Thursday, August 7, 2014

ንሥር (ክፍል ሁለት)

ንሥር ሳይፈትን አያምንም፤ አይተማመንምም፡፡ ሴቷ ንሥር ባል ማግባት ስትፈልግ አንድ እንጨት ታነሣና ወንዱ እየተከተላት ወደ ላይ ትመጥቃለች፡፡ እስከ ሰማይ ጥግ ከደረሰች በኋላም ያንን እንጨት ትለቀዋለች፡፡ ያን ጊዜ ወንዱ እንጨቱ መሬት ከመድረሱ በፊት በፍጥነት በመወርወር መያዝና ለሴቷ መልሶ ማምጣት ይጠበቅበታል፡፡ ሴቷም እንጨቱን ተቀብላ እንደገና ወደ ቀጣዩ ከፍታ ትመጥቅና እንጨቱን መልሳ ትጥለዋለች፡፡ አሁንም ወንዱ ንሥር ከእንጨቱ የውድቀት ፍጥነት ቀድሞ ያንን እንጨት በመያዝ ለሴቷ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ እንዲህ ያለው ፈተና ወንዱን ለሰዓታት ያህል ይጠብቃዋል፡፡ ከፍታው እየጨመረ፣ እንጨቱም ይበልጥ እየተወረወረ ይሄዳል፡፡ ሴቷ ንሥር ወንዱ ንሥር ፈጣንና የተወረወረለትን ለመያዝ ያለውን ቆራጥነት እስክታረጋግጥ ድረስ ፈተናው ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻም ቆራጥና ፈጣን፣ ማንኛውም ችግር የማይበግረው መሆኑን ስታረጋግጥ ባልነቱን ትፈቅድለታለች፡፡
ንሥርም እንዲህ ትልሃለች፡- በግላዊ ሕይወትህ፣ በንግድህም ሆነ በሌላው ኑሮህ ከሰዎች ጋር መወዳጀት፣ አብሮ መሥራትና መንገድ መጀመር ያለብህ ለዓላማቸው ምን ያህል ጽኑና ቆራጥ፣ ትጉና አይበገሬ መሆናቸውን አረጋግጠህ መሆን አለበት፡፡ ሳታረጋግጥ መግባት ትርፉ ፀፀት ነው፡፡ እንኳን ሌሎችን ራስህንም ለአዲስ ተልዕኮ ከማሠማራትህ በፊት ፈትነው፡፡
ንሥር በሕይወቱ የሚመጡ ለውጦችን እንደመጡ በአጋጣሚ አይቀበላቸውም፡፡ ተዘጋጅቶና ዐቅዶ እንጂ፡፡ ሴቷ ዕንቁላል የመጣያ ጊዜዋ ሲደርስ ባልና ሚስቱ ዕንቁላል ለመጣያ ምቹና ተስማሚ የሆነውን ቦታ ያፈላልጋሉ፡፡ ያ ቦታ ማንኛውም ዓይነት ጠላት የማይደርስበት፣ ከከፍታዎች ሁሉ በላይ የሆነና ከማንኛውም ዓይነት አደጋ  ራስንና ልጆችን ለመከላከል የሚመች መሆን አለበት፡፡ ቦታው በባልና ሚስቱ ከተመረጠ በኋላ ወንዱ ወደ መሬት ወርዶ እሾህ ለቅሞ ወደ ተራራው ንቃቃት ያመራል፡፡ በዚያም ይደለድለዋል፡፡ ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ወርዶ አስፈላጊ የሆኑትን እንጨቶች ሰብስቦ ወደ ንቃቃቱ ይመጣና በእሾሁ ላይ ይረመርመዋል፡፡ እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ምድር ይመለስና እሾህ ሰብስቦ ወደ ጎጆው ያመራል፤ በእንጨቱም ላይ ይረበርበዋል፡፡ ለአራተኛ ጊዜ ወደ መሬት ተመልሶም ለስላሳ ሣር ያመጣና በእሾሁ ላይ ያነጥፋል፡፡ በአምስተኛ ጉዞውም እሾህ አምጥቶ በሣሩ ላይ ያደርጋል፡፡ በስድስተኛ ጉዞውም በእሾሁም ላይ ሣር ይነሰንሳል፡፡ በመጨረሻውና በሰባተኛ ሥራው ላባዎቹን በመካከል ላይ ያደላድላቸዋል፡፡ በጎጆው ዙሪያ የተደረገው እሾህም ዙሪያውን ከጠላት ያጥርለታል፡፡
