Friday, September 5, 2014

ጳጉሜን - አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት

የመግቢያ ማስታወሻ
በጽሑፉ ውስጥ በግእዝ ቁጥሮች በቅንፍ ውስጥ የተጻፉት ሐሳቡን እንዲወክሉ ብቻ ነው፡፡ በኋላ (ቁጥር ፭ ተመልከት ቢል ያንን ሐሳብ መልሶ ለማየት እንዲረዳ ነው፡፡
የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ጳጉሜ የምትባል አሥራ ሦስተኛ ወር ስላለችን ነው፡፡ የቤት ኪራይና የወር ደመወዝ የማንከፍልባትና የማንቀበልባት፤ መብራትና ውኃ ግን ከነሐሴ ወር ጋር ጨምረው የሚያስከፍሉባት፤ ሲሻት አምስት፣ ሲያስፈልጋት ስድስት፣ ስትፈልግ ደግሞ ሰባት የምትሆን ወር ናት፡፡ እንዲያውም ከአሥራ ሁለቱ የኢትዮጵያ ወሮች ጳጉሜ በብዙ መንገድ የተለየች ናት፡፡
በአንድ በኩል በጣም ትንሿ ወር ናት፡፡ ሲቀጥልም ወርኃዊ በዓላት የማይውሉባት ወር ናት፡፡ እንዲያም ሲል ደግሞ ከሌሎች ወሮች በተለየ የቀኖቿ መጠን የሚቀያየሩ ብቸኛ ወር ናት፡፡ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወሮች በተለየም ስሟ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ወር ናት፡፡ በሁለት ዘመናት መካከልም እንደ መሸጋገሪያ የምትታይ ወርም ናት፡፡  


