Wednesday, October 1, 2014

ፍቅር፣ ቁልፍና ድልድይ

በሜልበርን እምብርት እየተሽረከርን በያራ ወንዝ ዳርቻ ስንዋብ ወደ ሌላ አቅጣጫ የመሻገሪያ የእግረኞች ድልድይ ላይ ደረስን፡፡ የያራ ወንዝ ዓባይን በሰኔ መስሏል፡፡ እዚህ ወንዝ ዳር ነው የዛሬ 179 ዓም እኤአ 1835 የሜልበርን ከተማ የተቆረቆረችው፡፡ ከ242 ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል ያራ ወንዝ፡፡ የመሻገሪያው ድልድይ ወንዙ መካከል በአንዲት አነስተኛ ጀልባ በምትመስል ኮንክሪት መሬት ላይ ቆሟል፡፡ ሀገሬዎቹ ደሴት ብርቃቸው ነው መሰለኝ ‹ፖኒ ፊሽ ደሴት› ይሏታል፡፡ መቼም ፈረንጅ ትንሽን ነገር ታላቅ በማድረግ የሚተካከለው የለም፡፡
ይህንን ድልድይ እያቋረጥን ስንሄድ በግራና ቀኝ በድልድዩ መደገፊያ ላይ የታሠሩና የተቆለፉ ቁልፎችን አየሁ፡፡ ሙሉ የድልድዩን ብረት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይዘውታል፡፡ አንዳንዶቹ በሀገራችን ለስታድዮም በር ብቻ ሊውሉ የሚችሉ ቁልፎች ናቸው፡፡ እነዚህ በፍቅራቸው ላይ ሥጋት ሳይኖርባቸው አይቀርም፡፡ አንዳንዶቹ ቁልፎችም ከቻይኖች ዓይን እንኳን ያነሱ ናቸው፡፡ ይህንን ዓይነት ነገር የገጠመኝ ፓሪስ ነበረ፡፡ በፓሪስ የሚገኙ ድልድዮች በዚያ ስማቸውን ጽፈውና ቁልፋቸውን ቆልፈው በሚያንጠለጥሉ ፍቅረኞች ምክንያት ለአደጋ መጋለጣቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ቢጮህ እንኳን ሰሚ አላገኘም፡፡ በተለይ ፖንቴ ደስ አርትስ በዚህ የተቸገረ ድልድ ነው፡፡እዚህ ሜልበርንም ተመሳሳይ ሥጋት ከመዘጋጃ ቤቱ እየተሰማ ፍቅረኞች ግን ከድልድዩ ይልቅ ፍቅራቸው ያሳስባቸዋል፡፡ ድልድዩ ቢሰበር እኛ ደኅና እንሁን እንጂ መልሰን እንሠራዋለን፡፡ የኛ ፍቅር ከተሰበረ ማን ይጠግነዋል? ይላሉ፡፡

