Tuesday, July 22, 2014

እንደገና እንጋባ

(ሁለተኛ ደብዳቤ)
ምን ብዬ ጠርቼሽ ልቀጥል
ለካስ እስካሁን የተዋደዱና የተጣሉ ሰዎች የሚጠራሩበት የቅጽል ስም እንጂ የተለያዩ፣ ግን ያልተጣሉ ሰዎች የሚጠራሩበት የቅጽል ስም የለንም፡፡ መቼም አንዳንዱን  ነገር የምንረዳው ሲገጥመን ብቻ ነው፡፡ በኑሯችን ውስጥ የሚጎድሉ፣ ነገር ግን ልብ የማንላቸው ጥቃቅን ነገሮች ብቅ የሚሉት ታላላቅ ነገሮችን አጥተን ቦታው ክፍት መሆኑን ስናረጋግጥ ብቻ ነው፡፡ ‹ውዴ› ብዬ እንዳልጠራሽ ተለያይተናል፤ ‹አንቺ ምናምን› ብዬ እንዳልጠራሽ ደግሞ እኔና አንቺ ተለያይተናል እንጂ ልቤና ልብሽ መለያየቱን እንጃ፡፡ ብቻ ለማንኛውም ዝም ብዬ ሐሳቤን ልቀጥል፡፡
ሰሞኑን ካንቺ ለመጨረሻ ጊዜ ተለያይቼ ከሌላ ሰው ጋር ስለ መኖር ሳስብ ነበር፡፡ ነገር ግን እስከ ዛሬ አስቤያቸው የማላውቅ ሐሳቦች ወደ ልቡናዬ እየመጡ ይሞግቱኝ ጀምረዋል፡፡ አንዱ ሞጋች እንዲህ አለኝ፡፡ ወደህ፣ ፈቅደህ፣ አፍቅረህ ካገባሃት፣ አብረሃትም ለዚህን ያህል ዓመት ከኖርካት፣ ከምታውቅህና ከምታውቃት፣ ካነበበችህና ካነበብካት ሴት ጋር አብረህ ለመኖር ካልቻልክ ከሌላዋ ጋር አብረህ ለመኖርህ ምን ዋስትና አለህ? ይህችንምኮ ያገባሃት አንተው ነህ፤ እንደ ጥንቱ ወላጆችህ አጭተውልህ ቢሆን ኖሮ በእነርሱ ታመካኝ ነበር፤ ያመጣሃትም የተጣላሃትም አንተው ነህ፤ ለእኔ የተሻልሽው አንቺ ነሽ ብለህ፤ ዐውቄሻለሁ፤ ተስማምተሽኛል ብለህ ያገባሃት አንተው ነህ፤ ያስገደደህ አካል አልነበረም፤ እንዲህ ብለህ ካገባሃት ሴት ጋር መኖር ለምን አቃተህ? እንዲህ ብለህ ካገባሃት ሴት ጋር መኖር ያቃተህ ሰው ከሌላዋ ጋር ለመኖርህ ምን ዋስትና አለህ?

