Wednesday, June 4, 2014

ያልሰማኸው ነገር

ይሄ ልጅ ለምን እዚህ እንደመጣ ግልጽ አልሆነላቸውም፡፡ ከሃያ ዓመት በኋላ ነው እንዲህ ቤት ውሎ ቤት ሲያድር ያዩት፡፡ ሥራ አለው፣ በትምህርት ተወጥሯል፤ ንግዱን እያጧጧፈ ነው ሲባል ነበር የሚሰሙት፡፡ በቤቱ ውስጥ የተሻለ የተማረ ሰው እርሱ በመሆኑ ሠርግና ልቅሶ ለምን አልመጣህም ብሎ የሚወቅሰው ቤተ ዘመድ አልነበረም፡፡ አንዳንዶቹም ስሙን ሰምተው እንዲሁ ያደንቁታል እንጂ አይተውት አያውቁም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድሮ በልጅነቱ እንዳዩት ናቸው፡፡
አሁን ግን ነገር ዓለሙን ሁሉ ትቶ እዚህ አያቱ ቤት መዋል ማደር ከጀመረ ሰነባበተ፡፡ አያቱ ደግሞ ይሳቀቃል ብለው ለምን መጣህ? ሥራና ትምህርትህንስ የት ተውከው? ብለው መጠየቅ ከብዷቸዋል፡፡ እጅግ በጣም የገረማቸው ደግሞ መቀመጫው ላይ ወስፌ እንደተተከለበት ሁሉ ለአፍታ ቁጭ ማለት የማይችለው ሰውዬ ደርሶ ቀኑን ሙሉ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ሲቆዝም መዋሉ ነው፡፡


አንድ ቀን ግን ደፍረው መጠየቅ እንዳለባቸው ወሰኑና ወደ እልፍኛቸው አስጠሩት፡፡ ‹‹ልጄ በደኅህ ነው? እንደዚያ ለምግብ እንኳን ጊዜ የለኝም የምትለው ሰውዬ ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለህ የምትውለው›› አሉና ጠየቁት፡፡ አንገቱን ደፍቶ መሬቱን በመነጽሩ ጫፍ እየጫረ ዝም አላቸው፡፡ ‹‹የሆንከው ነገር አለ? ምናልባትኮ ለእኔ ቀላል ይሆናል፡፡ መቼም የዛሬ ልጆች ትንሹን ነገር ሁሉ አክብዳችሁ ነው የምታዩት፡፡ ሰውዬው እህል ሊሸከም ተጠርቶ ዋጋ ሲነጋገር ‹ለመሆኑ ሸክሙ ከባድ ነው ቀላል?› ብሎ ቢጠይቅ አሸካሚው ሰው ‹እንደ ተሸካሚው ነው› ብሎ መለሰለት አሉ፡፡ነገር እንዳያያዝህ ነው››
‹‹አያቴ ለአንተ ምንም አያደርግልህም፤ ምናልባትም ደግሞ አያስደስትህም›› አላቸው ጭኑን በመዳፉ እየመታ፡፡
‹‹ሲያደርጉት ነበር እንጂ ይህንን ማሰብ፤ ከሆነ ወዲያ መናገር ምን ያከብዳል››
‹‹ከወንድሜ ጋር ተጣላን› አላቸው ቀለል አድርጎ››
‹‹እና ወንድምና ወንድም መጣላቱ አዲስ ነገር ነው እንዴ››
‹‹ጠቡ ከበድ ያለ ነው››
‹‹ማቃለሉን ትታችሁ ማካበዱን እንዴት ቻላችሁበት››
‹‹መጀመሪያም የከበደ ነበር››
‹‹እንዴት እንዴት ሆኖ››
‹‹አንተኮ ሁሉን ታውቀዋለህ አያቴ፤ ዝም ብለህ ነው የምታስለፈልፈኝ››
‹‹ዕውቀት ብዙ ዓይነት ነው ልጄ፡፡ አሟልተህ የማታውቀው አለ፤ አዛብተህ የምታውቀው አለ፤ ጨርሰህ የማታውቀው አለ፤ የምታውቀውም ነገር አለ፡፡ ለመሆኑ ምንድን ነው ያጣላችሁ?››
‹‹እስከ ዛሬ ማንነቱን አላውቀውም ነበር፤ በእኔ ላይ ሲጫወት የኖረ መሆኑን አላውቅም ነበር፤ ሲጨቁነኝና ሲበድለኝ የኖረ፣ እንዲህ ሆኜ እንድቀር ያደረገኝ መሆኑን ዛሬ ዐወቅኩት›› አላቸው እያንገፈገፈው፡፡
‹‹ሌላስ ያወቅከው ነገር የለህም›› አሉት ጋቢያቸውን ከራሳቸው ወደ ትከሻቸው ወረድ እያደረጉ፡፡
‹‹ታላቅ ነኝ ብሎ ስንት ስቃይ ሲያደርስብኝ ነው የኖረው፡፡ ይደበድበኝ ነበር፤ ይቀማኝ ነበር፣ ይንቀኝ ነበር፣ ጉልበቴን ይበዘብዝ ነበር፤ ምርጥ ምርጡን ለራሱ ብቻ ይወስድ ነበር፤ ስሜን እንኳን በትክክል አይጠራኝም ነበር፤ ለራሱ በሚስማማው የማሾፊያ ስም ነበር የሚጠራኝ ፡፡››
‹‹ይህ ሁሉ ሲሆን ለመሆኑ አንተ ነበርክ››
‹‹የተወሰነው ደርሼበታለሁ፣ ሌላውን አንብቤያለሁ፣ ሌላውን ደግሞ ከሰው ሰምቻለሁ››
‹‹መልካም ይህንን ብቻ ነው የነገሩህ ሌላ ነገር አልነገሩህም፤ ላንተ ያደረገልህን ነገርስ አልነገሩህም፤ አንተ በእርሱ ላይ ያደረግክበትን ነገርስ አልነገሩህም?››
ዝም አለ፡፡
‹‹አየህ የምንሰማውና የምንናገረው የምንፈልገውን ብቻ ከሆነ ችግር ነው፡፡ ወይ ጨርሰን አለመስማት አለማየት ነው፡፡ እንሰማለን እናያለን ካልን ደግሞ ሁሉንም ማየትና መስማት ነው፡፡ የዛሬ ልጆች ችግራችሁ መርጣችሁ ነው የምታዩትና የምትሰሙት፡፡ በከፊል ሰምታችሁ በሙሉ ትፈርዳላችሁ፣ በጥቂት ዐውቃችሁ በብዛት ትደመድማላችሁ፤ መርጣችሁ ሰምታችሁ ሳትመርጡ ታወግዛላችሁ፡፡ ስማ ልንገርህ፤ አንተምኮ ብዙ ነገር አድርገህዋል፡፡ በድንጋይ መተህዋል፤ ደብተሩንና መጽሐፉን ቀዳደህበታል፤ የሚያጠናበትን ክፍል በድንጋይ እየደበደብክ ከሠፈሩ እንዲለቅ አድርገህዋል፡፡ ስንት የለፋበትንና የደከመበትን የሥዕልና የቅርጻ ቅርጽ ሥራውን ድምጥማጡን አጥፍተህበታል፡፡ ይህንንስ አልነገሩህም፡፡ አንተ ምንም ሳታጠፋ ከመላእክት ጋር ነው የኖርከው አሉህ? አንተ ተመታህ እንጂ አልተማታህም፤ ተሰደብክ እንጂ አልተሳደብክም አሉህ? እርሱስ ላንተ ያደረገልህ ነገር የለም? አላስተማረህም? የእናት የአባታችሁን ርስት ለመጠበቅ ደም አልከፈለም? አንተን የሠፈር ጎረምሶች በተተናኮሉህ ቁጥር የግንባር ሥጋ ሆኖ አልመከተልህም? በክፉው ቀን አዝሎህ ለስንት ቀን የተጓዘበትን፣ በረሃብ ቀን አንተን አስቀድሞ ያበላበትን፣ ይህንን አልነገሩህም፣ አልጻፉልህም?››
ዓይኑን ከግራ ቀኝ እያንከባለለ ያያቸው ጀመር፡፡
‹‹ሴትዮዋ ጆሮዬ ታሟል አልሰማም ብለው ከዘመድ ተጠግተው ይኖሩ ነበር አሉ፡፡ አንድ ቀን ታድያ ዘመዶቻቸው ቡና እየጠጡ ያሟቸዋል፡፡ አልሰማም ብለዋልና ምንም ነገሩ ቢያበግናቸው ዝም አሉ፡፡ ሐሜቱ እየቀጠለ ሲሄድ ግን አልቻሉምና ‹‹ምነው እናንተ፣ ሳልሞት በቁሜ ታወራርዱኛላችሁ›› ብለው ተናገሯቸው፡፡ ሰዎቹም ደንግጠው ‹እማማ አልሰማም አላሉም እንዴ?› አሉና ጠየቋቸው፡፡ ሴትዮዋም ‹ክፉ ክፉውንማ እሰማለሁ› አሉ ይባላል፡፡ እናንተም ክፉ ክፉውን ብቻ ነው እንዴ የምትሰሙት፡፡ ዝንጀሮ የራሷ ጠባሳ አይታያትም እንደሚባለው እናንተስ የሠራችሁት ስሕተት የለም?
‹‹ልጄ የተነገረህን ተወው አልልህም፤ እንዴ ሰምተህዋልና፡፡ ነገር ግን ያልተነገረህን ፈልግ፡፡ ያልተነገረህ ብዙ ነገር አለ፡፡ ስለወንድምህ ያልሰማህው ብዙ ነገር አለ፡፡ ደግነቱንና መልካምነቱን የነገረህ የለም፤ ጥፋቱንና ድክመቱን ግንቅመም እየጨመሩ በደንብ አስጨብጠውሃል፡፡ ጎዱህ እንጂ አልጠቀሙህም፡፡ እኛ ድሮ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሂሳብ ስንሠራ ‹ተንጠልጣይ ሂሳብ› የሚባል ነገር ነበር፡፡ ሳይወራረድ፣ ሳይዘጋ እንዲሁ ከዓመት ዓመት ሲንከባለል የሚኖር ሂሳብ ነው፡፡ የእርሱ መዝጊያ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ውሳኔ ነው፡፡ በውሳኔ ይዘጋል፡፡ ያለበለዚያማ የርሱ አለመወራረድ አንሶ የቀጣዩን ዓመት ሂሳብም ይበጠብጠዋል፡፡ ያልተዘጋ ቁርሾም እንዲህ ነው፡፡ አልዘጋ ካለ ወስኖ መዝጋት ነው፡፡ ከዚያ ወደፊት መሄድ ነው፡፡ ወደማትቆጣጠረው ትናንት ሄዶ መከራ ከማየት ወደምትቆጣጠረው ነገ መሄድ ይሻልሃል፡፡
‹‹እኔ ልምከርህ፤ የሰማኸውን ብቻ ሰምተህ አትፍረድ፤ ያልሰማኸውን ደግሞ ፈልግ፡፡ አንዳንዴም ከሰማኽው ያልሰማኸው ይበልጣል፡፡ የለም ብለህ አትደምድም፤ ቢኖር ትደነግጣለህ፤ አለ ብለህ ባይኖር ግን ምንም አትሆንም፡፡
‹‹ልገድለው እያሰብኩ ነበር፡፡ መንገድ እየፈለግኩ ነበር፤ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነበር፡፡ አተረፍከኝ፡፡ እስኪ እውነትም ያልሰማሁት ነገር ካለ ልፈልገው፡፡ አሁን እንኳን አንተ ብዙ ያልሰማሁትን ነገር ነገርከኝ፡፡ ለካስ ያወቅኩ መስሎኝ ባላወቅኩት ነው ልፈርድ የነበረው››
ያን ምሽት እዚያ ቤት አላደረም፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡

52 comments:

 1. <> ቃለ ሂወት ያሰማልን ዲ.ዳንኤል መካሪና አስተዋይ ልቦና ይስጥልን

  ReplyDelete
 2. May God bless you, Dani. It is really a great lesson to two Ethiopian brothers, living in two regions, i.e. I and my brother.
  Let me go out in search of the good deeds which I haven't heard so far about him. I am just going. I hope I will be back with confessions. See you.

  ReplyDelete
 3. abet mastemar endi new enji yebel d/n dani belogehen manbeb kejemrku 3 amet honognal hulem eketatelalehu tsufochehen bewenet betam lewetewegnal asteway argewegnal berta e/r yabertah.

  ReplyDelete
 4. dani semonun be andand keleloch lay yeneberewn alemeregagatena betebet astaweskegn be universitiwoch wust yehonewen hulu sasebew tsufehem temesaselebegn endi honen semtew u u u u u tebale ewne5tu sitay yehonew hulu ..... ketel berta!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. Mekari ena Asteway abat aystan . Medhanit alem edmehn yabzalh

  ReplyDelete
 6. እኔ ምን እላለሁ?... እግዚአብሔር አንተን ያበረታልን ....

  ReplyDelete
 7. አስተዋይ የሚያደርግ መካሪ አያሳጣን

  ReplyDelete
 8. ለካስ ያወቅኩ መስሎኝ ባላወቅኩት ነው ልፈርድ የነበረው
  ቃለ ሂወት ያሰማልን ዲ.ዳንኤል መካሪና አስተዋይ ልቦና ይስጥልን
  06/04/2014@11:16

  ReplyDelete
 9. ዳኔየ፤ ጽሑፍሕ ለብዙ ሰው የገባው አልመሰለኝም። አልያም የጤሱ ሽታ አልሸተታቸውም ማለት ነው። የድንግል ልጅ ሰምተው፤ተመክረው ፤የቀና ልቦና ቡሩህ ዐይን እንዲገልጥ እንጸልይ ። አሜን
  በርታ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Endi Yelale :--- Yemekerakeregn mane new? wedena yekereb :: ESAYAS 50:8

   Delete
 10. There are two regions (brothers) in Ethiopia, there is a written and a verbally told single story that could have the two brothers fight against each other, hate each other, a single story that has no benefit, but z true brother says no this is not z only thing done to me but also z good ones and decides to love his brother than hating him.......kezam yezan ken bet aladerem......... Abet mn ale egziabhair yihn baderegew!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. Wow no word to say .thank you dn

  ReplyDelete
 12. This can a big lesson for those of who are taking history in the wrong way by people who mis gaied us just like about King Menelik the true leader of Ethiopia. I hope we will read and study more of the truth than just rumor with out evedence.

  ReplyDelete
 13. There's two sides of a coin.

  ReplyDelete
 14. እግዚአብሔር መልካሙንም ለመስማት ልቦናችንንም ጆሯችንንም ይክፈትል፡፡በጣም የሚገርመኝ ከላይ እስከ ታች ክፉውን እንጅ መልካሙን አለመናገር የጎዳንና የጎዳናቸው ብዙ ናቸው፡፡ ቃለ ሕይዎት ያሰማልን ዳንየ፡፡

  ReplyDelete
 15. ...ችግራችሁ መርጣችሁ ነው የምታዩትና የምትሰሙት፡፡ በከፊል ሰምታችሁ በሙሉ ትፈርዳላችሁ፣ በጥቂት ዐውቃችሁ በብዛት ትደመድማላችሁ፤ መርጣችሁ ሰምታችሁ ሳትመርጡ ታወግዛላችሁ፡፡...ለራስ እንደሚስማማ አድርጎ መተርጎም በቋንቋ አለመግባባት (እንደ ባቢሎን ሰዎች)

  ReplyDelete
 16. ወደማትቆጣጠረው ትናንት ሄዶ መከራ ከማየት ወደምትቆጣጠረው ነገ መሄድ ይሻልሃል፡፡

  ግዜክስ

  ReplyDelete
 17. ወንድሜ እግዚአብሔር ይባርክህ እድሜና ጤናውን ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 18. It is Really a Good View God Bless Ethiopia Than You Dani

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ እግዚአብሔር ይባርክህ እድሜና ጤናውን ይስጥህ የነገር ደሃ ከሚያሳድጉ ይጠብቅህ

   Delete
 19. Endi algen :-- Yematsedeke qerbe negn kenese gara yemekeraker mane new ?? ESAYAS 50:8

  ReplyDelete
 20. ዲ/ዳ ቃለ ህይወት ያሰማልን ለኛም ልቦና ይስጠን ቃልህን የምንጠቀምበት ያድርገን

  ReplyDelete
 21. ወንድሜ እግዚአብሔር ይባርክህ እድሜና ጤናውን ይስጥህ የነገር ደሃ ከሚያሳድጉ ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 22. ወንድሜ እግዚአብሔር ይባርክህ እድሜና ጤናውን ይስጥህ የነገር ደሃ ከሚያሳድጉ ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 23. ቃለ ህይወት ያሰማልን በእውነት
  ቆም ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል

  ReplyDelete
 24. I real appreciate your effort. And the nominees are all important to this country and the world at large. I a more inlined to Dr. Mina Hiruy, for he has all rounded personality and life long effort to move the country forward. His struggle for child right, helping the poor for their access to education from primary to university level, building schools and universities, his effort for urban reform, development and implementation of vocational training, leading environmental moves in the country and paper presentations for policy conferences and initiatives for business development in Ethiopia and his willingness and cooperativeness specially to work and help the poor makes him outweigh over the other.

