ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በሊቅነታቸው፣ በቆራጥነታቸው፣ ለየት ባለ አስተሳሰባቸውና
ለነገሮች በሚሰጡት አስደናቂ ምላሽ የሚታወቁ የትግራይ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ እስካሁንም እርሳቸውን በተመለከተ የሚተረኩ እጅግ
አስገራሚ ታሪኮች አሏቸው፡፡ አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አቡነ ዮሐንስ በዓላትን በተመለከተ የነበራቸው አስተሳሰብ ከብዙው ሰው
ለየት ያለ ነበር፡፡ ‹‹በዓል መከበር ያለበት በሥራ ነው›› ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት እንዲያውም በቀዳሚት ሰንበት
ሥራ ሲሠሩ ያያቸው ሰው ‹‹እንዴት ጌታ ባረፈበት ቀን ይሠራሉ›› ቢላቸው ‹‹እርሱኮ ያረፈው ሥራውን ጨርሶ ነው፡፡ እኔ መች
ሥራዬን ጨረስኩ ብለህ ነው›› ብለው መመለሳቸው ይነገራል፡፡
‹‹የበዓላትን ቀናት ለበዓሉ የሚስማማ ሥራ በመሥራት እንጂ እጅና እግርን አጣጥፎ
በመቀመጥ፣ መጠጥ ቤትና ጭፈራ ቤት በመዋል ማክበር ከማክበር አይቆጠርም፡፡ ሰው ምንጊዜም መቦዘን የለበትም፡፡ በየዕለቱ ለዕለቱ
ተስማሚ የሆነ ሥራ መሥራት አለበት›› ብለው ያም ይህንንም ያስተምሩ ነበር፡፡
ታድያ በአንድ ወቅት በበዓል ቀን ቤተ ክርስቲያን ሲያሠሩ ውለው ለጉዳይ ወደ ሌላ ቦታ
ይሄዳሉ፡፡ ለአቤቱታ ወደ እርሳቸው ዘንድ ከገጠር የመጣ አንድ ካህን እርሳቸውን ፍለጋ ወደሚያሠሩት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
ይመጣል፡፡ ሲመጣ እርሳቸው የሉም ነገር ግን ሠራተኞቹ በሥራ ተጠምደዋል፡፡ ተገረመም፣ ተናደደም፡፡ ‹‹እንዴት በበዓሉ ቀን
ትሠራላችሁ›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ያዘዟቸው አቡነ ዮሐንስ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡ ከኖረበትና
ከተማረው ውጭ የሆነ ነገር ሲፈጸም እያየ ዝም ማለቱን ኅሊናው አልተቀበለውም፡፡ በርግጥ ያዘዙት ሊቀ ጳጳሱ ናቸው፡፡ ነገር ግን
ሊቀ ጳጳሱም ቢሆኑ ሊሳሳቱ ይችላሉ አለና አሰበ፡፡
አስቦም አልቀረ ወደ ሠራተኞቹ ሄደና ‹‹በሉ ሥራችሁን አቁሙ›› አላቸው፡፡ እነርሱ
ግን ሊቀ ጳጳሱ ያዘዙትን እንደማያቆሙ ነገሩት፡፡ በዚህ ጊዜ መስቀሉን አወጣና አወገዛቸው፡፡ ያን ጊዜም ሠራተኞቹ ሥራቸውን
አቆሙና ቁጭ አሉ፡፡ እርሱም ሊቀ ጳጳሱን ፍለጋ ሄደ፡፡
አቡነ ዮሐንስ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመጡ ሠራተኞቹ ሁሉ ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ለምን ሥራ
ፈትታችሁ ተቀመጣችሁ?›› አሏቸው፡፡ ‹‹አንድ ካህን መጥቶ
አወገዘን›› አሉና መለሱላቸው፡፡ ካህኑ ይጠራ ተባለና ተፈልጎ መጣ፡፡ ‹‹አንተ ነህ ወይ ያወገዝካቸው›› አሉት፡፡ ‹‹አዎ››
አለ፡፡ ‹‹ለምን?›› ሲሉ መልሰው ጠየቁት፡፡ ‹‹አባቶቻችን
ያቆዩትን ሥርዓት ጥሰው ለምን በዓል ይሽራሉ ብዬ‹‹ አላቸው፡፡ ‹‹ያዘዝኳቸውኮ እኔ ነኝ›› አሉት፡፡ ‹‹ቢሆኑም ስሕተት
