Friday, August 15, 2014

ሕግና ሥርዓት - በሐበሻ አሜሪካ

አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ስዘዋወር ከአስተባባሪዎቹ የምሰማው ተመሳሳይ ሮሮ አለ፡፡ ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት የራሳቸው ሕንጻ እስኪያገኙ ድረስ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተከራይተው ይገለገላሉ፡፡ የራሳቸው ሕንጸ ያላቸውም ቢሆኑ ከአሜሪካዊው ማኅበረሰብ ጋር ይጎራበታሉ፡፡ በሰንበት ቅዳሴና የንግሥ በዓላት በሚከበሩባቸው ቀናት በመኪና ማቆሚያ፣ በድምጽ፣ በአካባቢው በብዛት በመገኘትና በጽዳት ጉዳዮች አብያተ ክርስቲያናቱ ካሉባቸው መንደሮች ነዋሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡

እነዚህ ግንኙነቶች ግን ብዙውን ጊዜ ሰላማውያን አይሆኑም፡፡ አልፎ አልፎ ችግሩ ከሌሎች ወገን ቢመነጭም ዋናው ችግር ግን ከራሳችን የሚመጣ መሆኑን አስተባባሪዎችም ማኅበረሰቡም ያምኑበታል፡፡ ፈታኙ ነገር ችግሩን ለማስተካከል አለመቻሉ ነው፡፡ ‹ከተማ የጉርብትና ሥርዓት ነው› የሚለውን የከተሞችን አንዱን መርሕ በጉልሕ ለማየት ከሚቻልባው ሀገሮች አንዷ በሆነችው አሜሪካ የመንደርተኞች ሕጎችና ባሕሎች ጥብቅ ናቸው፡፡ በተለይም ግለሰባዊ ኑሮን መሠረት ባደረገው የአሜሪካ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ በአንድ መንደር የሚከናወኑ ተግባራት የግለሰቦችን መብቶች እንዳይነኩ ጥንቃቄ ይደረግባቸዋል፡፡

አንድ የመንደሩ ነዋሪ የራሱን መብት አስጠብቆ፣ በሌሎቹ መብት ላይ ሳይደርስ፣ ነገር ግን ደግሞ አካባቢያዊ ግዴታውን ተወጥቶ የሚኖርበት የመንደር ሕግ ነው ያላቸው፡፡ እያንዳንዱ ነዋሪ ቤቱንና በቤቱ ዙሪያ ያለውን አካባቢ ያጸዳል፡፡ በተመደበለትና በተፈቀደለት ቦታ ብቻ መኪናውን ያቆማል፡፡ በተመደበው ጊዜ ቆሻሻውን ለሰብሳቢዎቹ ያስረክባል፡፡ ከተፈቀደለት መጠንና ሰዓት በላይ ድምፅ አያወጣም ፤ አይጠቀምም፤ በአካባቢው የተለየ እንቅስቃሴ ሲኖር ለፖሊስ ያሳውቃል፤ መንደሩን የሚነካ ጉዳይ ሲኖረው አስቀድሞ ያሳውቃል፤ በአካባቢው  የመንደሩን ገጽታና አነዋዋር የሚቀይር ነገር ሲኖር መንደርተኛው ይጠየቃል፤ ይወስናልም፡፡ እነዚህን መሰሉ መንደር ተኮር ሕጎች ናቸው ነዋሪዎቹ ተከባብረውና ተጠባብቀው በሰላም እንዲኖሩ የሚያደርጓቸው፡፡  


በሌላ በኩል ግን በሀገራችን መንደርን መንደር ያደረገው በታሪክ አጋጣሚ በአንድ አካባቢ ተሠርቶ መገኘቱ፤ ያለበለዚያም  በሆነ ፕሮጀክት በአንድ አካባቢ እነዚህ ቤቶች በመገንባታቸው እንጂ መንደርተኛውን የሚያስተባበረው፣ ተከባብሮና መብቱን ተጠባብቆ እንዲኖር፣ ግዴታውንም እንዲወጣ የሚያደርገው የመንደር ባሕልና ሕግ የለውም፡፡ አብዛኞቹ የመንደር ሕጎች እንደ ዕድርና ዕቁብ፣ ማኅበራዊ ኑሮን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ የጉርብትና ሕጎች አይደሉም፡፡ ቀበሌ ሲመሠረት ዝቅተኛ የመንደር መዋቅርን ለመትከል ታስቦ እንደነበረ ይነገራል፡፡ በኋላ ግን ከመንደር አልፎ የአንድ ከተማ መዋቅር ያዘ፤ አሁን ደግሞ የወረዳ መዋቅር ሆኗል፡፡