ይኼ ደግሞ ባልተጠገነ ፍቅር ምክንያት በልብ ሕመም የሞተችውን ሰርቢያዊቷን ናዳን ያስታውሳቸዋል፡፡ ናዳ በአንድ ትምህርት ቤት የምታስተምር ሴት ነበረች፡፡ ከሕይወት በአንዱ ቀን ሬልጃ ከተባለ የሰርቢያ የጦር መኮንን ጋር በፍቅር ወደቀች፡፡ ዘመኑ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ነበርና ሬልጃ ለጦርነት ወደ ግሪክ ሄደ፡፡ በሄደበት ግሪክ ‹‹እኔስ በአገሬ እንኳን ሰው ወፍ አለምዳለሁ›› የምትል ቆንጆ አገኘና ከእርሷም ጋር በፍቅር ወደቀ፡፡ በዚህም ምክንያት ናዳና ሬልጃ ተለያዩ፡፡ ናዳ በዚህ የተነሣ ኀዘንተኛና በሽተኛ ሆነች፡፡ ኀዘኑ ባስከተለባት የልብ ችግርም ምክንያት ገና በወጣትነቷ ሞተች፡፡
ይህ የናዳ ታሪክ የሰርቢያን ወጣቶች አስደነገጣቸው፡፡ የመጀመሪያውና የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አያሌ ወዳጆቻቸውን ያሳጣቸው የአውሮፓ ወጣት ፍቅረኞችንም ልብ ነካ፡፡ በዚህም የተነሣ የሚፋቀሩ ወጣቶች ላለመለያየት ብለው፣ የናዳም ዕጣ ፈንታ እንዳይደርስባቸው ፈርተው ቁልፍ እየቆለፉ ናዳና ራጃ አዘውትረው ይገናኙበት ነበር በተባለው ድልድይ ላይ ማንጠልጠል ጀመሩ፡፡ ከሺ ዘመናት በፊት በአውሮፓ የነበረው ይህ ባሕል በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ምክንያት እንደገና አገረሸና አያሌ ድልድዮችን አጥለቀለቀ፡፡
የፓሪሱ የፍቅር ድልድይ
ከቀድሞ ጀምሮ የሰውን ልጅ ሲያስጨንቁት ከኖሩት ሰብአዊ ጸጋዎች አንዱ ፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው አፍቃሪ ፍጡር ሆኖ ነው፡፡ እንስሳት ይኼ የላቸውም፡፡ እንስሳት ለአንድ ነገር የሚኖር አዝማሚያ (affection) ነው ያላቸው፡፡ ፍቅር የአምላክ ጸጋ ነውና ይህ ሊኖራቸው የሚችለው ሰውና መላእክት ናቸው፡፡ ሰው ሥጋዊ ፍጡር ስለሆነ ነው ስሜትም የሚኖረው፡፡ ስሜት በመላእክት ዘንድ የለም፡፡ ፍቅር ግን አለ፡፡ ማሰብ ከሌለ ስሜት እንጂ ፍቅር አይኖርም፡፡ ፍቅር አንድን ነገር መፈለግ፣ ወደ አንድ ነገር መሳብና ከአንድ ነገር ጋር መቆራኘት ብቻ ሳይሆን አብሮ የሞራልና የእምነት ሕግጋትም አሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ ማሰብን ይፈልጋል፡፡ ፍቅር በውስጡ ጽጌረዳ ብቻ ሳይሆን እሾህ፣ የዓሣ ሥጋ ብቻ ሳይሆን የዓሣ እሾህ፣ ማር ብቻ ሳይሆን የንብ ንድፊያ፣ አለው፡፡ አንዳንዴ ለመዳን መርፌን እንደምንወጋው፤ መርፌውም እንደሚያም፣ ነገር ግን መድኃኒቱ እንደሚያድነን፤ ለመድኃኒቱም ብለን የሚያመውን መርፌ እንደምንታገሠው፤ ፍቅርም እንዲህ ይሆናል፡፡ መድኃኒት የያዘ መርፌ ይሆናል፡፡ ይህንን ሁሉ ለማመዛዘንና ለመቀበል ደግሞ አሳቢ ፍጡር መሆን ግድ ነው፡፡ ስሜት የሚያውረውን ፍቅር ነው የሚያበራለት፡፡ ፍቅር ዓይናማ ነውና፡፡ ያውም የልቡና ዓይን፡፡
