Saturday, July 26, 2014

ጳውሎስ ኞኞ (1926-1984)


አዘጋጅ፡- ደረጀ ትእዛዙ
ኅትመት፡- 2006 ዓም
የገጽ ብዛት፡- 308
ዋጋ፡- 84 ብር
ስለ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና የታሪክ ሰው ጳውሎስ ኞኞ ታሪክ፣ ሥራዎችና ሀገራዊ አስተዋጽዖ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ደረጀ የጳውሎስ ጎረቤት ነበረ፡፡ ያደገውም እነ ጳውሎስ ሠፈር ነው፡፡ የልጅነቱ ትዝታ ስለ ጳውሎስ እንዲያጠና እንዳደረገው ይነግረናል፡፡ የጳውሎስን ሥራዎችና ስለ እርሱ የተጻፉ መዛግብትን አገላብጦ፤ ዛሬም በሕይወት ለታሪክ ቆይተው ያገኛቸውን የቅርብ ሰዎቹን አናግሮ ዙሪያ መለስ የሆነ ሥራ አቅርቦልናል፡፡ 
የጳውሎስን ጉዞ ከትውልድ መንደሩ እስከ ተጓዘባቸው የዓለም ክፍሎች፣ ከትውልድ ሥፍራው ቁልቢ እስከ መቀበሪያው ቀራንዮ 
መድኃኔዓለም ደረጀ ስለ ጳውሎስ የሚመሰገንበትን ብቻ ሳይሆን የሚወቀስበትን፣ የሚደነቅበትን ብቻ ሳይሆን የሚነቀፍበትን፣ ብርታቱን ብቻ ሳይሆን ድክመቱንም እንድናየው አድርጎናል፡፡ ከጠባዩ እስከ ችሎታው፣ ከእምነቱ እስከ ፍልስፍናው፣ ከኩርፊያው እስከ ደግነቱ ያሳየናል፡፡ 
በጳውሎስ ኞኞ ታሪክ በኩል የኢትዮጵያን ፕሬስ ጉዞ፣ የነበሩትን ዋና ዋና ተዋናዮች፣ የነበረባቸውን ፈተና፣ አስተዳደራዊ፣ ፖለቲካዊና ፍልስፍናዊ ተግዳሮት፣ በየዘመናቱ የተነሡ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እንዴት ይጋደሉ እንደነበር፣ ከንጉሥ እስከ ሰካራም፣ ከአንባቢ እስከ አለቃ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ ያሳየናል፡፡
ጳውሎስ ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን ራሱን በራሱ ያስተማረ፣ ታሪካችንን ፈልፍሎ በራሳችን ቋንቋ ሊያቀርብልን የሞከረ፣ በሀገሪቱ በተከሰቱ ልዩ ልዩ ችግሮች ወቅት ወገቡን ታጥቆ ለወገኑ የለፋ፣ ከመንደሩ ማኅበራዊ ግንኙነት እስከ ብሔራዊ ችግሮች ድረስ፣ ከድርቅ እስከ ሶማሌ ጦርነት ድረስ ለሀገሩ የደከመ ክቡር ዜጋ መሆኑን መጽሐፉ ያሳየናል፡፡
ጳውሎስ የተማረው እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነው፡፡ ራሱን በራሱ አስተምሮ ግን ከሊቃውንቱ በላይ ለመሥራት ችሏል፡፡ መማርን ለደመወዝና ለግድግዳ የምረቃ ፎቶ ብቻ ለሚያደርጉ ሰዎች ጳውሎስ ታላቅ ማስተማሪያ ነው፡፡ የውጤት መንገዱ ፍላጎት፣ ጥረትና ያለ መታከት መሆኑን ጳውሎስ ያሳየናል፡፡ ዛሬ ብዙ ዕድሎች ተመቻችተውልን ጊዜውን በቀልድ ለምናሳልፍ ሰዎች ጳውሎስ መውቀሻ ነው፡፡
ወጣቶች የከተፋና የቶሎ ቶሎ ሥራዎች ላይ ተጠምደዋል እየተባለ በሚተችበት በዘህ ጊዜ ደረጀ ትችቱን ሐሰት አድርጎ ጊዜ የሚወስድ፣ ሰነድ ማገላበጥን የሚጠይቅ፣ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ አያሌ ደጅ መጥናቶችን የግድ የሚል ሥራ ይዞ መምጣቱ ያስመሰግነዋል፡፡
ጳውሎስ ኞኞን የምታውቁት ትዝታችሁን ይጭርላችኋል፡፡ የማታውቁት ታሪኩን አብራችሁ የነበራችሁ ያህል ያሳያችኋል፡፡ በዚያውም የአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ታሪክ የሀገሪቱ ታሪክ መሆኑን በሚገባ ያሳያችኋል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ‹‹ምናለ አንዳንዱ ሰው ዳግመኛ ቢፈጠር›› ያለው ሊሠራባቸው ከሚገቡት አንዱ ጳውሎስ ኞኞ መሆኑን መጽሐፉን ስታነቡ ታረጋግጣላችሁ፡፡ 
መልካም ንባብ፡፡

