Wednesday, July 2, 2014

ድኻው ምን አረገ

ሰሞኑን ከአንድ ሰው ‹የማጭበርበር› ነገር ጋር በተያያዝ ከዚህም ከዚያም አስተያየት ይሰጣል፡፡ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃንም ትኩረታቸውን በሰውዬው ላይ አድርገው እንዴት እንዲህ ሊያደርግ ቻለ? ለምን እንዲህ አደረገ? ምን ነክቶት ነው? እያሉ ጉዳዩን ከማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ከሥነ ልቡና፣ ከእምነትና ከባሕል አንጻር እየተነተኑ ይገኛሉ፡፡
እኔ ግን ይህን ጉዳይ ስከታተል ትዝ የሚለኝ አንድ የሀገራችን ተረት ነው፡፡ ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን ዕቃ ይዞ ላጥ አለ፡፡ መንገድ ላይ ያዩት ሰዎች የሚያውቁትን ዕቃ አንድ ሰው ይዞ ሲሸመጥጥ በማየታቸው ይጠራጠሩና ያስቆሙታል፡፡ ፖሊስም በነገሩ ይገባበታል፡፡ ሰውም ከዚህም ከዚያም ይወርድበታል፡፡


ግርግሩ በዚህ መልክ እየቀጠለ ዕቃቸው የተሰረቀባቸው ሰዎች ኡኡ እያሉ ይደርሳሉ፡፡ ሲደርሱም የቤት ዕቃቸው በአንድ በማያውቁት ሰው ትከሻ ላይ ያገኛሉ፡፡ ግርግሩን ሰንጥቀው ይገቡና ‹‹ሞላጫ ሌባ›› እያሉ ሌባውን በጥፊ ሲመቱት ሌባው ተናድዶ ዕቃውን ያወርድና ጥፊውን በጥፊ ይመልሳል፡፡ ፖሊስ በድርጊቱ ተገርሞ ከዚያ ሁሉ ሰው ይልቅ ለባለቤቶቹ ጥፊ ለምን መልስ እንደሰጠ ሲጠይቀው ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ›› አለ ይባላል፡፡
የሰሞኑ ሁኔታም ይህን ነገር እንድናየው የሚያደርግ ነው፡፡ ለመጭበርበርና ለመታለል የሚችል አሠራር፣ አካሄድና አፈጻጸም የዘረጋነው እኛው ነን፡፡ ነገሮችን በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመርኩዘን ከመወሰን ይልቅ በሚወራ ወሬ፣ በሚገነባ ገጽታና ከሚዲያ በምንሰማው ነገር ላይ ብቻ የመመራትን አሠራር ያሰፈንነው እኛው ነን፡፡ ዛሬ ቀን ጥሎት የተጋለጠው ሰው ላይ በወደቀ ዛፍ ላይ የሚበዛውን ምሣር ሁሉ እናዘንብበታለን እንጂ ሌሎች ወደፊት እንዳይከሰቱ የሚያደርግ አደረጃጀት፣ አሠራርና አስተሳሰብ ግን አልዘረጋንም፡፡  
እንዲያውም የዚህን ሰው በዚህ መልኩ መምጣት ለሀገራችን ተቋማትና ኃላፊዎች ‹በረከተ መርገም› የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ‹ዓመት ባል ካልመጣ ሁሉ ሴት፣ ክረምት ካልመጣ ሁሉ ቤት› የሚባል አባባል አለ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ባይኖሩ የኃላፊዎቻችንን፣የምሁሮቻችንንና የመሥሪያ ቤቶቻችንን የተዝረከረከ አሠራር እንድናይ ማን ያደርገን ነበር፡፡ እዚህ ሀገር ምን ዓይነት ሰዎች ምን ዓይነት ቦታ እንደሚይዙ አሳይቶናል፤ ሴትዮዋ ‹አፍ ያለው ያግባሽ ከብት ያለው› ስትባል ‹‹አፍ ያለው ያግባኝ፣ አፍ ያለው ከብቱን ያመጣዋልና›› ያለችው እውነቷን ነው እንድንል አስችሎናል፡፡ አፍ ካለ፣ መናገር ከተቻለ፣ መስጠት ከተቻለ፣ እዚህ ሀገር ውስጥ ዕድሉም መንገዱም ወለል ብሎ እንደሚከፈት አይተናል፡፡ ሚዲያዎቻችንም የማጣረት፣ የመመርመርና ከግራ ቀኝ የማየት ዐቅማቸው የት ድረስ እንደሆነ አሳይቶናል፡፡ ‹ማን ምን አለ› እንጂ ‹ያለው ልክ ነው ወይ?› ብሎ ለማረጋገጥ ጥቂት እርምጃዎች መሄድ የሚችሉ ሚዲያዎች እንደዋልያ ‹ብርቅዬ ድንቅየ›› መሆናቸውን ተምረንበታል፡፡
እንዲህ ያለ ሰውማ ይምጣ፡፡ እዚህ ሀገር ድፍረት እንጂ ዕውቀት፣ ትውውቅ እንጂ ዕውውቅ፣ ዘመድ እንጂ ችሎታ፣ ቅልጥፍና እንጂ ጉብዝና ዋጋ እንደሌላቸው እናይ ዘንድ፡፡
እኔን ምን አገባኝ የሚሉት አጉል ወግ
እርሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ
የሚል ግጥም ልጽፍ ተነሣሁኝና
ምን አገባኝ ብዬ ተውኩት እንደገና
ብሎ የጻፈውን ባለ ቅኔ እውነት እንድናየው አድርጎናልና እንዲህ ያለ ሰውማ ይኑር፡፡
