Thursday, July 10, 2014

እንደገና እንጋባ

ይህንን ደብዳቤ ስጽፍ ፊት ለፊቴ የቤተሰባችንን ፎቶ ግድግዳው ላይ እያየሁ ነው፡፡ ‹‹ይናገራል ፎቶ›› አሉ፡፡ አቤት በፎቶማ እንዴት ያምርብናል፡፡ ፎቶ ላይ ያለው ፈገግታ እንዲሁ ትዳር ውስጥም ቢቀጥል እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ ግርም ይላልኮ፡፡ፎቶ አንሺዎች ሁሉ ከአንድ እናት የተወለዱ ይመስል ለምንድን ነው በግድ ‹‹ፈገግ በሉ›› የሚሉት፡፡ በቃ ፎቶ ማለት ደስታን ማሳያ ብቻ ነው እንዴ፡፡ የከፋው ሰው ፎቶ አይነሳም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ፎቶ አንሺዎችና ቪዲዮ ቀራጮችኮ በገዛ ሠርጋችን ተዋንያን ያደርጉናል፡፡ እንደ ራሳችን ሳይሆን እንደ እነርሱ ፈቃድ ያስኬዱናል፣ ያሳስሙናል፣ ያስተቃቅፉናል፣ ያሰልፉናል፣ ያጣምሙናል፣ ያቃኑናል፡፡ እነርሱ ግን የፊልም ዳይሬክተር ናቸው ወይስ የሠርግ ቪዲዮ ቀራጮች? እኛስ ሙሽሮች ነን ወይስ ተዋንያን?
ከተለያየን ጀምሮ ይህንን ፎቶ ደጋግሜ እያየሁ ደጋግሜ አስባለሁ፡፡ ለብቻ መሆን አንድ የሚጠቅመው ነገር ቢኖር የማሰቢያ ጊዜ መስጠቱ ነው፡፡ ሰው ለመኖር ለካ ከምግብና መጠለያ እኩል የማሰቢያ ጊዜም ያስፈልገዋል፡፡ እንዲሁ ስንዞር፣ እንዲሁ ስንወጣና ስንወርድ፣ እንዲሁ ቀዳዳ ለመሙላት ወዲህ ወዲያ ስንል፣ እንዲሁ ጠዋት ወጥተን ማታ ስንገባ አይደል እንዴ የኖርነው? አሁን ሳስበውኮ የኑሮ ወንዝ ወደወሰደን ፈሰስን እንጂ አስበን አልኖርንም፡፡

