ሁለት ፈረሶች እንደነበሩ ተነገረ፡፡ አንደኛው እጅግ ለምለም በሆነ ሰፊ ሜዳ ላይ
ተሠማርቶ፣ ሲያሻው ደግሞ በግራ በቀኝ ገብስ ፈስሶለት፣ ሲጠማው የሚጠጣው ውኃ በሜዳው መካከል ኩልል ብሎ እየወረደለት፣ አውሬ
እንዳይተናኮለው ዙሪያውን በውሻ እየተጠበቀ ይኖር ነበር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሣር ዘር ለአመል ያህል ብቻ እዚህም እዚያም
በበቀለበት፣ ጭው ባለ ደረቅ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ ያገኛትን እየነጨ፣ ከዕለታት በአንድ ቀን ከደጋ የዘነበ ዝናብ በአካባቢው
ሲያልፍ የሚያገኘውን ጥፍጣፊ ውኃ እየተጎነጨ፣ ሌትና ቀን ምን ዓይነት አውሬ መጥቶ ይዘነጥለኝ ይሆን? እያለ በሥጋት ይኖር ነበር፡፡
ምንም እንኳን ሁለቱም ፈረሶች በኑሮ በማይቀራረብ ሜዳ ላይ በመከራና በቅንጦት
ተለያይተው ቢኖሩም የኑሮ ጥያቄ ግን አገናኝቷቸው ኖሯል፡፡ ያ እንዲያ በለመለመ መስክ ተሠማርቶ እምብርቱ እስኪነፋ ሆዱ
እስኪቆዘር እየበላ ሲተኛ ሲነሣ የሚውለው ፈረስ ‹‹ይኼ ሣር ያለቀ ዕለት፣ ይኼም ውኃ የነጠፈ ጊዜ፣ እነዚህም ውሾች እኔን
መጠበቅ ትተው የሄዱ ጊዜ፣ ይኼስ ገብስ የጠፋ ቀን ምን ይውጠኝ ይሆን? ያስ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡ ይኼ ጥያቄ
ምንጊዜም ይረብሸው ነበር፡፡
ያ በደረቅ ሜዳ ላይ እዚህም እዚያም የበቀለች ሣር እየነጨ ከርሱን ሲደልል የሚውለው
ፈረስ ደግሞ ‹‹መቼ ይሆን አልፎልኝ ለምለም መስክ ላይ ውዬ፣ ከፈሰሰ ውኃ እንደ ልቤ ተጎንጭቼ፣ ያለ ሥጋት አድሬ የሚነጋልኝ? ያ ቀን መቼ ይሆን?
ይል ነበር፡፡
እዚህ ሀገር ያለን ሰዎች በሁለቱ ፈረሶች ጥያቄ ውስጥ ወድቀናል፡፡ አንደኛው መስኩ
ለምልሞለት፣ ውኃው መንጭቶለት፣ ሥጋቱ ጠፍቶለት፣ ሕይወቱ ቀንቶለት የሚኖረው ሰው ጥያቄ ነው፡፡ እንዴት ሜዳው ላይ እንደደረሰ
አያውቀውም፤ ብቻ አንድ ቀን ተቀለጣጥፎም፣ ተጣጥፎም፣ ተለጣጥፎም፣ ራሱን ሜዳ ላይ አግኝቶታል፡፡ ለስንትና ስንት ፈረስ
የሚበቃውን መስክ ብቻውን ተሠማርቶበታል፡፡ አገር የሚያጠጣውን ወንዝ ብቻውን ይንቦራችበታል፡፡ ጥጋብን ከልኩ በላይ፣ ምቾትንም
ከመጠን አልፎ ቀምሶታል፡፡ ድህነትን ረስቶ የት መጣውን ዘንግቶታል፡፡ ግን ሥጋት አልለቀቀውም፡፡
ይኼ መሥመር የተበጠሰ ዕለት፣ ይኼ ሥርዓት ያለፈ ቀን፣ ከእገሌ ጋር የተጣላሁ ጊዜ፣
ቀን የዞረችበኝ ሰዓት፣ የተነቃ ለታ፣ ዕቁቡ የተበላ ጊዜ፣ ካርታው ያለቀ ቀን፣ መንገዱ የታወቀ እንደሆን፣ ሕግ የተቀየረ ቀን፣
ምን ይውጠኝ ይሆን? ያችስ ቀን መቼ ትሆን? እያለ ይጠይቃል፡፡ እየበላ ይሠጋል፣ እየጠጣም ይጨነቃል፤ አይቷል፣ ሰምቷል፡፡
ድንገት ለምለሙ ሜዳ ላይ ተገኝተው ድንገት ከሜዳው የጠፉ አሉና፡፡
አሁን ሆዱ ተቀይሯል፤ አንገቱ ተቀይሯል፤ እጁ ተቀይሯል፤ መቀመጫው ተቀይሯል፤ ማረፊያና መዋያው ተቀይሯል፡፡ ይህንን
ያጣ ዕለት ምን ይውጠዋል?