ሳውዝ ባንክ የእግረኞች ማቋረጫ
ሰው ፍቅርንና ስሜትን መለየት እያቃተው፣ አንዳንድ ጊዜም ከፍቅር ይልቅ ስሜቱን እያስበለጠ ነው ራሱን መከራ ውስጥ የሚጥለው፡፡ ስሜት ለፍቅር አንዱ ግብዐት እንጂ ብቸኛው ነገር አይደለም፡፡ በፍቅር ውስጥ ከስሜት ሌላ ማሰብ፣ መታገሥ፣ ራስን መግዛት፣ መሸከም፣ ቆራጥ፣ ኃላፊነትን መውሰድ፣ ይቅር ማለትና ሌሎችም አሉበት፡፡ ስሜት ግን የፍቅር ማስጀመሪያ እና ፍቅር ማለስለሻ ነው፡፡ ለአንድ መኪና ባትሪው የሞተሩ ማስነሻ እንደሆነው ሁሉ፤ በባትሪ ብቻ ግን መሄድ እንደማይቻል፤ ያለ ባትሪም መሄድ እንደማይቻል ማለት ነው፡፡ ስሜት እንደ መኪና ቅባቶችና ዘይቶች ያለ ነው፡፡ ቅባትና ዘይት ያነሰው መኪና ችሎ ችሎ አንድ ቀን ወይ ይነጫነጫል፣ ወይ ይቆማል፣ ወይ እሳት ያስነሣል፣ ወይ ሞተር ይነክሳል፡፡ ስሜት ጠፍቶባቸው ሞተር የነከሱ ብዙዎች ናቸው፡፡
ቅባትና ዘይት ግን ለሞተሩና ለሌሎች ዕቃዎች ሕልውና ሲባል የሚደረግ እንጂ በራሱ ሕልውናውን ለብቻ የሚያስቀጥል አይደለም፡፡ ለዘይቱ አይደለም ሞተሩ፤ ለሞተሩ ነው እንጂ ዘይቱ፡፡ እንደዚሁም ነው፡፡ በፍቅር ውስጥ ለሚገኙት ወሳኝ ነገሮች ነው ስሜት የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንጂ ለስሜቱ አይደለም እነርሱ የሚያስፈልጉት፡፡ ስሜት ብቻ የያዙ ‹‹ፍቅረኞች›› ናቸው እንደ ሬልጃ እዚህም እዚያም መሄድ፣ ያዩዋትንም ሁሉ መመኘትና እንደ ተረት ገጸ ባሕርይ ‹‹ሲሄዱ፣ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ›› የሚኖሩት፡፡
ይኼ እንግዲህ የሰው ዘር ሁሉ ጭንቀት ነውና እስኪ በቁልፍ አሥረን እንሞክረው ብለው ነው ስማቸውን ጽፈው፣ ቁልፍ ላይ ለጥፈው፣ ቁልፉንም ቆልፈው ድልድይ ላይ የሚያስቀምጡት፡፡እንዲህ ዘወትር ሳንለያይ ያኑረን ብለው፡፡ በተለይ በዚህ እና ባለንበት ዘመን ሰው የሰውን ጸባይ ቀርቶ የራሱን ጠባይ መቻል እያቃተው፣ ሰው አንዳች መሥዋዕትነትን ለመክፈል እየሰሰተ ባለበት ጊዜ መሸከምንና መሥዋዕትነትን የሚፈልገው ፍቅር በስሜትና በጊዜያዊ ፍላጎት (ፈቲው) እየተተካ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ነው የሰው ልብ መሸከም ያቃተውን ነገር ድልድዮችን ለማሸከም መከራ የሚያየው፡፡ ድልድዮች ደግሞ ‹እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ›› አላሉም፡፡ በምን ዐቅማቸው ይሸከሙታል፡፡
ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው
ከድንጋይ ይከብዳል ለተሸከመው ሰው
አለ የሀገሬ ገጣሚ፡፡
ሜልበርን፣ አውስትራልያ፡፡