ጳጉሜ ማለት በግሪክ ‹ጭማሪ› ማለት ሲሆን ዓመቱን በሠላሳ ቀናት ስንከፍለው የሚተርፉትን ዕለታት ሰብስበው የሰየሟት ተጨማሪ ወር ናት፡፡ ወይም በየዕለቱ በፀሐይና በጨረቃ አቆጣጠር መካከል የሚፈጠረውን ልዩነት ሰብስበው ያከማቹባት ወር ትባላለች፡፡ ዓመቱ በዐውደ ፀሐይ ሲለካ 365 ቀናት ከ15 ኬክሮስ 6 ካልዒት ሲሆን በጨረቃ ሲለካ ደግሞ 354 ቀናት ከ22 ኬክሮስ፣ 1 ካልዒት፣ 36 ሣልሲት፣ 52 ራብዒት፣ 48 ኀምሲት ነው፡፡ (60 ኬክሮስ አንድ ቀን ነው)በሁለቱ መካከል(በፀሐይና በጨረቃ) በዓመት ውስጥ ያለው ልዩነት 11 ቀናት ከ7 ኬክሮስ ይሆናል፡፡ [በነገራችን ላይ በዘመን አቆጣጠራችን ውስጥ ከዕለት በታች የምንቆጥርባቸው ስድስት መለኪያዎች አሉ፡፡ ኬክሮስ፣ ካልዒት፣ ሣልሲት፣ ራብዒት፣ ኀምሲትና ሳድሲት፡፡ 60 ሳድሲት አንድ ኀምሲት፣ 60 ኀምሲት አንድ ራብዒት፣ 60 ራብዒት አንድ ሣልሲት፣ 60 ሳልሲት አንድ ካልዒት፣ 60 ካልዒት ደግሞ 1 ኬክሮስ ይሆናል፡፡ 60 ኬክሮስ ደግሞ 1 ዕለት፡፡ 1 ኬክሮስ 24 ደቂቃ ነው]
ጳጉሜን ለማግኘት የሚጠቅመን የየዕለቱን ልዩነታቸውን መመልከቱ ነው፡፡ በየዕለቱ በጨረቃና በፀሐይ መካከል 1 ኬክሮስ 52 ካልዒት(60 ካልዒት አንድ ኬክሮስ ነው)፣ ከ 31 ሣልሲት(60 ሣልሲት አንድ ካልዒት ነው) ይሆናል፡፡[ይህም ማለት 5 ሰዓት ከ48 ደቂቃ ከ46 ካልዒት(ሴኮንድ?)] ይህ ልዩነት በአንድ ወር ምን እንደሚደርስ ለማወቅ በ30 እናባዛው፡፡ 30 ኬክሮስ፣ 1560 ካልዒት፣ ከ930 ሣልሲት ይሆናል፡፡ የዓመቱን ለማግኘት ደግሞ በ12 እናባዛው፡፡ 360 ኬክሮስ(፩)፣ 18720 ካልዒት(፪)፣ 11160 ሣልሲት(፫) ይመጣል፡፡
ቀደም ብለን 60 ኬክሮስ አንድ ዕለት ይሆናል ባልነው መሠረት 360 ኬክሮስ ለ60 ሲካፈል 6 ዕለታትን ይሰጠናል(፩)፡፡ 18720 ካልዒትን(፪) በስድሳ በማካፈል 312 ኬክሮስን እናገኛለን፡፡ ያም ማለት ትርፉን 12 ኬክሮስ ትተን 300ውን ኬክሮስ ለ60 በማካፈል 5 ዕለት እናገኛለን፡፡ ይኼም ማለት 5 ዕለት ከ12 ኬክሮስ(፬) ይሆናል፡፡ 11160 ሣልሲትን(፫)ለ60 ብናካፍለው 186 ካልዒት ወይም ደግሞ 3 ኬክሮስና 6 ካልዒት(፭) ይሆናል ማለት ነው፡፡
ከላይ ኬክሮስን በዓመቱ ቀናት አባዝተን ያገኘነው(፩) 6 ዕለት አለ፡፡ ይኼ ዕለት ሕጸጽ ይባላል፡፡ ፀሐይና ጨረቃን እኩል መስከረም አንድ ላይ ዓመቱን ብናስጀምራቸው ፀሐይ የወሯ መጠን ምንጊዜም ሠላሳ ሲሆን ጨረቃ ግን በአንደኛው ወር 29 በሌላኛው ወር ግን 30 ስለምትሆን ዓመቱ እኩል አያልቅም የጨረቃ ዓመት ነሐሴ 24 ቀን ያልቃል፡፡ ይህም ማለት ጨረቃ በሁለት ወር አንድ ጉድለት ታመጣለች፡፡ ያንን ነው ሊቃውንቱ ሕጸጽ(ጉድለት) ያሉት፡፡ በዚህም መሠረት ከላይ ኬክሮሱን(፩) በዓመቱ ቀናት አባዝተን ያገኘነውን 6 ዕለት ለጨረቃ ሕጸጽ ስንሰጠው የመስከረም/ ጥቅምት (1)፣ የጥቅምት/ ኅዳር(2)፣ የጥር/ የካቲት(3)፣ የመጋቢት/ ሚያዝያ(4)፣ የግንቦት/ ሰኔ (5)፣ የሐምሌ ነሐሴ (6) ሆነው ተካፍለው ያልቃሉ፡፡