ምሁሮቻችን ያላስተማሩት ተማሪ ከፊታቸው ቆሞ አስተምራችሁኛል ሲላቸው፣ ተማሪዎቹ ብቃት አንሷችሁ እኔን ማየት ሳትችሉ ቀርታችሁ ነው እንጂ አብሬያችሁ ተምሬ ነበር ሲላቸው፣ የዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደሮች ረስታችሁኝ ነው እንጂ ሸልማችሁኝ ነበር ሲላቸው፣ በቅቼ ተሠውሬ ነው እንጂ አብሬያችሁኮ ነው የምሠራው ሲላቸው፤ የቤተ መንግሥት ሰዎች በእሳት ሠረገላ ገብቼ አላያችሁኝም እንጂ ከአቶ መለስ ጋር አብሬ ነበርኩኮ ሲላቸው ዝም ያሉት ‹ዝምታ ወርቅ ነው›› ብለው አይደል፡፡ የዝምታችን ነገር የት ድረስ እንደሚደርስ፣ ስሕተትን የመቻል ዐቅማችን የት ድረስ እንደሆነ፣ የተበላሸን ነገር የመሸከም ችሎታችን ምን ያህል እንዳደገ፣ ውሸትን የመቀበል ብቃታችን ጨምሮ ጨምሮ እዚህ መድረሱን በሚገባ አሳይቶናል፡፡ ኑርልን ባክህ፡፡
ባለፈው ጊዜ በዓለም ዋንጫ ጉዟችን አንድ ተጨዋች ሁለት ቢጫ ካየ በኋላ እንደገና ተሰልፎ በመጨዋቱ ፊፋ ቀጣን፡፡ ይህ ቅጣት ብዙ ሰዎችን አሳዘነ፡፡ ያ ቅጣት ግን ብናውቅበት ኖሮ በረከተ መርገም ነበር፡፡ የፌዴሬሽናችንን አሠራር ቁልጭ አድርጎ በአደባባይ ያሳየን፡፡ እንኳንም ተጨዋቹ ተቀጣ፣ እንኳን ፌዴሬሽኑም ተዝረከረከ፡፡ ያንን ዝርክርክነት እንዴት አድርገን እናየው ነበር፡፡ ከዚያ በፊትምኮ ከዚያ የባሱ ዝርክርክ አሠራሮች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በድብብቁ አሠራራችን ምክንያት ‹ሽል ሆነው ከመግፋት ይልቅ ቂጣ ሆነው እየጠፉ› ሳናያቸው ኖርን፡፡ ያንን አጋጣሚ ማለፍ ግን አልተቻለም፡፡ ዓለም ያወቀው፣ ዓለም ሊያውቀውም ግድ የሚለው ጥፋት ነበረና፡፡
የሚገርመው ነገር እንዲያ ዓይነት አገርን አንገት ያስደፋን ጥፋት ሲሆን እንዳይፈጸም፣ ካልሆነም እንዲታረም የሚያደርግ አሠራር ባለመዘርጋታችንና አመለካከታችንንም ባለማስተካከላችን በሴቶች እግር ኳስ ላይ ተደገመና የፓስፖርት መጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባትን ተጨዋች ለማሰለፍ ሜዳ ውስጥ እስከማስገባት ደረስን፡፡ ይኼኛውን ዝርክርክነት ለማወቅ የቻልነው ለማወቅና ለመታወቅ የግድ የሚለው ዓለም አቀፋዊ አሠራር በመኖሩ የተነሣ ነው፡፡
ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ(ገሞራው) ‹በረከተ መርገም› በሚለው ግጥሙ ላይ ‹ድኻው ምን አረገ ሊቆቹን ነው መርገም› ይላል፡፡ አሁን መረገም ያለበት ተቋማዊ አሠራራችን፣ አስተሳሰባችን፣ የመረጃ አያያዛችን፣ ነገሮችን በንሥር ዓይን ከማየት ይልቅ በተወራውና በተባለው ብቻ መመራታችን፣ የዘመድ አዝማድ አካሄዳችን፣ የተጠጋጋውን ሁሉ የሚያምነው አሠራራችን ነው፡፡ መረገም ያለበት ለመታለል፣ ለመሞኘት፣ ለመሸወድ፣ ለመጭበርበር እጅግ ቀላልና እጅግም ዝግጁ የሆነው ቢሮክራሲያችን ነው፡፡
ይህን መሰል ሰዎች መምጣታቸው በሀገራችን እጅግ ተወዳጁ ምግብ ‹ምላስና ሰንበር› መሆኑን እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ ምላስና ሰንበር ካለህ የፈለግከውን ተናገር - ትሰማለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ የፈለግከውን ነኝ በል - ትታመናለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ የፈለግከው ቦታ ደርሻለሁ በል - ትደነቃለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ እንደ ኢዲ አሚን ሁሉንም መዓርግ ለራስህ ስጥ - ትሞገሳለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ ዐዋቄ ኩሉ ነኝ በል - ተከታይ ታገኛለህ፡፡ የዚህን መሰል ሰዎች መነሣት ይህንን አሳይቶናል፡፡ እንኳንም ተነሣችሁ፡፡
ደግሞስ እነርሱ ባይኖሩ ይህንን መሰሉን የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የተወካዮች ምክር ቤት፣ ዋናው ኦዲተር፣ ያልደረሰባቸውን የተበላሹ አሠራሮች እንዴት እናያቸው ነበር? ኧረ እንኳን ኖራችሁ፤ ለኛ በረከተ መርገም ናችሁ፡፡ 
 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

