Monday, August 25, 2014

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ


ዋጋ 60 ብር

17 comments:

 1. Bravo Dani, lela yenurachin referece ametahilin aydel, eskemanebew chekuyalehu, egziabher amlak ejochihin yaberta.

  ReplyDelete
 2. Thanks a lot to give us your Book God Bless You

  ReplyDelete
 3. You are shaping a generation. God Bless your hands.

  ReplyDelete
 4. ታላቅ የበዓል ስጦታ እግዚአብሔር ይመስገን

  ReplyDelete
 5. If our country lacks those people like you, what will be our fate? Thank U Dani.

  ReplyDelete
 6. I live out side of Ethiopia. So how can I get your new book please?

  ReplyDelete
 7. God bless you,it has been a pleasure to read what you always have put on the blog.

  ReplyDelete
 8. በአማን ነጸረAugust 27, 2014 at 12:06 PM

  “ውልብድና” እና “ኢውልድብና”…..!!
  የዳንኤል ክብረትን ባለ200 መቶ ገጽ የ30 ወጎች፣ታሪኮች፣እይታዎች፣ምክሮች… የያዘ “ስማችሁ የለም እና ሌሎች” መጽሐፍ….. አነበብኩት፡፡
  ሀ. የመጽሐፉ ውልብድና (ውልብድና የሚለውን ቃልትርጉም የፈለገ መጽሐፉን ገዝቶ ገጽ-117 ላይ ይመልከት፡፡)
  1-መታሰቢያነቱን የስራቸውን ያህል በቁምም በህልፈትም ላልተዘከሩት መምህር(አባ) ወልደ ሰማዕት በማድረጉ ደስ አለኝ፡፡እኚህ አባት የቅድስት ሀገር ኢሩሳሌሟን ደብረ ገነት ኪ/ምሕረት ቤ/ክ አፄ የሐንስ ከግብጽ (ቱርክ) ወራሪ ማርከው በሰጧቸው ገጸ-በረከት አሳንጸው በዘመነ-አፄ ምኒልክ ሲጨርሱ የቤ/ክርስቲያኑ በር ላይ በአፄ ዮሐንስ ገጸ-በረከት እንደተሰራ የሚገልጽ የድንጋይ ጽሑፍ በማጻፋቸው በአጼ ምኒልክ ዘመን እንዴት አፄ ዮሐንስ አሳነጹት ትላለህ ተብለው ድርጊቱ የአፄ ምኒልክን መንግሥት እንደማሳነስ ተቆጥሮባቸው በግዞት ያለፉ አባት ናቸው፡፡(አደራ ወንድሞች ጉዳዩን የሸዋና የትግራይ ታሪካዊ የዘር ጥል ማሳያ አድርጋችሁ እንዳትሳሳቱ፡፡ምክንያቱም በዘር ከሆነ የአባ ወልደ ሰማዕት አገር የሆነው ቡልጋ ከአፄ ዮሐንሱ ተንቤን ይልቅ ለምኒልኩ አንኮበር ይቀርባል፡፡ ሙሉ ታሪኩን የፈለገ የዮሐንስ ገብረ ማርያምን ክርስትና በኢትዮጵያ ያንበብ!!)
  2-ዳኒ በቤተክሕነቱ ያሉ ችግሮችን ብቻ ሳይሆን መፍትሄዎችንም ለመጠቆም ጥሯል፡፡ለምሳሌ፡ “ምን አይነት ቅ/ሲኖዶስ ያስፈልገናል?” ሲል ከገጽ-43 ጀምሮ የሚያቀርበው ሀተታና ገንቢ አስተያየት የሚያስመሰግን ነው፡፡ “ኦርቶዶክሳዊ መምህር፣ዕውቀቱና ክሂለቱ” የሚለው ከገጽ-68 ጀምሮ ተከሽኖ የቀረበው ጽሁፍም ድንቅ ነው-አስተዋይና አንባቢ ሰባኪ ካነበበው!!
  3-መጽሐፉ በያገባኛል፣በኃላፊነት እና በተቆርቋሪነት ስሜት መጻፉ ደስ ያሰኛል፡፡
  4-የዳኒን በዘይቤ ቀምሞ፣ለአንባብያን በሚገቡ ቃለት እና ገለጻዎች ከሽኖ የማቅረብ ችሎታ “ዝኒ ከማሁ” ብሎ ከማለፍ ውጭ ቃላት ማባከን የተገባ አይሆንም፡፡ተሰጥቶታላ!! እኔማ “ተውሕቦ ብዕር ለዳንኤል…” ማለቴን አልተው!!
  5-ቤ/ክ ከቤ/መንግሥት ያላትን ታሪካዊ ግንኙነትና በቤተክሕነቱ ያለው ብሔር-ተኮር መሳሳብ ድንገት አሁን የተከሰተ ሳይሆን ነዋሪ-ነባሪ ችግር መሆኑን የገለጸበት መንገድ “ይበል” ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. በአማን ነጸረAugust 27, 2014 at 12:10 PM