እስኪ ልጠይቅሽ ለመሆኑ ለኛ ትዳር ምንድን ነበር? አንድ ቤት መኖር፣ አንድ አልጋ ላይ መተኛት፣ ልጆች መውለድ፣ ወላጆቻችን ቤት አንድ ላይ መሄድ፣ መጎራረስ፣ <ከባለቤትዎ ጋር> ተብሎ መጠራት፣ ምንድን ነው ግን ትዳር? ለመሆኑ ሠርገን ነበር ወይስ ተጋብተን ነበር? ጋብቻ ነበረን ወይስ ትዳር? አቤት ለሠርጋችን እንዴት ነበር የለፋነው፡፡ ‹‹ጋብቻ የትዳር መጀመሪያው ሥነ ሥርዓቱ ነው፤ ሠርግ ማጀቢያው ድግስ ሲሆን፣ ትዳር ደግሞ በዚህ በኩል ተገብቶ የሚኖረው ኑሮ ነው›› የሚል ካነበብኩ በኋላ ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ጀምሬያለሁ፡፡ አዳራሽ ለማግኘት፣ መኪና ለማግኘት፣ የሠርግ ልብስ ለመምረጥና ለማሰፋት፣ ድግሱን ለማሣመር፣ የሚጠሩ ሰዎችን ለመምረጥ፣ ሚዜዎቻችንን ለመምረጥ ስንቴ ነበር ያሰብነው፤ ሰሐንና ብርጭቆ እንኳን ሳይቀር አስበንበት፣ ሰው አማክረን፣ ዙረን መርጠን፣ ከሌሎች ልምድ ወስደን ነበር የተከራየነው፡፡
በእኔና ባንቺ ሠርግ ስንት ሰዎች ተሳተፉ፣ ስንቶች ለፉ፣ የስንት ሰዎች ሐሳብ ተዋጣ፣ የስንቶች ልምድ ተቀሰመ፣ የስንቶች ጉልበትስ ፈሰሰ፡፡ በያንዳንዱ ጉዳይ እንወያይ፣ እንከራከር፣ እንጨቃጨቅ፣ እንለያይ ነበር፡፡ በያንዳንዱ ጉዳይ እንደገና እንገናኝ፣ እንግባባ፣ እንስማማና እንታረቅ ነበር፡፡ በብዙ ሰዎች ታግዘን አግብተን ትዳርን ብቻችንን ገጠምነውና አልቻልነውም፡፡ ሠርግ ላይ ያለው እገዛ ትዳር ላይ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር፡፡
አሁን ሳስበው የለፋነው ለሠርጋችን እንጂ ለትዳራችን አልነበረም፡፡ እስኪ ትዝ ይበልሽ፡፡ ከኛ በፊት የተጋቡ ሙሽሮችን ልምድ የወሰድው ስለ ሙሽራ ልብስ፣ ስለ ቬሎ፣ ስለ ሚዜ፣ ስለ መኪና፣ ስለ ድግስ፣ ስለ አዳራሽ፣ ስለ መጥሪያ ካርድ፣ ስለ ባንድ፣ ስለ ቪዲዮ እንጂ ስለ ኑሯቸው አልነበረም፡፡ እነርሱምኮ ‹ዲል› ባለ ድግስ፣ የሁላችንንም ቀልብ በማረከ ሥነ ሥርዓት ተጋብተው ይሆናል፡፡ ከዚያስ? ነው ጥያቄው፡፡ የኛስ ሠርግ ጉ-ድ የተባለ አልነበረም፡፡ እስካሁን ድረስ የእኔና የአንቺን ሠርግ እንደ ትንግርት የሚያወሩት አሉኮ፡፡ ከሠርጉ በኋላ የሆንነውን ስለማያውቁ፡፡
አንድ ወዳጄ ትዳርና ችግኝ አንድ ነው ብሎኛል፡፡ ሁለቱም ክብካቤ ይፈልጋሉ፡፤ ሁለቱም በየጊዜው መኮትኮትና ማሳደግን ይጠይቃሉ፡፡ ሁለቱም መከርከምና ድንጋይና አረሙን እንዲያስወግዱላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ሁለቱም የዕለት ተዕለት ትኩረት ይሻሉ፡፡ እኛ ግን እንደዚያ ያደረግን አይመስለኝም፡፡ ጉልበታችን ሁሉ ለሠርጉ ፈሰሰና ትዳሩ ላይ አቅም ጠፋ፡፡ ‹‹ዳገት ላይ ሰው ጠፋ›› አሉ ፕሮፌሰር መስፍን፡፡ ድሮ ልጆች ሆነን
ገንዘባችን ሁሉ አለቀ በሻይ
ሚስት ሳናገባ ዓለምን ሳናይ - እንል ነበር፡፡ ከየት የመጣ ግጥም እንደሆነ እንጃ፡፡ የኛም ጉልበታችንና ዐቅማችን ሁሉ ሠርጋችን ላይ ፈሰሰና ‹ዓለምን ሳናይ› ቀረን፡፡ ይገርምሻል፡፡ በቴሌቭዥን ሰሞኑን የችግኝ ተከላ ዜና ሲነገር ትዝ የሚለኝ የእኔና የአንቺ ትዳር ነው፡፡ ድሮ በሠፈራችን በሚገኝ ጋራ ላይ ሰኔ በመጣ ቁጥር በቀበሌ ትእዛዝ እየወጣን የምንተክለው ችግኝ ነበር፡፡ ከተከልነው በኋላ ግን ዞር ብሎ የሚያየው የለም፡፡ ሰኔና ሰኞ የገጠመለት  ችግኝ ይጸድቃል፡፡ ሌላው ግን ደርቆ ይቀራል፡፡ ቀበሌውም ማስተከል እንጂ ማሳደግ አያውቅበትም፡፡ የብዙዎቻችን ትዳር እንደዚያ ይመስለኛል፡፡ ልክ አንድ አገር ሰው ተሰብስቦ ችግኝ እንደሚተክለው ሁሉ አንድ አገር