ።(ገፅ 14)”

  ሰውየው እንዲ ቢሉ መግቱ፣ መልካም ነገር ከትግራይ ሊወጣ ይችላልን? በሚል ቃና፡፡ “የትውልድ ሀገሩ አክሱም አካባቢ መሆን የሚያጠራጥረው እዚህ ላይ ይጀምራል። አንደኛ፥ ጥንቁቁ ወርቄ የመንደሩን ስም አልነገረንም፤ ሁለተኛ፥ እሱ የሚያስተምረው አክሱም ከሆነ፥ እንዴት ነው ጠላቶቹ ንጉሡ አፄ ሱስንዮስ (1600-1625) አለበት ደንቀዝ (ደምቢያ) ድረስ ብዙ ጊዜ እየተመላለሱ የውሸት ክስ የሚያቀርቡበት? አክሱምና ደንቀዝ ሰዉ ጧት ማታ የሚመላለስባቸው ጎረቤት ከተሞቶች አይደሉም።”

  ዘርአ ያዕቆብ ያለው ግን “(ሰዎች) ብዙ ጊዜ ከንጉሡ ዘንድ የውሸት ክስ አቀረቡብኝ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አዳነኝ።” በኢትዮጵያዊ ባህል ንጉስ ያለበት ነው ሰው የሚከሰሰው፡፡ ሰውየው ደቂቀ እሰጢፋኖስ በሚል መፅሓፋቸው ደቂቀ እስጢፋኖስ ቡዙ ግዜ ውደ ደበረ ብርሃን ይመላለሱ እንደነበሩ ፅፈዋል፡፡ ታድያ እንዲት ነው ከ1000ኪ.ሜ ርቀት ያለው ደብረብርሀን ሳይርቅ 350ኪ.ሜ ደንብያ የራቀ፡፡ በጎንደር ዘመነ መንግስትም ጎንደር መግቢያ ላይ ትግሬ መጮህያ የሚበል የትግራይ ሰው ክሰ የሚያቀርበተ ሰፈር እንደነበረና አሁኑም በዘህ ስም የሚጠራ ሰፈር እንዳለ ይታወቃል፡፡

  ዘርአ ያዕቆብ የትግራይ ሰው እንደሆነ የሚያራጋግጥልን ደግሞ በገፅ 16 ይገኛል፡፡”አንድ አንድ ጊዜ ወጣ እልና ወደገበያ ወይም ከአምሐራ ሰፈሮች ወደአንዱ ብቅ እል ነበር። ለአምሐራ ሰዎች ምጽዋት የሚለምን ባሕታዊ መነኲሴ እየመሰልኳቸው የምበላውን ይሰጡኛል። የት እንደምኖር ግን ሰዎች አያውቁም።” የትግራይ ሰው ከላሆነ በሰተቀር እንዴት የአመሓራ ሰው ብሎ ፃፈ፡፡

  ReplyDelete
 16. ዘርኣ ያዕቆብ በእግዜብሔር አያምንም ብለው የሚጽፉት ፡ ጽሁፉን አንብበው ከሆነ ይህን የሚሉት ፡ ሊላ ሰው አንብቦ እንዲነግራቸው ያሻል።

  የሱ አስተማመን እንደእኔ ትክክል አይደለም ከሆነ አባባሉ ፥ መልሱን እሱ እራሱ በመጽሃፉ ውስጥ መልሶታልና ፡ የምለው የለኝም።

  ሌላውና አሳዛኙ ፡ ዋናው ሊያወያይ የሚችለው የጸሃፊው መሰረተ ሃሳብ ችላ ተብሎ ፥ የተወለደበት ቦታ ለመነጋገርያ አርስትነት መመረጡ ነው፡፡ ይህም የሚያመለክተው ፡ ጭንቅላታችን ጎልቶ ቢታይም ፡ አይምሮዋችን ግን ፡ ከትውልድ ወድ ትውልድ እየጠበበ መምጣቱን ነው።

  በተርፈ ፡ ዘርኣ ያዕቆብ እንዳለው ፡ ክፉና ደጉን መለየት የሚያስችለውን ፡ ስጦታ እንድናገኝ ፡ ሁላችንም ወደ አምላካችን እንፀልይ!

  ReplyDelete
 17. ዘርአ ያዕቆብ atheist (እግዚአብሔር የለም ብሎ የሚያምን) ኣይደለም፡፡ ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘው እንጂ፡፡ ሶቅራጠስ እንዳለው ‘the unexamined life is not worth living ያልተፈተነ ሕይወት ሕይወት አይደለም፡፡’ ዘርአ ያእቆብ ከተናገራቸው ዋናው ቁም ነገር የሚመስለኝ 'ከመፃሕፍት ይሁን ከሌላ የምናገኛቸው እውቀቶች ሳንመረምር መቀበል የለብንም' የሚል ነው፡፡ እሱ 'የሰውና የእግዚአብሔር' የሚላቸው እውቀቶች ኣሉት፡፡ በሁለቱም መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ ቀላል ነው፡፡ ከእግዚኣብሕር የሚገኝ እውቀት ከሰው ባህርይና ጠባይ ጋር የሚስማማ ሲሆን በተቃራኒው ከሰው የሆነ እውቀት ለሰው ባህርይ የሚመች አይደለም፡፡ በርግጥ የዘርአ ያእቆብን ፍልስፍና በተግባር እናውለው ከተባለ ብዙ ነገሮች ማፍረሳችን ነው፡፡ ከባህላችን እና ስርአታችን ጋር የሚጋጩ ሐሳቦች ኣሉበት፡፡ ስለሆነም እኛ ማድረግ ያለብን ከህሊናችን ጋር የማይጋጭ ለልቦናችን ተስማሚ የሆነ ተግባር መፈፀም ነው፡፡

