ዓርብ ዕለት የተከበረውን የአቡነ አረጋዊ በዓል ለማክበር አውስትራልያ አደላይድ
ነበርኩ፡፡ እዚያ ከተማ የሚገኝ አንድ የድሮ ወዳጄ በፌስ ቡክ አገኘኝና አደላይድ መሆኔን ነገርኩት፡፡ ‹‹የት እንገናኝ››
ሲለኝ ‹‹ነገ (ቅዳሜ) የአቡነ አረጋዊን በዓል ለማክበር ስለምሄድ እዚያ እንገናኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹አንተም እርሱን በዓል
ታከብራለህ?›› አለኝ፡፡ በዓይነ ኅሊናየ ራሱን እየነቀነቀ ታየኝ፡፡ ‹‹እንዴት?›› አልኩት፡፡ ‹‹የእነ እንትና ታቦት አይደል
እንዴ›› አለኝ የሆነ የኢትዮጵያ አካባቢ ጠርቶ፡፡ ‹‹ማን እንደዚያ አለ?›› ስል ጠየቅኩት፡፡ ‹‹ምን፣ የታወቀኮ ነው››
አለኝ፡፡ እየገረመኝ ተለያየን፡፡
በማግሥቱ በዓሉ ላይ ተገኘሁ፡፡ በዓሉን እኩለ ቀን ላይ ጨርሼ ስወጣ ሌላ የጥንት ዘመዴን አገኘሁት፡፡ ያ ትናንት ማታው ጓደኛዬ እዚህ ከተማ እንዳለ የማላውቅ መስሎት ይኼኛው ነገረኝ፡፡ እኔም ሰው ላለማጋጨት ብዬ ያለኝን ሳልዘረዝር እንዴው በደፈናው ደውዬለት መምጣት አልችልም እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ ይኼኛውም እኔ እንዳልነግረው የደበቅኩትን እርሱ ገልብጦ ነገረኝ ‹‹የኛ ታቦት ሲሆንኮ እነ እንትና አይመጡም›› አለኝ ፈገግ እያለ፡፡ ‹‹ማን ነው የእናንተ ታቦት ያደረገው›› አልኩ በአግራሞት›› ‹‹ያው አቡነ አረጋዊ የኛ ሀገር ሰው አይደሉ›› አለኝ የሠፈሩ ሰው ያህል ርግጠኛ ሆኖ፡፡ ወይ ግሩም፣ ይኼ በሽታ ለካ ማናችንንም ሳይለይ በደንብ ይዞናል አልኩ በልቤ፡፡
ጋሽ ግርማ ከበደ ‹‹ሰው የሚጠላውን ኃጢአት ደጋግሞ ይሠራዋል›› ይል ነበር፡፡
ብዙዎቻችን የሌላውን ሰው ዘረኛነት ለመግለጥ የምንጠቀምበት መንገድ ራሱ ዘረኛ ነው፡፡ አሁን እየተጓዝንበት ያለው አቅጣጫ
በመካከላችን ምንም ዓይነት የጋራ ነገር እንዳይኖረን የሚያደርግ ነው፡፡ የጋራ ሆነው የቆዩትን ነገሮች እንኳን አሁን አሁን ወደ
ራስ መውሰድ፣ አለበለዚያም ደግሞ የሌላው ብቻ አድርጎ ከራስ ክልል ማስወጣት ጀምረናል፡፡ ምንም እንኳን የኔታ እሸቱ ‹‹የጎጥ
ጀግና የለም፤ ጀግና ከሆነ የሁላችንም ነው፤ ያለበለዚያ ደግሞ ጀግና አይደለም›› ቢሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምንኖርባትንና የቆምንባትን
ኢትዮጵያ ያወቅናት አልመሰለኝም፡፡ ከሰሜን የጀመረ መስቀል ደቡብ፣ ከደቡብ የጀመረ ቆጮ ሰሜን በዘለቀባት ሀገር፤ የኮንሶ
የእርከን ሥራ የትግራይ ገበሬ ገንዘብ፣ የትግራይ አምባሻ የደቡብ የቅንጦት ምግብ በሆነባት ሀገር፣ የኦሮሞ ጉዲፊቻ የሁሉም ባህል
በሆነባት ምድር፣ ይኼ የእነ እገሌ ብቻ ነው፣ እኛን አይመለከትም ብሎ ለመናገር እንደመድፈር ያለ የአላዋቂ ድፍረት የለም፡፡
ማንኛውም ነገር መነሻ ይኖረዋል፡፡ ዓባይ ከግሼ ዓባይ እንደሚመነጨው፡፡ ነገር ግን
መነሻው መድረሻው አይደለም፡፡ ዓባይ ከግሼ ዓባይ ስለመነጨ የጎጃም ቀርቶ የኢትዮጵያ ብቻ ሊሆን አልቻለም፡፡ አዋሳኙ ሁሉ የእኔም
ነው ብሎ ሲመክርበት ይኖራል፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ የተጀመሩትን ኦሪትን፣ ክርስትናንና እስልምናን የኛ አድርገን እየኖርንባቸው
አይደል እንዴ ? ከአውሮፓ የወረስነውን ኮትና ሱሪ ቂቅ ብለንበት እየተዳርንበት አይደለም እንዴ? በፖርቹጋሎች በኩል ከሜክሲኮ
የደረሰን በርበሬ ይኼው የአበሻ መለያ ሆኖ የለም እንዴ፤ የአውስትራልያ ባሕር ዛፍ ኢትዮጵያዊ ሆኖ የለም እንዴ፤ እንዴት ነው
ጎበዝ፡፡ ጤፍ ለምግብነት ዋለ የሚባለው ከክርስቶስ ልደት በፊት 5000 ዓመት ቀደም ብሎ በሰሜን ደጋማ ቦታዎች ነው፡፡ ዛሬ
ግን ይኼው ድፍን ሐበሻ ባሕሉ አድርጎት፤ ዘልቆም ድፍን ዓለም ሊበላው እየተሻማ ይገኛል፡፡ የሰሜን ነው ብሎ ማን ተወው፡፡
መልካም ነገር ከአንድ ቦታ ይነሣል፡፡ ከዚያም ሌላውም ከባሕሉና እምነቱ ጋር እያዛመደ
ይዋረሰዋል፤ ወይም ገንዘብ ያደርገዋል፡፡ ከዚያም የእርሱም ጭምር ይሆናል፡፡ በተለይ በታሪካችን ውስጥ ከአንዱ የተነሣ ነገር
ሰፍቶና መልቶ የሌላውም ገንዘብ የሆነበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ እንዲያውም በሚያስደንቅ መልኩ ከመነሻው ጠፍቶ ከመድረሻው የተገኘ
ብዙ ነገር አለ፡፡
ከላይ መነሻዬ ከሆነው የአቡነ አረጋዊ ነገር ልጀምር፡፡ አቡነ አረጋዊ ሀገራቸው ኢትዮጵያ
አይደለም፡፡ ሮማዊ ናቸው፡፡ በ5ኛው መክዘ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ አቡነ አረጋዊ መጨረሻቸውን
በደብረ ዳሞ፣ ትግራይ ቢያደርጉትም በወሎ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በደቡብ ታሪክ ውስጥ ግን አሉ፡፡ ደቡብ ጎንደር ውስጥ
ጥንታዊው ገዳማቸውና የዝማሬ መዋሥዕት ማስመስከሪያው ዙር አባ አረጋዊ አለ፡፡ ጣና ቂርቆስ፣ አዲስ አበባ አጠገብ የሚገኘው
የረር፣ እንዲያውም ከዚያ ተሻግሮ ጋሞጎፋ የምትገኘው ብርብር ማርያም ታሪካቸውን ከእርሳቸው ጋር ያገናኛሉ፡፡ የመጨረሻውና ታላቁ
ገዳማቸው ደብረ ዳሞ ስለሆነ የኛ አይደሉም ብለው አያውቁም፡፡ የጎንደር ሊቃውንት በ17ኛውና በ18ኛው መክዘ ለዓመት የሚቆመውን
ዚቅ ሲያዘጋጁ ቦታ ከሰጧቸው ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው፡፡ የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ ድንበር ጠባቂ ሆኖ