እነሆ ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ምንጊዜም ለለውጥ ራስህን አዘጋጅ፡፡ ነገሮች ድንገት እንዲደርሱብህ ዕድል አትስጣቸው፡፡ አስበህ፣ ተዘጋጅተህ፣ ወስነህ፣ ሂሳብ ሠርተህ እንጂ፡፡ ኑሮህ በድንገቴና በአጋጣሚ የተሞላ አይሁን፡፡ የቻልከውን መጠን ያህል ተዘጋጅ እንጂ፡፡ መጽሐፉስ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› አይደል የሚለው፡፡ ለማደግ ተዘጋጅ፣ ለመማር ተዘጋጅ፣ ለጓደኝነት ተዘጋጅ፣ ለማግባት ተዘጋጅ፣ ለመውለድ ተዘጋጅ፣ አዲስ ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅ፣ ቤት ለመሥራት ተዘጋጅ፣ መኪና ለመግዛት ተዘጋጅ፣ ለምትለውጣቸው ነገሮች ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ይኑርህ፡፡
ንሥር ትዳሩን በእኩልነት ነው የሚመራው፡፡ ወንዱ ንሥር ጎጆውን ሠርቶ ሲጨርስ ሴቷ ወደ ጎጆው ትገባና ዕንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡ ትዳርን በእኩልነት ነው የሚመሩት፡፡ እርሷ ዕንቁላል ስትጥል እርሱ ደግሞ አካባቢውን ከጠላት ይጠብቃል፡፡ ወደ መሬት እየተመላለሰም ምግብ ይሰበስባል፡፡ ልጆችን መመገብ፣ ማሳደግ፣ በረራ ማለማመድ፣ ከጎጇቸው ርቀው እንዲያድኑ ማሠልጠን የሁለቱም የጋራ ኃላፊነት ነው፡፡ ድርሻ ይካፈላሉ እንጂ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች አይሆኑም፡፡
ስለዚህም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ትዳር የእኩልነት ጉዞ ነው፡፡ የሥራ ድርሻ ክፍፍል እንጂ የበታችና የበላይ ክፍፍል አይኖረውም፡፡ ሁሉም የችሎታውንና የተፈጥሮውን የሚያደርግበት፣ የጋራ ኃላፊነት የሚወሰድበት ቤት ነው ትዳር፡፡
ንሥር ልጆቹን ደስታንም መከራንም ያስተምራቸዋል፡፡ የንሥር ጫጩቶች አምሮና ደኅንነቱ ተጠብቆ በተሠራው ጎጆ ይፈለፈሉና ወላጆቻቸው እየመገቧቸው እዚያ ጥቂት ያድጋሉ፡፡ ለዐቅመ ንሥር ሲደርሱ የምቾቱ ድልቅቂያ ያበቃና ሴቷ ንሥር ጫጩቶቹን ከጎጆዋ እያወጣች ዐለቱ ላይ ትጥላቸዋለች፡፡ ጫጩቶቹ በፍርሃት ይዋጡና ተመልሰው ወደ ጎጆው እየዘለሉ ይገባሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ማደፋፈሪያ ነው፡፡ የማያድሩበት ቤት አያመሻሹበትም ይባል የለ፡፡‹ሰው እናትና አባቱን ይተዋል› የሚለው በእነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሊኖር ይችላል ማን ያውቃል፡፡ ለጥቂት ጊዜያት እንዲህ ታለማምዳቸውና በቀጣዩ ጊዜ ከጎጆው አውጥታ ወደ ዐለቱ በመጣል የጎጆውን ለስላሳውን ክፍል ታነሣባቸዋለች፡፡ እነርሱም እንደለመዱት ወደ ጎጆው ሮጠው ዘለው ሲገቡ እሾሁ ይቀበላቸዋል፤ ያቆስላቸዋል፣ ያደማቸዋልም፡፡ እነርሱም እንዲያ የሚወዷቸው እናትና አባታቸው ለምን እንደሚያሰቃዩዋቸው ግራ እየገባቸው ወደ ዐለቱ ተመልሰው ይወጣሉ፡፡