45 comments:

 1. SERIKO KEMASEB EJIN MESEBSEB YILAL YAGERE SEW TESERKO KEMASEBIM DEJIN MEZIGAT YETESHAL NEW AND TERET TI ALEGN SETIYEW AND YEMITAMINAT WUSHA ALECHAT ENA BETUA HULU KIFT NEW TADIYA SETIYEWA ZEWER SITIL WUSHAWA YEFELEGECHIWUN TADERGINZ TEMELISA ENDECHEWA BOTAWA LAY TIGEGNALECH HUNETA YASASEBAT SETIYO WUSHAWAN TEYEKCHAT " MINEW ANCHI WUSHA YALANCHI EZIH BET YEMIGEBA YELEM GIN YANORKUTIN NEGER WETICHE SIMELES ALAGEGNEWUM" WUSHAWAM MELESECH "YEKEDNSHIWUN NEKICHALEHU YALKEDENSHIWUNS TICHALEHU" ALECHAT YIBALALA

  ReplyDelete
 2. "እንዲህ ያለ ሰውማ ይምጣ፡፡ እዚህ ሀገር ድፍረት እንጂ ዕውቀት፣ ትውውቅ እንጂ ዕውውቅ፣ ዘመድ እንጂ ችሎታ፣ ቅልጥፍና እንጂ ጉብዝና ዋጋ እንደሌላቸው እናይ ዘንድ"