ሞያሌ ላይ ይገኛል፡፡ ለሁለቱ ኢትዮጵያውያን የምንኩስና መሠረቶች ለአቡነ ተክለ ሃይማኖትና አቡነ ኢየሱስ ሞአ ምንኩስናን
የሰጠው ደብረ ዳሞ ነው፡፡ ዋርካው ሲሰፋ እዩት፡፡
እንግዲህ እኒህን ከሁሉም በላይ ሆነው፣ የሁሉም የሆኑትን አባት ነው አንዳች ጎጥ
ውስጥ ልንከታቸው መከራ የምናየው፡፡ ልክ አንዳንዶቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ከሸዋ ብሎም ከአማራ ጋር ለማያያዝ እንደሚሞክሩት፡፡
እንዲያውም በሚገርም ሁኔታ ገድላቸው የአያቶቻቸውን ጥንተ መሠረት ከትግራይ፣ በኋላም ከዋድላ ጋር ነው የሚያያይዘው፡፡ በኋላም ሥርዓተ
ምንኩስናን የፈጸሙት በአምሐራና በሐይቅ እስጢፋኖስ(ወሎ)፣ በስተ መጨረሻም በደብረ ዳሞ(ትግራይ) ነው፡፡ በውስጣቸውም የትግራይ
ገዳማትን የመጎብኘት ልዩ ፍላጎት ስለነበራቸው ለብዙ ዓመታት በዚያው በትግራይ እየተዘዋወሩ አገልግለዋል፣ ተሳልመዋልም፡፡
ታላቁንና የሰሜን ኢትዮጵያ የምንኩስና መሠረት ከሆኑት አንዱ የሆኑትን አቡነ መድኃኒነ እግዚእንም አመንኩሰዋል፡፡ እንዲያውም እዚያው
ትግራይ ውስጥ ቀንጦራር በተባለ ቦታ(በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ?) ለመቅረትና ገዳም ለመመሥረት ፈልገው ነበር፡፡
አያሌ የኤርትራና የትግራይ ገዳማት የምንኩስና ሐረጋቸውን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት
የሚጀምሩትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ እንደ አጭር ማሳያ የዋልድባውን አቡነ ሳሙኤልና የቆየጻውን አቡነ ሳሙኤል መጥራቱ ብቻ
ይበቃል፡፡ በጣና ገዳማት የሚገኙት የግድግዳ ላይ ሥዕሎች ሁለቱን አባቶች - አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ጎን
ለጎን ነው የሚሥሏቸው፡፡
ከሰሜን ተነሥቶ ደቡብ መምጣት፣ ከደቡብ ተነሥቶም ሰሜን መሄድ እንዲህ እንዳሁኑ ከባድ
አልነበረም፡፡ እነ አቡነ ፊልጶስና አቡነ አኖሬዎስ ነገሥታቱ ሲያሳድዷቸው የተጠለሉት በትግራይ ገዳማት ነበር፡፡ የተጋዙትም ወደ
ዝዋይና አርሲ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሠራዔው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ ደርሰው አስተምረዋል፡፡
የአኩስም ጽዮን ካህናት ከዮዲት መዓት ለማምለጥ ወደ ዝዋይ ነበር የመጡት፡፡ ያለ ሀገራችሁ፣ ያለ ክልላችሁ ያላቸው
አልነበረም፡፡ በ14ኛው መክዘ በነበረው የሰንበት ክርክር ጊዜ የሞረቱ ዜና ማርቆስ ገዳም መነኮሳት በቦታ ከሚቀርባቸው ደብረ
ሊባኖስ ገዳም ይልቅ የኤርትራ ገዳማት የያዙትን አቋም ደግፈው ነበር፡፡ የሙገርን ቅዱሳን ያስተማረው ሐራንኪስ የአኩስም ተወላጅ
ሲሆን የቡልጋን ቅዱሳን ያስተማረው ሕይወት ብን በጽዮን ደግሞ የተማረውና የማስተማሪያ መጽሐፉን ያገኘው ከትግራይ ገዳማት
ነው፡፡ እንዲያውም ለብዙ ዓመታት በትግራይ ገዳማት ቆይቶ ተምሮ ሲመለስ የተወለደባትን ዞረሬን ባያት ጊዜ ‹‹እንደ ሀገሬ እንደ
አኩስም መሰለችኝ›› ነበር ያላት፡፡
በኤርትራ ታላቅ ቦታ ያላቸው አቡነ አብራንዮስ የጎጃም ሁለት እጁ እነሴ ተወላጅ
ሲሆኑ፣ በምሥራቅ ጎጃምና በደቡብ ጎንደር ታላቅ ቦታ ያላቸው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ደግሞ የኤርትራ ተወላጅ ናቸው፡፡ የምሥራቅ
ጎጃም ገበሬ በኤዎስጣቴዎስ ከማለ መላሽ የለውም፡፡ የሙገሩ አቡነ አኖሬዎስ በሸዋ የነበረው ገዳማቸው ሲጠፋ በላስታና በደቡብ
ወሎ ግን ገዳማቸው አሁንም በክብር አለ፡፡ እንዲያውም ልብሳቸው፣
መስቀላቸው፣ የጸሎት መጽሐፋቸው የሚገኘው ላስታ፣ ዋናው ገድላቸው የሚገኘው ተንቤን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ አኩስም ቢወለድም ድጓው
የሚገኘው ደቡብ ጎንደር ቤተልሔም፣ ዝማሬ መዋሥዕቱ የሚገኘው ደቡብ ጎንደር ዙር አምባ ነው፡፡ አሁን በያሬድ ዜማ ሲዘም ማን
አኩስምነቱ ትዝ ይለዋል፡፡ የላስታው ላሊበላ በላስታ ካለው ደብር በላይ በምዕራብ ጎጃም ያለው ይልጣል፡፡ በዚያ ከአምስት በላይ
በስሙ የሚጠሩ አድባራት አለው፡፡ በጉራጌ ትልቁን ሐዋርያነት የሠሩት የሰሜን ሸዋው አቡነ ዜና ማርቆስ ናቸው፡፡ በጎንደር ደግሞ
ትልቁን ሥራ የሠሩት የጉራጌ ሊቃውንት ናቸው፡፡
በግራኝ አሕመድ ዘመን ከሆነው ጥፋት በኋላ ጎንደርን ሊያቀና የተነሣው ዐፄ ሠርፀ ድንግል
ትልቅ ችግር የሆነበት ለጎንደር አድባራት የሚሆኑ ሊቃውንትን ማግኘት ነበር፡፡ በኋላ ግን እነዚህ ሊቃውንት ከጉራጌ ምሑር
ኢየሱስ ገዳም ተገኙ፡፡ እነዚህ ‹‹አርባዕቱ ሊቃውንተ ምሑር›› በመባል የሚታወቁት አባ መሰንቆ ድንግል ዘቤተ ልሔም፣ አባ
ለባዌ ክርስቶስ ዘዙር አምባ፣ አባ ብእሴ እግዚአብሔር እና መምህር ተክለ ወልድ ዘለገደባ ማርያም ናቸው፡፡ በላይ ጋይንት ደብረ
ማርያም የሚገኘው ሃይማኖተ አበው ‹‹ዐርባዕቲሆሙ ኅቡረ፣ ቃላቲሆሙ ሥሙረ - አራቱም አንድ ነበሩ፣ ቃላቸውም የሠመረ ነበረ››
ይላቸዋል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት ነበሩ እየተማከሩ ጎንደርን እንደገና አቅንተው የሊቃውንት መፍለቂያ ያደረጓት፡፡ በጎንደር ከተማ የዘር
ነገር የማይነሳው ለዚያ ይሆን?