እናንተ ሥራ ውላችሁ ስትመጡ ድንገት የመንደራችሁ መንገድ ተቆፍሮ ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡ ቀድሞ ለማሳወቅ ግዴታ ያለበት አካል የለም፡፡ ወይም ከበራችሁ አጠገብ የዕድር ድንኳን ሊተከል መሆኑን የሚነግራችሁ የለም፡፡ ልጆቻችን እናጫውትበታለን ያላችሁት ሜዳ በድንገት አንድ ቀን የሠፈሩን ማንነት የሚቀይር ሕንፃ እንዲሠራበት ሲቆፈር ታዩት ይሆናል፡፡ ጎረቤቶቻችሁ ሦስት መኪኖቻቸውን አቁመው እርስዎ ለአንድ መኪና ቦታ ቢያጡ የማመልከቻ ቢሮ የለዎት ይሆናል፡፡ የሠፈሩ ሜዳ በሙሉ የቴሌቭዥን ዲሽ መትከያ ሲሆን ሥርዓት የሚያስይዝ አካል አይኖርም፤ ድግስ በተደገሰ፣ ማኅበር በተጠጣ፣ ሰው በተሰበሰበ ቁጥር እስከ ላንቃው በተከፈተ ሙዚቃና ጭፈራ ሲረበሹ ወይ ቀድሞ የሚነግርዎት አለያም እስከ መቼ አንድሚቀጥል የሚያሳውቅዎት አይኖርም፡፡

ይህንን በመሰለው የመንደር አኗኗር የኖረው ማኅበረሰባችን ነው እዚህ አሜሪካ ሲመጣ ችግር የሚገጥመው፡፡ 

ምንም እንኳን በአብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ለመኪና ማቆሚያ የተፈቀደና የተከለከለውን ሥፍራ የሚገልጥ ማስታወቂያ ቢኖርም በተከለከለው ቦታ መኪኖቹ ይቆማሉ፡፡ ሲብስም የነዋሪዎቹ የግል የመኪና ማቆሚያ ላይ እንዲቆሙ ይደረጋሉ፡፡ የከፋው ዘመዳችንም የነዋሪዎቹን የመውጫ መግቢያ በር ዘግቶ መኪናውን ያቆማል፡፡ በብዙዎቹ መንደሮች በሣር ላይ መጓዝና መንዳት ክልክል ቢሆንም እኛ ስንሰበሰብ ግን ሣሮች መከራቸውን ያያሉ፤ አንዳንዴም ቀድመው እንዲያውቁ ሳይደረግ ድንገት የከበሮው ድምጽ አካባቢውን ያናውጠዋል፡፡ የመኪና ጥሩንባ ሠፈሩን ያተራምሰዋል፡፡ 

ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ምግብና መጠጥ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ይከለክላሉ፤ በጉልሕ ጽፈው በሚታይ ቦታ ያስቀምጣሉ፡፡ እኛ ግን ጥሰን ይዘን እንገባለን፡፡ የሚያስደንቀው ደግሞ እዚያው ጥለነው እንወጣለን፡፡ መጽሐፎቻቸው ይበላሻሉ፤ ዕቃዎቻቸው ይተራመሳሉ፤ መጸዳጃዎቻቸው ይዝረከረካሉ፤ ጽዳቱ ይጓደላል፤ ዕቃቸው ይሰበራል፡፡  

አሜሪካውያን ሌሎች ማኅበረሰቦችን በፍርሃት ማየታቸው፣ በሌላም በኩል በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮበት ፖሊስ በአካባቢው ሰዎች የቅሬታ ስልክ ይጨናነቃል፡፡ የፈቀዱ አካላትም ጫና ይበዛባቸዋል፡፡ ያስፈቀዱ አካላትም ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡ አንድ ላይ ተዳምሮም በአንዳንድ አካባቢዎች ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች አዳራሽ የሚያከራይ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ የሚሸጥ፣ መስኮችንና ሜዳዎችን የሚፈቅድ እየጠፋ መጥቷል፡፡ ቢፈቀድ እንኳን እጅግ ጥብቅ በሆነ ግዴታና እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ እየሆነ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታዎችም የፖሊስ ኃይል ለማቆም፣ የጽዳት ሰዎች ለመመደብ፤ እንቅስቃሴውን የሚከታተሉ የድርጅቱ ሰዎችን ለማሠማራትና የሚበላሹ ዕቃዎችን ለመከታተል እያሉ የሚቆልሉት ዋጋ አስመራሪ ሆኗል፡፡

