Sunday, October 12, 2014

‹ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለም፣ ካህናቱ›

ቅዱስ ጳውሎስ ተከስሶ በቂሣርያው ገዥ በፊስጦስ ፊት በቀረበ ጊዜ አይሁድ ለብቻቸው ቀርበው በቅዱስ ጳውሎስ ላይ ይፈርድበት ዘንድ ጎትጉተውት፣ እነርሱ ማስረጃ ያሉትንም አቅርበውለት፣ ሕጋቸውንም ጠቅሰው ማሳመኛ አቅርበውለት ነበር፡፡ አሕዛባዊው ገዥ ፊስጦስ ግን እግዚአብሔርን እናውቃለንም፣ እንፈራለንም ከሚሉት አይሁድ ተሽሎ ያሉትን ከማድረግ ራሱን ከለከለ፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ጉዳዩን አቀረበላቸው፡፡ ፊስጦስ አይሁድ ያቀረቡትን ስሞታ፣ ውትወታና ክስ ተቀብሎ በቅዱስ ጳውሎስ ላይ ያልፈረደበትን ምክንያት ለአግሪጳ ሲገልጥለት ‹‹ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም፣ ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፣ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም›› ብሎ መሆኑን ነግሮታል (የሐዋ.25÷16)፡፡
ይህ በሮማውያን ዘመን እጅግ የታወቀውን ራስን በእኩል ደረጃ የመከላከል መብት በተመለከተ ሮማዊው ታሪክ ጸሐፊ አፒያን (95-165ዓም) በጻፈው Civil War በተሰኘው መጽሐፉ (3:54) ላይ ‹‹የምክር ቤት አባሎች፣ ሕጉ የተከሰሰ ሰው የተከሰሰበትን ሰምቶ በእርሱ ላይ ከመፈረዱ በፊት መልስ የመስጠት መብት አለው ይላል›› ሲል አሥፍሮት ነበር፡፡ ፊሊክስ የጠቀሰው ይኼንን ነው፡፡ አበው በትርጓሜያቸው ‹አሕዛብ ፍርድ ይጠነቅቃሉ›› ሲሉ የመሰከሩት እንዲህ ያለው የሮማውያንን ሕግ ነው፡፡ ለዚህ ጥንቁቅ የፍርድ ሥርዓትም ሲሉ አያሌ የሮማውያንን የፍተሕና የፍርድ ሐሳቦች በቤተ ክርስቲያን የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ (በቀኖና) እንዲገቡና እንዲሠራባቸው አድርገዋል፡፡

ይህንን የምትተረጉምና የምታስተምርን ቤተ ክርስቲያን እንወክላለን የሚሉ ሰዎች ናቸው ሰሞኑን ተሰብስበው ተከሳሹ በሌለበት ፍርድ ሲሰጡ ያየናቸው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ተሳሳተ ተብሎ እንኳን ቢሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአርዮስና ለንስጥሮስ፣ ለመቅዶንዮስና ለሰባልዮስ የሰጠችውን መብት ቤተ ክህነቱ ለማኅበረ ቅዱሳን ሊነፍገው አይገባም ነበር፡፡ በቀደዱላቸው ቦይ መንጎድ፣ ተጠልቷል ብለው በሚያስቡት ላይ መፍረድ ሃይማኖታቸው የሆነ፤ ፓትርያርኩን ምን ያስደስታቸዋል እንጂ የትኛው እውነት ነው ለሚለው የማይጨነቁ ሰዎች የክስ መዓታቸውን ሲያዘንቡ ማኅበሩ መልስ እንዲሰጥ ዕድል ሊሰጠው ይገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰዎቹ ለበዓሉ የሚስማማውን ቀለም ትተው ለባለ ሥልጣኑ የሚስማማውን ቀለም መረጡ፡፡ ሊቁ ክፍለ ዮሐንስ ‹ካህን ከመሆን እረኛ መሆን ይሻላል› እንዳለው ከቤተ ክህነት ፊልክስ ተሽሏል፡፡
ፊሊክስ ለቅዱስ ጳውሎስ፣ ሠለስቱ ምእት ለአርዮስ፣ ማኅበረ ኤፌሶን ለንስጥሮስ የሰጡትን ዕድል ቤተ ክህነቱ ለማኅበረ ቅዱሳን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለምን?
ሰዎቹ እውነቱን ለመጋፈጥ ዐቅም አንሷቸዋል ማለት ነው፡፡ የሚሉት ነገር የሆኑ አካላትን ስለማስደሰቱ እንጂ እውነት ስለመሆኑ ርግጠኞች አይደሉም፡፡ ስለዚህም ተከራካሪያቸውን ለመስማትና የእነርሱ ‹እውነት› ሲሞገት ለማየት ዐቅም ያንሳቸዋል፡፡ ወይም ደግሞ
ከክርክሩ በፊት ውሳኔውን ወስነው ጨርሰዋል፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስን ለደርግ አሳልፈው የሰጡት የቤተ ክህነት ሰዎች እንዲህ ነበር ያደረጉት፡፡ ፓትርያርኩን አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ውሳኔውን ወስነዋል፡፡ ነገር ግን ለውሳኔው ምክንያት መፈለግ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህም አቡነ ቴዎፍሎስ ሠሩ ያሏቸውን ጥፋቶች ለብቻቸው ተሰብስበው፣ ‹በደላቸውን› ዘርዝረው፣ እርሳቸው መልስ ሊሰጡ በማይችሉበት ሁኔታ ለደርግ አስተላለፉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለብቻቸው መሰብሰብ የፈለጉት፣ የፓትርያርኩንም መልስ የመስጠት መብት የነፈጉበት አንዱ ምክንያት ፓትርያርኩ በሚሰጡት መልስና በሚያቀርቡት ማስረጃ እውነታቸው ነፋስ ያየው ገለባ እንዳይሆንባቸው ነው፡፡ ወይም
እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ሥራ አይደለም እየሠሩ ያሉት፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲበጠብጡ የኖሩት ካህናተ ደብተራ (ከቤተ ክህነት ደመወዝ እየወሰዱ ለቤተ መንግሥት ሲሠሩ የኖሩ ካህናት ነን ባዮች) ዋናው መለያቸው የሚሠሩት የራሳቸውን ሥራ አለመሆኑ ነው፡፡ የመለካዊነት ጠባይ ስላላቸው ሌሎች ተናገሩ የሚሏቸውን ይናገራሉ፣ ፈጽሙልን የሚሏቸውን ይፈጽማሉ፤ አውግዙልን የሚሏቸውን ያወግዛሉ፤ አጽድቁልን የሚሏቸውንም ያጸድቃሉ፡፡ የሚሠሩት ሥራ የላኳቸውን ሰዎች ማርካቱን እንጂ የሚያስከትለውን ነገርና የሚያስከፍለውን ዋጋ አያውቁትም፡፡ እነዚህ ነበሩ አባ በጸሎተ ሚካኤልን ያሰደዱት፣ እነዚህ ነበሩ አባ ፊልጶስን ያንከራተቱት፣ እነዚህ ነበሩ እጨጌ ዕንባቆምን ለልብነ ድንግል ከስሰው ምንም ባላጠፋው ጥፋት ‹ጉንጽ› በተባለው ዓለም በቃኝ እስር ቤት ያሳሠሩት፤ በኋላም ለሀገሪቱ ጥፋትን ያመጡት፡፡ ጥይት የመታው ሰው ተናድዶ ‹‹ምነው እንዲህ ታበላሸኝ›› ቢለው ‹‹እባክህ እኔ አይደለሁም፣ እኔ ተተኮስኩ እንጂ ተኳሹ ሌላ ነው፤ እኔ መልክተኛ ነኝ›› አለው፡፡ ‹‹ተኳሹ የት አለ?›› ቢለው ‹‹እርሱማ አይታይም ተደብቆ ነው የሚተኩሰው፤ እርሱ ስለሚደበቅኮ ነው እኔ የመጣሁት›› አለው ይባላል፡፡
ወይም እነዚህ ሰዎች ስንፍናቸውን የሚያሳይባቸውን፣ ድካማቸውን የሚገልጥባቸውን፣ ሊያጠፉት ወድደዋል፡፡ ሰውዬው ዶሮውን በጦም አርዶ ለምን አረድከው ቢባል ‹‹እሱ ነው ጠዋት እየተነሣ መንጋቱን የሚያሳብቅብኝ፣ አርፌ እንዳልተኛበት፡፡እርሱ ባይጮህ ኖሮ መንጋቱን ማን ያውቅ ነበር? ተኛህ ብሎስ ማን ይከሰኝ ነበር›› አለ አሉ፡፡ ከመንቃት ይልቅ ማንቂያውን ማጥፋት፡፡ የ13ኛው መክዘ የደቡብ ሐዋርያ አቡነ አኖሬዎስ ታላቁ በካህናተ ደብተራ ተከስሶ ወደ ንጉሥ ሰይፈ አርእድ የቀረበበት ክስ አስቂኝ ነበር፡፡ ‹‹ከንጉሡ የሚበልጥ ቤተ ክርስቲያን ሠርቷል›› ነበር የተባለው፡፡ ጉዳዩን ሊያጣራ የሄደው የጉዳም አለቃ ያገኘው ቤተ ክርስቲያን ግን እንደተባለው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ከክሱ ንጹሕ መሆኑ ቅጣቱን አላስቀረለትም፡፡ ከገዳሙ ወጥቶ በወለቃ በረሃ እንዲከራተት ሆኗል፡፡ ምናለ ከንጉሡ የሚበልጥ ቤተ ክርስቲያን ቢሠራ? የሚያስመሰግነው እንጂ የሚያስነቅፈው አልነበረም፡፡ ለካህናተ ደብተራ ግን ይኼ ስንፍናቸውን ይገልጠዋል፣ እንደ አውራ ዶሮውም መተኛታቸውን ያሳይባቸዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ አሁን መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆሟል፡፡ የሚቀርቡት ክሶች ለምን ቀረቡ ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን በአይሁድ አደባባይ ፍርድ ሲጓደል፣ እንደ ጲላጦስ ሚስት የሚያስጠነቅቅ ያስፈልጋል፡፡ ገለልተኛ አካል አቋቁሞ የተባሉትን ያጣራ፡፡ ራሱ የማኅበሩ አመራር ለተከሰሰበት መልስ ይስጥ፡፡ አሕዛባዊው ፊሊክስ ለቅዱስ ጳውሎስ የሰጠውን መብት ሲኖዶሱ ለማኅበሩ መስጠት አለበት፡፡ ተጣርቶ በተገኘው ማስረጃና ምስክር መሠረት ውሳኔ ይሰጥ፡፡ ጥፋተኛው ይታረም፤ እውነተኛው ይገለጥ፡፡
በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ቀራንዮ መድኃኔዓለም አለቅነት ተሾመው የሄዱትን አባት ካህናቱ አስቸገሯቸው፡፡ ለጥቂት ጊዜ የተላኩበትን ሊሠሩ ሞከሩ ግን አልሆነም፡፡ በመጨረሻም ለንጉሡ እንዲቀይሯቸው አመለከቱ፡፡ ንጉሡም ምነው ምን ገጠመህ? ቢሏቸው ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ ሰቃይ ተሰቃይና የመስቀያ ቦታ አንድ ሲገናኙ ያ ነው ክፉ ዘመን፡፡
ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡ 

164 comments:

 1. it it really critical time for our church and our country. 2007: puching factors for change dominated. It seems it is time God.

  ReplyDelete
 2. ካህናተ ደብተራ- እነዚህ ነበሩ አባ በጸሎተ ሚካኤልን ያሰደዱት፣ እነዚህ ነበሩ አባ ፊልጶስን ያንከራተቱት፣ እነዚህ ነበሩ እጨጌ ዕንባቆምን ለልብነ ድንግል ከስሰው ምንም ባላጠፋው ጥፋት ‹ጉንጽ› በተባለው ዓለም በቃኝ እስር ቤት ያሳሠሩት፤ በኋላም ለሀገሪቱ ጥፋትን ያመጡት፡፡

  ReplyDelete
 3. ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 4. kalehiwet yasemalen

  ReplyDelete
 5. mesematunes joro yalew yisema

  ReplyDelete
 6. ‹ካህን
  ከመሆን እረኛ መሆን ይሻላል›

  ReplyDelete
 7. Thank you Diaco Daniel. God bless you. The true man speaks without taking side. Again, God bless you.

