Tuesday, June 10, 2014

የ2006 ዓም የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች ተሸለሙ

ከ120 ተጠቋሚ ኢትዮጵያውያን መካከል በበጎ ሰው ዳኞች የተመረጡት ሰባት ኢትዮጵያውያን ‹በጎ ሰዎች› ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓም በኢሊሊ ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ተሸለሙ፡፡

የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ከየትምህርት ቤቱ የተጋበዙ ወጣቶችና ሌሎችም በተገኙበት በተከናወነው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን፣ በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ብጹዕ አቡነ ዮናስ፣ በርዳታና ሰብአዊ ሥራ ዘርፍ ዶክተር በላይ አበጋዝ፣ መንግሥታዊ  የሥራ ኃላፊነትን በመወጣት ዘርፍ አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ፣ በጥናትና ምርምር ዘርፍ አምባሳደር ዘውዴ ረታ፣ በቅርስ፣ ባሕልና ቱሪዝም ዘርፍ አብዱላሂ ሸሪፍ፣ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ደግሞ አባባ ተስፋዬ ሣሕሉ ተሸልመዋል፡፡

ሽልማቶቹን የተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የሸለሙ ሲሆን ከተሸላሚዎቹ መካከል አምባሳደር ዘውዴ፣ አምባሳደር ቆንጂትና  ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን ለሥራ ከሀገር ውጭ በመሆናቸው በተወካዮቻቸው በኩል ተቀብለዋል፡፡

ለሀገር በጎ ሥራ መሥራትንና ያለውንም በጎ ተጽዕኖ በተመለከተ ዶክተር እሌኒ(የ2005 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ) እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋየ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ገጣሚ አበባው መላኩና ገጣሚ ምንተስኖት ደግሞ ግጥሞችን አቅርበዋል፡፡
የመዝጊያ ንግግሩን ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራችና የ2006 የበጎ ሰው ሽልማት ዕጩ አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት አቶ ሰይድ ለአባባ ተስፋየ አሥር ሺ ብርና ሙሉ ልብስ ሲሸልሙ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ለሜሪ ጆይ አሥር ሺ ብር ለግሰዋል፡፡

ዳሽን ቢራ መርሐ ግብሩን በክብር ስፖንሰር አድርጓል

ሸገር ሬዲዮ፣ ኢቢኤስ ቴሌቭዥን፣ ኢሊሊ ሆቴል፣ ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት አጋሮቻችን ሆነው ለሰጡን አገልግሎት እናመሰግናለን

34 comments:

 1. God Bless You!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 2. ለዚህ ለተከበረው ስራ ሁሉ እግዚሐብሔር ይባርክህ በሰፊ እጁ ዲ. ዳንኤል

  ReplyDelete
 3. Replies
  1. I an sooooooo happy too!!! Dani is our Angel,

   Delete
 4. what an outsanding idea from you!so glad zat ababba tesfaye won this prize! (abrehot)

  ReplyDelete
 5. Thank you,historical megazine should be prepared,

  ReplyDelete
 6. ሰላም ዳንኤል ጥሩ ስራ ነው፡፡ት
  የመስገና እና የአድናቆት እርሀባችን ከእህል ውኃ ችግራችን ይገዝፋል ነው የሚሉት አዋቂዎች ፡፡ጥሩ\ በጎ ሰው የማበረታታ አቅማችንን ችለናል ማለት ይቻላል? አሁን፡፡ ልክ በምግብ ሰብል እራሳችን ችለናል አንደተባለው ሁሉ፡፡
  እኔ ይህንን ስራ ወድጀዋለሁ፡፡ በዚች ገጽህ ላይ ግን የሚያደንቅ አስተያየት አይጻፍም ብየ እገምታለሁ፡፡ ለምን የአድናቆት የቃላት እጥረት ስላለብን፡፡ መልካም ተርፎ ሊድር ክፉ ተናግሬ ተቃጠለ መስል ሸተተኝ አገሬ ነው መሰል ዘፋኝ ያለው፡፡
  እኔ ከገመተካቸው ሰዎች ያለተሸለሙት አቶ ይረጋና ዶ\ር ወረታው ነበሩ፡፡
  አቶ ይረጋ አሁን ስራውን በመልቀቁ ሞራል ይሆነው ነበር ብየ ነው፡፡ አብረው የተወዳደሩትም ከባድ ሰዎች ናቸው፡፡ በተለይ የተበለጠውም በአንገፋ ዲፕሎማት እና ሴት በመሆናቸው ታሪካቸውን ስሰማ እኔ ተቀብየወለሁ፡፡
  ለሚቀጥለው ጊዜ ለመመረጥና ለመሸለም መስራት ይኖርብናል፡፡ በአጠቃለይ ከጀርባ ሆነው ስራውን ያስተባበሩ፣የመሩ፣የደገፉ ፣የሰሩ አባለት እና ኮሜቴዎችን ማመስገን ይኖርብናል፡፡
  ለአገራችን አኑረን እንጂ ኑረን ብቻ እንዳናልፍ አግዛብሔር ይርዳን ፡፡ አሜን