ከጎንደር ሳንወጣ ዛሬ አደባባይ ኢየሱስ የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጥንት
የነበረው ከምባታ ነበር፡፡ (በገድለ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አካባቢው ባደረጉት ጉዞ መጀመሪያ የተከሉት ታቦተ
ኢየሱስን መሆኑ ይናገራል፤ ምናልባት እርሱ ሊሆን ይችላል) በግራኝ ጊዜ በተፈጠረው ስደት ካህናቱ ተሰደዱ፡፡ ታቦቱንም በአንድ
ቦታ ሠረወሩት፡፡ የመከራው ጊዜ ሲያልፍ ደብሩን እንደገና ቢደብሩትም ታቦቱን ግን ማግኘት አልቻሉም፡፡ በዐፄ ሠርፀ ድንግል
ዘመን አባ ንዋይ የተባሉ አባት ወደ ከምባታ ወርደው ታቦቱ ያለበትን ቦታ ለ47 ዓመት ሲፈልጉ ቆይተው በ1570 ዓም አካባቢ
አገኙት፡፡ ወደ ንጉሡም ይዘውት መጡ፡፡ ዐፄ ሠርፀ ድንግልም ያመፀውን ባሕረ ነጋሽ ይስሐቅንና ቱርኮችን ለመውጋት በዝግጅት ላይ
ስለነበሩ በ1572 ዓም ደንቢያ ላይ እያሉ ከአባ ንዋይ ጋር ተገናኙ፡፡ በዚህ ጊዜ የባሕረ ነጋሽ የትዕቢት መልእክት ከሁለት
ጥይት ጋር መጥቶላቸው ነበርና አንዱን በታቦተ ኢየሱስ፣ ሌላውን በግምጃ ቤት ማርያም ላይ አድርገው እንዲጸልዩበት አዘዙ፡፡
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ታቦተ ኢየሱስ ከንጉሡ አልተለየም፡፡ በ1572 ረዳዒ የተባለውን
የቤተ እሥራኤል መሪ፣ በ1579 ጎሼን ለመውጋት ሲዘምቱ አብሮ ነበረ፡፡ በኋላ በዐፄ ፋሲል ዘመን አደባባይ ኢየሱስን ሠርተው
ታቦቱን በዚያ አኖሩት፡፡ ይኼው ከከምባታ መጥቶ ጎንደር ላይ ተተክሎ ይኖራል፡፡ ልክ ወሎ መካነ ሥላሴ የነበረውና በግራኝ
ተቃጥሎ ፍራሹ የሚታየው የመካነ ሥላሴ ታቦት አሁን አራት ኪሎ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚገኝው ማለት ነው፡፡ የቁልቢ ገብርኤል ታሪክ
ከአኩስምና ከቡልጋ ጋር እንደተያያዘው፡፡
መርጡለ ማርያምን ቤተ ክርስቲያንን ከግራኝ ዘመን ትንሽ ቀደም ብሎ ባመረ ሁኔታ እንደገና
አሠርተዋት የነበሩት እቴጌ ዕሌኒ የሐድያ ተወላጅ ነበሩ፡፡ ሕዝቡ በደግነታቸው ስለሚወዳቸው በሞቱ ጊዜ ከሩቅ ሀገር ሳይቀር
እየሄደ መርጡለ ማርያም ከመቃብራቸው ላይ ያለቅስ ነበር ይላል አልቫሬዝ፡፡
እንዴው ባጠቃላይ እንደ ዘሐ ዘጊ ወዲህና ወዲያ እንዲህና እንዲያ በተዋረሰውና
በተወራረሰው ሕዝብ መካከል ‹‹የዚያ ብቻ›› ወይም ‹‹የእኔ ብቻ›› የሚል ነገር ማምጣት ካለ ማምጣቱ ይልቅ የሚከብድ
ይመስለኛል፡፡ እንኳን ደጉ ነገር ክፉው ነገራችን እንኳን ተዋርሶ ተዋርሶ የሁላችን ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን የራሳችን ቋንቋ፣ ባሕልና
ማንነት ቢኖረንም፣ የበለጠ የሚያዋጣን የኛንም ሸጠን፣ የሌላውንም ገዝተን የተዋርሶና የተገናዝቦ ማንነት ብንፈጥር ነው፡፡ ከአጥሩ
ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡ ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
አደላይድ፣ አውስትራልያ
እንዴው ባጠቃላይ እንደ ዘሐ ዘጊ ወዲህና ወዲያ እንዲህና እንዲያ በተዋረሰውና በተወራረሰው ሕዝብ መካከል ‹‹የዚያ ብቻ›› ወይም ‹‹የእኔ ብቻ›› የሚል ነገር ማምጣት ካለ ማምጣቱ ይልቅ የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ እንኳን ደጉ ነገር ክፉው ነገራችን እንኳን ተዋርሶ ተዋርሶ የሁላችን ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን የራሳችን ቋንቋ፣ ባሕልና ማንነት ቢኖረንም፣ የበለጠ የሚያዋጣን የኛንም ሸጠን፣ የሌላውንም ገዝተን የተዋርሶና የተገናዝቦ ማንነት ብንፈጥር ነው፡፡ ከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡ ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
ReplyDelete"ወይ ግሩም፣ ይኼ በሽታ ለካ ማናችንንም ሳይለይ በደንብ ይዞናል አልኩ በልቤ፡፡" በትክክል ገልፀኸዋል ዲያቆን ዳንኤል። የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ ከክፉ ነገር ይጠብቅህ።
DeleteDani,just to get peace of mind, it is good to share your view.But i believe something has escaped from our (Ethiopians) hand.While the church is trying to build strong united Ethiopia, the politicians are doing their best to dismantle the church more than ever. Eventhough i dont believe that they can succeed, there would be their print here and there that can be an obstacle for the coming generation.In short if we stand together we can withstand the pressure from anti-church group otherwise the country as a whole and inparticular the chrch would be in problem in the future.May God save his Church and the country as a whole.Amen.
ReplyDeletePdf
ReplyDelete‹‹የጎጥ ጀግና የለም፤ ጀግና ከሆነ የሁላችንም ነው፤ ያለበለዚያ ደግሞ ጀግና አይደለም››!!!
ReplyDeleteእንኳን ደጉ ነገር ክፉው ነገራችን እንኳን ተዋርሶ ተዋርሶ የሁላችን ሆኗል፡፡
ReplyDeleteምን እላለሁ እግዚአብሔር ይስጥልን።
እዚህ ባለሁበት ሎስ አንጀለስ እንኳን አቡነ ጳውሎስና አባ ሰረቀ የተከሉት እሾህ ይኼው እስከ አሁን አልነቀል ብሎ የኖረው "የእኛ ብቻ ናቸው" በሚል ነው።
በዚህ ምክንያት እኛ እነሱ ጋር ሳንደርስ እነሱም እኛ ጋር ሳይመጡ ተለያይተን ልንቀር ነው። የሚገርመው ግን ልጆቻችን ይህን ሁሉ ጉድ አያውቁም ሲያውቁ ምን ይሉ ይሆን????
Gonder ye aratu hayalan mirkat tebrarto. it is so goooood
ReplyDeletesintu yanebew yihon.tim qorachu wondime bertalilgn
ReplyDeleteእንግዲህ የሚያውቅ ተናግሮ ያስታርቀን እንጂ እኛስ እንጃለን!!!!!!!!!!!! ስሜታዊነት የትም አያደርስም::እናመሰግናለን ዳንኤል!!!!!!!!!!
ReplyDeleteEgziyabher yebarke
ReplyDeleteYegna albeka belo tabotaten lemekefafel anemoker lehulum egziyabeyer lebyesten Amen.
ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
ReplyDeleteትልቁ ጠላታችን ስለታሪካችን አለማወቃችን ሳይሆን አይቀርም!!!!!!!!!
ReplyDeleteይገርማል....!!!!!!! እንደዚህ ነው እንዴ ለካ???? ወንድሜ ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ:: ይቅር በይኝ ሀገሬ!
ReplyDeleteufff....temesgen! diyakon daniel kibret....yanten thufoch manbeb kejemerku wedih le hagere tru smet endinoregn adrgognal.....tarikn letwulid bemayiselech na ende mar eyetefete endiyanebew na sle hageru bzu awuko lageru yechalewun endisera manesasat emichil thuf eyetafik newuna....egzabher edmihen yarzmew,,,,,egzabher degag sewoch ....tarikn emiyawersu abatochn na endante deg na kin yehonu besal sewoch endiyabeza egzabhern lemenkut.....ewunetim ante lik ene nisir neh! geta hoy endih aynet wendm sleseteken temesgen!
ReplyDeleteእግዚብሔር ይስጥልን ዲ.ን ዳንኤል አምላከ አበዊነ የመለያየትን መንፈስ አስወግዶ የአንድነትን መንፈስ ያሳድርብን ዘንድ የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን ፀሎታቸው አይለየን
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል……ኢትዪጵያ ውሥጥ ትግሬ የሚባል ህዝብ የለም…እባክህን አንተም እንደመሰሎችህ ችግር ከሌለብህ በቀር…..ትግራይ ብለህ ጥራን..ፃፍ….የትግሬ ገበሬ ሳይሆን የትግራይ ገበሬ ብልኅ ፃፍ….አዎን ደግሜ እነግርሃለው…ውስጠ ወይራነታቸሁ ሰልችቶናል..መሮናል….እኛ ትግራዪች አንጂ….ትግሬዎች አይደለንም….እናንተ እኛን ትግሬ የምትሉ ሆን ብላችሁ ለማሳነስ እንደሆነ እናውቃለን…..እውነታው ግን በነንዳንተ ዓይነት የጥላቻ ቃላት መቼም ቢሆን ኣናንስም….ትልቅና ባለታሪክ ህዝቦች ነንና!!!
