Tuesday, November 11, 2014

የማያለቅስ ልጅ

ፎቶ - ሐራ ተዋሕዶ

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን ሕግ በተመለከተ አሠረ ሐዋርያትን የተከተለ ሆኖ እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡ አባቶቻችን በቤተ ክርስቲያን ላይ ግለሰባዊ አምባገነንነትን አልፈቀዱም፡፡ ጸሎተ ሃይማኖቱም ‹ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት›› በማት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ዘሐዋርያት መሆንዋን ያመለክታል፡፡ በ50/51 ዓም በኢየሩሳሌም የተሰበሰበችው ሲኖዶስም ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› አለች እንጂ  ‹እኔ› የሚል ግለሰባዊ ድምጽ አልተሰማባትም፡፡

ኢትዮጵያውያን አበው የቅዱስ ሲኖዶስን ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ሌሎችን የቤተ ክርስቲያን የአመራር ሥርዓቶች ከግለሰብ አምባገነንነት ለማውጣት መልካም የሆነ ሥርዓት ሠርተዋል፡፡ ቅዳሴው በአምስት ልዑካን እንዲሆን፣ አጥቢያው በሰበካ ጉባኤ እንዲመራ፣ ገዳማት በምርፋቅ (ጉባኤ አበው) ወይም በማኅበር እንዲመሩ፣ ጵጵስናን አንድ ጳጳስ (ፓትርያርክ እንኳን ቢሆን) ብቻውን እንዳይሰጥ፣ ቢያንስ ሦስት አበው ሊኖሩ እንደሚገባ፤ አንድ አባት ብቻውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንዳይለውጥ፤ አድርገው የሠሩበት አንዱ ምክንያት ግለሰባዊ አምባገነንነትን ለመቋቋም እንዲቻል ነው፡፡


ይህንን ማኅበራዊና ጉባኤያዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን አሠራርና አመራር ለማስወገድ በየዘመናቱ ጥረት ተደርጓል፡፡ የዚህም ምክያቱ ግልጽ ነው፡፡ ግለሰባዊ የሆነ አመራር ለሦስት ነገሮች የተጋለጠ ነውና፡፡ የመጀመሪያው ክህደትንና ኑፋቄን ለማስገባት ይመቻል፡፡ አንዱ ወሳኝ ሌላው ‹ኦሆ በሃሊ› ስለሚሆን እርሱ ትክክል ነው ያለው ትክክል፣ ስሕተት ነው ያለው ደግሞ ስሕተት ይሆናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤያዊት በመሆንዋ አንዳንድ ግለሰቦች በየዘመናቱ ያመጡትን ክህደት በጉባኤ ተመልክታ በጉባኤ ለማውገዝ ጠቅሟታል፡፡ ደገኛ ትምርትና ድርሰት ሲገኝ ደግሞ እንዲሁ በጉባኤ ተመልክታ ለመቀበል ረድቷታል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መጽሐፈ ምሥጢርን ጽፎ በጨረሰ ጊዜ ጉባ ሊቃውንቱ ተመልክተው ‹አማንኬ ዮሐንስ አፈወርቅ ወቄርሎስ አፈ በረከት ተንሥኡ በመዋዕሊነ፡፤ ኢትዮጵያ ተመሰለት በቁስጥንጥንያ፤ ወተአረየታ ላዕለ እስክንድርያ - በእውነት ዮሐንስ አፈወርቅና አፈ በረከት የሆነው ቄርሎስ በዘመናችን ተነሥተዋ፡፡ ኢትዮጵያም ቁስጥንጥንያን መስላለች፤ ከእስክንድርያም ልቃ ከፍ ከፍ ብላለች›› ብለው ምስክርነታቸውን ሰጥተው ነበር፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ለሌሎች አካላት ቁጥጥር ስለሚመች ነው፡፡ ጌታችን አስቀድሞ ኃይለኛውን ማሠር እንዳለው መሪውን የያዘ ቤተ ክርስቲያኒቱን አን ልቡ ለመዘወር ይመቸዋል፡፡
ይኼ ነገር በዘመነ ሱስንዮስ ጊዜ ታይቷል፡፡ ሮማውያን ግብጻዊውን ጳጳስ በሮማዊ ጳጳስ በመተካት ቤተ ክርስቲያኒቱን በሮማዊ ጳጳስ ለማስመራትና ለመቆጣጠር ፈልገው ነበር፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጠባይ ማኅበራዊና ጉባኤያዊ በመሆኑ ጉባኤ ሊቃውንቱ ከግብጹ ጳጳስ ጋር ሆኖ ተቃወማቸው፡፡ ጳጳሱና ሊቃውንቱም እስከ ደም ማፍሰስ ድረስ መሥዋዕት ሆኑ፡፡ ጥቅምት 19 ቀን 1621 ዓም በምዕራብ ጎጃም በምትገኘው ደብረ መዊዕ የተሰበሰቡት የቤተ ክርስቲያን ማኅበርተኞች ለዚህ ማስረጃ ናቸው፡፡ በዚህ የደብረ መዊዕ ጉባኤ እስከ 7000 የሚደርሱ ምእመናን፣ ካህናት፣ መነኮሳትና ሊቃውንት ተሰባስበው ነበር፡፡ የጉባኤው መሪዎችም እነ አባ ተስፋ ኢየሱስ፣ አባ ዘጊዮርጊስ ዘዋሸራ፣ አባ እንጦንዮስ፣ አባ ግርማ ሥሉስ ዘውይት ነበሩ፡፡ የጉባኤው አፈ ጉባኤ ደግሞ አባ ግርማ ሥሉስ ነበሩ፡፡በዚህ ጉባኤ የተገኙት ሁሉ ንጉሡንና አዲሶቹን ሮማውያን የሃይማኖት መሪዎች ተቃውመው እንደ አንድ ልብ መክረው እንደ አንድ ቃል ተናግረው በተዋሕዶ ጸኑ፡፡ የንጉሥ ሱስንዮስም ጦር ጥቅምት 19 ቀን ከብቦ ፈጃቸው፡፡ 
እነዚህ ጽኑአን ጉባኤተኞች ነበሩ በኋላ ዐፄ ሱስንዮስ ሐሳባቸውን እንዲቀይሩና ‹ፋሲል ይንገሥ፣ ሃይማኖት ይመለስ› እንዲሉ ያደረጋቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ መኪና መሪውን የያዘ መኪናውን ወደ ፈለገው ሊወስደው የሚችልባት ቦታ ብትሆን ኖሮ ዘመነ ሱስንዮስን መሻገር ባልቻለች ነበር፡፡ 

ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ዘመን የፈቀደለት ሁሉ ልቡ የወደደውን በቤተ ክርስቲያን ላይ እንዳይጭን ነው፡፡ በተለያዩ ዘመናት የተነሡ መንግሥታት ለራሳቸው የሚመቻቸው መሪ በቤተ ክርስቲያን ላይ ለማስቀመጥ ሞክረው ነበር፡፡ የቤተ ከርስቲያን አሠራር፣ ሕግና ሥርዓት ግን በአንድ ሰው የሚዘወር ባለመሆኑ ገመዱን ከመበጣጠስ ያለፈ ጀነሬተሩን ማቋረጥ አልተቻላቸውም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎችም በጉባኤ እንጂ በአንድ ሰው ኅሊና ብቻ የሚወሰኑ ባለመሆናቸው አስተዳደራዊ ጥቅም ከማግኘትና በደል ከማድረስ ባለፈ አጥንቷን ለመስበር ዐቅም አላገኙም፡፡ 

ይህንን ታሪካዊና ቤተ ክርስቲያናዊ ሐሳብ ጠንቅቆ በመረዳት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ግለሰባዊ አምባገነንነት የሚወስደውን  መንገድ በማረም የቤተ ክርስቲያኒቱ ራስ ክርስቶስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱም የበላይ ወሳኝ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን በሕገ ቤተ ክርስቲያን አጽንቶታል፡፡ 

የሀገራችን ሰው ሲተርት ‹የማያለቅስ ልጅ በእናቱ ጀርባ ይሞታል› ይላል፡፡ ይራበው አይራበው፣ ይታፈን አይታፈን፣ ይመመው አይመመው፣ ይመቸው አይመቸው አይታወቅምና፡፡ ምናልባትም ዝምታው እንደ ጨዋነት ታስቦለት ዘወር ብሎ የሚያየው ላይኖርም ይችላል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በቤተ ክርስቲያን ላይ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይና በሊቃነ ጳጳሳት መብት ላይ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግሉ በተነሡ ማኅበራትና ወጣቶች ላይ፣ በየገጠሩ በተሠማሩና የመከራ ገፈት በሚቀምሱ ካህናትና ምእመናን ላይ የሚደርሰውን በደልና ጫና እየሰሙና እያዩ ዝም ቢሉ በእናታቸው ጀርባ ላይ ሆነው መሞታቸው የማይቀር ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት ለማስከበር ደግሞ አስቀድሞ የቅዱስ ሲኖዶሱ መብት መከበር አለበት፡፡ ያልቆመ አንገት ራስን አይሸከምም እንዲሉ፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አንድ ሆነው የቅዱስ ሲኖዶሱን መብት እንዳስጠበቁትና ቤተ ክርስቲያኒቱንም ከግለሰብ አገዛዝ እንደታደጓት ሁሉ በአጠቃላይ የሰበካ ጉባኤውና በቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤ የቀረቡትን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን አንድ ሆነው ለመፍታት በቀጣይ  መነሣት አለባቸው፡፡    

76 comments:

 1. D/n Daniel, you said what we should think and say. You touched the most critical issues that might follow if the intention of some individuals was real. May God be with you!!!

  ReplyDelete
 2. Our big problem is fear to accept our problems, but we have to accept and try hard work to resolve the problem otherwise how we can be ONE!!! They try to left behind their problem....... with post to another person that is wrong!!!!!!

  ReplyDelete
 3. ከተራ ሰባኪ እስከ ፓትርያርክ ያሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን በየጊዜው ታሪክ እየጣቀስክ መሄሰህ ደስ ያሰኛል፡፡ያንተ ምክር ጎደሎ የሚያደርገው በማኅበራትና በማኅበራዊ ሚዲያው መስመር ዘለል ሆኖ እያቆጠቆጠ ስላለው አባቱን መዝለፍ እንደ መብትና ተቆርቋሪነትን እንደማሳያ የወሰደ ትውልድ ትንፍሽ ለማለት አለመፍቀድህ ነው፡፡
  1--አንተ ጋር ተጣልተው እስክትታረቁ ስትጽፍ ቆይተህ ስትታርቅ ዝም የምትለው የማኅበሩ ችግር ስለተፈታ ነው ወይስ አንተ ጋር አለመግባባት ካልተከሰተ ችግሩ አይሰማህም??
  2--እውነት ቀድሞ እነ ደጀሰላም አሁን ደግሞ ፎቶውን የቀዳህበት ሐራ ተዋሕዶ እከሌ እዚህ ወሰለተ፣አባ እከሌ ወታደር ነበሩ፣አባ እከሌ ኤች አይ ቪ አለባቸው፣እነ እንትና አማሳኝ ናቸው፣የመሳሰሉ ግድፈቶችን እያያችሁ እናንተ ታላላቆቻችን ካላረማችሁ ችግሩ ይፈታልን??
  3--ለመሆኑ የሚያጸውን ከሚያናውጸው ለይተው የማይፅፉ ኅቡዕ መፍቀሬ ማህበረቅዱሳን ብሎጎችን ማን ነው የሚዳኝልን??(የእነ ስም አይጠሬንስ አንዴ ለምደነዋል!)
  4--ከግብፅ አባቶች ብቻ ናቸው እንዴ ልምድ መውሰድ ያለባቸው እኛስ አባትን አክብሮ ችግርን በውስጥ መፍታትን ለምን ከግብፅ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አንማርም??
  5--እውነት በግብፅ እነ አቡነ ሺኖዳን ሲያንኳስስ የኖረ ብሎግ ነበር??
  6--እውነት እኛ አባቶችን እንደ ልጅ ቀርበን እያገዝን ነው ወይስ ህጸጽ ነቃሽ ሆነናል??
  እኔ የዚህ ትውልድ አባልና ከጥብቅ ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦች የተገኘሁ አጥባቂ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ፡፡ነገር ግን ትውልዱ እየሄደበት ያለው መንገድና የእናንተ የታላላቆቻችን አርአያነት አባቶቻችንን በቅንነት በሚያግዝ መልኩ እየሄደ ሆኖ አይሰማኝም፡፡ጦማሮቻችንም ከዐለማዊ ጋዜጣ በባሰ መልኩ ስላሽቆለቆሉ ደስታ አይሰጡኝም፡፡በበኩሌ በዚህ ዙሪያም ብትጽፍ ደስ ይለኛል፡፡በቅ/ሲኖዶስ ልዕልና ጉዳይ ግን መቼውንም አንደራደረምና በዚህ ረገድ ያለውን ሀሳብህን እደግፋለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. correct understanding Mr. Anonymous....correct.