ሰው ተሰብስቦ ትዳር የሚባለውን ችግኝ የሠርግ ቀን ይተክለዋል፡፡ ችግኙን ማንም ዞር ብሎ እንደማያየው ሁሉ ትዳርን የሚከባከበው፣ ውኃ የሚያጠጣው፣ አረም የሚነቅልለት፣ አፈር የሚያደርግለት፣ ፋንድያ የሚደፋለት፣ አውሬ እንዳያበላሸው አጥር የሚቀጥርለት የለም፡፡ ልክ ያደለው ችግኝ በዕድል አድጎ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ያደለው ትዳርም አድጎ ተመንድጎ እናየው ይሆናል፡፡ ‹‹አፍራ ያለው ተኝቶም ያፈራል›› ይባል የለ፡፡ ብዙ ትዳሮች ግን እንደ ብዙዎቹ ችግኞች ከስመው ቀርተዋል፡፡
እኔማ አንዳንዴ ‹ለሠርጋችን ከተጨነቅነው ግማሹን እንኳን ለትዳራችን አድርገነው ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ባልሆንን ነበር› እላለሁ፡፡ እንዴው ብቻዬን ስለሆንኩ ሰው አያየኝም እንጂ፣ ያበድኩኮ ነው የምመስለው፡፡ ብቻዬን እስቃለሁ፤ ብቻዬንም አወራለሁ፡፡ ባለፉት ዓመታት ያወራናቸውን ሳስባቸው ስለ ቤት ወጭ፣ ስለ ልጆች ትምህርት ቤት፣ ስለ ወላጆቻችን፣ ስለ ጎረቤቶቻችን፣ ስለ ልቅሶና ሠርግ፣ ስለ ርዳታና መዋጮ፣ ስለ መኪናና የቤት ዕቃ፣ ስለ ሥራ ቦታ ችግሮች ሆነው አገኛቸዋለሁ፡፡ እነዚህ ነገሮች ግን ብቻ እንዴት ትዳርን ያሳድጉታል? እንዴትስ ፍሬያማ ያደርጉታል? ስለ እኔና ስለ አንቺ፣ ስለምትወጅውና ስለምትጠይው፣ ስለምንጨምረውና ስለምናርመው፣ አንቺን ይበልጥ ስለማስደሰትና እኔን ይበልጥ ስለማርካት፣ እኔ ላንቺ ማድረግ ስላለብኝና አንቺ ለእኔ ማድረግ ስላለብሽ ነገር ማውራታችንን፣ መወሰናችንንም አላስታውስም፡፡
ደግሞ የሚገርምሽ ነገር፤ ዛሬ ዛሬ ሳስበው ግርም የሚለኝ፣ የምንነጋገረውኮ በሚያጋጥሙን ነገሮች ላይ ብቻ ነው፡፡ አንዳች ነገር ካልገጠመን አንነጋገርም፡፡ ለነገሩማ በዝምታ አድገን እንዴት መነጋገር እንልመድ ብለሽ ነው፡፡ ‹‹ጥፋቱስ አይደለም ካንቺ ወይም  ከእኔ፣
ፍቅር በመሆኑ እንጂ ጽድቅና ኩነኔ፣
አንቺ አንቺን መሆንሽ እኔ እኔን መሆኔ››
አሉ አብዬ መንግሥቱ እውነታቸውን ነው፡፡ እንዴው ጊዜ ወስደን፣ ከሌላው ነገር ወጣ ብለን፣ እየተዝናናንም ቢሉ ወይም ለራሳችን ጊዜ ሰጥተን ስለ ወደፊት ኑሮአችን፣ ስለ እኔና አንቺ ጉዳይ፣ ልናደርገው ስለምንፈልገው ነገር ወይም መሆን ስለምንሻው ጉዳይ አውርተን እናውቃለን ብለሽ ነው? እንዴው ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ አንድ ነገር ይገጥመናል፣ በዚያ ላይ እናወራለን፣ ጉዳዩ ከእኔ ወይንም ካንቺ ጋር ይገናኝና አንዳችን አጥቂ ሌላችን ተከላካይ እንሆናለን፡፡ ከዚያማ ‹‹ጨሰ አቧራው ጨሰ›› ማለት ያኔ ነው፡፡ ግን ለመሆኑ ይህንን ‹‹ጨሰ አቧራው ጨሰ›› የሚል የሠርግ ዘፈን ያመጣው ማነው? መቼም እንደኔ አግብቶ የፈታ ሰው መሆን አለበት፡፡
በተለይማ ልጆች ከመጡ በኋላ ባሰብን፡፡ እኔም ባልሽ መሆኔ ቀርቶ የልጆችሽ አባት ሆንኩ፤ እንቺም ሚስቴ መሆንሽ ቀርቶ የልጆቼ እናት ሆንሽ፡፡ ለመሆኑ ግን ከኛ የሚተርፈንን ጊዜ ነው ለልጆች መስጠት ያለብን ወይስ ከልጆች የሚተርፈውን ጊዜ ነበር እኛ መውሰድ የነበረብን? ለመሆኑ በትዳር ውስጥ ዋናው ጉዳይ ምንድን ነው? ‹ባለቤቴ› የሚለውን ባሕላዊ አጠራር የወደድኩትም ያደነቅኩትም አሁን ነው፡፡ ለምን መሰለሽ? በቀጣዩ ደብዳቤዬ እነግርሻለሁ፡፡
ብንጣላም፣ ብንለያይም፣ ባንግባባም፣ ግን ደኅና ሁኚ፡፡
ያንቺው የቀድሞ ባለቤት
(ሳምንት ይቀጥላል)
 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው40 comments:

 1. Always an excellent observation! May I ask you a question that where can I get soft copy Geez books in word/pdf format? Particularly, tselot metsahft, melkamelk, Mezmure Dawit, Metsihaf Kidus wezete. Sorry for the language mix.

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአማን ነጸረJuly 11, 2014 at 10:16 AM

   just search using z key word,i.e;
   www.ethiopianorthodox.org
   i hope u will freely get z online library of our mother EOTC.No defamatory word,no simulation of advocacy in z name of EOTC,no accusation of fathers...u shall only b confronted with amizing huge collection of classic EOTC books!!

   Delete
  2. Dear bro use the following sites
   http://debelo.org/
   http://www.ethiopianorthodox.org/amharic/holybooks/ and if u need to buy @ http://www.mereb.com.et/rs/?pn=1&ct=mai&sc=&cat2items=Eth.%20Orthodox%20Tewahedo%20Church&cat1=Books in addition @ Face book join groups working on such books like book for all and Ethiopian orthodox Tewahedo books

   Delete
 2. በጣም የሚገርም ታሪክ ነው መጨረሻቸው ምን ይሆን እግዚአብሄር በጐ ነገር እንደሚያደርግ ሙሉ እምነት አለኝ እኒ አንተንም እግዚአብሄር ረጅም የአገልግሎት ዘመን ይስጥህ በዚህ ጉዳይ አንተም ቢሆን ገብተህበት የነዚህን ሰዎች ትዳር ወደ ነበረበት እንደምትመልሰው ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ

  ReplyDelete
 3. ይህ ታሪክ የብዙ ትዳሮችን ቤት ያንኳኳል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን የኛ ይቅርታ ጠያቂነትን እንደውርደት እየቆጠርን እየተፈላለግን ስንቶቻችን ቤታችንን አፍርሰናል ልጆቻችንን ያለ አባት ያለ እናት አስቀርተናል እባካችሁ ወንዶች በትዳራችሁ ውስጥ ሰው በተለይ ቤተሰብን /እናትና እህት የሚባሉትን ሰዎች እየከተታችሁ ቤታችሁን አትበትኑ የኔም ትዳር በእናቱና በእህቱ በተለይ በተለይ በእናቱ ምክንያት ተበትኗልና ይቅርታ ጠያቂ መሆን ደግሞ ትልቅ ትልቅ አዋቂነት ነው አጉል መጃጃልና አላዋቂነት እኔ እበልጣለሁ ማለት ስለሆነ አሁንም የዚህን ሰዎች ታሪክ ያነበባችሁ ሙሉውንም ባያልቅ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰበት ራሱ የተነካው ነው የሚያውቀውና ሳይረፍድባችሁ ይቅርታ ጠይቃችሁ ኑሯችሁን ወደ ነበረበት መልሱት ትልቁና ዋነኛው ተጐጂ ለትዳር መፍረስ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ እናንተ ወንዶች ናችሁና ይልቁንም ለትዳራችሁ ክብር ስጡ ሴቶችም ትዳሯችሁን አክብሩ በተረፈ ዳኒ ለአንተ እግዚአብሄር ያድልህ ምናልባትም ብዙ ሰዎች ከጸብ በኋላ ከቤተሰባቸው ጋር በገቡት ቃለ መሐላ ማለትም አልፈልግም ትዳሬን ካሉ በኋላ ወደ ራሳቸው ሲመለሱ ዙሪያው ገደል ስለሚሆንባቸው እፍረትም ስለሚይዛቸው ከአፈርኩ አይመልሰኝ ለሚሉ ትምህርት ሊሆናቸው ስለሚችል እንደነዚህ ዓይነት ጽሁፎች ትልቅ ትምህርት ሊሰጡ ስለሚችሉ በዚሁ ቀጥል

  ReplyDelete
 4. እኔማ አንዳንዴ ‹ለሠርጋችን ከተጨነቅነው ግማሹን እንኳን ለትዳራችን አድርገነው ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ባልሆንን ነበር› እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. ሠርጉ በሰፊው ተደግሶ ውስኪው በየጠረጴዛው ቆሞ እስክስታ ካልመታማ ፡ ትዳር ምን ትርጉም አለው፡፡ ወገበ ረጂሙ መኪና ለሙሽሮቹ ብቻ ሳይሆን ለሚዜዎቹም አስገላጊነቱ ያማያከራክር ጉዳይ ነው፡፡ ጥሎሹስ ? ግን ይብቃኝ ፡ ማለቂያ የለውምና፡፡

  ታንገት ከረባት ቂጥ ባዶ አሉ! ይህም ባልከፋ ነበር ፡ እኛጋ ጭንቅላት ባዶዎቹ በዛንና ጉድ ፈላብን እኮ!