ነው፡፡ ስሕተቱን እያየሁ ዝም ማለትም ሌላ ስሕተት ነው›› አላቸው፡፡
አቡነ ዮሐንስ ተገረሙ፡፡ ካህኑን በመኪናቸው አሳፈሩና ወደ ቤታቸው ወሰዱት፡፡ ‹‹በል
ያንተን ጉዳይ በጉባኤ ነው የማየው፤ እስከዚያ እዚሁ እኔ ቤት እየበላህ እየጠጣህ ተቀመጥ›› አሉት፡፡ አቡነ ዮሐንስ ለጉዳይ
የሚመጣ የገጠር ሰው ከገጠማቸው ከተቻለ ጉዳዩን ዕለቱኑ ይፈጽሙለታል፡፡ ካልተቻለ ደግሞ እዚያው ራሳቸው ቤት አስቀምጠው ጉዳዩ
እስኪያልቅ ያስተናግዱታል፡፡ ክሱ የሚቀርበው በእርሳቸው ላይ ቢሆንም ሰውዬው በቤታቸው መስተናገዱ ግን አይቀርም፡፡
ቀን ተቀጠረና በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ ጉዳዩ ታየ፡፡ የመቀሌ ከተማ ሕዝብ፣ ካህናትና
ሊቃውንት ተሰበሰቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስ በሚሰጡት ለየት ያለ ፍርድ፣ በሚናገሩት ዘመን ተሻጋሪ ንግግር ይታወቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት
ወደ እርሳቸው የመጣ ሰው ‹‹ተማር›› ቢሉት ‹‹ምን እየበላሁ ልማር›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ታድያ የደነቆርከው ምን
እየበላህ ነው›› ብለው ጠይቀውታል ይባላል፡፡
ያ ካህን ቀረበ፡፡ ‹‹ለምንድን ነው ሠራተኞቹን የገዘትካቸው?›› ተብሎ ተጠየቀ፡፡ ‹‹አባቶቻችን ባቆዩን ሥርዓት በበዓል እንዲህ ያለ ሥራ መሠራት
የለበትም ብዬ ነው›› አላቸው፡፡ ‹‹ያዘዝኩት እኔ ነኝ፣ አንተ ይህንን ስታደርግ ሊቀ ጳጳሱ ይቀጡኛል፣ ከሥራ ያባርሩኛል፣
ክህነቴን ይይዙብኛል ብለህ አላሰብክም›› አሉት፡፡ ‹‹ቢያባርሩኝም፣ ክህነቴን ቢይዙብኝም መቀበል ነው እንጂ ምን ይደረጋል፡፡
ስሕተት እያየሁ ግን እንዴት አልፈዋለሁ፡፡›› አላቸው፡፡ ‹‹እና የሚመጣብህን ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተሃል›› አሉት ‹‹ከመጣ
ምን ይደረጋል›› አለ ካህኑ፡፡ ‹‹ከምቀጣህ ለምን ግዝትህን አታነሣም›› አሉት፡፡ ‹‹እርሱማ አቋም ነው፡፡ እምነቴ ነው፡፡
ቃሌ ነው፡፡ ይኼማ ከእርስዎ የባሰ ስሕተት መሥራት ነው›› አላቸው፡፡
ያን ጊዜ አቡነ ዮሐንስ ተነሡ፡፡ ሕዝቡም ምን ሊፈርዱበት ይሆን? እያለ በጉጉት ጠበቀ፡፡ ግማሹ እንዲያ ግማሹም እንዲህ አሰበ፡፡ አቡነ ዮሐንስም
የመጣበትን አውራጃ ጠየቁት፡፡ ነገራቸው፡፡ አሁን ሕዝቡ የቅጣቱ ደብዳቤ ለአውራጃው እንደሚጻፍ አረጋገጠ፡፡ አቡነ ዮሐንስም
አውራጃውን ከሰሙ በኋላ ‹‹እገሌ የተባለው የዚህ አውራጃ ሊቀ ካህናት እንዲህ ወደተባለ አውራጃ ተዛውሯል›› አሉ፡፡ ያን ጊዜ
ሕዝቡ ‹‹የኃጥኡ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ›› ብሎ ተረተ፡፡ በዚህ ካህን ዕዳ ሊቀ ካህናቱ በመቀጣቱ አዘነ፡፡ አቡነ ዮሐንስም
ቀጠሉ፡፡ ‹‹የዚህ አውራጃ ሊቀ ካህናት ግን ይህ ቄስ ይሆናል›› ሲሉ ሕዝቡ በአግራሞት አጨበጨበ፡፡ካህኑም ግራ ገባው፡፡
የጠበቀውና ያገኘውም ተለያየበት፡፡ ሕዝቡም በጥያቄ ተወጠረ፡፡ ለምን?