   Delete
  2. be ye betekrstianu yetesegesegew musegna ye enchet shibet shimagle hulu abat ketebale yasazinal bewunu bewunu ante atibaki ortodox kehonk beye debru yalew yebetekrstian zirfia zeregnnet yemiskin kahinat ena diakonat merir enba gid ayilihm.
   lemehonu patriarichu yesinodosin siltan lementek min anesasaw 10 kemaibeltu amasagn zerafiwoch gar betekrstianin lemadakem engi esu kehawaryat yebelete hono betekrstianin liyashashil adelem

   Delete
  3. I accept the main team of your comment. But I do not agree on blaming somebody else to show our view.
   I believe blaming our bishops will end in nothing, or else it will critically affect our church. I will not do anything for current and future generation.

   Delete
  4. ለጥያቄዎቹ መልስ ካላችሁ ወዲህ በሉ፡፡ማኅበሩንና ያፈራቸውን ሰዎች እስክንታዘብ ድረስ በየኅቡዕ ሚዲያው ባሳዛኝ መልኩ እየዘቀጠ የሄደውን ጭፍን አስተያየት የጥቂት ካሕናትን ድክመት በማጮህ መሸፈን አይቻልም፡፡ካሕናቱ አማሳኝ ናቸው ማለት ማኅበሩ ንጹህ ነው ማት አይደለም፡፡የእነሱ አማሳኝ መሆን የተናገሩትን ሁሉ ሀሰት አያደርገውም፡፡ደግሞም ትዝ ይበላችሁ፡፡ለ22 አመታት የካሕናትን ደካማ ጎን ስታዘሩ ኖራችኋል፡፡ግን ትውልዱ ንፁሁን ካሕን ከሙሰኛው ደባልቆ እንዲሸሸው ከማድረግ በቀር በጸያፍ ሂደታችሁ የፈየደቻሁት የለም፡፡
   በተለይ የ22 አመት ብሶታቸውን ካሕናቱ አንድ ቀን ቢናገሩ ራሳችሁን “እኛ እንደ ዮሴፍ፣እንደ አኖሬዎስ፣እንደ ፊልጶስ፣እንደ ክርስቶስ ተከሰስን፤ያውም በሌለንበት” ስትሉ አየናችሁ፡፡ንጽጽሩ ባይጥምም በመርሁ ላይ አልተሳሳታችሁም፡፡
   1--ነገር ግን እናንተስ ሰዎችን የማኅበራችሁን ሥም ያነሱ እለት ጠብቃችሁ ከፍርድና ከቅ/ሲኖዶስ በፊት (የቅ/ሲኖዶስንና የፍ/ቤት ውሳኔን ተከትሎ ቢባሉ ችግር የለብኝም) አማሳኝ፣ተሐድሶ፣ዘረኛ፣ወያኔ….ስትሉ ተከሳሾቹን አቅርባችሁ፤የክሱን ግልባጭ ሰጥታችሁ፣የማስተባበል እድላቸውን ጠብቃችሁ ነበር??
   2--ስም መዘርዘሩ ይቆየንና የእናንተን ሥም ሳይጠሩ በጉያችሁ ተደብቀው ሀብት ስለሚያደልቡት ትንፍሽ ሳትሉ ስለሌሎች ብትናገሩ እንዴት እናምናችኋለን??
   3--ቋሚ የማኅበሩ ተቀጣሪ ሆነው ሳለ በበጎ ፈቃደኞች ሥም ተጠልለው ካሕናቱን “ርግብ ሻጮች” የሚሉትን የማኅበሩ ቋሚ ተቀጣሪዎችስ ምን እንበላቸው??
   4--እውነት በየማኅበራዊ ሚዲያው የሚቀርበው ፈር የለቀቀ ሐተታ በአባቶች በበጎ ጎኑ ይታያል??የመድረኩ ተደራሲዎችስ (የብሎጎቹ አንባብያን/ሰማዕያን) አባቶች ናቸው??
   5--በአባ ሰላማ (በግልጽ የተሐድሶዎች መሆኑ እንደተጠበቀ) እና በሐራ ተዋሕዶ (በገደምዳሜ የማኅበሩ ልሳን መሆኑ እንደተጠበቀ) መሀል ከሥነ-ምግባራዊ ዘገባ አንጻር ይህ ነው የሚባል ልዩነት አለ??
   አይ!! ተውትማ፡፡ልባችሁ ያውቃል!!በቅጡ ሁኑ፡፡ውስጣችሁን አጥሩ፡፡አሁን በተያያዛችሁት “ኅቡዑን ከገሐድ እያጣቀሰ” የሚሄድ ጎዳና ከቀጠላችሁ ራሳችሁን ብቻ ሳይሆን ቅድስት ቤተክርስቲያንንም ትጎዱዋታላችሁ፡፡እንግዲህ “ማኅበሩ የሰዎች ስብስብ ነው” እያላችሁ ሰው ስለሆነ እንተቸው ሲባል ለተቺዎች ስም ለማውጣት የምትሽቀዳደሙ ከሆነ ወይ ለማኅበሩ ጽላት አስቀርጹለት፤ወይም አንድያውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለውን ቃል ማኅበረቅዱሳን ብላችሁ ቀይሩት፡፡
   ወደ መዋቅሩ ግቡና የተጓደለውን በፍቅር መንፈስ አቃኑ ሲባል ከረከሰ የሂሳብ ሥርዓት ጋር አንጓተትም እያላችሁ በእቡይነት መንፈስ በመሸሽ “በተቋም ውስጥ ሌላ ከማዕከላዊ አስተዳደር የራቀ ተቋም እንሁን” ከሆነ ጉዟችሁ ይቅናችሁ፡፡መድረሻችሁን እናያለን፡፡ምን ታረጉ!!የቤተክህነቱን ንዝህላልነት ተጠቅማችሁ ሚዲያውን ተቆጣጠራችሁ፡፡ሚዛን (check and balance) ሲጠፋ ራሳችሁን “አንድ ለእናቱ” እያላችሁ በተዐብዮ ትንጎማለላላችሁ፡፡እረፉ!!!!በቅጥ ሁኑ!!!ይቺን 2 ሚሊኒየም የተሻገረች ቅድስት ቤ/ክ የ2 አሰርተ አመታት እድሜ ባለው ማኅበር ቁመት አትለኩ!!ቅ/ሲኖዶስ እናንተም ሞዴላ ሞዴል እንድትጠቀሙ ወስኗል እሱን ተግባራዊ አድርጉና የሌላውን ጉድፍ ንቀሱ!!
   ስለራሳችሁ፡-ራሳችሁ ከሳሽ፣ራሳችሁ ምስክር፣ራሳችሁ ዳኛ እየሆናችሁ በየጊዜው እዛና እዚህ የተምታታ፣ፖለቲካን ከሃይማኖት የሚያስተሳስር ድኩም አመክንዮ በመደርደር ሚዲያውን ማጥለቅለቃችሁ ከተቋሙና ከተቋሙ መሪዎች ተባብሮ በግልጽነት በመስራት ረገድ ያለባችሁን የአፈንጋጭነት ችግር አይሸፍነውም!!ውስጣችሁን ፈትሹ!!
   መራራውን ክኒን ዋጡት!!