  ReplyDelete
 8. In a way, what goes around comes around to MK. When MK was so fiercely labeling many innocent believers "tehadesos" and causing them to be expelled out of the church in the name "guarding the faith", it didn't appear that the same dismay come after hunting MK leaders.
  Well, live and learn!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Only those "tehadesos" once were proving themselves not to be one.
   Leban Leba kalalut ... endeser lekotraw yechelal.

   This is not the time to look things at individual level at this point it is more of YeHager guday!

   Delete
  2. Dear who are the innocent believers? Aba Yonas, Tsigie Sitotaw?... Lets be genuine! Give us documents that show MK's wrong doing?

   Delete
  3. AG from Virginia ,USAOctober 22, 2014 at 5:00 AM

   Egzeabher bemyawekew, bête kerstyanen eyatefat yalew ke betekrstian eyebela agelgelot lay yelelew ke atbya jemero eske teklaye bête kehnet yetsegesge eamani new. esti beyalachehubet debre tazebachehu kehone tsehafi, kuteter, hisab shum, genzeb yaje , ke atbya weche yale astedadari yasekedesal yekorbal yakorbal ? mahlet yekomal?....ende fabrica serategn enkua seat akbero bero aygeba... endew tenegro ayalkem.
   ene yewech sew aydelehum bedikuna yagelegelku HTTC be thewology temerke besbket yagelegelku negn.
   ye embeten yemelja melse ke amlak etebekalehu?

   Delete
  4. ዳኒ አመሰግናለሁ ፍርዱ ትክክል አይደለም፡፡ግን ስሜታዊ ሁነህ ነው የጻፍከው አባቶችን ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠትህ አግባብ አይደለም፡፡

   Delete
  5. ሞክሼ Anonymous ዲ/ን ዳንኤል ጽሑፍ ላይ ምንም ስድብ አላነበብኩም። ከየት ፈጠሩት እርስዎ? የእርስዎ 'አባቶች'ስ ምን ሰዳቢ ያስፈልጋቸዋል? ሥራቸው አለ አይደለም እንዴ! ለሚሳደብስ ምን ነጋሪ ያስፈልገዋል?
   እውነቱ እና መልካሙ ምክር ሁሉ እየቆረቆረው "ይህስ ይሳደባል" ማለት ለካ ዛሬም አለ! እኔስ ከንፁህ አምላክ ከክርስቶስ ክስ እና ፍርድ በኋላ የተወገደ መስሎኝ ነበር። ደግሞም "ሊቀ ካህናቱን እንዴት ትናገረዋለህ!" ብሎ በጥፊ ሚማታ ይኖር ይሆን?
   የኔታ ዳንኤል - የመረጣቸውን ቅዱሳኑን ያከበረ፤ ስለ ክቡር ስሙ እና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ በተቀበሉት መከራ ያጸናቸው የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቅዎ። የጻድቃኑ ቃልኪዳን አጋዥ ይሁንዎ።

   Delete
 9. እግዚአብሄር ይርዳችሁ፡፡ እውነት ሁሌ ታሸንፋለች፡

  ReplyDelete
 10. THANK YOU DANI. Lib Yalew Lib Yibel

  ReplyDelete
 11. TheAngryEthiopian/ቆሽቱ የበገነውOctober 12, 2014 at 10:17 PM

  ስለደርግና ስለ አቡነ ቴዎፍሎስ ካነሳህ አይቀር፣ እስቲ ዘርዘር አድርገህ በሚቀጥለው ጡመራህ ላይ በደንብ የተቀናበረ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርብልን። ለግንዛቤና ለትምህርት ይረዳል - በተረፈ ተከሳሹ በሌለበት ሲካሄድ የነበረው የክስ ትዕይንት ይኼን ይመስል ነበር - (google - "The trial of Mahibere Kidusan" )

  PT 1 https://www.youtube.com/watch?v=KbbUXfbFsaU
  PT 2 https://www.youtube.com/watch?v=jejc0VNegi8
  PT 3 https://www.youtube.com/watch?v=A6bpGTYobug

  ReplyDelete
 12. Ewunet Belehal Dani danienet Lemesmat yetekebaw kesashe Honena yehulu abat tebelo Seletan yetesetew ye tewesenut agafariwoch Lemewedede yemiyashergedu seqaleyane ayehude abat. Bicha. Hono. Sigegne. Men Yedereg ferd keleyegnaw. Abat. Metebeke. New

  ReplyDelete
 13. Dani Ye seqaliyan kerestos ayehud mekeniyat Honew keresetosen lesekelat Biyadersutm alem Denobetal Yengnehko le lebiete Kerstiyan Edeget yemiyameta Sayehon yebiet Kerstiyanen Wudeket KemesatbYeserut Yepoletikegnochena Yeaderbayovh Siera new

  ReplyDelete
 14. "ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲበጠብጡ የኖሩት ካህናተ ደብተራ (ከቤተ ክህነት ደመወዝ እየወሰዱ ለቤተ መንግሥት ሲሠሩ የኖሩ ካህናት ነን ባዮች)"...

  ReplyDelete
 15. It is great God bless those who work for the best of our church

  ReplyDelete
 16. It is time to rise up and defend MK and the church. It is not enough to say " isu yametawin iskemelisaw initseliyalen" not at all. We were saying the same when they did it to Waldba monastery. Had it been we actually did something strong when they do it in Waldba they wouldn't have tried this one. Our brave grand and grand grand parents handed us down the church and our beloved country by giving their one life if needed . Not by hiding and saying what we are saying . Some times you got to give some thing more than prayer for God if needed. Nobody says I am going to pray if somebody unexpected and unwanted show up in ones doorstep to take what is inherently one's.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agree that Befekad Egzeyabhier eyetemeru, Beselot eyetagezue, we need to do something but, What do you suggest we should do?

   Delete
 17. I am surprised to see this article. It really touches the very heart of our wound. Many of people in the Protestant churches were dismayed by the EOC priests and leadership by their reckless resistance for the good things.Thank you Dani, you described them WELL!! If they change, I think many of us who are in the protestant society will return back to our mother church work for the good of our christian faith. these the so-called priests are the source of all troubles. They always looks the earthly gains, not the heavenly mission. kalehiwet yasemalin Dani!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Even though source of trouble, they are also the eye Christ.

   Delete
  2. የምን ጠጋ ጠጋ፡፡ ራስህን ችለህ ቁም፡፡ ፕሮቲስታንት ለመሆንህ ካህናቱን ማመካኘት የለብህም፡፡ የኦረቶዶክስ እና የፕሮቲስታንቱ ልዩነት እኮ አስተዳደራዊ አይደለም፡፡ በጣም ብዙ መሰረታዊ የእምነት ልዩነቶች አሉን፡፡የምን ቀዳዳ ፈልጎ መጠጋት ነው፡፡ መርሳት የሌለብህ ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችን ይዘህ ሁሉንም ካህናት ጥፋተኛ ናቸው ማለት በጣም ስህተት መሆኑን ነው፡፡ ግን ክርሰቶስን ስለሰው ብለህ ነው የምታመልከው? ካህናት ደግሞ የእግዚአብሔር አይን ናቸው- ቤተክርሰትቲያናችን እንዳስተማረችን፡፡ ግንዱን ትተህ ቅርንጫፉ ላይ አትንጠልጠል፡፡ ማስተዋል ይስጠን፡፡

   Delete
  3. የምን ጠጋ ጠጋ፡፡ ራስህን ችለህ ቁም፡፡ ፕሮቲስታንት ለመሆንህ ካህናቱን ማመካኘት የለብህም፡፡ የኦረቶዶክስ እና የፕሮቲስታንቱ ልዩነት እኮ አስተዳደራዊ አይደለም፡፡ በጣም ብዙ መሰረታዊ የእምነት ልዩነቶች አሉን፡፡የምን ቀዳዳ ፈልጎ መጠጋት ነው፡፡ መርሳት የሌለብህ ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችን ይዘህ ሁሉንም ካህናት ጥፋተኛ ናቸው ማለት በጣም ስህተት መሆኑን ነው፡፡ ግን ክርሰቶስን ስለሰው ብለህ ነው የምታመልከው? ካህናት ደግሞ የእግዚአብሔር አይን ናቸው- ቤተክርሰትቲያናችን እንዳስተማረችን፡፡ ግንዱን ትተህ ቅርንጫፉ ላይ አትንጠልጠል፡፡ ማስተዋል ይስጠን፡፡

   Delete
 18. እንዲህ የልብ መሻት የሚነግር ሰው እግዚአብሔር አያሳጣን!

  ReplyDelete
 19. ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ ሰቃይ ተሰቃይና የመስቀያ ቦታ አንድ ሲገናኙ ያ ነው ክፉ ዘመን፡፡
  ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 20. ንጉሡም ምነው ምን ገጠመህ? ቢሏቸው ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ ሰቃይ ተሰቃይና የመስቀያ ቦታ አንድ ሲገናኙ ያ ነው ክፉ ዘመን፡፡

  ReplyDelete
 21. This Group is forcing all orthodox Christians to join Maheber Kidusan and fight for our religious right.

  ReplyDelete
 22. አመሰግናለሁ ዳንኤል
  የክስ ሂደቱ የቀረበበት መንገድ ተገቢ አይደለም ያልከው ተገቢ ቢሆንም የማህበሩ አሁን ያለበት አካሄድ ግን ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ ብዙዎች የማህበሩን ገጽ እንጂ አካሉን አያውቁትም፤ ስለዚህ እሰኪያውቁት ድረስ ከሰው ህሊና ለማፍረስ ያስቸግር ይሆናል፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ማህበሩ ራሱን የቻለ አካል ነው ወይስ ከቤተ ክርስቲያናችን ስር ያለ፤ ምክንያቱም እየሰራ ያለው ሥራ አንድ ከቤተ ክርስቲያኒቷ ሥር ያለ ማህበር ያደርገዋል ተብሎ የማይጠበቅ ሥለሆነ /ማለት የፈለግኩት ተደጋጋሚ የሆነ የመዋቅ ጥሰት ነው/ ይህ ነው የቅዱስ ሲኖዶሱን የወደፊት ህልውና የሚፈታተነው ባይ ነኝ፡፡
  ባለፈው ዓመት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ከአጠገቤ ነበርክ እናም “ማህበሩ የእኛው ከሆነ በውስጥ ኦዲተር ለምን አይመረመርም” በማለት በመጋቤ ካህናት ኃይለሥላሴ ለተነሣው ጥያቄ የሰጠኸው በጭብጨባ የተደገፈ አጸፋ ከዚህ ጽሁፍህ ጋር አልጣጣም አለኝ፡፡
  እንደ እኔ እንደ እኔ ማህበሩ የቤተ ክርስቲያኒቷ አካል ነኝ ካለ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቷ መምሪያ በሚመራበት ሂደት መመራ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ሂደቱ እንኳን ባይጥመው ለማሳደግ መጣር እንጂ ተገንጥሎ “ዘመናዊ” አሠራርን እንከተላለን፣ የተማረ የሰው ኃይል አለን ተብሎ አሁን ያለው መዋቅር መናጋት የለበትም፡፡
  ቅዱስ ሲኖዶስም ይህንን በዚህ ጉባኤው ቢያሳውቅ እረፍት ነበር፡፡ በየዓመቱ ስንት ሥራ እያለ ስለ አንድ ማህበርና ስለ ተሐድሶ ብቻ መወራ አለበት እንዴ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wedaje, Ategebih neberku minamin alkina antenetihn gin Anonymous bileh seyimeh Tasfik. Daniel eko Yalew, Mahibere Yimtana Yetekesash dimitsun Yist new. Tekesash Sayinor Fird Ayiset new. Zebraqa Bite neh

   Delete
  2. I think you don't know who MK is .... you are writing because it is free. If you are really concerned to know what mk is doing you can be part of it then ...you will see what is going on.