20 comments:

 1. ይህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ መጽሃፍ ነው። ዲን የዚህ ምርጥ ሰው ታሪክ መጻፉን በማብሰርህ ምስጋና ይገባሃል!

  ReplyDelete
 2. Thank u so much I have no words to say thank you to dereje pawlos gnogno one of the great Ethiopian who contribute a lot to readers . I born and raise in his area we close family I can wait to read the book I have got a lot of memory by the way I was class mate to dereje thanks again yonas from dallas tx usa

  ReplyDelete
 3. That is a good news .Thank you d.n

  ReplyDelete
 4. ጳውሎስ ኞኞ የተቀበረው ቀጨኔ መድኃአለም አይደለም ፤ ቀራንዮ መድኃዓለም ነው ፤ እድሜዬ አስር ሳለ በቤተክርስቲያኑ ሳለሁ ለጳውሎስ ኞኞ የመጣውን የሰው ብዛት እስከ አሁን ይገርመኛል… በቀራንዮ መድኃኒዓለም ዋናው ግቢ መቃብሩ በካህናት መግቢያ በኩል ይገኛል

  ReplyDelete
  Replies
  1. please read the article correctly before giving comment. Daniel didn't say KECENE MEDHANEALEM

   Delete
  2. ጳውሎስ ኞኞ የተቀበረው ቀጨኔ መድኃአለም አይደለም ፤ ቀራንዮ መድኃዓለም ነው
   መነጽር መግዛት ሳያስፈልግህ አይቀርም

   Delete
  3. ይችን ክርክር ጳውሎስ ሰምቷት ቢሆን ኖሮ!?

   Delete
 5. Dear brother Daniel,

  Thank you for citing us the overview of the book!

  But, I wonder why you are not stopping giving us quotes from songs and singers every time!!! Now Tilahun Gesese!

  You are referring us to take up fleshy/secular activities!!! Many christian people watching your outputs are feeling bad about it. please, please, please stop it!!!

  Thank you if you are hearing

  ReplyDelete
  Replies
  1. It doesn't matter where the quotes taken from, the only thing we should focus on is the message that the quotes talks about. dear anonymous, I the point is positive thinking.

   Delete
  2. ዲን አንብብልኝ አላለክ ፥ ካልተስማማህ አለማንበብ!

   የዘፋኙ ጥቅስ የረበሸው ጻዲቅ!
   ከአንተ ይልቅ ዘፋኙ ለፈጣሪ ቅርብ ይሆናል።

   Delete
 6. Please read attentively. The author said the funeral place is Keranio.

  ReplyDelete
 7. የጳውሎስን ጉዞ ከትውልድ መንደሩ እስከ ተጓዘባቸው የዓለም ክፍሎች፣ ከትውልድ ሥፍራው ቁልቢ እስከ መቀበሪያው ቀራንዮ
  መድኃኔዓለም

  ReplyDelete
 8. to And Adergen: you said the burial for Paulos is not Ketchene Medhanealem but Keranio. Was that mentioned in the book or you think Dn Daniel said Ketchene Medhanealem? The writing above said born in Kulebi and buried at Keranio. I am just observing. Didn't get the book yet.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የመጀመሪያ ፖስት ቀጨኔ ነው የሚለው ከዛ ተስተካክሏል…