ያኛውም ፈረስ አለ፡፡ እንደ ዐርባ ቀን ዕድል ሆኖ የደረቀ መስክ ላይ ውሎ እንዲያደር የተፈረደበት፤ ቢሄድ ቢመጣ፣
ቢወርድ ቢወጣ ከዚያ መስክ መላቀቅ ያቃተው፡፡ መቼ ይሆን የእኔስ ሜዳ በሣር ተሞልቶ እንደነዚያ ሣር የምጠግበው እያለ ምኞት የገደለው፡፡
የእኔስ ወንዝ መቼ ይሆን ውኃ ሞልቶት ሳልጨነቅ የምጠጣው? እያለ ሃሳብ ያናወዘው፡፡ የእርሱ ቤት እየፈረሰች ከጎረቤቱ ዘጠኝ ፎቅ ሲበቅል
አይቷል፡፡ ስትተከል፣ ውኃ ስትጠጣ፣ አላያትም፡፡ እንዲሁ ብቻ ፎቋ በቀለች፡፡ ስትገዛ ያላያት፣ ፍንጥር ያልጠጣባት መኪና እንዲሁ
ሽው እልም ስትል አያት፤ እናም ምን ዓይነት ፈረሶች ይሆኑ ለዚህ የሚበቁት እያለ ይጠይቃል፡፡ ዝርያቸው ምን ቢሆን ነው? መልካቸውስ ምን ቢሆን ነው? የፈረስ ጉልበታቸውስ ምን ያህል
ቢሆነ ነው? ፍጥነታቸውና ቅልጥፍናቸውስ እንዴት ያለ ቢሆን ነው? ጌቶቻቸውንስ እንዴት አድርገው ቢያገለግሏቸው ነው? እንዲህ ለምለም መስክ ላይ
የለቀቋቸው? እኛም ስናገለግል ኖረናል፤ ጋሪ ስንጎትት፣ እህል ስንሸከም፣ ዕቃ ስናጓጉዝ ኖረናል፤ ጌቶቻችን ሲጋልቡን ኖረናል፤
ግን እነርሱ ምን ያህል ቢያስደስቷቸው ነው ይህንን ዕድል የሰጧቸው? እያለ ይጠይቃል፡፡
ለመሆኑ እነርሱ ናቸው ወደ እኛ የሚመጡት ወይስ እኛ ነን ወደ እነርሱ የምንሄደው? ለመሆኑ የኛን ድህነት ነው
ወይስ የእነርሱን ሀብት ነው የምንካፈለው? በርግጥ ከኛም የሄዱ አሉ፤ ከእነርሱም የሚመጡ አሉ? ይላል፡፡ አንዱ ሜዳ ላይ ተሠማርተን እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን መጋጥ ሲገባን
ለምን ሁለት ዓይነት ሜዳ ሆነ፡፡ አሁን እኛና እነርሱ እኩል ‹‹ፈረስ›› ተብለን እንጠራለን? እኛ ‹‹ሌጣ ፈረስ›› ነን፣
እነርሱ ደግሞ ‹‹ባለ ወግ ፈረስ›› ናቸው፡፡
ግን ይሁን፤ እሺ መቼ ይሆን እኛስ እንደነርሱ የምንሆነው? መቼ ይሆን ያለ ሥጋት ውለን የምናድረው? ለምለሙን መስክ ማን ይነካዋል፤