  ReplyDelete
 25. ውድ ዳንኤል፣ ትልቅ ሥራ እየሠራህ ነው፤ በርታ። እንደ አጋጣሚ ነው ድረገጽህን ያገኘሁት፤ ከንግዲህ እከታተላለሁና አንተም በርታበት። ዘመን ካለፈ በኋላ እንዳይጸጽትህ ሳትፈራ እውነቱንና ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅመውን ሁሉ ጻፍ ለጥፍ። እግዚአብሔር ይጠብቅህ። ቶለሳ ከአሜሪካ

  ReplyDelete
 26. Hi, Dani I like it so much however the two brothers have different languche and alphabet. At the moment you wrote in Amharic for Amara Ethiopian. To get his brother Oromo attention you have to write in Latin. They have the same mother, her name is Ethiopia but they don't speak, think and write the same languche because devil divided them to get power, If they become one then devil will lose soon so he always divide them. Thank you so much for your effort.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለአንድነት እና ለመፋቀር የልብ እንጂ የቐንቐ ወጥነት ያስፈልጋል እንዴ? ቢያስፈልግስ ይቻላል? ቐንቐችን አንድ ሆኖስ ያውቃል እንዴ?ደግሞስ የአንድ ታላቅ እትዮጲያዊ ቐንቐ ተናጋሪ ሌላውን ታላቅ ቐንቐ አያውቅበትም ማለት ይቻላል እንዴ? አማርኛስ የአንድ ብሔር ብቻ ቐንቐ ሆኖ አለመወለዱ እና አለማደጉ ተደርሶበት የለም እንዴ? ለአንድነት አንድ ቐንቐ ካስፈለገ ያ ቐንቐ ፍቅር አይደለም እንዴ? ቅኔው ይገባኛል ግን የሰው ልጆችን ቐንቐ የቀላቀለው ሰይጣን ሣይሆን እግዚአብሄር ነው፣ እንደው ለነገሩ ማለቴ ነው፡)

   Delete
 27. Hooooooooo Dani, We have been grown up by listening false statement. It is not easy to change our mind with one article. However I will pass your idea to my son. My dad, Mom and teacher learn from this government, and then they always told me about my brother bad work, so I always hate him because of their false statement. It is not easy to forget in instant but I will try to love all Ethiopian as a brother. Please pray for me.

  ReplyDelete
 28. ወደማትቆጣጠረው ትላንት ሄዶ መከራ ከማየት ወደምትቆጣጠረው ነገ መሄድ ይሻላል፡፡


  ReplyDelete
 29. ችግራችሁ መርጣችሁ ነው የምታዩትና የምትሰሙት፡፡ በከፊል ሰምታችሁ በሙሉ ትፈርዳላችሁ፣ በጥቂት ዐውቃችሁ በብዛት ትደመድማላችሁ፤ መርጣችሁ ሰምታችሁ ሳትመርጡ ታወግዛላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 30. ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል፤
  እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ እውነትም ያጣነውና የተቸገርነው በዋናነት ይህን ይመስለኛል፡፡ ያደግንበት ማኅበረሰብ፤ የተፈጠሩብን የውስጥ እና የውጭ ተጽእኖዎች በሙሉ በጎ በጎውን እንድናይ ያደረገን አይመስለኝም፡፡ ውስጠታችንም ለዚህ የተዘጋጀ አይመስለኝም፡፡ በእውነቱ ከባድ አለመታደል ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬም በእንዲህ አይነት አስተሳሰብ እንድንጓዝ እና እንድንመራ ከፉከራ በዘለለ መስራት ይኖርብናል፡፡ በድጋሜ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ የዘወትር አንባቢህ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 31. ዲ/ን ጌታየ ዘላሊበላJune 7, 2014 at 5:45 PM

  ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ መባል አዝማች ሆ•ልና ይቅርታ ጠይቂ ልጀምር፡፡ ድሮ ‹‹ነገርን አዳምጦ እህልን አላምጦ›› ይባል ነበር፡፡ ነገር መነሻ ምንጭ አለው፤ መገስገሻ ልዩ ክዋኔ አለው፤ መድረሻ ትእይንት አለው፡፡ ምግብም እንደቀረበ አይበላም የምግቡ ጠባይ፤ አሰራር፣ የተሰራበት ቅመማ ቅመም፣ የተሰራበት ቀን፣ የተሰራበት ምክንያት መለየት አለበት፡፡ ሁሉም ምግብ ለሁሉም ሰው እኩል አይስማማምና፡፡ ለአንዱ ሥጋ የምግብ ምርጫው ሲሆን ለአንዱ አባቱን የገደለበት ያኸል ይጠላዋል፣ ለሌሎች የሰውነት ቅርጻቸው እንዳይበላሽ ወይንም (ዳይት) ላይ ስለሚሆኑ አይበሉም፣ ሌላው የዘወትር ምርጫው ቆሎ ብቻ ይሆንና ሌላ ምግብ አይስማማውም ……. ምግብ እንደየ ምርጫ ይሠራል፣ እንደየ ምርጫ ይበላል፡፡ በምርጫ ሲሆን ይስማማል፡፡ ምግብ በመጠን ይበላል፤ መጠጥ በመጠን ይጠጣል ይህ ካልሆነ ሲበዛ በሽታ ነው፡፡ ለዚህ ነው አበው ‹‹ዘበልዐ በአቅሙ የሃድር በሠላም፤ መጥኖ በአቅሙ የበላ መሠላም ያድራል›› በማለት የተናሩት፡፡
  ነገር ደግሞ ከምግብ ይከፋል እንደተሰማ አይወራም፤ ለእያንዳንዱ በሚመጥን መልኩ ይወራል፡፡ የእናቶች አቅም፣ የአባች ለዛ ያለው ወሬ ወዳጅነት፣ የወጣቶች ችኩልነት፣ የህጻናት አስረግጦ ለማወቅ መፈለግ ይህ ሁሉ ከተጣራ በኋላ ይወራል፡፡ ምክንያቱም ለህጻናት የማይወራ ወሬ ሲኖር ህጻናት ከተኙ በኋላ ይወራል፤ ለሴቶች የማይስማማ ወሬ ካለም እነሱ በሌሉበት ይወራል ለሌሎች እንደዚሁ፡፡ በተለይ ከወሬ ክፉ የስሚ ስሚ ሰምቶ እንደነበሩ አድርጎ ማውራት፤ በተረትና ምሳሌ ‹‹ማን ያውራ የነበር ማን ያርዳ የቀበር›› ይባላል፡፡ ይህ ለተናጋሪውም ለሰሚውም አስተማሪ ብሒል ነው፡፡
  ስለዚህ ስንሰማ ከምንጩ ማረጋገጥ፣ የተለያዩ ሰዎችንም በጉዳዩ ዙሪያ መጠየቅ፣ ስንናገርም እርግጠኛ ያልሆንበትን ከማውራት መቆጠብ ይገባል፡፡ ወሬ እንደሰማን ከመናደድ ማስተዋል መረዳት መጠየቅ ምን ሊሉ እንደፈለጉ ዙሪያ ገባውን ማጤን ተገቢ ነው፡፡ ከሌሎች ፍጥረታት ሰውን የሚለየውም ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይበልጣልና›› በወሬ በርካታ ትዳሮች ፈርሰዋል፤ በወሬ ሰዎች የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፣ በወሬ ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል፣ በወሬ ብዙ ሊቃውንት ሀገር ጥለው ተሰደዋል ….. ስለዚህ ስንሰማ መርጠን ስንናገርም ነገር አስረግጠን ቢሆን ዓለማችን ሠላም ትሆናለች፡፡
  ይቆየን

  ReplyDelete
 32. Ye dani dewel endeketele new, Egnam eyetemaren new.

  ReplyDelete
 33. ከእድሜክ ተቀንሶ ለማን ይሰጥ ብባል ለዳንኤል እል ነበር ነገር ግን እግዚአብኤር ዘመንክን ይባርከው

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቼም ይች ጥያቄ የለችምና!