በአንድ በኩል በጉርብትና ሕግ ውስጥ አለማደጋችንና የልምድ ችግራችን ለዚህ ዳርጎናል፡፡ ለሕግና ሥርዓት ያለን ቦታና የተገዥነት ልምድ ማነስ ጉዳት አስከትሎብናል፡፡ ከሕግ አውጭው እስከ ሕግ ተመሪው ድረስ ሕግንና ሥርዓትን መጣስ ልማድ በሆነበት ማኅረሰብ ውስጥ ማደጋችንም አጋልጦናል፡፡ የሠለጠነ ማኅበረሰብ ከሚገለጥባቸው ነገሮች አንዱ ‹በሕግና ሥርዓት መመራት› ነው፡፡ እኛ ዘንድ ግን በተለይ ‹ከተሜ በሚባለው አካባቢ› በሕግና ሥርዓት አስከባሪው እንጂ በሕጉና ሥርዓቱ የመመራቱ ባሕል እምብዛም ነው፡፡ ከሕጉ ይልቅ የሕግ አስከባሪው ይፈራል፤ ይከበራልም፡፡ በዚህም ምክንያት ሕጉ ሰውየው ሆኗል፡፡ ለዚህም ይመስላል የትራፊክ ፖሊስ ሲኖርና ሳይኖር የትራፊክ ሕጉ አከባበር የሚለየው፡፡ ሕጉ የባለሥልጣኑ መሪ ሳይሆን፣ ሕጉ የባለሥልጣኑ ተገዥ ነው፡፡ 

ዕቃ ስንገዛ ማንዋሉን፣ ልብስ ስንገዛ ስለ አስተጣጠብና አተኳኮሱ የሚገልጠውን አብሮት የተሰፋውን መግለጫ የማንበብና በዚያ የመመራት ልማድ ያለን ስንቶቻችን ነን?  

ሌላው ችግር ደግሞ ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ነው፡፡ ጽዳት፣ ሥርዓት፣ ፕሮቶኮል፣ ውበትና ሥምረት ለራስ ከሚሰጥ ዋጋ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ጃፓኖች ተቀምጠውበት የነበረውን ስታዲዮም አጽደተው ሲወጡ የተመለከተው ዓለም አድናቆቱን ችሯቸዋል፡፡ ለራሳቸው ያላቸውን ዋጋም አሳይተውናል፡፡ እነርሱ ለዓለም በጎን ነገር እንጂ አንዳች ክፉ ነገርን ለማበርከት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል፡፡ የሚመጥናቸው ምን እንደሆነ እንድናይም አድርገዋል፡፡

ሌላው ደግሞ መዋቅራዊ ያልሆነን ኃላፊነት የመወጣት ልማዳችን አነስተኛ መሆኑ ነው፡፡ መዋቅራዊ ኃላፊነት ማለት በአንድ የተወሰነ መዋቅር ወይም ድርጅት ወይም ደግሞ አሠራር ውስጥ በመመረጥ፣ በምደባ ወይም ደግሞ በሹመት የሚመጣ ኃላፊነት ነው፡፡ የዚህ ክፍል አባል፣ ኃላፊ፣ ጸሐፊ፣ ተጠሪ፣ ሰብሳቢ፣ እየተባለ የሚጠራው፡፡ ኃላፊነትን እንዲህ ላሉ አካላትና ግለሰቦች እንሰጥና ‹እኔን አይመለከተኝም› እንላለን፡፡ ሥልጡን ማኅበረሰብ ግን ኃላፊነት የሚሰማውን ዜጋ መፍጠር የቻለ ነው፡፡ ‹ለአካባቢው ሰላም፣ ጽዳት፣ ዕድገት፣ ጤናና ማኅበራዊ ደኅንነት እኔም ድርሻ አለኝ› የሚል ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ፡፡ እስኪታዘዝ፣ እስኪነገረው፣ እስኪጨቀጨቅ የማይጠብቅ ዜጋ፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያ፣ በኮሚቴ ምሥረታ፣ በማኅበር ማቋቋም ወቅት ሰዎች ኃላፊነትን ወስደው፣ ቃል ገብተውና ምለው ተገዝተው ይመረጡና በኋላ ዘወር የሚሉት፣ ካልተለመኑና ካልተጨቀጨቁ የማይሰበሰቡትና የማይሠሩት ውስጣቸው ‹ኃላፊነት› የሚባለው ነገር ስለሌለ ነው፡፡ በየውይይቱ ‹እገሌ ለምን እንዲህ አያደርግም› እንጂ ‹እኔ ለምን እንዲህ አላደርግም› የሚል ቁጭት የጠፋው ‹ኃላፊነት መውሰድ› የሚባለው ነገር ስለሌለ ነው፡፡  

