Monday, October 20, 2014

የአውስትራልያ ትምህርት በረከቶች ለአፍሪካ፡- ዕድሎችና ተግዳሮቶች(ሪፖርታዥ)

ርብራብ
ኃይለ ልዑልና ዶ/ር ብርሃነ ከቀድሞው የአውስትራልያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኬቪ ሩድ ጋር
በየሀገሩ ስዞር ለሀገራቸውና ለወገናቸው ልዕልና ያለው ሥራ የሚሠሩ፣ ወግ ያለው ታሪክ ያላቸው፡፤ ከመንደርተኛነትና ወንዘኛነት ድንበር ተነጥቀው በሉላዊነት መንበር ላይ የተቀመጡ፣ ከምድጃ ሥር ወሬ ርቀው ዓለም ተኮር ነገር ውስጥ የሚዘውሩ ዜጎቻችንን ሳይ ትፍትፍ እላለሁ፡፡ እሥራኤሎች በልዩ ልዩ ሀገር ሆነው ለሀገራቸው የሠሩ ዜጎችን ታሪክ ሲጽፉ ‹የኛ ሰው በዚህ ቦታ› የሚሉት ዓይነት ርእስ ይሰጣሉ፡፡ ‹የኛ ሰው በደማስቆ› እንዲል ማሞ ውድነህ፡፡


ባለፈው ኀሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓም እናንተ አቦን ስታከብሩ እኔ ደግሞ እዚህ ሜልበርን ለየት ያለ ግብዣ ደረሰኝ፡፡ የጋበዘኝ የአፍሪካና አውስትራልያ ማኅበር(African Australian Association - AAA ) ዋና ዳይሬክተሩ በሆነው ኃይለ ልዑል ገብረ ሥላሴ በኩል ነው፡፡ ኃይለ ልዑል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ካበረከተቻቸው አዳጊ የማኅበረሰብ መሪዎች አንዱ ነው፡፡ ከ ላ ቶቤ የኑቨርሲቲ በ2000 በዓለም አቀፋዊ ልማት ማስተርስ ያገኘ፣ በ2008 ከሜልበርን ዩኒቨርሲቲ በማኅበረሰባዊ ፖሊሲና አስተዳደር በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ ሰው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከ22 ዓመታት በፊት በሜልበርን እንድትተከል ከመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን ጋር የተላከውና ዛሬ በአውስትራልያ ለምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይዋን ያስቀመጠው ኃይለ ልዑል አፍሪካ በአውስትራልያ ገንዘብ፣ ዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንድትጠቀም በአውስትራልያ የሚገኙ የአፍሪካ ዳያስጶራዎችም አህጉራቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ የተመሠረተውን የአፍሪካ አውስትራልያ ማኅበር ከመሠረቱትና ከሚመሩት ልሂቃን አንዱ ነው፡፡
በሚኖርበት በቪክቶርያ ግዛት ለአፍሪካውያን የመሪነት ኮርስ ለመስጠት የሚያስችል መርሐ ግብር እንዲቀረጽ ከዶክተር ብርሃን አሕመድ ጋር የተጋ፣ ሥራውም ውጤታማና ተቀባይነት አግኝቶ እስከ 2018 የሚዘልቅ መርሐ ግብር በቪክቶርያ መንግሥት የተያዘለት፤ እስካሁንም ከ30 የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ 140 አዳጊ የአፍሪካ ማኅበረሰባዊ መሪዎችን በዚህ መርሐ ግብር ማስመረቅ የቻለ ፕሮጀክት ለመዘርጋት የቻለ ሰዋችን ነው፡፡