  ReplyDelete
 3. ‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ››
  ለኔ ይህች ሃገር የኔ ባይ የሌላት ጠፍ መሬት ሆና ነዉ የምትታየኝ ሌባና አጭርባሪ በሞላባት አስመሳዮችና ሳይማሩ ጠምጣሚዎች በተንሰራፉባትና በማን አለብኝ በሚኖሩባት ሃገር የሳሙኤል ነገር እንደ ታምር መወራቱ የማኅበረሰቡን ሞራል ልሽቀት ያሳያል እንደኔ ከሳሙኤል ይልቅ በየት/ት ቤታችን በየቢሯችን ያሉ ትልቅ ኃላፊነት ተቀብለዉ የሚኖሩ ሳሙኤሎች ሊሳስቡን ይገባል ብየ አስባለሁ እኔ በተማረኩበት የኒቨርስቲ አንድ ከህንድ የመጣ መምህር ነበረን ይህ ሰዉ ሲያስተምር በጣም ያስደነግጣል በዘርፉ ልዩ ስልጠና ያለዉ ቀርቶ ትምህርቱን እንደ ቤዚክ ኮርስ እንኳን የተመረዉ አይመስልም ስለዚህም ደግመን ደጋግመን ከዩኒቨርስቲዉ ኃላፊዎች ጋር ተነጋገርን የተሰጠን መልስ ግን ያመጣዉ ወረቀት በዘርፉ ልዩ ስልጠና እንዳለዉ ያሳያል አርፋችሁ ተማሩ ነበር ትንሽ ቆይቶ ግን ሌላ ትምህርት ያስተምረን የነበረ መምህር ለቀቀና ክፍተት ተፈጠረ እናም ያ ስፔሻላይዝድ አድርጌበታለሁ የሚለዉን የትምህርት አይነት ማስተማር አይችልም እያልን የከሰስነዉ መምህር ችግር የለም እኔ ላስተምርላችሁ እችላለሁ አለ እነርሱም ሌላኛዉን የት/ት አይነትም እንዲያስተምር ፈቀዱለትና ቀለደብን - አሁን ለዚህ ተጠያቂዉ ድህነት ከህንድ አሰድዳ የመጣችዉ ባዕድ ወይስ ይህች ሃገር ከሌላት ቆርሳ ያስተማረቻቸዉ የሾመቻቸዉ ምሁራን
  እንዲያዉ ይህን ሰዉየ ለምሳሌ አነሳሁት እንጂ በየዘርፉ ከዉጭ ሃገር የሚመጡት ባለሞያዎች የርሱ አምሳዮች ናችዉ

  ReplyDelete
 4. yibel xhuf new dani ejochihn ybarkilin

  ReplyDelete
 5. እኔ እምለው ዶ/ር ፣ ኢንጅነር ሳሙኤል ዘ/ሚካኤል ምነው የበፊት ስራው ይሻለው ነበር ማክሰኞ ማክሰኞ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በማታው ኘሮግራም ወንጌል ያስተምር የነበረው ፡፡ግን ምን አለ መሠለህ ዳኒ "ያደቆነ ሠይጣን ሳያቀስስ አይተውም " ይባል የለ ሁልጊዜ ልቡ ላይ ያለውን ማድረጉ የሚገርም አይደለም ምኞት በራሱ የሃጢያት ስር መሆኑን እመድረክ ላይ ሆኖ ሲሰብክ የሰማው የነበረ ቢኖር ያስታውስ ነበር ምኞታችን ሁልግዚ ከመስመር ያወጣናል ምናለበት መሆን ያሰበውን መሆን ከተማረ ይችላል ግን ምንአለ መሰለህ ልጆች ሲያድጉ አባታቸውን እና እናታቸውን መስለው ነው የሚያድጉት እሱ ደግሞ እያየ ያደገው አባቱን ( ውሸታም የሆነው የሀገር መሪውን ነው ) ስለዚህ ቢያስብ አይገርምም ውሸታም መሪ ውሸታም ልጅ ይዞ ነው የሚሄደው የሚገርመው ግን በሂደበት ሁሉ ያፍዝ ያደንግዝ ይዞ እንደሆነ ነው እንጂ ምን ማለት ነው አሁን ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ሚዲያውም ዘራፍ የሰማው ሁሉ ዘራፍ በፊት ቀረ ዘራፍ ማለት እንደውም አበጀህ መባል ነበረበት ፡፡

  ReplyDelete
 6. ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ››

  ReplyDelete
 7. Dani, Tebarek !