ሠለጠኑ በሚባሉ ሀገሮች ከሚገኙ ወገኖቻችን ከሽቱና ቦርሳ፣ ከልብስና ቀሚስ በላይ ዕውቀትና ሥልጣኔን እንጠብቃለን፡፡ ሌሎቹ ቁሳቁሶች እነዚህ ሲገኙ እዚያው ይመረታሉና፡፡ አልፎ አልፎ እንደሚታየው ግን ሕግና ሥርዓትን በማወቅና በማክበር ረገድ በአንድ ቀን የፖሊስ ትምህርት ተለውጦ የግራ ጠርዙን ይዞ የሚጓዘው የሀገሬ ገበሬ እጅግ ተሽሎ ይታያል፡፡ ያ ሁሉ ገበሬ መሥመር ጠብቆ ሲሄድ አንድም የትራፊክ ፖሊስ በአካባቢው አይታይም፡፡ ታድያ ቦታ ተቀያይራችሁ ትሞክሩት እንዴǃ  

ሚነሶታ፣ሚንያፖሊስ

51 comments:

 1. Hi Dani thank you so much for your comment. I live in USA in Virginia. I used to go St George church that located at Columbia pike and Thomas Street. It used to lead by Aba Sereke Brhan. One day when I went that church, it was close because we passed the neighborhood rule and regulation then we moved into Cristal city drive and 23rd street after three years we got the same problem. In addition that we paid more than $ 500 for the car towed company because we park somebody’s properties. The bad thing is when you tried to teach them the called you “ WHITE” Our people think living with rule and regulation is been a white. I have been many churches in Virginia. Especially St Kidane Mheret and St Silasa, we paid more than $ 500 per week for the tow company but we donate less than $ 300 for the church. I am not saying I am not the victim of this knowledge but my question is what kind action will change us to think as a human being?
  I would like to thank you Kesis Zebene Lema and Like Eruyan Kisis Yesake Wolde Eruyan that they teach for the community very well even if they didn’t change many people. God bless USA.
  I HAVE ESPACIAL MESSAGE FOR ALL YOUR FOLLOWER, THIS IS FASTING TIME SO WE HAVE TO PRAY FOR OUR PRIVOUS FATHER, HIS NAME IS ABA SEREKE BRHAN, HE USED TO BELIVE GOD. AT THE MOVEMENT HE DOESN’T BELIVE SO WE HAVE TO PRAY FOR HIM TO BRING HIM BACK.

  ReplyDelete
  Replies
  1. please write in Amharic, go to school for english! amarach ateh bihon yihun enilalen, min malet feligo neu eyalku manbeb gin yidebiral!

   Delete
  2. Hello the Anonymous person August 17, at 10:16 pm. I read the above comment it is clear to understood but he/she add out of topic issue. Personal issue is not related with the topic but he or she mentioned personal issue. In addition that he/she add about Aba Sereke Brhan, it may fact but we can not prove it. I think the Anonymous person is part of Mahibere Kidusan otherwise it is not easy to blame a single person like this. I live with Aba Sereke Brhan at the movement so please don't hate him evenif he doesn't care about our churches. God bless Ethiopia.

   Delete
 2. ahununu wede geter mehede new yeketemaw hizbma ohhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhh

  ReplyDelete
 3. I also agreed. We need honest and loyal ruler even though not letrate than a courrupt and barbarian ruler

  ReplyDelete
 4. I think we can learn many think to change our country. thank you dani

  ReplyDelete
 5. It is so amazing I hope I will let you know that what kind diffrent I will bring soon in my area. I kive in Merkato so you will see or hear from the media what kind diffrence I will bring

  ReplyDelete
 6. I never been USA but I trust you. Our weakness spreed in the world. Are we able to blame our family,leader or church for this bad culture? How will change this bad culture? We always blame our goverment what we expect from goverment. The goverment has the best policy but nobody tried to do something. Who will care for the next generation.

  ReplyDelete
 7. What we learned from this message? America has only 365 years old histor but Ethiopia has more than 3,000 years. Why we are behind from America. Most people say black people have less mind than white the others say Ethiopia follow wrong relagion so God didn't bless her. Are Europian and American follow the true way of God than Ethiopian? Why we are the poorest country in the world? Why we don't have democratic elected goverment? Are we a human being or made up of other material? Please give me your comment I would like to know the above questions answer. Thank you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. The way towards ... very wide, but the way to...is very narrow.

   Delete
  2. I don't think black people has less mind than white and I don't think the religion that we follow.

   There were two monks they travell on the desert on their way they found a girl she stack inside the pit and she screaming and shouting to help her one of the monk said lets pick her up the other said no. why not replied the other due to our monastry rule and regulation 'Don't touch a girl' the other one jump in to the pit and pick her up and carry her until she is okay later on she prised him and she start walking say them good bye the monk start talking about the situation why you carry her why you carry her this is not our rule the monk replyed again i carry her one but you carry her so far. That means we are talking still our rockhuen church, axum so on....

   priory is the main thing to develop the country even yourself. We don't know about priority for any thing. As we know we are the poorest and dirtest country in the world according to forbs.

   when i say this i remembered Napolion he was reading a catholic chruch newespapaer and the title of the newsapaper said church is mother and church is school then he laughed and said church is school i agree, but try to cancel chruch is mother coz i have never seen a mother who built a building when her kids are starving. We got lots of Cathedral school like Lideta uruael bole medhanialem do you think it build for the poorest people is the poor can afford the fee of the school i don't think so.