40 comments:

 1. ፍቅር አንድን ነገር መፈለግ፣ ወደ አንድ ነገር መሳብና ከአንድ ነገር ጋር መቆራኘት ብቻ ሳይሆን አብሮ የሞራልና የእምነት ሕግጋትም አሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ ማሰብን ይፈልጋል፡፡ ፍቅር በውስጡ ጽጌረዳ ብቻ ሳይሆን እሾህ፣ የዓሣ ሥጋ ብቻ ሳይሆን የዓሣ እሾህ፣ ማር ብቻ ሳይሆን የንብ ንድፊያ፣ አለው፡፡ አንዳንዴ ለመዳን መርፌን እንደምንወጋው፤ መርፌውም እንደሚያም፣ ነገር ግን መድኃኒቱ እንደሚያድነን፤ ለመድኃኒቱም ብለን የሚያመውን መርፌ እንደምንታገሠው፤ ፍቅርም እንዲህ ይሆናል፡፡ መድኃኒት የያዘ መርፌ ይሆናል፡፡ ይህንን ሁሉ ለማመዛዘንና ለመቀበል ደግሞ አሳቢ ፍጡር መሆን ግድ ነው፡፡ ስሜት የሚያውረውን ፍቅር ነው የሚያበራለት፡፡ ፍቅር ዓይናማ ነውና፡፡ ያውም የልቡና ዓይን፡፡

  ReplyDelete
 2. Hellow Dani: Great analysis.

  ReplyDelete
 3. Can a person fall in love with a girl at his initial meeting with her?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥሩ ነጥብ ነው ያነሳኸው። በፍቅርና በስሜት መካከል ያለውን ልዩነት በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል። በኔ እምነት ሰዎች በመጀመሪያ እይታ በፍቅር ሊወድቁ አይችሉም ስሜት ያይልባቸዋል እንጂ። ይኼን ስሜት ወደ ፍቅር ለመግራት የመጠናናት ጊዜ ማሳለፍ ይኖርባቸዋል። በዚህ የመጠናናት ጊዜ ውስጥ የሚኖረው ትውውቅ በመጀመሪያ የነበረውን ስሜት ወይ ያዳብረዋል ወይ ያኮስሰዋል። በሚኖራቸው ትውውቅ የመጀመሪያው ስሜት እየዳበረ ከሄደ ሰዎቹ ፍቅር እያደረጁ ነው ማለት ነው። በተመሳሳይ መልኩ ትውውቃቸው ከማቀራረብ ይልቅ እያራራቃቸው ከመጣ ያ መጀመሪያ የነበርውም ስሜት እንዲሁ እየጠፋ ይመጣል። እንግዲህ ሁለቱም ሌላ የፍቅር አቻዎቻቸውን ይፈልጋሉ ማለት ነው። መጠናናት ለምን ያህል ጊዜ? በኔ እምነት ከአንድ ዓመት ያላነሰ።

   Delete
  2. asabken egawalw

   Delete
 4. wow................

  ReplyDelete
 5. Thank you Dani, for your view presentation on keys at the bridge....

  ReplyDelete
 6. ድልድዮች ደግሞ እናተ ሸክማቹ የከበደ ወደኔ ኑ አላሉም

  ReplyDelete
 7. በተለይ በዚህ እና ባለንበት ዘመን ሰው የሰውን ጸባይ ቀርቶ የራሱን ጠባይ መቻል እያቃተው፣ ሰው አንዳች መሥዋዕትነትን ለመክፈል እየሰሰተ ባለበት ጊዜ መሸከምንና መሥዋዕትነትን የሚፈልገው ፍቅር በስሜትና በጊዜያዊ ፍላጎት (ፈቲው) እየተተካ በመሄድ ላይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. ይሄ ቁልፍ ለእኛ አገር አፍቃሪ የሚሆን አይመስለኝም ምንክንያቱም አመሉ ብዙ ነው ተሳስቶ እንኳን እወድሻለው ያለ እንደሆን በቃ ዘመን እቅኪቀየር ድረስ አይደግመም ያው የወረደ ባህሪውን ነው የሚያሳየሁ በመሞጋገስ ገና ብዙ ይቀረናል

  ReplyDelete
 9. ለዚህ ነው የሰው ልብ መሸከም ያቃተውን ነገር ድልድዮችን ለማሸከም መከራ የሚያየው፡፡ ድልድዮች ደግሞ ‹እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ›› አላሉም፡፡

  Yes it is Right!!!