  ለ. የመጽሐፉ ኢውልብድና!!(ኢውልብድና የሚለውን ቃል ትርጉም የፈለገ መጽሐፉን ገዝቶ ገጽ-117 ላይ ይመልከት፡፡)
  1- ‘የቤ/ክ ችግር ቤተክሕነት ነው’ በሚል መነሻ መጻፉ ለህሊና ይከብዳል፡፡ተቋሙ ላይ በዚህ መጠን ጨክኖ ከመተኮስ ይልቅ አደገኛ ናቸው የተባሉ የተቋሙን ግድፈቶች መዘርዘር የተሻለ ይመስለኛል፡፡ልክ “ሰውየውን ሳይሆን ሀሳቡን መተቸት” እንደምንለው ሁሉ ለተቋም ሲሆን ደግሞ “ተቋሙን ሳይሆን አሰራሩን” እያሉ ተቋምን ከአሰራር ለይቶ መውቀስ የተገባ ሆኖ ይታየኛል፡፡ያለበለዚያ ማን ያቀለለውን…ያስተርታል!!
  2-ከጽሁፉ አንጻር ቤተክሕነት የሚለው ቃል የትኞቹን የቤ/ክ አስተዳደር አካላት እንደሚያካትት መግቢያው ላይ መነሻ ሳይሰጥ ቀጥታ ወደ ወቀሳ መግባቱ ደስ አላሰኘኝም፡፡ቤተክሕነት የሚለው ቃል መንበረ-ፓትርያርኩ ያለበት የጠቅላይ ቤተክሕነት ጽ/ቤት ብቻ የሚመስለው ቀላል የማይባል ትውልድ ስላለ ቤተክሕነት ስንል እነማንን እንደሚያካትት መዘርዘሩ አይከፋም ነበር፡፡
  3-በዘመነ-አቡነ ባስልዮስ የተገኘው የፕትርክና መንበር በየጊዜው ያስገኛቸውን ትሩፋቶች እንዳላዩ አልፎ አሁንም ወደ ግብፅ ናፍቆት ማዘንበሉ ቅር አሰኝቶኛል፡፡ለምሳሌ፡ የ1966ቱ አብዮት የቤ/ክ ይዞታዎችን ቢነጥቅም ቤ/ክ አስተዋይ ኢ/ዊ አባቶች በቀረጹት ቃለ-ዐዋዲ (ቃለ-ዐዋዲውንና መመሪያዎችን ዳኒ ለማጣቀሻነት ባይጠቀማቸውም) ተመርታ በካሕናትና ምዕመናን ሕብረት በኢኮኖሚ ረገድ ከመንግሥት ጥገኝነት መላቀቋ፣የአገራችን ፖለቲካ ያን ያህል ሲዋዥቅ ቤ/ክ ግን እስካሁን ድረስ ለ40 አመታት ያላቋረጥ የሰ/ጉባኤ ምርጫ በማካሄድ ከመንግሥት ተሽላ መገኘቷ፣አንዳንዴ የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተግባራዊ አለመሆን ቢያሳዝነንም ቅ/ሲኖዶሳችን ባገራችን ካሉ የሃይማኖት ተቋማት ቀርቶ ከኢፌዲሪ ፓርላማ የተሻለ የሀሳብ ልውውጥ ያለበት ሕያውና ማዕከላዊነቱን የጠበቀ ተቋም መሆኑ፣ማበብ የጀመሩ ውጥን ልማቶች፣ወዘተ…ሊበረታቱ ይገባ ነበር፡፡ዳኒ ግን ዘለላቸው!!ህጸጽ ብቻ መንቀስ ያንጽ ይመስል!!