ላለው ነው ድሮም የሚጨመርለት፤ የኛ የድኾቹን መስክ ነው ለሀብታሞቹ የሚሰጡት፤ የድኾቹን ደረቅ መስክ ሀብታሞቹ የሚቀኑበትን ያህል
እኛ በእነርሱ ለምለም መስክ አንቀናም፡፡ ደግሞ አንድ ቀን ይመጣሉ፡፡ ‹‹ይህንን መስክ ለምለም ማድረግ እንፈልጋለን›› ይላሉ፡፡
እኛም ደስ ይለናል፡፡ የዘመናት ምኞታችን አይደል? መንገዱ ጠፍቶን እንጂ እኛም ለምለም ማድረግ እንፈልግ ነበርኮ? መንገዱን ያወቀው ሰው ሲመጣ ለምን እንቃወመዋለን፡፡
ግን ይቀጥሉና ሌላ ነገር ይሉናል፡፡ ‹‹መስኩን ግን ለምለም የምናደርገው ለእኛ እንጂ ለእናንተ አይደለም›› ይሉናል፡፡
ለምን? ለምን? እኛ ለምለም ሣር አይወድልንም? እኛ ለምለም የምናደርግበትን መንገድ ለምን አያሳዩንም? ባያሳዩንስ ለምን አይፈቅዱልንም? ባይፈቅዱልንስ ለምን አይተውንም? እንላለን፡፡ ይህ ግን ጥያቄ
ነው እንጂ መልስ የለውም፡፡ እኛም ጥያቄውን የምናውቀውን ያህል መልሱን አናውቀውም፡፡ ስንጠይቅም ‹‹ምላሽ›› እንጂ ‹‹መልስ››
የሚሰጥ አናገኝም፡፡
እኛም ከዚያ መስክ እንወጣለን፣ ወደሌላ መስክም እንዛወራለን፤ አሁንም ቅንጥብጣቢ ሣር እንፈልጋለን፤ ጥፍጣፊ ውኃ
እናስሳለን፡፡ ያ እኛ የነበርንበት መስክ ግን በአንድ ጊዜ ይለመልማል፡፡ ውኅው ጅረት ሆኖ ይፈስበታል፡፡ ይገርመናል፡፡ እኛ እዚያ
ሳለን፡፡ ውኃ አልነበረም፡፡ እንደ ወር በዓል ቀን ቆጥረን ነበር የምናገኘው፡፡ አሁን ግን ይንፎለፎላል? ለመሆኑ እኛ ምን ብለን መጠየቅ
ነበረብን? ይኼ ራሱ ሌላ ጥያቄ ይሆንብናል፡፡ መቼ ይሆን እኛስ እንዲህ ባለው መስክ ላይ የምንሠማረው? እንላለን፡፡ የማይሳካ ምኞት
እንመኛለን፤ የማይመለስ ጥያቄ እንጠይቃለን፡፡
እዚያም ቤት ሌላ ጥያቄ አለ፡፡ ፀሐይዋ እንደወጣች ትቀጥል ይሆን? ወንዙ እንደፈሰሰ ይቀጥል ይሆን? ነፋሱ እንደነፈሰ ይቀጥል ይሆን? ሣሩ እንደለመለመ ይዘልቅ ይሆን? እኔስ እንደተወደድኩና ሞገስ
እንዳገኘሁ እኖር ይሆን?
ሰውየው ስለ አውሮፕላን አነዳድ የሚገልጥ ማኑዋል አገኘና አውሮፕላኑን አስነሥቶ አበረረ፡፡ ገጹን ይገልጣል፤ የተጻፈውን
ይፈጽማል፤ አውሮፕላኑም ይበራል፡፡ በቀጣዩ ገጽ ላይ ምን እንዳለ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ገጹ ተገንጥሎ ቢገኝ ምን ማድረግ
እንዳለበትም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ብቻ ይገልጣል፣ ያነባል፣ ይነካካል፣ ይበራል፡፡ አውሮፕላኑ ተነሥቶ በሃያ አምስት ሺ
ጫማ ከፍታ ላይ ሲደርስ የመጨረሻው ገጽ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹ክፍል ሁለትን በክፍል ሁለት መጽሐፍ ይመልከቱ›› ይላል፡፡ ክፍል ሁለት
መጽሐፍ ግን የለውም፤ የት እንዳለም አያውቅም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበትም አልተዘጋጀም፡፡ ስለዚህም እንደወጣ መውረድ ጀመረ፡፡
ያውም በዝግታ ሳይሆን እየተምዘገዘገ፡፡
እናም እኛ በለምለም መስክ ላይ ያለን ፈረሶች፣ አንድ ክፉ ቀን መጥቶ ‹‹ክፍል ሁለትን በሌላ መጽሐፍ›› ቢለንስ? ምን ይውጠናል? ለመሆኑ ክፍል ሁለት የት ነው
ያለው? እስካሁን ያሳየን የለም፡፡ እኛ የምናውቀው የየዕለቱን ምዕራፍ ብቻ ነው፡፡ ያንን እናነባለን፣ በእርሱ እንኖራለን፣
ቀጣዩን ምዕራፍ አናውቀውም? ስለዚህም እኛም እንጠይቃለን? እንዲሁ እንዘልቅ ይሆን? ብለን፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት
ላይ የወጣ ነው
እኛ በለምለም መስክ ላይ ያለን ፈረሶች፣ አንድ ክፉ ቀን መጥቶ ‹‹ክፍል ሁለትን በሌላ መጽሐፍ›› ቢለንስ? ምን ይውጠናል? ለመሆኑ ክፍል ሁለት የት ነው ያለው? እስካሁን ያሳየን የለም ክፍል ሁለትን ለማግኘት የሠራዊት ጌታን ሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል አለበለዚያ በቆምንበት Pause ሆነን መቅረት ነው ወዳጄ
ReplyDeleteለምለሙ ሣር ላይ ላለ ሰው ጌታን የሙጥኝ ማለት አያዋጣም እንዴት ሆኖ፣ ምን ሰርቶ፣ ከሌላው በምን ተለይቶ እዛ እንደደረሰ ጌታምያውቃልና ስለዚህ ያንን ቀን /የሚመጣውን/ ከመጠበቅ በስተቀር።
DeleteThis is great! Gin min yadergal, Lemlem meda lay yalew feres ayanebewum! Gize yelewuma!
ReplyDeleteDon’t be foolish, he will read it. Do you know 1 to 5 groups? From 40 million adult people 8 million are part of ” Lemelem Meda Lay Yalew Feres “ so if you have four friend one of them is not your friend. He is the reporter of your day to day life.
Deleterely
Delete80 ሚሊዮን ከሚሆነው ህዝብ 16 ሚሊዮን የሚጠጋው ፡ ለምለም ሜዳ ላይ ነው ያለው በለኛ!
Deleteግን ስለ ኢትዮጵያ መፃፍህን እርግጠኝ ነህ? ተምታቶብህ እንዳይሆን፡፡
The second chapter will open soon, both hours will die.
ReplyDeleteI apologize for the mess spell word, I feel so bad because I wrote HOURS instead of HORSE. I don’t mean I am a perfect person but I have to make sure before I post it. I know many people got confused by my mistake but it happened ones. I will give attention for the future. This is my first time when I made a mistake so I hope everybody will give me mercy. From the bottom of my heart I ask all Ethiopian people apologize for my mistake. I all follower know that English is not our first languche so people will accept my apology. I feel embrace when I read it. I love you so much Dani I ask you direct apology for my mistake I will correct for the future.
Deleteood,good,good. How hours will die? Come to us we will teach you how to spell horse. Please call us to register class. Our Address is Merkato next to Tana Market. Phone 0911234567.
DeleteI love it. It is the best advertizing method. You guys are so funny.
DeleteMelis yemisex yisxen . Mirx hasab Thank u
ReplyDeleteስንጠይቅም ‹‹ምላሽ›› እንጂ ‹‹መልስ›› የሚሰጥ አናገኝም፡፡yes
ReplyDeleteI didn’t get it free, I fought 17 years to get the best grass. Talking is not the solution; if you have power you can fight me. To rich this destination I lost my mother, brother, sister and best friends. Now you want to share without paying any price. Shame on you and don’t mean on me.
ReplyDeleteSo, in your little mind being woyane soldier gives you the right to own the whole country for yourself and treat the rest as slaves, is that what they taught you in your camp. God, your are just stupid and dangerous beyond words.
Deleteere bakih?! Demihin afiseh agegneh?... denez
DeleteSorry and Shame on you Mr. X. Are you fought to get the best grass? One day you will get the consequences with all your family.
DeleteI think it is fact the Anonymous person didn’t lie. He/She scarified a lot to get this place. However we are an Ethiopian so we have to share our country resource equal. They always think they came into this power by fight so they expect someone to fight them to lose their position. We have to teach them war is not a solution. In addition that we have to give them good evidence, that we will not revenge them. When we are aggressive to them, they always scare to lose their position. Again the Anonymous person wrote all facts so we have to come up with new idea to convince them. God bless you Dani.
DeleteBring a chair bring a chair to me
DeleteI can sit, you can sit, sing along with me.
I have best grass; I don’t want sing with you.
I know it, I know it, that’s why I begging you to sing.
You were foolish, you were foolish, I am not foolish for you.
If you know it I fought seventeen years for this.
You fought seventeen years but you have been eaten twenty two years so far
I know it; I know it waiting me until I die.
You fought 17 years.The ignorant mind, with its infinite afflictions, wrath, and evils, is rooted in the three poisons. Greed, Anger, and delusion.
DeleteWe will die one day but if they will work like Mandela we will thank them forever or if the continue like Meles, they thank each other. All of thier HERO, it is fact all Ethiopian ENEMY. All their ENEMY , it is fact all Ethiopian HERO.
ReplyDeleteስንጠይቅም ‹‹ምላሽ›› እንጂ ‹‹መልስ›› የሚሰጥ አናገኝም፡፡ ...What an impressive article!...ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል…ስምን ኤልሳዕ የተባለ መልአክ አወጣው፡
ReplyDeletethanks to much D/Dani i always Search your blog and read your articles, it is a good lesson , your lesson shape my attitude and personality ,so don’t give up. i always wish you almighty god give you along life with health
ReplyDeleteThis is true and the way most of us live in this country deprived of even our basic needs.
ReplyDeleteThanks Dani
Minew wegenoch yeEthiopia Amlak yiferdal eko melkam ken endemimeta tesfa adrigu hulum yistekakelal!
ReplyDeleteዶሮ ማታ ፡ ዶሮ ማታ
Deleteእንኳን ዶሮ ፡ የለም ሽሮ
The second chapter will open soon
ReplyDeleteInfact, these kinds of ideas are very frustrating ,but we hope
ReplyDeleteour future would be good with the help of God.
thanks for reminding us to also think this way.
thanks
ReplyDeleteThank you so much Dani.the way express your concept always makes my heart to satisfy.it is an alarm to those who are in "lemelem meda" to gives concern for "chewe balew derek meda lay lalut".yesema yasetewel ,asetewal yetegeber.
ReplyDeleteay d/n dsaniel assabu betam yegermal astemarim new ente endalkew awuroplan mabrerun chelo mawredun kalchalubet adegaw yekefa new mihonew lek ende kefel hulet anway enamesegenalen egziabeher yebarkeh
ReplyDeleteመልስ እምናገኝበት ቀንማ እሩቅ አይሆንም!
ReplyDeleteዳንሾ፣ አቀራረጽህ ግሩም ነው። "የሁለት ፈረሶች ጥያቄ" ስትል መሳ ለመሳ የሆኑ ይመስላል። የተመቸው ፈረስ ጥቂቶችን ሲወክል፣ ያልተመቸው የሚወክለው ብዙሐኑን ነው። ብዙሐኑ እስከ መቸ እንዲህ ይቀጥላሉ? ጥቂቶቹስ እስከ መቸ እንዲህ ይቀጥላሉ? አንድ ቦታ ላይ አንድ ነገር መፈጠር ይኖርበታል።
ReplyDelete‹‹ክፍል ሁለትን በክፍል ሁለት መጽሐፍ ይመልከቱ››
ReplyDeleteለመሆኑ እነርሱ ናቸው ወደ እኛ የሚመጡት ወይስ እኛ ነን ወደ እነርሱ የምንሄደው? ለመሆኑ የኛን ድህነት ነው ወይስ የእነርሱን ሀብት ነው የምንካፈለው? በርግጥ ከኛም የሄዱ አሉ፤ ከእነርሱም የሚመጡ አሉ?
This is absolutely true view of the situation Ethiopian people's life. Dani you are the only one writer who dared to speak out the real situation in my country. However, even though the gov't authorities have eyes to see or to read,have ears to listen,they are not willing to change this situation since all of them belong to the same garbage mind. They have 0% their country's love and people's respect.I hope there will be one day when the tear of the hopeless Ethiopian people reaches to God and things will be reversed.
ReplyDeleteእግዚአብሔርማ ጥረህ ግረህ ፡ እንጀራህን ብላት! ብሏልና ፡ አልቅሶ መብላት የለም።
Deleteክፍል 2 ቀላል ነው።
ReplyDelete1ኛ. ማስተዋል- የሚያስተውል አለቃ አወዳደቁ ያምራል፣ የሚረከበው ጀግና ያገኛል። የማያስተውሉና ነገን የጠፋበቸው ሳያስቡት ገጹ (መሪው) ያልውና ከላይ መፈጥፈጥ፣ እስር ቤት ተሰልፎ መግባት፣ በጠባሳ ታሪክ መወከል... ሌሎችም
2ኛ. ታሪክን መረዳት- ለምለሙን ሜዳ ብቻቸውን ለመኖር የሞከሩ ነበሩ፣ ግን ከንቱ ሆነው ባልጠበቁትና በረሱት ዘመን ውረደት ገጥሟቸዋል፣ እናም ያለፈውን የሚረዳ ለምለሙን ሜዳ በጋራ ይፈጥራል
3ኛ. እግዚአብሔርን በመፍራት ይቅርታ መጠየቅ. እግዚአብሔርን የሚፈሩ ከስህተታቸው ይማራሉ፣ የበደሉትንን ሁሉ ይቅርታ ይጠይቃሉ። ካለፈው ጥፋታቸው በይቅራታና በመካስ ይቅርታ ያገኛሉ። አሁንም የበደሉ መውረድ ሳይመጣ እግዚአብሔርን በመፍራት እግዚአብሔርንም የበደሉትን ህዝብ ይቅር ይበሉ።
የሰው አለቃ እንጅ የጊዜ አለቃ የለውም
እኩል የሐብት ክፍፍል ችግር ወቅታዊ አይመስለኝም፡፡ በታሪካችን መሬት በጥቂቶች እጅ፣ የፖለቲካ ስልጣን በተመረጡ ጥቂቶች መዳፍ፣ የመማር እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች በችሮታ መልክ ሲሰጡን ኖረናል፡፡ እንደውም የኢትዮጵያ የህዝቧ ታሪክ ከ ኢትዮጵያ ታሪክ ይለያል ብዬ የማስብበት ዋነኛ ምክንያት ብዙሀኑ የሐገሪቱ ህዝብ ለሀብቱ እና ሊያገኘው ለሚገባው ጥቅም ባይተዋር ሆኖ በመኖሩ ነው፡፡ ተራው ህዝብ ግዴታውን ከመወጣት ባሻገር መብቱን አያውቀውም፣አይጠይቀውም፡፡ የአገሪቱን ነጻነት እና ስልጣኔ ለዝንት አለም አስከብሮ የኖረው ሕዝብ ከራስ ጥቅም በነጻ መልኩ ነው፣ ምክንያቱም ተጠቃሚዎቹ ራሳቸውን በአረንጓዴ መስኩ ላይ ያስቀመጡት ወገኖቹ ናቸው፡፡
ReplyDeleteለዚህ ግልጽ ብዝበዛ መፍትሄው ትምህርት ነው፡፡ እስኪ አስቡት መሐይምነት 80 በመቶ በሆነበት አገር ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ቢኖር ነው የሚገርመው፡፡ ወገንን መርጦ መጥቀም እና በጥቅም መተሳሰር ባህል በሆነበት አገር አዋቂነት ዋጋ ባያጣ ነው የሚገርመው፡፡ ቆስለናል፣ ሞቶብናል አገር “ነጻ አውጥተናል” ስለዚህ የበለጠ ጥቅም ይገባናል ማለት ወደ አማርኛ ሲተረጎም እኮ ‘’አገሪቱ በ ጥረጣችን ያቆምናት ኩባንያ ናት ስለዚህ የትርፍ ተካፋይ መሆን የሚገባን እኛ ባለአክስዎኖቹ ነን ማለት ነው’’፡፡ ምልባት ለዛ ይሆናል ሰዎቹ አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ምንምነኛ ዜጋ አለ ያሉት፣ ማለቴ ባለ አክሲዎኖቹን እና አክሲዎን አልባዎቹን ቆጥረው፡፡
ግብር አጭበርብሮ ምጽዋት በሚሰጥ፣ የእርዳታ እህል ሽጦ ፎቅ ለመስራት ወደኋላ በማይል፣ የሌላውን ሌብነት ለመቃወም ራሱ ሰርቆ ከአገር የሚጠፋ፣ ስርቆት በጠበጠን እያለ የሌባ ዘመዱን የስርቆሽ ንብረት በሚበዘብዝ ማህበረሰብ ውስጥ የሐብት ክፍፍል ፍትሀዊ ቢሆን ተአምር ነው፡፡
የህግ የበላይነት የማይተካ ሚና አለው፡፡ የፍትህ ስርአቱ ጠንካራ እና ለህዝብ ጥቅም የቆመ ቢሆን ኖሮ ደሃ ማልቀሻ እና የመፍትሄ ተስፋ ይኖረው ነበር፡፡ እስከዛ ግን እባካቹ፣ በናታቹ አትበዝብዙን ከማለት በቀር ምን እድል አለ? ይዘገንናል እኮ ለብዙ ትውልድ በመብት እና በህግ ሳይሆን በመተዛዘን መኖር? በመከባበር ሳይሆን በመፈራራት መዝለቅ?
እና ፍትሐዊ የሐብት ክፍፍል ለማምጣት መሰረቱ የለንም ነው የኔ THEORY ለዚህ ደገሞ ሁላችንም (ያሉትም የሞቲትም) ተጠያቂ ነን፣ ባህል ተጠያቂ ነው፡፡
Thanks Dani for sharing your eagle view ideas. It will be much better if you incorporate some indications how the horses can came to agreement to live together. Stay blessed
ReplyDelete‹‹ክፍል ሁለትን በሌላ መጽሐፍ›› ቢለንስ? ምን ይውጠናል? ለመሆኑ ክፍል ሁለት የት ነው ያለው? እስካሁን ያሳየን የለም፡፡ እኛ የምናውቀው የየዕለቱን ምዕራፍ ብቻ ነው፡፡ ያንን እናነባለን፣ በእርሱ እንኖራለን፣ ቀጣዩን ምዕራፍ አናውቀውም? ስለዚህም እኛም እንጠይቃለን? እንዲሁ እንዘልቅ ይሆን? ብለን፡፡
ReplyDeleteጠያቂ በዛ ፡ መልስ ሰጭ የለም፡፡
Deleteሁላችንም የቁም እንቅልፍ ላይ ነን ፡ ምን ያነቃን ይሆን ? ጦሙን እያደረ ፡ "ደህና ነኝ" የሚል ሰው የሚኖርበት ምድር!
Dn Daniel Eyedeberegn meta, lemehonu qena neger maseb sinchil lemndnew metfo metfowin bicha yemnasbew. Posetively hulum mekeyer kememoker???????
ReplyDeletethanks to much D/Dani i always Search your blog and read your articles, it is a good lesson , your lesson shape my attitude and personality ,so don’t give up. i always wish you almighty god give you along life with health
ReplyDeleteልብ ያለው ልብ ይበል: በተለይ በስልጣን ላይ ላላችሁና ለስርአቱ ደጋፊዎች ምክንያቱም ሁሉም ኢትዮጵያውያን እኩል የሀገሪቱን ሀብት የመጠቀም መብት አላቸውና::
ReplyDelete