   I think this help

   Delete
  3. learn english first

   Delete
  4. Could u correcct me please

   Delete
  5. can you explain me what was my mistake and could you correct me?

   Delete
  6. you are confused person,don't confuse us

   Delete
  7. It's not a matter of religion. Japan and Europe exercise different religion. but they r punctual. so change ur mind and stop blaming religion.

   Delete
 8. We have the best runner in the world but we have the last mind in the world.

  ReplyDelete
 9. I think we have to create new religion for Ethiopian people to change our country.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What is the use of having a developed country like that of Europe for a religious person. "Our home is in heaven...".

   Delete
  2. You need to change your heart not your religion.

   Delete
 10. One year ago Marry came to us but we didn’t accept her. At the movement she is in the jail for three years. Nobody fight back the current government for her release but we are looking for change our country. If anybody likes to see change in Ethiopia, we have to fight for St Marry relies.

  ReplyDelete
  Replies
  1. so many crazy people live out there, you are one of them

   Delete
 11. One year ago Marry came to us but we didn’t accept her. At the movement she is in the jail for three years. Nobody fight back the current government for her release but we are looking for change our country. If anybody likes to see change in Ethiopia, we have to fight for St Marry relies.

  ReplyDelete
 12. Everybody want to teach us but nobody tried to clean or organize the community except Gash Abera Mola, he quite Gudau Saymola.

  ReplyDelete
 13. በጣም ጥሩ አስተያየት ነዉ

  ReplyDelete
 14. 100% I agree with you. Dani it's excellent observation. You told us the reality of our dally practices which we couldn't learn from others. God bless you.

  ReplyDelete
 15. Hi Dani,

  I like your 360 view God bless you but I want to request a question about the Church that we rented from the white people. If the Church is ours do we rent them? No, for sure coz one time after the service the community presented some gift for the manager of the church due to her assistance. But she said this is not my house this is the house of Christ . Then I asked myself this question If this church is ours do we rent for any other religion? And i asked all of my friends all of them the gave me same answer never never never ......

  ReplyDelete
 16. በመጀመሪያ ዲ/ን ዳንኤል ለሰጠኸው ምልከታ ከልብ እናመሰግናለን። ልብ ያለው ልብ ይበል! ይሏል እንዲህ ነው። በመቀጠል ግን በዲያቆን ዳንኤል የጡመራ መድረክ ላይ ከማገኘው ትምህርት ዉጭ እኔን ከሚያስቁኝና ከሚያዝናኑኝ ነገሮች መካከል የተከታዮቹን ምልከታ ማንበብ ነው። እርግጠኛ ነኝ ራሱ ዲ/ን ዳንኤልም እሄ ሳይሆን አይቀርም ሃሳብ የሚጽንስለት። ቅቅ ። ነገሮችን ከተለያዬ አንግል ለማየት ስፈልግ ተከታዮቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን? ይላሉ በሚል ሂሳብ አስተያየቶችን ማንበብ አንዳንዴ ከልብ ያስቁኛል። ሌላ ጊዜ ከልብ ያነፍሩኛል። ቅቅቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ግሉል ያደርጉኛል። መቼም ጊዜ ቢሆን ተቀራራቢ ምልከታዎችን መጠበቅም ሞኝነት ነው። ዳሩ ግን ልዩነት ዉበት ነው፤ እንዲሉ ልዩነታችንን የበለጠ ለማስፋት ከመጣር ሽንቁሩን ጨርሶ ለመዝጋት መሞከሩም መልካም ሳይሆን አይቀርም። በተለይ ደግሞ ሃገርን ያክል፣ እምነትን፣ ቤተክርስቲያንን ያክል ትልቅ ነገር በዓለም ከሚያስነቅፍ አጓጉል ልማዶችና ባህሪዎች ለመታረም ጥልቅ የባህሪ ለዉጥ ያሻናል። ኤዲያ! ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ! ሆነና ይዘነው የመጣነውን ልማድ መርሳት አልቻልንም።