ከጎጆው ውጭ በአድናቆት መቆማቸውን የምታየው ኣናታቸው ከዐለቱ ገፋ ታደርጋቸውና አየር ላይ እንዲንሳፈፉ ትለቃቸዋለች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አየሩን የቀዘፉት ጫጩት ንሥሮች በፍርሃትና በድንጋጤ ተውጠው ወደ ታች ሲወረወሩ አባታቸው ይመጣና ከመውደቃቸው በፊት ቀልቦ በትከሻው ተሸክሞ ወደ ዐለቱ ያወጣቸዋል፡፡ እነርሱም በደስታ ይዋኛሉ፡፡ እናት ስትወረውር፣ አባት በአየር ላይ ሲቀልብ፣ ልጆችም ሲወረወሩና ሲጨነቁ፣ አባታቸው ሲቀልባቸው ሲደሰቱ ጥቂት ጊዜያት ያልፋሉ፡፡ በአካል እየጠነከሩ፣ ከመከራውም ከደስታውም እየተማሩ፣ አካባቢውንም እየለመዱት ይሄዳሉ፡፡ በመጨረሻም ራሳቸውን ችለው ይበራሉ፡፡ ከወላጆቹ ጋር ኖሮ የሚያረጀውን ቢያዩ ኖሮ ንሥሮች ምን ይሉ ይሆን?
ለዚህ ነው ንሥር እንዲህ የሚለው፡- ለልጆቻችን ከልክ ያለፈ ክብካቤ መስጠት የትም አያደርሳቸውም፡፡ መከራውንም፣ ችግሩንም፣ ፈተናውንም፣ ትግሉንም፣ ተግዳሮቱንም እንዲለምዱት ማድረግ አለብን፡፡ አፈር አይንካህ፣ የፈሰሰ ውኃ አታቅና፣ ማንም በክፉ አይይህ፣ እንደ ዕንቁላል ትሰበራለህ፣ እንደ መስተዋት ትሰነጠቃለህ እያሉ ነገ በእውኑ ዓለም የማያገኙትን ቅንጦትና ምቾት ብቻ ማሳየቱ የትም አያድርሳቸውም፡፡ እሾሁንም፣ ዐለቱንም፣ መወርወሩንም፣ መውደቁንም፣ መታገሉንም፣ ማሸነፉንም ይልመዱት፡፡ ነገን በጥቂቱ ዛሬ እናሳያቸው፡፡ የሚወዱን ሰዎች ማለት የሌለ ገነት ፈጥረው የሚከባከቡን ማለት ብቻ አይደሉም፡፡ ሰው መሆን ለሚያጋጥመው ተግዳሮት ሁሉ ዝግጁ እንድንሆን የሚያደርጉን እንጂ፡፡ ቤት ሣርና ላባ ብቻ ሳይሆን እሾህም ሊኖረው ይገባል፡፡
ንሥር ሲዳከም የት መሄድ እንዳለበት ያውቃል፡፡ ንሥር ሲዳከም ላባዎቹ ደካሞች ይሆናሉ፡፡ እንደቀድሞው በፍጥነት እንዲበር፣ ወደ ላይም እንዲመጥቅ አያስችሉትም፡፡ እንደ በረቱ መዝለቅ የለ፡፡ ጉልበቱ ሲደክም፣ ላባው ሲነጫጭና የሞት ሽታ ሲሸተው፣ ጉልበቱ ሳይከዳው በፊት ወደ አንድ ማንም ወደማይደርስበት የተራራ ጫፍ ያመራና በንቃቃቶቹ መካከል ጎጆ ሠርቶ ይቀመጣል፡፡ እዚያ ምግቡን አከማችቶ ያርፋል፡፡ የጽሞና ጊዜም ይወስዳል፡፡ የተረፉትን ላባዎቹን እየነጨ መለመላውን ይቀራል፡፡ ቀስ በቀስም አዲስ ላባ ያበቅላል፡፡ ኃይሉም እንደ ጥንቱ ይታደሳል፡፡ ያን ጊዜ ወደ ቀድሞ ኑሮው በአዲስ ጉልበትና በአዲስ መንፈስ ይመለሳል፡፡
እናም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ጉልበትህና መንፈስህ፣ ሐሳብህና የማመንጨት ዐቅምህ ሲዳከም ዝም ብለህ አትናውዝ፤ እስክትደከርትም አትሟዘዝ፡፡ ነገሮች እንጨት እንጨት ሲሉህ፣ የማስቲካው ቃና ሲያልቅ፣ የሸንኮራው ጣዕም ሲሟጠጥ ‹ደኅና ነኝ› እያልክ ራስህን አትሸንግል፡፡ ይልቅ የት መሄድ እንዳለብህ አስብ፡፡ የጽሞና ጊዜ ውሰድ፤ ለአእምሮህ ምግብ የሚሆኑህን ሰብስብና መንን፡፡ የማሰቢያ፣ የማሰላሰያም ጊዜ ውሰድ፡፡ የድሮ ሐሳቦችህን እንደ ላባዎቹ ነቃቅል፡፡ በቃኝ በል፡፡ ጊዜ ወስደህ ካሰብክ፣ ካነበብክ፣ ከመረመርክ፣ ካሰላሰልክ፣ ካወጣህና ካወረድክ አዳዲስ መንገዶች፣ አዳዲስ ሐሳቦች፣ አዳዲስ ነገሮች፣ አዳዲስ አመለካከቶችን ማብቀል ትችላለህ፡፡ ያን ጊዜ በአዲስ ጉልበት እንደገና ለመመለስ ትበቃለህ፡፡
እንደ ሰው ብትፈጠርም እንደ ንሥር ኑር፡፡
(መረጃ የሰጠኝን የሲያትሉን ኃይለ ኢየሱስ አመሰግነዋለሁ)