   Delete
  3. Yeaserar chiger binor enkuan maheberun bemaferes meftehe yigegn yimeselhal. Y20 ameten lfat ymillion Christian gulber b1 qne yadarash sebseba maferes deg new bleh tamenalh? Manen yemitekem yimeselhal?

   Delete
 23. አቤቱ አምላኬ ሆይ መስጋና ለአንተ ይሁን፡፡

  ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማፍረስ የሚሯሯጡትን ወደ ህሊናቸው ይመለሱ ዘንድ አንተ እርዳቸው፡፡ አቤቱ አምላኬ ሆይ ለምን አባቶቸ ለዚች ከንቱ አለም ለስጋቸው አደሉ? ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ያነበቡትን ታሪክ እምን ውስጥ ከተቱት?
  " አባቶች " ለማንኛውም ስለእወነት ተናገሩ፡፡ እግዚአብሄር ልቡና ይሥጣቸሁ

  ReplyDelete
 24. እግዚአብሄር ይርዳችሁ::

  ReplyDelete
 25. ዳኒ! እነዚህ ሰዎች ሁሉም ኦርቶደያዊ ልቡ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር መሆኑንና እንደሌላው የማፈራረስ ሴራ ቀላል እንልሆነ በትዕቢታቸው ምክኒያት ሊረዱ አይችሉም

  ReplyDelete
 26. Ohhhhhhh great Dani egziabher yistish

  ReplyDelete
 27. "ሰውዬው ዶሮውን በጦም አርዶ ለምን አረድከው ቢባል ‹‹እሱ ነው ጠዋት እየተነሣ መንጋቱን የሚያሳብቅብኝ፣ አርፌ እንዳልተኛበት፡፡እርሱ ባይጮህ ኖሮ መንጋቱን ማን ያውቅ ነበር? ተኛህ ብሎስ ማን ይከሰኝ ነበር›› አለ አሉ፡፡ ከመንቃት ይልቅ ማንቂያውን ማጥፋት፡፡"

  ReplyDelete
 28. EGZYABHAR ulunme yayel!!!!!

  ReplyDelete
 29. በዚህ በጭንቅ ጊዜ እውነቱን የሚናገርና የሚጽፍ መምህር ኣሳጣን፡፡ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ስለዚህ ማህበር ከኛ በላይ ላሣር ሲሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ አሁን ግን ምነው ድመፃቸው ጠፋ ጎበዝ?

  ReplyDelete
 30. It hurts both, the Church and the Country. Both leaders should take care before making irreversible mess! Dn. Dani we really appreciate your concern & insight.

  ReplyDelete
 31. (ከቤተ ክህነት ደመወዝ እየወሰዱ ለቤተ መንግሥት ሲሠሩ የኖሩ ካህናት ነን ባዮች

  ReplyDelete
 32. ዳኒ!

  እኛ የአዋሳ ከተማ ሕዝቦች የታድሶ እኩይ ረብሻ አኮላሽተን ወደ ልማት ስንዞር ዳግም ሊያንራሩ የሚዳክሩት እዚያ የተፈጠረላቸውን አጣሚ ተገን በማድረግ መሆኑን ተገንዝበናል
  ዛሬም ከተላንቱ በተሻለ እንመከክታቸዋለን

  ReplyDelete
 33. Thanks DAN z Eagle EYE!!! U put it clearly:-MK has to respond and this kios has to come to the end.

  ReplyDelete
 34. 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፥15
  የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

  ReplyDelete
 35. መምህር ወመገስጽ ዘኢያደልዎ ለገጽ . . . እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን ሰቃልያንን ያስታግስልን

  ReplyDelete
 36. ጥይት የመታው ሰው ተናድዶ ‹‹ምነው እንዲህ ታበላሸኝ›› ቢለው ‹‹እባክህ እኔ አይደለሁም፣ እኔ ተተኮስኩ እንጂ ተኳሹ ሌላ ነው፤ እኔ መልክተኛ ነኝ›› አለው፡፡ ‹‹ተኳሹ የት አለ?›› ቢለው ‹‹እርሱማ አይታይም ተደብቆ ነው የሚተኩሰው፤ እርሱ ስለሚደበቅኮ ነው እኔ የመጣሁት›› አለው ይባላል፡፡

  ReplyDelete
 37. የኢህአዴግ ስውር እጆች… ዛሬ በግልጽ ታዩ፡፡ ቀን አለ ቀና ብለን እንሄዳለን፡፡ የመናፍቁና የድርጅታቸው ኢህአዴግ ስውር እጆች… ዛሬ በግልጽ ታዩ፡፡ ቀን አለ ቀና ብለን እንሄዳለን፡፡

  ReplyDelete
 38. ማህበረ ቅዱሳንን ማዋከቡ ይቁም !
  ትዉልድን በመልካም ምግባር የሚያንጹ ተቋማትን ማበረታታት ሲገባ ለምን ይዋከባሉ?
  ሁሉም ክርስቲያን አንግቦት ሊነሳ የሚገባዉ መፈክር "እኛ ሁላችን ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነን!" የሚል ነዉ::

  ReplyDelete
 39. ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 40. ካልደፈረሰ አይጠራምና አትጨነቅ

  ReplyDelete
 41. ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 42. ጥይት የመታው ሰው ተናድዶ ‹‹ምነው እንዲህ ታበላሸኝ›› ቢለው ‹‹እባክህ እኔ አይደለሁም፣ እኔ ተተኮስኩ እንጂ ተኳሹ ሌላ ነው፤ እኔ መልክተኛ ነኝ›› አለው፡፡ ‹‹ተኳሹ የት አለ?›› ቢለው ‹‹እርሱማ አይታይም ተደብቆ ነው የሚተኩሰው፤ እርሱ ስለሚደበቅኮ ነው እኔ የመጣሁት›› አለው ይባላል፡፡

  ReplyDelete
 43. ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማፍረስ የሚሯሯጡትን ወደ ህሊናቸው ይመለሱ ዘንድ አንተ እርዳቸው::

  ReplyDelete
 44. ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን
  በማደንበሽ
  እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 45. እንግዲህ የመጨረaዉ ዘመን መቃረቢያ “ተኩላ ከ በግ መለየት በማያስችል ሁኔታ የተወሳሰበ ይመስላል”፡፡

  እንግዲህ የመጨረaዉ ዘመን መቃረቢያ “ተኩላን ከ በግ መለየት በማያስችል ሁኔታ የተወሳሰበ ይመስላል”፡፡
  “ሰዎቹ እውነቱን ለመጋፈጥ ዐቅም አንሷቸዋል ማለት ነው፡፡ የሚሉት ነገር የሆኑ አካላትን ስለማስደሰቱ እንጂ እውነት ስለመሆኑ ርግጠኞች አይደሉም፡፡ ስለዚህም ተከራካሪያቸውን ለመስማትና የእነርሱ ‹እውነት› ሲሞገት ለማየት ዐቅም ያንሳቸዋል”፡፡
  እንግዲህ የመጨረaዉ ዘመን መቃረቢያ “ተኩላን ከ በግ መለየት በማያስችል ሁኔታ የተወሳሰበ ይመስላል”፡፡
  “ሰዎቹ እውነቱን ለመጋፈጥ ዐቅም አንሷቸዋል ማለት ነው፡፡ የሚሉት ነገር የሆኑ አካላትን ስለማስደሰቱ እንጂ እውነት ስለመሆኑ ርግጠኞች አይደሉም፡፡ ስለዚህም ተከራካሪያቸውን ለመስማትና የእነርሱ ‹እውነት› ሲሞገት ለማየት ዐቅም ያንሳቸዋል”፡፡

  ReplyDelete
 46. ‹‹...ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም››

  ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል፡፡
  እንደ እኔ ግን እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች መደናገጥ ያለብን አይመስለኝም፣ ዲያብሎስ እንዳይደሰት፡፡ ይልቅ እስራኤልን በኤርትራ ባህር ያሻገረ፣ የኢያሪኮን ቅጥር አፍርሶ ህዝቡን ለምድረ ከነዓን ያበቃ አምላክ፣ አሁንም ለለመኑት ቃልኪዳኑ ህያው ነውና በእምነት እንጽና፣ ወጀቡ ያልፋል፣ ፈርዖንም ይሸነፋል፡፡ ንቁም በበህላዌነ…

  ReplyDelete
 47. wondmi daniel lemhonu mahibere kdusan mindinewl ? min yiseral ? leman ? lebete khinet ? lemimenan ?

  melsehin intebkalen

  amesgnaleh
  demissie

  ReplyDelete
  Replies
  1. Pls visit this website:www.eotcmk.org

   Delete
 48. የክስ ሂደቱ የቀረበበት መንገድ ተገቢ አይደለም ያልከው ተገቢ ቢሆንም የማህበሩ አሁን ያለበት አካሄድ ግን ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ ብዙዎች የማህበሩን ገጽ እንጂ አካሉን አያውቁትም፤ ስለዚህ እሰኪያውቁት ድረስ ከሰው ህሊና ለማፍረስ ያስቸግር ይሆናል፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ማህበሩ ራሱን የቻለ አካል ነው ወይስ ከቤተ ክርስቲያናችን ስር ያለ፤ ምክንያቱም እየሰራ ያለው ሥራ አንድ ከቤተ ክርስቲያኒቷ ሥር ያለ ማህበር ያደርገዋል ተብሎ የማይጠበቅ ሥለሆነ /ማለት የፈለግኩት ተደጋጋሚ የሆነ የመዋቅ ጥሰት ነው/ ይህ ነው የቅዱስ ሲኖዶሱን የወደፊት ህልውና የሚፈታተነው ባይ ነኝ፡፡
  ባለፈው ዓመት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ከአጠገቤ ነበርክ እናም “ማህበሩ የእኛው ከሆነ በውስጥ ኦዲተር ለምን አይመረመርም” በማለት በመጋቤ ካህናት ኃይለሥላሴ ለተነሣው ጥያቄ የሰጠኸው በጭብጨባ የተደገፈ አጸፋ ከዚህ ጽሁፍህ ጋር አልጣጣም አለኝ፡፡
  እንደ እኔ እንደ እኔ ማህበሩ የቤተ ክርስቲያኒቷ አካል ነኝ ካለ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቷ መምሪያ በሚመራበት ሂደት መመራ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ሂደቱ እንኳን ባይጥመው ለማሳደግ መጣር እንጂ ተገንጥሎ “ዘመናዊ” አሠራርን እንከተላለን፣ የተማረ የሰው ኃይል አለን ተብሎ አሁን ያለው መዋቅር መናጋት የለበትም፡፡
  ቅዱስ ሲኖዶስም ይህንን በዚህ ጉባኤው ቢያሳውቅ እረፍት ነበር፡፡ በየዓመቱ ስንት ሥራ እያለ ስለ አንድ ማህበርና ስለ ተሐድሶ ብቻ መወራ አለበት እንዴ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ante dingay eras ahun yihen hasab beleh tedegagmewaleh?? ... kante aynetu ye woyane telalaki kezih belay aytebekem!!!

   Delete
  2. I think you don't know who MK is!!!

   Delete
 49. ‹‹...ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም››

  ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል፡፡
  እንደ እኔ ግን እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች መደናገጥ ያለብን አይመስለኝም፣ ዲያብሎስ እንዳይደሰት፡፡ ይልቅ እስራኤልን በኤርትራ ባህር ያሻገረ፣ የኢያሪኮን ቅጥር አፍርሶ ህዝቡን ለምድረ ከነዓን ያበቃ አምላክ፣ አሁንም ለለመኑት ቃልኪዳኑ ህያው ነውና በእምነት እንጽና፣ ወጀቡ ያልፋል፣ ፈርዖንም ይሸነፋል፡፡ ንቁም በበህላዌነ…

  ReplyDelete
 50. Thank you so much Daniel. If you like his idea please distribute to others. The best way to participate is copy and past it on your Facebook, ETV media, ESAT media and share for your friends. This fight is about our church not other group. There is no difference between us.