‹‹አያችሁ ወገኖቼ›› አሉ አቡነ ዮሐንስ፡፡ ይህ ሰው ሊቀ ጳጳሱን አወገዘ፡፡ እንደ
ሥርዓታችን ልክ አልነበረም፡፡ ቢያንስ ለምን እንደዚያ እንዳደረግን እንኳን መጠየቅ ነበረበት፡፡ ነገር ግን በአቋሙ ትክክል
ነው፡፡ ሰው ማለት፤ ጀግና ማለት፣ ጎበዝ ማለት አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ የበላዩን የማይፈራ፤ ፈጣሪውን ብቻ የሚፈራ፡፡
ላመነበት እውነት የሚቆም፡፡ በአቋሙ ምክንያት የሚመጣበትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ የሆነ፡፡ አሁን እኔ ሥልጣኑን ልይዝበት፣ ከሥራ
ላግደው፣ ጨርሶም ላወግዘው እንደምችል ያውቃል፡፡ ይህንን ሁሉ እያወቀ ግን ላመነበት እውነት መጽናቱ ጀግና ያደርገዋል፡፡
ማክበር ያለብን የሚፈሩንን፣ ቅዱስ ቅዱስ የሚሉንን፣ የሠራነውንም ያልሠራነውም የሚያደንቁልንን፣ የሚያወድሱንን ብቻ መሆን
የለበትም፡፡ ይህማ የማንም ሰው ጠባይ ነው፡፤ አክባሪውን የማይወድ ማን አለ፡፡ እኛም ጀግና የምንሆነው የሚገሥፁንን፣
የሚቆጡንን፣ ስሕተታችንን በድፍረት የሚናገሩንን፣ ሥልጣናችንን ሳይፈሩ ያመኑበትን እውነት የሚመሰክሩልንን ጭምር መውደድና
ማክበር አለብን፡፡
እናንተ እንደምቀጣው ነው የጠበቃችሁት፡፡ የሚገሥጹንን ሁሉ ግን መቅጣት የለብንም፡፡
ያመኑበትን ስሕተታችንን የሚነግሩንን፣ በአቋም የሚሞግቱንን ሁሉ መቅጣት የለብንም፡፡ እንዲያውም መሸለም አለብን፡፡ ለዚህ ካህን
ክህነቱን የሰጠሁት እኔ ነኝ፡፡ ስሰጠውም ‹ደኻ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ በል› ያልኩት እኔ ነኝ፡፡ ያን የሰጠሁትን እኔ ላይ
ሲፈጽመው መናደድ የለብኝም፡፡ ፍርደ ገምድል መሆንም የለብኝም፡፡ እንዲያውም እንዲህ ያለ ልጅ በማድረሴ ልኮራ ይገባል፡፡ ሞኞች
የሚገሥጽዋቸውን አይወዱም፡፡ ግን ቢሆንም እየመረረን እንኳን መቀበል አለብን፡፡ አሠራሩ ስሕተት ቢሆንም አቋሙ ግን ልክ ነው፡፡
ቆራጥነቱ ግን ልክ ነው፡፡ ማንንም አለመፍራቱ፣ ላመነው እውነት ብቻ መቆሙ፣ የሚመጣበትን ለመቀበል መዘጋጀቱ ግን ልክ ነው፡፡
ስለዚህ ሸልሜዋለሁ፡፡
አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ፡፡ ካህኑም መሬት ወድቆ እጅ ነሣ፡፡ ታሪክም ለእኛ እንዲህ
ሲል አቆየን፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው
የሚገሥጹንን ሁሉ ግን መቅጣት የለብንም፡፡ ያመኑበትን ስሕተታችንን የሚነግሩንን፣ በአቋም የሚሞግቱንን ሁሉ መቅጣት የለብንም፡፡ እንዲያውም መሸለም አለብን፡፡ ለዚህ ካህን ክህነቱን የሰጠሁት እኔ ነኝ፡፡ ስሰጠውም ‹ደኻ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ በል› ያልኩት እኔ ነኝ፡፡ ያን የሰጠሁትን እኔ ላይ ሲፈጽመው መናደድ የለብኝም፡፡ ፍርደ ገምድል መሆንም የለብኝም፡፡ እንዲያውም እንዲህ ያለ ልጅ በማድረሴ ልኮራ ይገባል፡፡ ሞኞች የሚገሥጽዋቸውን አይወዱም፡፡ ግን ቢሆንም እየመረረን እንኳን መቀበል አለብን፡፡ አሠራሩ ስሕተት ቢሆንም አቋሙ ግን ልክ ነው፡፡ ቆራጥነቱ ግን ልክ ነው፡፡ ማንንም አለመፍራቱ፣ ላመነው እውነት ብቻ መቆሙ፣ የሚመጣበትን ለመቀበል መዘጋጀቱ ግን ልክ ነው፡፡ ስለዚህ ሸልሜዋለሁ፡፡
ReplyDeleted/n Daniel qalehiwot yasemalen.bedemie betsega yetebeqelen. awo eyemererenem bihon ewneten mekebele aleben.