ReplyDeleteትግራይ ሀገሩ ሲሆን ትግሬ የነዋሪዎቹ/የሰዎቹ መለያ መጠሪያ መሰለኝ (ትክክል ነኝ?)፡፡ የትግሬ /ትግሬ ገበሬ ደግሞ በጣም ጠንካራ ገበሬ ነው፡፡
Deleteየአማራውን "አማሬ" አትለውም መቼም:: የኦሮሞውን "ኦሮሜ" አትለውም:: ስለዚህ የትግራዩን - "ትግሬ" ሲሆን ልክ አይሆንም:: ከዚያም በላይ የሽርደዳ ወይም ደረጋቶሪ ነው:: በሶስተኛ ደረጃ የስሙን ታሪካዊ አመጣጥና ማን ሰጠው የሚለውን ማየትም ያስፈልጋል:: ሰው በወደደው ነው የሚጠራው:: እንዲሁ ማህበረሰቦችም በወደዱትና ራሳቸው ለራሳቸው በሰጡት ስም ሊጠሩ ይገባል:: በመሆኑም ያ ህ/ሰብ ራሱ የራሱን ስም ሊያወጣ ይገባል:: ሕ/ሰቡ ለራሱ የሚሰጠውን ስም ደግሞ ከቋንቋው ነው የምታገኘው:: አለያም ህ/ሰቡ ለኔ ክብር ይመጥናል የሚለውን ከሌሎች ቋንቋዎች ይመርጣል::
Deleteበዚህ መሰረት የትግርኛ ስሞቹ - ትግራዋይ- ለወንድ ትግራዋይቲ- ለሴት ይሆናል:: የብዙሃን ስሙ ደግሞ "ተጋሩ" ይሆናል:; ስለዚህ ጸሐፍት እንዲሁ "ደረጋቶሪ" ቃላት እንደወረዱ ያለምንም ጥንቃቄ መጠቀማቸው ተገቢ አይደለም:: ሲብስ ደግሞ አላዋቂነት ነው:: ከዚያም ከከፋ ለህዝቡ ያላቸው አመለካከት ያጋልጣል:: እንዲህ አይነት ጽሁፎች በጥቅሉ መቻቻልን እየሰበኩ በሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የተዛቡና ከፍሬሙ የማይዛመዱ መሆናቸው የመልክቶቹንም ተደማጭነት ይቀንሳል ወይም በጽኑ ይጎዳል::
እንደው ወንድሜ ከዛ ሁሉ ሰፊ ፅቡቅ እና የተቀደሰ ሃተታ የታየህ ይሄ ነው?? ምነው comment ማድረግህ ካልቀረ you should have written it with a clear concious!! & I wonder from where z inferiority talk comes from! Dani Keep on spreading the love - አንድ የሆነችውን የእግዚአብሔርን መንግስት ግን ተከፋፍለን መውረስ ይቻል ይሆን?????
DeleteDear AnonymousOctober 27, 2014 at 10:42 AM
DeleteWhy you shout like that? There are lots of Gentle ways to correct.
What you raised is about wording, which a very tiny matter of the written piece.
Is your intention to divert the agenda? I believe it is impossible by now (already posted).
Any ways thanks for one thing, you have add me one wording knowledge.
In the future be patient and gentle in addressing issues.
kalat kemkuter kumnegeru layi enatekur yihe erasu lela zeregnet newu
DeleteKalat kememirt kumnegerun binayi melkam newu yihe erasu lela zeregnet newu
DeleteDear anonymous (@October 27/2014; 10:42)! We know people called "Tigre" as we have "Gojjame", "Gondere", and so on. Definately!
Delete"ከሰሜን የጀመረ መስቀል ደቡብ፣ ከደቡብ የጀመረ ቆጮ ሰሜን በዘለቀባት ሀገር፤ የኮንሶ የእርከን ሥራ የትግራይ ገበሬ ገንዘብ፣ የትግራይ አምባሻ የደቡብ የቅንጦት ምግብ በሆነባት ሀገር፣ የኦሮሞ ጉዲፊቻ የሁሉም ባህል በሆነባት ምድር፣ ይኼ የእነ እገሌ ብቻ ነው፣ እኛን አይመለከትም ብሎ ለመናገር እንደመድፈር ያለ የአላዋቂ ድፍረት የለም፡፡ "
Deleteይህ አባባል ፡ በትግርኛ ነው ፡ ወይስ ባማርኛ?
Deleteትግሬ ሳይሆን ትግራዋይ/ትግራዋይቲ/ተጋሩ ላልከው አስተያየት ሰጪ። ዳንኤል ክብረት ፅሁፉን ያቀረበው በአማርኛ ነው። ስለሆነም በአማርኛ ውስጥ ትግራዋይ/ትግራዋይት/ተጋሩ የሚሉ ቃላት ስለሌሉ በምትካቸው ያሉት አማርኛ ቃላት ትግሬ እና ትግሬዎች ስለሆኑ ነው ዳንኤል በዚህ መልኩ የተጠቀመው። ፅሁፉን በትግርኛ ፅፎት ቢሆን ኖሮ ትግራዋይ/ትግራዋይቲ/ተጋሩ እያለ ይጠቀም ነበር። ልክ በትግርኛ ስለ አማራ ሲፃፍ አምሃራይ እየተባለ እንደሚፃፈው ማለት ነው። ወይም በአማርኛ ሲፃፍ አሜሪካዊ እንጂ አሜሪካን እንደማይባለው፤ ጣሊያናዊ እንጂ ኢታሊያኖ እንደማይባለው። ልክ እንደዚያው ሁሉ አሜሪካኖቹም ስለ ኢትዮጵያዊ ሲፅፉ ኢትዮፕያን እንጂ ኢትዮጵያዊ እንደማይሉት ማለት ነው። እናም ወንድሜ ነገሩ የቋንቋ ጉዳይ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም።
DeleteKAle Hiwot yasemalen!!!
ReplyDeleteThank you Dani this issue raised on Friday on our office he .Thank so much we got the answer.
ReplyDeleteGOD bless you and wish you long live
ከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡
ReplyDeleteየሚገርመው ነገር ስለአቡነ አረጋዊ ብቻ ሳይሆን እየሱስን ማለት የከበደበት ዘመን ነው እየሱስ የሚመሰላቸው ለኘሮቴስታንት እንጂ ለፍጥረት ሁሉ የማይመስለው ሕዝብ ውስጥ እንዳለን አስብ የመረዳት ነገር በጣም ከባድ ነው ዘረኝነት ደግሞ ትልቁ ነቀርሳ ነው ስለዚህ ስለታቦቶች ያለንን ግንዛቢ ማለትም የአማራው የትግራዬ ከማለት ይልቅ አመጣጣቻው እንዴት እንደሆነ እንደዚህ አንደአሁኑ አይነት አገላለፅ ላይ ትንሽ ሰፋ በማድረግ ብታስረዳ ማለት ለአብያተ ክርስቲያናት ቅርብ ነገር ስላለህ ማለቴ ነው ፡፡ ሌላው ነገር አማላጅና ፈራጅ በራሱ አንድነትና ልዩነት የሌለበት ዘመን ላይ ደርሰናል ትውልዱ የሚፈልገው መረዳት ነው እንጂ ማባበል አይደለም እባክህ ሕዝቡን ከፈላ ውሃ ውስጥ ለማውጣት የራስህን ጥረት አድርግ ስለወለድካው ልጆች ብቻ ሳይሆን በወንጌል ሁሉም የራስ ልጅ ነውና ፡፡
ReplyDeleteይቅርታ ይደረግልኝና አንተ/አንቺ እንደጠራኸው/ሽው ሲጠራ እኔም ደስ አይለኝም ምክንያቱም ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንዲህ በነጠላው አይጠሩትም፡፡ አረ እንደውም ጥንታውያኑ የመጽሐፍ ቅዱስ አብነቶች አንድም ቦታ ስሙን በነጠላው ጠርተውት አያውቁም ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ስሙን በክብር እንደሚጠሩት እንዲህ እያሉ፡- ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና፤ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ በአንደበት መመስገኑ ከፍ ከፍ ይበልና፤ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ክብር ይግባውና “የአብ የባሕርይ ልጅ አምላክ ወልደ አምላክ አይደለህም” ብለው የካዱትን አሁንም በዚህ መንገድ የሚክዱትን እንደዚሁም “በሰው ፊት የመሰከረልኝን እኔም በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ” ባለው ቃሉ መሠረት ምስክርነታችንን ስሙን ስንጠራው ጀምሮ መሆን እንዳለበት ቤተ ክርስቲያን አስተምራኛለችና እንዲሁ በነጠላው “ኢየሱስ” እያሉ ሲጠሩት ስሰማ እኔም ደስ አይለኝም ስሙ ቀላል ስም አይደለምና “ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም” ነውና፡፡ የዓለም ሁሉ መድኃኒት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባው፡፡
DeleteThank you. The name of Our God is above the names of all.
DeleteEgizabhare yestehe D/n Daniel eya sawuoche sanawuke sehetatewuste enwadekaline manbabena, teyko mardatene yamasala tilke nagare yalam God bless you Dani thank you very much!!!