  ReplyDelete
 51. It is so sad to hear all these smoke screen! I thought Ethiopian Orthodox Tewahido Church is has a long history endearing all troubling times! [the era of yodit and Giragn] I seeing that many of us are thinking that the existence of EOTC is gravely dependent on the Mahibere Kidusan! How was we sang that "Tewahido nitsihit kidist emnetachin, nuri lezelalm tekebresh...."? I didn't know the existence of Mahiber Kidusan is so connected to the existence of this centuries old church! As for me, there is no coalition between the the two existences! Our church is more that anybody! I am not saying MK should be destroyed. As you said Dani, they may need to be given fair decisions. But, I don't agree with the notion that thinks that if MK is closed, EOTC is finished. It is so naive! MK is just one group in the church of thousands of monasteries, Debirs and school of wisdom! It shoud be treated like that! This is not the time to worry for this or that group. But, we need to discuss about the people who are taken by Arab and the likes funded wolves! Isn't it Dani?

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think you are the one who gave up by the arab and wolves. This false accusation is not directly from the church fathers; it is from others who want to kill the young generation by their own fathers and take the church with their members in the late future.

   Delete
  2. Hi knowing english is not knowing the sentence. He doesn't say anything about what you are acusing. He said it clearlyabout justice. Nither about the church Nor for MK.
   Please we know what you think.
   Belive it or not Mk is trying to protect the thousands of years church from its threats.
   So to fight the threats we need Mk badly.
   Danie Yedengel lege Eyesus Kirestos Lebona Yestachew. Egna endenesu tefaten anemegnem yemenamelkew adagnun enji gedayun aydelemena.
   Egziabher Ethiopian Yebark

   Delete
 52. Hi, Daneil
  I am not sure about the detail but their concern is money. They said that this organization run by itself instead of under the church rule and regulation. Is this organization has separate income that not belong to the church? Where come from that money? Is there any rule and regulation that allowed for this organization to have money separate from the church? Is there any agreement with the church to have this kind of benefit? Who is the leader of this organization? Who put him/her in this position, when established and why the church condemns them on public media instead of talking under the church? Why ETV or EBC gave them big coverage?

  ReplyDelete
 53. ewnetegnaw Amlak firdun iynesam bewstim bewchim laut yehaymanot abatoch metseley yehulachinim halafinet newna ebakachu firdun le Silasse seten betselot enitga!!!!!

  ReplyDelete
 54. OMG God bless you my beloved brother Daniel. You see, this is why Mahberekidusan must be vanished. Why? Because it brings such a bright person like you. A person who can stands for Truth, Country, Religion and... The world we are living is not welcomes a great person like you and religious guard like Mahberekidussan. The patriarch and Synods they only need to read you last paragraph.

  I love you my brother! I have been bleeding for the last couples of days and now all good!

  ReplyDelete
 55. ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡

  ReplyDelete
 56. ስለማይነገር ስጦታው እግዚዓብኄር ይመስገን!!
  ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት አንተን የስጠን አምላክ ይክብር ይመስገን፤ መልካም ብለሃል ጆሮ ያለው ይስማ!!

  ወንድሞቻችን ፈተናው የተጀመረው ዛሬ አይደለም፡ እናንተ ግን ለእምነታሁ እና ለቤተክርስትያን ባላችሁ ቅናት ራሳችሁን አሳልፋችሁ በመስጠታችሁ እግዚዓብኄር አምላክ በቸርነቱ እየጠበቀ ብዙውን ፈተና በጽናት እንድታሸንፉ ረድቱዋቹኋል ወደፊትም ይረዳችኋል። ስለዚህም በመልካም ሥራችሁ ጽኑ።

  ReplyDelete
 57. የጠላቴ ጠላት ለኔ ወዳጄ ነው ብላችሁ ማህበሩን ለመበተን ከተሀድሶ ጋር አንድነት የፈጠራችሁ ሁሉ እግዚአብሄር ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewnet bilehal eyazenkum yalehut bezih asitesasebachew new.

   Delete
 58. Egziabehar libon yestachew Orthodox bekirstose dem yetmeseretrch nat atinawotsme

  ReplyDelete
 59. Mehabere Kidusan(MK) is now getting it's own medicine. I have never been a fan of MK as they have been full of themselves and organized like the mafia. Because of them, " Sreate Kehenet" was distorted and people were getting "dikuna" in there 20's and 30's against the church's tradition and teaching. They also chased out several true orthodox Christians, accusing them being " tehadesos" with out any evidence. It is interesting to see Daniel now arguing that MK wasn't given a fair hearing while when he was at the helm of MK, his organization denied several true orthodox Christians the chance to challenge MK in public, rather teaming up with the same corrupt priests now accusing MK, let several faithful out of the church because they disagree with them. No sympathy for MK. The church has been there for several hundred years and will be there for several hundred more years. Comparing to the church history, MK's existence of 20 or so years is insignificant.
  The church is at a crossroad. Despite the increase in population size, the number of Orthodox Christians in the country is dwindling. Instead of expanding the gospel and bringing in new souls to the church, MK was busy chasing the Christians in the church and is partially responsible for the shrinking number of the faithful in the church. Time for MK to go. Thanks but no thanks.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Anonymous, your arguments So much Contradictory. you said "number of Orthodox Christians in the country is dwindling" and then you said "Time for MK to go".. These ideas clearly indicate your personality.

   Delete
  2. Your words reveal that you even don't know who MK is!!! know it before the critics!!! Shame on U!!!

   Delete
  3. @anonymous@ 10:06 AM: I don't see any contradiction in the argument. MK is partly responsible for dwindling the number of orthodox Christians in the country by chasing out every one who doesn't agree with them. And MK is an organization and the demise of the organization doesn't mean that its members will go away with the organization. If the members are going away from the church because of MK, then that is even a bigger problem for MK as they see MK above the church. I don't know if you are a "tenkway" to tell my personality by reading an argument on a tread. God bless you.

   @Anonymous@1:42 PM, dear brother, i don't have to say anything to you as you apparently said nothing. May God bless you.

   Delete
  4. It is interesting to see how the enemies of Tewahedo, the enemies of Dingel Mariam, the enemies of the Christ, led by Lucifer orchestrate an elaborate scheme to destroy the true saints of our time that the Lord handmade. Tehadso protestants are rejoicing exchanging gifts and congratulations! Sodomism, atheism, secularism and Protestantism have joined hands and are out at Qeranyo to re-crucify the Lord one more time.

   Forgive them Lord for, yet again, they know not what they are doing.

   Delete
 60. Kalehiwet yasemalen Dani

  ReplyDelete
 61. ተከሳሹ በሌለበት ሲካሄድ የነበረው ለተባለው እናንተ በሐስት ከሳችሁ ስንቱቹን ካህናት በሌሉበት አስወገዛችሁ ? እናንተጋ ሲሆን ነው እንዴ የፍርድ ሂደቱ ትክክል ኣይደለም ሚባለው ? እንደ አጋግ ስንቱችን ከማህጸነ ቤተክርስቲያን ጨፍጭፋችኋል ? ሞት መሪር ነው ቢሆንም የ ግፍ ጽዋችሁ ሞልቷል አሁን መጠጣት ትጀምራላችሁ ትረኛ ናችሁ : ተረኛ ነሽ ና እነዳትሸበሪ ስጠፊ አያለሁ ማቅ (ማህይም ቅለጭ) ደህና ሁኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የጠላቴ ጠላት ለኔ ወዳጄ ነው ብላችሁ ማህበሩን ለመበተን ከተሀድሶ ጋር አንድነት የፈጠራችሁ ሁሉ እግዚአብሄር ልብ ይስጣችሁ

   Delete
  2. ማህብረ ቅዱሳን ሲጠፋ ማየት አሰኜህ አይደል??? ተስፋህን ቁረጥ እሽ!!! እግዚአብሔር ማህበረ ቅዱሳንን አይደለም ከዚህ ሀሰተኞች ተራ ዉንጀላ ቀርቶ በእሳትም ዉስጥ ቢሆን ከቶ አንዳች ነገር ሳይሆን በሰላም ሊያሻግረዉ እንደሚችል አልገባህም ማልት ነዉ!!! ማህብረ ቅዱሳን ከእግዚብሔር ነዉና ጉዞዉን ሊገታ የሚቸል አንዳች አካል ከቶ ሊኖር አይችልም!!!

   Delete
  3. kalehiwot yasemalin

   Delete
 62. ባለፈው ዓመት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ከአጠገቤ ነበርክ እናም “ማህበሩ የእኛው ከሆነ በውስጥ ኦዲተር ለምን አይመረመርም” በማለት በመጋቤ ካህናት ኃይለሥላሴ ለተነሣው ጥያቄ የሰጠኸው በጭብጨባ የተደገፈ አጸፋ ከዚህ ጽሁፍህ ጋር አልጣጣም አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 63. እንደ እኔ እንደ እኔ ማህበሩ የቤተ ክርስቲያኒቷ አካል ነኝ ካለ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቷ መምሪያ በሚመራበት ሂደት መመራ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ሂደቱ እንኳን ባይጥመው ለማሳደግ መጣር እንጂ ተገንጥሎ “ዘመናዊ” አሠራርን እንከተላለን፣ የተማረ የሰው ኃይል አለን ተብሎ አሁን ያለው መዋቅር መናጋት የለበትም፡፡

  ReplyDelete
 64. dani berta behayimanot tsinu

  ReplyDelete
 65. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማህበረ ቅዱሳን ሳይሆር የኖረች ነች ወደ ፊትም የምትኖር ናት ማህበረ ቅዱሳን ውስጡን ያፅዳ እንደ ውጭ ተራዶ ትንሽ በትኖ ብዙ መሰብሰብ ነው ስራቸው አብዛኛው ራጉኤል የሚገኙ ሱቆች የማህበርቅዱሳን ሰዎች ነው ተምረናል በሚል ስም ስንት የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ላይ ነው አንገታቸውን ሲያረዝሙባቻ የነበረው ለምሳሌ ለተምሮ ማስተማር ለማፍረስ በዋነኝነት ሲታገሉ ነበር ስለዚህ ፅዋ ተርታቸውን ይቅመሱ፡፡ ቤተ ክረስቲያናችን ግን ምንም አትሆንም ምክንያቱ በክርስቶስ ደም እንዲ በማህበረ ቅዱሳን ደም ስላልተመሰረተች፡፡ ቤተክህነትም ቢሆን እራሱን ለማስተካከል ይጣር በሚያልፍ ዓለም ላይ ነው ያለነው አንድ ይዘነው የምንሄደው ነገር የለም ካህናት ሲባል አሁን ብቻ ሳይሆን ጌታ ባለበት ዘመን ቢሆን የማትመቹ ናቸው፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው ለካህናት፡፡ ዳኒ ማህበር ስለሆነ ተቆረቆርክ ማህበረ ቅዱሳን ግን ዋጋውን ማግኘት አለበት በማህበሩ ስም ስንት ወጣቶች አልቅሰው ከማህበሩም ከሃይማኖቱም ወጥተዋል፡፡ ጌታዮ ስላሴ ይጠብቁህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን አንቺ አትፈርሽም? ማህበረ ቅዱሳን በሚሊየኖች ልብ ውስጥ ያለ በተራራ ላይ ያለ መብራት ነው፣አንቺም ሆንሽ መሰሎችሽ መናፍቃን ስለጮሀችሁ የምታመጡት ነገር የለም፣ አባ ጳውሎስ ና መለስም ማህበሩን ለማፍረስ ሲሯሯጡ ፣ ተቀሰፉ፣ ከቀዳሚያቸው የባሱት አባ ማትያስም ውድቀታቸውን እያፋጠኑት ነው፣ ማሕበረ ቅዱሳን ለዘላለም ይኖራል ።።።።።

   Delete
  2. "ክፉ ጎረቤት ገቢዉን እንጅ ወጭዉን አያይም" በእርግጥ አስተያየት መስጠቱ ጥሩ ነዉ ነገር ግን አስተያዬት ለመስጠት ነገሩን በጥልቀት ማወቅ ግድ ይላል::
   ከላይ ስለ ማህበረ ቅዱሳን የሰጠሽዉ ሀሳብ እብርግጥ ስላ ማህበሩ ምንም እንደማታዉቂ(መረጃ) እንደሌለሽ ያመላክታል ብዙ ከማለት ግን ትንሽ ማወቅ የተሻለ ስለሆን ዝም ብለሽ ከምታወሪ እዉነቱን ይዘሽ ብታወሪ የተሻለ ነዉ::
   am not speakin as a memebr of mk but reaally really mk have done many things 4 our church