አሁን ልፍታት፣ ልለያት ከምትላት ሴት ጋር ስትገናኝ የምታወራውን ነው ከሌላዋ ሴትም ጋር የምታወራው፤ አሁን ልለያት የምትላትን ወድጃታለሁ እንደምትለው ነው ሌላዋንም ወደድኩ የምትለው፤ አሁን ለመለየት አፋፍ ላይ የደረስካትን ሴት ባየህበት ዓይን ነው ሌላዋንም የምታየው፤ ከዚህችኛዋ ይልቅ ከዚያችኛዋ ጋር እንደሚሳካልህ በምን ዐወቅክ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡ እዚህ ጨው ጎድሎ እንደሁ እዚያ ሽንኩርት ይጎድላል፣ እዚህ በርበሬው አርሮ እንደሆነ እዚያ ዘይቱ ይንጨረጨራል፣ እዚህ ወጡ ቀጥኖ እንደሆን እዚያ እንጀራው ይቆመጥጣል፣ እዚህ አልጋው አልመች ብሎ እንደሆነ እዚያ ወንበሩ ይቆረቁራል፣ እዚህ አንሶላው ቢቀዘቅዝ እዚያ ፍራሹ ይጎረብጣል፤ ሁሉም ጋ ጎደሎ አለ፡፡ ሽሽትህ አንዱን ጎደሎ በሌላ ጎደሎ ለመተካት ነው ወይ? ከነብር ሸሽተህ ከአንበሳ ለመጠለል ነው ወይ? ከዝናብ ሸሽተህ እሳት ለመግባት ነው ወይ? ከጉድጓድ አመለጥኩ ብለህ አዘቅት ለመውደቅ ነው ወይ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡ ያቺንስ በምን አረጋገጥካት? ልክ እንደዚህቺኛዋ ከውጭ አይደለም ወይ ያወቅካት? ስትገባ ምን እንደሚያጋጥምህ ማን ነው ያረጋገጠልህ? ብሎ ይሞግተኛል፡፡
ለመሆኑ ጎደሎ የሌለበት፣ ሁሉም የተሟላለት ሰው አለ ወይ? የትዳር ዓላማው መሟላት አይደለም ወይ? በሂደት እየገጠሙ፣ እየገጠሙ፣ እየገጠሙና እየተሟሉ መሄድ አይደለም ወይ? የስንዴው መዘራት፣ መብቀል፣ መታጨድ፣ መወቃት፣ መለቀም፣ መፈጨት፣ መነፋት፣ መቦካት፣ በእሳት መብሰል አይደለም ወይ ዳቦውን ዳቦ አድርጎ የሚያወጣው? ይኼ ሁሉ ሂደት ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለመለየት፣ ፍሬውን ከገለባው ለመነጠል፣ ሽርክቱን ከላመው ለመለየት፣ የተለያየውን የስንዴ ቅንጣት አንድ ለማድረግ፣ አንድ አድርጎም ለማዋሐድ፣ አዋሕዶም ለማብሰል አይደለም ወይ ጥቅሙ? እንደ መዘራቱ ሁሉ መታጨዱ፣ እንደ መሰብሰቡ ሁሉ መወቃቱ፣ እንደ መበጠሩ ሁሉ መፈጨቱ፣ እንደ መቦካቱ ሁሉ በእሳት መጋገሩ አስፈላጊ አይደለም ወይ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡
ትዳርስ እንዲህ አይደለም ወይ? በጉዞ ውስጥ የሚያጋጥሙት ክፉውም ደጉም አይደሉም ወይ ትዳርን ትዳር የሚያደርጉት? የሚያዋሕዱት? የሚያበስሉት? ገበሬው እህሉ ወድቆ እንዳይቀር እንጂ እንዳይታጨድ አይደርገውም፡፡ ጋጋሪዋም ዳቦው እንዳያር እንጂ እንዳይበስል አታደርገውም፡፡ ትዳርስ እንዲህ አይደለም ወይ? እህሉ ወድቆ ቢቀር ገበሬው፣ ዳቦውም ቢያርር ጋጋሪዋ አይደለችም ወይ ተጠያቂው? የሃይማኖት አባቶች ምን ይላሉ፡፡ አዳም ቢያጠፋም እግዜር ግን ‹ፍጠረኝ ሳይለኝ ፈጥሬው ልተወው አይገባም› ብሎ የፈጠረውን ሰው ራሱ ሊያድነው ሰው ሆነ፤ የአዳምን ቅጣት ራሱ ወሰደ፡፡
አንተስ ትዳሩ ‹መሥርተኝ› ብሎሃል? ጎጆው ቀልሰኝ ብሎሃል? ራስህ አይደለም የጀመርከው? ስለዚህ ትዳርህን የመዋጀት ግዴታ አለብህ፡፡ ችግሩን የመፍታት ግዴታ አለብህ? መሥርተኝ ሳይልህ የመሠረትከውን ትዳር፣ ውለደኝ ሳይሉህ የወለድካቸውን ልጆች ትተህ የመሄድ ሰዋዊ መብት ማን ሰጠህ? ለመሆኑ ይኼ ነጻ መውጣት ነው ወይስ ሽሽት? ችግር መፍታት ነው ወይስ ሽንፈት? እያለ ይሞግተኛል፡፡