   Delete
 9. seifemichael zeejereJuly 29, 2014 at 1:21 PM

  አንት ከዚህ በላይ የፃፍከው ሰው እባክህን እጅግ የጠበበ አስተያየት አትስጥ፡፡ ጥላሁንም ሆነ ሌሎች ዘፋኞች እግዚአብሔር በሚሰጣቸው የ አንድ ደቂቃ ጊዜ ምናልባትም እንደ ፌያታዊ ዘየማን አንተን ሁሉ ቀድመው መንግስተ ሰማያት ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በመጨረሻው ሰአት እባክህ በቀኝ አውለኝ ብለው ከእግዚአብሄር ሊታረቁ ይችላሉ፡፡ ብዙ ታላላቅ ሰዎች በዚህ አለም ሳሉ እጅግ ጠቃሚ ቃላት ለኛ ለቀረንው በሙሉ ሊያስተምር የሚችል ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ተናጋሪዎቹ ስፖርተኞችም፣ ዘፋኞችም፣ ሌሎች አርቲስቶችም፣ ሙስሊሞችም፣ ካቶሊኮችም፣ ፖለቲከኞችም፣ ሰካራሞችም፣ ጥቁሮችም ቀዮችም ነጮችም ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እስከ ዛሬ ዳንኤል ስንቱን ነጭ ሊቃውንት ጠቅሷል፡፡ ምንም አላልክም፡፡ የጥላሁን ገሰሰ ስም ሲነሳ አዞረህ፡፡ ለምን ቢባል በእግዚአብሄር ቦታ ገብተህ ጥላሁንን ገሃነም አስገብተህዋላ፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ በአንዱም በሌላውም ያስተምራል እንደተባለ የተባለውን ማስተዋል እንጂ ከእገሌ ከዘፋኙ፣ ከሰካራሙ፣ ከነጩ ከጥቁሩ እየተባለ እጅግ ለማራራቅ አትሞክር፡፡ ደግሞም መዝሙር መዝሙር ነው፡፡ እራሱ ስብከትና አስተማሪ ነው፡፡ እና ምኑ ይጠቀሳል እንዳለ ከማዳመጥ በቀር፡፡ ወይስ እገሌ የተሰኘው ዘማሪ እንዳለው ተብሎ እንዲፃፍ ፈለግክ፡፡ ክርስቲያኖች ከአህዛብ ጋር ይኖራሉ፡፡ መልካም ምግባራቸውን ይጋራሉ፡፡ መጥፎ ድርጊታቸውን አይጋሩም፡፡ የነሱን አትንኩ፣ ያሉትን አትናገሩ፣ የኛ የቅዱሳኑን ብቻ ካልክ በራስህ መንገድ ኑር፡፡ ዳንኤልም በመረጠው መንገድ ይኑር ይፃፍ፡፡ ፖለቲከኛው ስለ እነ እገሌ ምንም እንዳትል እያለ፣ ክርስቲያን ነኝ ባዩም እራሱ ከፈረጃቸው ሃጢያተኞች አትናገር እያለ የሚኖር ቢሆንማ ይህች አለም የእነምንም አትበሉ የእንምንም አትናገሩ ትሆን ነበር፡፡ ዳንኤል የሚያስተምር ነው ያልከውን ፃፍ እኛም የነገርከንን ሁሉ ሳይሆን የሚበጀንን እንወስዳልን፡፡አንት ከዚህ በላይ የፃፍከው ሰው እባክህን እጅግ የጠበበ አስተያየት አትስጥ፡፡ ጥላሁንም ሆነ ሌሎች ዘፋኞች እግዚአብሔር በሚሰጣቸው የ አንድ ደቂቃ ጊዜ ምናልባትም እንደ ፌያታዊ ዘየማን አንተን ሁሉ ቀድመው መንግስተ ሰማያት ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በመጨረሻው ሰአት እባክህ በቀኝ አውለኝ ብለው ከእግዚአብሄር ሊታረቁ ይችላሉ፡፡ ብዙ ታላላቅ ሰዎች በዚህ አለም ሳሉ እጅግ ጠቃሚ ቃላት ለኛ ለቀረንው በሙሉ ሊያስተምር የሚችል ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ተናጋሪዎቹ ስፖርተኞችም፣ ዘፋኞችም፣ ሌሎች አርቲስቶችም፣ ሙስሊሞችም፣ ካቶሊኮችም፣ ፖለቲከኞችም፣ ሰካራሞችም፣ ጥቁሮችም ቀዮችም ነጮችም ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እስከ ዛሬ ዳንኤል ስንቱን ነጭ ሊቃውንት ጠቅሷል፡፡ ምንም አላልክም፡፡ የጥላሁን ገሰሰ ስም ሲነሳ አዞረህ፡፡ ለምን ቢባል በእግዚአብሄር ቦታ ገብተህ ጥላሁንን ገሃነም አስገብተህዋላ፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ በአንዱም በሌላውም ያስተምራል እንደተባለ የተባለውን ማስተዋል እንጂ ከእገሌ ከዘፋኙ፣ ከሰካራሙ፣ ከነጩ ከጥቁሩ እየተባለ እጅግ ለማራራቅ አትሞክር፡፡ ደግሞም መዝሙር መዝሙር ነው፡፡ እራሱ ስብከትና አስተማሪ ነው፡፡ እና ምኑ ይጠቀሳል እንዳለ ከማዳመጥ በቀር፡፡ ወይስ እገሌ የተሰኘው ዘማሪ እንዳለው ተብሎ እንዲፃፍ ፈለግክ፡፡ ክርስቲያኖች ከአህዛብ ጋር ይኖራሉ፡፡ መልካም ምግባራቸውን ይጋራሉ፡፡ መጥፎ ድርጊታቸውን አይጋሩም፡፡ የነሱን አትንኩ፣ ያሉትን አትናገሩ፣ የኛ የቅዱሳኑን ብቻ ካልክ በራስህ መንገድ ኑር፡፡ ዳንኤልም በመረጠው መንገድ ይኑር ይፃፍ፡፡ ፖለቲከኛው ስለ እነ እገሌ ምንም እንዳትል እያለ፣ ክርስቲያን ነኝ ባዩም እራሱ ከፈረጃቸው ሃጢያተኞች አትናገር እያለ የሚኖር ቢሆንማ ይህች አለም የእነምንም አትበሉ የእንምንም አትናገሩ ትሆን ነበር፡፡ ዳንኤል የሚያስተምር ነው ያልከውን ፃፍ እኛም የነገርከንን ሁሉ ሳይሆን የሚበጀንን እንወስዳልን፡፡

  ReplyDelete
 10. Dear Anonymous,
  You can take only the quote. Why do you focus on the source? If you think positively it doesn't matter if the quote has good message.

  ReplyDelete
 11. Dear repliers to the comment on the quote from secular songs,

  I think we are not on the same page!!! No word you said corresponds to my idea! I was not saying Tilahun went to hell. But, we know, sharing secular songs is sin. In the bible, it is clearly articulated that song is fleshy fruit. Our forefathers repeated it several times. How can you then blindly defend Dn, Daniel for this? Orthodox Tewahido has common ground for basic beliefs which all follower shall obey! This is the shining sign of the CHURCH!!! Otherwise, individual thinking prevails. But, individualism is the identification for others.

  Do you like Daniel? Then, does it mean that you should confirm whatever he says or writes is OK??? Do you feel you are encouraging him side to the right or are you misleading him by writing such suboptimal comments on me? And how do you know that you are thinking of him any better than me for the righteousness of him? Please, be open minded and be zealous for your kinsmen whether they are on the right track (prayer) or missing their ways (both prayer and rectification). Let me depart you with the following text from King Solomon. ‹‹የጠላት መሳም የበዛ ነው ፡ የወዳጅ ማቁሰል የታመነ ው››፡፡

  Please, forgive me and forget my all words if you are not Christians!!

  ReplyDelete
 12. As Paulos' was entwined with two different political periods, the book is important to further understand the challenges posed particularly to journalists.

  ReplyDelete
 13. ዳንኤል የሚያስተምር ነው ያልከውን ፃፍ እኛም የነገርከንን ሁሉ ሳይሆን የሚበጀንን እንወስዳልን፡፡

  ReplyDelete
 14. why we forget the main thing that the book of Derej ( paulos's profil book )?
  pleas let we back....

  ReplyDelete