click here for pdf
ከለም ሆቴል ወደ ካዛንቺስ የሚሄድ
ታክሲ ውስጥ ገብቼ ከኋላ ወንበር ተቀመጥኩ፡፡ ከጎኔ ሁለት በዕድሜ ወደ ሠላሳዎቹ አጋማሽ የሚሆኑ ሴቶች ተቀምጠዋል፡፡ ታክሲው ሲንቀሳቀስ
‹‹ለመሆኑ ምን ዓይነት ነገር ቢገጥምሽ ነው ለመንገር ያስቸግራል የምትይኝ›› አለቻት መካከል ያለቺዋ ወደ መስኮቱ ጥግ የተቀመጠችውን፡፡
እንደ ታክሲ መቼም ማኅበራዊ ኑሯችንን የምናውቅበት ምቹ መድረክ የለምና ጆሮዬን ጣል አደረግኩ፡፡ ‹‹ባክሽ ችግሩን ከመሸከሙ ችግሩን
መግለጡ ይከብዳል›› አለች ያችኛዋ፡፡
አንድ ሊቅ ‹‹እጅግ አስቸጋሪው
ችግር ሊገልጡት የሚያስቸግር ችግር ነው›› ያሉትን አስታወሰኝ፡፡ ምን እንደገጠማት ባላውቅም አንዳንድ ችግር ግን የሕመሙን ያህል
መግለጫ ነገር አይገኝለትም፡፡ ሲናሩት ተራ ወይም ቀላል ይሆናል፡፡ ሰሚውም ‹‹አሁን ይኼ ችግር ነው?›› ይላል፡፡ ተናጋሪውም ንግግሩ
ቀላል ስለሚሆንበት ከችግሩ በላይ ያመዋል፡፡