በዚህ ጊዜ ነው አንድ ወዳጄ ‹‹ጓደኝነት በመኪና እንደመሄድ ነው፡፡ ቢደብርህ የፈለግክበት ቦታ ላይ ወርደህ በእግርህ ትሄዳለህ፡፡ አቁምልኝ ማለት ብቻ ነው፡፡ ቢበዛ ፖሊስ ይቀጣሃል፡፡ አለቀ፡፡ ትዳር ግን በአውሮፕላን እንደመሄድ ነው፡፡ ዝም ብለህ ደበረኝ፣ ሰለቸኝ፣ መረረኝ ብለህ የሆነ ቦታ ላይ መውረድ አትችልም፡፡ አውሮፕላኑ እስከሚሄድበት ቦታ ድረስ የመሄድ ግዴታ አለብህ፡፡ በመኪና ስትሄድ ዕንቅልፍህ ቢመጣ አቁመህ ወርደህ ትተኛለህ፤ በአውሮፕላን ግን እዚያው ነው የምትተኛው፡፡ በመኪና ስትሄድ ቢርብህ ወርደህ ሆቴል ገብተህ ትመገባለህ፡፡ በአውሮፕላን ስትሄድ ግን እዚያው የሚሰጥህን ነው የምትበላው፡፡ በመኪና ስትሄድ አየር መቀበል ቢያምርህ ከመኪናህ ወርደህ ወደ አንድ ነፋሻ ቦታ ትጓዛለህ፡፡ በአውሮፕላን ግን የሚሰጥህን አየር ነው የምትተነፍሰው፡፡›› ያለኝ ትዝ አለኝ፡፡
እስኪ አስቢው ወላጆቻችን በዘመናት ያዳበሯቸው የትዳር ችግሮች መፍቻ መንገዶች ነበሩ፡፡ እነዚህን መንገዶች ‹ኋላ ቀር ናቸው፣ የሴቶችን መብት የሚጨቁኑ ናቸው፣ የልጆችን መብት የማያስከብሩ ናቸው፣ የወንድ የበላይነትን የሚያነግሡ ናቸው፣ ኃይልና ጉልበትን የሚቀላቅሉ ናቸው› ብለን አወገዝናቸው፡፡ ይሁን፣ አንዳንዶቹ እንደሚባለው ናቸው፡፡ ችግሩ ችግሩን ማወቃችንና ማውገዛችን አልነበረም፡፡ በሌላ፣ እኛ ዘመናዊና የተሻለ በምንለው መፍትሔ አለመተካታችን ብቻ ነው፡፡ አንድ ቤት ውስጥ ያለውን ዕቃ ‹ኋላ ቀር ነው› ብለን አስወጥተን ጥለን ቤቱን ወና ብናደርገው የአይጥ መጨፈሪያ ነው የሚሆነው፡፡ አንድን የኖረ መፍትሔ አስወግደን በሌላ ካልተካነውም ችግሩን ያለ መፍትሔ ነው የተውነው፡፡ አንድን ነገር ማስወገድ ማለት በተሻለ ነገር መተካት ማለት አይደለም፡፡ መተካትም እንደማስወገድ ቀላል አይደለም፡፡ ይኼው እንደምታዪው ለኢራቆች ሳዳምን ማስወገድ፣ ለሊቢያዎችም ጋዳፊን መግደል ቀላል ነበረ፡፡ የተሻለ ማምጣት ግን እንደ ማስወገዱ ቀላል አልሆነላቸውም፡፡
እኔና አንቺም እንዲሁ የሆንን ይመስለኛል፡፡ እኛ ከወላጆቻችን በልጠን ዘመናዊ ያደረግነው ነገር ቢኖር ፍችን ራሱን ይመስለኛል፡፡ አሁን ፍቺ ዘመናዊ ሆኗል፡፡ እጅግ በጣም ቀሏል፡፡ ዘመናዊ ትዳር፣ ዘመናዊ መፍትሔና ዘመናዊ አኗኗር ግን ገና አላመጣንም፡፡ በዚያ እኛ <ኋላ ቀር> ባልነው የትዳር መርሕ ውስጥ ሆነው ሃምሳ ዓመት፣ ስድሳ ዓመት፣ ሰባ ዓመት የኖሩ ባለ ትዳሮች እያየን ነው፡፡ ዘመናዊ በተባለው ትዳር ውስጥ ግን ዐሥር ዓመት ብርቅ እየሆነ ነው፡፡ ታድያ ምኑን ዘመንነው? ምናልባት ያለፉትን ነገሮች ኋላ ቀር ናቸው እያልን ስናስወግድ አብረን ያስወገድነው ‹የትዳር ዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒት› ይኖር ይሆን?
ይህንን ሁሉ የምለው ነገሮችን በረጋ ኅሊና፣ በሰከነ ልቡና፣ በበሰለ አእምሮ፣ እንደገና ማየት እንችል እንደሆነ ብዬ ነው፡፡ ነገሮችን እንይና፣ እናርምና፣ እንሞረድና፣ እንደገና እንጋባ፡፡ እንዲያውም ትዳር ለመመሥረት አሁን ነው የተሻለው ጊዜ፣ የተሻለው ሁኔታ፡፡ ችግሩ በደንብ አብስሎናላ፡፡
በእውነቱ እዚህ ላይ አንድ ይቅርታ መጠየቅ አለብኝ፡፡ ‹‹ባለቤቴ›› ስለሚለው ነገር እጽፋለሁ ብዬ ነበር፡፡ ለካስ እርሱ ቃል ያላወቅነው ጥልቅ ነገር አለው፡፡ ለዚህ ሲባል ብቻ አንድ የደብዳቤ ዕድል ስጭኝ፡፡
በሦስተኛው ደብዳቤዬ እነግርሻለሁ፡፡
ያንቺው (የሆንኩትም፣ የነበርኩትም፣ ምናልባትም የምሆነውም)