   Delete
  3. @maru erasih fires tadiya ante ashebari ayidelehim bibal man yaminal!!! hasabuan mestet mebit alat. Abatachinin memehir Girman tenkuay yale mahiber ye orthodox mahiber ayidelem. eskezarem beye sirichawu yehulunim eyita eyanebebin tenshewaren kerten neber

   Delete
  4. @maru ለማሕበረ ቅዱሳን ያሳየኸው መቆርቆር በክርስትያናዊ ስነ ምግባር ቢገለፅ መልካም ነው፡፡ ሀሳብን በሀሳብ ማሸነፍ እየተቻለ ለምን በስድብ እንከላከላለን፡፡ አውቀው ከሚያጠፉት በተጨማሪ ማህበረ ቅዱሳንን ሳያውቁ የጠሉት ብዙ የዋህ ክርስትያኖች መኖራቸውን ሳትዘነጋ የነሱን ስሜታዊ የሆነ አስተያየት ስሜታዊ ሆነህ አትከላከል፡፡

   Delete
 66. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል

  ReplyDelete
 67. በአማን ነጸረOctober 14, 2014 at 12:01 PM

  የረፈደበት የዳኒ የፍትሐዊነት ጥያቄ….የማስተባበል መብት…አይ ዳኒ!!
  አንተ ራስህ ፓትርያርኩንና ቤተክሕነቱን እያብጠለጠልክ ይሄን ጽሑፍ ስትጽፍ በእነሱ በኩል ስላለው መከራከሪያ ትንሽ እንኳ ሚዛናዊ ለመሆን አልሞከርክም እኮ!!አዝናለሁ!!ብዕርህን ብወደውም በማኅበረቅዱሳንና በቤተክሕነት ግንኙነት ዙሪያ ግን አንተ ፍትሀዊና ሁለቱን ወገኖች በእኩል የሚመለከት ዐይን ይኖርሀል የሚለውን ተስፋየን ላያንሰራራ ቀብረኸዋል፡፡ተው ዳኒ!!አይተንሀል እኮ!!
  1- ስለ አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እጽፋለሁ ብለህ ነገሩን ከግራቀኝ ሳታጣራ (ለማጣራት ፍላጎቱም አልነበረህም) የክሕነት አባታህን በጸያፍ መንገድ ከጋዳፊ እያነጻጸርክና በ20 አመታት ምንም እንዳልሰሩ ስታስመስል አይተን ወደ ውስጥ አንብተናል!!
  2- አሁንም ከፓትርያርኩና ከቤተክሕነቱ በማኅበሩ አንጻር የሚነሱት ቅሬታዎችን አግባብነት ለመመርመር ጋት ሳትራመድ ውርጅብኙን ታወርደዋለህ፡፡
  3- ስለ ማኅበረቅዱሳን አንዳች ነገር በአደባባይ ከተነገረ ከዜናው ጀርባ ወይ ተሐድሶ የሚል ተቀጽላ ይለጠፍበታል ወይም የወያኔ ሴራ የምትል መሸሸጊያ ትፈጠራለች፡፡ስለ ቤተክሕነቱና ስለ ፓትርያርኩ ግን ማንም የፈለገውን ያለምንም ማስተባበያ ዜና ከግራቀኙ ሳያጣራ መጻፍ ይችላል፡፡ባለፉት 22 አመታት የሆነውና አሁንም እየሆነ ያለው ይሄ ነው፡፡ማኅበረቅዱሳንን እንደ መደብ አጋር የሚመለከተው በስሙ የቀረው ነጻ ሚዲያና ያገራችን ተቃዋሚም ይሄንኑ ቅኝት ተከትሎ ይነጉዳል፡፡እነ ዳኒም ስለ ሚዛናዊነት ለመናገር አደባባዩ ላይ የሚሰየሙት ማኅበሩ የተነሳ እለት ብቻ ነው!!ምክንያቱም ቤ/ክ ለሚለው ቃል ተቋማዊ ትርጉሙ ከሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ማኅበረ - ምዕመን ያለው ኅብረት ሳይሆን ራሱ ማኅበረቅዱሳን ነው ተብሎ ላለፉት 22 አመታት ተሰበከ፡፡
  4- እናም አጥራችን ተነቀነቀ የሚባለው የማኅበሩ የበላይ የሆነው ቤተክሕነት እና ቅ/ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳትን የሚዘልፉ ጸያፍ ጽርፈቶችና ማቃለሎች ሲነገሩ ሳይሆን ስለ ማኅበሩ ሲነሳ ብቻ ሆነ!!እንግዲህ በተዘዋዋሪ ቤ/ክ ማለት ማኅበረቅዱሳን ማለት ነው እያላችሁን ነው!!
  5- አይ ዳኒ!!ባለፈው የማኅበሩ ስብሰባ መዋቅርን ጠብቆ የተጠራ አይደለም ተብሎ ሲታገድ ከማኅበሩ በላይ ጩኸቱን ቀምተህ ማኅበሩ ስላደረገው ተገቢነት የሌለው ጥሪ አንዳችም ሳታጣራና ለማኅበሩ ተግሳጽ ቢጤ እንኳ ሳትሰጥ ፍጻሜውን ብቻ እያየህ በስብሰባው አለመደረግ ስለደረሰብን ጉዳት ልትሰብከን ሞከርክ፡፡ወይ ሚዛናዊነት አልን!!ስብሰባ ታግዷልና ኑ በእለተ - ስቅለት እንሰለፍ የሚልን ጥሪ ነውር ነው ለማለት ያልደፈረ ሚዛናዊነት!!ስንትና ስንት ኅብረብሔራዊ ሲቪክ ማኅበራት ባሉበት አገር ኢህአዴግ የሚጠላን ኅብረብሔራዊ ስለሆንን ነው ተብሎ ሃይማኖታዊ ምሁርነት የተቀባ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ በነባር አባላቱ በየሚዲያው ሲዘራ እንዳላየ የሚያልፍ ሚዛናዊነት!!
  6- በነጻ ጉልበትና ሀብት እያዋጣን ስለምናገለግል አትናገሩን የሚልና አባቶች ልጆቻቸውን እንዳይገስጹ የሚያሸማቅቅ የሚዲያ መረብ ለ22 አመታት ዘርግቶ ሽቅብ የሚያንጓጥጥ ትውልድን ለመገሰጽ ያልዋለ ብዕር ገለልተኛ መስሎ ሲመጻደቅ ማየት ያሳምማል፡፡
  7- በአፉ …እኛ ቅዱሳንን እንዘክራለን አልን እንጅ ቅዱስ ነን አላልንም… እያለ በተግባር ግን ማኅበሩ ላይ የአካሄድ ቅሬታዎችን በሚያነሳ ላይ ሁሉ የተሐድሶነት፣የአማሳኝነትና የወያኔነት ፍረጃ ከማስረጃ በፊት እየለጠፈ የሚያሳድድ ትውልድ ማኅበራዊ ሚዲያውን ሞልቶት እያየን ድርጊቱን ለራስ ቅድስና ከመስጠት የመነጨ ከማለት በቀር ሌላ የምንሰጠው ሥም የለም!!
  ተወኝማ ዳኒ!!ልደበቅ!!ይቅርብኝ!!ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው…ሑር ሕዝብየ ወባእ ቤተከ፣ወእጹ ኆኅተከ፣ወተኀባዕ ኅዳጠ ምዕረ፣እስከ የኀልፍ መዐቱ ለእግዚአብሔር…እያልኩ ልተክዝ!!ይሄ ማኅበርስ እንደናንተ፡- የኛና የእነሱ አይነት የቡድን አካሄድ ገና ሳያስቀይመን አይቀርም!!ብቻ እሱ የድንግል ልጅ ይሁነን!!
  ዳኒዬ ያንተ ቤተክሕነትንና አመራሮቹን እንደ ባዳ የሚመለከት ብዕር ሚዛናዊ ይሆናል ብየ እንዳልጠብቅ ተስፋ ስላስቆረጥከኝ አመሰግናለሁ፡፡በርቱ!!ስለግብጽ ከጣራ በላይ በመደስኮር፣ስለ ማኅበረቅዱሳን ቅድስና ብቻ በመመስከር፣ስለ ቤተክሕነቱ ድክመት ብቻ በየዐለማዊው ሚዲያና በማኅበሩ ላሳናት በመተረክ የሚገነባ ውስጣዊ አንድነትና ጥንካሬ ካለ ለማየት እጓጓለሁ፡፡


  ReplyDelete
  Replies
  1. Beaman nestere,yemengist akahed'ko bizu miemenanen aswosidual.endene if you care about our church,mahiberun lekek argiw/ew.

   Delete
  2. Mr Netsere, kekesashoch wusti ante yetegnaw neh?
   kahne tebyew woyis lelagnaw?

   Delete
  3. ewenet woyanema alebet

   Delete
  4. am not Dani. Why you didn’t mention their point of view. I heard the all program they said that all M.K. members are educated and the church leaders are uneducated so the church leader scare MK. As we all know our government scares educated people so most Ethiopian people said that this idea came from current government. When I read your comment, you look like well understood the situation but you tried to separate the church leader from the current government idea. We live here so we know who scare educated people. It is so confusing because they are not educated so they are mean for educated people. Our church leader has been corrupted for many years by cheating math but M.K. are educated so they can’t cheat them. Gash Abere Mola said “when you clean dirty area, the people live there will get mad because other people know about their laziness”

   Delete
  5. As an ordinary citizen and a christian i know very well what MK had done in the 80's and 90's in preaching the truth and attracting millions of people and bringing many youths to the truth our forefathers belongs.It it after those young preachers many more appears as favorite preachers for most of present generation.
   so,
   How could you compare them with terrorists? Is terrorism about true love for every one ? that was what i heard of them
   Do you really have good reason to accuse them before the truth ?
   To whom you really stand for ? for truth?
   i feel that we are on the critical time to be tested.money + ethnicity + power or Truth

   Delete
  6. በአማን ነፀረ አሁን እንካን እይታህ ተንሸዋራል። ለአንተ ሚዛናዊነት ማለት እውነቱን በድፍረት በግልፅ መናገር ሳይሆን ሁሉም እንዳይከፋው መሸፋፈን ነው። የቤተ ክህነት ሰዎች እንዳይከፋቸው ሲዘርፉ ዝም፣ ተሀድሶዎች ስርአት ሲንዱ ዝም፣ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ሲያምስ ዝም፣ ዳንኤል ማንንም ሳይፈራ ሲፅፍ ገረን ብእርህን ከአፎቱ ትመዛለህ።በዚህ አቃምህ አንተ መካከል ላይ ያለህ የቤተክህነት ሰው ትመስለኛለህ። ከመንግስትም ፣ ከቤተክህነትም፣ ምንአልባትም ከተሀድሶም የምታገኘው ጥቅማጥቅም አለ። ስለዚህ ሁሉም እንዲነኩ አትፈልግም። ምንም ሥጋዊ ጥቅም የማታገኝበት ማ/ቅዱሳን ሲሆን ግን ብእርህን ታሾላለህ። አሁን ለቤተክርስቲያን ወቅታዊ ፈተና የሆኑትም እንዳንተ አይነት ለራሳቸው ጥቅም ብቻ በቤተክህነቱ የተሰገሰጉ የተማረ መሳይ ናቸው። ማ/ቅዱሳን ሲያጠፋ አይመከር፣አይገሠፅ የሚል አቃም በፍፀም የለኝም ዳኒም አብዛኞቹ አባላቱም እንደሌላቸው አምናለሁ። ችግሩ ድብቁን አላማ በግልፅ ለማስፈፀም የሚደረገው እንቅስቃሴ ነው። ማ/ቅዱሳን ማዳከም፣ማፍረስ፣ ተሀድሶን ማጀገን፣ ቤተክርስቲያኒቱን እንዳልነበረች ማድረግ። ወንድሜ አንተ እንዳልኸው/ወተኀባእ/በዚህ ጊዚ መደበቅ አይቻልም። ይህ ሀይማኖት ን ው እውነቱን መስክሮ የሚመጣውን መቀበል ግድ ይላል። አንተ ግን ሚዛናዊነት የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ እንደገና ተማረው።