  ReplyDelete
 10. Wow it is interesting.

  ReplyDelete
 11. ሰው አንዳች መሥዋዕትነትን ለመክፈል እየሰሰተ ባለበት ጊዜ መሸከምንና መሥዋዕትነትን የሚፈልገው ፍቅር በስሜትና በጊዜያዊ ፍላጎት (ፈቲው) እየተተካ በመሄድ ላይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 12. dani nice expalnation but it need additional expalanation about love........thank you.

  ReplyDelete
 13. Hawariyawa Paulos, zarem behiywet alehi? Endihum Atinatios z egpt

  ReplyDelete
 14. andi sew bicha landit ager edime ysitih

  ReplyDelete
 15. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እጅግ በጣም ለማመስገን እፈልጋለሁ እይታዎችህ በጣም ያስደስታሉ፡፡ እባክህን በርታልን!!!!

  ReplyDelete
 16. MINEW MHITEM SILEBETESU Yematisifew?

  ReplyDelete
 17. የማይተማመን ባለእንጀራ (ባለትዳር) በየወንዙ ይማማላሉ
  በሀገራችን በአውሮፓ ብየድልድዩ ሆነ እንዴ?

  ReplyDelete
 18. Dani, I remember that you criticize Minister Zenebu on her support for gay rights. That was good, why do you keep silent then when Sheferaw declare and order us to put our "maeteb"??? ... please keep on being our voice!!!

  ReplyDelete
 19. ፍቅር የአምላክ ጸጋ ነውና ይህ ሊኖራቸው የሚችለው ሰውና መላእክት ናቸው፡፡ ሰው ሥጋዊ ፍጡር ስለሆነ ነው ስሜትም የሚኖረው፡፡ ስሜት በመላእክት ዘንድ የለም፡፡ ፍቅር ግን አለ፡፡ ማሰብ ከሌለ ስሜት እንጂ ፍቅር አይኖርም፡፡ ፍቅር አንድን ነገር መፈለግ፣ ወደ አንድ ነገር መሳብና ከአንድ ነገር ጋር መቆራኘት ብቻ ሳይሆን አብሮ የሞራልና የእምነት ሕግጋትም አሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ ማሰብን ይፈልጋል፡፡ ፍቅር በውስጡ ጽጌረዳ ብቻ ሳይሆን እሾህ፣ የዓሣ ሥጋ ብቻ ሳይሆን የዓሣ እሾህ፣ ማር ብቻ ሳይሆን የንብ ንድፊያ፣ አለው፡፡ አንዳንዴ ለመዳን መርፌን እንደምንወጋው፤ መርፌውም እንደሚያም፣ ነገር ግን መድኃኒቱ እንደሚያድነን፤ ለመድኃኒቱም ብለን የሚያመውን መርፌ እንደምንታገሠው፤ ፍቅርም እንዲህ ይሆናል፡፡ መድኃኒት የያዘ መርፌ ይሆናል፡፡ ይህንን ሁሉ ለማመዛዘንና ለመቀበል ደግሞ አሳቢ ፍጡር መሆን ግድ ነው፡፡ ስሜት የሚያውረውን ፍቅር ነው የሚያበራለት፡፡ ፍቅር ዓይናማ ነውና፡፡ ያውም የልቡና ዓይን፡፡
  "ዳን ግን መክፈቻውነን የሚያስቀምጡት የት ነው?"

  ReplyDelete
 20. Kulf Siletederederebet Dildiy Sitawera Angetih lay Yalewun Meskelihn Ministeru Sifetut Tayaleh.

  ReplyDelete
 21. I feel like am just in front of a mirror..this article enables me to know what is missing in my marriage..I read it so many times...This is really a Word of God! Edmena tena yistelin our brother!!!

  ReplyDelete
 22. Ketenkolegnoch ena ketetenakuwayoch yitebqh.