45 comments:

 1. ‹ጓደኝነት በመኪና እንደመሄድ ነው፡፡ ቢደብርህ የፈለግክበት ቦታ ላይ ወርደህ በእግርህ ትሄዳለህ፡፡ አቁምልኝ ማለት ብቻ ነው፡፡ ቢበዛ ፖሊስ ይቀጣሃል፡፡ አለቀ፡፡ ትዳር ግን በአውሮፕላን እንደመሄድ ነው፡፡ ዝም ብለህ ደበረኝ፣ ሰለቸኝ፣ መረረኝ ብለህ የሆነ ቦታ ላይ መውረድ አትችልም፡፡ አውሮፕላኑ እስከሚሄድበት ቦታ ድረስ የመሄድ ግዴታ አለብህ፡፡

  ReplyDelete
 2. I appreciate your view, but this view does not apply for majority of divorce case. Divorce happen because one or both of them do not want to accept responsibility. They were hanging out as boy/girl friend leaving all other responsibilities on the shoulders of their respective families. Now, when the time comes to manage their wealth and time, they fail. Evenif one of them is ready, the other my have lack of respect or ability to obey or listen to his/her partner. Through time frustration builds up and love fades. That's why people get divorce. If they have very little positive feeling of each other as you mention, they would not have gone for divorce at all.
  anyway, you have raised nice points, but it's too ideal.

  ReplyDelete
  Replies
  1. hi I don't speak for Daniel but you may wanna read it again he didn't say this is the only reason however one of the main reason why divorce rate is hike

   Delete
  2. Dear anonymous July 23,
   Are you divorced...

   Delete
  3. Dear Anonymous July 25,
   Does it matter for you?

   Delete
 3. አሁን ልፍታት፣ ልለያት ከምትላት ሴት ጋር ስትገናኝ የምታወራውን ነው ከሌላዋ ሴትም ጋር የምታወራው፤ አሁን ልለያት የምትላትን ወድጃታለሁ እንደምትለው ነው ሌላዋንም ወደድኩ የምትለው፤ አሁን ለመለየት አፋፍ ላይ የደረስካትን ሴት ባየህበት ዓይን ነው ሌላዋንም የምታየው፤ ከዚህችኛዋ ይልቅ ከዚያችኛዋ ጋር እንደሚሳካልህ በምን ዐወቅክ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡ እዚህ ጨው ጎድሎ እንደሁ እዚያ ሽንኩርት ይጎድላል፣ እዚህ በርበሬው አርሮ እንደሆነ እዚያ ዘይቱ ይንጨረጨራል፣ እዚህ ወጡ ቀጥኖ እንደሆን እዚያ እንጀራው ይቆመጥጣል፣ እዚህ አልጋው አልመች ብሎ እንደሆነ እዚያ ወንበሩ ይቆረቁራል፣ እዚህ አንሶላው ቢቀዘቅዝ እዚያ ፍራሹ ይጎረብጣል፤ ሁሉም ጋ ጎደሎ አለ፡፡ ሽሽትህ አንዱን ጎደሎ በሌላ ጎደሎ ለመተካት ነው ወይ? ከነብር ሸሽተህ ከአንበሳ ለመጠለል ነው ወይ? ከዝናብ ሸሽተህ እሳት ለመግባት ነው ወይ? ከጉድጓድ አመለጥኩ ብለህ አዘቅት ለመውደቅ ነው ወይ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡ ያቺንስ በምን አረጋገጥካት? ልክ እንደዚህቺኛዋ ከውጭ አይደለም ወይ ያወቅካት? ስትገባ ምን እንደሚያጋጥምህ ማን ነው ያረጋገጠልህ? ብሎ ይሞግተኛል፡፡እኛ ከወላጆቻችን በልጠን ዘመናዊ ያደረግነው ነገር ቢኖር ፍችን ራሱን ይመስለኛል፡፡ አሁን ፍቺ ዘመናዊ ሆኗል፡፡ እጅግ በጣም ቀሏል፡፡ ዘመናዊ ትዳር፣ ዘመናዊ መፍትሔና ዘመናዊ አኗኗር ግን ገና አላመጣንም፡፡ግሩም ጸሐፊ የስንቶቻችንን ቤት አንኳኳ ብዙ ባለትዳሮች ቢያውቁትና የራሣቸውን ትዳር ቢያዩበት ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ጽሁፉ የኔና የባለቤቴን ታሪክ ቁልጭ አድርጉ ያሳየን ሲሆን ያፈራናቸውን ልጆችና ንብረት ለመበታተን የምናደርገውን ሩጫ ትተን ወደ መፍትሄ እንመጣ ነበር፡፡ ይህ ለመሆንና ለማንበብና ልቦናችን የተሰበሰበና ፈሪሃ እግዚአብሄር በውስጣችን ሲኖር ብቻ ነው ወንድሜ ሆይ የአንተን ትዳር ወደነበረበት ይመልስልህ ዘወትር ምኞቴ ነው እህቴ ሆይ አንቺም ልብሽን ለእግዚአብሄር አስገዢ የሚሆነው ነገር ይሆናል የማይሆን አይሆንም እግዚአብሄር ሁሌም ለኛ ይጨነቃል ያስባል ምናልባትም ምን ያህል የይቅርታ ልብ እንዳለሽ ምን ያህል ቤትሽን እንደምትወጂ ልታይበት የምትችይውን ችግር ነውና የሚሰጠው እባክሽን ወደ ነበረው ኑሮሽ ተመለሽ ይህ ለኛም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ጽሁፍ ሆኖ ስላገኘሁት ነው ይህን የምልሽ እኔም በ21 ዓመት የትዳር ቆይታ በኋላ ነው ቤቴ ተበጥብጦ ባለቤቴ ልጆቹን፣ ቤቱንና ንብረቱን ጥሎ ዛሬ በፍ/ቤት ላይ የምገኘው ስለዚህ ከመፋታት ምንም አይገኝምና ትዳራችሁን ወደ ነበረበት መልሱት ዳኒ አንተንም እግዚአብሄር ይባርክህ