   Delete
  5. በወቅቱ ባልኖርም ዛሬ ስላነበብኩት ነው፡፡ አንተ ከላይ አስተያየት የሰጠኸው ወንድም /እህት አንተ የቤተክህነት ተቆርቋሪ ሆነህ እንደዚህ የምትናገረው አንድ ጥያቄ ብቻ አንስቼ ልለፍ ለመሆኑ የማህበረ ቅዱሳንን ያህል ቤተክህነት ለወንጌል ያደረገው አስተዋጽኦ አሳየን እስኪ፤ በሚዲያ ነው፣ በመጽሐፍ፣ በመጽሄት፣በጋዜጣ ነው፣ በስብከት ነው፤ እንደው አሳፋሪ ቤተክህነት ትውልዳችን ተረክቧል፡፡ ስለዚህ ዘራፍ እያልክ ወሬህ የምታወራው ቤተክህነቱ እኮ ድምጹን የምንሰማው በማህበረ ቅዱሳን በኩል ነው፡፡ እንደው ወንድሜ እዚያ የምትሰራ ከሆነ እባክህ ለመሳደብና ለመንቀፍ አንደበትህ ከማዘዝ፤ ለወንጌል አገልግሎት የሚኖር ህሊናህን ማዘጋጀት ስትጀምር አንተ ለስድብ ያዘጋጀኸውን አንደበትህ መግራት ትጀምራለህ፡፡ አለበለዚያ አስቸጋሪ ነው፡፡ በሐይማኖት ላይ የሚኖር ትውልድ ቤተክርስቲያናችን ከቤተክህነት እስከ ምእመናን ሞልተዋታል አላጣችም፤ እርሷ ያጣቸው ለሐይማኖት የሚኖርላት ነው፡፡ ማስተዋል ይስጥህ፡፡

   Delete
 4. የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዲህ ቢያስቡ ምን አለበት!!! ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያብዛልህ!!!

  ReplyDelete
 5. "... የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎችም በጉባኤ እንጂ በአንድ ሰው ኅሊና ብቻ የሚወሰኑ ባለመሆናቸው አስተዳደራዊ ጥቅም ከማግኘትና በደል ከማድረስ ባለፈ አጥንቷን ለመስበር ዐቅም አላገኙም፡፡ ..."

  ReplyDelete
 6. "... የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎችም በጉባኤ እንጂ በአንድ ሰው ኅሊና ብቻ የሚወሰኑ ባለመሆናቸው አስተዳደራዊ ጥቅም ከማግኘትና በደል ከማድረስ ባለፈ አጥንቷን ለመስበር ዐቅም አላገኙም፡፡ ..."

  ReplyDelete
 7. ዲ/ን ዳኒኤል መልካም ብለሃል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጊዜውን ፈተና እንድትቋቋም እኛ ሁላችንም ከአባቶቻችን ጋር ሆነን የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በየደረጃችን ተግባራዊ ለማድረግና ሕገ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ ለማስጠበቅ በተሰጠን አቅም መትጋት አለብን፡፡ የብጹዓን አባቶቻችን መልካም ገድል አስደስቶኛል፡፡ የሲኖዶሱንም ትንሣኤ እያሳዩን ነው፡፡ዳኒ አንተም ወቅታዊ መረጃዎችን ከማስተላለፍ አትቆጠብ፡፡ እየሠራህ ያለውን መልካም ነገር እንደ ትንሽ አትቁጠረው፡፡ እግዚአብሔር ብርታቱን ያድልህ፡፡

  ReplyDelete
 8. አይ ዳንኤል ማቅን እሺ በጀ ብለው ለተገዙት ዻዻሳትን ነው? አይ አንተ ታዘብኩህ ።

  ReplyDelete
 9. Egizabehare Yestilghne! Amlak Kidusan yirdan Amen.

  ReplyDelete
 10. Tiru hassab yimesilal .....fetta adergeh bedenib betabraraw melikam neber.....FERAH ENDE?