  ReplyDelete
 8. Our medias are not a such reliable especially those medias under the supervision and fiscal allocation of the government. if the medias (ERTA) appreciate and recognize the chatting of Samual where is the mistake of guys?

  ReplyDelete
 9. Dani yezan hulu bado chnqlat wtweta afer abelahew.Hegerachn mn aynet sewochn endaferach asayehne.Abo amlak kezih yebelete mastewal yadlh.

  ReplyDelete
 10. ‹‹አውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አቤት አይልም›› ይላሉ አባቶቻች/እናቶቻችን ዲ.ዳንኤል ለአገራችን መሪዎች የአሰራር ግድፈቶችን እያወቁ የተውት ይመስለኛል ምክንያቱን ለነሱ ሌብነት እንዲመቻቸው ማለት ነው፤ ብዙ አይነት ሌብነቶች አሉና የሂሳብ አያያዝ፣የቅጥር፣የዝውውር አረ ምን ቅጡ ብቻ ለነሱ ሲሆን አይታያቸውም ክፍት ባገኘው ለገባው ግን ስርቆት /ሌባ ነው ብቻ ፍርድ ከፈጣሪ እንጠብቅ ቢዘገይም የሚቀድመው የለምና
  ማረጉ ይቅርበትና የሳሙኤል ግን እንተደባለውም እንኳን መጣ ነው የሚያስብለው ህዝቡ እንዲህ በምክንያት በውስጡ ያለውን ፍጅት/ረመጥ/ቁጭት ተነፈሰበት/ተናገረበት
  ዲ.ዳንኤል እግዚሐብሄር ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 11. great view!!!!!

  ReplyDelete
 12. There are many no where but in our home, too.

  ReplyDelete
 13. እንዲህ ያለ ሰውማ ይምጣ፡፡ እዚህ ሀገር ድፍረት እንጂ ዕውቀት፣ ትውውቅ እንጂ ዕውውቅ፣ ዘመድ እንጂ ችሎታ፣ ቅልጥፍና እንጂ ጉብዝና ዋጋ እንደሌላቸው እናይ ዘንድ"

  ግዜክስ

  ReplyDelete
 14. amlake kidusan msitewal yisten

  ReplyDelete
 15. leferd yekereben lemagenazeb yeraqen egna woyolen!!??

  ReplyDelete
 16. ዳኒ ላመሰግንህ እወዳለው ከሁሉም ሚዲያ በተሸለ እይታ ጠቅሰከዋል፡፡እኛ ሀገር የአንድ ሰው ስም ሲገን አብረን ሆዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎዎ እንላለን በሆነ አጋጣሚ ትንሽ ከተንገዳገደ ግን የተገላቢጦሽ ይሆናል፡፡እኛ ይህንን ግለሰብ በየስብሰባችን በክብር እንግድነት የጠራነው፣ በሬድዬ ፕሮግራም ላይ አድማጭን ሰርፕራይዝ ለማድረግ የጋበዝነው፣ለዩኒቨርስቲ ምሁራኖቻችን የአቅም ማሳደጊያ ስልጠና እንዲሰጥ በክብር የጋበዝነውን፣ ባለስልጣኖች ሃሳብ እንዲያካፍላቸው የጋበዙትን፣ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ዳኝነት እንዲሰጥ የመረጥነውን ግለሰብ ዛሬ የአለማችን ብቸኛው አጭበርባሪ አድርገን በየሚዲያው አንድን ተራ ግለሰብ ማውገዛችን ምን ያክል ማህበራዊ ችግር እንዳለብን የማህበረሰብ ምሁራኖች ቢያብራሩ መልካም ይመስለኛል፡፡የዚህን ግለሰብ ጉዳይ ትተን አሰራሮቻችንን ብንፈትሽ መልካም ይሆናል ፡፡

  ReplyDelete
 17. abejeh belut........