የፉት ስክሬይ ማኅበረሰብ የሥነ ጥበብ ማዕከል የቦርድ አባል፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የአውስትራልያ ማኅበረሰቦች የሚያካትተው Ethnic Communities’ Council of Victoria ሊቀ መንበር፣ የአፍሪካ የሐሳብ ማዕከል (African Think Thank) ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ማኅበረሰቡን እያገለገለ ነው፡፡ ለዚህና ለሌሎቹ አገልግሎቶቹ  የዊኒስተን ቼርቺል ፌሎው - ሽልማት(2008)፣ የዊልያምሰን ማኅበረሰብ አመራር መርሐ ግብር- ሽልማት(2009)፣ የጋራ ብልጽግና አገሮች የሚኒስትሮች አማካሪ ኮሚቴ ለአፍሪካ - ሽልማት(2012)፣ እጅግ የተዋጣለት የማኅበረሰብ መሪ - ሽልማት(2011)፣ እንዲሁም በብዝሐ ባሕል የተዋጣለት ሥራ ለሠሩ የአውስትራልያ ሰዎች የሚሰጠውን (Meritorious service in the community) ሽልማት ከቀድሞው የቪክቶርያ ገዥ(Premier) በ2004 ተቀብሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ትምህርትና ሥልጠና፡ ዕድሎችና ተግዳሮቶች

ዘንድሮ በሜልበርን ከተማ ቪክቶርያ ዩኒቨርሲቲ ኣዳራሽ የተካሄደው የአፍሪካ አውስትራልያ ማኅበር ዋና አጀንዳ በትምህርትና ሥልጠና ላይ ያተኮረ ነበር (Doing Business in Africa: Opportunities in International Education and Training)፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ከቪክቶሪያ ግዛት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከኩባንያዎችና አፍሪካ ላይ ከሚሠሩ ተቋማት የመጡ ተወካዮች ሐሳቦቻቸውን፣ ሥራዎቻቸውንና ያጋጠማቸውን ነገር አቅርበው ነበር፡፡ በተለይም ባለ ሥልጣናቱ አውስትራልያ ከአፍሪካ ጋር እስከ ዛሬ የነበራት ግንኙነት ማዕድንን የተንተራሰ እንደነበርና ከ65 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆነ የአውስትራልያ ኢንቨስትመንት በአፍሪካ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የትምህርት ግንኙነት ለአውስትራልያ 4ኛው የገቢ ምንጭ መሆኑንና ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በየዓመቱ ለሀገሪቱ ሲያስገኝ ከ100 ሺ ሰዎች በላይ ደግሞ በሥሩ ተሠማርተው ገቢ እያገኙበት መሆኑን ነግረውናል፡፡ አውስትራልያ ትምህርት አሰጣጧን በማስተካከል፣ የተሻለ ልምድ ካላቸው ሀገሮች ደረጃዎችን በመውሰድ፣ ለተማሪዎች የሚሻሉ መንገዶችን በመዘርጋት በዓለም ከሚመረጡ የትምህርት ተቋማት ወገን የሆኑ ተቋማትን ለመመሥረት መቻሏን ነግረውናል፡፡ ‹በዓለም ላይ የትምህርት ልዕለ ኃያል ሀገር - super power in Education› ብለዋታል፡፡ የትምህርት ጥራትና ደረጃ አካዳሚያዊ ነጻነትን፣ በባለሞያ የሚመራ የትምህርት ሥርዓትንና ገለልተኛ የሆነ ገምጋሚ አካልን እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡ እኔም የሀገሬን ከፍተኛ ተቋማት እንዳስብ አድርገውኛል፡፡


 በተለይም ከትምህርት ተቋማት የመጡት ባለሞያዎችና ባለሥልጣናት በአንድ ነገር ላይ ተስማምተው ሲናገሩ ነበር፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ላይ የበጀት፣ የሰው ኃይልና የአሠራር ድጋፍ በማድረግ የአውስትራልያ መንግሥት በየጊዜው የተሻለ ሥራ ቢሠራም ሁለት ነገሮች ግን ለውጤቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች ደግሞ የሚገኙት ከተማሪዎች ነው፡፡ እነርሱም ፍላጎትና የተፎካካሪነት ስሜት(Interest and Competitiveness)፡፡ የምዕራቡ ዓለም ተማሪዎች የተሻለ ትምህርትና የትምህርት መሣሪያዎች ቢሟሉላቸውም ፍላጎትና ተፎካካሪነትታቸው ግን የእስያ ተማሪዎችን ያህል መሆን አልቻለም፡፡ በዚህም የተነሣ በአነስተኛ ወጭና ባልተሟሉ ሁኔታዎች ውስጥ የሚማሩት የእስያ ተማሪዎች የተሻለ ፍላጎትና የተሻለ ተፎካካሪነት ስለሚያሳዩ በተሻለ በጀት ከሚማሩት የምዕራቡ ተማሪዎች ይልቅ በውጤትማነት የተሻሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተከበሩ ፊል ሀኔውድ የተባሉ የሥነ ትምህርት ባለሞያና የአውስትራልያ ዓለም ዐቀፍ የትምህርት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዳሉት ለተማሪዎች ውጤታማነት ወሳኞቹ ነገሮች ከውስጥ የሚመነጩት ሁለቱ ኃይሎች - ፍላጎትና የተፎካካሪነት ስሜት ናቸው፡፡