በሌላም በኩል ደግሞ በጨረቃና በፀሐይ ዑደት መካከል በዓመት ያለው ልዩነት 11 ቀናት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት) ይሆናል፡፡ ስድስቱን ዕለታት ጨረቃ ለምታጎልበት (ሕጸጽ) ብንሰጠው ቀሪ 5 ዕለት ይኖረናል፡፡ ጳጉሜ ማለት እነዚህ 5 ቀናት ናቸው፡፡ አሁን የአሥራ አንዱን ዕለታት ከፈጸምን ሽርፍራፊዎቹን (15 ኬክሮስና 6 ካልዒት) እንይ፡፡
ከላይ እንዳየነው በፀሐይና ጨረቃ ዓመታት መካከል የተፈጠሩትን 11 ቀናት ስድስቱ ለሕጸጽ ማሟያ ሲገቡ የቀሩት 5 ዕለታት ናቸው ጳጉሜ የምትባለውን ወር በመሠረታዊነት የፈጠሯት፡፡ በጎርጎርዮሳውያኑ አቆጣጠር እነዚህ 5 ተጨማሪ ዕለታት በጃንዋሪ፣ ማርች፣ ሜይ፣ ጁላይና ኦገስት ላይ ስለተጨመሩ እነዚህ ወራት 31 ለመሆን ተገድደዋል፡፡ (ይህንን የከፈለው በ46 ቅልክ የነበረው ዩልየስ ቄሣር ነው፡፡ ለአራቱ ወሮች 30 ቀን፣ ለአንዱ 28/29 (በየአራት ዓመቱ)፣ ለቀሩት ሰባት ወሮች ደግሞ 31 ሰጥቷቸዋል፤ ለአምስቱ ወሮች 31 ያደረጋቸው ከጳጉሜ ወስዶ ሲሆን ለሁለቱ ወሮች አንዳንድ ቀን የጨመረላቸው ከፌቡርዋሪ 2 ቀናት ወስዶና ወሩን 28 አድርጎ ነው)፡፡
ከእንግዲህ የሚቀሩን ከላይ የየዕለቱን ልዩነት ለዓመት ስናባዛ (ቁጥር ፪ና ፫ ተመልከት) የቀሩን 15 ኬክሮስና 6 ካልዒት ናቸው፡፡ ሁለቱን  ከላይ ያየናቸውን (፬ና፭) ስንደምራቸው (12 ኬክሮስ + 3 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት) 15 ኬክሮስ ከ 6 ካልዒት ይመጣሉ፡፡
ቀደም ብለን አንድ ዕለት 60 ኬክሮስ ነው ብለናል፡፡ ስለዚህም አንድ ዕለት (60 ኬክሮስ) ለማግኘት ከላይ ያገኘነውን 15 ኬክሮስ በ 4 ማባዛት አለብን፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ጳጉሜ 6 የምትሆነው እነዚህ በየዓመቱ የተጠራቀሙት 15 ኬክሮሶች አንድ ላይ መጥተው በአራት ዓመት አንድ ጊዜ አንድ ዕለት ስለሚሆኑ ነው፡፡ እርሷም ሠግር(leap year) ትባላለች፡፡ ጎርጎርዮሳውያኑ ይህቺን ሠግር በፌቡርዋሪ ወር ላይ ጨምረው ወሩን በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ 29 ቀን ያደርጉታል፡፡
15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ተደምረው አንድ ዕለት መጡና በአራት ዓመት አንዴ ጳጉሜን ስድስት አደረጓት፡፡ የቀረችው 6 ካልዒትስ (ቁጥር ፭) የት ትግባ?