  ReplyDelete
 18. ዳንየ፤ ይሕ አልፎ ሐቅ ፤ሐሰትን አሸንፎ ፤ዘመን ታሪክ ተቀይሮ ፤ ነገር በነበር ተተክቶ ለማየት እንድንበቃ አድሎ ለማያውቅ አምላክ ኦንጸልይ።እግዚአብሔር ከአንተጋር ይሑን።

  ReplyDelete
 19. አሁን መረገም ያለበት ተቋማዊ አሠራራችን፣ አስተሳሰባችን፣ የመረጃ አያያዛችን፣ ነገሮችን በንሥር ዓይን ከማየት ይልቅ በተወራውና በተባለው ብቻ መመራታችን፣ የዘመድ አዝማድ አካሄዳችን፣ የተጠጋጋውን ሁሉ የሚያምነው አሠራራችን ነው፡፡ መረገም ያለበት ለመታለል፣ ለመሞኘት፣ ለመሸወድ፣ ለመጭበርበር እጅግ ቀላልና እጅግም ዝግጁ የሆነው ቢሮክራሲያችን ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. ይህን ጉዳይ ግለሰቡ ብቻውን የተወነው ነው ብሎ ለመቀበል ያስቸግራል። የቀድሞው ፕሬዚደንት ግርማ አንዳሉት ግለሰቡ ቤተመንግስት መግባት ከጀመረ አራት ወይም አምስት ዓመት ገደማ ይሆነዋል። ቤተመንግስት ድረስ ሲገባ ቅጥ ባጣው ስለላቸው ሕዝቡን መተንፈሻ መላወሻ የሚያሳጡት ደሕንነቶች ሳያውቁ ነው ለማለት ይከብዳል። ሁለተኛ ሁሉም ዩንቨርስቲዎች በሕጋቸው ላይ አንድ ባለሙያ የተባባሪ ፕሮፌሰር ማዕረግ ለማግኘት መጀመሪያ ረዳት ፕሮፌሰር መሆን በተጨማሪም አራት ዓመታት ማስተማር አና ቢያንስ ሁለት የምርምር ስራዎችን ማሳተም አንደሚያስፈልገው በግልጽ ተቀምጧል። ይህን ሕግ ተላልፈው የተባለውን ማዕረግ ሊሰጡት የሚችሉት ከላይ የሚያስገድድ አካል ሲኖር ብቻ መሆኑን መገመት አያዳግትም። በዛ ላይ የዩንቨርስቲዎች ኃላፊዎች በሙሉ በመንግሥት ታማኝነት የተመደቡ አንጂ በሙያ ብቃትና በልምዳቸው አለመሆኑን ስንደምርበት ነገሩ የበለጠ ግልጽ ይሆናል።

  ስለመገናኛ ብዙሃን ችግር ብዙ ተብሏል ነገር ግን ትልቁ ትምህርት አንድን ሰው ቃለመጠይቅ ከማድረጋቸው በፊት የራሳቸውን የቤት ሥራ መስራት አንደሚገባቸው ነው። ይህን ቢያደርጉ ኖሮ በቀላሉ የመረጃ መረብ ላይ ስሙን በመፈለግ የሚለው ማንነት ባዶ አንደሆነ ማወቅ በቻሉ ነበር። ለምሳሌ የፌስ ቡክ ገጹ ላይ የሚጽፋቸው እንግልዘኛዎች የሃርቫርድ ምሩቅ ቀርቶ ከማንኛውም የአሜሪካ ዩንቨርስቲ የተመረቀ ሰው አንደዛ አንደማይጽፍ ያሳብቃሉ። በአሜሪካ አና አውስትራሊያ ዩንቨርስቲዎች ለመማር የአንግሊዝኛ ፈተና ማለፍ የመጀመሪያው መስፈርት መሆኑን ልብ ይሏል። ተማርኩ በሚልባቸው ዩንቨርስቲዎች ድረገጽ ላይ ስሙ አለመገኘቱም ሌላ ፍንጭ ሊሆን ይችል ነበር። በርግጥ ሁሉም ዩንቨርስቲዎች ይህን ላያደርጉ ይችላሉ የሚል ሙግት ሊነሳ ይችል ይሆናል ነገር ግን የተባሉትን ተቁአማት ትልቅነት ከግምት ስናስገባ አንደዚያ ከሚያአደርጉት ውስጥ አንድንመድባቸው አንገደዳለን። አንድም የታተመ የምርምር ሥራ አለመኖሩም አንደዚሁ ። ሁአይት ሃውስ የላቀ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች ፕሬዚደንቱ ዘንድ ሲያቀርብ ከፍተኛ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አንደሚሰጠው የታወቀ ሆኖ ሳለ አንዴት በመረጃ መረብ ፍለጋ ሊያገኙት አልቻሉም? አፍሪካ ቪዥናርስ የሚለውም ተቁአም ድረገፅ ከፊት ገጹ ባላፈ ወደየትም የሚያገናኝ ነገር አለመኖሩም ትልቅ ጥያቄ ማጫር ነበረበት። አዛ ላይ የተጻፈውም የወረደ አንግሊዘኛ ሌል ፍንጭ መሆን ይችል ነበር።