© ሁለቱም ክፍሎች በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ወጥተዋል

44 comments:

 1. Thank you DANI I will take this advice seriously GOD bless you and your family

  ReplyDelete
 2. yehawariyat tselotina limena semta yetegeletsech emebetachin yantenim tsegawun tabzalih memhirachin

  ReplyDelete
 3. Thanks Deacon Daniel.yeante eyita betam tilik neew betam astemarie neew.EGIZIABIHAIR BICHA BEEDMIE BE TSEGA YITEBIKILIN.

  ReplyDelete
 4. Egziabeher Yeante Aynet Sewochen Ayasatan, Melkam Ethiopiawi Nehe.

  ReplyDelete
 5. Replies
  1. Getahun (Arba Minch)August 8, 2014 at 12:38 PM

   Wishing Long life,Dani

   Delete
 6. Egziabher Yabertah tilik timihirt honognal amesegnalehu!!!

  ReplyDelete
 7. Deacon Daniel betam des yemil tsuf new.Sile ensesat(Anima) manbeb betam des yemil neger new.THANK YOU DANI....Le la degemo ye ensesat(Anima) endemitsef Tesfa adergalew.lemisale ye nib,gundan,ebab....e,t.c.Thank you again.

  ReplyDelete
 8. ወይ ንስር ወንድሜ ዳኒ ምን እንደምል አላውቅም ግን ባንተ ጹሁፍ እግዚአብሔር ያስተምረኛልና በርታ እግዚሔብሄር ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 9. Dear dani tnxs for all abizto geta yibarkih

  ReplyDelete
 10. dani, u really inspired me for better change. Thank u so much.

  ReplyDelete
 11. Betam des yemil eyeta naw.. Egizyabeher Yestelen!!!

  ReplyDelete
 12. kalehiwet yasemln .

  ReplyDelete
 13. betam arif neger new. Egizabher yebarkeh.

  ReplyDelete
 14. Betam Arief tsehuf new. bezu kum negerochen yestameral. Egizabher yebarkeh.