  ReplyDelete
 11. ሁሉም የየራሱን መስቀል ይሸከም!!
  የቅዱስ ሲኖዶሱን ያልተለባበሰና ግልጽ ውይይት ልናደንቅ ይገባል፡፡የየዕለቱ ውሎዎቹ ላላስፈላጊ የሚዲያ ማራገቢያነትና አባቶችን ለከመከፋፈያ የሚውሉበት መንገድ ግን ሊታረም ይገባል፡፡ሁሉም አባቶቻችን ናቸው፡፡ፓትርያርኩ ጠላት፤ጳጳሳት ወዳጆች ብለን ጎራ አንክፈል፡፡የወሬ ፍጥነታችንና ለመፈራረጅ መሯሯጣችን በዚህ ከቀጠለ ሌላ የሲኖዶስ መከፋፈል እንዳናስተናግድ ያሰጋል፡፡ስለዚህ አሉባልታ ባይበዛ ጥሩ ነው፡፡የመጣውን ፓትርያርክ ሁሉ ማሳደድ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዳችንስ እንደ አማኝ ከሚጠበቅብን ውስጥ ምን አደረግን፣ካሕናቱና ጳጳሳቱስ በየአህጉረ ስብከቶቻቸው ምን አይነት አስተዳደር፣ስብከት፣ልማት እየተገበሩ ነው ብለን ማየት አይከፋም፡፡አንድ ፓትርያርክ ብቻ በማብጠልጠል ለውጥ እንደማይመጣ ካለፉት ቅዱሳን ፓትርያርኮቻችን የተማርን ይመስለኛል፡፡ለልማቱም ለውድቀቱም አንድ ሰው ብቻ ተጠያቂ ሊሆን አይገባም፡፡ ሁሉም የየራሱን መስቀል ይሸከም!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ መስቀል መሸከም...እስኪ anonymousun ተወውና በስምህ እውነታውን አፍረጥርጠውና መስቀሉን ተሸከም። በስማቸው የሚያወጡትን ከመተቸት።መቸም ችግሩ የት ላይ እንደሆነ አታጣውም ብየ ነው ሞክሼ Anonymous.

   Delete
 12. ጥሩ ምልከታ!

  ReplyDelete
 13. God Bless You Dn. Daniel. That is the core of the continuing problem "Silence". There is time to be silent and time to react. Now it is time for our fathers that their voice should should be heard by God, and by Mimenana. Unless we hear them, how do we know that they are on the "True Appostolic Mission" . If one person is silent for ever, & not to speak the truth, the logical approach i guess would be there is a silencer mounted on the mouth. But for those who cry daily to be heard by God, & fearless on their stand, let God take your tears to clean our Tewahido Church from what is happening these days.

  ReplyDelete
 14. Time is change and obstacle increase day to day, however we don’t give up. Everybody has obstacle such as our mother, father, sister, brother and preacher so we have to understand each other. As you know that before Abune Matias came to this position, all Weyane supporter nominated by Abune Paulo’s to lead the church. At the movement it is so difficult for Abune Matias to reorganize the leader. In addition that the current government force them to divide the church. As we all know Abune Matias takeover the position by the current government help, so it is difficult to expect for Abune Mathias that oppose the current government. We are the people of our church and our country, to solve all problem we have to fight just like Egypt, Burkina Faso and other countries as well. Please join Gnbot 7 for the best democracy. If you interested to join please email to asfaaa.backar@gmail.com or call ESAT TV. In addition that registers to vote the position party, even if they don’t get the position, we have to express how we hate the current government policy. God bless our country. Legese Alemu from Kolfe.

  ReplyDelete
 15. Ewinet tenagary ayasatan

  ReplyDelete
 16. Fetari ,Endnalekis Yrdane.
  Kalehiwot Yasemalen.

  ReplyDelete
 17. Yes indeed, our father did the right thing for our mother church. if someone want to diktat he needs to go to catholic church or protestant .....

  ReplyDelete
 18. hhhhhhhhhhhhh......meche yehon netsuh wengel mesemaw? meche yehon netsuh wengel manebew? hulum buden abejto yequaselal. Hulum sele hulum yale rehrahe yenageral. Hulum lerasu mimechewen tiksena tarik matakesha yaregal. KEZI BELAY MIASAZEN MEN ALE? Ene ahunes kealem hulu reke bechayen menor feleku. Ye Egziabheren kal endezih madamet alchalkum.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why do not you take ABBA ENTOS as your for front. The place to MENEKUSEI is not hear.
   I think this is social media, not designed for WENGEL only.
   You better try to understand what a social media is.

   Delete
  2. Wow..What a great comment. Tnx....i will not waste my time on social media again. A lot thanks....its a great comment i accept.

   Delete
 19. እርስ በርሳችሁ እንደ ውሻ እየተናከሳችሁ ለማስተማር እና ለመዘመር ሲሆን፣ ለማስመ ለክና ለማሰገድ ሲሆን፣ የአዞ እንባ እያነባችሁ መድረክ ላይ ትወጣላችሁ፡፡ እርስ በርሳ ችሁ ከበርሊን ግንብ የጠነከረ የመለያያ ግንብ እየገነባችሁ ሕዝቡን ግን አንድ ሁኑ፣ ተስ ማሙ፣ ታቻቻሉ እያላችሁ ታስተምራላችሁ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሁሉ ፓስተር፣ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ መነኩሴ፣ባሕታዊ፣ ዑላማ፣አሰጋጅ፣አስመላኪ፣ የእምነት አባት፣እያላት ነው ኢትዮጵያ እንዲህ ስሟ በድህነት እና በጦርነት የሚነሣው? ሙስና እና የዘመድ አሠራር፣ ጠባብ ነት እና ዘረኛነት፣ስግብግብነት እና ማጭበርበር፤ ክፋት እና ምቀኛነት የበዛው ይኼ ሁሉ አገልጋይ እያላት ነው? ለመሆኑ እናንተ ባትኖሩ ኖሮ ይህች ሀገር ከዚህስ የከፋስ ምን ትሆን ነበር?

  ለመሆኑ ተከፋፍላችሁ፣ተከፋፍላችሁ፣ተከፋፍላችሁ መጨረሻችሁ ምንድን ነው? ለመሆኑ አንድ ባትሆኑ እንኳን ለመግባባት፤ ለመገነዛዘብ፤ ቢያንስ ላለመጠላላት፤ ቢያንስ በጠላትነት ላለመተያየት፤ ላለመወጋገዝ፤ ላለመነቃቀፍ አስባችሁበት ታውቃላችሁ? የሀገራ ችሁ ፖለቲከኞች እንኳን የሥነ ምግባር ደንብ ይኑረን ሲሉ እናንተ ለመሆኑ የሥነ ምግባር ደንብ አላችሁ? ሻማ ሲበራ ዋናው ጨለማ ከሻማው ሥር ነው የሚገኘው፡፡ ሌላውን ታበራና ሻማዋ ለራሷ ጨለማ ትሆናለች፡፡ እናንተስ? በየቤተ እምነታችሁ ያለውን ችግር መቼ ፈታችሁ ነው ሕዝብ እናስተምራለን የምትሉት? ለናንተ ሁልጊዜ ጠላታችሁ ሌላ እምነት የሚከተለው ብቻ ነው? ለራሳችሁ ግን ከራሳችሁ በላይ ጠላት የለውም፡፡ ሕዝቡኮ አንዳችሁ ሌላውን ስትተቹ፤ አንዳችሁ በሌላው ስትሳለቁ፤ አንዳችሁ በሌላው ላይ ነጥብ ስታስቆጥሩ፤ አንዳችሁ የሌላውን ኃጢአት ስትዘረዝሩ መስማት ሰልችቶት ነበር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ere Ante/Anchi Maneh/sh? Endih Enante, Yenante Minamin Eyalik/sh Yemitizebarik/ki? Endih Bemalet Yemidan Messeleh/sh? Esti Rasihin/shin Zor Bileh/sh Temeleket/chi. Fetari Endehon Hulachininim Endeyeserachin Be-Ekul Yiferdenal Enji Ante, Anchi, Enante Bilo Ayileyayen.