የአፍሪካ ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው ፍላጎትና ተፎካካሪነት የተሻለ በመሆኑ በአውስትራልያ ትምህርት ቤቶች በተመደበላቸው ትምህርት ጊዜ በመጨረስ የአፍሪካ ተማሪዎች ውጤታማ ሆነዋል፡፡ የሀገሬው ተማሪዎች የመጨረስ ዐቅም 70 ከመቶ ሲሆን የአፍሪካ ተማሪዎች ግን 94 በመቶ ነው፡፡

ይህንን ልምድ በመያዝም በስኮላርሺፕ ብቻ ከመገናኘት ይልቅ ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን ለመሥራት እየጣሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም 20 የአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ከ51 የአፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመሥረት ይህንን ሥራ ለማስፋፋት እየሠሩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በተመለከተ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች ድጋፍ ያለፈ ሪፖርት አልሰማሁም፡፡ በዚህ ረገድ ኬንያና ናይጄርያ የአንበሳውን ድርሻ መያዛቸው ነው የተነገረው፡፡

የአፍሪካ ተማሪዎች የበጀትና ትምህርት አመራር ድጋፍ ከተሰጣቸው የተሻለ ፍላጎትና ተፎካካሪነት አላቸው፡፡ በመሆኑም የአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በአውስትራልያ የትምህርት ደረጃና ጥራት የሚሰጡ መርሐ ግብሮችን በአፍሪካ ለመዘርጋት እየተሞከረ ነው፡፡ ይኼ ሁኔታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መልካም ዕድል በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚጠየቁትን ዝግጅት ከኤምባሲው በመውሰድ በጋራ ለመሥራት ቢነሡ ሀገራቸውን ለመጥቀም ይችላሉ፡፡ ተማሪዎቻችንን እንዲህ ባለ ዕድልና ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንጅ በስብሰባ ብቻ ብቁ ዜጋ ማድረግ አይቻልምና፡፡

click here for pdf

ሚሲስ ጃኩሊን ዝዋምቢላ የተባሉ በዚምባብዌ የቀድሞ የአውስትራልያ አምባሳደር እንደገለጡት የአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ገንዘብና የሰው ኃይላቸውን ይዘው፣ በአውስትራልያ ደረጃ ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት አራት መሠረታዊ ችግሮች ገጥመዋቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ብዙዎቹ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ሳይሆኑ የማስተማሪያ ዩኒቨርሲቲዎች (lecturing rather than research) መሆናቸው ከዓለም የጥናት ሥራዎች አስተዋጽዖ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 1% ብቻ እንዲያበረክቱ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኞቹ የሚያሠለጥኑት ለመንግሥት ሥራ(educating for public sector) እንጂ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚችሉ መስኮች አይደለም፡፡ ሦስተኛ ሆኖ የተነሣው የአፍሪካ ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ችግር ሊፈታ የሚችል፣ ራስ ተኮርና ራስ ፈጠር የሆነ መንገድና ደረጃ በመከተል፣ ዘላቂና ወጥ የሆነ፣ ብሔራዊ ቀለም ያለው የትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመቅረጽና በርሱም በቁርጠኛነት ከመመራት ይልቅ አውሮፓ ተኮር(Euro centric) መሆናቸው ነው፡፡ አራተኛው ብዙዎቹ ሀገሮች ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቂ በጀት ለመስጠት ባለመቻላቸው  በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለው ልዩነት የሰርተፊኬቱ ደረጃ ብቻ እንዲሆን ማድረጉ ነው፡፡ በአንድ ጥናት ላይ እንደተመለከተው ከአፍሪካ ዓመታዊ ገቢ(GDP)1% ብቻ ለከፍተኛ ትምህርት ይመደባል፡፡

