Wednesday, October 8, 2014

አርሴማ


ዐጽሟ ያረፈበት አርመን የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን
ቅድስት አርሴማ በ290 ዓም በአርመን በሰማዕትነት ያረፈች ወጣት ክርስቲያን ሰማዕት ናት፡፡ ትውልዷ ሮም ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበለችው አርመን ነው፡፡ እኛ አርሴማ ስንላት እነርሱ Saint Hripsime ይሏታል፡፡ ታሪኳን የፈለገ ሰው በዚህ ስሟ ጎጉል ላይ ቢፈልግ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መስከረም 29 ቀን ወይም ኦክቶበር 9 ሰማዕትነት የተቀበለችበትን ቀን ያከብራሉ፡፡ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን በስሟ የተሠራውም አርመን ኤችሚዚን ውስጥ በ395 ዓም ነው፡፡ ይህ የአርሴማ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ሳይፈርሱ ከኖሩት እጅግ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ነው፡፡


የዚህች ወጣት ሰማዕት ታሪክ በስንክሳር በመስከረም 29 ቀን ተጽፏል፡፡ በሀገራችን ገድላቸው ከተተረጎመላቸው የውጭ ቅዱሳን አንዷ አርሴማ ናት፡፡ የዚህ ምክንያቱ የታወቀ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ አርመን ከአርመንም ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱና የሚመጡ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ በ10ኛው መክዘ አካባቢ በአርመን የደረሰውን የፋርሶችን ወረራ በመሸሽ አያሌ አርመናውያን ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውንና ዛሬ ሐይቅ እስጢፋኖስ በተባለው ቦታ መሥፈራቸውን የአርመን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በአርመንኛ ‹ሐይቅ› ማለትም ገዳም ማለት ነው ይላሉ፡፡
                        በአርመን ቤተ ክርስቲያንዋ የሚታወቀው ሥዕል ይህ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በ13ኛው መክዘ ኢትዮጵያዊው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ መጀመሪያ ወደ ግብጽ (1330-32 ዓም)፣ ከዚያም ወደ እሥራኤል በመጨረሻም ወደ አርመን ተጉዘው በዚያ ለአሥራ አራት ዓመታት ከቆዩ በኋላ በ1352 ዓም ዐርፈዋል፡፡ ከእርሳቸው ዕረፍት በኋላም ደቀ መዝሙሮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ እነዚህ የተመለሱ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ደቀ መዛሙርት ብዙ የውጭ ሀገር ቅዱሳት መጻሕፍትን ይዘው በመምጣትና ወደ ግእዝ በመበተርጎም ታላቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ (ዝርዝር ታሪኩን የፈለገ ‹አራቱ ኃያላንን› መመልከት ነው)፡፡ በጎንደር መንግሥት ጊዜም አቡነ ዮሐንስ የተባሉ ቆሞስ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስን ተረፈ ዐጽም ይዘው በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን መጥተው ነበር፡፡ እነዚህ ከወዲህና ከወዲያ የነበሩ ግንኙነቶች ቅድስት አርሴማን በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንድትታወቅ አድርጓታል፡፡ ገድሏም ወደ ግእዝ ሊተረጎም ችሏል፡፡
በአሁኑ ዘመን አርሴማ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዘንድ ይበልጥ እየታወቀችና እየተከበረች መጥታለች፡፡ ወጣቱ የወጣቷን ሰማዕት አርአያ ማንሣቱ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ክርስቶስ ስትል የከፈለችውን ሰማዕትነት፣ ድንግልናን በብጽዐት ለመጠበቅ ስትል የተቀበለችውን መከራ፣ ወጣትነቷ ሳያጓጓት ለእምነት የከፈለችውን ዋጋ፣ በሕይወቷ ሳለች ከሠራችውም በላይ በሰማዕትነቷ ያፈራችውን ፍሬ በማሰብና ከእርሱም በመማር ዘመኑን ከመዋጀት ይልቅ የሰማዕቷን ዝክር ከትዳርና ከፍቅረኞች፣ ከጥራጥሬና ከታሪኳ ጋር ከማይሄዱ ነገሮች ጋር ማገናኘቱ መልካም አይደለም፡፡
                                                    ቅድስት ባርባር
ሌላው ቀርቶ በአሁኑ ጊዜ የቅድስት አርሴማ ሥዕል ነው ተብሎ በስፋት የሚታወቀው ሥዕል በኦርቶዶክስ ሥነ ሥዕል (አይኮኖግራፊ) የቅድስት ባርባራ ሥዕል ነው፡፡ አርመን ኤችሚዚን በሚገኘው መቃብሯ ላይ የሚገኘው ሥዕሏ ከታች የተገለጠው ነው፡፡ ጣና ደሴት ውስጥ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያንዋም ኢትዮጵያዊውን ሥዕል ማግኘት ይቻላል፡፡
                በመቃብሯ ላይ የሚገኘው ሥዕል
በአጠቃላይ ቅድስት አርሴማ ታሪኳ በመላው ዓለም ክርስቲያኖች ዘንድ የታወቀ፣ ከንጽሕናና ቅድስና ጋር በእጅጉ የተገናኘ፣ ለወጣት ሰማዕታት ታላቅ አርአያ የሚሆን፣ ንጽሕናን ለመጠበቅ ፈታኝ በሆነበት በዚህ ዘመን ምሳሌ የሚሆን፣ ቀደምት እናቶቻችንና እኅቶቻችን ስለ ክርስቶስ ሲሉ የከፈሉትን ዋጋ የሚያሳይ በመሆኑ በዓሏም በዚህ መንፈስ መከበር ይኖርበታል፡፡ 
ሜልበርን፣ አውስትራልያ