  ጋዜጠኛ ተብዬዎች ሆይ ማንም ይሁን ማንም ከማናገራችሁ በፊት ስለግለሰቡ የተቻላችሁን ያህል ፍተሻ አድርጉ ያኔ ሰውየው የሚፈልገውን ሳይሆን አንናንተ አንዲናገር የምትፈልጉትን ነገር መጠየቅ አና ማናገር ትችላላችሁ ።

  ReplyDelete
 21. ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ሰዎች ፡ ሥልጣን ላይ ያልተቀመጡበት መስሪያ ቤት አለ ብሎ የሚያምን ካለ ጻድቅ ነው፡

  ሟቹ ጠ/ምኒስቴር በአንድ ወቅት ሲናገሩ ፡
  ዋናው አስፈላጊ የባለስልጣናት የምርጫ መስፈርት "ታማኝነት" እንደሆነ አስገንዝበዋል።
  እኛ አገር ታማኝነት ጄኔራል ያረጋል፡፡

  ReplyDelete
 22. AhunimZim.............!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያልተነፈሰ ሊፈነዳ ይችላልና ፡ ጠነቀቅ!

   Delete
  2. ተወው ዲ. ዳንኤል ነገሩ ጌታዋን የተማመነች በግ …………………. ይመስለኛል

   Delete
 23. ዳኒ ጥያቄ አለኝ " የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን " የሚባል ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ነው?
  ካለ የሥራ ድርሻው "ጉቦ የማይበላውን" ፈልጎ መቅጣት መሆን አለበት!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተናግረህ ሞተሃል ጅል

   Delete
 24. ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ››

  ReplyDelete
 25. Dr. Eng. Samuel Zemichael I rally appreciate U.
  God bless you!

  ReplyDelete
 26. እባካችሁ ዘመዶቼ አንዳችን አንኳን ምን አለ ልቦና ይሰጠው ለማለት አምላክ ቢረዳን፡፡ በእውነቱ የሳሙኤል እጅግ በጣም በዛ እንጂ እኛስ ቢሆን እስኪ ስለራሳችን አብዝተን እናስብ፡፡ ይሄ የሀገራችንን ጉድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አሪፍ ተውኔት ነው ፊልም የሚመስል፡፡ አሰራራችንን እንመርምር፡፡ለወንድማችን ልቦና ይሰጠው!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አምላክ እንደ አበሻ ልመና የሰለቸው ነገር ይኖር ይሆን?

   Delete
 27. This guy is very intelligent than weyane group!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውሮች አገር አንድ ዓይና ብርቅ ነው!

   Delete
 28. ወየው ጉድ አንዳንዴ ግርም ይለኛል አንዳንድ ወጣ ያለ ነገር አይተህ ብትናገር ያንተን ሃሳብ እርጥብ መሃል እንደተገኘች ደረቅ መሬት ረጋግጠው ያጠፉብሃል ወይም እብዶች መሃል አንተ ብትገኝ እብድ አንተ እንጂ እነሱ ያልሆኑ ሁሉ ሊመስልህ ይችላል እናም ዝም ማለት በማትችልበት ቦታ ብትናገር ወይም ሃሳብ ባታቀርብ ሰው ሁሉ እንደጉድ ሲያይህ እንዴ ልክ አይደለሁም እንዴ ትላለህ እርግጠኛ ነኝ እንዲህ ያለ ነገር ብዙ ጊዜ እንዳጋጠመህ ዲያቆን ዳኒ የአገልግሎት ዘመንህን እግዚአብሔር ይባርክልህ

  ReplyDelete
 29. Hello Daniel
  can you please tell me were can I find this book(ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ(ገሞራው) ‹በረከተ መርገም› )
  regards