  ReplyDelete
 7. God bless you, good job!!!

  ReplyDelete
 8. yemengist sewoch endemetut hulu, opposition leaders kelkel bitadergi yebelete yihon neber....biyanse enkua Lidetun atiterawum neber LOl

  ReplyDelete
 9. ሀይ ዳንኤል ሰራዎቸህ በጣም ጥሩ ናቸው ። ለካ አንድ ሰው ሀግር መቀየር ይቸላል ። አመላኬ አብዝቶ ፅጋውን ይስጥህ ። I don't have anything to say Danie. Am sure hope one day your dream will come true. 'የበጎ ሰው ሽልማት' will be national issue.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you so much the Anonymous person I love your comment, I have been read many comment but this is the best word coice and fact. I love you so much be proud by your postive attitude. God bless you.

   Delete
 10. ጀማሪ ብቻ ሣይሆን እንደ አባባ ተስፋየ ዘላቂነት እንዲሰጥህ የድንግል ማርያም ልጅ ንጉሡ አየለይህ ፣ በርታ!

  ReplyDelete
 11. The program is good but it could be better if u find other sponsor than alcohol producing company.

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is not relagion program. He selected best people that have been worked for Ethiopia and alcohol producing company sponsor it. In addition that it is aloud to drink alcohol in the bible. I don't get it why you wrote this comment.

   Delete
 12. ለሜሪ ጆይ ኤዶሚያስ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር 5ዐዐዐ ብር ለግሷል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Shame on you what kind comment is this?

   Delete
 13. ለሜሪ ጆይ ኤዶሚያስ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር 5ዐዐዐ ብር ለግሷል፡፡

  ReplyDelete
 14. Dear all,

  I am rely impressed by the event and my god bless the initiator (Dakon Danieal) and his supporters for the realization the event. To this end, let us ask ourselves what I did best for the criticizes and/or the support we provide for those doing good and scarifies their time and resources. Keep it up all!

  With best regards,

  Temesgen Kassa

  Bahir Dar

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wow I love your comment God bless you.

   Delete
 15. I am really proud of you, but also jealous of you in a positive way. keep up the good work,

  behulet bekul yetesale seyf hunu!

  ReplyDelete
 16. Thank you so much Dani, we love you so much. Most of us, we don't know what kind father, mother, sister and brother we have but know we know that there are many good people in Ethiopia. I don't have enough word to exress how much love you. I just want to say God bless you and your family. Your lover AD.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What do you mean we don't know what kind father, mother, sister and brother we have? If you don't know what kind family you have that is your business otherwise all Ethiopian we know our family.

   Delete
 17. Good job Dani, echi ke woyane sewoch tega tega gin alamarechignim

  ReplyDelete
  Replies
  1. All of us an Ethiopian. His message is to bring peace and to avoide discrimination. If you like to grow your country you have to love all Ethiopian. Most of Ethiopian people don't like this goverment but we didn't bring any change. We gave our country only for a certain group. We have to stand beside our enemy and apriciate their good job and oppose their bad job. Please don't be obstacle for his best job. Poltics never end. God bless Ethiopia and Dani.