  ReplyDelete
 17. you guys said bad culture, what is the solution? Those who rent small churches has the same problem like Ethiopians. It is not the problem of Ethiopian only but minorities. criticizing is not civilization. there are a lot of kids who are really lost joining other culture like ethists and others like gbresodom, what ever it cost us we have to teach them the right path. I think this issue is somewhere in the east coast. For example in middle or west coast, Ethiopians have very huge churches with parking lots, but still Ethiopians love their church and holidays so there maybe some parking problems. parking problem exists where you go to church or not that is our own responsibility as we did it when we go shopings.
  Anyways, rather you guys are bad because you don't know really your culture. Besides, for those who can realize, going to church is not considered as a culture but a must to be done for your eternity. Every 50 years politicians will give a new culture, but not ..... eternity

  ReplyDelete
 18. ያልጠቀስካችው ዉርደቶቻችን አሉ እንጂ ፡ ያልከው ሁሉ እውነት ነው።

  መንገድ ላይ ሲፀዳዳ ያደገው አበሻ በኤሮፕም ይህንኑ ተግባሩን በየጥጋ ጥጉ ማስተናገዱን ማቆም ተስኖታል እኮ። ቆሻሻ በየመንገዱ መጣልማ አራድነት ነው፡፡ ቢራ ጠጥቶ ለቡጢ መንጠራራትም አለ። አልኮሉ ቶሎ ነዋ ጭንቅላት አልባውን የስው ምስል የሚቆጣጠረው።
  አበሻ ከሁሉም የተሻለ ምርጥ ዘር ስለሆነ የሌላውን መብት ማክበር አይጠበቅብትምኮ! "ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ"

  በዓለም በግለሰብም ሆነ በመንግስት ደረጃ የታወቅንበት ሙያ ልመና ሆንዋል። ሙሉ ጤነኛ ሆኖ በመንግስት ድጎማ ነዋሪው አበሻ ፡ በፈረንጆቹ አገር ቁጥር ስፍር የለውም። ስርቶ ከመኖር ይልቅ የመንግስት ተረጂ ሆኖ መኖር ምን ያህል የትሻለ እንደሆነ ሊያስረዱ የሚቃጣቸውም አሉ። ፈረንጆቹ በዚህ ላይ ቀልድ ሁሉ አላቸው። አልጽፈውም! ይቅርባችሁ።

  የዛሬውን አያርገውን አበሻ በፈረንጆቹ አገር የሚያኮራ ስም ነበረው፡፡ ነበር ምን ዋጋ አለው!

  ReplyDelete
  Replies
  1. dani, please these lemagn woyane brought begging to the central Ethiopia and then start insulting us. "bagoresku tenekesku", my grand ma told me long time ago, when she when there for hidar tsion, the first time she saw beggar was in axum All food stamp receivers were both eritirians and tigrians even now, there are a lot of tigrians and Eritrean working as process facilitator to get food stamp. actually they are writing their own experience on the behalf of the innocent hard working people. So can u filter these arrogance human diseases.

   Delete
  2. Afer billa Aram awardehewu motehal, woyanie

   Delete
  3. ዘረኝነት የድንቁርና ምልክት ነው!
   አንተን ብሎ ዳኒን መካሪ፡፡

   Delete
  4. ውርደት ማለት ምን ይሆን?
   ችግርን መግለፅ ውርደት አይደለም፡፡ እራስን ማታለል ፥ ያልሆኑትን ሆኖ ለመታየት መሞከር ፡ እንደጋቢየተደራረበ ውርደትን ያለብሳል።
   እስከመቼ ይዘለቃል ፡ ይህ ካንገት ከረባት ቂጥ ባዶ የሆነ ኖሯችን?

   Delete
  5. Anonymous @August 17, 2014 at 1:12 AM
   You nailed it!!! Egziabher Yibarkih!! I always feel bad for those who proudly tell you how they beat z system & leave in welfare or section 8...

   Delete
 19. egzioooooo!!!! mastawelun yesten!!! Dn.Daniel bertalen betaam gerum yehunu mlektochen newe ymtsefew yehi mleket eninem ye 60 ametwan azawent yakatetenjal yastemrenjalem.TEBREK!!!!

  ReplyDelete
 20. Great observation...a number of more can be made about EOC churches outside of Eth. I often go to St. Mary's on Buchanan in D.C. Its annoying how parents don't supervise their kids. Most of the time children are running around and making noises during Kidase ..Its annoying and disturbs others. If you go after hours there is always group of people (usually they are members of sunday school groups or sth ) sitting inside the church talking about other people and laughing out loud. And then there is the overall teaching from the priests. They still have the old ways of scaring tactics. We need to go back to the books ...research and read and relate with people's everyday life. That's how you maintain your membership. Anyhow as in everything we still have along way to go. Yemiyasazinaw ..we are not either part of the modern culture and then we are also messing up age old traditions ....

  ReplyDelete
 21. Thank you Dani. Some of us, we did it with the lack or knowledge so this message help us to improve our selves. I will teach my family and I will tell for my friend to read your blog. Have bless day.