ReplyDeleteቃለ ሒወት ያሰማልን፣ እግዚሐብሔር ዳግሞ ይባርክህ ዲ.ዳንኤል ለኛም ለባሮቹ የምናስተውልበትን ልቦና ያድለን አሜን
ReplyDeleteየትም ብንሆን በአቋማችን መፅናት አለብን! በትምህርት፣ በእምነት፣ በሥራ፣ በፖለቲካ፣ በትዳር፣ በጓደኝነት፣ ወዘተ.
ReplyDeleteማክበር ያለብን የሚፈሩንን፣ ቅዱስ ቅዱስ የሚሉንን፣ የሠራነውንም ያልሠራነውም የሚያደንቁልንን፣ የሚያወድሱንን ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ይህማ የማንም ሰው ጠባይ ነው፡፤ አክባሪውን የማይወድ ማን አለ
ReplyDeleteግዚከስ
ሰው ማለት፤ ጀግና ማለት፣ ጎበዝ ማለት አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ የበላዩን የማይፈራ፤ ፈጣሪውን ብቻ የሚፈራ፡፡ ላመነበት እውነት የሚቆም፡፡ በአቋሙ ምክንያት የሚመጣበትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ የሆነ፡፡ gezax
ReplyDeleteዳኒ ፈቃድህ ከሆነ ስለ አቡነ ዮሐንስ ካልዕ(በዓለም ስማቸው ገ/መስቀል) ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኩሎን አድያማተ ትግራይ እኔም ትንሽ ልጨምር…1
ReplyDeleteጳጳስ ከኢ/ያውያን መሾም አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ክርከር ሊቃውንቱን ለ2 ከፍሎ ነበር፡፡ግብጻውያን በጊዜው ከኢ/ያ አይሾም ብለው ለሚከራከሩ ሊቃውንት ኦሜጋ ሰዓት ይሸልሙ ስለነበር አንድ ሊቅ በክርክሩ መሀላ ተነስቶ “በየሰዐቱ ቃላችሁን እየለዋወጣችሁ አትበጥብጡን” ብሎ የግብጽ ወገንተኞችን ስለመሸንቆጡ ይነገራል፡፡በወቅቱ አቡነ ዮሐንስ፡ኢ/ያ በሥጋ ነጻ ሀገር ናት፤በመንፈስም ከግብጽ ቤ/ክ ጭቆና ነጻ መውጣት አለብን ብለው በኃይለቃል ሲናገሩ ቀኃሥ ነገሩን ለማብረድ፡እባካችሁ በዲፕሎማቲክ ቀስ አድርገን የያዝነውን ነገር እንዳታበላሹብን ጥንቃቄ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡ወዲያው አቡነ ዮሐንስ፡ጃንሆይ የምን መለማመጥ ነው፤ጳጳስ ከውጭ ካስፈለገን ንጉሥም ከውጭ ይምጣ ሲሉ ቀኃስ አኩርፈው ከጉባኤው ወጡ፡፡ሆኖም የንጉሱና የጳጳሱ ልዩነት የአካሄድ እንