Wednesday, June 25, 2014

የታጋዩ የልጅ ልጅ

<<ስኩል ኦፍ ኖርዘርን ስታር›› ከሚባለው ውድ ትምህርት ቤቱ የአያቱ ሾፌር ወደ ቤቱ ሲያመጣው ልቡ ከመኪናው ፍጥነት በላይ ነበር ወደ ቤቱ የሚሮጠው፡፡ ያየውንማ ለአያቱ መንገር አለበት፡፡ አያቱ እንዲህ ታዋቂ  አክተር መሆናቸውን አያውቅም ነበር፡፡ ፊልሙን ሲመለከት አያቱን በመሪ ተዋናይነት በማግኘቱ ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ጋር በኩራት ነበር ያወራው፡፡ እነርሱም የታዋቂ ሰው የልጅ ልጅ በመሆኑ ከፊልሙ በኋላ እንደ ንብ ነበር የከበቡት፡፡ ብዙዎቹ እንዲያውም በወረቀት ላይ አያቱን አስፈርሞ እንዲያመጣላቸው፣ ከተቻለም ፎቷቸውን እንዲሰጣቸው ለምነውታል፡፡  
ቤቱ ሲገባ አያቱ የሉም፡፡ ደወለላቸው፡፡ እየመጡ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ መክሰስ ለመብላት እንኳን ሆድ አልቀረለትም፡፡ ይህን አስገራሚ ነገር ከአያቱ ጋር ማውራት እጅግ አጓጉቶታል፡፡ እየደጋገመ ‹ፐ› ይላል፡፡ አባቱና እናቱ ራሳቸው ይህንን የሚያውቁ አልመሰለውም፡፡ ይህንን ነገር ያወቀ የመጀመሪያ ሰው እርሱ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ገምቷል፡፡ ‹ፐ›፡፡
አያቱ መጡ፡፡


‹‹አያቴ ቴክ ፋይቭ›› አለና በአምስት ጣቱ አምስት ጣታቸውን ገጨ፡፡
‹‹ምን ተገኘ ዛሬ›› አሉ አያትዬው ደንቋቸው፡፡
‹‹እኔኮ አክተር መሆንህን አላውቅም ነበር፡፡ ጓደኞቼ ሁሉ አያቴ አክተር መሆኑን ሲያውቁ ሪስፔክት አደረጉኝ›› አላቸው በሳቅ እየተፍለቀለቀ፡፡ በጣቱ እንደ ሽጉጥ ያለ ነገር ሠርቶ፣ በእግሩ ተንበረከከና በግድግዳው ላይ ‹‹ቷ-ቷ-ቷ-ቷ›› አደረገ፡፡
‹‹የምን አክተር ነው››
‹‹እንዴ የሠራኸውን ፊልምኮ አየነው፡፡ ትምህርት ቤታችን ውስጥ አየነው፤ መሥራትህን ረሳኽው እንዴ››
‹‹የምን ፊልም ነው የሠራሁት››
‹‹አክሽን ፊልም ሠርተኻልኮ፤ ፓ ትልቅ ገን ይዘህ ተርርርርር ስታደርግ ጓደኞቼ አጨበጨቡልህ፤ ስታሩ አንተ ነበርክ እንዴ? ኢነሚዎችህ ሲተኩሱብህኮ ዘለህ ገደል ውስጥ ገባህ፤ ተንከረባበትክኮ፤ ከዚያ ደግሞ ቦንብ በጥርስህ ነቅለህ ወረወርክና ቦዋ ሰጠኸው፤ ከዚያ ታንኩ ሲተኩስብህ በገደሉ ውስጥ ገብተህ አመለጥካቸው፡፡ ልክ ስታመልጥ ጓደኞቼ እያፏጩ አጨበጨቡ፡፡››
አያት ሊገባቸው አልቻለም፡፡ ለልጁ ምን አሳይተውት እንደሆነ ግራ ገባቸው፡፡
‹‹እስኪ ያየህውን ቀስ ብለህ ንገረኝ››
‹‹እይ፣ በትምህርት ቤታችን ‹ሂስትሪ ዊክ› አለ፡፡ ትናንት ፊልም ነበር፡፡ ‹ዘ ፋይተርስ› የሚል የኢትዮጵያ ፊልም አሳዩን፡፡ የድሮ ታሪክ ነው ብለዋል፡፡ እና - እና እዚያ ላይ አየሁህ፤ አሪፍ አክተር ነበርክ ለካ፡፡ ለምን ግን አክተርነት ተውክ? ነጋዴ ከመሆንኮ አክተር መሆን ይበልጣል፡፡ ዳድ ነጋዴ ነው፡፡ ጓደኞቼ ግን አድንቀውት አያውቁም፡፡ አንተ አክተር መሆንህን ሲያዩ ግን ከበቡኝኮ››
አሁን አያትዬው ገባቸው፡፡
‹‹ያየህውኮ እውነተኛ ታሪክ ነው›› አሉት፡፡
‹‹ቤዝድ ኦን ትሩ ስቶሪ - ነው››
‹‹ኖ ኖ ኖ ኖ፣ ያ የኛ የታጋዮች ታሪክ ነው፡፡ አክተር ሆኜ አይደለም፡፡ ከደርግ ጋር ያደረግነውን ውጊያ ፊልም ነው ያሳዩዋችሁ››
‹‹እንደ ደርግ ሆኖ የሠራው አክተር ማን ነበር? ታንክ ምናምን እየነዳ - ቡልቅ አድርጎ ሲተኩስ - ፓ››
‹‹ይህኮ ፊልም አይደለም፤ የተደረገ ታሪክ ነው፡፡
‹‹እንዴ አያቴ፣ አንተ ፋይተር ነበርክ እንዴ?››
‹‹አዎ››
‹‹ገን ምናምን ይዘህ›
‹‹አዎ››
‹‹ኦ- ማይ ጋድ -እና ሰው ገድለሃል?›› ስቅጥጥ አለው ልጁ
አሁን አያት እንዴት እንደሚያስረዱት ግራ ገባቸው፡፡ እርሱ ደግሞ አያቴ አክተር ነበሩ ብሎ ያገኘው ክብር ሲናድበት ታየው፡፡
‹‹አየህ ድሮ ደርግ የሚባል መንግሥት ነበረ›› ብለው ሲጀምሩለት
‹‹ደርግ ምን ማለት ነው? እዚያ ፊልሙ ውስጥም ደርግ ደርግ ይል ነበር፤ እኛኮ የአክተር ስም መስሎን ነበር››
አንገታቸውን ከግራ ወደ ቀኝ እየነቀነቁ ለማስረዳት ቃላት ፍለጋ ገቡ፡፡
‹‹እርሱን ለማስወገድ ጫካ ገብተን ብዙ ዓመት ተዋግተናል››
‹ለምን ታወግዳላችሁ? ፊልሙ ራሱ ያልቅ ለም እንዴ››
‹‹ፊልም አይደለም ብዬህ››
‹‹ቆይ ግን ቢች አካባቢ ብቻ ነበር እንዴ ፋይት የምታደርጉት››
‹‹እንዴት›› አሉ ገርሟቸው
‹‹ቁምጣ ብቻ ነበራ ሁላችሁም ያረጋችሁት››
ሳቁ፣ እስኪበቃቸው ሳቁ፡፡
‹‹ግንኮ እይ›› አለና አንድ መጽሔት ይዞላቸው መጣ፡፡ የፋሽን መጽሔት ነው፡፡ እዚያ ቤት ደንበኛ የሆነ መጽሔት ነው፡፡ ‹‹እይ ፀጉራቸውን እንደ እናንተ አቁመው የሚበትኑትኮ ሴለብሪቲስ ናቸው፡፡ እይ›› ዘፋኞችና የፊልም ተዋንያን እዚያ መጽሔት የፊት ለፊት ሽፋን ላይ ፀጉራቸውን አንጨብረው ተነሥተዋል፡፡ ‹አክተር ካልሆናችሁ ፀጉራችሁን ለምን እንደዚህ አደረጋችሁት?››
‹‹እኛኮ ትግል ላይ ነበርን፤ እንደ እናንተ ንጽሕና ለመጠበቅ፣ ገላ ለመታጠብ፣ ፀጉር ለመቆረጥ ጊዜ አልነበረንም››
‹‹እና ሻወር አትወስዱም ማለት ነው? ሚስ ዝም ትላችኋለች?››
‹‹በኛ ጊዜ ሚስ የለም›› አሉ ለመገላገል፡፡
‹‹እንዴት፣ ሚስ የሌለው ትምህርት ቤት አለ እንዴ? እንደዚያ ዓይነት ትምህርት ቤት በ‹አይስ ኤጅ› ጊዜ ብቻ ነው የሚኖረው››
‹‹እኛ እንደናንተ የመማር ዕድል አላገኘንም፣ትግል ላይ ነበርን››
‹‹ፋይት ብቻ ነበር ሥራችሁ ማለት ነው፤ እኛን ግን ዳድ ፋይት አታድርጉ ይለናል፡፡ እኔና ሳሚኮ ዋተር ገን ይዘን ፋይት ስናደርግ፣ ፋይት ጥሩ አይደለም ይላል፡፡ እናንተን ግን አባታችሁ ዝም ይላችኋል አይደል? ታድላችሁ፤ እስኪ ዳድን አስፈቅድልን››
‹‹ፋይት ማድረግማ ጥሩ አይደለምኮ››
‹‹ታድያ እናንተ ለምን ፋይት አደረጋችሁ››
‹‹እኛኮ ከደርግ ጋር ነው ፋይት ያደረግነው››
‹‹በቃ ወይ እኔ ወይ ሳሚ ደርግ እንሆናለና››
‹‹እይውልህ ጃክየ ወደፊት በደንብ አስረዳሃለሁ፤ አሁን ገና ልጅ ነህ››
‹‹ቆይ ቆይ አያቴ፣ እነዚያኞቹ፣ ኢነሚዎቹ ደርግ ናቸው ብለሃል፣ እናንተ ማንን ሆናችሁ ነው ፊልሙን የሠራችሁት›› ፊልም የሚለው ነገር ከልቡ ሊወጣ ባለመቻሉ እያዘኑ
‹‹የኛ ስም ኢሕአዴግ ይባላል››
‹‹እኛ ግን ሁለቱንም ስሞች አማርኛ ስንማር አልተማርናቸውም፤ ሚስም አታውቃቸውም ማለት ነው›› አለና በሳሎኑ መስኮት ውጭ ውጪውን ማየት ጀመረ፡፡
‹‹ጃክ ምነው አያትህ ፋይተር በመሆኔ ከፋህ እንዴ›› አሉት አያቱ፡፡
‹‹እኔ ግን ፋይተር ከምትሆን አክተር ብትሆን ነበር ደስ የሚለኝ፡፡ ጓደኞቼ ሁሉ አያቴ አክተር ነው ስላቸው ጎል እንዳገባ ተጫዋች ነበር ያቀፉኝ››
‹‹ፋይተር ነበር፣ ፈሪደም ፋይተር ነበር በላቸዋ››
‹‹እና ከዚያ ሰው ገድሏል ወይ? ለምን ገደለ? ማንን ነው የገደለው? ቢሉኝስ፤ እኔንስ ቢፈሩኝስ፣ አያቱ ቁምጣ ለብሶ አየነው ብለው ቢስቁብኝስ፤ የአያቱ ፀጉር ተንጨብሯል ቢሉኝስ፤ በ‹አይስ ኤጅ› ጊዜ የነበረ ነው ቢሉኝስ፣ አልነግራቸውም››
አያቱም በተራቸው በመስኮቱ በኩል ወደ ውጭ ማየት ጀመሩ፡፡ ‹‹ተተኪው ትውልድ ግን እንዲህ ነው የሚረዳን ማለት ነው? የእርሱ ዘመን ጀግኖች ሌሎች ናቸው ማለት ነው? ወታደራዊ ታሪክን ማድነቅ ትቶ መዝናኛዊ ሰብእናን የሚያደንቅ ትውልድ ነው ያፈራነው ማለት ነው? ምናልባት ከኛ በፊት ለነበሩት ሌሎች ታጋዮችና አርበኞች ቦታ ባለመስጠታችን አዙሪቱ እኛም ላይ እየደረሰ ይሆን? ውጊያችንን እንደ ፊልም ነው የሚቆጥሩት ማለት ነው? ›› ማለቂያ የሌላቸውን ጥያቄዎች በመስኮቱ በኩል ይወረውራሉ፤ ጥያቄዎቹ ግን በመስኮት እንደወጡ ነው የቀሩት፤ አልተመለሱም፡፡
 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

50 comments:

 1. Lezehe teweled teteyakiw hulum ne. kelay ke mengest gemero eske enatn abatochachen ders teteyakiwoch nachew.
  ahunem geze alacheu yemeketelewen lemastetkakel.
  Thank you D.Daniel

  ReplyDelete
 2. yegna hager chigir yihe new hule tarik kenga endijemir enfeligalen yaleziya litefa yemaychil mehon alebet

  ReplyDelete
 3. ኡፍ.... አስተነፈስከኝ.... እግዚአብሔር ይስጥልን ዳኒዋ ይኼ ፊልም የሚታይባቸው ወራት ሲመጡ...ደግሞ መጣ አያፍሩም እንዴ ጣሊያን፣ እንግሊዝ....ጋር የጀገኑ መሰላቸው እንዴ? ምነው የሚነግራቸው ጠፋ..የሚለው....የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጥያቄ ነው.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለአደዋ ( ዳግማዊ ሚኒሊክ) መታሰቢያ ነው ፊልሙ የሚታየው?

   Delete
  2. Menelik did nothing in the batte of Adwa. He hide him self in near by church.

   Delete
  3. Menelik did nothing in the battle of Adwa. He hide him self in a nearby church

   Delete
  4. yihe ekonew chigrachin. abatochachin ena enatochachin yeserutn sira yalemakber. ehit/wondm!!! yane minilik church wust sidebek antem abreh neberk aydel????

   Delete
  5. Getaw, meri eko amerar yisetal enji mesmer gebto aywagam. Marshalun litaschers asebk ende? Kalawekih zim bitl min alebet? Af sikefet chinkilat yitayal yibalal. Leziyawm sidib kemenager zim malet tiru new. Zim Ayneqzm.

   Delete
  6. tarikin yemanakebir dedeboch honenanal, berigit min madireg yichalal. yeminawukew ehe menigist le agezaz endimechew and gileseb yaleteinat befelegew astesaseb yetsafewun tarik new yeminawukew

   Delete
 4. When we have bad history, it is hard to pass for next generation. His grandfather didn’t tell him why he fought with Derg because he is doing the same thing at the movement. In addition that killing was killing his brother to get better life not Ethiopian people freedom so he always lie to next generation.

  ReplyDelete
 5. Thank you so much Dani, our dream come true. We fought seventeen years to bring peace for this generation, at the movement they think about film and movie actors. We used to think what to eat and about war. At the movement our country annual growth is around 10%. With is the next twenty years we will bit all African country. Our people used to be eating one time per day, at this time all Ethiopian’s eat three times per day. We will work hard to give free condominium for all Ethiopian people. Thank you so much Dani please continue writing this kind of fact. God bless you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሳንሞት ገነት ልንገባ ነዋ!

   አበሻና ሆድ ፡ አሉ

   Delete
  2. ኡኡቴ!! እንዴት ይሻለናል

   Delete
  3. 10%, soste meblat, netsa condominium,.......????????
   lante lihon yichilal yelelochin temelseh temelket

   Delete
  4. soste belan eyalk 'teret teret' taworaleh aydel,atafrem? i thk u didnt understand z above story...hahaha..read it again ok...

   Delete
  5. i think he cant understand Amharic. don't judge him

   Delete
 6. እኩል የሐብት ክፍፍል ችግር ወቅታዊ አይመስለኝም፡፡ በታሪካችን መሬት በጥቂቶች እጅ፣ የፖለቲካ ስልጣን በተመረጡ ጥቂቶች መዳፍ፣ የመማር እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች በችሮታ መልክ ሲሰጡን ኖረናል፡፡ እንደውም የኢትዮጵያ የህዝቧ ታሪክ ከ ኢትዮጵያ ታሪክ ይለያል ብዬ የማስብበት ዋነኛ ምክንያት ብዙሀኑ የሐገሪቱ ህዝብ ለሀብቱ እና ሊያገኘው ለሚገባው ጥቅም ባይተዋር ሆኖ በመኖሩ ነው፡፡ ተራው ህዝብ ግዴታውን ከመወጣት ባሻገር መብቱን አያውቀውም፣አይጠይቀውም፡፡ የአገሪቱን ነጻነት እና ስልጣኔ ለዝንት አለም አስከብሮ የኖረው ሕዝብ ከራስ ጥቅም በነጻ መልኩ ነው፣ ምክንያቱም ተጠቃሚዎቹ ራሳቸውን በአረንጓዴ መስኩ ላይ ያስቀመጡት ወገኖቹ ናቸው፡፡
  ለዚህ ግልጽ ብዝበዛ መፍትሄው ትምህርት ነው፡፡ እስኪ አስቡት መሐይምነት 80 በመቶ በሆነበት አገር ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ቢኖር ነው የሚገርመው፡፡ ወገንን መርጦ መጥቀም እና በጥቅም መተሳሰር ባህል በሆነበት አገር አዋቂነት ዋጋ ባያጣ ነው የሚገርመው፡፡ ቆስለናል፣ ሞቶብናል አገር “ነጻ አውጥተናል” ስለዚህ የበለጠ ጥቅም ይገባናል ማለት ወደ አማርኛ ሲተረጎም እኮ ‘’አገሪቱ በ ጥረጣችን ያቆምናት ኩባንያ ናት ስለዚህ የትርፍ ተካፋይ መሆን የሚገባን እኛ ባለአክስዎኖቹ ነን ማለት ነው’’፡፡ ምልባት ለዛ ይሆናል ሰዎቹ አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ምንምነኛ ዜጋ አለ ያሉት፣ ማለቴ ባለ አክሲዎኖቹን እና አክሲዎን አልባዎቹን ቆጥረው፡፡
  ግብር አጭበርብሮ ምጽዋት በሚሰጥ፣ የእርዳታ እህል ሽጦ ፎቅ ለመስራት ወደኋላ በማይል፣ የሌላውን ሌብነት ለመቃወም ራሱ ሰርቆ ከአገር የሚጠፋ፣ ስርቆት በጠበጠን እያለ የሌባ ዘመዱን የስርቆሽ ንብረት በሚበዘብዝ ማህበረሰብ ውስጥ የሐብት ክፍፍል ፍትሀዊ ቢሆን ተአምር ነው፡፡
  የህግ የበላይነት የማይተካ ሚና አለው፡፡ የፍትህ ስርአቱ ጠንካራ እና ለህዝብ ጥቅም የቆመ ቢሆን ኖሮ ደሃ ማልቀሻ እና የመፍትሄ ተስፋ ይኖረው ነበር፡፡ እስከዛ ግን እባካቹ፣ በናታቹ አትበዝብዙን ከማለት በቀር ምን እድል አለ? ይዘገንናል እኮ ለብዙ ትውልድ በመብት እና በህግ ሳይሆን በመተዛዘን መኖር? በመከባበር ሳይሆን በመፈራራት መዝለቅ?
  እና ፍትሐዊ የሐብት ክፍፍል ለማምጣት መሰረቱ የለንም ነው የኔ THEORY ለዚህ ደገሞ ሁላችንም (ያሉትም የሞቲትም) ተጠያቂ ነን፣ ባህል ተጠያቂ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዜር ይስጥልኝ፡፡ ግን እኔ እኮ የሁለት ፈረሶች ወግ ለሚለው ጽሁፍ ነበር ለምለም በለል ስም ከላይ ያለውን ጽኁፍ የለጠፍኩት፣ በ24/06/2014 በብሎጉ አቆጣጠር ማለቴ ነው፡፡ ነገሩን ማለቴ ነው እንጂ ይሄን ያህል ትልቅ ነገር ሆኖ አይደለም፡፡

   Delete
  2. አስተውላቹ ከሆነ የአስራ ሰባት አመቱ የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት በአመት ሶስቴ ይዘከራል፡፡ የካቲት አስራ አንድ፣ ግንቦት ሃያ እና በቅርቡ መከበር በጀመረው የሰኔው የሐውዜን አውሮፕላን ድብደባ ዝክር፡፡ ሰዎች ልጆቻቸውን እና ዘመዶቻቸውን አጥተዋል፣ አገሪቱ በጦርነት ስትቆላ እና በጠላትነት በተፈራረጁት ወንድማማቾች ደም ስትጥለቀለቅ ባጅታለች፡፡ ታሪኩ ቢዘከር ክፉ ባይመስለኝም አዲሱ ትውልድ ያልተዛባ አመለካካት እንዲኖረው ቢደረግ ግን ጥሩ ነው ብዬ አስባለው፡፡
   አሁን የምናየው ግን ቂምን ለማወራረስ አላማ ያለው እና የባለእዳነት ስሜት በአዲሱ ትውልድ ላይ ለመፍጠር ያሰበ የሚመስል ነውና አካሄዳችንን ብናሳምር ጥሩ ነው አለበለዛ በሌላ ደም መፋሰስ የሚሰራ የቤት ስራ መተዋችን ነው፡፡
   አሁን ባለው ሁኔታ የአባቶቻቸውን ታጋይነት የሚያውቁ (አንዳንዴ እንደውም የብሔር ማንነታቸው ታጋይ የሚያደርጋቸው የሚመስላቸው) ከማወቅ አልፎ የሚኮሩበት፣በረሐ መወለዳቸውን የባላይነት መንስኤ የሚያደርጉት መአት ናቸው፡፡
   እንደው ለነገሩ ማለቴ ነው :):)

   Delete
  3. I really apologize if I disappointed you when I copy and paste your idea. I know and you right, you posted it on The two horse blog but I love it so much and it has excellent message for all Ethiopian people in addition that the idea works for this article as well so I did it. I didn’t mention my name because it is not my idea so I posted it with Anonymous person. I should explain where I found it or I have to write your name. I really apologize again I didn’t do it to get respect or to say my idea. Thank you so much Lemlem for your detail comment, it helped me to improve my view.

   Delete
  4. apology accepted :)

   Delete
 7. "ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ነገርግን የሚያነበው የለም" ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ We always live for ourselves so we don’t care about next generation so our children never know about our country fact. We will die one day but hour house, car and money not go with us. Please never forget you will die.

  ReplyDelete
 8. mnew ashkabeth bakih? yenesun gedl man negeren aleh. beyeseatu singat yeminorew new ante degmo lekek argen. lela lelawn tsaf.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቂጣ በቀደደው አፍህ! አሉ

   Delete
  2. please dont kiss some ones ass

   Delete
 9. ምናልባት ከኛ በፊት ለነበሩት ሌሎች ታጋዮችና አርበኞች ቦታ ባለመስጠታችን አዙሪቱ እኛም ላይ እየደረሰ ይሆን? OMG, very nice conclusion

  ReplyDelete
  Replies
  1. በትክክል " የሁዋላው ከሌለ የለም የፊቱ " እንዳለው አርቲስቱ ማለት ነው የ100 አመት ታሪክ እያሉ ታሪክን መካድ ለዚህ አይነቱ ትውልድ ማፍራት አስተዋጽኦ ይኖረዋል

   Delete
 10. I think this is right. It is an undeniable fact!!! ከኛ በፊት ለነበሩት ሌሎች ታጋዮችና አርበኞች ቦታ ባለመስጠታችን አዙሪቱ እኛም ላይ ደረሰ:: Mastewal gin kegna zend rikalech... GOD BLESS YOU!!!

  ReplyDelete
 11. I think this kid is very lucky, he went American school so it is so difficult for him our poltics and speaking his native languche .

  ReplyDelete
 12. Deacon Daniel,
  u made me laugh inside.

  ReplyDelete
 13. እግዚአብሔር ይጠብቅህ ዳኒ.
  በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም፤፤ ያውም ድንበርን ከጠላት ባርነት ለጠበቀ ጀግና ንቀት ምን ይሉታል፤፤

  ReplyDelete
 14. ጥያቄ፡ ታላቁን የማያከብር ታጋይ እሱ እንዴት ይከበራል?
  ፡ የታላቁን ታሪክ ገደል የከተተ የእርሱ የት ይገባለታል?

  ReplyDelete
 15. minew Danii yemitsfew atah ende??

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውን ይህ ጽሁፍ ክፋት አለው?

   ዘረኝነት እንደ ተስቦ ነዉና በያለንበት እንጠንቀቅ!

   Delete
  2. eski ante kezih yeteshale tsafna asayen,,i thk zis is a great message for all of us, zere are so many ideas in zis topic...

   Delete
  3. Anibesa yerasun tarik eskitsif dires, adagnu yitsifiletal (Dani) you ar good

   Delete
 16. መልከማርያምJune 26, 2014 at 3:51 PM

  ሆድና ጀርባ
  አባት ለልጁ በአጽንኦት የግድ የሚያስተላልፈው ታሪክ አለ፣ ነገር ግን ለመናገር የማይመችና ቢነገርም የማያኮራ ታሪክ ከልጅልጅ አይተላለፍም ልክ እንደዚህ ታሪክ። ሁለት ወንድማማቾች ለጥቅም ቢዋጉ ሁልጊዜም አሸናፊው ወንድሙን ማሸነፉን በኩራት ሊናገር አይችልም፣ ቢናገርም ለማን? እንኳንም ያ ሽማግሌ ለልጅልጁ የሱን የእውነተኛ ጦረኛነት ማስተላለፍ ተሳነው፣ አለያ ሌላ የጦር አክትር እየመጣ....
  ለመነኛውም ልብ ያለው ያስተውል ትውልዱ ግራ ገብቶታል፣ በታሪኩ አፍሯል፣ እናም የጋራ ጀግና የማያፍር፣ ለሁሉም የሆነ የስፈልገናል

  ReplyDelete
 17. ጠያቂ በዛ ፡ መልስ ሰጭ የለም፡፡
  ሁላችንም የቁም እንቅልፍ ላይ ነን ፡ ምን ያነቃን ይሆን ? ጦሙን እያደረ ፡ "ደህና ነኝ" የሚል ሰው የሚኖርበት ምድር!

  ReplyDelete
 18. I think this is right. It is an undeniable fact!!! ከኛ በፊት ለነበሩት ሌሎች ታጋዮችና አርበኞች ቦታ ባለመስጠታችን አዙሪቱ እኛም ላይ ደረሰ:: Mastewal gin kegna zend rikalech... GOD BLESS YOU!!!

  ReplyDelete
 19. ታሪክ በተወሰኑ ክፍሎች የግል ፍላጎት ተገልብጦ ሊጻፍ የሚችል ፡ የሚመስለው ካለ ተሳስቶዋል። በርግጥ ለግዜው ሊመስለን ይችላል። አንዳንዴ እውንት ወጥታ ምስክርነት እስክትሰጥ ገዜ ይፈጃል።

  ለምሳሌ ደርግ ፡ ዛሬ ላለንበት ውድቀት መሰርቱን በመጣሉ በታሪክ ይታወሳል። የሰው ልጅ አስከሬን የመፈክር መለጠፊያ ተደርጎ ፥ ሰውነቱ ውስጥ ባለው ጥይት ቁጥር ፡ ቤተስቦቹ ገንዘብ ከፍለው እሬስ ሲያነሱ ፥ ትውልድ በቁሙ ተዋረደ፡፡ አገር ተዋረደች፡፡ አገር መኩሪያንትዋ ቀርቶ ፡ ማፈሪያ ሆነች፡ ደርግ ግዑዝ ነገር ሳይሆን ፡ ሰው የመሰሉ አውሬዎች ጥርቅም ነበር፡፡

  በዚህ ሁኔታ የታነጸው ትውልድ ዛሬ ፡ ከድጡ ወደማጡ እያዘገም ነው፡፡
  አብርሃም ሊንከንን ፡ ዳግማዊ ሚኒሊክን ማንዴላን የመሳሰሉ ፡ ታሪክ የሰሩን ሰዎች ን ፡ ታሪክ ለሟንቋቅሽ መሞከር ፡ እራስን ከፍ የሚያደረግ ሳይሆን ፡ እራስን የሚያዋርድ እኩይ ትግባር ነው፡፡ አንድ ቀን ለልጅ ፥ ለልጅ ልጅ ማፈሪያ ይሆናል፡፡ እውነት ትመነምናለች እንጂ ፡ አትሞትምና!
  መንገደኛው

  ReplyDelete
 20. Daniel is now getting out of his wolf jacket and showing his true color. He is at a point of no return on his path of deception. He will continue to spiral down the slide of condemnation he chose to follow.

  ReplyDelete
 21. seifemichael zeejereJune 30, 2014 at 5:06 AM

  ጽሁፎች ሁሉ ወደስራ የሚመሩ፣ ድህነትን የሚያከብሩ ሳይሆኑ የሚረግሙና በስራ ለማስወገድ ከመቀመጫ የሚያስነሱ፤እጅግ ከከረፋ የጥላቻ መርዝ አላቀው ወደ ይቅርታ የሚመልሱ፣ ሰዎችን እነርሱ ባጠለቁት መነፅር ብቻ ከማየት እግዚአብሄር በሰጣቸው ህሊና ብቻ ፈርደው የሚመዝኑ ቢያደርጋቸው እወዳለሁ፡፡ ደርግ ለምን ተሸነፈ አልልም፡፡ በኔ አስተሳሰብ ደርግ መወገድ ነበረበት፡፡ ደርግ ሲወገድ ግን የተተካው መንግስት እንደ ደርግ አሳቢ እንደ ደርግ ኗሪ መሆን የለበትም፡፡ ለዴሞክራሲ እና ለህዝቦች እኩልነት የሚታገል መሆን አለበት፡፡ ደርግ ጥሩ የሰራውን በጥሩ፣ ንጉሱም በጥሩ የሰሩት በጥሩ ቢነሱ ኖሮ ኢህአዴግም ዛሬ የሰራቸው መሰረተ ልማቶች፤ ትምህርት ቤቶች ሁሉ በነገው ትውልድ በበጎ ይነሳሉ፡፡ በተገኘው መድረክ ሁሉ ሲቪል ሰርቪስ ዛሬ የተፈጠረ ይመስል የበፊቱ ሲቪል ሰርቪስ የመከነ ነው ብሎ ማሰብ እርሱ በራሱ ምክነት እና በጎ ካለማሰብ የመነጨ ነው፡፡ መድረክ አገኘን ብላችሁ አፋችሁን አትክፈቱ፡፡ የሚያዳምጣችሁ ሰው ነው፡፡ ቴፕ አይደለም የሰማውን ቀድቶ የሚቀር፡፡ ምንም ባይናገር በተናገራችሁት ይፈርዳል፡፡ ያለፈው ሲቪል ሰርቪስ የሰራው ነበረ፡፡ የመከነ ከሆነ ምንም አልሰራማ፡፡ የዛሬውስ ሲቪል ሰርቪስ አይዘርፍም፣ አይቀጥፍም፡፡ ደርግ፣ ወያኔ እያልክ በክፉ እና በጥላቻ የተሸፈንክ ሁሉ አይንህን ፍታና በጎ በጎውንም እይ፡፡ ለበጎው እውቅና ስጥ፡፡ጽሁፎች ሁሉ ወደስራ የሚመሩ፣ ድህነትን የሚያከብሩ ሳይሆኑ የሚረግሙና በስራ ለማስወገድ ከመቀመጫ የሚያስነሱ፤እጅግ ከከረፋ የጥላቻ መርዝ አላቀው ወደ ይቅርታ የሚመልሱ፣ ሰዎችን እነርሱ ባጠለቁት መነፅር ብቻ ከማየት እግዚአብሄር በሰጣቸው ህሊና ብቻ ፈርደው የሚመዝኑ ቢያደርጋቸው እወዳለሁ፡፡ ደርግ ለምን ተሸነፈ አልልም፡፡ በኔ አስተሳሰብ ደርግ መወገድ ነበረበት፡፡ ደርግ ሲወገድ ግን የተተካው መንግስት እንደ ደርግ አሳቢ እንደ ደርግ ኗሪ መሆን የለበትም፡፡ ለዴሞክራሲ እና ለህዝቦች እኩልነት የሚታገል መሆን አለበት፡፡ ደርግ ጥሩ የሰራውን በጥሩ፣ ንጉሱም በጥሩ የሰሩት በጥሩ ቢነሱ ኖሮ ኢህአዴግም ዛሬ የሰራቸው መሰረተ ልማቶች፤ ትምህርት ቤቶች ሁሉ በነገው ትውልድ በበጎ ይነሳሉ፡፡ በተገኘው መድረክ ሁሉ ሲቪል ሰርቪስ ዛሬ የተፈጠረ ይመስል የበፊቱ ሲቪል ሰርቪስ የመከነ ነው ብሎ ማሰብ እርሱ በራሱ ምክነት እና በጎ ካለማሰብ የመነጨ ነው፡፡ መድረክ አገኘን ብላችሁ አፋችሁን አትክፈቱ፡፡ የሚያዳምጣችሁ ሰው ነው፡፡ ቴፕ አይደለም የሰማውን ቀድቶ የሚቀር፡፡ ምንም ባይናገር በተናገራችሁት ይፈርዳል፡፡ ያለፈው ሲቪል ሰርቪስ የሰራው ነበረ፡፡ የመከነ ከሆነ ምንም አልሰራማ፡፡ የዛሬውስ ሲቪል ሰርቪስ አይዘርፍም፣ አይቀጥፍም፡፡ ደርግ፣ ወያኔ እያልክ በክፉ እና በጥላቻ የተሸፈንክ ሁሉ አይንህን ፍታና በጎ በጎውንም እይ፡፡ ለበጎው እውቅና ስጥ፡፡

  ReplyDelete
 22. ማለቂያ የሌላቸውን ጥያቄዎች በመስኮቱ በኩል ይወረውራሉ፤ ጥያቄዎቹ ግን በመስኮት እንደወጡ ነው የቀሩት፤ አልተመለሱም፡፡ማን ይመልሰው ዘረኝነት ትልቁ ነከርሳ እያለ ተጠንቀቅ ወገኒ

  ReplyDelete
 23. ምናልባት ከኛ በፊት ለነበሩት ሌሎች ታጋዮችና አርበኞች ቦታ ባለመስጠታችን አዙሪቱ እኛም ላይ እየደረሰ ይሆን? በትክክል " የሁዋላው ከሌለ የለም የፊቱ " እንዳለው አርቲስቱ ማለት ነው የ100 አመት ታሪክ እያሉ ታሪክን መካድ ለዚህ አይነቱ ትውልድ ማፍራት አስተዋጽኦ ይኖረዋል

  ReplyDelete
 24. ዳነ! እግአብሄር ይባርክህ የንስር አይን ይስጥህ

  ReplyDelete
 25. እንደተለመደው ይህን እውነተኛ የሆነ አስተያየት እንደማትለጥፈው አውቃለው ግን ቢሆንም አንበው።እውነት ስለሆነ።ሁሌ እንደምልህ ዋናውን ትልቁን የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን ችግር አንስተህ ሰዉ እሱ ላይ ተግባብቶ፥ተማምኖ መፍት ሄ እንዲፈልግ ብታደርግ ይሻልህ ነበር።ይህን ማድረግ ግን አልፈለክም አልቻልክም።ለእውነት የሚከፈልን መስዋዕትነት መክፈል ከባድ እንደሆነ ብረዳም ለውሸት፥ለድንቁርና፥ለዘረኝነት/ አፓርታይድም ማጨብጨብ ለጊዜው ካልሆነ ጥሩ አይደለም።ፊልሙ ላይ እንዳነሳኸው ለምን አይነት ነፃነት ነው ያሉ መስዋዕትነት የተከፈለው ?ታላቋ ትግራይ ሪፐብሊክን ለመመስረት እንደሆነ ብታነሳውስ ኖሮ ምን ይልህ ነበር????????? የልጅ ጆቻቸው ውድ ትምህርት ቤት የሚማሩት፥ልጆቻቸው የናጠጡ ነጋዴ የሆኑት ስ ከየት በመጣ ኃብት እንደሆነ ለምን አትጠይቃቸውም ነበር።የ አፓርታይድ ስርዓት ውስጥ ያሉ ልጆች የ አያቶቻቸውን ታሪክ እንደፊልም ይተረክላቸው የጫካ ውጊያው አንተም ያን በደም የጨቀየ ታሪካቸውን ለማጠብ የውሸት፥የዘረኝነት ተባባሪ ሁን።እኛም የምርጫ ዘጠና ሰባትን እና ሌሎችን የ አፓርታይድ ታሪክ ለልጆቻችን እየነገርን እናሳድጋለን።እውነቱ የፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ ያሸንፋል።የሆዳች ሁን ትልቅነት በቀሚሱ ፥ የጭንቅላታች ሁን ባዶነት በቆብ የሸፈናች ሁ፥የወገናች ሁ መገደል፥መታረድ፥መሰደድ፥ያለ ፍት ህ መታሰር፥መፈናቀል ምንም ያላላች ሁ የታሪክ፥የኃይማኖት፥የባህል፥የትውፊት፥የፖለቲካ ተመልካቾቻን ሆዳች ሁ ሲጎድል እና ወያኔ እንደማስቲካ አኝኮ ሲተፋቹ ያኔ ኢሳት ላይ ቀርባች ሁ ተገድጄ ነው ለልጄ ብዬ ነው ብትሉ ትርፉ ት ዝብት ነው።ክርስትናን ከምርጫ ዘጠና ሰባት አጣሪ እጅግ የተከበሩ እውነተኛ ሰው አቶ ፍሬህይወት ሳሙኤል ተማሩ።ክርስትና በቃል ሳይሆን በተግባር።ክርስቲያን ያልሆኑት ስ ቢዋሹ አይገርምም።የእግዚአብሔርን ስም እየጠሩ መዋሸት ልማታዊ ሰባኪ መሆኑ ግን ይደብራል።እውነት ነፃ ያወጣል።

  ReplyDelete