   Delete
 68. ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲበጠብጡ የኖሩት ካህናተ ደብተራ (ከቤተ ክህነት ደመወዝ እየወሰዱ ለቤተ መንግሥት ሲሠሩ የኖሩ ካህናት ነን ባዮች) ዋናው መለያቸው የሚሠሩት የራሳቸውን ሥራ አለመሆኑ ነው፡፡ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 69. ጥይት የመታው ሰው ተናድዶ ‹‹ምነው እንዲህ ታበላሸኝ›› ቢለው ‹‹እባክህ እኔ አይደለሁም፣ እኔ ተተኮስኩ እንጂ ተኳሹ ሌላ ነው፤ እኔ መልክተኛ ነኝ›› አለው፡፡ ‹‹ተኳሹ የት አለ?›› ቢለው ‹‹እርሱማ አይታይም ተደብቆ ነው የሚተኩሰው፤ እርሱ ስለሚደበቅኮ ነው እኔ የመጣሁት›› ዳኒ አንተ እንዳልከው ተደብቆ ሳይሆን ደረቱን ነፍቶ እውነትን ይዞ የሚተኩስ ክፍተታችንን የሚሞላ ቀዳዳችንን የሚደፍን ልዩነታችንን የሚያስታርቅ ርቀታችንን የሚያጠብ ነው የሚያስፈልገን፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
 70. ማንም የፈለገዉን ይበል : ቢፈልጉ ህንፃዉን አይደለም ራሳቸዉን ይስቀሉ ማህበረ ቅዱሳንን በደንብ አዉቀዋለሁ :አስተምሮኛል ካስተማረኝ ዉስጥ አንድም ለሽብርተኛነት የሚያበቃ ነገር የለዉም :: ስለ ሃገር ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ መማር ሽብርተኝነት ከሆነ አዎ ሽብርተኞች ነን :: የኦርቶዶክስ ትክክለኛ አስተምህሮ ማስተማርና መማር ሽብርተኛ የሚያስብል ከሆነ እኔ ቀንደኛ ሽብርተኛ ነኝ :: የመናፍቃንን እና የአህዛብን ድብቅ ሴራ ማጋለጥ አሸባሪነት ከሆነ እኔ ወደር የማይገኝልኝ ሽብርተኛ ነኝ:: እኛ ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያናችንን እንወዳለን ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ነን ህንፃዉን አፍርሱት በልቤ ዉስጥ ያለዉ ህንፃ ግን ማፍረስ አትችሉም ::አዝናለሁ ::

  ReplyDelete
 71. ምኑው አስተያየቴን አላወጣኅውም በሌላ ብሎግ ሰፋ አድርጌ እጽፍብሃለሁ

  ከባህር ዳር ጊዩርጊስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. He never rejects other people idea, so I don’t agree with your question. If addition that if he didn’t post your original suggestion why he posted your question. Please don’t disturb the peace. Malala from England.

   Delete
 72. አኛ ሁላችንም ማአበረ ቅዱሳን ነን ለቤተክርሥርስቲያን !!! ( Ethiopian)
  We are Mahibere Kidusan for our church!!! (ENGLISH)
  Estamos Mahibere Kidusan para nuestra iglesia!!! ( SPANISH)
  نحن Mahibere Kidusan لكنيستنا!(( ARBIC
  Wir sind Mahibere Kidusan für unsere Kirche !!! ( GERMAN)
  Ons is Mahibere Kidusan vir ons kerk !!! ( AFRIKAANS)
  Vi er Mahibere Kidusan for vår kirke !!! ( NORWEGIAN)
  Мы Mahibere Kidusan для нашей церкви !!! RUSSIAN
  私たちは、教会のためにMahibere Kidusanです!JAPANESE
  我們Mahibere Kidusan為我們的教會!CHINESE
  Είμαστε Mahibere Kidusan για την εκκλησία μας !!! GREEK

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you so much the Anonymous person. Now everybody know that what we are and what we stand for.

   Delete
  2. Wow thank you so much.

   Delete
  3. YES WE ARE, YES WE ARE, WE ARE MK FOR OUR CHURCH. MY FATHER WENT TO RADIO STATION TO TELL ABOUT ME. WHY HE DIDN'T TELL ME AT HOME, BECAUSE HE THINK I AM SMARTER THAN HIM. GOD BLESS YOU THE ANONYMOUS PERSON.

   Delete
 73. እኛም እኮ ብረት አንስተን ታግለናል መንግስት ይህን ማኅበር ካፈረሰ ወይም እንድፈርስ ካደረገ ታርካዊ ስህተት ነው ማንም የፈለገዉን ይበል : ቢፈልጉ ህንፃዉን አይደለም ራሳቸዉን ይስቀሉ ማህበረ ቅዱሳንን በደንብ አዉቀዋለሁ :አስተምሮኛል ካስተማረኝ ዉስጥ አንድም ለሽብርተኛነት የሚያበቃ ነገር የለዉም :: ስለ ሃገር ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ መማር ሽብርተኝነት ከሆነ አዎ ሽብርተኞች ነን :: የኦርቶዶክስ ትክክለኛ አስተምህሮ ማስተማርና መማር ሽብርተኛ የሚያስብል ከሆነ እኔ ቀንደኛ ሽብርተኛ ነኝ :: የመናፍቃንን እና የአህዛብን ድብቅ ሴራ ማጋለጥ አሸባሪነት ከሆነ እኔ ወደር የማይገኝልኝ ሽብርተኛ ነኝ:: እኛ ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያናችንን እንወዳለን ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ነን ህንፃዉን አፍርሱት በልቤ ዉስጥ ያለዉ ህንፃ ግን ማፍረስ አትችሉም ::አዝናለሁ ::
  «ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ። ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር። ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው? ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።»
  1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ 4፣12-19

  ReplyDelete
  Replies
  1. የሰጠኸው አስተያየት ከጥፋት ህይወት ወጥተን ዛሬ ላይ በእግዚአብሄር ቤት የምንኖረውን የማህበሩ ውለታ ያለብንን ብዙዎቻችንን የሚወክል ስለሆነ ስለአስተያትህ እግዚአብሄር ይስጥልን

   Delete
 74. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል

  ReplyDelete
 75. ንጉሡም ምነው ምን ገጠመህ? ቢሏቸው ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ ሰቃይ ተሰቃይና የመስቀያ ቦታ አንድ ሲገናኙ ያ ነው ክፉ ዘመን፡፡

  ReplyDelete
 76. ማህበረ ቅዱሳንን በመቃወም ሀሳብ የምታቀርቡ ሆይ እስቲ አንድ ተጨባጭ ማስረጃ አቅርቡ ቤተ ክኀነትስ ለምን የቤተክርስትያኗን ህልውና ክፉኛ እየተፈታተኑ ያሉትን የሙስና፣ የአድልዎ አሰራር፣ የምዝበራ፣ የዘረኝነት፣ የዝምድና እና የወገንተኝነት አሰራሮችን ለማጥራት ለምን አትተገጋም? በነገራችን ላይ ከላይ የተዘረዘሩትን እና ሌሎችም ብልሹ አሰራሮች በቤተ ክርስትያናችን እንደተስፋፉ ቅዱስ ፓትርያርኩ ራሳቸው አምነወዋል፡፡ እወደድ ባይ ካህናትስ ለምን በቅድሚያ የአይናቸውን ውስጥ ግንድ አይመለከቱም? በነሱስ ዘንድ ጠጥቶ መስከር፣ አራጣ ማበደር ፣ የነሱ ያልሆነውን መመኘት እና ሌሎች ሀጥያቶች አልተስፈፋፈፉም ? ኸረ አንድ ስለሚያደርገን ተግተን እንስራ እግዚአብሄር ሆይ አንድ አርገን!

  ReplyDelete
 77. Accusing MK out of invalid claims and countrclaims clearly show that preaching Jesus Christ is percieved as Alshaba. So weakining, dismantling MK is a deleberate move.But this the red line for us christians. This is too much. This is unacceptble.

  ReplyDelete
 78. ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 79. ማንም የፈለገዉን ይበል : ቢፈልጉ ህንፃዉን አይደለም ራሳቸዉን ይስቀሉ በደሞዛችን ነው የሠራነው ሰርቀን አደለም ከሙዳዩ ምጽዋት መዝብረን አይደለም ፈጣሪ ያውቀዋል ምንጊዜም እውነት መራራ ናትና እንታገሳለን ፈጣሪም ፍርዱን ይሰጣል በእውነት ዝም ዐይልም ታያላችሁ ብቻ ዕድሜ ይስጠን፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን በደንብ አዉቀዋለሁ :አስተምሮኛል ካስተማረኝ ዉስጥ አንድም ለሽብርተኛነት የሚያበቃ ነገር የለዉም :: ስለ ሃገር ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ መማር ሽብርተኝነት ከሆነ አዎ ሽብርተኞች ነን :: የኦርቶዶክስ ትክክለኛ አስተምህሮ ማስተማርና መማር ሽብርተኛ የሚያስብል ከሆነ እኔ ቀንደኛ ሽብርተኛ ነኝ :: የመናፍቃንን እና የአህዛብን ድብቅ ሴራ ማጋለጥ አሸባሪነት ከሆነ እኔ ወደር የማይገኝልኝ ሽብርተኛ ነኝ:: እኛ ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያናችንን እንወዳለን ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ነን ህንፃዉን አፍርሱት በልቤ ዉስጥ ያለዉ ህንፃ ግን ማፍረስ አትችሉም ::አዝናለሁ

  ReplyDelete
 80. dear brothers and sisters ,ethiopians . we know who is working for the church. how could forget that MK is working on the expansion of church. i know that a lot of churches are built by selling of bread via the coordination of MK. i know why the govt is doing such thing,it is their strategy /divide and rule/ we will not divide WOYANE WOYANE WOYANE>>>>>>>>>>>>>>>>>> let us stand to fight.

  ReplyDelete
 81. Now I really understand why the Wolff with sheep skin always talking negative hates about M.K when I was California I was told by one of the so called monk M.K is Pentecostal. The truth comes out that monk even teaching wrong, and also he don't like the young Mezemeran because they have good base from EOTC. When I moved to North Carolina. The other priest replied hate, so when I went Ethiopia I spent my time traveling different Monastery. The monk who lived in the monastery witnessed what M.K did for the church, so after two months I returned to. Addis Ababa I found my classmates we haven't seen each other over 10 years, we discussed almost every thing including about religion, he said such and such our class mate became protestant how can you didn't change? He asked me, I told him there is no way I change my religion by the way Can you tell me if you have an idea what is M.k . He said he likes Hamer metsehat and took me to Kideste maryam M.k store. I was so amzed I bought so many books and I brought it. It benefits me alot all the book I read gives me a lot of knowledge, I let most people read those books they love . Me and my friends and neighbors are addicted to read especially about Eotc and Ethiopian History.now I know who hate M.k and Why. But they have God and also truth always win

  ReplyDelete
  Replies
  1. You always give this example. Please read more book to provide other example. I know you very well, we met in Cali and you told me this sheet again. Please read more book. I love M.K. but I hate to read one example more than hundred times.

   Delete
  2. example is not necessary.. "LEtebit aned kale beki neww,," Sorry if one example is not enough for you, I am afraid you may not understand with 1000 examples....