  ReplyDelete
 4. የየራሳችንን ሰው የራስ ስለማድግ በማሰብ ብቻ ለምንሮጥ ሰዋውያን ከሩጫችን የሚያስረጋጋን ምርጥ እይታ!!!!!!!!

  ‹‹ጓደኝነት በመኪና እንደመሄድ ነው፡፡ ቢደብርህ የፈለግክበት ቦታ ላይ ወርደህ በእግርህ ትሄዳለህ፡፡ አቁምልኝ ማለት ብቻ ነው፡፡ ቢበዛ ፖሊስ ይቀጣሃል፡፡ አለቀ፡፡ ትዳር ግን በአውሮፕላን እንደመሄድ ነው፡፡ ዝም ብለህ ደበረኝ፣ ሰለቸኝ፣ መረረኝ ብለህ የሆነ ቦታ ላይ መውረድ አትችልም፡፡ አውሮፕላኑ እስከሚሄድበት ቦታ ድረስ የመሄድ ግዴታ አለብህ፡፡ በመኪና ስትሄድ ዕንቅልፍህ ቢመጣ አቁመህ ወርደህ ትተኛለህ፤ በአውሮፕላን ግን እዚያው ነው የምትተኛው፡፡ በመኪና ስትሄድ ቢርብህ ወርደህ ሆቴል ገብተህ ትመገባለህ፡፡ በአውሮፕላን ስትሄድ ግን እዚያው የሚሰጥህን ነው የምትበላው፡፡ በመኪና ስትሄድ አየር መቀበል ቢያምርህ ከመኪናህ ወርደህ ወደ አንድ ነፋሻ ቦታ ትጓዛለህ፡፡ በአውሮፕላን ግን የሚሰጥህን አየር ነው የምትተነፍሰው፡፡››  ReplyDelete
 5. ዲ/ዳንኤል ፈጣሪ ላንተ ነገሮችን በተለየ መልኩ እንድታይ የሰጠህ መክሊት አለ፡፡ መክሊትህን ከዚህ በበለጠ ለማብዛት መጣር አለብ በአንተ ብሎግ ብዙ ነገር እየተማርኩ ነው የሚገርምህ የኔ ትዳር ፈተና ውስጥ ነበር ነገር ግን የመጀመሪያውን ደብዳቤ ሳነብ በደንብ ወደ ውስቴ ማየት አስችሎኝ ትዳሬን ከፈተና ለመታደግ ትረት በማድረግ ተወሰነ ደስ የሚል ለውጥ እየመጣ ነው በጣም አመሰግናለሁ፡፡በርታ ፈጣሪ ለኛ የሰጠን በረከታችን ነህ ዘርህ ይብዛ ዕውቀትህ የሌሎችን ጨለማ ያብራ፡፡ የሁል ግዜ ብሎግህን አንባቢ ዜድ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 6. ዲ/ዳንኤል ፈጣሪ ላንተ ነገሮችን በተለየ መልኩ እንድታይ የሰጠህ መክሊት አለ፡፡ መክሊትህን ከዚህ በበለጠ ለማብዛት መጣር አለብ በአንተ ብሎግ ብዙ ነገር እየተማርኩ ነው የሚገርምህ የኔ ትዳር ፈተና ውስጥ ነበር ነገር ግን የመጀመሪያውን ደብዳቤ ሳነብ በደንብ ወደ ውስጤ ማየት አስችሎኝ ትዳሬን ከፈተና ለመታደግ ጥረት በማድረግ የተወሰነ ደስ የሚል ለውጥ እመጣ ነው በጣም አመሰግናለሁ፡፡በርታ ፈጣሪ ለኛ የሰጠን በረከታችን ነህ ዘርህ ይብዛ ዕውቀትህ የሌሎችን ጨለማ ያብራ፡፡ የሁል ግዜ ብሎግህን አንባቢ ዜድ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 7. ዳ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅህ!!!