ካልዒት አንዲት ዕለት ትሆን ዘንድ 3600 ካልዒት ያስፈልጋሉ፡፡ ይህንን ያህል ካልዒት ለማግኘት 600 ዓመታት ያስፈልጉናል፡፡ ለዚህ ነው ጳጉሜ በየስድስት መቶ ዓመታት ሰባት የምትሆነው፡፡ እስካን የጠየቅኳቸው የባሕረ ሐሳብና የታሪክ ሊቃውንት በታሪካችን ውስጥ ጳጉሜን 7 የሆነችበትን ዘመን እንደማያውቁ ነግረውኛል፡፡ ሒሳቡ ሲሰላ በየ 600 ዓመቱ ሰባት ትሆናለች ቢባልም አስቦ በስድስት መቶኛው ዓመት ሰባት የሚያደርጋት እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ በፈረንጆቹ ብሂል ‹ፌብሩዋሪ 30› ማለት የመሆን ዕድል ያለው ነገር ግን ሆኖሞ የማያውቅ ሊሆንም የማይችል(possible but never happen)› ተደርጎ እንደተወሰደው ሁሉ ምናልባት በኛም ጳጉሜን 7 ማለት እንደዚያው ይሆን ይሆናል፡፡
በነገራችን ላይ ጳጉሜን 5 ቀን በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድ ‹ዕለተ ምሪያ› ወይም የተመረጠች ቀን ትባላለች፡፡ የጌታችን ልደት ለመጠበቅ ሊቃውንቱ ሲያሰሉባት የቆየችው ዕለት በመሆኗ ነው ይህንን ስያሜ ያገኘችው፡፡ የጌታችንን ልደት ቀን የምትወስነው ጳጉሜ 5 ቀን ናት፡፡ ልደት የሚውለው ጳጉሜ 5 በዋለበት ቀን ነው፡፡ ለምሳሌ ዘንድሮ ጳጉሜን 5 ቀን ረቡዕ ነው የምትውለው፤ ስለዚህም በ2007 ዓም ልደት የሚውለው ረቡዕ ነው፡፡ በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ ጳጉሜን 6 ስትሆን ልደት በ28 የሚከበረው ዕለተ ምሪያን ስለማይለቅ ነው፡፡ ስድስተኛዋ ቀን ልደትን በአንድ ቀን ስታዘልለው እኛ በ28 እናከብረዋለን፡፡ ልደት ጳጉሜ 5 ቀንን(ዕለተ ምሪያን) ስለማይለቅ፡፡ ታድያ ምነው እነ ጥምቀትና ግዝረት አይለወጡም? ቢሉ፡፡ ሊቃውንቱ የሚሰጡት መልስ ‹ትውልድ ሱባኤ እየቆጠረ በተስፋ የጠበቃት ዕለተ ልደትን ስለሆነ ነው፤ ሌሎቹ የመጡት በልደቱ ምክንያት ነው›› የሚል ነው፡፡
በጎርጎርዮሳውያንም ቢሆን በአራት ዓመት አንዴ ልደት ዝቅ ትላለች፡፡ የእነርሱ የማይታወቀን ጭማሪዋ ፌብርዋሪ ላይ ስለሆነች ነው፡፡ ያ ደግሞ አዲሱን ዓመት ካከበሩ በኋላ ስለሚመጣ ነው፡፡ የእኛ ግን የምትወድቀው ጳጉሜን መጨረሻ ላይ በመሆኗ ከአዲስ ዓመት በፊት ስለምትጨመር ጎልቶ ይታወቃል፡፡
እንግዲህ ጳጉሜ የምትባለው አስገራሚ ትንሷ ወራችን እንዲህ በስሌት የተሞላች፣ አምስት ሆና ቆይታ በየአራት ዓመቱ አንዴ ስድስት፣ በየስድስት መቶ ዓመቱ ደግሞ ሰባት የምትሆን ናት፡፡ ታላላቆቹ ወሮች ምንም ሳይፈጥሩ የልደትን ቀን የምትወስን፣ የዓመቱን ሠግር የምታመጣ፣ ታሪከኛ ወር ናት፡፡ ትንሽ ትልቅ ማለት እንዲህ ነው፡፡