ፕሮፌሰር ዴቪድ ሞሪሰን የተባሉ የሞርዶክ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምክትል ቻንስለር አውስትራልያ በሚከተሉት ጉዳዮች በአፍሪካ ትኩረት እንደሰጠች ገልጠዋል (በአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር ለምታስቡ ተማሪዎች ወይም በጋራ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለመሥራት ለምትፈልጉ ተቋማት)፡፡ በአርብቶ አድር ልማት፣ በእርሻና ማዕድን፣ ለእናቶችና ሕጻናት ደኅንነት የዐቅም ግንባታ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ከአውስትራልያ ተቋማት ጋር አብረው ከሚሠሩ ወይም ከሚያጠኑ ጋር ለመቀናጀት መርሐ ግብር አላቸው፡፡ ‹‹ትልቁ ችግር›› አሉ ፕሮፌሰሩ ‹‹የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ምርምር ላይ ትኩረት ስለማይሰጡ የጥናት ባሕላቸው ዝቅተኛ ነው(underdeveloped research culture)፡፡ በዚህም ምክንያት የአውስትራልያ ተቋማት እንዲደረግ የሚፈልጉት ጥናትና የአጥኝው ዐቅም አለመጣጣም ይከሰታል፡፡ እኒህ የጥናት ባለሞያ ደጋግመው እንደገለጡት ‹የአንዲት ሀገር የመፍጠር ዐቅም በሳይንስ መሠረቷ የተጽዕኖ ዐቅም ይወሰናል(the country’s ability to innovate is influenced by the size of its science base)፡፡››

በአሁኑ ጊዜ 4.5 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በየሀገሩ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ ተማሪዎች በፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካና ሳዑዲ ዐረቢያ ነው የሚማሩት፡፡ በአውስትራልያ ከሚማሩ ዓለም ዐቀፍ ተማሪዎች መካከል ቻይናውያን 27.4፣ ሕንዶች 10.4፣ ቬትናማውያን 5.1 በመቶውን ይዘዋል፡፡ በአውስትራልያ ትምህርት ቤቶች ለመማር ከሚያመለክቱት መካከል አፍሪካውያን ከ1 - 15 ከሚገኙ ዋና አመልካች ሀገሮች ውስጥ የሉበትም፡፡ ለዚህ ዋና ምክንያቱ ቪዛ ለማግኘት ያለው ጣጣ፣ በቂ የመኖሪያ ወጭ ሽፋን አለመኖር(10 በመቶዎቹ ብቻ በተማሪዎች መኖሪያ ይኖራሉ)፣ አውስትራልያ እስያ ላይ በማተኮሯ፣ በአፍሪካ የሚገኙ ትምህርት ኤጀንሲዎች ስለ አውስትራልያ ትምህርት ዕድሎች በቂ ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑ፣ ቻይና ለአፍሪካ የተሻለ ስኮላርሺፕ በመስጠቷ መሆኑ ተገልጧል፡፡ በአውስትራልያ ለመማር የሚያስቡ ይኼንን ገጸ ድር ቢያዩት ተመክረዋል -

   www.studyinaustralia.gov.au

ከ2012 ጀምሮ ከ8000 በላይ የአፍሪካ ተማሪዎች በአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም 1500ዎቹ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ 40ዎቹ የዶክትሬት ዲግሪ እየሠሩ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የአውስትራልያ የትምህርት ተቋማት 14000 አፍሪካውያን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው፡፡ የአውስትራልያ መንግሥትም በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 5000 የማስትሬትና የአጫጭር ኮርሶች ዕድል ለአፍሪካውያን ማዘጋጀቱ ተገልጧል፡፡ ለአጫጭር ኮርሶች ይህንን ድረ ገጽ በማየት መጠቀሙ መልካም ነው -

www.australiaawardsafrica.org

ለቢዝነስ ጉዳዮች ደግሞ ወደዚህ ይዙሩ

www.dfat.gov.au

በጉባኤው ከነበሩት አቅራቢዎች ለአፍሪካውያን ስኮላርሺፕ ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ የተነሣው ለትምህርት የሚመጡ ተማሪዎች ወደ ሀገራቸው ያለመመለሳቸው ችግር ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም የስኮላርሺፕ ዕድላቸው የተንጠለጠለባቸው ሀገሮች አሉ፡፡ አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች በኮሪደር ወሬ ኢትዮጵያ ከእነዚህ አንዷ መሆኗን ነግረውኛል፡፡

