Tuesday, July 15, 2014

ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬ ዳዋ

(አርቲስቱና ሽቅርቅሩ የድሬዳዋ ሕዝብ)

ደራሲ፡- አፈንዲ ሙተቂ
የገጽ ብዛት፡-191
ዋጋ፡- 46 ብር
የኅትመት ዘመን፡- 2006 ዓም
አፈንዲ ሙተቂ ያበረከተልንን መጽሐፍ አነበብኩት፡፡ ከአዋሽ ወዲያ ማዶ ያለውን ሀገራችንን ሙልጭ አድርገን ለማወቅ የሚጎድለን ነገር መኖሩን የምንረዳው የእርሱን መጽሐፍ ስናነብ ነው፡፡ እንኳን እንደ እኔ በጎብኝነት የሚያውቀው ቀርቶ ተወልጄበታለሁ አድጌበታለሁ የሚለው ሁሉ የቀበሌ መታወቂያውን እንደገና እንዲያወጣ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው፡፡
ሰው የሚያውቀውን ሲጽፍ ወይም የሚጽፈውን ሲያውቅ እንዲህ ያለ መጽሐፍ ይገኛል፡፡ ባሕሉ አልቀረ፣ ትውፊቱ አልቀረ፣ አባባሉ አልቀረ፣ ታሪኩ አልተዘለለ፣ መልክዐ ምድራዊ መረጃው አልተዘነጋ፣ አፈ ታሪኩ ቦታውን አልሳተ፣ ሁሉም በመልክ በመልኩ ተሰድሮ እንደ መልካም የወታደር ሠልፍ የቀረበበት መጽሐፍ ነው፡፡

አፈንዲ ለአካባቢው ወግና ታሪክ ቅርበት ብቻ ሳይሆን ፍቅርም እንዳለው፣ ፍቅር ብቻም ሳይሆን ጥናትም እንዳለው፣ ጥናትም ብቻ ሳይሆን ትኩረትም እንዳለው መጽሐፉ ያሳየናል፡፡ የሕዝቡን ፍቅርና አንድነት፣ መተሳሰብና አብሮነት፣ የቆየውን የመተጋገዝ ልማድና ተግባቦት ያሳየባቸው ወጎቹ የመለያየት ጥላ ላጠላበት ህልውናችን ፈዋሾ ናቸው፡፡
በተለይም የሐረርጌ ኦሮሞን ትውፊትና ባሕል፣ የአስተዳደር ታሪክና ዕምቅ ብቃት ያሳየበት ጹሑፉ እዚያው ሕዝቡ ውስጥ ያለን ያህል እንድንረዳው የሚያደርግ ነው፡፡ አፈንዲ የአካባቢውን ነገር ሲነግረን በአንዳንዶች ዘንድ እንደሚታየው እንድንጠብ አድርጎ ሳይሆን እንድንሰፋ አድርጎ ነው፡፡ ያንን አካባቢ ከእኛ ውጭ አድርገን እንድናየው አድርጎ ሳይሆን ውስጡ እንድንገባበት አድርጎ ነው፡፡
አፈንዲ ሦስት ነገሮች አሉት፡፡ ርትዕ፣ ዕውቀትና የኃላፊነት ስሜት፡፡ ነገሮችን ያየበት መንገድ ርትዕ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ በአካባቢው ለተደረጉ ነገሮች ሁሉ ሃይማኖትና ዘርን ሳይለይ ለሁሉም የድርሻውን ሰጥቷል፡፡ የተለያዩ እምነቶች፣ ባሕሎችና ግለሰቦች በአካባቢው የነበራቸውን በጎ ሚና ለማጉላት፣ ክፉውንም በጨዋነት ለማረም ያደረገው ጥንቃቄ የሚያስመሰግነው ነው፡፡
አፈንዲ በተለይ ከአዋሽ ማዶ ስላለው ታሪክ፣ ባሕል፣ ትውፊትና መልክዐ ምድር ለሌላውም ሊተርፍ የሚችል ዕውቀት ስላለው የሚጽፈው የቃላት ስብስብ አይደለም፡፡ በእያንዳንዱ ቃል ላይ ዕውቀት ያዘለ ነገር አለው፡፡ የሚጽፍ ሰው የሚጽፈው ነገር የት እንደሚደርስ አያውቅምና በኃላፊነት ስሜት እንዲጽፍ ይመከራል፡፡ አፈንዲ በዚህ መጽሐፉ በእምነቶች፣ በሕዝቦች፣ በጎሳችና በፖለቲካ መሪዎች መካከል ተግባቦት ይፈጠር ዘንድ፣ መደናነቅና መከባበር እንዲኖር የሚያደርጉ ሐሳቦችን በኃላፊነት መንፈስ ጽፏል፡፡ ‹‹እንዴው ዘራፌዋ›› የሚል ነገር አላየሁበትም፡፡ ታላቅ ችሎታና ብስለት ነው፡፡

አንቡት፡፡ ታውቃላችሁ፣ ትዝናናላችሁ፣ ትጨምራላችሁ፡፡


22 comments:

 1. I am so eager to read the book, thank you Dn Daniel. God be with you!!!

  ReplyDelete
 2. me too, eager to read it

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሔር ይባርክህ ዲ.ዳንኤል፡፡ ምን አለ እንዳተ አይነት ፀሀፊዎች ቢበረክቱልን፡፡ አሁን ላይ የተያዘዉ ፋሽን ከእኔ በላይ አዋቂ የለም እኔ ከማንም በላይ ነኝ ነዉ እንጂ ልክ እንደ አንተ ፀሀፊዎችን ማድነቅ እና ከዚያም አልፎ ሌላዉ ሕዝብ እንዳቃቸዉ እና ስራቸዉን እንዳነብላቸዉ የሚያደርግ ታላቅ ሰዉ አጥተናል፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ እይታዎችህንም ይባርክልህ!!! አሜን!!!