  ReplyDelete
 8. ዳ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅህ!!!

  ReplyDelete
 9. ዳ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅህ!!!

  ReplyDelete
 10. ዳ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅህ!!!

  ReplyDelete
 11. Awesome as usual, thanks Dani!

  ReplyDelete
 12. amlaki mechchlun ysten .

  ReplyDelete
 13. መቼም ታረቁ ፥ ተቻቻሉና ኑሩ የሚለው ምክርህ ፡ በቤታቸው ሰላም ያጡ ባለትዳሮች የችኮላ ውሳኔ እንዳይወስኑ አስተማሪ ነው። በርታታበት!

  ግን

  " ይኼው እንደምታዪው ለኢራቆች ሳዳምን ማስወገድ፣ ለሊቢያዎችም ጋዳፊን መግደል ቀላል ነበረ፡፡ የተሻለ ማምጣት ግን እንደ ማስወገዱ ቀላል አልሆነላቸውም፡፡"

  ያልካት አስገራሚ መልክት ነች!

  የትሻለ ነገር አይመጣምና ወያኔ ይግዛችሁ ይመስላል፡፡ ምንዋ ዲን ፥ እረ አይገባም፡፡
  የማያውቁትን ጉዳይ መተውን የመሰለ ነገር የለም፡፡

  አውቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሀፍ አጠበች! እንዳይሆንብህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውድ ጸሐፊው ምነው አንድ ነገርን ለምን በበጐ መመልከት አንችል አልን ወያኔንም ቢሆን እኮ እግዚአብሄር ፈቅዶና ወዶ ያስቀመጠው እንጂ በአንተ ወይንም በእኔ ወይንም በራሱ ፍላጐት አይደለም የተቀመጠው ማንሳትም ማስቀመጥም የኛ ስልጣን ሳይሆን የእግዚአብሄር ፍቃድ ነው ምናለ አንድን ነገር በአንድ አይንና በጥላቻ እናስተናግዳለን እባክህ የቅንነት ጉዳይ እንጂ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ክርክርም ሆነ አባባል የለበትም ትችት ለመተቸት ከምንቸኩል እስኪ ጽሁፉን በደንብ አንብበውና ትዳር ውስጥ ካለህ የራስህን ትዳር እይበት ከሌለህም ወደፊት ለምትመሠርተው ትዳር ትዳር ምን ያህል ጥንቃቄ እንደሚፈልግ እወቅበት እንጂ አትተች ከሌላ ነገር ጋር አታያይዝ

   Delete
  2. " ይኼው እንደምታዪው ለኢራቆች ሳዳምን ማስወገድ፣ ለሊቢያዎችም ጋዳፊን መግደል ቀላል

   አልሆነላቸውም፡፡"

   Delete
  3. "እግዚአብሄር ፈቅዶና ወዶ ያስቀመጠው"

   ቅድም አያቴን ፈልግና ፎግራቸው!

   ጥረህ ግርህ እንጀራህን ብላት ፥ ፈጣሪ ማለቱን የሰማህ አይመስለኝም፡

   Delete
  4. አንተ ከቅድመ አያትህ ስለመሻልህ እርግጠኛ ነህ?

   Delete
 14. Le bale tidaroch bcha sayhon gena beguadegnet lay lalenewem astemari yehone mel-ekit!!!!