ReplyDeletetaric awaki lememsel atdkem train atawkmna endelemedachihut some hodachihu btasbu yawatachual
ReplyDeleteMy friend please if you think d/n daniels article is not acurate you can give us the correct historical account. You just can not dismiss ones article without any hitorical evidence. Just because you know some english words don't jump and critisize.
Deletewhich English r u talking about? he knows neither English nor History
Deleteከፋፋዮች በበዙበት ዘመን አንድነትን የሚሰብክ አያሳጣን፤ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ቃለ ህይወትም ያሰማህ አሜን።
ReplyDeleteእግዚብሔር ይስጥልን ዲ.ን ዳንኤል አምላከ አበዊነ የመለያየትን መንፈስ አስወግዶ የአንድነትን መንፈስ ያሳድርብን ዘንድ የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን ፀሎታቸው አይለየን
ReplyDeleteGod bless you D. Daniel. ከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡ ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
ReplyDelete"....የሚያዋጣን የኛንም ሸጠን፣ የሌላውንም ገዝተን የተዋርሶና የተገናዝቦ ማንነት ብንፈጥር ነው፡፡ ከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡ ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡"
ReplyDeleteከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡
ReplyDeleteDaniel, As to me the article is just a fiction. U create some idea in your mind and narrate by giving it a character. If it is real, if the guys were not ashamed when talking in such a foolish way, why u fell shame for them and hide their names?
ReplyDeleteIf it is real, there is a popular saying : " tell me about your friends and I will tell u about you.
what shame full logic you provide? do you have any know how how to write articles? who say unless the individual names are mentioned , article is fiction? pls out from the pit of ignorance and hate.
DeleteThe ignorance is on u. I didn't say that any article without real name is fiction. I said most Daniel's article when he refers about someone, he writes just a fiction or his own idea in the name of someone.
DeleteAs Prof. Mesfin said, "he writes not because he knows the issue, rather to be known as a knowledgeable person."
So what you're saying is: "There are no people who're saying what Daniel was talking about." That's not true. We know that there are "Ethiopians" who think locally rather than nationally. Your conclusion about the "fictionness" of the article is too shallow. You cannot assume an article is a fiction, just because names are not mentioned. You hide names to protect the people from being negatively judged by their deeds. Besides, what if the story's fiction? What's important is the message. One more thing: The last saying that you mentioned at the end doesn't add up to your argument. So please, don't "quote" just for the sake of quoting. Be reasonable.
DeleteMy brother Anony,
DeleteI can give you lots of real life experience. For example here in Los Angeles, people are greatly separated by this... It is not fiction. IT is real life. If you need further clarification, I can give you one more... Go to San Diago, they are separated, one in San Jose... the same thing...We need to fix instead of having a fence.
tnx
ReplyDeleteአይ ዳንኤል!!!!!! እስኪ መጀመሪያ አንተ እና የማህበራችሁ መሰሎችህ ዘረኘረነቱን ቀድማችሁ ተውት፡፡
ReplyDeleteFor :Anonymous October 28, 2014 at 8:30 AM
DeleteYou brought after many years a new concept and way to insult.
I feel you have finished all your spares.
for : AnonymousOctober 29, 2014 at 9:02 AM
Deletethis is how you look constructive critisism.but, i assure you your labeling never make us as you say.
I am really feel sad when I heard that ውስጠ ወይራነታቸሁ ሰልችቶናል..መሮናል….እኛ ትግራዪች አንጂ….ትግሬዎች አይደለንም….እናንተ እኛን ትግሬ የምትሉ ሆን ብላችሁ ለማሳነስ እንደሆነ እናውቃለን…..እውነታው ግን በነንዳንተ ዓይነት የጥላቻ ቃላት መቼም ቢሆን ኣናንስም….ትልቅና ባለታሪክ ህዝቦች ነንና!!!. this is the first time to see the difference but the way he explain is generalization about the whole. this is the problem we looking things.
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ሕይወትህን ሁሉ ይባርክልህ፡፡
ReplyDeleteየልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያክል ይስቃል እንደሚባለው የልብ አውቃ የሆንክ ሰው በዘመናችን ያለህ ቅዱስ ጳውሎስ ነህ፡፡ አንተን የፈጠረ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ አንዳንድ ወገኖች በአስተያየት አሰጣጥ እንኳን አሁንም ያልታረመ ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ ምን ጊዜም እግዚአብሔር የማይወደው የመጀመሪያውን ጥፋት ሳይሆን ደግመን የምንሰራውን ነው፡፡ ለዚህም መጻጉን በቤተ ሳይዳ አድኖት በቤተ መቅደስ ሲያገኘው ደግመህ እንዳትበድል ብሎታል፡፡ ያችንም በዝሙት ምክንያት የተያዘች ሴት ከሳሾቿ ጥለዋት እንደሄዱ ባየ ጊዜ ደግመሽ አንዳትበድይ ብሏታል፡፡ ይህንን ያነሳሁት መጀመሪያ ከሁለቱም ጎራ ቆመው ያጠፉትን ለማረም በሚደከመው ድካም የዘሩት ዘር አልበቃቸው ብሎ ፀጉር እየሰነጠቁ ቃላት ተሳስተሃል ፣ሆድህን ሙላ፣ ታሪክ አታውቅም ወዘተ... ያሳዝናል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖነ ማርያም በምትባለው የእመቤታችን የምስጋና መጽሐፍ ላይ በእለተ እሁድ ምስጋና ምዕራፍ 4 ቁጥር 3 ላይ ድንግል ሆይ ከመታበይ ልቡናን ከማደንደን አድኝኝ፡፡ ልበ ደንዳና ሰው እግዚአብሔርን ይቃወማልና ብለው ጸልየዋልና ልበ ደንዳና አንሁን እንማር፣እንታረም፣አስተያየት አሰጣጣችንም ስርዐት ይኑረው፡፡ ፀሐፊው ቢሳሳት እንኳን አራሚው መብለጡ የሚታወቅበትን አስተያየት በሚያስተምር ሁኔታ ይስጥ፡፡ እሱ የሰጠው አስተያየት ለፀሐፊው ብቻ ሳይሆን ለሌላውም አንባቢ አስተማሪ ስለሚሆን ማለት ነው፡፡ ሌላው ግን ኢትዮጵያውያን ወይም ኦርቶዶክሳውያን ካልሆናችሁ ልትወቀሱ አይገባችሁም፡፡ አንድም ለጥፋት አንድም ባለማወቅ ገደል ተከባችኋልና፡፡ ይቅርታ እንግዲህ እኔ አስተያየት ልሰጥ ከተነሳሁበት ሃሳብ ወጥቼ ወንድሞቼን ለመውቀስ በማሰቤ አዝናለሁ፡፡ ወደ መነሻ ሃሳቤ ስሄድ ወንድም ዳንኤል ያነሳኸው ሃሳብ በጣም አስደስቶኛል ልክ እንዳንተ እኔንም ስለገጠመኝ ነው፡፡ ከምሰራበት ቦታ አቡነ አረጋዊን ለማንገስ የሁለት ቀን ፈቃድ በመጠየቅ ሐሙስ እለት ወደ ሆነ ቦታ እሄዳለሁ፡፡ በዚህም አጋጣሚ ከቅዱስ ሚካኤል ታቦት ጋር ድርብ የአቡነ አረጋዊ ታቦት እንዳለ በማውቀው ቦታ ነበረና የሄድኩት ምናልባት ላይከበር ይችላል በሚል ቀድሜ በዋዜማው በማጣራት ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ እናም ቤተ ክርስቲያኑ ባለቦት ቦታ ደርሼ ሳጠራ ይከበራል ዛሬም ዋዜማ ይቆማል የሚል መልስ በማገኘት እየተመለስኩ ሳለ አንዲት እህታችን ከቤተክርስቲያን ወጥታ ስትሄድ መንገዳችን አንድ ሆኖ መወያየት ጀመርንና ስለ አከባበሩ ስነ ስርዐት፣ስለ ሃገሩ ባህል ወዘተ... ስጠይቃት በድንገት አቋርጣ አንተ ብሔርህ ምንድነው አለችኝ፡፡ እኔም አማራ ነኝ አልኳት፡፡ እንዴት አቡነ አረጋዊን ታከብራለህ አለችኝ፡፡ አቡነ አረጋዊ የማናቸው የሚከበሩት በጽድቃቸው ነው እንጂ የማን ሁነው ነው አልኳት፡፡ አይ እኔ ትግሬ ነኝ እስካሁን በማውቀው አማራና ኦሮሞ በሳቸው ሲቀልድና ሲሰድባቸው ነው እንጂ ሲያነግሷቸው አይቸ አላውቅም አለችኝ፡፡ በእውነት በጣም አዘንኩ አቡነ አረጋዊ እኮ ሃገራቸው ሮም ነው ደብረ ዳሞ የጸሎት ባዕታቸው ነው፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ስዱስም እንግዲህ ኦሮሞና ጉራጌ ክልል ስላሉ እነሱም የኛ ናቸው ይበሉና አልኳት፡፡ አቡነ አረጋዊ እኮ የነ አቡነ ተክለ ሐይማኖት የምንኩስና አባት ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሐይማኖት ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው በደብረ ዳቦ ተራራ ላይ ነው፡፡ አቡነ አረጋዊ በጽድቃቸው እንኳን ለኢትዮጵያ ለዓለም የጸለዩ የዓለም አባት ናቸው፡፡ እንኳን እሳቸው አክሱም ተወልደው ሹም ውሃ በሚባለው ቦታ በየቀኑ ሌሊት ሲፀልዩ ባህሩን ያበሩት የነበሩት ዘራቸው ከገበዘ አክሱም ነው የሚባሉት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እንኳን አክሱምን ለቀው ወደ ዋልድባ ሲሄዱ አንዲት ጧፍ አብርተው ከአክሱም ዋልድባ በመግባታቸው ዛሬ በዋናነት ዋልድባ ገዳም በዓመት አንድ ጧፍ እየያዘ አክሱም እንደሚያበረክት ሌሎችም የአቡነ ሳሙኤል ገዳማት እንዲሁ እንደሚሰሩ ይነገራል፡፡ ያሁንን ባለውቅም ዋልድባ የጐንደር ክፍል እንደነበረ ጽድቃቸው ለመላው ኢትዮጵያ እንጂ ለትግራይ እንዳልነበረ፡፡ እኛ ሀገር ከነበሩ ቅዱሳን ውጪ የምናከብራቸው ፣ የምንማፀናቸው በሙሉ ሀገራቸው ሌላ ቢሆንም ፈረንጅ መጥሮ ያንግሳቸው እንዳላልን፣ አማራና ኦሮሞ ይሳደባሉ ለሚለው የማያውቅ ግለሰብ መሳደቡ እንደማይቀር ለዚህም የዛግዌ ነገሥታትን ንግሥና ወደ ቀዳማዊ ምንሊክ የንግሥና ዘር እንደሚመለስ ትንቢት የተናገሩ አቡነ ተክለ ሐይማኖት በሮሃ ግለሰቦች እንደሚወቀሱ በማስረዳት እኔ አቡነ አረገዊ ዘርህ አማራ ነው ሳይሉ ከዚህ በፊት ብዙ መከራ ደርሶብኝ እንደረዱኝ መከራየን እንዳራቁልኝ ነግሬ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው እኛ ሀገራችን በሰማይ ነው፡፡ ማለትም አንድ መንግስተ ሰማይ እንደሆነ መለያየት እንደማንችል በማስረዳት ከተለያየን በኋላ ይሄን በሽታ የምነግርበት ድረ ገጽ የለኝ እንዴት ዝም እላለሁ በፌስ ቡክ ላይ ፖስት አደርገዋለሁ ስል ወንድም ዳንኤል ሃሳቡን በማንሳትህ በጣም ነው የተደሰትኩት፡፡ ያየሁትም ማንም ሰው አስተያየት ሳይሰጥበትም ነበር፡፡ ቶሎ በፃፍኩት ስልም አስቸኳይ ሥራ ይዞኝ ተመልሼ ሳየው በርካታ ወገኖች አስተያየት ሰጥተውበትም አየሁ፡፡ በጣም ጥሩ ትምህርት ነው አንሳሳት በመጨረሻም በማቴ. 12፣25 ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም። ይለናልና እኳን መንግስተ ሰማያትን በምንወርስባት ቤተ ክርስቲያን ይቅርና ምድራዊ ሕይወትን በምንኖርባት ሀገራችንም መለያየታችን አያዋጣም፡፡ ወንድም ዳንኤል ወቅታዊ ጉዳዮችን ስለማንሳትህ በሃገራችን ስንቅ ያለቀበት አንድ ገበሬ ያለውን ስንኝ በማንሳት ሃሳቤን እቋጫለሁ፡፡ በቡሄ በቆሎ ደርሶለት በላና ባለ ሰባት ልብሱ በቆሎ ባልነበር ዘንጋዳስ ቀውላሌ አስወስዶኝ ነበር እንዳለው ወቅታው መድሃኒት ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ስላበዛሁት ይቅርታ፡፡
ዲ/ን ዘላለም
ዲ/ዳንኤል ክብረት በትውልዱ ውስጥ ከታዩት ጎበዝ ጸሐፊዎች አንዱ አንተ መሆንህን መመስከር ይቻላል፡፡ነገር ግን በአንድ ብሔር ላይ ተለይቶ በዓለማዊና መንፈሳዊ ጦማሪዎች የሚቀነቀነውን አግላይና ዘረኛ አካሄድ ለማስታገስ የሰራኸው ሥራ በቂ አይደለም፡፡እንዲያውም ብዙ ጊዜ አንተም ተደራቢ ሆነህ ከጀርባ እናይሀለን፡፡የእነሱን ጩኽት ተከትለህ በማስተጋባት፡፡
ReplyDeleteአሁንም ከቻልክ በደጀሰላምና በአንድ አድርገን የሰለቸንን እና አሁንም በሐራ ዘተዋሕዶ በመቀጠል የአንድ ብሔር ተወላጅ አባቶችን በማኅበር ቀናኢነት እያሳበቡ ከሌሎች ለይቶ ጥፋታቸውን እያጋነኑ የማሳደድ አባዜ እንደታላቅነትህ ተግሳጽ ቢጤ ብትሰጥ ጥሩ ነው፡፡
አንተ የምትቆጣው በሥጋ ተለይተውን በመንፈስ ሕያው ስለሆኑ አባቶች ብቻ ከሆነ ግን አካሄድህ “ይሄን አለ” ለመባል ብቻ እንደሆነ ቆጥሬ ነው የማልፈው፡፡ከስምዓ ጽድቅ አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ ብሎግ ከፈትን እያሉ ወንጌልን ሳይሆን ወንጀልን በመዝራት የካሕኑን አመኔታ ስለሚሸረሽሩ ወጣኒዎች አንድ በል፡፡በተቆርቋሪነት ሥም ስሜታችን እየተጎዳ ነው፡፡
አቤቱ ለስድብ ቃል “ቃለ ሕይወት ያሰማልን” ማለትን ያስለመዱ የስድብ አፎችን አስታግሥልን!!
ወንጀል እንደ ወንጌል ማንበብ የመረረው ወንድምህ ….
ነቅዐጥበብ ሠዐረ
Ante menafik afihin atizegam?
Deletefesam hula taric atawkm
ReplyDeleteWhy do not you say only 'taric atawkm'. The first words are not to the standard of this blog or any social media. They will reduce your weight.
Deleteወይ አንተ ሰው እስኪ እግዚአብሔር ያቆይህ!!!
ReplyDeleteSuch 'racist' opinions should not be motivating factors for writing, I believe.
ReplyDeleteኧረ አሁንም የማይማር ትውልድ አለ እነዝህ ያንተን ጽሑፍ የምነቅፉ ሰዎች ውስጣቸው ትልቅ የማይድን የዘረኝነት እና ታላቅ ነኝ በሚያስብል ነቀርሳ ተይዘዋል በፍጹም የምድኑ አይመስሉም
ReplyDeleteኧረ አሁንም የማይማር ትውልድ አለ እነዝህ ያንተን ጽሑፍ የምነቅፉ ሰዎች ውስጣቸው ትልቅ የማይድን የዘረኝነት እና ታላቅ ነኝ በሚያስብል ነቀርሳ ተይዘዋል በፍጹም የምድኑ አይመስሉም
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን። ያላወቅነውን ነገር ስለነገርከንና ስላሳወቅከን አሁንም እናመሰግንሃለን። ያኑርህ። ኑርልን። እድሜና ጤናውን ይስጥህ። አሜን።
ReplyDeletefetera yimesilal yihe!!!! እኔም ሰው ላለማጋጨት ብዬ ያለኝን ሳልዘረዝር እንዴው በደፈናው ደውዬለት መምጣት አልችልም እንዳለኝ ነገርኩት፡፡engdih yihen siyanebu yitalalu malet new eko. yam hone yih ergiti new anidand sewoch bezeregninet kufu menfes yetetelekefu aliyam demo kalewum yepoletica tikusat anitsar endezih liyasibu yichilal honom gin adelem keanid biher yikirina ke ebet ebet enkuan le kidusan yemisetewu bota yileyayal. egna sefer le gebriel tilik boata ale lelawu sefer demo le mikael enga bet ke mariyam yebelete le kidane mihiret tilik bota ale lelawu bet demo le bahita. "የኛ ታቦት ሲሆንኮ እነ እንትና አይመጡም" ene bebekule endih yemilu sewoch alu biye alamnim. yalewun tinish chigir abizto erasin le andinet tekorkuary adirgo lemasayet yetetsafe yerasin misl ginbata yimesilal.