  ሼራተን ሆቴል ያየሁት የሴት ሰባት ሚዜ ፡ የወንድ ሰባት ሚዜ ያሰለፈ ሠርግ ፥ ጉዳዩ ማለቂያ የሌለው የፉክክር መድረክ መሆኑን እማኝ ሁኖ አሳይቶኛል፡፡ ለመሆኑ ይህ ባህል ከየት መጣ? የኛው የራሳችን ባህል ነው እንዳልል መረጃ የለም፡፡ ዓለመን የተቆጣጣርዋት ነጮችም እንዲህ አይነቱን ድግስ ተጠርተው ለመብላት እንጂ ፥ ጠርተው ለማብላት ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ አበሻ ግን ነጮቹም አገር ነዋሪ ሆኖ የሚቀይረው ነገር የለውም፡፡

  ለትዳሩ እግዜአብሔር ያውቃል ፥ የድግሱን ጉዳይ ግን ወደ እግዜአብሔር ለመግፋት?

  አበሻን ሆድ! አሉ ፍሮፌሰር መስፍን

  ReplyDelete
 6. I think the husband came from abroad by force. If he doesn’t like work with his previous wife, she will put him in jail until he die or as she said before she will kill him after she get all information. At the movement he has many supporters in the world especially in England. In addition that the entire world has been demonstrated to bring him back. She has been hearing many things from his supporter. I think if he agree to married her back she will keep him as a free man otherwise he will die soon. Everything has been on his choice because she is in love so she wants married him back. Most people think, he doesn’t want married her back because he doesn’t agree with her leadership. He likes unity to change the country but she likes separation to stay on her leadership until she dies. Most of his people like his idea but she has power to kill everybody. He knows that she is rude when somebody brings new idea but he prefers to die for his people. I hope we will hear good news on the next chapter.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What are you talking about? You make me feel "didn't i read the article properly?".

   Delete
  2. Thank you so much the Anonymous person, whatever she said, he will not marry her back. As you said we will stand beside him. He fought for us the past 40 years, his unity idea bother her and she has been follow him for many years, now she got him but he doesn’t want married her back. I hope he will release soon with God permission. He fought for us more than anybody in Ethiopian history. God bless Mr Andargachew Tsege

   Delete
 7. It great and deep insight observation of real face. God bless you and your family.

  ReplyDelete
 8. ቃለ-ሒወት ያሰማልን ዲ. ዳንኤል በዚህ ጉዳይ ብዙ ወገኖቻችን በችግር ላይ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም እናም ብዙ ትንተናና ትምህርት ያስፈልገዋል ስሊዚህ እግዚሐብሔር በሰጠህ ፀጋ የብዙዎችን ሰዎች ሂወት እንደምትታደግ ተስፋ አለኝ እግዚሐብሔር ያበርታህ ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 9. I can't wait to read the upcoming story. till then i prefer to say nothing!

  ReplyDelete
 10. I wonder, I wonder, I wonder very much from grade three she married a husband. As we all know that Ethiopia has the worst culture in the world. Many of our sisters get married in early age so they are not matured to lead the house so they prefer to divorce. I know most of these blog followers not accept my idea because you guys live in Addis Ababa or outside the country but 85% of Ethiopian live in the rural area and I am taking about them not the rest of 15% people. To protect divorce we have to change this stupid culture. In addition that, we have to teach our old people about this situation. Even if we teach the children, they are not the decision maker. The past two years, I traveled some Oromia, Amhara and Tigray region and I loved Tigray region they are very smart people and they changed the old fashion thinking but Oromia and Amara region are stupid and we have to send some people from Tigray region to change their mind otherwise our country will suffer the next 200 years. God bless Tigray people.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አማኑኤል ሆስፒታልም ኢንተርኔት ገብቷል ማለት ነው?

   Delete
  2. @anonymous July 11,2014 at 5;23 PM; Zerega atehun. The way you wrote is stupid, insulting & disrespectful! if You really want to change situations you mentioned first learn how to communicate messages with love!