42 comments:

 1. Dani I love to read your blog but this is not good. It has a lot of number so it is so difficult to understand the current government leaders. As you know that most of us came from forest so we don’t want deal with number. That’s why we said Ethiopia has one hundred year history because we can’t read more books. Please make it easy to us and don’t play with number. Thank you.

  ReplyDelete
 2. nice explanation kale hiwot yasemalen

  ReplyDelete
 3. Egziabhair Agelgotihin yimiralh

  ReplyDelete
 4. Ye tenesh telek malete yehi new...lol lemen gen Dani be English em atesefeme.?

  ReplyDelete
 5. በጣም አሪፍ ማብራሪያ ነው ከዚህ ቀደም የማናውቀው፡፡ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
 6. ዳኒ በጣም የሚግረም ነው
  ባሕረ ሐሳብን ለማወቅ ብዙ አባቶች ተመኝተው ነበር። ይሁን እንጂ ሁሉ የሚሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና የመንበረ እስክንድርያ አስራ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ ለነበረው ለቅዱስ ድሜጥሮስ ተጸልጾለታል። ድሜጥሮስ ማለት መስታወት ማለት ነው። መስታወት፦ በጥርስ ያለውን እድፍ በጸጉር ያለውን ጉድፍ እንደሚያሳይ ሁሉ ድሜጥሮስም የተሰወሩ በዓላትን እና አጽዋማትን አሳይቶናል፤ አንድም ድሜጥሮስ ማለት መነጽር ማለት ነው። መነጽር፦ የራቀውን አቅርቦ ፣የረቀቀውን አጉልቶ፣ የተበተነውን ሰብስቦ እንደሚያሳየው ሁሉ ድሜጥሮስም የራቁ አዝማናትን አቅርቦ፣ የተበተኑ አጽዋማትን ሰብስቧልና መስታወት ተብሏል።
  ድሜጥሮስ እጅግ የበቃ ሰው ነበርና ቀድሶ ሲያቆርብ የሰው ኃጢአት ተገልጾለት ‘’አንተ ለስጋ ወደሙ በቅተሃል ቁረብ፣ አንተ አልበቃህም ተመለስ’’ ይል ነበር። በዚህን ጊዜ ሕዝቡ ‘’በንጹሑ በማርቆስ ወንበር ላይ ከነሚስቱ መቀመጡ አንሶት እርሱ እንዳንቆርብ ይከለክለን ጀመር’’ በማለት በሐሜት ወደቁ በዚህም የሚጎዱ ሆኑ። በዚህን ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ለድሜጥሮስ ተገልጾ ‘’ኢትፍቅድ አድኅኖ ርእስከ አላ ክሥት ዘሀሎ ምስሌከ ወማእከለ ብእሲትከ- በአንተና በእርሷ መካከል ያለውን ሚስጢር ግለጽ፤ ኖላዊሰ ኄር ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግዒሁ - እውነተኛ እረኛ ለበጎቹ እራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነውና፤ እራስህን መግለጽ ውዳሴ ከንቱ አይሆንብህም’’ ብሎታል። ድሜጥሮስም መልአኩ እንዳዘዘው ሕዝቡን አንድ አንድ እንጨት ይዘው እንዲመጡ አዟቸዋል። በዕለተ ሰንበትም የተሰበሰበውን እንጨት እንደ መስቀል ደመራ አቃጥሎ ቅዳሴ ገባ። ከቅዳሴም ከወጣ በኋላ በሚነደው እሳት ውስጥ ገብቶ እየተመላለሰ ያጥን ጀመረ። ‘ሚስቱን’ ከምቋመ አንስት ጠርቶ ስፍሒ አጽፈኪ - ልብስሺን ዘርጊ ብሎ ከእሳቱ ፍም እየዘገነ በልብሷ ላይ አድርጎላታል። እርሷም በሕዝቡ መካከል ዞራ ብታፈሰው ከልብሷ ዘሃ አንዲት እንኳን አልጠቆረም። ሕዝቡም አባታችን ይህንን ያደረከው ለምንድን ነው? ብለው ጠየቁት። እርሱም እኔ እሾምበት እከብርበት ብዬ አይደለም ይልቁንም እናንተ በሐሜት እንዳትጎዱ በማለት መልአከ እግዚአብሔር ግለጽላቸው ስላለኝ ነው። ይህ እሳት እኔ እና እርሷን እንዳላቀጠለን ሁሉ ይህን ያህል ዘመን አንድ ምንጣፍ አንጥፈን አንድ አንሶላ ተጋፈን ስንኖር በአዳማዊ ግንኙነት /በሩካቤ / ሳንተዋወቅ እርሷ ሴት እኔም ወንድ እንደሆንን ነው የምንኖረው አላቸው። በዚህን ጊዜ ሕዝቡ “ኦ አቡነ ሥረይ ለነ ኃጢአተነ - አባታችን ሆይ ይቅር በለን” በማለት ከእግሩ ስር ወድቀዋል። እርሱም “ይፍታሕ ወይሥረይ ይኅድግ ወያንጽሕ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” ብሎ ናዝዋቸዋል። ኑዛዜም በዚህ ጊዜ እንደተጀመረ አባቶቻችን ይናገራሉ።


  ዳኒ ይህን ለመረዳት መንፈስ ቅዱስ ካልቃኘው በሰቅ አእምሮ አይቻልም
  ለድሜጥሮስ የገለጠ ላንተም ያናገርረህ አምላክ ይክበር ይመስገን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you, I love it

   Delete
  2. ዳኔ መድኃኔአለም አይለይህ የተሰጠህ ጸጋ ዘላቂ ያርግልህ ። መልካም አዲስ እመት ለምንወዳት አገራችን እና ለሞላው ቤትሰብህ።አሜን

   Delete
 7. ለምትሰጠን ዘመኑን የዋጀ ትምህርት እግዚአብሔር ከዚህ በላይ አብዝቶ ይስጥህ!ለምትሰጠን ዘመኑን የዋጀ ትምህርት እግዚአብሔር ከዚህ በላይ አብዝቶ ይስጥህ!

  ReplyDelete
 8. ለምትሰጠን ዘመኑን የዋጀ ትምህርት እግዚአብሔር ከዚህ በላይ አብዝቶ ይስጥህ!ለምትሰጠን ዘመኑን የዋጀ ትምህርት እግዚአብሔር ከዚህ በላይ አብዝቶ ይስጥህ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለህይወት ያሰማልን

   Delete
 9. qale hiwet yasemalinge.