ነፍሱን ይማረውና ጋዳፊ በአንድ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ ‹የአደጉትን ሀገሮች የአየር መበከል፣ የጦርነትና የፖለቲካ ችግር እንደምንካፈለው ሁሉ የእነርሱን ሀብትና ዕድገትም መካፈል አለብን‹ ብሎ ነበር፡፡ ናይጄርያውያንና ኬንያውያን ከአፍሪካ፤ ሕንድ፣ ቻይናና ቬትናም ከእስያ የአውስትራልያን የትምህርት ስጦታና ዕድል በሚገባ እንደሚጠቀበሙት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትምህርት ተቋማትና በአውስትራልያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስጶራ ተጋግዘን ዕድሉን ብንጠቀምበትና ለሀገራችን ሰው ብናፈራበት መልካም ይመስለኛል፡፡ በተለይም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና መካከለኛ ተቋማት ከአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለመሥራት የተዘጋጀውን መርሐ ግብር ተሻምቶ በመጠቀም በትንንሹ ዳቦ ከምንራኮት ትልቁን እንጀራ እንቁረስ፡፡ ወደ 310 ሚሊዮን ዶላር ለስኮላርሺፕ መንግሥት መመደቡን አብሥረዋል በጉባኤው ላይ፡፡ መልካም ዕድል፡፡

ሜልበርን፣ አውስትራልያ


33 comments:

 1. I am impressed. Keep up with the great work and thank you for your services Haile Leul

  ReplyDelete
 2. That's a great news. Thanks Daniel for your fantastic report and we have so many unsung heroes.

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሄር ይስጥህ ብዙ ግዜ እኮ እንሞክራለን ግን ያው ታውቀው አይደል ችግሩን

  ReplyDelete
 4. tebareke selesetehene mreja...

  ReplyDelete
 5. This is amazing! Keep the momentum. It is great to see people working hard and getting good results. Most of the problem with us is we talk a lot and work little. We talk about the 'what should be' but very reluctant to put that in to action. You are our role model and champion. Thanks Daniel for posting this great news.

  ReplyDelete
 6. በሚጠቅመን መረጃ ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ሁለ ገብ ሰው በመሆንህ ልቤ ባአንተ ኮራ !
  ቸር ያሰማልንን !

  ReplyDelete
 7. I was wondering how the Australia prime minster was the first foreign pm to wish for Ethiopian new year with full of his heart. I got an answer now, that was the result of Haile Luel and others long time effort.
  Thank you Dani, for sharing this.

  ReplyDelete
 8. Thank You Dani !! Nice Job as usual. Long Life !!

  ReplyDelete
 9. Replies
  1. What do you mean? it doesn't make any different writhing ኤድያ if you don't read poltics or something fight you don't like. Shame on you, he doesn't get paid but he did whatever he can for Ethiopian people. I feel you are not a human being because you say ኤድያ. Please pray for you not for us or Ethiopian people. We love Daniel, he is our messager from God.

   Delete
  2. Don't expect all people enjoy good story. Some are sad when they read nice story such as this. Others prefer to read sad stories and nonsense politics and we should embrace them. When you achieve something good you find many opponents and the above writer is one need urgent help.

   Delete
 10. Hi, Daniel most Ethiopian people don't like to read or give feedback for this kind of idea. So please write that motivate us. For example comment on goverment, church, leader or company. We need someone like you to motivate us to destroy this goverment and his followers. Aster Tadese from Kolfe

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኅቴ አሁን ይኼ አስተያት ከጽሑፉ ጋር ምን አገናኘው፡፤ ዳንኤልን ሞቲቬት አርገን ምናምን ከምትዪ የራስሽን ጣጣ እዚያው ለምን ራስሽ አትወጭም፡፡ ባንቺ ቤት ማስመታትሽ ነው፡፡

   Delete
  2. Thank you so much Aster, evenif I don't agree with your idea I am very glad when I see our sister participate on poltics. Good luck and let me know if you need my support. Abebe Lakew from Kolfe

   Delete
  3. ' የራስሽን ጣጣ እዚያው ለምን ራስሽ አትወጭም' wow exelent, Daniel wrote the fact so if Aster want or not he doesn't care. He lives for Ethiopian people. I think she works under the current goverment. I know her very well. God bless Daniel and his family.