   Delete
 11. እኩል የሐብት ክፍፍል ችግር ወቅታዊ አይመስለኝም፡፡ በታሪካችን መሬት በጥቂቶች እጅ፣ የፖለቲካ ስልጣን በተመረጡ ጥቂቶች መዳፍ፣ የመማር እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች በችሮታ መልክ ሲሰጡን ኖረናል፡፡ እንደውም የኢትዮጵያ የህዝቧ ታሪክ ከ ኢትዮጵያ ታሪክ ይለያል ብዬ የማስብበት ዋነኛ ምክንያት ብዙሀኑ የሐገሪቱ ህዝብ ለሀብቱ እና ሊያገኘው ለሚገባው ጥቅም ባይተዋር ሆኖ በመኖሩ ነው፡፡ ተራው ህዝብ ግዴታውን ከመወጣት ባሻገር መብቱን አያውቀውም፣አይጠይቀውም፡፡ የአገሪቱን ነጻነት እና ስልጣኔ ለዝንት አለም አስከብሮ የኖረው ሕዝብ ከራስ ጥቅም በነጻ መልኩ ነው፣ ምክንያቱም ተጠቃሚዎቹ ራሳቸውን በአረንጓዴ መስኩ ላይ ያስቀመጡት ወገኖቹ ናቸው፡፡
  ለዚህ ግልጽ ብዝበዛ መፍትሄው ትምህርት ነው፡፡ እስኪ አስቡት መሐይምነት 80 በመቶ በሆነበት አገር ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ቢኖር ነው የሚገርመው፡፡ ወገንን መርጦ መጥቀም እና በጥቅም መተሳሰር ባህል በሆነበት አገር አዋቂነት ዋጋ ባያጣ ነው የሚገርመው፡፡ ቆስለናል፣ ሞቶብናል አገር “ነጻ አውጥተናል” ስለዚህ የበለጠ ጥቅም ይገባናል ማለት ወደ አማርኛ ሲተረጎም እኮ ‘’አገሪቱ በ ጥረጣችን ያቆምናት ኩባንያ ናት ስለዚህ የትርፍ ተካፋይ መሆን የሚገባን እኛ ባለአክስዎኖቹ ነን ማለት ነው’’፡፡ ምልባት ለዛ ይሆናል ሰዎቹ አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ምንምነኛ ዜጋ አለ ያሉት፣ ማለቴ ባለ አክሲዎኖቹን እና አክሲዎን አልባዎቹን ቆጥረው፡፡
  ግብር አጭበርብሮ ምጽዋት በሚሰጥ፣ የእርዳታ እህል ሽጦ ፎቅ ለመስራት ወደኋላ በማይል፣ የሌላውን ሌብነት ለመቃወም ራሱ ሰርቆ ከአገር የሚጠፋ፣ ስርቆት በጠበጠን እያለ የሌባ ዘመዱን የስርቆሽ ንብረት በሚበዘብዝ ማህበረሰብ ውስጥ የሐብት ክፍፍል ፍትሀዊ ቢሆን ተአምር ነው፡፡
  የህግ የበላይነት የማይተካ ሚና አለው፡፡ የፍትህ ስርአቱ ጠንካራ እና ለህዝብ ጥቅም የቆመ ቢሆን ኖሮ ደሃ ማልቀሻ እና የመፍትሄ ተስፋ ይኖረው ነበር፡፡ እስከዛ ግን እባካቹ፣ በናታቹ አትበዝብዙን ከማለት በቀር ምን እድል አለ? ይዘገንናል እኮ ለብዙ ትውልድ በመብት እና በህግ ሳይሆን በመተዛዘን መኖር? በመከባበር ሳይሆን በመፈራራት መዝለቅ?
  እና ፍትሐዊ የሐብት ክፍፍል ለማምጣት መሰረቱ የለንም ነው የኔ THEORY ለዚህ ደገሞ ሁላችንም (ያሉትም የሞቲትም) ተጠያቂ ነን፣ ባህል ተጠያቂ ነው፡፡

  ReplyDelete

 12. 1Paul, called to be an apostle of Jesus Christ through the will of God, and Sosthenes our brother,

  2Unto the church of God which is at Corinth, to them that are sanctified in Christ Jesus, called to be saints, with all that in every place call upon the name of Jesus Christ our Lord, both theirs and ours:

  3Grace be unto you, and peace, from God our Father, and from the Lord Jesus Christ.