  ReplyDelete
 10. Egziabher yagelglot zemenehn yibark.

  ReplyDelete
 11. Informative. But most readers would benefit more if one writes about the basics on Ethiopian calender per se. How come we have a separate calander from the rest of the world? Is it Julian (as some say so)? is it the same as the coptic calender? How come we don't have leap year correction as the gregorian? what is the effect?....

  ReplyDelete
 12. ጳጉሜ ማለት የትንሽ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዳኒ ልክ እንዳንተ ጌታዬ ስላሴ እድሜ ጤና ማስተዋል ይስጡህ ድንግል ትጠብቅህ

  ReplyDelete
 13. ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡ ረጅም የአገልግሎት ዕድሜን ይስጥልን፡፡ አሜን!!!

  ReplyDelete
 14. Phagume - chimari(yametu,yeweru...?) Stay blessed

  ReplyDelete
 15. is there someone who can explain the difference b/n Ethiopian calendar and European ? why we are seven years late?

  ReplyDelete
  Replies
  1. I found this resource from Zebene Lema. As he said the European stared counting the date from Rome cevilization. Ethiopia start from Jessuse Chrise born. Other people say Italy was tried to conolized Ethiopia so Ethiopia doesn't want to follow European calander. However it doesn't make sence to me the second conclution because we had calander more than 1500 years but italy was tried to takeover Ethiopia 116 years. The Anonymous person, my suggestion to you, if you live in Ethiopia use Ethiopian calander or if you live Europe use European calander. All the time history is change so don't trust anybody. As you read Danial Kebret note. He said Paguma sometimes will be seven. I never heard when Pagume with number seven. What I know was three years 5 and one year 6. now he change the number.

   Delete
  2. European started from Rome cevilization and Ethiopia started from Crise Borne.

   Delete
  3. The difference is both in years and days. According to the Ethiopian calendar, the current year is 2007, which is clearly Seven (eight) years behind the Gregorian. The Ethiopian months are also lagging by seven, eight, nine or ten days depending on where the two calendars' months match. We have 12 months with 30 days each and a 13th month with five or six days. The 13th month is called "Pagumen" to mean the thirteenth. It is either six or five days whether the year is leap year. The hours of the day are not named and divided in the same way as in the European. For example, the European say 12 O'clock (AM) when it is actually 6 at midday. In the Ethiopian evenings are considered parts of the next day. In this article, it is attempted to give scriptural background to the 7(8) years difference in the calendars according to the teachings of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. The difference lies in determining the exact date of the birth of Christ. According to Dionasius, a Roman monk, the birth of our Lord Jesus Christ was 753 years after the foundation of the city of Rome. It is according to his calculation that the world joins the second millennium, in spite of the fact that, researchers many years after him have already discovered he has made a mistake by at least four years. Their argument was based on the Biblical clues given at Mt. 2:1 and Lk.3: 1-3, 22-23. In Mt. 2.1, it was mentioned that Jesus was born during the time of King Herod. The King died just after the birth of Christ. Meanwhile, it was also recorded that the king died 750 years after the city of Rome was founded. The other Gospel tells us that Jesus was 30 by the time he began his ministry. It was also mentioned that this was the fifteenth year of the reign of Tiberius Caesar. Historians...

   Delete
  4. The Ethiopian calendar (Amharic: የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር?; yä'Ityoṗṗya zämän aḳoṭaṭär) is the principal calendar used in Ethiopia and also serves as the liturgical calendar for Christians in Eritrea and Ethiopia belonging to the Orthodox Tewahedo churches, Eastern Catholic Church and Lutheran Orthodox Church. It is a sidereal calendar based on the older Alexandrian or Coptic calendar, which in turn derives from the Egyptian calendar, but like the Julian calendar, it adds a leap day every four years without exception, and begins the year on August 29 or August 30 in the Julian calendar. A seven- to eight-year gap between the Ethiopian and Gregorian calendars results from an alternate calculation in determining the date of the Annunciation of Jesus.