   Delete
 34. This is what the Patriarch is doing unto Mahibere-Kidusan (MK). He has been serving abroad in his whole life, and knows nothing about what MK has contributed to the church. He only heard false accusations from the enemies of MK, who never told him of the good deeds of the association! It's like the saying 'LAM BALWALECHIBET KUBET LEKEMA'. He is deciding on what he doesn't know! He may repent when he learns the truth, but he refused to listen to the Archbishops, who witnessed the works of MK at their respective dioceses -- My God give him the wisdom and open his eyes to know the truth, Amen.

  ReplyDelete
 35. ዲያቆን ዳንኤል ማንን ነው ታናሽ ያልከው ለሚለው …… ተዘጋጅ

  ReplyDelete
 36. ወደማትቆጣጠረው ትናንት ሄዶ መከራ ከማየት ወደምትቆጣጠረው ነገ መሄድ ይሻልሃል፡፡

  ReplyDelete
 37. Daniel, Antem yalsemahew ena yalayehew bizu neger silale eyitahin asfaw.

  ReplyDelete
 38. That is really a good view....But my comment, the view only focused on hearing all sources without screening led by our interst, the big question is how to differentiate the true story with the wrong one not get biased on the reality.... you need to include it to make it complete.....Otherwise it is good

  ReplyDelete
 39. thank you dr.Mikiru!

  ReplyDelete
 40. እግዚአብሔር እድሜና ዘመኑ የፈጠረውን ቴክኖሎጂ ሰጥቶኝ ያንተን በሐይማኖት የታነፀ በዜግነት የበለፀገ በአእምሮ የዳበረ አስተምሮትህን ስላሳየኝና አለን የምንለው ኢትዩጲያዊ ስለሰጠን ዘወትር እናመሰግነዋለን፡፡ ዓለም በዘርና በቋንቋ ልዩነት በምትታመስበት ሰዓት ቋንቋን ስለመስማትና ትርጉም ስለመስጠት እንዲሁም በጎ ነገርን ስለማሰብ እየጻፍክ ብርሃን ስለምትረጭባት ፈጣሪ የሰጠህን በረከት አይንሳህ እላለሁ፡፡ በርታ

  ReplyDelete
 41. ወደማትቆጣጠረው ትናንት ሄዶ መከራ ከማየት ወደምትቆጣጠረው ነገ መሄድ ይሻልሃል፡፡

  ReplyDelete
 42. i think we all need positivism. that is very important that is why we are still poor no body appreciated what someone did

  ReplyDelete
 43. Our culture is based on hear-saying than reading and figuring out things.My generations is based on watching than still reading. Most of us hate reading. If we find somebody who reads and struggling to know, we give him a good nick name which discourages him not to read anymore.

  ReplyDelete
 44. grum new yastemral

  ReplyDelete
 45. ‹ዕውቀት ብዙ ዓይነት ነው ልጄ፡፡ አሟልተህ የማታውቀው አለ፤ አዛብተህ የምታውቀው አለ፤ ጨርሰህ የማታውቀው አለ፤ የምታውቀውም ነገር አለ፡፡...'

  አዎ አሟልተን የማነውቃቸው ዕውቀቶች ለራሳችን ሰለማችንን አጥተን ሌሎቹን ሰላም እንዲናሳጣቸው እያደረጉን ነው! ትክክለኛ መካሪ እና ትዕግስት ያስፈልገናል! እግዚአብሔር ልቦና ይስጠና!

  ReplyDelete
 46. ‹‹ዕውቀት ብዙ ዓይነት ነው ልጄ፡፡ አሟልተህ የማታውቀው አለ፤ አዛብተህ የምታውቀው አለ፤ ጨርሰህ የማታውቀው አለ፤ የምታውቀውም ነገር አለ፡፡ ...

  አዎ አሟልተን የማነውቃቸው ዕውቀቶች ለራሳችን ሰለማችንን አጥተን ሌሎቹን ሰላም እንዲናሳጣቸው እያደረጉን ነው! ትክክለኛ መካሪ እና ትዕግስት ያስፈልገናል! እግዚአብሔር ልቦና ይስጠና!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሟልቼ የማውቀውን ልጽፍ ወረቀት ያዝኩና ፡ ሁለት ሰዓት አባክኜ ፡ በቅል እራስነቴ አዝኜ ፡ ጉድ እኮ ነው ፡ ብሎ ሲታዘበኝ የነበረውን ብዕሬን ፡ እንዳይጎዳ በዝግታ ከጠረጴዛው አጋድሜ ተገላገልኩ፡፡

   Delete