38 comments:

 1. kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear, dainel Kibret a nice and timely article. As you have mentioned it above true Icon of saint Arsema in Ethiopian this modern age is not very accessible to the general public.
   In addition other saint's Icons have been mistakenly taken as Arsema. It is not only Saint Barbara's Icon but also Saint Kyriaki's, Saint Catherine Alexandria's and Saint Lucia are called as Saint Arsema Icon.
   However, the scarcity of Information dose not mean that Ethiopian Iconographers did not know or paint this holy martyr because;
   In addition to the example you mentioned I have Seen Two Icons Of Saint Arsema painted by Ethiopian Iconographers.

   The First is in a manuscript about lives of martyrs (Gedle Semaetat) Ethiopian Monastery dedicated to saint Jhon (Yohannes) near Mekelle, Tigray. This books is suppose to weigh abut 36kg. I don't have the Icon though found on this manuscript b/c my camera batteries were dead at that moment but i can show you some Icons found there.

   Link to the image of the book:- https://drive.google.com/file/d/0B5_9e_DZJEwOZ3F1UmpVamhJZzQ/edit?usp=sharing and
   https://drive.google.com/file/d/0B5_9e_DZJEwONDBHQU9xaU9HRFk/edit?usp=sharing

   The Second Icon that I found about saint Arsema in Ethiopia is a diptych panel painting by the First Gondarien Style (around 17th Century) the place of origin and current place is unknown.

   Link to the image of the panel:- https://drive.google.com/file/d/0B5_9e_DZJEwOd2I3ZkpKZVJTbjg/edit?usp=sharing

   I hope you and every one on this forum found this info helpful. If GOD willing I am in the process of creating website about Ethiopian Orthodox Icons and share Holy Icons, articles and other materials with fellow Orthodox brothers and Sisters.
   May GOD bless your Service.
   if you want to contact me about EOTC Icons here is my email
   ethioicons@gmail.com or shihaile@gmail.com.

   Delete
 2. በእውነት ዲ/ን ዳንኤል ሁሌም እላላሁ ረጅም እድሜ ለአንተና ለቤተሰቦችህ!!!
  እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ያነሳኸው በአሁኑ ወቅት የወጣቷን ሰማዕት ንጽህና ፣ቅድስና ፣ ተጋድሎ እያሰብን ከመባረክ ይልቅ ለስጋ ፍላጎታችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አርሴማ እከሌን አግቢ አለችኝ እከሌን አግባ አለችኝ የምንለው በዝተናል ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው፡፡ ሲጀመር እኛ ራዕይ ይታየን ዘንድ ምን ተጋድሎ አድረገናል እራሳችን እንፈትሽ፡፡ በቅተናል የምንል ካለን ደግሞ በልባችን እንያዘው እንዲህ አይደለም ስርአታችን ትውፊታችን፡፡ እና እላለሁ ሰውን ከሚያሳስት ራስንም ከሚያጠፋ ከዚህ ስህተት ፈጣሪያችን ይጠብቀን!!!! እኛም እንጸልይ!!!!!!!


  ReplyDelete
  Replies
  1. በእውነት ዲ/ን ዳንኤል ሁሌም እላላሁ ረጅም እድሜ ለአንተና ለቤተሰቦችህ!!!
   እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ያነሳኸው በአሁኑ ወቅት የወጣቷን ሰማዕት ንጽህና ፣ቅድስና ፣ ተጋድሎ እያሰብን ከመባረክ ይልቅ ለስጋ ፍላጎታችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አርሴማ እከሌን አግቢ አለችኝ እከሌን አግባ አለችኝ የምንለው በዝተናል ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው፡፡ ሲጀመር እኛ ራዕይ ይታየን ዘንድ ምን ተጋድሎ አድረገናል እራሳችን እንፈትሽ፡፡ በቅተናል የምንል ካለን ደግሞ በልባችን እንያዘው እንዲህ አይደለም ስርአታችን ትውፊታችን፡፡ እና እላለሁ ሰውን ከሚያሳስት ራስንም ከሚያጠፋ ከዚህ ስህተት ፈጣሪያችን ይጠብቀን!!!! እኛም እንጸልይ!!!!!!!