  ReplyDelete
 15. ግሩም እይታ ፀጋውን ያብዛልህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን

  ReplyDelete
 16. ለባለትዳሮችም ሆነ ወደፊት ትዳር ለመመስረት ሃሣቡ ላላቸው በጣም ጠቃሚ ትምህርት ነ፡፡ ቃለህይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 17. ዳኒ ”ትዳር የሚሰራው ቤት ውስጥ ነው ሰርጉ መግቢያ ነው” ብለህ በሬድዮ የተናገርከው የትዳሬ ስንቅ ሆኖኛል ቃለህይወት ያሰማልኝ

  ReplyDelete
 18. I like most of them but some of them are hard to read and it is far from fact for example “አዳም ቢያጠፋም እግዜር ግን ‹ፍጠረኝ ሳይለኝ ፈጥሬው ልተወው አይገባም› ብሎ የፈጠረውን ሰው ራሱ ሊያድነው ሰው ሆነ፤ የአዳምን ቅጣት ራሱ ወሰደ” it is very false statement and you should take out from your composition because Devil created by God but God didn’t die for devil. As we all know that Devil never asked to created by God.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear anonymous,
   What you know about religion is 1+1=2, but there are lots of equations that bring 2.
   Devil did not ask... but Adam did...

   Delete
  2. Dear Anonymous July 24,
   ሰይጣን እኮ ተፀፅቶ አምላኩን ይቅርታ እንደ አዳም አልጠየቀም።

   Delete
  3. ወንድሜ ታዲያ ዲብሎስ ፈቅዶ እ/ሄርን እንደተቃወመ አዳምን ግን ዲብሎስ በተንኮልና በቅናት ተነሳስቶ እንዳሳተው አትርሳ፡፡ በኔ እይታ የሰይጣን አፈጣጠርና ኃጢአት ከሥጋ አባታችን አዳም ጋር ለየቅል ናቸው፡፡

   Delete
  4. If the creation and sin of devil and Adam are quite different, then why would YOU bring the analogy of Adma’s sin to devil’s sin for this issue? Yes devil is created by God. The reason why God didn't die for devil is because devil does not have repentance thought. The analogy of devil and Adam shall not be bring in this issue, in my view. ልክ ነህ ሰይጣን እና አዳም ለየቅል ናቸው፡፡

   Delete
 19. nice view we are going to be ready which havent got married yet!!!

  ReplyDelete
 20. ”ትዳር የሚሰራው ቤት ውስጥ ነው ሰርጉ መግቢያ ነው” ብለህ በሬድዮ የተናገርከው የትዳሬ ስንቅ ሆኖኛል

  ReplyDelete
 21. dn.Daniel EGZIABEHIR bewqet lay ewqet,, be tebeb lay tebeb,behulu yesteh. bertaaaaaaa!!!! Ethiopian EGZIABEHIR ytebqlen enganem bemhretu yaseben, ytbarke tedar ytbarke tweled ysten AMEN!

  ReplyDelete
 22. ወያኔ ይግዛችሁ-------- ብለህ መልእክት የፃፍክ ወንድም ምነው ጌዜ አባከንክ ዲ.ዳንኤል ያለው አልገባህ ብሎ አይመስለኝም እንዲሁ ግን ቅን ካለማሰብ የመጣ ይመስለኛል እዚህ ላይ የተነገረው የእግዚሐብሔር ቃል ለበጎች ነው ምናለ በግ/የዋህ/ቅን/ ሆነህ ብታስብ የፖለቲካ ጥያቄ ካለብህ ስለፖለቲካ ሲወራ አውራ ወንድሜ ልቦና ይስጥህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. " ይኼው እንደምታዪው ለኢራቆች ሳዳምን ማስወገድ፣ ለሊቢያዎችም ጋዳፊን መግደል ቀላል

   አልሆነላቸውም፡፡"

   Delete
 23. ወገን እንንቃ!!!

  የመጀመሪያ ደወል:  ራሱን የሙስሊሞች ከሊፋ (መሪ) ብሎ የሰየመው የኢራቁ Islamic State of Iraq and the Syria (ISIS) መሪ በቅርቡ የሙስሊሞች ሀገር (Islamic State) ብሎ ባወጣው ካርታ መሠረት በአፍሪካ ውስጥ ሶስት ክፍላተ-ሐገራት ያካተተ ሲሆን አንደኛዋ ክፍለ ሀገር ሐበሻ (The Land of Habesha) የምትባል ስትሆን በውስጧም ጁቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያን ያከተተች መሆኑ ተዘግቧል።