  4I thank my God always on your behalf, for the grace of God which is given you by Jesus Christ;

  5That in every thing ye are enriched by him, in all utterance, and in all knowledge;

  6Even as the testimony of Christ was confirmed in you:

  7So that ye come behind in no gift; waiting for the coming of our Lord Jesus Christ:

  8Who shall also confirm you unto the end, that ye may be blameless in the day of our Lord Jesus Christ.

  9God is faithful, by whom ye were called unto the fellowship of his Son Jesus Christ our Lord.

  10Now I beseech you, brethren, by the name of our Lord Jesus Christ, that ye all speak the same thing, and that there be no divisions among you; but that ye be perfectly joined together in the same mind and in the same judgment.

  11For it hath been declared unto me of you, my brethren, by them which are of the house of Chloe, that there are contentions among you.

  12Now this I say, that every one of you saith, I am of Paul; and I of Apollos; and I of Cephas; and I of Christ.

  13Is Christ divided? was Paul crucified for you? or were ye baptized in the name of Paul?

  14I thank God that I baptized none of you, but Crispus and Gaius;

  15Lest any should say that I had baptized in mine own name.

  16And I baptized also the household of Stephanas: besides, I know not whether I baptized any other.

  17For Christ sent me not to baptize, but to preach the gospel: not with wisdom of words, lest the cross of Christ should be made of none effect.

  18For the preaching of the cross is to them that perish foolishness; but unto us which are saved it is the power of God.

  19For it is written, I will destroy the wisdom of the wise, and will bring to nothing the understanding of the prudent.

  20Where is the wise? where is the scribe? where is the disputer of this world? hath not God made foolish the wisdom of this world?

  21For after that in the wisdom of God the world by wisdom knew not God, it pleased God by the foolishness of preaching to save them that believe.

  22For the Jews require a sign, and the Greeks seek after wisdom:

  23But we preach Christ crucified, unto the Jews a stumblingblock, and unto the Greeks foolishness;

  24But unto them which are called, both Jews and Greeks, Christ the power of God, and the wisdom of God.

  25Because the foolishness of God is wiser than men; and the weakness of God is stronger than men.

  26For ye see your calling, brethren, how that not many wise men after the flesh, not many mighty, not many noble, are called:

  27But God hath chosen the foolish things of the world to confound the wise; and God hath chosen the weak things of the world to confound the things which are mighty;

  28And base things of the world, and things which are despised, hath God chosen, yea, and things which are not, to bring to nought things that are:

  29That no flesh should glory in his presence.

  30But of him are ye in Christ Jesus, who of God is made unto us wisdom, and righteousness, and sanctification, and redemption:

  31That, according as it is written, He that glorieth, let him glory in the Lord.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why you end up in nothing relative to the article???

   Delete
 13. በዚህ ዘመን የዲያብሎስ እና የሰራዊቱ አይኖች በትኩረት እና በንቃት እየተከታተሉ እያጠቁት ውጤትም እያስመዘገበላቸው ያለ የሰዉ ልጃች ብቸኛ ተቋም «ትዳር» ባለትዳሮች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የዲያብሎስ ስራ አስፈፃሚ በመሆን አ
  ዓለማችንን ያለጊዜዋ እያፈረስናት ነው ለዚህም ማሳያ የሚሆኑን ከእንደዚህ አይነት ትዳር የወለድናቸው ልጃች ናቸው የሚመስሉትም የሚያክሉትም የሚመኙትም የሚያስቡትም የሚያደርጉትም የሚያወሩትም የሚሆኑትም ልክ እንደ አባታቸው ዲያብሎስ መንፈሳቸው የሉሲፈር መንፈስ ምን ይሻለናል???

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰው ምስሉን ይወልዳልና ፥ ዲያቢሎስ ወልደህ ከሆነ እራስህን መርምር!