   Delete
  2. እንካን ወዳጅን ጠላትን መውደድ የሌለበት ክርክር በተአምር ለነፍስ አይጠቅምም፡፡ እምነት የጠብ ምክንያት የሚሆነው ደሃ ህዝብና ሀገር ላይ ብቻ ነው!!!!!

   Delete
  3. Tsehufu eko Dn. Daniel kibret Ketsafew semachehu besemay yelem kemilew lay copy paste yarekut new...degme post kemareg beker berase yechemerkut andach kal yelem......enen lemn teweksalachu. Wekesawen lewanaw Tsehafi endianebew forward aregewalew.

   Delete
  4. Gen after all le comentu amesegnalew....tekebyalew. kenem mistekakel neger besh ale.

   Delete
 20. ዲያቆን እግዚአብሄር ይስጥህ ፣ በጣም ጥሩ ጹሑፍ ነው። አባቶቻችንም ጤናውን ና እድሜን ይስጣቸው ፣ በእውነት አኮሩን፣ ተሐድሶ አባ ማትያስን ተጠቅሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሊመታ ነበር፣ አባቶቻችን የተሐድሶ መሪ የሆነውን የሰይጣንን ራስ ሰባበሩት፣ በእውነት አምላከ ቅዱሳን እንዳልተወን አሁን ተረጋገጠ ። በሚቀጥለው ጉባኤ ደግሞ ሌላው ችግር እንደሚቀረፍ ምንም ጥርጥር የለኝም ። ተመስገን።።።።።።

  ReplyDelete
 21. Thanks dany it is a very good news.

  ReplyDelete
 22. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 23. a very nice view, as usual!!!

  ReplyDelete
 24. እውነት ነው… እግዚአብሔር አምላክ ከደቂቅ እሰከ ትልቅ ልብ ይስጠን… የቤተክርስቲያን እና የሃይማኖት ጉዳይ የሁሉም ነው… እርሱ ፍቅር ነውና ፍቅር ይስጠን… በፍቅር ልብ እንፀል!

  ReplyDelete
 25. የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አንድ ሆነው የቅዱስ ሲኖዶሱን መብት እንዳስጠበቁትና ቤተ ክርስቲያኒቱንም ከግለሰብ አገዛዝ እንደታደጓት ሁሉ በአጠቃላይ የሰበካ ጉባኤውና በቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤ የቀረቡትን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን አንድ ሆነው ለመፍታት በቀጣይ መነሣት አለባቸው፡፡

  ReplyDelete
 26. የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አንድ ሆነው የቅዱስ ሲኖዶሱን መብት እንዳስጠበቁትና ቤተ ክርስቲያኒቱንም ከግለሰብ አገዛዝ እንደታደጓት ሁሉ በአጠቃላይ የሰበካ ጉባኤውና በቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤ የቀረቡትን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን አንድ ሆነው ለመፍታት በቀጣይ መነሣት አለባቸው፡፡

  ReplyDelete
 27. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን አባቶቻችን እናንተን ያቆይልን አሁንም የቤተክርስቲያን ጠላት የሆኑትን አንድ ሁናችሁ እያወገዛችሁ ለዩልን፡እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡

  ReplyDelete
 28. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን አባቶቻችን እናንተን ያቆይልን አሁንም የቤተክርስቲያን ጠላት የሆኑትን አንድ ሁናችሁ እያወገዛችሁ ለዩልን፡እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡

  ReplyDelete
 29. well said Dn. Daniel. God bless you!!!

  ReplyDelete
 30. Our Fathers should keep themselves keen and strong for the future. Satan will re-appear in a more organized way.
  Thanks Dan: we should give credit where credit is Due.
  Abatochachin Bertulin

  ReplyDelete
 31. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን አባቶቻችን እናንተን ያቆይልን አሁንም የቤተክርስቲያን ጠላት የሆኑትን አንድ ሁናችሁ እያወገዛችሁ ለዩልን፡እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡

  ReplyDelete
 32. ቤተ ክርስቲያን እንደ መኪና መሪውን የያዘ መኪናውን ወደ ፈለገው ሊወስደው የሚችልባት ቦታ ብትሆን ኖሮ ዘመነ ሱስንዮስን መሻገር ባልቻለች ነበር፡nice

  ReplyDelete
 33. የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አንድ ሆነው የቅዱስ ሲኖዶሱን መብት እንዳስጠበቁትና ቤተ ክርስቲያኒቱንም ከግለሰብ አገዛዝ እንደታደጓት ሁሉ በአጠቃላይ የሰበካ ጉባኤውና በቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤ የቀረቡትን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን አንድ ሆነው ለመፍታት በቀጣይ መነሣት አለባቸው፡፡

  ReplyDelete
 34. የማያለቅስ ልጅ ችላ የሚባለውን ያህል በየሰበብ አስባቡ የሚያለቅስ ልጅም ልማዱ ነው ተብሎ በቸልተኝነት ሊጎዳ ስለሚችል ለቅሷችንም በቅጡ ቢሆን፡፡ልንጠፋ ነው፣ልንሰቀል ነው፣ከአካላዊነት ወደ መናፍስትነት ልንቀየር ነው የመሳሰሉ የጥቅምትና የግንቦት ጋዜጣና ብሎግር ማድመቂያ ባንተ ቋንቋ አስለቃሽ የሆኑ ቋንቋዎች ለከት አጡሳ፡፡እርጋታ፣ማስረጃ፣አስተዋይነት፣ሚዛናዊነት፣ትህትና፣እውቀት ጎድሏል፡፡what a shameful kind of lobby from both extremes,especially MK(including d/n daniel) & gv't-Affiliated priests!! i'm irritating of bi-annual holy synod meetings b/c of ur unfettered propaganda.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁንማ ምን ለቅሶ አለ። አማሳኞች ''በረሃብ ልናልቅ ነው እያሉ'' ያልቅሱ እንጅ።

   Delete
 35. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 36. Dear Daniel & readers

  First and for most I’m very surprised to see what has happening within the Ethiopian Orthodox Church at the moment.