   Delete
 82. በቤተክርስትያናችን ውስጥ እየተፈጠረ ባለው ሁኔታ በጣም የሚያሳዝን ነው ይሉቁንም በተለይም እንደኔ አመለካከት ወንድም ዲ/ዳንኤል የተጠቀምክባቸው አብነቶች አንድም ችግሩን ያንድ ወገን የሚያስመስል በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ግዜ ምን ያህል የማህበሩ ኣባላት በትእቢት እንደተወጠረ የሚያመላክት ነው አንድ መታወቅ ያለበት ሲኖዶስን ማንቃሸሽ ማለት ማህበሩን ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ ነውና ለ ሃይማኖት ኣባቶች ያላችሁን ንቀት ለከት ይደረግበት፡፡በ ዘመናዊው ትምህርት መበርታት ለበሰተክርስትያናችን ጠቃሚ ቢሆንም ከቅድስና በላይ ግን አይደለም አይሆንምም

  ReplyDelete
  Replies
  1. The guy who commented above this - do you really know about what you wroteare? Seriously? wait a minute.. who was saying that our fathers to throw their Askema and go away if they dont want to agree with their idea and who harrased and kicked our fathers in their home at the very Nose of the Abuna last time...About respecting our Fathers, go read a lot of writings and teachings MK has delivered..even assigned a dedicated column in Hamer and Simatsidke Megazins...go get some life man!..May God be Glorified!

   Delete
 83. Kale hirate yasamalen

  ReplyDelete
 84. ምነው ዳኒ ሠውን ሁሉ ታባላዋለህ ማንነትህን በደንብ ግለጠውና ይውጣልህ !!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. tew enji dear "anonymous" endante/endanchi anonymous bemil 'tekula' huno alkerbem eko.

   Delete
 85. ማህበረ ቅዱሳንን ማዋከቡ ይቁም !
  ትዉልድን በመልካም ምግባር የሚያንጹ ተቋማትን ማበረታታት ሲገባ ለምን ይዋከባሉ?
  ሁሉም ክርስቲያን አንግቦት ሊነሳ የሚገባዉ መፈክር "እኛ ሁላችን ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነን!" የሚል ነዉ::

  ReplyDelete
 86. እውነቱ እንዲህ ነው፡፡ በእምነት መፅናትን፤ በእምነት መራመድን፤በእምነት መኖርን፤ሀገር መውደድን፤ለሎች እምነቶች ክብር መስጠትን፤ ለእውነት መስራትን፤ድህነትን ተጸይፎ ወደነበርነበት የጥነቱ ክብር እንመለስ ዘነድ ማንነት ማወቁ ላይ፤ በወጣትነት እድሜያችን በሱስ እነዳነጠመድ ፤ በባህል ወረራ ማንነታችንን እንዳናጣ ፤ በቅጡ እነበላ ዘንድ፤በወጉም እንለብስ ዘንድ አረስንቱን ወዘተ… ብለን እናልፈው ዘንድ ግድነውና ወዘተ ብለን እንለፈው፡፡
  ክፍተታችንን ሞልተው ጠማማነታችንን አርቀው ለዚህ ቀን ያበቁን ቁርጥ የተወህዶ ልጆች ፤የቅድሲቲቱ ቤተክርስትያናችን ለክፉ ቀን ደራሾች እነዚህ ዛሬ አነ አማን ነጸር የሚያብጠለጥሏቸው ማሕበረ ቅዱሳን ናቸው፡፡
  የማህበሩን ቅን አገልግሎትም ለቤተክርሰትያኒቱም ይሁን ለሀገረችን እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አይደለም የተወህዶ ልጆች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉም የሌሉም የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድሞች በግልፅ ያወቁታል፡፡ዓለምም ያውቀዋል፡፡ሁሉም ይረዳዋል፡፡
  የማህበረ ቅዱሳን ወንድሞች ፀብ ያላቸው በእምነት ስም ካባ ለብስው በቤተክርስትያኒቱ ስም በሚነግዱት፤ እራሰቸው ሳይታደሱ ቤተክርስቲየያንን እነድሳለን ብለው ሌተ ከቀን በሚያሴሩ ማንነተቸውን በልተረዱ የቤተክርስትያን ጠላቶች እና በመሳሰሉት ላይ ቢሆን አንጂ ከራሳቸው ይልቅ ለሌሎች ቅድሚያን የሚሰጡ በትህትናና በፍቅር የታነፁ ናቸው ብል ተግባረቸውን የሚያወቁ ሁሉ ይጋሩኛል፡፡
  ሌብነትን፤ለሀገርና ለወገን ማሰብን ወደጎን በማድረግ በልመና ምእመኑን አስመርረው የሚሰበስቡትን ገንዘብና ሃብት ለግል ጥቅም የሚያወሉትን ግለኛ ጥቅመኞችን መቃወም በመንግስት በኩልም ይሁን በእውነተኛ የቤተክርስትያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው በእግዚአብሄርም ዘነድ የተወደደ እነጂ የሚየስነቅፍ ወደ ጥላቻም የሚሰድ ተግባር አልነበረም፡፡
  እውነት በትዘገይ እነጂ መገለጧ አይቀሬ ነው፡፡ ነገር በማወሳሰብና እውነተኛ ጎዳናላይ ያለ ሕገዊ ሆኖ የሃገሪቱን ህግና ደንቦች ፤የቤተክርስትኒቱንም ዶግማና ቀኖና፤መመሪየያዎችና ደንቦች አክብሮና ታዞ የሚሰራን የቤተክርስትያን እውነተኛ ልጅ እደግ ይሉት እንደሆን እንጂ ከፊቴ እነደላይህ ቢሉት የሚሰማማ ፀባይ እይደለም፡፡
  መንግስትም ይሁን እውነተኞቹ የቤተክርስትየያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች ምዕመኑም ቢሆኑ ማህበረ ቅዱሳንን በትክክል ያውቁታል፡፡ ማንም ተነስቶ ያ እንዲህ ነው ያም እነድያነው ስላለቸው በትጉህ የንብ መንጋዎች ቀፎ ላይ ከማሩ ለመጠቀም መሀሩን ለመሰባሰብ ቢሀሆን እንጂ የማሪቱ ባለቤት ዳግመኛ ማር እንደትሰጥ በቀፎው ስር አሳት አያነዱም፡፡ እነድያ ከሆነ ግን ግዜ ለኩሉ ነውና ያስተዛዝባል፡፡ ለሞት እነኳን ቢያደርስ ክርስትና መሰረቱ ሰለእውነት መሞት ጸጋው ነውና በክብር እንቀበላለን እንጂ በዋዛ ፈዛዛም ሊታለፍ የሚችልም አይደለም እውነት ምህዳሯን ትስታለችና ነው፡፡ ስለዚህ የገሬ መንግስት መረጃዎችን አጥርቶ እነደያይ፤ የጉዳዩ በለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስም የዚህ ክፉ ደባ ትዋኔ ምንጩ ከየት ሊሆን እነደሚችል አጥርቶ በማየት እነደሰው ሣየሆን እነደ እግዚዘበሄር መንግድ እነዲፈርድ ፤ ህዝበ ክርስትያኑም ቢሆን ቤተክርስትያኑን በትጋት እነዲመለከታት በፀሎቱም እነዲተጋ አኔ የሚሰማኝ እወነቱ አነዲህ ነው እላለሁ፡፡ ይህን ሳልል ባልፈው የመከሩን የገሰፁን በእምነት ጎዳና የመሩን የአውነተኛይቱ ቤተክርስትያን የተዋህዶ ልጆች አባት፤ በአነድነት በሶስትነቱ የሚመሰገን የማያንቀላፈው ሎላዊ እረኛችን እግዚአቢሄር በእውነት አደባባይ ላይ የሚፈረደኝ ይመስለኛልና ነው፡፡
  እግዚአቢሄር አገረችን ከክፉ መካሪዎች፤አባቶችን ከልጆች፤መንግስትን ከህዝብ ከሚያቃቅሩ የእውነት አስመሳይ ሌቦችና ከሃዲዎች ይጠብቃት ! አሜን!!!

  ReplyDelete
 87. The problem is that MK and their members truly believe that the church won't survive without them. They totally forgot that the church has survived difficult problems in the past by the grace of God. It is really disappointing that MK that was conceived in BLATEN military training camp by the students who went there to train how to kill the current members of the current Ethiopian authoritarian government, all of a sudden claims as if it is a pillar of the church. Leave it to God. God is a living God he knows how to take care of his church, his bride. If i were you i will obey to save the church division and respect the authority.

  ReplyDelete
 88. Dani at your last paragraph ,if Mk disappears Sinodos will be disappeared too.it sounds like this.is it correct?

  ReplyDelete
 89. ለምን አንቺ አትፈርሽም? ማህበረ ቅዱሳን በሚሊየኖች ልብ ውስጥ ያለ በተራራ ላይ ያለ መብራት ነው፣አንቺም ሆንሽ መሰሎችሽ መናፍቃን ስለጮሀችሁ የምታመጡት ነገር የለም፣ አባ ጳውሎስ ና መለስም ማህበሩን ለማፍረስ ሲሯሯጡ ፣ ተቀሰፉ፣ ከቀዳሚያቸው የባሱት አባ ማትያስም ውድቀታቸውን እያፋጠኑት ነው፣ ማሕበረ ቅዱሳን ለዘላለም ይኖራል ።።።።።

  ReplyDelete
 90. ለምን አንቺ አትፈርሽም? ማህበረ ቅዱሳን በሚሊየኖች ልብ ውስጥ ያለ በተራራ ላይ ያለ መብራት ነው፣አንቺም ሆንሽ መሰሎችሽ መናፍቃን ስለጮሀችሁ የምታመጡት ነገር የለም፣ አባ ጳውሎስ ና መለስም ማህበሩን ለማፍረስ ሲሯሯጡ ፣ ተቀሰፉ፣ ከቀዳሚያቸው የባሱት አባ ማትያስም ውድቀታቸውን እያፋጠኑት ነው፣ ማሕበረ ቅዱሳን ለዘላለም ይኖራል ።።።።።

  ReplyDelete
 91. ማህብረ ቅዱሳን ሲጠፋ ማየት አሰኜህ አይደል??? ተስፋህን ቁረጥ እሽ!!! እግዚአብሔር ማህበረ ቅዱሳንን አይደለም ከዚህ ሀሰተኞች ተራ ዉንጀላ ቀርቶ በእሳትም ዉስጥ ቢሆን ከቶ አንዳች ነገር ሳይሆን በሰላም ሊያሻግረዉ እንደሚችል አልገባህም ማልት ነዉ!!! ማህብረ ቅዱሳን ከእግዚብሔር ነዉና ጉዞዉን ሊገታ የሚቸል አንዳች አካል ከቶ ሊኖር አይችልም!!!

  ReplyDelete
 92. ማህብረ ቅዱሳን ሲጠፋ ማየት አሰኜህ አይደል??? ተስፋህን ቁረጥ እሽ!!! እግዚአብሔር ማህበረ ቅዱሳንን አይደለም ከዚህ ሀሰተኞች ተራ ዉንጀላ ቀርቶ በእሳትም ዉስጥ ቢሆን ከቶ አንዳች ነገር ሳይሆን በሰላም ሊያሻግረዉ እንደሚችል አልገባህም ማልት ነዉ!!! ማህብረ ቅዱሳን ከእግዚብሔር ነዉና ጉዞዉን ሊገታ የሚቸል አንዳች አካል ከቶ ሊኖር አይችልም!!!

  ReplyDelete
 93. Yemereja chigr yelelebet amlak hulunm temlkto yastekakilew.Hulun awaki newuna.Lebetekirstianm melkamu yadrglat.Telat seitan michu huneta teftroletal,liamisen.Eskemechereshaw yetsena ersu yidnal.

  ReplyDelete
 94. ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም››
  ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔር የሚበጀውን ያድርግ

  ReplyDelete
 95. Do you know what are you talking about? You think you are smart but you are dum. Be a human being. This is pointless idea. If you don't like or like his idea give comment otherwise keep silent. You think just like old FISH. I don't blame you because you came from unwise mother and father. Wurgat and Brla kit.