  ReplyDelete
 18. ዲ/ን ዳንኤል ከክርስቶስ ክብር ይልቅ ለኢትዮጵያ ክብር የበለጠ የምትጨነቅ አስመስሎሃል፡፡ ሰውየውን ኢትዮጵያዊ ላማረግ እንደሆነ ፊት ገፅ ላይ መጣፉን እንድናነብ ስታጋብዘን አሳብቆብሃል፡፡ ዳንኤል ከለጠፈውማ ብዬ እኔም አነበብኩት እንዲህ አይነት መፅሃፍ ብዙም አላነብም ፡፡ ወርቄ ምንም እንኳ የእግዚአብሔርን መኖር ባይጠራጠርም ክርስትናን ግን ይሳደባል፡፡”ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ሥጋዌ የመድኃኒታችንን ነገር ቸል በማለቱ አናመሰግነውም።” እንዳሉ አለቃ ደስታ
  ስለዚህ ሰዎች እንዲጠራጠሩ መሰናክል መሆን ያለብህ አይመስለኝም አንተም ስታስተምረን ሌሎችን እንዳታሳስቱ ተጠንቀቁ ብለሃልና!!

  ReplyDelete
 19. sewyew kenekletu mekabir bewerd yishalew neber

  ReplyDelete
 20. ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ› የተሰኘውን መጽሐፍ በተመለከተ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ(እድሜያቸውን ያርዝምና)........... daniel,aquamihin silegerken tnx................

  ReplyDelete
 21. ይህቺ ናት ፍልስፍና፡፡ ጾም አያስፈልግም፤ ምንኩስና አያስፈልግም፤ ርኩሰት የሚባል ነገር የለም፤ ወዘተ… በዚህ አይነት መናፍቁ ሁሉ ፈላስፋ ነው ማለት ነው፡፡ አዎን ፕሮፌሰሩን ያሰንብትልን፡፡ የወርቄን ማንነት እንድናውቅ ስላደረጉን እናመሰግናለን፡፡ ፈላስፋ ነው ሲባል ሰምተን ኢትዮጵያ ለካስ ፈላስፋ አላት ብለን ነበር፡፡ አዬ ጉድ ፤ እንዲህ አድርጎም ፈላስፋ የለ፡፡

  ReplyDelete
 22. dn. danielm ezih chifn tilacha azeqt wust gebah? betamun yigermal. profesoru kezih befit tiru sirawoch sileseru'na erjina sayengolajachew silalqere( sew siarej wede hitsaninetu sile mimeles) bizum alazenkubachewum, dn daniel Gin germehgnal lezawum lehuletegna gizeh new kezih befit "yelelewun filega" bileh betsafkew tsihuf aleka kidanewoldin ashqentireh aba yohanis keman yemutign sitil aychehalew come on dn. amezazin.

  ReplyDelete
 23. dn. danielm ezih chifn tilacha azeqt wust gebah? betamun yigermal. profesoru kezih befit tiru sirawoch sileseru'na erjina sayengolajachew silalqere( sew siarej wede hitsaninetu sile mimeles) bizum alazenkubachewum, dn daniel Gin germehgnal lezawum lehuletegna gizeh new kezih befit "yelelewun filega" bileh betsafkew tsihuf aleka kidanewoldin ashqentireh aba yohanis keman yemutign sitil aychehalew come on dn. amezazin.

  ReplyDelete
 24. I have read the article and it is such a wonderful philosophical thinking. As per my understanding from the article, it tells you a lot about distortions of facts but doesnot deny existence of God. Some of you commented as he didnot believe in God but from the article it doesnot say. Personally I like it though I dont agree with some of his ideas. But, I dont believe that his work is something that should be abandoned. Rather let us take the good points and criticize the ones that are not. After all he was/is a person and he makes mistakes. But donot multiply the good works by zero and the bad one by infinity. In my opinion this is not wise.

  ReplyDelete
 25. I have read the article and it is such a wonderful philosophical thinking. As per my understanding from the article, it tells you a lot about distortions of facts but doesnot deny existence of God. Some of you commented as he didnot believe in God but from the article it doesnot say. Personally I like it though I dont agree with some of his ideas. But, I dont believe that his work is something that should be abandoned. Rather let us take the good points and criticize the ones that are not. After all he was/is a person and he makes mistakes. But donot multiply the good works by zero and the bad ones by infinity. In my opinion this is not wise.

  ReplyDelete