  I believe there are few questions we need to ask ourselves including: Is the Holy Synod operating effectively? Do we have the right management to run one of the biggest and oldest organisations in Ethiopia? Is the Church free from political interference and political influence? Do we have the right vision such as what the Church looks like in 50 years? Do we have the right human resource (man power) to lead the church over the next decades? Do we work hard to equip the young generation with appropriate training to tackle current & future challenges?

  One of the challenges seems to me we allowed bishops to manage the daily administration of the Church. They are trained to preach and baptise their flock and that should be their primary objectives and leave the daily administration of EOC for professional people.

  I believe the Synod should focus on leading the Church to reach out the community, to preach the word of God and look after families who needs the church’s support.

  Before doing this the Synod members ask themselves how many of them accumulating private wealth for themselves. Similarly I ask the hard question: before asking MK’s money how many bishops and monks, who supposedly rejected this world to follow the way of the cross, built luxurious villas in Addis Ababa? How many bishops live outside bishops residence and why? The Church provide them free accommodation, food, free car and drivers and why they prefer to stay outside the compound and can they justify this act?

  My suggestion to the “Holy Synod” is do your homework before asking others???

  Boru, Australia


  ReplyDelete
  Replies
  1. Shame on you!!! Shame! Shame! Shame! Who you are you told us to run the church in your way. As you know that Daniel is crazy, if you follow him all time, you will be crazy. He knows how to write and lead but he doesn't know team work. I used to work with him more than five years. He never take other people idea. Leading is not easy as we think. Please wash your mind with areal to become perfect. God bless you.

   Delete
 37. ለጥርሳቸው ንክሻ አሳልፎ ያልሰጠን፣ የማይተኛ ፣ የማያንቀላፋ እረኛችን እግዚአብሔር ይመስገን !!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አልሰሜን ግባ በለው!

   አላምጠው ተፉንኮ!

   Delete
 38. ትክክል ብለሃል ጃል፡፡የካቶሊክ ጳጳሳት የስብሰባ ውጤት በጥብቅ ምስጢር ተካሂዶ ነው ይፋ የሚሆነው፡፡የካቶሊኮቹ ይቅርና የኢህአዴግ ስብሰባ እንኳ መግለጫ እስኪሰጥበት ተጠብቆ በሥርዓቱ መረጃ ይወጣል እንጅ በዚህም በዛም እየሾለከ ላላግባብ ጫና አይጋለጥም፡፡
  ከደጀሰላም ብሎግ ምስረታ ወዲህ ያለው የእኛ ሲኖዶስ ስብሰባ ግን “ሲኖዶስን በብሎግ እናስመለክታለን” በሚሉ ኃይሎች ጫና ውስጥ ወድቋል፡፡የምዕመናን ኑዛዜ ተቀብለው ንስሐ ይሰጣሉ የሚባሉ ጳጳሳት በዚህ በትንሹ ነገር መታመን አቅቷቸው የሲኖዶሱን ስብሰባ ሜሴጅ እየተላላኩ የቤ/ክ ክበር ማስጠበቅ አለመቻላቸው ያሳዝናል፡፡ብሎጎቹ ቆመጥ የላቸውም፤ዳኛ አይደሉም፡፡ነገር ግን ከፍ/ቤት በላይ፣ከሲኖዶሱና ከጳጳሳቱም በላይ ይፈራሉ፡፡ታዲያ ዳንኤል ክብረትስ ቢሆን ሰው አይደለ እንዴ በምን አቅሙ ተቋቋሞ ነው እነሱን የሚጋፈጥ፡፡ብሎጎቹን ያመጣቸው እስኪመልሳቸው ዝም ብሎ መመልከት ነው፡፡የቤ/ክ ቋሚ ተቀጣሪ ሰራተኞችማ ስለእነሱ ከተናገርን አቅጣጫ የሌለው መርከብ ሆነን ጎዳንችን ስለሚጠፋ ዝም ነው የምንል፡፡እነሱ ማንንም የማብጠልጠል መብት አላቸው፡፡መረጃ አምጡ አይባልም፡፡ባይሆን እንደፈለጉ ሲናገሩ ቃለሕይወት ያሰማልን ነው የሚባለው፡፡

  ReplyDelete
 39. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት 33ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ባለ 21 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ፡፡ጉባኤው ካሳለፋቸው ነጥቦች ውስጥ የሚከተለው ይገኛል፡፡
  ፫.፲፱.የማኅበራትን እንቅስቃሴ በተመለከተ
  “ከቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ አግኝተውም ሆነ ፈቃድ ሳይኖራቸው በተለያየ መልኩ ተደራጅተው በማገልገል ላይ ያሉ ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት የራሳቸው ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ችግሮች እየተፈጠሩና የቤተ ክርስቲያን ሰላም እየደፈረሰ ይገኛል፤ የዚህ ዐይነት ችግሮችን ለማስቀረት እንዲቻል ቅዱስ ሲኖዶስ በጥልቀት መርምሮ አስፈላጊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉባኤው እየጠየቀ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነውን ውሳኔ በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ውስጥ ለማስፈጸም ሁላችንም ዝግጁዎች መሆናችንን በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናረጋግጣለን፡፡”
  ‹‹ከቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ አግኝተውም ሆነ›› የሚለው አገላለጽ ማንን ለማመልከት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ባለፈቃዶችም አትዝናኑ፡፡የጉባኤው የአቋም መግለጫ ይከበር፡፡
  የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔም ዳግም እንዳይዘነጋ፡፡ማኅበሩ በታዘዘው መሰረት “ሞዴላሞዴል” ይጠቀም:: የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ በሌሎች ላይ ሲሆን ማወደስ በራስ ላይ ሲመጣ ማንኳሰስ አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 40. አባቶቻችን ያልካቸው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርን ሁለተናዊ ጥቅም ለማስከበር እና በሁሉም መስክ አገሪቷን ለማውደም የበግ ለምድ የለበሱትን ተኩላዎች መሆኑን ህሊናህ እያወቀ ለሆድህ መሆኑ ሌላ ት ዝብት ነው።ችግሩን ከመሰረቱ የማይፈቱ፥በሁለት ቢለዋ የሚበሉ ፥ለድሀው የማይቆረቆሩ፥ነውረኞች ናቸው።እውነትን አያውቋትም።የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ስልጣን የሚለቅ ከሆነ ቆባችንን ጥለን የለመድነው ጫካ እንገባለን ብለው በ አደባባይ የሚናገሩ የኃይማኖት አባት ለመባል ብቃት የላቸውም።በምርጫ ዘጠና ሰባት የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ሲገድለን በግፍ መገደላችንን የደገፉ የኃይማኖት አባት ለመባል ብቃት የላቸውም።ዳሩ ጠብ መንጃው በእጃቸው ስለሆነ ይቀልዱ።ይጨማለቁ።አንተም የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርን ታሪክ አሰማምር።እውነቱ ሲወጣ ተገድጄ ነው እንዳትል።