  4-ዳኒ ብዙ ጊዜ ለምዕመኑ ሲቆረቆር አይዋለሁ-ደስ ይለኛል፡፡በዚህ መጽሐፉም ይሄው ተንጸባርቋል፡፡በሌላ በኩል ለምዕመን መቆርቆሩን አባቶችን በማጣጣልና ስለ እነሱ ክፉ-ክፉውን ብቻ በመናገር ለማሳየት የተጋ ሆኖ ይሰማኛል-እናም-ይከፋኛል፡፡ስንት ደጋግ ሰባክያነ-ወንጌል አባቶች እያሉን ሁሉን ጀምሎ “አልቦ ጳጳስ” በሚል ድምጸት ማጣጣል የዕጓለማውታነት ስሜት ይፈጥራል፡፡ብዙ ጊዜ በማኅበረቅዱሳንና በሰ/ት/ቤቶች ዙሪያ ስላሉ ድክመቶች ከመናገር ይልቅ የእነሱንም ድክመት ምንጊዜም የቤ/ክሕነት ችግር አድርጎ ሳየው- ‘ወንድሜ የመደብ ታጋይ ሆነብኝ እንዴ’ እላለሁ፡፡አልዋሽም!!አንድም የሚበዙት የዳኒ አንባቢዎች የሰ/ት/ቤት እና የማኅበረቅዱሳን አባላት ስለሆኑ፣እንዲያም ሲል የእሱም መንፈሳዊ ሕይወት (የመደብ ጀርባ) ከእነሱ ስለሚመዘዝ እሱ ላይ እስካልተነሱበት ድረስ ስለ እነሱ ድክመት አያነሳም ወደ ማለቱ ይቃጣኛል፡፡በእሱ ላይ ከመጡማ…ስውሩ አመራር…የሚል ቃለ-ተግሳጽ እንደሚያወጣ አይቻለሁ፡፡
  5-በገጽ 60 ላይ ዳኒ ለአቡነ ጳውሎስ ከ10 አመት በፊት ስለ ቤ/ክ የወቅቱ ፈተናዎች ቃለመጠይቅ ሲያደርግላቸው አቀርቅረው ካለቀሱ በኋላ የዛን እለት ብቻ የተናገሩት ነገር ግን ቀድሞም ሆነ ኋላ ያልተናገሩት ነገር እንባቸው በጉንጫቸው እየፈሰሰ እንደተናገሩ፣ከዛ ቀን ጀምሮ ስለ እሳቸው ያለው ስሜት እንደተዘበራረቀ፣ያን ሁኔታ ሲያስበው “እኒህ አባት ሁላችንም ያላወቅንላቸው የተደበቀ ሰብዕና ይኖራቸው ይሆን?” እንደሚል ይገልጻል፡፡ይሄ አገላለጽ 2 ጊዜ ልቤን አደማው፡፡አንድም እሱን እንዲህ ያስገረመው ንግግራቸው ምን እንደሆነ ሳይገልጽ ለራሱ ተዘባርቆበት እኔን ማዘባረቁ፣ሲቀጥልም “የተደበቀ መልካም ሰብዕና ይኖራቸው ይሆን?” በማለት ልክ አቡነ ጳውሎስ በ20 አመታት ውስጥ ምንም ያለልሰሩ እና መልካም ሰብእናቸው ከተደበቀበት በቁፋሮ ብቻ የሚወጣ እኩይ ሰው አድርጎ በመሳሉ ቅር ብሎኛል!!ይሄ ትልቅ ኢውልድብና ነው!!
  ቢሆንም ስደመድም….ዝ መጽሐፍ ከመ ወይን (ቃለ-) ጣእሙ፣እስኩ ድግሙ-ድግሙ….የሚለውን ማኅሌተ-ገንቦ ለዳኒ በማቅረብ ነው!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ ሆይ
   እኔም እንደ ዳንኤል የቤተ ክርስቲያንዋ የዘመኑ ፈተና ቤተ ክህነቱ ነው ባይ ነኝ፡፤ ቤተ ክህነት ያልነበረበትን ዘመን ከነበረበት ዘመን ስናስተያው ይህንን እንረዳለን፡፤ ለመሆኑ የቤተ ክህነቱ መኖር ምን አመጣልን፡፡ ጉቦ፣ ዘረኛነት፣ የሊቃውንት እንግልት፣ ቢሮክራሲና የተበላሸ አሠራር ብቻ፡፡ እስኪ ከቤተ ክህነት የተገኘ አንድ መልካም ነገር ይንገሩን፡፡ ደግሞም ቤተ ክህነት የሚለው ስም ሰዎቹን ይገልጣል ‹በስመ ማህደር› ነውና፡፡