   Delete
  2. Please don't repeat ten times, if you post one that is ok for us. HONEY SELLER.

   Delete
 3. በእውነት ዲ/ን ዳንኤል ሁሌም እላላሁ ረጅም እድሜ ለአንተና ለቤተሰቦችህ!!!
  እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ያነሳኸው በአሁኑ ወቅት የወጣቷን ሰማዕት ንጽህና ፣ቅድስና ፣ ተጋድሎ እያሰብን ከመባረክ ይልቅ ለስጋ ፍላጎታችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አርሴማ እከሌን አግቢ አለችኝ እከሌን አግባ አለችኝ የምንለው በዝተናል ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው፡፡ ሲጀመር እኛ ራዕይ ይታየን ዘንድ ምን ተጋድሎ አድረገናል እራሳችን እንፈትሽ፡፡ በቅተናል የምንል ካለን ደግሞ በልባችን እንያዘው እንዲህ አይደለም ስርአታችን ትውፊታችን፡፡ እና እላለሁ ሰውን ከሚያሳስት ራስንም ከሚያጠፋ ከዚህ ስህተት ፈጣሪያችን ይጠብቀን!!!! እኛም እንጸልይ!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. Berketua Yedrrben

  ReplyDelete
 5. Berketuwa. Yederesen

  ReplyDelete
 6. kale hiwot yasemalin .

  ReplyDelete
 7. መምህራችን ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን። ዲያቆን በአሁኑ ሰእት ማለት በዚህ ሳምንት አክራሪው ፕሮቴስታንት ሽፈራው ተክለ ማርያም የተዋህዶ ልጆችን ማተብ አስበጥሳለሁ ብሎ ፈክሯልና በዚህ ጉዳይ ላይ የተለመደውን ወርቃማ ጹሑፍህን እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው ይህ ርዕሰ መናፍቃን የሆነ ግለሰብ ክፉ ስራው እያሳበደው ያለ ይመስለኛል ።

  ReplyDelete
 8. Hi, Dani, thank you so much. However you didn't mentioned what she did. I know most Ethiopian know about her but some of us we don't know her. You gave us to google but everything wrote in English. In addition that I don't know how wrote about her so I don't want to pick wrong information. For example when I read Wikipedia, it said her church bulit by Catholic, is that true? If she was catholic why we follow her journey? Please give us ditail information. God bless you.

  ReplyDelete
 9. Yabatochachin amelak xegawen yabezalh yanesahachiwe nexebochi kewqetu ena kegna hyiwet gar ymihad new yih gudayi yeyandandu ortodox emenet tektayiwechin y emimilkt bemhonu bexam xeru new ybelx litasebebet yigbal bexelot endenberta semaetuw terdan

  ReplyDelete
 10. መልካም ነገር ነገርከን ዲ/ን ዳኒኤል

  ReplyDelete
 11. በእውነት ዲ/ን ዳንኤል ሁሌም እላላሁ ረጅም እድሜ ለአንተና ለቤተሰቦችህ!!!
  እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ያነሳኸው በአሁኑ ወቅት የወጣቷን ሰማዕት ንጽህና ፣ቅድስና ፣ ተጋድሎ እያሰብን ከመባረክ ይልቅ ለስጋ ፍላጎታችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አርሴማ እከሌን አግቢ አለችኝ እከሌን አግባ አለችኝ የምንለው በዝተናል ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው፡፡ ሲጀመር እኛ ራዕይ ይታየን ዘንድ ምን ተጋድሎ አድረገናል እራሳችን እንፈትሽ፡፡ በቅተናል የምንል ካለን ደግሞ በልባችን እንያዘው እንዲህ አይደለም ስርአታችን ትውፊታችን፡፡ እና እላለሁ ሰውን ከሚያሳስት ራስንም ከሚያጠፋ ከዚህ ስህተት ፈጣሪያችን ይጠብቀን!!!! እኛም እንጸልይ!!!!!!!