  ReplyDelete
 41. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ እውቀቱን ያብዛልህ ተባረክ ብሩክ ሁን፧

  ReplyDelete
 42. Ya Dn you are all ways to the safe side especially when it comes to EPRDF related matters. This has been your general trend all along. You work for them in a very diplomatic but hidden way. I do not deny what our holy fathers did and they deserve to be recognized. However the general tendency that we are seeing is being fan not religious. I see many people care about MK than the Holy church. Some argue that being critical on MK is being Tehadso. It is a very hasty kind of generalization and a systematic way of covering weakness. It is also obvious that Tehadesso is a real challenge that we all Ye Tewahedo lijoch need to fight against. However to your surprise people are using this card to disgrace honest and true christian followers of the church. MK is seen loosing its power to control its members somehow. This has been an issue for so long. Individual MK members are creating so much confusion and challenge to the true believers of the church in many parts of the world. One good example is you yourself Dn. Remember what you said in your time of disagreement, trying to shoot them down. I also know that you said sorry later on though it wasn't in a true christian sense. They also accepted you because they do not have another option because of who you are. Another example for me is the recent incident in our church in Oslo. Our church is in turmoil because of few members of MK and their families. I mean accepting once wrong doing leads to learn and grow stronger in our EOTC faith. I believe with all the MK hard work including yours Dn when it comes to the religious matter and especially in preaching the bible. However; I do believe MK needs to work on this matter and serve our church and grow stronger.
  I am a strong supporter of MK since my childhood and I will continue to do so no matter what because I saw our Holy church benefiting from MK in many ways.
  Thanks

  ReplyDelete
 43. ለጥርሳቸው ንክሻ አሳልፎ ያልሰጠን፣ የማይተኛ ፣ የማያንቀላፋ እረኛችን እግዚአብሔር ስላለ አታስብ

  ReplyDelete
 44. MK is not "never cry" boy.
  MK is" ever cry" boy

  ReplyDelete
 45. I feel you are my God. Whatever I wrote you posted on your blog. I know God gave us full democracy to believe him or not. To pray him or not. You did the same thing what God did. I wish to have this kind of democracy in Ethiopia. I work for the Ethiopia government but I never asked question because they think I am not their supporter. I fell I am animal because there is no freedom when you work the current government. Dani, you are my God you can change this country if you participate in politics. God bless you my God. Please don’t take me wrong when I said you are my God. I just compare your democracy and God democracy.

  ReplyDelete
 46. ende hara tewahdo ena ye mk sebakyan kahn misadeb sew alhonem. never. kegebi gubae sera asfetsami jemro yemahberu agelgay neberku. ahun hulum ke haymanot sera wede poletics tekeyere....kahun behuala NEVER. ABRE ALSERAM.

  ReplyDelete
 47. If I am wrong please correct me. I believe our life is setup by God. We created by God and he setup our life. Before someone born God know about that person future. I mean the person may go heaven or Siol, so that person can’t change anything. At the movement our church runs by the current government that God setup before we born. We are the poorest country in the world and USA is the richest country in the world. Everything setup by God so if something bad or good that is God setup so we can’t change anything. I am Cristian because my family is Christian. My friend is Muslim because his family is Muslim so what can we do about religion. we follow from our family that everything setup by God. If everything setup by God, why we blame the leader of our church or Ethiopian government. In conclusion if you want change please pray to God then he will change the direction so don’t west your or other people time to bring change. I said to God” please give us best leader that care for his people”.

  ReplyDelete
 48. ያለፈው ትውልድማ በየመስኩ ድንቅ ትሪክ ሰርቶ አልፏል፡፡ የዛሬዎቹ ፡ አባት የለ ልጅ የለ፡ ወጥ በውጥ ሆነናል፡፡ ዛሬ መመሪያው ፥ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" ይመስላል፡፡

  ReplyDelete
 49. sile mahiberat bitsif tebilo tetkiso ayehu gin ante lemn atisifm? dani tnx

  ReplyDelete
 50. ለጥርሳቸው ንክሻ አሳልፎ ያልሰጠን፣ የማይተኛ ፣ የማያንቀላፋ እረኛችን እግዚአብሔር ይመስገን

  ReplyDelete
 51. ደጅ ከተኙት ሰዎች መሃል ፡ ድምጽ የቀሰቀሰው ሰው ተነስቶ ፡ አጠገቡ ያለውን
  "የምን ድምጽ ነው የምሰማው ?" ቢለው

  ተጠያቂው " ተው ዝም በል ፡ ጅብ የኔን እግር እየበላ ነው" አለው አሉ፡፡
  ዛሬ ብዙዎቻችን መልሳችን ይህ ነው፡፡
  " የእግዜብሔር ፈቃድ ሰለሆን ነው" የምንልም አንጠፋ፡፡ ይህን መልስ የሚቃወም ፡ ከፈጣሪ ሊጋጭ ፡ ይችላልን መልስ የለውም፡፡

  ReplyDelete
 52. እንካን ወዳጅን ጠላትን መውደድ የሌለበት ክርክር በተአምር ለነፍስ አይጠቅምም፡፡ እምነት የጠብ ምክንያት የሚሆነው ደሃ ህዝብና ሀገር ላይ ብቻ ነው!!!!!

  ReplyDelete