   Delete
  2. በአማን ነጸረAugust 28, 2014 at 6:50 PM

   1-አነሰም በዛ ዛሬ የምንወቀወሰው ራሱን የቻለ ሲኖዶስ አለን፣በራሳችን ቤ/ክ የተቀረጸ መተዳደሪያ ቃለዓዋዲ አለን፣ባለፉት 40 አመታት ውስጥ ሰ/ት/ቤቶች ተመስርተዋል-ተስፋፍተዋል፣በሺህ የሚቆጠሩ ሰባክያነ-ወንጌል ከቅ/ሥላሴ እና ጳውሎስ ኮሌጆች እንዲሁም እንደ ዘዋይ ከመሳሰሉ ከ8 በላይ የካሕናት ማሰልጠኛዎች ወጥተው የማታ የስብከት መርሐግብር ተጠናክሯል፣አዲስ አበባ ላይ ከሆንክ በየቤተክርስቲያኑ እየሄድክ በማበብ ላይ ያሉትን ህንጻዎች ተመልከት፣አራት ኪሎ ላይ የተጠናከረ የመ/ፓ/ክ ጽህፈት ቤት ከሙዚየምና ቤተመጻህፍት ጋር ታንጾ በዘመናዊ መልኩ ተደራጅቷል፣የኢኦተቤክ ተራድኦ ኮሚሽን ስለሚሰራቸው በጎ ተግባራት ብዙ ማለት ይቻላል፣ቀኖናን በተመለከተም፡ የገና ጾም አገባብን፣ዓሳ ይበላ-አይበላ ማለትን፣የመዝሙር መሳሪያ አጠቃቀምን፣የ81ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖናን…የደነገገው ይሄው ጠዋት ማታ ወቀሳ ብቻ የተረፈው ቤተክህነት ነው፡፡ለጋው ቤተክህነት-ከግብጽ ሞግዚትነት ከወጣ ገና 55 አመት ብቻ የሆነው!!
   2-ጉቦ እና ዘረኝነት ቤተክሕነት ከተመሰረተ በኋላ የመጡ አይደሉም፡፡ለዝርዝሩ ከፈለክ ይሄንኑ የዳኒ መጽሐፍ አንብበው፡፡የመጠን ጉዳይ ካልሆነ በቀር ድሮም ነበረ፡፡አሁን ላይ መባባሱን ግን እኔም አልክድም፡፡ቅር የሚለኝ ብቸኛ መገለጫ ሆኖ ሲቀርብ ነው፡፡መልካም ጎኑ ተደብቆ-የቤተክሕነቱ!!
   3-በነገራችን ላይ ቤተክሕነት ስንል ስለ አስተዳደር መዋቅሩ ማለታችን ነው፡፡የአስተዳደር መዋቅሩ ደግሞ 6 ዋና ዋና የስልጣን እርከኖች አሉት፡፡(1)ቅ/ሲኖዶስ፣(2)ቋሚ ሲኖዶስ፣(3)ጠቅላይ ቤተክሕነት፣(4)ሀገረስብከት ጽ/ቤት፣(5)ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት እና (6) የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡እነዚህም በየራሳቸው ዝርዝር አደረጃጀትና ተግባራት ያላቸው ሲሆን ሁሉም በቃለዓዋዲው ተቆጥሮ-ተሰፍሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡
   4-ለምሳሌ በብዙዎቻችን አእምሮ ቤተክህነት ሲባል ወደ አእምሯችን የሚመጣውን ጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያዎች ልዘርዝራቸው፡(1)የሊቃውንት ጉባኤ፣(2)ስብከተ-ወንጌል፣(3)ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ፣(4)ትምህርትና ማሰልጠኛ፣(5)አስተዳደር፣(6)ካሕናት አገልግሎት፣(7)ገንዘብና ንብረት፣(8)ቁጥጥር አገልግሎት፣(9)ቅርስ ጥበቃና ምዝገባ፣(10)ሰ/ት/ቤት ማደራጃ፣(11)እቅድና ጥናት፣(12)ሕግ አገልግሎት፣(13)መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣(14)ሕግ አማካሪ፣(15)ሥርዓተ-ተክሊል፣(16)ውጭ ግንኙነት፣(17)ገዳማት አስተዳደር፣(18)ትንሣኤ ዘጉባኤ፡፡እነዚህ 18 አካላት መምሪያ በሚል ስያሜ በቃለዓዋዲ የተሰጣቸውን ተግባራትን የሚያከናውኑ ናቸው፡፡በተጨማሪነትም፡ ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን፣ህጻናትና ቤተሰብ ኮሚሽን፣ቤቶችና ህንጻዎች አስተዳደር እንዲሁም ማኅበረቅዱሳን በተቅላይ ቤተክህነት ስር የሚተዳደሩ ተቋማት ናቸው፡፡ወደ አጥቢያ ስንመጣም፡ ጥበቃው፣ሰባኪው፣መምገህራን፣ዲያቆናት፣ቀሳውስት፣የቢሮ ሰራተኞች፣አስተዳዳሪው፣ወዘተ….ይገኛሉ፡፡