  ምንጭ: Sudan Tribune, July 13, 2014

  ሁለተኛው ደወል:  የሱዳን መንግስት የቤተ ክርስቲያን ግንባታ ሀገሪቱ እንደማይካሄድ እና የቤተ ክርስቲያን መስሪያ ፍቃድ እንደማይሰጥ guidance and Religious Endowments ሚኒስትር ሳህሊል አብዱሏህ ማስታወቃቸው፣ ይህም ውሳኔ
  የተላለፈው ደቡብ ሱዳን ከተገነጠለች በኋላ በሀገሪቱ የሚኖሩ ሕዝበ ክርስቲያናት ቁጥር ዉስን በመሆኑ እና ያሉትም አብያተ-ክርስቲያናትም ለህዝብ-ክርስቲያኑ በቂ መሆናቸው መጠቀሱ፣ ነገር ግን በሀገሪቱ የሚኖሩ ቀሳውስት ውሳኔውን መቃወማቸው
  መታወቁ ተዘግቧል።

  ምንጭ: The Tablet, July 16,2014

  ReplyDelete
 24. good point Daniel

  ReplyDelete
 25. tilek timhret naw berta

  ReplyDelete
 26. አዳም ቢያጠፋም እግዜር ግን ‹ፍጠረኝ ሳይለኝ ፈጥሬው ልተወው አይገባም› ብሎ የፈጠረውን ሰው ራሱ ሊያድነው ሰው ሆነ፤ የአዳምን ቅጣት ራሱ ወሰደ፡፡
  አንተስ ትዳሩ ‹መሥርተኝ› ብሎሃል? ጎጆው ቀልሰኝ ብሎሃል? ራስህ አይደለም የጀመርከው? ስለዚህ ትዳርህን የመዋጀት ግዴታ አለብህ፡፡ ችግሩን የመፍታት ግዴታ አለብህ? መሥርተኝ ሳይልህ የመሠረትከውን ትዳር፣ ውለደኝ ሳይሉህ የወለድካቸውን ልጆች ትተህ የመሄድ ሰዋዊ መብት ማን ሰጠህ? ለመሆኑ ይኼ ነጻ መውጣት ነው ወይስ ሽሽት? ችግር መፍታት ነው ወይስ ሽንፈት? እያለ ይሞግተኛል፡፡

  ReplyDelete
 27. በትዳራችን ውስጥ መተጋገዝ የሌለን፣ ሁሉን አንድ ወገን ብቻ እንዲከውንና እኛ ግን ምንም እንዳይጎድልብን የምንፈልግ ስንት ባለትዳሮች አለን? ወይ ካልተረዳዳን ወይ ጭቅጭቁን ካላቆምን ለታይታ ብቻ ታዛዥና ትዳር አክባሪ ከሆንን ከቤታችን ጉዳይ ይልቅ ለሌሎች ጉዳዮች ብቻ ቅድሚያ የምንሰጥ ከሆነ ታዲያ መጨረሻችንስ ምን ሊሆን ይችላል?

  ReplyDelete
 28. ምነዋ ዋናውን ትዳር አፍራሽ ሚሳኤል ፥ ገንዘብን የሚጠቅሰው ጠፋ!

  ReplyDelete
 29. እጅግ የማከብርህ እና የምወድህ ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ለኛም እንደነዚህ አይነቶች መካሪ ወንድም እግዚአብሔር ያብዛልን፡፡በእድሜ በጤና ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
 30. እጅግ የማከብርህ እና የምወድህ ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ለኛም እንደነዚህ አይነቶች መካሪ ወንድም እግዚአብሔር ያብዛልን፡፡በእድሜ በጤና ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
 31. አሁን ልፍታት፣ ልለያት ከምትላት ሴት ጋር ስትገናኝ የምታወራውን ነው ከሌላዋ ሴትም ጋር የምታወራው፤ አሁን ልለያት የምትላትን ወድጃታለሁ እንደምትለው ነው ሌላዋንም ወደድኩ የምትለው፤ አሁን ለመለየት አፋፍ ላይ የደረስካትን ሴት ባየህበት ዓይን ነው ሌላዋንም የምታየው፤ ከዚህችኛዋ ይልቅ ከዚያችኛዋ ጋር እንደሚሳካልህ በምን ዐወቅክ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡

  ReplyDelete
 32. አሁን ልፍታት፣ ልለያት ከምትላት ሴት ጋር ስትገናኝ የምታወራውን ነው ከሌላዋ ሴትም ጋር የምታወራው፤ አሁን ልለያት የምትላትን ወድጃታለሁ እንደምትለው ነው ሌላዋንም ወደድኩ የምትለው፤ አሁን ለመለየት አፋፍ ላይ የደረስካትን ሴት ባየህበት ዓይን ነው ሌላዋንም የምታየው፤ ከዚህችኛዋ ይልቅ ከዚያችኛዋ ጋር እንደሚሳካልህ በምን ዐወቅክ? ይለኛል ሞጋቹ፡፡

  ReplyDelete