   Like the Coptic calendar, the Ethiopic calendar has twelve months of exactly 30 days each plus five or six pagome days, which comprise a thirteenth month (all of which is a public holiday). The Ethiopian months begin on the same days as those of the Coptic calendar, but their names are in Ge'ez. The sixth epagomenal day is added every four years without exception on August 29 of the Julian calendar, six months before the Julian leap day. Thus the first day of the Ethiopian year, 1 Mäskäräm, for years between 1901 and 2099 (inclusive), is usually September 11 (Gregorian). It, however, falls on September 12 in years before the Gregorian leap year.

   The current year according to the Ethiopian calendar is 2007, which began on September 11, 2014 AD of the Gregorian calendar
   Enkutatash is the word for the Ethiopian new year in Amharic, the official language of Ethiopia, while it is called Ri'se Awde Amet (Head Anniversary) in Ge'ez, the term preferred by the Ethiopian Orthodox Church. It occurs on September 11 in the Gregorian calendar, except for leap years, when it occurs on September 12. The Ethiopian calendar year 1998 'Amätä Məhrät ("Year of Mercy") began on September 11, 2005. However, the Ethiopian years 1996 and 1992 AM began on September 12, 2003 and 1999, respectively.

   Delete
  5. የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ።

   በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።

   የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ. ሆነ።

   የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም።

   በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም። ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው።

   Delete
  6. Solar year is divided into ordinary year and leap year. First, 365 days divided by 12 equals 30 and remainder 5 is called an ordinary year. Second, 366 days divided by 12 equals 30 and remainder 6 is called leap year.
   The Tropical/Ethiopian calendar month is a standard division of time (365 or 366 days divided by 12 months) is equal to 30 and remainder 5 or 6. 12 calendar months of Ethiopia are called Meskeram, Tikimit, Hidar, Tahisas, Tir, Yekatit, Megabit, Miyazia, Ginbot, Sene, Hamle and Nehase; each has 30 days, and the remainder Pagume has 5 or 6 days in a leap year.
   The basic problem in today’s Ethiopia is there is neither salary income nor income tax revenue during 5 or 6 days of Pagume. Besides, although the economics of Pagume is undiscovered there are many Ethiopians who illicitly believe that Pagume is the 13th month. I also was one of these who used to write Pagume as the 13th month. For example, I wrote that 13th months of Sunshine could not be beautiful with only 12 months of salary. Thus I recommended all employers must begin to pay salary to employees during Pagume and government of Ethiopia could mobilize tax revenue during Pagume.
   But I discovered very recently that only 5 or 6 days of Pagume cannot be equivalent with 30 days of each month so that it cannot deserve to be called 13th month. Moreover, both the 1953 Ethiopia’s income tax law and the current income tax law oblige every employer how to treat the income tax base of Pagume.

   “Employers have an obligation to withhold the tax from each payment to an employee, and to pay the withheld amounts to the Tax Authority the amount withheld during each calendar month, in applying preceding income attributable to the months of Nehase and Pagume shall be aggregated and treated as the income of one month.” Income tax law (2002) at 1873
   The statement income attributable to the months of Nehase and Pagume shall be aggregated and treated as the income of one month perfectly reveals that Pagume is a subset of special 12th month. This means that 30 days of Nehase and 5 or 6 days of Pagume is equal to 35 or 36 days of one month.

   2The Gregorian calendar months

   Grant and Hill (1962:41-42) explained that the calendar in use is the Gregorian calendar, and dates from the year 1582, when Pope Gregory caused the necessary changes to be made in the calculation of

   Delete
  7. The Ethiopian calendar has a year of 365 days and leap years of 366 days. The Ethiopian year is divided into 12 months of thirty days each and one intercalary month of 5 days, or 6 days in a leap year.
   The Ethiopian Calendar is similar to the Julian calendar in that it has a leap year every four years and does not miss one at the turn of the century. However it is not true to say that Ethiopia uses the Julian calendar. In fact their calendar owes more to the old Coptic Calendar.