  ReplyDelete
 4. እናመሠግናለን ገዝተንም እናነባለን

  ReplyDelete
 5. I admire the person. I listen the interview on Sheger Radio. I will buy his book soon.

  ReplyDelete
 6. Metsehafun eskanebew betam guaguaw.

  ReplyDelete
 7. TIRU GIBZHA NEW ENAMESEGINALEN!!

  ReplyDelete
 8. DANIYE KENE BITESEBH YEBEREKET SEW YBELH. BERTA

  ReplyDelete
 9. Where is part two, I am waiting. If you don't like it to post it you shouldn't tell us otherwise you have to post it. God blessed you & I love you so much Danie.

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንደ ወፍ ጫጩት ፡ ተቀምጦ መጉረስ ለመድንና ተቸገርን ፡፡

   Delete
  2. What do you mean? I asked him what he promised for us. I didn’t ask him to do something special to me. In addition that he think how his follower love his article. You may know only this proverb so you use it in unnecessary time. Please keep in until you get the wright mistake. I don’t blame you because you grew-up by talking behind people not asking what do you want. Furthermore you don’t know Danial Kbret because it you know him, you know what democracy mean. This is the only site freedom of speech. Please think twice before you comment somebody idea. SHAME ON YOU .God blesses Danial.

   Delete
 10. Thanks for your recommendation. I appreciate what you are doing. God will be with you!

  ReplyDelete
 11. እንዳነብ ስላነሳሳከኝ አመሰግለሁ፡፡

  ReplyDelete
 12. Dn. Dani.... Hw U? I just appreciate z way you right always.....am just recommend one thing with out this topic.... knw wat you just promise to write "Endegena engaba" part two after a week but now it is almost 15 days so please am so eager to read it so please post as soon as you can...! thank you...! God bless you and z whole Ethiopian people...!

  ReplyDelete
 13. Hello the Anonymous person July, 17, 2014 at 9:03PM.
  Your have right to question, but how do you asked matter. You look like bossy. As a matter of fact Daniel Kbret is a human being so we don’t know in what situation involved at this time. He may write books, travel outside the country, spending his time with family or other problem. In addition that nobody pay him for his time, he works voluntarily, so we should respect his privacy. When we ask him any kind of question, we have to ask him in appropriate manner. For example “Hello Diakon Daniel, I read the previous article and I love it so much, as you told us the second chapter will continue, I am very interested to read that part so please post is as soon as you can”. God bless you and your family. “ If you wrote just like this nobody comment for your request but you wrote just like bossy. Please think before you post something.

  ReplyDelete
 14. መጸሐፉን በተመለከተ በውስጤ ያለውን አጉል ነገር ለማውጣት፣
  አንብበሕ እዳነበው ላደረከው ሁሉ አመሰግንሀለው፡፡

  ReplyDelete
 15. አመሰግናለሁ፤ መጽሐፉን ገዝቼ እያነበብኩ ነው፡፡ ነገር ግን ዋጋው አንተ ከጠቀስከው በብር 14.00 ጭማሪ አለው ለምን የሚል ጥያቄ በውስጤ ስላነሳብኝ የጭማሪውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 16. አመሰግናለሁ፤ መጽሐፉን ገዝቼ እያነበብኩ ነው፡፡ ነገር ግን ዋጋው አንተ ከጠቀስከው በብር 14.00 ጭማሪ አለው ለምን የሚል ጥያቄ በውስጤ ስላነሳብኝ የጭማሪውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 17. I think you bought it from retailers on the road ....gas stations & other places. ..but you shouldn't because they will erase the real price and they will put there own price tag...I used to buy from retailers in cafés and gas stations but I regret it now...last week I accidentally go to a book store at yeha building in front of stadium and I was really shocked that there was a price difference from 15-130 birr on most of my book collections which I bought from the street vendors. ......SO my advice is NEVER EVER BUY BOOKS FROM STREET VENDORS UNLESS U WANTED TO BE CHEATED GO AND BUY BOOKS FROM BOOKSTORES NEAR YOUR PLACE

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለሰጠኸኝ ምላሽ አመሰግናለሁ፤ ለወደፊቱ እንድጠነቀቅ ረድቶኛል፡፡

   Delete

 18. ከመስቀል በዓል ጋር በተያያዘ ጥያቄ ነበረኝ ይኸውም በቤተ/ክርስትያናችን የደመራ ዕለት በየቤቱ ካህናት/ዲያቆናት እየተዞሩ እንኳን አደረሳችሁ የሚሉበት ስርዓት አለ ወይ? ዘንድሮ ለመጀመሪያ ግዜ ያጋጠመኝ ስለሆነ ማወቅ ፈልጌ ነው፤ ለምላሹ በቅድሚያ አመሰግናለሁ፡፡

  ReplyDelete