   Delete
  2. We are all Ethiopian, if we are not close to them they will be far. How long we separate from them? what is the point? What benafit we got in the past? what is our dutiy for our country? All of us we hate goverment, do you think Somala is better than us because they don't have goverment the past 21 years? This goverment work hard to divide us, you told to Danial their sprit, how long we will be the victum of segrigation? We are an ethiopia with diffrent languche and many culture. Please reting before you write something . God bless our country.

   Delete
  3. ዳ/ን ዳንኤል, በእዉነት ምስጋና ብቻ ሳይሆን ክብር ላንተ ይገባል እላለሁ ፤ ሰዉ ከዉስጡ በጎ ነገር ሲኖር፣ በጎ ነገር ማሰብ ሲችል ነዉ በጎ ሰዉ እዳለ የሚያስበዉ ና ሁሉም በቀና ሊያይ የሚችለዉ ብየ አስባለሁ ፡፡ አንተም ይህ አስተሳሰብ ስላለህ ነዉ እንዲህ ሀገርን ለመለወጥ የቻልከዉ ለዚህ,ም ይህን ስራ ስለጀመርከዉ ብቻ በእዉነት ልትኮራ ይገባሀል ሰዉ ለሰራዉ ስራ ማክበርና ቦታ ሰጥቶ ለሽልማት ማብቃት ለራስም ክብር መስጠት ነዉ ፡፡ “”ክብር ለሚገባዉ ክብርን ስጡ””

   Delete
  4. ዳ/ን ዳንኤል, በእዉነት ምስጋና ብቻ ሳይሆን ክብር ላንተ ይገባል እላለሁ ፤ ሰዉ ከዉስጡ በጎ ነገር ሲኖር፣ በጎ ነገር ማሰብ ሲችል ነዉ በጎ ሰዉ እዳለ የሚያስበዉ ና ሁሉም በቀና ሊያይ የሚችለዉ ብየ አስባለሁ ፡፡ አንተም ይህ አስተሳሰብ ስላለህ ነዉ እንዲህ ሀገርን ለመለወጥ የቻልከዉ ለዚህ,ም ይህን ስራ ስለጀመርከዉ ብቻ በእዉነት ልትኮራ ይገባሀል ሰዉ ለሰራዉ ስራ ማክበርና ቦታ ሰጥቶ ለሽልማት ማብቃት ለራስም ክብር መስጠት ነዉ ፡፡ “”ክብር ለሚገባዉ ክብርን ስጡ””

   Delete
 18. Egzeabhere Yestehe. Egzeabhere Ferewhchen Abzeto Abzeto Yebarkelhe. Egzeabehere Amlak Benefsem Besegam Keberun Yagonasfhe.Egzeabhere Ethiopian Yebarkate

  ReplyDelete
 19. Daniye yene geta EGEZIABHER demo anten ena wede betesebochen be tsega yeshelemachu!! yesebekewen yesafekewen yemetenor EGEZIABHER bezih zemen yasenesah wede ye tewahdo lej neh!! adera dani ante tenesh enkuan betesasat emisenakewlew sew be milionoch yemikoter sew new ena adera Daniye ! Balebetehen ende Abereham Sara Lejochen demo ende Yesehak ena Yosef yadergeleh!

  ReplyDelete
 20. Thanks to God to help you to did this. I wish God be with your work.

  ReplyDelete
 21. ኢዮብ ብርሃነJuly 3, 2014 at 3:28 AM

  ለበጎ ሥራ የምስጋና ሽልማት ሰናይና ይበል የሚያሰኝ ነው ተሸላሚዎቹ ግን የግድ ገዥዎቻችንን የማይጎንጡት ብቻ መሆን የለባቸውም ለአብነት ለአገራችን ፍትህና እኩልነት ለሁሉም አንባገነኖች ጋር ሚታገሉት አንጋፍው ምሁርና የሰብዓዊ መብት ታጋይ ፕ/ሮ መስፍን ወ/ማርያም መዘንጋት የለባቸውም እላለሁ።
  ያክብርልኝ በብዛት ዳኒ!!!

  ReplyDelete