  ReplyDelete
 30. ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን ዕቃ ይዞ ላጥ አለ፡፡ መንገድ ላይ ያዩት ሰዎች የሚያውቁትን ዕቃ አንድ ሰው ይዞ ሲሸመጥጥ በማየታቸው ይጠራጠሩና ያስቆሙታል፡፡ ፖሊስም በነገሩ ይገባበታል፡፡ ሰውም ከዚህም ከዚያም ይወርድበታል፡፡


  ግርግሩ በዚህ መልክ እየቀጠለ ዕቃቸው የተሰረቀባቸው ሰዎች ኡኡ እያሉ ይደርሳሉ፡፡ ሲደርሱም የቤት ዕቃቸው በአንድ በማያውቁት ሰው ትከሻ ላይ ያገኛሉ፡፡ ግርግሩን ሰንጥቀው ይገቡና ‹‹ሞላጫ ሌባ›› እያሉ ሌባውን በጥፊ ሲመቱት ሌባው ተናድዶ ዕቃውን ያወርድና ጥፊውን በጥፊ ይመልሳል፡፡ ፖሊስ በድርጊቱ ተገርሞ ከዚያ ሁሉ ሰው ይልቅ ለባለቤቶቹ ጥፊ ለምን መልስ እንደሰጠ ሲጠይቀው ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ›› አለ ይባላል፡፡

  ReplyDelete
 31. 10qqqq! mihur yetebale zirkrik hulu gudu wota. the guy did great b/c now a days this is the only way to live in this country.

  ReplyDelete
 32. beaserar hulum siletegna hulun yemiyasawuk sitet honual

  ReplyDelete
 33. እንዲህ ያለ ሰውማ ይምጣ፡፡ እዚህ ሀገር ድፍረት እንጂ ዕውቀት፣ ትውውቅ እንጂ ዕውውቅ፣ ዘመድ እንጂ ችሎታ፣ ቅልጥፍና እንጂ ጉብዝና ዋጋ እንደሌላቸው እናይ ዘንድ፡፡

  ReplyDelete
 34. Certificate yemiyasfeligew, laltaweke chilota misikir ena maregagecha endihon new. Yemibalews "yemisikir wereket" aydel. Samuel ye maneqaqat chilotaw betegbar tayto ketewededelet ena yemaneqaqat tegbarun gib kaderese, wereqet baynorew minchigr alew? Engdiama Paulos Gnogno 4th grade bilen lanqebelew new? Samuel eko engineering alastemarem. Ph. D. lesim madmekia ena langet masgebia metekemu..."lam balwalebet" hono awaredew enji. Sami yeleyelet "washo" new, gin degmo arif tenagari ena aneqaqi (motivational speaker) new, yaw ende cadre malet new. Yagaletutm, legazetegna yesetut leloch kegonu yeneberu tekenakagnochu nachew. Siketatelut bizu koytewal. Maneqaqia nigigiru chigir yelebetm. Bewashonetu gin afriletalehu. Wishetu egir awtito yihedal kerbo lesemaw. 1 Billion birr alegn bilo be Sheger F.M. bezihu amet Arb qen mishit be Zena semichewalehu. Lelam yaltenegere bizu wushet alew eko, rasu sami. Bicha metew new. Kezih yeminimarew, Yemyawq yastemr. Af silale bicha aninager. ANWASH.

  ReplyDelete
 35. Deacon Daniel Kibret, i would like to appreciate your point of view and thank you for putting it out there.

  This story is an indication of how far up we Ethiopians still have to go on the ladder of civilization. In a civilized society incidents like this rarely happen, so we need to change. Guess what? Change begins from oneself and the firsr step is to be a responsible citizen, a quality Mr. Samuel Zemichael lacked.

  ReplyDelete
 36. በጣም ጎበዝ ነው ሰሚ ሰራሸልት ይህን የኢትዮጵያን ህዝብ ጀዝባ ሁሉ አሁን ከልብ አይሠራም የምንግሰት ሠራተኞች ሁሉም ሌባ ነው ይህም ሰንሳቸው ነው ሰው አለባበሱ ከማረ ንግግር አፍን ከፍቶ ከተናገረ ይሰማል ብቻ ፓለቲካዊ ነገሮች አያንሳ እንጂ ሀሀሀ ሰራላችሁ ያገራችን ደከማ ጎን አለማጣራት ያልተማረ ይግደለኝ ይላሉ ጎበዝ ነው

  ReplyDelete