ReplyDeleteቃላት ስንጠቃ በዛ ላይ መጥፎ ተጠራጣሪ መሆን እንዴት አይነት በሽታ ነው:: ይቅር ይበላችሁ
Deleteይሄ የዘረኝነት ጉዳይ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡ በዘመነ እና ሰፊ አገር እየኖሩ እንደዚያ ጥብብ ማለታቸው የጤንነት አይመስለኝም፡፡ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ያሉ ዜጎች ናቸው፡፡ ልንፀልይላቸው ይገባል፡፡ ወደ አገር ቤት ቢመጡ እና ቢሰነብቱ…ይህች ሀፈረ እግዚአብሄር ከዚ ደዌአቸው ትፈውሳቸው ነበር፡፡
ReplyDelete"ወንድሞች ሆይ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይኖር አንድ ልብ አንድ ሃሳብ እንዲኖራችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትስማሙ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኃሁ" ... የመጀ/የሐ/ጳዉ/መል/ወ/ቆሮ ም 1፤10
ReplyDeleteDiacon Daniel egiziabher abizito yistih tebark
ReplyDeleteDiacon Daniel egiziabher abizito yistih tebark
ReplyDeleteKale heiwote yasamahe kaenaBatasabehe
ReplyDeleteyewshet lijoch
ReplyDeleteDiacon Daniel egizabher yebarekeh. hulgezi yemetanesaw rese betam astemari new. egiziabher enanem kemognatelena kzeregenet yetebeken.
ReplyDeleteእኔም በዚህ አጋጣሚ የአቡነ አረጋዊ ተዓምር እንድናገር እድል አገኘው ከስምንት (8) ዓመት በካኩማ ስደት ካምብ ውስጥ ዘመዴ ለሆቴሏ በጥዋት ተነስታ በትልቅ ድስት ወጥ ለመስራት ሥጋውን ለመክተፍ እንዲመች ገንፈል እያረገች እኔ ቤተክርስትያን ተሳልሜ ስመለስ ዛሬ ዕለቱ ማነው የሚታሰበው አለች ሥጋውን እያማሰለች አበነ አረጋዊ አልኳት እሳም የነእንትና ታቦት ብላ ከአፋ ሳትጨርስ ድስቱ ምንም ሳይነካው ተገልብጦ እጃን ሲያቃጥል እኔ እና ባለቤቷ አጠገቧ ቆመን እሷ ስትጮህ ምንም እርዳታ ማድረግ አልቻልንም ምን እንደያዘንም አናውቅም ከዚያ ቦሃላ በየወሩ ታዘክር ጀመረች.
ReplyDelete...ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡...
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባረክህ! ቃለ ህይወት ያሰማልን! ጽሁፉ ትልቅ ቁም ነገር የያዘ አስተማሪ ነው፡፡ ምናልባት ለኔም የመጀመሪያ ጊዜየ ነው ስሰማው ትግራዋይ- ለወንድ ትግራዋይቲ- ለሴት የሚለው የቃላት ማስተካከያ ካልሆነ በስተቀር ለጤነኛ ሰው ይሄ ጽሁፍ እንከን ይወጣለታል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ነገር ግን እኔን የሚገርመኝ የተወሰኑ አስተያየት ሰጭዎች አስተያየት ነው፡፡ እንዲያው ወደፊት የሚቻል ከሆነ የብዙ አንባቢ አስተያየትንም ለመቀበል እንዲቻል በአንድ ነክ (click) በቻ እስማማለሁ ወይም አልስማማም (like or dislike) ለማለት የሚያስችል ኣማራጭ ቢኖረው ይቻልና ይሻል ይሆን?
ReplyDeleteእግዚአብሄር መቼም እግዚአብሄር ነው የእግዚአብሄር መንገድ የሚያሳዩ ሰዎች ደግሞ እነርሱም የተባረኩ ናችው:: አንተ ደገሞ አንዱ ነህና እግዚአብሄር ይባርክህ::
ReplyDeleteHi, Daniel I like your idea but why all Tigray priest opened churches with this name. In addition that all Tigray going to these churches. Why they don’t participate other church. Furthermore if someone goes their church, they never open their place to other some churches preached by Tigrigna and they song by Tigrigna In addition that after the ceremony they never talk Amharic or English to participate others.
ReplyDeleteHi, Daniel sometimes some Ethiopian not represent the majority Ethiopian. I know 5% present of Ethiopian follow this idea but 95% don’t follow the idea. But you hear this situation from many people. Most of Ethiopian never goes church but they talked about the situation in addition that all protestant preacher teaches about the 5% Ethiopian Orthodox believer so all the people spread to attack our church. In other hand the current Ethiopian government supporter they talk about this situation to divide the Ethiopian people. Sampling is the best way to destroy the majority idea. For example in USA 97% of the people not support gay marriage and only 1% of the people are gay but the gay activist spread their idea around the world. So when you write something please specific the percentage. Thank you for your concern.
ReplyDeleteWell said. Please think of our first father and mother from which we have been descended and all of us are equally humans. Why do we discriminate each other? Who do you think will benefit from this racist thinking? As I could understand what Dn. Daniel wrote is very good and all of us have to build on this novel ideas against wrong ones.
ReplyDeleteWhat will be your reason for not telling your friends the actual feeling of yours there in Australia if you are going to write it anyways. Have you asked them why they are doing it? Don't you think it is important to know what causes them to react as such?
ReplyDeleteqaliwot yaemalin
ReplyDeletekale hiwot yasemalin! Mistrun Tibebun yebelete yigletsilih!
ReplyDeleteሰላም ለኩልክሙ!
ReplyDeleteወይ አንተ ሰው እስኪ እግዚአብሔር ያቆይህ!!!
ReplyDeleteወይ አንተ ሰው እስኪ እግዚአብሔር ያቆይህ!!!
ReplyDeleteከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡ ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
ReplyDeleteወገኖቼ አበሾች ስንባል ሁልጊዜ ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ዙሪያውን መዞር እንፈልጋለን እናማ ችግሩን ለምን በትክክል አናስቀምጠውም እጅግ ኃላ ቀር የሆነ አስተሳሰብ አለ! እራሳቸውንና ዘራቸውን እደ ጥንቱ ኦሪታውያን ለክህነት የተመረጡ የሚመስላቸው ከነሱ ውጪ ፖለቲከው አይሳካም ብለው ያስቡ የነበሩ አሁን በዚህኛው መድረክ ሲሸነፉ ጉዳዮን ወደ መንፈሳዊ ህይወት ያመጡ በተለይ የፖለቲካ ምሽጋቸ ከቅንጅት ጋር የነበረ በተፈጠረው ችግር ዞረው ማህበረ ቅዱሳን ብለው ሥራቸው ግን የረከሰ በየቦታው ተሰግስገው ያሉ የአባቶቻቸው ልጆች ችግር ይመስለኛል፡፡ በጣም የሚገርመኝ ሌላው ነገር ከአምሐራና ከትግራይ ውጪ ሌላው ህዝብ ሲነዱት የሚነዳ ነው እንዴ ለምን ቢያንስ ገለልኛ ሆኖ ስህተቶችን አካፋውን አካፋ በማለት አይገልፀውም መቼም ከሁለቱ ትክክለኛ ፍርድ መጠበቅ ይከብዳል ምክንያቱም የስልጣን ወራሴ ትግላቸውን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን እየጎተቱት ስለሆነ ማለቴ ነው
ReplyDeleteQalihiwot yasemalin lantern erejim edme legal libe yesten!