  ReplyDelete
 12. አንድ ነገር ልናገር የአርሴማ ምስል አሁን አንተ እንዳሳየኸው ሳይሆን ያየሁት ሁለት ዓይን በሳህን የሚመስል ነገር ይዛ እና ዘንባባ ይዛ ነው በየቤተክርስቲያኑ የሚሸጠው የትኛው እውነት ነው  ሌላው በራእይ ታየን የምንለው ነገር በዝቷል ትዳሩም ቢሆን የሚሠጠው ከሠማይ አምላክ ነው ሆኖም ማግባት መሠረታዊ ነገር ሆኖ ከተገኘ መጀመሪያ ስለትዳር መማር የሚያስፈልግ ይመስለኛል በስሜት የምናደርገው ነገር ሁልግዜ መጨረሻው አያምርም እባካችሁ ትዳርና ልጅ ዝምብሎ የሚሠጥ እየመሰላችሁ አትሳሳቱ ሊሰጠን ካሰበ ከልካይ የለውም የምንለምነው አውቀን እንፈልግ ሁልግዚ ፋሲካ እየመሰለን ከገባንበት በኋላ መውጫ ቀዳዳ የጠፋበት ሰው መሆን የለብን ደስታ እንዳለ ሁሉ ችግርም አለ ሲያገኝ ወይም ሲኖራት አብሮ ሆኖ ሲጐል መሸሽ ያሳፍራል ስለዚህ አርሲማ ሰጠችኝ ተብሎ የሚያሳፍር ስራ መስራትም የሰማእቷን ክብር ማጓደል ይመስለኛልና በአለማመናችን ላይ ትንሽ ጠንቀቅ ብለን ብንጠይቅ መልካም ነው ከአለማመን ብዙ ነገር ይቀራልና ፡፡

  ReplyDelete
 13. .... በ13ኛው መክዘ ኢትዮጵያዊው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ መጀመሪያ ወደ ግብጽ (1330-32 ዓም) .....


  Isn't this 14th century?

  ReplyDelete
 14. EGZABHER YESEMAETWAN BERKET BEHULACHEN YASADREBEN

  ReplyDelete
 15. ድሮም የቅድስት ባርባራን ሥዕል የአርሴማ ነው ብላችሁ ምዕመኑን ያሳሳታችሁ ማኅበረ ቅዱሳኖች ናችሁ፡፡ ዛሬ ደርሶ አራሚ ሆንክ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኣባክህ ምላስህን ለአስነዋሪነት አትጠቀም :: ኣግዚአብሄር ይገስጥህ

   Delete
 16. I really appreciate your passion to truth, religion, history and national love. I am surprised about the true image of St. Arsema.
  I would be pleased if you say something about the first Apostle to Ethiopia, Abune Selama Kesate Birhane as only few Ethiopian Cristians know about him and his contribution to Ethiopia and to Ethioian Cristianity.
  Finally, I wish you live for ever surving ethiopia.

  ReplyDelete
 17. I admire your passion on Truth, Religion, History and National Love.
  I'm surprised of wathing the true image of St. Arsema.
  I'm looking forward to your posting about Abune Selama Kesate Birhane.

  ReplyDelete
 18. Dani ebakih kechalk Sile KIDIST BARBARA tsafilin weyim yeminanebewin neger tekumen. EGZIABHER yibarkh.

  ReplyDelete
 19. Ya Dani, I need also to know about saint Barbara. Eg/re sirahn yibarkilh!!!

  ReplyDelete
 20. AMILAKE KIDUSAN ke Kidesit Arsema Redeiat ena Berket yasatfen D.Danii yemitsetew atita kale Hiwoten yademalin

  ReplyDelete
 21. Si'ilna foto meleyet alebin.Foto malet bekamera yeminesa sihon ketita balebetun yemimesil newu si'il gin yebalebetun wana dirgit ayayizo manignawunim yesewu misil bemansat(bichal armenawi kehone armenawi indimesil,Etyopiawi kehone itiyopiawi indimesil ) yemisal newu Lemisale yearsema armenawi timeslalech aganintin sitgerf bezenbaba ina begeta meskel titekemalech,Inegnih nachewu bizu gize keirswa sil gar yemitayut.Bearmen rejimun meskel ategebwa biyakomu ityopia wust degmo beijwa biyasizu minim liyunet yelewum. metshaf kidus tarkin betshuf indemiyasalif sil degmo beiyita yastemirenal.Menafikan arsema bemekberwa kitl alachu ide gena siraawan mech ayachihuna

  ReplyDelete
 22. Dani, Please say something about st.Barbara

  ReplyDelete
 23. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 24. Kale hiwot yasemalen Muhaze tibebat Daniel

  ReplyDelete
 25. Please attach us z PDF... I cudn't read it with my phone

  ReplyDelete
 26. please attach us with the pdf.. i couldnt read this with my phone... please...

  ReplyDelete
 27. kale hiywaten yasemalen.....asera abewen yekefalelen!

  ReplyDelete
 28. kale hiwot yasemalen wandemachen d/n danial kibret!

  ReplyDelete
 29. ቅድስት ባርባር!

  ReplyDelete
 30. Egezehabeher zemenhen yebarkew, Kale hiwot yasemalen

  ReplyDelete
 31. እግዜር ይስጥልን

  ReplyDelete
 32. kale hiwot yasemalen wandemachen d/n danial kibret!

  ReplyDelete