   Delete
  2. please comment him in a friendly way

   Delete
 14. ይህ ታሪክ የብዙ ትዳሮችን ቤት ያንኳኳል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን የኛ ይቅርታ ጠያቂነትን እንደውርደት እየቆጠርን እየተፈላለግን ስንቶቻችን ቤታችንን አፍርሰናል ልጆቻችንን ያለ አባት ያለ እናት አስቀርተናል እባካችሁ ወንዶች በትዳራችሁ ውስጥ ሰው በተለይ ቤተሰብን /እናትና እህት የሚባሉትን ሰዎች እየከተታችሁ ቤታችሁን አትበትኑ የኔም ትዳር በእናቱና በእህቱ በተለይ በተለይ በእናቱ ምክንያት ተበትኗልና ይቅርታ ጠያቂ መሆን ደግሞ ትልቅ ትልቅ አዋቂነት ነው አጉል መጃጃልና አላዋቂነት እኔ እበልጣለሁ ማለት ስለሆነ አሁንም የዚህን ሰዎች ታሪክ ያነበባችሁ ሙሉውንም ባያልቅ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰበት ራሱ የተነካው ነው የሚያውቀውና ሳይረፍድባችሁ ይቅርታ ጠይቃችሁ ኑሯችሁን ወደ ነበረበት መልሱት ትልቁና ዋነኛው ተጐጂ ለትዳር መፍረስ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ እናንተ ወንዶች ናችሁና ይልቁንም ለትዳራችሁ ክብር ስጡ ሴቶችም ትዳሯችሁን አክብሩ በተረፈ ዳኒ ለአንተ እግዚአብሄር ያድልህ ምናልባትም ብዙ ሰዎች ከጸብ በኋላ ከቤተሰባቸው ጋር በገቡት ቃለ መሐላ ማለትም አልፈልግም ትዳሬን ካሉ በኋላ ወደ ራሳቸው ሲመለሱ ዙሪያው ገደል ስለሚሆንባቸው እፍረትም ስለሚይዛቸው ከአፈርኩ አይመልሰኝ ለሚሉ ትምህርት ሊሆናቸው ስለሚችል እንደነዚህ ዓይነት ጽሁፎች ትልቅ ትምህርት ሊሰጡ ስለሚችሉ በዚሁ ቀጥል

  ReplyDelete
 15. I think the husband came from abroad by force. If he doesn’t like work with his previous wife, she will put him in jail until he die or as she said before she will kill him after she get all information. At the movement he has many supporters in the world especially in England. In addition that the entire world has been demonstrated to bring him back. She has been hearing many things from his supporter. I think if he agree to married her back she will keep him as a free man otherwise he will die soon. Everything has been on his choice because she is in love so she wants married him back. Most people think, he doesn’t want married her back because he doesn’t agree with her leadership. He likes unity to change the country but she likes separation to stay on her leadership until she dies. Most of his people like his idea but she has power to kill everybody. He knows that she is rude when somebody brings new idea but he prefers to die for his people. I hope we will hear good news on the next chapter.

  ReplyDelete
 16. degnet degso mablat new endie balebiti ena eni bezih entalalen mela belun

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንኩን በቁማችን ስንሞትም መደገስ እንዳለበት ተምረናላ! ቀስ አርገሽ አስረጂው ፡ ታንገት ከረባት ቂጥ ባዶ የሆነ ሕይወታችን መከራችንን አበዛው፡፡

   Delete
 17. Ehhhhh, Ere tew Dani yelibachine eyenegerk atasdengten. God bless you Dani you always have a good view on life. long life Dani.

  ReplyDelete
 18. weeeyguuuuud!! weynedoooo!! dn.Daneal Fetari tdarehn ybarkeleh.

  ReplyDelete
 19. Selam wondime who gave the first comment.
  You can visit www.ethiopianorthodox.org to get all kinds of books.

  ReplyDelete
 20. It great and insightful story but where is the part two of it, just waiting. One of the reasons I buy Addis Gudai is your article.

  ReplyDelete
 21. ለነገሩማ በዝምታ አድገን እንዴት መነጋገር እንልመድ ብለክ ነው? በክፍል ሁለት እንዴት የሚለውን አብረን ብናይጥ ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 22. andandochachen yemensfewen enquan yemnawk aymesleghm englsh language aweken belen bankebater teru new dani leant long live

  ReplyDelete
 23. Thank you Diyakon you are always precious I have no word other than that appreciate that this issue is my family,my friends etc.

  ReplyDelete
 24. Dani you are right. you helped me to see my destiny b/c what you wrote is a copy of life i am leading. we just celeberate the weeding ceremony but still not married.

  ReplyDelete
 25. እውን ይህ ታሪክ ክፍል ሁለት ያስፈልገዋል?
  ይታረቁ? ቆንጨራ ይማዘዙ? ብጤዎቻቸውን አግብተው ፡ እህትና ወንድም ይሁኑ? ወይስ ሁላችንም ከክፍል አንድ ተምረን ፡ ፍጻሜውን በተግባር እንጻፍ?

  ReplyDelete
 26. menew baletariku zegyehben yanten mecheresha lemawek kefetegn gugut lay negh ebakehen tolo aswekegn

  ReplyDelete
 27. ምነው መጨረሻህን አዘገየህብን በጣም ነው ለማወቅ የጓጓሁት ስለዚህ እባክህን ጻፍልንና እኛም እንደሰት ጥሩ ዜናም እንደምታሰማን ባለሙሉ ተስፋ ነን

  ReplyDelete