  ReplyDelete
 23. ከፍቅር እና ከስሜት ምናልባት ስሜት ሊቀድም ይችል ይሆናል
  ወዲያው ግን በፍቅር እና በማስተዋል ቁጥጥር ስር መዋል…ማደር…መኖር አለበት፡፡

  ReplyDelete
 24. ዳኒ እይታዎችህ ድንቅ እና ዘመን ተሸጋሪ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ብርታቱን ጸጋውን ያብዛልህ…ይጠብቅህም፡፡
  እስኪ እባክህ ስለ ቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታ…ውስጣዊ ተግዳሮት…የአሰራር ንቅዘት….እና መፍትሔዎቹ…የምእመናን እና ባለድርሻ አካላት ድርሻ….አንድ ነገር በለን፡፡ አሊያ በዚህ አካሄድ የነገዋን ቅድስት ቤተክርስቲያን ማሰብ ይከብድ ይመስለኛል፡፡ እኛም ዛሬ ካልሰራን በትውልድም በእግዚአብሔር ዘንድም ተወቃሾች መሆናችን አይቀርም፡፡ ስራ ለመስራት ዛሬ ከነገ ይሻላልና፡፡

  ReplyDelete
 25. i personally have this problem......what should i do??????? d daniel..

  ReplyDelete
 26. እኔ ግን የሚያሳስበኝ ለክፉም ለደጉም ብለዉ መክፈቻዉን ይዘዉ ወደ ቤት የሚመለሱ ከሆነ ነዉ

  ReplyDelete
 27. Yihis metadeli new kegizeri yetesetehi
  Yihew New mignote ahunim yabizalihi


  ReplyDelete
 28. endet melkam negern negerken wedajachin edme ke tena gar ystln Amen!!!!!

  ReplyDelete
 29. ፍቅር በውስጡ ጽጌረዳ ብቻ ሳይሆን እሾህ፣ የዓሣ ሥጋ ብቻ ሳይሆን የዓሣ እሾህ፣ ማር ብቻ ሳይሆን የንብ ንድፊያ፣ አለው፡፡ አንዳንዴ ለመዳን መርፌን እንደምንወጋው፤ መርፌውም እንደሚያም፣ ነገር ግን መድኃኒቱ እንደሚያድነን፤ ለመድኃኒቱም ብለን የሚያመውን መርፌ እንደምንታገሠው፤ ፍቅርም እንዲህ ይሆናል፡፡ መድኃኒት የያዘ መርፌ ይሆናል፡፡ ይህንን ሁሉ ለማመዛዘንና ለመቀበል ደግሞ አሳቢ ፍጡር መሆን ግድ ነው፡፡ ስሜት የሚያውረውን ፍቅር ነው የሚያበራለት፡፡ ፍቅር ዓይናማ ነውና፡፡ ያውም የልቡና ዓይን፡፡

  ReplyDelete
 30. ሰው ፍቅርንና ስሜትን መለየት እያቃተው፣ አንዳንድ ጊዜም ከፍቅር ይልቅ ስሜቱን እያስበለጠ ነው ራሱን መከራ ውስጥ የሚጥለው፡፡ ስሜት ለፍቅር አንዱ ግብዐት እንጂ ብቸኛው ነገር አይደለም፡፡ በፍቅር ውስጥ ከስሜት ሌላ ማሰብ፣ መታገሥ፣ ራስን መግዛት፣ መሸከም፣ ቆራጥ፣ ኃላፊነትን መውሰድ፣ ይቅር ማለትና ሌሎችም አሉበት፡፡ ስሜት ግን የፍቅር ማስጀመሪያ እና ፍቅር ማለስለሻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 31. Dear Dn.Daniel ,great investigation and good life experience? Just, one question, how do you see yourself through this mirror?

  ReplyDelete
 32. ስውን ስሜቱ ብቻ ከገዛው, እውነትም ችግር አለ.....

  ReplyDelete