ReplyDeleteመረዳታችን እንደየሰዎች አመለካከት ይመስለኛል አንቺ/አንተ/እርስዎ እየሱስን ቤተክርስቲያን እንዳስተማረችን መጠን ልንጠራ አንችላለን ዋናው ቁም ነገሩ ሁሉ አሁን እንደተገለፀው ሳይሆን በተማርነው መለኩ ጠርተነው የማንጠቀምበት ብቻ ከሆነ የአፍ ክርስቲያን መሆኑ ስለማይቀር እርስዎ /አንቺ/አንተ እኔ ደስ አይለኝም መልስ አይሆን እየሱስ ሐብታምና ደሐ ብሎ ሳይለይ የሁሉም አዳኝ መሆኑን ስለማምንበት ባጠራር ላይ ችግር የፈጠርኩ አይመስለኝ ስመ እግዚአብሔርን ስንጠራ በጥንቃቄ ነው የተባለበት ምክንያት አረዳድ ለኒ የሚመስለኝ መሐላ ላይ ነው እየሱስ ጊታ ነው የጊቶችም ጌቶች ብዬ ባመሰግነው የሚያስከፋ አየመስለኝ ጥንቃቄው አጠቃቀሙ ላይ ነው የሚመስለኝ
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል፡ ቃለ ህይወትን ያሰማልን፡፡ እንደ ሙሁር የጻፍከውን ጽፈሃል፤ ልብ ያለው ደግሞ ልብ ይበል፡፡ አለበለዚያ ከነ ችግራችን ሳያምርብን ዘመናችን ይፈጸማል፡፡ ያስቀመጥከው ጽሑፍ አንድ እርምጃ ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ ነፍስ ወከፍ ምዕመናን የሚመለከተንን የቤት ስራ ለመስራት ድርሻችንን መውሰድ አለብን፡፡ ትናንት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በማታው መርሃ ግብር ኮርስ ከተነሳው የውይይት ነጥብ አንዱ ይህ ነበር፡፡ ይህ ችግር ከባዱ የቤተ ክርስቲያናችን ነቀርሳ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ክርስቶስ የተሰቀለው ለሰሜኑ ወይም ለደቡቡ፤ ለምዕራቡ ወይንም ለምስራቁ አልነበረም፡፡ የመፍትሄ ባለቤት እግዚአብሔር ይታረቀን፡፡ ያበርታህ፡፡
ReplyDeleteሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
ReplyDeleteIngidih "and jil yetekelewun shih likawunt ayneklewum"
ReplyDelete1yaregen
ReplyDeleteእኔ ባለሁበት ኢሮፕ ፡ በየከተማው የመንግስትና የተቃዋሚ ታቦት አለ፡፡
ReplyDeleteከሚሳለመው የሚቀድሰው እንዳትሉ!
EGZIABHER yitebkih yibarkh hulem
ReplyDeleteEthiopia ende dabo kircha yekoraresechiw bezemene minellik 2nd new ! haset yemil sew kale masreja makreb ytebekbetal
ReplyDeleteነገሩን ካነሳኸው አይቀር የሚባለው እንዲህ ነው።በውጭ አገራት ያሉ ቤተክርስቲያኖች የመለስ ዜናዊ ወይም የትግራይ እና የእግዚአብሔር ወይም የኢትዮጵያ በመባል ነው የሚታወቁት።በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል የመለስ ዜናዊ ወይም የትግራይ በመባል የሚታወቁት ማምለኪያ ቤቶች የሚገነቡት በትግራይ ልማት ማህበር ኢንዶውመንት ፈንድ ፎር ዘ ሪሀቢሊቴሽን ኦፍ ትግራይ ሲሆን አንተን መሰል ሰዎች ካላች ሁበት መጥታች ሁ ትግሬዎች ቤተክርስቲያን ሰብካች ሁ ትመለሳላች ሁ እንጂ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን አትረግጡም።ምክንያቱም ገንዘብ የላትም።ልዩነቱና የልዩነቱ ምንጭ ይህ ሆኖ ሳለ ታቦትን የትግሬ የ አማራ ያልከው ውሸት ነው።ታቦት ላመነበት ታቦት እንጂ ዘር የለውም።እንዲያ የሚያስብም የለም።የመለስ ወይም የትግራይ ቤተክርስቲያ የዘር መድሎ የነገሰባት፥ውሸት የማያሳፍርባት፥አገልጋዮቿ በ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር የከበሩባት፥የሰው መታረድ የማያሳስባቸው ቁስ አምላኪዎች የሞሉባት ናት።ምደባውም በዘር እና በገንዘብ መሆኑን አሳምረህ ታውቃለህ።ልዩነቱ ይህ ብቻ ነው እንጂ ከአቡነ አረጋዊ ወይም ከ አቡነ ተክለ ኃይማኖት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም። ችግሩን ከስር መሰረቱ አንስቶ ማቅረብ እንጂ ከትልቁ ችግር የመጡ ትናንሽ ችግሮችን እያነሱ ዋናውን ችግር ማስረሳት ጥሩ አይደለም። አሸዋ ላይ ቤት ሲሰራ ዝም ብሎ አይቶ ሲያልቅ የሚቀባው ቀለም ላይ አስተያየት ማቅረብ አይነት የሚመስሉ ተራ ጉዳዮችን አታንሳ።የምታነሳ ከሆነ ልዩነቶቹን ከመጀመሪያው ጀምረህ ማንሳት።ያኔ ሁሉም ይማርበታል።ጥፋተኛም ጥፋቱን ስ ህተተኛም ስ ህተቱን ሊያውቅ በሚችል መልኩ እውነተኛ ሆነህ አቅርብ።ማንሳት ከነበረብህ ታቦታቱን ሳይሆን ሰዉ ወደ ዘር ቆጠራ ለምን ገባ፥ማን ጀመረው ፥ማን ተጠቀመ ማን ተጎዳ የመሳሰሉትን ብታነሳ የችግሩ ምንጭ ይታወቃል።መፍት ሄም ይበጅለታል።
ReplyDeleteእጅግ በጣም አድርገን ነው የምናመሰግነው ዲ.ዳኒኤል ጥሩ ነገር ማንበብ ካቆምን ቆይተናልና እባክህን ይህንን አቅምህን አትንፈገን ቀጥልበት አደራህን በአሁኑ ሰዓት በዘረኝነትና በመለያየት የተመረዘው የብዙ ኢትዮጵያዊ አመለካከት ትቀይራለህና፡፡ ቃለ ሂዎት ያሰማልን!
ReplyDeleteእባካችሁ ወገኖቼ ከሁሉ አስቀድመን የክርስትናችን መሠረተ እምነት የሆነውን በቅዱስ መጽሐፍ የተገለጠልንን የቤተክርስቲያናችንን ትምህርት (ዶግማና ቀኖናውን) ለይተን በእምነት ከሚያስተምሩን አገልጋይ አባቶች ጠንቅቀን በመረዳት እንመን፡፡ ከእምነት የሚገኘውን መልካም ሥራ በመንፈሰ እግዚአብሔር መሪነት እንድንሠራ ትህትናንና መከባበርን ገንዘብ እናድርግ፡፡ መለያየትንና ነቀፋ የሆነውን የሥጋ ሥራ መገለጫን በማስወገድ ለሌሎች መልካም አርአያ ለመሆን የቅዱሳንን የወንጌል ተጋድሎ ሕይወት አብነት ይሁነን እንጂ በመጠላላት ጌታችንና አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አናሳዝን፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ እንዲህ ይለናል፡-
ReplyDeleteከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ።ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ቅንዓትና አድመኛነት ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል። (ያዕ.3፡13-18)
ከእንግዲህ በዘመኑ በተሰጠን ይህን ዘመናዊ መገናኛ ዘዴ እንደ ክርስቲያን ብዙዎችን ለማነጽ የሚጠቅም ከጥፋት ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚገኝበትን የጽድቅ ሥራ በኃላፊነት እንሥራበት፡፡ ከዚህ ውጪ የሆነ ክፉ ጥላቻ ግን የዲያብሎስ ግብር መሆኑን ተረድተን ከአምላካችን የፍርድ ቅጣት በማምለጥ፤ በዘመናችንም ለእግዚአብሔር አምላካችን ከዚህ ዓለም ክፋት ሥራ የተለየንለት የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች እንሁን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Selam Dn,Daniel God bless you and your wonderful thought. We all are blame for the Ethiopian Orthodox Church Separation, by mixing up our political view ,flashes desire and wish with the eternal and spiritual life. If we are the followers of Jesus Christ, we have to obeyed his words and rules practically, through love of our bothers and sister's, because he crucified him self for the love of the world, we have to respect our difference and brotherhood, because he thought us respecting each other by washing the feet of his followers and so on. Please Our Ethiopian Father's ,Mother's, Brother's and Sister's this is the right time to learn from our mistake and take correct action, We all are belonging to his kingdom if we do the right things in our little year( century), If we miss this fruitful short time we all are thrown to eternal fire, So please please don't trying to use our bad political separation idea to the clean and united spiritual thought.
ReplyDeleteAmelake Kidusan ,Sele Entu Kidese Dingele Mariam ,Sel Kidusan Melaeketu ena Tsadika Semaeta . Hagerachenen Kemeleyayete Beshita Yitebeken. Amen
ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡
ReplyDeleteDo Good Leave the Rest to God. May God help us never depart from As.
ReplyDelete