   5-ስለዚህ ቤተክህነት ስንል የእነዚህ ሁሉ ድምር ማለታችን ስለሆነ በጅምላ ከመውቀስ ይልቅ ለይቶ በተለይ ደግሞ ሊታረሙ ይገባቸዋል የሚባሉትን ተግባራት ከሚመለከተው የቤተክሕነት ክፍል አቆራኝቶ መናገር ትቺቱን የተሳካ ያደርገው ነበር፡፡አሁን እየተደረገ ያለው ግን በጅምላ ፈርጆ ሁሉም ላይ በእሩምታ መተኮስ ነው፡፡ይሄ በእኔ እምነት ገንቢ አይደለም፡፡
   6-ሁሌ ወቀሳ ብቻ የሚነገር ከሆነ አባቶችም ልማዳቸው ነው እያሉ ጆሮ አይሰጡንም፣ምዕመኑንም ወደ አላስፈላጊ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንከተዋለን፣አብዛኛው ምዕመንና ቤ/ክ በገጠር ውስጥ በሚገኝባት ቤ/ክ ቅን አገልጋዮችን ጨምሮ የ4ኪሎውን ህጸጽ ማሸከምም ነውር ነው፣ተቋሙ ያለውን አገራዊና ዓለምአቀፍ ተቀባይነትም ይጎዳል….
   7-ስለዚህ ስንተች፡ በተቻለ መጠን ለተሰሩ ስራዎች እውቅና በመስጠት፣ጣታችን መቀሰር ብቻ ሳይሆን እኛም ለጥፋቱ በአንድም በሌላም መነግድ አስተዋጽኦ እንዳደረግን አምነን፣ለመወንጀል ብቻ ሳይሆን ለማነጽ አልመን፣ተቋሙ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተቋማት አንጻር ገና ለጋ (55 አመት)መሆኑን አስበን፣እንደ እንጀራ ልጅ በየአደባባዩ ወሬ አንጠልጥሎ ለመናፍቃን መዘባበቻ ከማድረግ ይልቅ እንደ ልጅ ችግራችንን በውስጥ ውይይት ለመፍታት በመሞከር፣እኛ ብቻ ነን አዋቂና ንጹህ ኦርቶዶክስ ከሚል ስሜት ወጥተን፣ወዘተ….ቢሆን ደስ ይለኛል፡፡
   8-በተለይ በተለይ ይሄ በጅምላ ቤተክሕነት እያሉ ጸያፍ ነገር መናገር ቢቀር ደስ ይለኛል፡፡ቃሉ ራሱ እኮ ያሳዝናል፡፡የክህነት መገኛ ማለት ነው፡፡ስለዚህ ቤተክሕነት ተብሎ ሲሰደብም ሆነ ሲፈረጅ ከላይ የተዘረዘሩትና ቤ/ክንን ቤ/ክ የሚያሰኙ አካላትም አብረው ስለሚራከሱ ጥንቃቄ ብናደርግ ደስታየ ነው፡፡ኃላፊነት ለመውሰድም እንዲመች ቢቻል ኃላፊውን ካልሆነም መምሪያውን ብቻ ለይተን እንውቀስ!!
   …አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት?...የሚለውን አቡነ ማርቆስ ቃል ወደ እኛም እንዳይዞር ጥንቃቄ አድርገን እንራመድ!!እንዴ!!ሁሉን ከወቀስን እኛስ ይቺን ቤ/ክ ከማን ተቀበልናት ልንል ነው??

   Delete
  3. beaman netserem danim tiru neger eyastemarachihun new neger gen ande tsenfe yizo sayhon negerochen memelket weta bilo negerochin beatkurot memelket tiru new! kalehewot yasemachuu!

   Delete
 10. I always read ur book and I learnt a lot from ur view

  ReplyDelete
 11. ስምሽ የለም ከሚል መርዶ እግዚአብሄር ይጠብቀን በብዙ መልኩ ማለት ነው

  ReplyDelete
 12. Hi

  Dani, But how about your name, It is written, do you find your name there, who are you to say that
  who are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say thatwho are you to say that

  ReplyDelete
 13. ዳኒ

  ያንተስ ስም አለ እዚያ ወይም ያንተ አይነት ግብር የሚሰሩ ሰዎች ስም አለ

  ለማወቅ ያህል
  ዳኒ

  ያንተስ ስም አለ እዚያ ወይም

  ያንተ አይነት ግብር የሚሰሩ ሰዎች ስም አለ

  ለማወቅ ያህል

  ደመቀ ነኝ

  ReplyDelete