  ReplyDelete
 22. The person that commented above about woyane. I did not see a word or sentence to match the comment you made. Can you stop and listen to yourself, there is a thing called love and peace in life than hater and bitterness. please tray to find that to yourself, so you will find reset before you die, life is to short to live the way you are living now. When you read this I know you may say horrible things about me but, you are forgiven! So you know!

  ReplyDelete
 23. Hi guys,
  I live in Midwest, USA. I share the writers idea. In our church we have a problem of parking. During Holidays, we park on grass land, by the side of neighbors, which are all illegal. The committee members always announce not to do, but still we are using. So, I believe that we Ethiopian need to do a lot to change according to the US law. Let God bless us to avoid this "Gedeleshenet'. Amen

  ReplyDelete
 24. እኛ ዘንድ ግን በተለይ ‹ከተሜ በሚባለው አካባቢ› በሕግና ሥርዓት አስከባሪው እንጂ በሕጉና ሥርዓቱ የመመራቱ ባሕል እምብዛም ነው፡፡ ከሕጉ ይልቅ የሕግ አስከባሪው ይፈራል፤ ይከበራልም፡፡ በዚህም ምክንያት ሕጉ ሰውየው ሆኗል፡፡ ለዚህም ይመስላል የትራፊክ ፖሊስ ሲኖርና ሳይኖር የትራፊክ ሕጉ አከባበር የሚለየው፡፡ ሕጉ የባለሥልጣኑ መሪ ሳይሆን፣ ሕጉ የባለሥልጣኑ ተገዥ ነው፡፡

  ReplyDelete
 25. 100 % right i agree this idea we are careless.

  ReplyDelete
 26. U KNOW WHY U ARE RUBBISH NARROW MIND" lemagn woyane brought begging to the central Ethiopia and then start insulting us. "bagoresku tenekesku"

  ReplyDelete
 27. lemagn woyane brought begging to the central Ethiopia and then start insulting us. "bagoresku tenekesku"

  ReplyDelete
 28. Thumbs up as usual but more so at this time. Uncivilized, Uneducated and oppurtunistic arrogancy describes most tribes of Ethiopia all over the world

  ReplyDelete
 29. Dn.Getaye ZelalibelaAugust 27, 2014 at 5:17 PM

  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ ያርታህ
  ‹‹የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ›› ይላሉ አበው፡፡
  ይህ እውነታ ነው፡፡ ልማድ ትልቅ ህመም ወይንም በሽታ ነው፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ኃጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል፤ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል›› የሚባለው፡፡ አብዝኃኛዎቻችን በተወለድንበትና በአደግንበት አካባቢ፣ በተማርንበት ት/ቤት፣ በኖርንበት ማኅበረሰብ አስነዋሪዉን፣ አስቀያሚውን፣ ነውሩን፣ ጸያፉን፣ ስድቡን፣ ውሸቱን፣ ለሕግ ለሥርዓት አለመታዘዝን፣ ከእኔ በላይ አዋቂ የለም ማለትን፣ አለማድመጥን፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ቅድሚያ አለመስጠጥት፣ አለመከባበርን፣ ከእኔ ትብስ አለማለትን፣ ይቅርታ አለመጠየቅን ሳንማር፣ ሳናውቅ፣ ሳንረዳ ነው ያደግነው፡፡
  እነዚህንም ያስተማረን የነገረን የለም ቢነግሩንም በሰከነ መንፈስ ሊያስተምር በሚችል መንገድ ሳይሆን በዱላና በግድ ነው የተነገሩን፡፡ እነዚህን እየመረረን ሰማናቸው፣ ሳንፈልግ አስተማሩን በዚህም እኛም የእነርሱን ይዘን አደግን ‹‹አንድ ጅል የተከለውን አሥር ብልህ አይነቅለውም›› ነውና እድሜ፣ ጾታ፣ ቋንቋ ሳይገድበን አፋችን ነውር ሲናገር ይውላል፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል እንዳልከው ጃፓኖች ወደ አንድ አካባቢ ሲመጡ በርከት ብለው በአንድ ላይ ነው፡፡ አንድ ወቅት ሁሉም በመሸፈኛ አፍና አፍንጫቸውን ሸፍነው ይሔዳሉ፡፡ ለምን እንደዚህ እንዳደረጉ ስጠይቅ የመጡበት አካባቢ በጣም ንጹሕ እንደሆነችና ሌላ ቦታ ሲሔዱ ከበሽታ ራሳቸውን ለመጠበቅ መከላከያ እንደሚጠቀሙ ተረዳሁ፡፡
  ስለዚህ በዚህ ማኅበረሰብ ያደግን ሌላ ቦታ ስንሔድ እንዴት ከአካባቢው ማኅበረሰብ እንስማማለን፣ እንዋኃዳለን፣ እንግባባለን? ችግሩ ከምንጩ ነው፡፡
  ቀድሞ አባቶቻችን ለንጽሕና፣ የሰውን መብት በማክበር፣ በሰላም አብሮ በመኖር ለዓለም ምሳሌ ነበሩ፡፡ እኛ ግን ይህ ጠፍቶብን እንዲሁ በዘፈቀደ እንኖራለን ይህንን ወላጆች፣ ት/ቤቶች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ መምህራን፣ የሃይማኖት አባቶች ከመሠረቱ ትውልዱን ቀርጸው ማሳደግ እንዳለባቸው አምናሉ፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው አደግንና ከሀገራችን ውጪም ሕጋቸው፣ ወጋቸው፣ ሥርዓታቸው፣ ባህላቸው፣ አኗኗራው፣ የሥራ ጠባያቸው፣ የኑሮ ዘይቤአቸው ጋር የማይዛመድ ድርጊት የምንከውነው፡፡ አረ እንታረም፣ እንስተካከል ያስብላል፡፡
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 30. አክሊለ ሰማዕትAugust 29, 2014 at 11:44 AM

  ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን! ይህ ችግር እኮ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ በየገዳማት በማኅበር ጉዞ ሲደረግ የሚያጋጥም ነው፤ በይበልጥ ግን በቆሻሻ ማስወገድ ሥርዓታችን። ነገር ግን በማኅበር ጉዞ ጊዜ የጉዞው አዘጋጅ ኮሚቴ በመኖሩ ብዙ ችግሮች እንዲቃለሉ ያደርጋል። ለምሳሌ ቆሻሻ ገዳሙን እንዳያበላሸው ከምዕመናን ማንም የተጠቀመበትን እቃ መሬት ላይ እንዳይጥል፣ ከጣለም በስነሥርዓቱ ማብቂያ ላይ እንዲያነሱ ያደርጋል። ለጉዞው ቅድሚያ ዝግጅት ያደርጋል፤ ከእነዚህም ዝግጅቶች አንዱ የመኪና ማቆሚያ መኖሩን ያረጋግጣል። ስለዚህም መነኮሳቱም በምዕመናኑ አይማረሩም፤ ስነሥርዓት የማስከበርም ሥራ አያጋጥማቸውም። በዚህ አንፃር በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ምዕመናን እንዲህ ዓይነት ችግራቸውን ለመቅረፍ በዚህ አካሄድ ቢሄዱ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በግል መምጣቱ ችግሩ ብዙ ነው፤ የሥርዓት አጠባበቁ እጅግ ደካማ ነው። በማኅበር መሄዱ ግን ብዙ ነገር ያቃልላል፤ በግል መኪና ከመሄድ ባሶችን(buses) ተከራይቶ ብዙ ምዕመናንን ቢወስድ የመኪና ማቆሚያ ችግርን ያስወግዳል፤ የሚከሰተውንም የሕግ አለማክበር እና መቀጮ ያስወግዳል እንዲሁም የነዳጅ ፍጆታን ይቀንሳል። በሥርዓት አጠባበቁም ላይ ብዙ ጥቅም አለው። ብቻ ቢያስቡበት ብዙ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።

  ReplyDelete
 31. አልፎ አልፎ እንደሚታየው ግን ሕግና ሥርዓትን በማወቅና በማክበር ረገድ በአንድ ቀን የፖሊስ ትምህርት ተለውጦ የግራ ጠርዙን ይዞ የሚጓዘው የሀገሬ ገበሬ እጅግ ተሽሎ ይታያል፡፡ ያ ሁሉ ገበሬ መሥመር ጠብቆ ሲሄድ አንድም የትራፊክ ፖሊስ በአካባቢው አይታይም፡፡ ታድያ ቦታ ተቀያይራችሁ ትሞክሩት እንዴǃ

  ReplyDelete
 32. .....ያ ሁሉ ገበሬ መሥመር ጠብቆ ሲሄድ አንድም የትራፊክ ፖሊስ በአካባቢው አይታይም፡፡ ታድያ ቦታ ተቀያይራችሁ ትሞክሩት እንዴǃ
  endeza sayshal ayikerm

  ReplyDelete
 33. Wow that is really true. Let me add something Dn Daniel from my recent experience. It was on our lady st Mary fast season. Our new church was giving service for the 16 days from 4 Am to 8pm. They told us not to park in front of the church for weekdays since there are some renters who used that spot. Even they kept a red con on the entrance. We have big parking space but u need to walk a min or 2 to the church. But, some fox kept doing it not to walk that short distance. I was surprised to see that and tried to justify that those people might not knew or it could be their 1st day. But it was not. We just are ignorant and do not care what the church governing body says. Any ways like your "miliketa"

  ReplyDelete