  ReplyDelete
 15. Betam astemari tsehuf new. Dn.Danile minim enkwane yegna ye Ethiopian astedadeg tolo rasen chilo lemenor yemiyaschil bayehonim andande sew erasun chilo sinor degmo maberetatate yasfelegale beye amnalehu.

  ReplyDelete
 16. Dn.Daniel !!!! ahunem Egziabhir tina,selamun yesteh, bewqet lay ewqetun ychmreleh. enat Ethiopian AMLAKACHEN ytebqlen Embrehan enatachen meljawa ke hulachne ayleyen.

  ReplyDelete
 17. Magnificent! Truly exceptional Dn. Dani!!! Kalehiot yasemalin, Egziabher bandim belelam yastemirl

  ReplyDelete
 18. Egziabher bandim belelam yastemiral, So Magnificent view.
  Kale hiot yasemalin!

  ReplyDelete
 19. ይገርማል፤አስተማሪነቱ ብዙ ነዉ፤እናመሰግናለን፣ዳኒ፡፡

  ReplyDelete
 20. Hello my brother Daniel, God bless you for this great job. Please don’t post anything from” አዲስ ጉዳይ መጽሔት “ At the movement this magazine is part of terrorist organization so it will be bad for us to see you in the jail. I know this magazine will get permission after 2007 election so you can copy from this magazine after the election. Please we don’t want see you in the jail so stop posting from this magazine. I am very scare to write this comment but you don’t scare to write the fact on your blog. I think you are crazy just like Andargachew Tega because you don’t care about your life. God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you so much the Anonymous person for your comment. However you use a bad word "CRAZY" He is not crazy but he love his country more than his family. Evenif you use a bad word I love your comment and now I know how people care for other. Daniel please listen the Anonymous person suggestion otherwise you will in trouble. I remember before you fired from Mahabere Kdusan many people gave you advise but you didn't listen them then you got fired. This is the same situation so please listen the Anonymous person. Thank you.

   Delete
  2. ኢትዮጵያ ዉስጥ terrorist organization ማለት የወያኔን አቋም የሚቃወም ተቀናቃኝ ፓርት ወይም ግለሰብ ማለት ነው፡፡

   Delete
 21. Thank you very much D/n Daniel appreciated!! Fetari edmiena tiena yistih!

  ReplyDelete
 22. interesting I like it bless you !!

  ReplyDelete
 23. Dn,Daniel beyitegnawum ye hiwot ketemeyochi maleteme kelejinete esekewuket ,matatena magengete ,dikamina birtat,hiwotatchinen endete bezedena betegate memerate endalebe yemiastemr tsehufe new. Egiziabehere yistilen , Amelake Kidusa Yitebikeh.

  ReplyDelete
 24. u r so genius,tnx dani

  ReplyDelete
 25. Dani your awesomeness is way appreciable! you work hard, you read hard, you write hard, you search hard to feed us menfesawi and hagerawi advice.How lucky are we ? sit and type Daniel kibret view then eat all sweet from his blog. Thank you Danyee !! word not enough to express my happiness to have you in our life. Peace.

  ReplyDelete
 26. interesting I like it bless you !

  ReplyDelete
 27. God bless you Dani, you changed my life. I am always reading your blog. In addition that you allowed for us to write whatever we think. You are an Ethiopian people HERO. I love you so much.

  ReplyDelete
 28. ተአምር እንዲፈጠር ፀልይ ፥ ኑሮህን ለማሻሻል ታገል፡፡
  የአኩዪኑ ቶማስ

  ReplyDelete
 29. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን ዲ. ዳንኤል ክብረት እንዲሁም የሲያትሉን ኃይለ ኢየሱስ

  ሰለ ንስር ከመፅሐፍ ቅዱስ፡-

  ኦሪት ዘዳግም

  28፥49-50
  እግዚአብሔር ቋንቋቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል።
  32፥11
  ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ በክንፎቹም አዘላቸው።

  መጽሐፈ ኢዮብ
  39፥27
  በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን?