   The relationship between the Ethiopian and the Gregorian calendars varies when ever the Gregorian Calendar misses a leap year. The present situation (that is between 1900 and 2099 Gregorian) is that the year starts on 11th September (Gregorian) and from then until 31st December the year number is seven less than the Gregorian year number. From 1st January to 10th September the difference is eight. This means that the Ethiopians celebrated the dawning of the millennium (AD2000) at midnight on 10th September 2007 (Gregorian). The difference in year numbering is due to the Ethiopian Orthodox Church disagreeing with the Roman Catholic Church about when Christ was born. The Ethiopian Orthodox Church believe that Christ was born exactly 5,500 years after the creation of the world which they then equate to 7BC. Some experts believe that they are probably nearer the true date than the Gregorian calendar.

   Delete
 16. THANK YOU DANI. EGZIYABHER YIBARKIH!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 17. desyelal..I wish you could tell us more on this subject.

  ReplyDelete
 18. ዳኒ ይህን ለመረዳት መንፈስ ቅዱስ ካልቃኘው በሰተቀር በደፈናው ለመረዳት አይቻልም
  ለድሜጥሮስ የገለጠ ላንተም ያናገርረህ አምላክ ይክበር ይመስገን
  መልካም አዲስ አመት

  ReplyDelete
 19. ደግነቱ ይህ ፈተና ላይ አይመጣም! ወይ አማርኛ ፥)

  ReplyDelete
 20. ዳኒ በተጨማሪ በሂወት ስላሉና በቅርብ ግዜ ይዘመኑ ፈተና ያሽነፉ መንፈሳዊ ኣባቶችን ሂወት ፃፍልን እባክህ ትንሽ ወንድምህ ስሆን ተረዳኝ

  ReplyDelete
 21. ወንድም ዳንኤል ጥሩ አገላለጽ ነው ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ታላላቅ አባቶቻችን የመጻሕፍት ትርጓሜ ላይ ያላቸው አገላለጽ የመጀመሪያሪዎቹን ጥሬ ቃል ቢንስ አውቆ ለቀረበ ነው እንጂ የሚገባው ወይም የሚቀለው ለየኔ ቢጤው ከባድ ነውና እንደዚህ ዘርዝሮ ማስረዳት ብዙ ወገንን ከድንግዝግዝ አመለካከት ያወጣልና ጥሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችንም ያድርግልን አሜን፡፡
  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 22. Great! Great! Great!

  ReplyDelete
 23. Can you imagine the depth of the knowledge of our fathers had? Thank you Dn. Daniel. Keep on letting us know such histories.

  Regards

  ReplyDelete
 24. ዳኒ ይህን ለመረዳት መንፈስ ቅዱስ ካልቃኘው በሰተቀር በደፈናው ለመረዳት አይቻልም
  ለድሜጥሮስ የገለጠ ላንተም ያናገርረህ አምላክ ይክበር ይመስገን
  መልካም አዲስ አመት

  ReplyDelete
 25. I adore the work of the church to maintain this knowledge. But I think this is earthly knowledge which is very important to determine holydays. But what we should be very careful is such knowledges may change and when they do we should not ascribe this change with the theology.

  The very concern that I have is that, for example, in time of Galileo, the catholic church was thought to have believe the earth was flat. However, when it was discvored it is not, the church scholars tried to detain this thought as if the belief that the roundness of the earth contradicts the church theology. But this is presumption not actual theology.

  ReplyDelete
 26. አስተያየቴን ታየዉ እና ምላሽ ትሰጠኛለህ ብየ ተሰፋ አደርጋለሁ! በአመርኛ ፊደል ዉስጥ ተደጋጋሙ ፊደሎች አሉ ያለትርጉም አልተደጋገሙም የሆነ ምክንያት ይኖረቸዋል፡፡ልዩነታቸዉ ግን ለኔ እንቆቅልሽ ሆኖብኛል…..ልምሳሌ ሀ ከ ኀ ከሐ……ሰ ከ ሠ ጥናት የሚፈልግ መስለኛል (ይርጉ ፋነታ እባላለሁ)

  ReplyDelete
 27. ሒሳቡ ሲሰላ በየ 600 ዓመቱ ሰባት ትሆናለች ቢባልም አስቦ በስድስት መቶኛው ዓመት ሰባት የሚያደርጋት እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ቢታሰብበት (ማይቻል የለም)

  ReplyDelete
 28. ቆንጆ ገለፃ

  ReplyDelete
 29. God bless u!! I wish long life 4 u!!

  ReplyDelete
 30. God bless u!! I wish long life 4 u!!

  ReplyDelete