   Delete
  4. that is non sense girl, ደሞ ብለሽ ፖለቲከኛ ልታደርጊው ወደድሽ.....I know what you r planning... live him out of this.... Daniel knows what he is doing!!!

   Delete
  5. Change will not come if we wait for some other person or some other time. We are the ones we've been waiting for. We are the change that we seek.
   Barack Obama

   Delete
  6. come on Aster, please declare prayer and fasting as your name symbolizes the great lady. Do you really want Dani to continue his blog from kality? please be measured when you write unless you have other agenda.

   Delete
  7. Aster
   I respect your opinion but I don’t understand your motives and generalisations.
   You have the right not to read or express your lack of interest as you may not be interested to read a good story that motivate and inspire our young Ethiopians. Your suggestion to create a link between this article and the government seems bizarre and you probably need help and nothing to do with Danny. Danny tried to share his experience in Australia and shade the light for others to learn from the conference. If you are interested about politics please go to other websites which can cater your interest. Finally I would encourage you not to make a general statement on behalf of all readers. Don’t tell us we all are interested to read about politics and not interested articles such as this which is absolutely wrong. WE ARE VERY HUNGRY TO LEARN FROM OTHER EXPERIANCES AND THIS IS ONE! DANNY PLEASE SHARES WITH US SIMILAR ARTICLES WHENEVER YOU TRAVEL SO THAT WE ARE ENLIGHTEN FROM OTHER EXPERIANCES.

   Delete
 11. ዉድ ዲያቆን ዳንኤል!!
  መልእክቶችህ እጅግ መልካም ናችዉ፡፡ እንደ አንድ መልካም ዜጋ ያስተላለፍከዉ መልእክት ልብ ላለዉ እጅግ ትልቅ ነዉ እንደሁልግዜም፡፡ መልእከቱ በቀጥታ ይመለከተናል የምንል አብዝቶ በመትጋት መንገዶቹን በሚገባ በመመርመርና በመሞከር እድሉን ተጠቅመን ራሳችንንም ሀገራችንንም እንለዉጥበት፡፡ ሌሎችም መንገዱን እንዲያዉቁና እንዲከተሉ እናመቻች፡፡
  እግዚአብሄር ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 12. you said you are anonymous at the end you are Aster.What a miss up?

  ReplyDelete
 13. ብዙዎቹ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ሳይሆኑ የማስተማሪያ ዩኒቨርሲቲዎች (lecturing rather than research) መሆናቸው ከዓለም የጥናት ሥራዎች አስተዋጽዖ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 1% ብቻ እንዲያበረክቱ አድርጓቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 14. አስታዋሽ አያሳጣህ!

  ReplyDelete
 15. Thank you Dn. Daniel.
  1) The Australian scholarship option for Ethiopia is limited to mainly Agriculture.
  2) I had a chance to bring to Professors from two different universities of Australia for short term training of colleagues in our university, here in Ethiopia. I asked (rather I beg) my university middle and higher managers to use the opportunity for creating University-University linkage. It was tiresome and finally failed.
  Zeberga

  ReplyDelete
 16. I gud!!!!!!!! Sint ayinet sew ale? degmo beatsede nefs yalutin kidusan abatochachin endih mekefafel jemeru?? yasazina?
  Please God return back us to the former unity.

  ReplyDelete
 17. Thank you Daniyee from the bottom of my heart. You are exceptional.I am glad to have you in our life.

  ReplyDelete
 18. Thank you Daniel. long live!!!!!!!!

  ReplyDelete
 19. ዲ/ን ዳንኤል በጣም እናመሰግናለን።
  ሊቀ ዲ/ን ሀይለልዑል በርታ ቀጥልበት።

  ReplyDelete
 20. Dear Daniel, we really thank you for this important information concerning schorships in Australias' Universities. for your information, Addis Ababa University has a joint programme in computer science and information technology with Melbourne Institute of Technology (MIT), which they give a name African Vertual University (AVU).

  ReplyDelete
 21. so wonderful Dn Danial Thank you Helel Lule keep it up.

  ReplyDelete