  መዝሙረ ዳዊት
  103፥5
  ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
  139፥9
  እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥

  መጽሐፈ ምሳሌ
  23፥5
  በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።

  ትንቢተ ኢሳይያስ
  40፥31
  እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።

  ትንቢተ ኤርምያስ
  48፥40
  እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።
  49፥16
  በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፥ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
  49፥22
  እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።

  ሰቆቃው ኤርምያስ
  4፥19
  ቆፍ። አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስር ይልቅ ፈጣኖች ሆኑ በተራሮች ላይ አሳደዱን፥ በምድረ በዳ ሸመቁብን።

  ትንቢተ ሕዝቅኤል
  17፥3
  ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ ረጅምም ማርገብገቢያ ያለው ላባም የተሞላ፥ መልከ ዝንጕርጕር ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
  17፥7
  ታላቅ ክንፍና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ እነሆም፥ ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ።

  ትንቢተ ዳንኤል
  4፥33
  በዚያም ሰዓት ነገሩ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ ጠጕሩም እንደ ንስር፥ ጥፍሩም እንደ ወፎች እስኪረዝም ድረስ ከሰዎች ተለይቶ ተሰደደ፥ እንደ በሬም ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ።

  ትንቢተ ሆሴዕ
  8፥1
  መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ንስር ይመጣል።

  ትንቢተ ሚክያስ
  1፥16
  ተማርከው ከአንቺ ዘንድ ወጥተዋልና ስለ ተድላሽ ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ጠጕርሽንም ተቈረጪ ቡሃነትሽንም እንደ ንስር አስፊ።

  ትንቢተ አብድዩ
  1፥4
  እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦

  ትንቢተ ዕንባቆም
  1፥8
  ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።

  የዮሐንስ ራእይ
  4፥7
  ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
  8፥13
  አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ። ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።
  12፥14
  ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።

  ReplyDelete
 30. I learned alot; ;thanks

  ReplyDelete
 31. egziabher yistih D/N Dani.tiru food new.

  ReplyDelete
 32. EGZIABHER yistih,eske mecheresha bebego sira yatsnah,

  ReplyDelete
 33. ምንጊዜም ለለውጥ ራስህን አዘጋጅ፡፡ ነገሮች ድንገት እንዲደርሱብህ ዕድል አትስጣቸው፡፡ አስበህ፣ ተዘጋጅተህ፣ ወስነህ፣ ሂሳብ ሠርተህ እንጂ፡፡ ኑሮህ በድንገቴና በአጋጣሚ የተሞላ አይሁን፡፡ የቻልከውን መጠን ያህል ተዘጋጅ እንጂ፡፡ መጽሐፉስ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› አይደል የሚለው፡፡ ለማደግ ተዘጋጅ፣ ለመማር ተዘጋጅ፣ ለጓደኝነት ተዘጋጅ፣ ለማግባት ተዘጋጅ፣ ለመውለድ ተዘጋጅ፣ አዲስ ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅ፣ ቤት ለመሥራት ተዘጋጅ፣ መኪና ለመግዛት ተዘጋጅ፣ ለምትለውጣቸው ነገሮች ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ይኑርህ፡፡

  ReplyDelete
 34. ምንጊዜም ለለውጥ ራስህን አዘጋጅ፡፡ ነገሮች ድንገት እንዲደርሱብህ ዕድል አትስጣቸው፡፡ አስበህ፣ ተዘጋጅተህ፣ ወስነህ፣ ሂሳብ ሠርተህ እንጂ፡፡ ኑሮህ በድንገቴና በአጋጣሚ የተሞላ አይሁን፡፡ የቻልከውን መጠን ያህል ተዘጋጅ እንጂ፡፡ መጽሐፉስ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› አይደል የሚለው፡፡ ለማደግ ተዘጋጅ፣ ለመማር ተዘጋጅ፣ ለጓደኝነት ተዘጋጅ፣ ለማግባት ተዘጋጅ፣ ለመውለድ ተዘጋጅ፣ አዲስ ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅ፣ ቤት ለመሥራት ተዘጋጅ፣ መኪና ለመግዛት ተዘጋጅ፣ ለምትለውጣቸው ነገሮች ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ይኑርህ፡፡

  ReplyDelete
 35. THANK YOU Dn.Daniel .I read it on right time really thank you very much . God bless you more

  ReplyDelete