  ReplyDelete
 96. እውነት መራራ ናት

  ReplyDelete
 97. sewoch niku bakachihu Ato daniel yemilen MK ena enanite yemitaworulet MK yeteleyayu nachewu. le woyane yalen tilacha ayinachinin yizot new enji mehaberu sayihon chigiru wustu yalu mafiyawoch nachew. esti asibut memehir giraman tenkuy, asimategna eyalu minim sayisakeku mesebku jeginawoch, yewushet debdabe azegajitewu sew mikesu, sewunim kesachew lememeles yewushet mesikel kesemay worede bilewu yewushet misebku. liki mengistachin endemiyaregewu kenesu yeteleye hasaba yalewu sew tehadiso, menafik bemalet miyasadidu enezihin lehig makireb yigebachewal. ebakachiwu ebakachiwu sewoch woyanen yetekawome hula tamagn adelem!!!! ato daniel rasihin mermir nisiha giba sayirefid!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማህበረ ቅዱሳን አንድም ቀን ስለ መምህር ግርማ የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ነገር ሲያወጣ አላየሁም ነገር ግን አንዳንድ ዌብሳይቶች ሆን ብለው ማ/ቅን በዚህ ለመጥለፍ የሚጥሩ ያሉ ይመስለኛል። እንደ አንድአድርገን አይነቶች። አሁን እንካን በዚህ የፈተና ሰአት ያንኑ ያሉባልታ ወሬያቸውን ለጥፈዋል። እና እናስተውል የጭቃ እሾህ ተንኮለኞች በዝተዋል ግማሹም ማ/ቅን ከፖለቲካ ጋር ለማነካካት። ብቻ ፈተናው ስለበዛ በስሎት መትጋትና በጣም ማስተዋል ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

   Delete
 98. ‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል
  ያ የተማርነው የመስዋትነት ዘመን ደረሰ ይሆን? ይህችንቤተክርስቲያን ለማጥፋት ያላቸው ን ሁሉ አንግበው ተነስተዋል አንገልም እንጅ እንሞታለን ፍርሃትከእኔ ይራቅ
  ቀራንዮ አማረኝ

  ReplyDelete
 99. ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 100. በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ቀራንዮ መድኃኔዓለም አለቅነት ተሾመው የሄዱትን አባት ካህናቱ አስቸገሯቸው፡፡ ለጥቂት ጊዜ የተላኩበትን ሊሠሩ ሞከሩ ግን አልሆነም፡፡ በመጨረሻም ለንጉሡ እንዲቀይሯቸው አመለከቱ፡፡ ንጉሡም ምነው ምን ገጠመህ? ቢሏቸው ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ ሰቃይ ተሰቃይና የመስቀያ ቦታ አንድ ሲገናኙ ያ ነው ክፉ ዘመን፡፡

  ReplyDelete
 101. Dingay sint zemen wiha wist nore?¿¿¿dingay edime zemenu wiha wist binorim wana aychilim . . . .abet dingay wana mewagnet yechale leta . . . .ena min lilachihu felige meselachihu minim.dani gin GBU lemin danin bicha¿¿¿hulachihunim degafi,tekawami,temelikach,asmelikach,minamin GOD . . . . .

  ReplyDelete
 102. ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 103. ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ ሰቃይ ተሰቃይና የመስቀያ ቦታ አንድ ሲገናኙ ያ ነው ክፉ ዘመን፡፡

  ReplyDelete
 104. I think people are missing the big picture-TEWAHDO.I am saying this b/c parties at both end are obsessed about the blame game that is pushing them an edge of oblivion which at the end will shake the foundations TEWAHDO,so its wise if we all stop the blame game and give each other the love we deserve in the name of Jesus.i am writing this due to the fact the both parties have contributed and are still contributing the preservation of the big picture and may God help us all in seeing beyond the blame game into preserving the big picture

  ReplyDelete
 105. ዲ/ን ዳኒ በፅሁፍህ እረክቻለሁ፡፡ ነገር ግን የኛ ሰው ሙሉውን ሀሳብ ከመረዳት ይልቅ ነገሩን ለማስረዳት የተጠቀምንበትን ትንሽ ነገር ማራገብ ይወዳል፡፡ አሁን አንተ “ካልካቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲበጠብጡ የኖሩት ካህናተ ደብተራ (ከቤተ ክህነት ደመወዝ እየወሰዱ ለቤተ መንግሥት ሲሠሩ የኖሩ ካህናት ነን ባዮች) እና ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› የሚሉትን ይዘው አንዳንዶቹ በፅኁፍኅ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ እነዚህን ይደግሟቿል፡፡ በአካል ያገኘኋቸውም እንዳንዶቹ ደግሞ ከካህናት እኛ ምዕመናን እንሻላለን በማለት በክፉዎቹ ካህናት ነን ባዮች የተሳደዱትን ካህናተ እግዚአብሔርን በመርሳት ክብረ ክህነትን ዝቅ የሚያደርጉና የሚገባቸውን ክብር የሚነፍጉቸው አሉና እባክህን ስለ እውነተኞቹ ካህናት ክብር ፃፍ፡፡ ከጥቂት አመታት ወዲህ የማየው በአጭበርባሪ ካህናት ነን ባዮች ምክንያት የመዋረድ፣ የመናቅ ግፍ በደጋጎቹ ላይ ሲወርድ አይቼ አዝኛለሁ፡፡ ስንት ምርጥ ካህናት አሉ እኮ ምነው ህዝቡ በአንድ ላይ ጨፈለቃቸው፡፡ ምናለ ባናዋክባቸው ፡፡ ቤታችን ካልመጣችሁ እያሉ ጨቅጭቀው ወስደዋቸው ሆዳቸውን ስለሚገመግሙት ስስታሞች እባክህን አንድ ነገር ፃፍ፡፡

  ReplyDelete
 106. ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 107. ጠላት ያነቃል ያተጋል፡፡ ሰይጣን እጎዳለሁ ሲል ይጠቅማል፡፡

  ReplyDelete
 108. ትዉልድን በመልካም ምግባር የሚያንጹ ተቋማትን ማበረታታት ሲገባ ለምን ይዋከባሉ?
  ሁሉም ክርስቲያን አንግቦት ሊነሳ የሚገባዉ መፈክር "

  ሁላችን ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነን!!!!!!!!!! ከዚህም በኋላ በእጥፍ እንበዛለን እንተጋለን ለማህበሩ ያለንን ፍቅርና ክብር እንገልፃለን ማኅበሩም ለእግዚአብሔር ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ለአንዲት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ያለውን ፍቅርና ክብር የበለጠ ይገልፃል ለዚህም እግዚአብሔር የረዳናል እኛ የምንፈልገው በቤተክህነት መዝገብ መኖራችንን አይደለም በሰማያዊት ከሰው ልጆች በተሰወረችው ክርስቶስ በዘጋጃት ለመኖር ነው፡፡ የተጣለው ሳጥናኤል ከሊቀመላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጋር ተዋገቶ እንደነበር በመፅሀፍ ተገልጧል፡፡ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ቤ/ክ ይዋጋል እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ሁላችን ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነን ማንም አይገታንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው !!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 109. ሁላችን ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነን!!!!!!!!!!
  ማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡
  ከዚህም በኋላ በእጥፍ እንበዛለን እንተጋለን ለማህበሩ ያለንን ፍቅርና ክብር እንገልፃለን ማኅበሩም ለእግዚአብሔር ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ለአንዲት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ያለውን ፍቅርና ክብር የበለጠ ይገልፃል ለዚህም እግዚአብሔር የረዳናል እኛ የምንፈልገው በቤተክህነት መዝገብ መኖራችንን አይደለም በሰማያዊት ከሰው ልጆች በተሰወረችው ክርስቶስ በዘጋጃት ለመኖር ነው፡፡ የተጣለው ሳጥናኤል ከሊቀመላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጋር ተዋገቶ እንደነበር በመፅሀፍ ተገልጧል፡፡ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ቤ/ክ ይዋጋል እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ሁላችን ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነን ማንም አይገታንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው !!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 110. ዳኒ አመሰግናለሁ ፍርዱ ትክክል አይደለም፡፡ግን ስሜታዊ ሁነህ ነው የጻፍከው አባቶችን ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠትህ አግባብ አይደለም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሞክሼ Anonymous ዲ/ን ዳንኤል ጽሑፍ ላይ ምንም ስድብ አላነበብኩም። ከየት ፈጠሩት እርስዎ? የእርስዎ 'አባቶች'ስ ምን ሰዳቢ ያስፈልጋቸዋል? ሥራቸው አለ አይደለም እንዴ! ለሚሳደብስ ምን ነጋሪ ያስፈልገዋል?
   እውነቱ እና መልካሙ ምክር ሁሉ እየቆረቆረው "ይህስ ይሳደባል" ማለት ለካ ዛሬም አለ! እኔስ ከንፁህ አምላክ ከክርስቶስ ክስ እና ፍርድ በኋላ የተወገደ መስሎኝ ነበር። ደግሞም "ሊቀ ካህናቱን እንዴት ትናገረዋለህ!" ብሎ በጥፊ ሚማታ ይኖር ይሆን?
   የኔታ ዳንኤል - የመረጣቸውን ቅዱሳኑን ያከበረ፤ ስለ ክቡር ስሙ እና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ በተቀበሉት መከራ ያጸናቸው የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቅዎ። የጻድቃኑ ቃልኪዳን አጋዥ ይሁንዎ።

   Delete
 111. Dane Egizabehare yesetehe pdf

  ReplyDelete
 112. Daniyee God be with MK !! it is critical time for our church please please keep up the good work.Yemariam lij kenante gar yehun.

  ReplyDelete
 113. መምህር ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን፡፡በፈተና ጊዜ የሚያበረታን እንደ አንተ አይነት ሰዉ አያሳጣን፡፡
  እኔ በአባቶቸ አንደበት ይህን በመስማቴ እጅግ በጣም አዝኛለሁ፡አባቶቻችን እኛ ብናጠፋ እኮ መኮርኮም ይችላሉ አሁን ግን ለማን ነዉ የሚከሱን ??? ማን አለን እኛ???

  ReplyDelete
 114. ማህበረ ቅዱሳን በእንዲህ ያሉ ሰዎች አፍ አገልግሎቱ እንዲህ ሲነቀፍ ስናይ ምን ያህል አገልግሎቱን በብቃት እየተወጣ እንደሆነ ያሳየናል። አንድ ሌባ ፖሊሶችን ቢጠላ ስለ ፖሊስም ምን ያሀል ቢናገር እና ቢያጥላላ ፖሊሱ ይህን ቢሰማ አይደንቀውም፣ አይረበሽምም፤ ሥራውን የሚያደናቅፍበትን ስርቆቱን የሚከለክለውን ቢጠላ አይገርመውም። ማህበረ ቅዱሳንን የተለያዩ የመናፍቃን ቡድኖች ቢጠሉት እና ስሙን ቢያጠፉት ምን እንዳደረጋቸው ብንጠይቃቸው "ፕሮቴስታንቲዝምን በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዳስፋፋን ሁሉ በኢትዮጵያም እንዳናስፋፋ ያደረገን ማህበሩ ነው፤" ይላሉ። የአሁኖቹ የቤተ ክህነት ሰዎች እና የአንዳንድ አድባራት አስተዳዳሪዎች ደግሞ እንዲህ የምትወርዱበት ማህበሩ ምን አደረጋችሁ ብለን መጠየቅ ሳያስፈልገን በራሳቸው አፍ "ዳቦ እንዳንበላ ከለከለን"(የቤተክርስቲያንን ገንዘብ እንደፈለገን፤ እንዳሻን እንዳንሆንበት ከለከለን) ብለዋል። አይደለም ለካህናት ለምዕመናንም ለማይበጅ የዓለም ቅንጦት ብለው ራሳቸውን ከተሐድሶ ጎራ አስቀምጠዋል። ቤተክርስቲያናችንን፣ መልካም አባቶቻችንን እና ማህበረ ቅዱሳንን እግዚአብሔር አምላካችን በሰላም ይጠብቅልን፤ ይህ ውርጅብኝ ማህበሩ ባይኖር ኖሮ በቤተክርስቲያን ላይ በወረደ፣ ምዕመናንም በተሰደዱና ቤተክርስቲያን በተከፋፈለች ነበር።

  ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፣ እግዚአብሔር አምላክ ረጅም ዕድሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር ይስጥህ።

  ReplyDelete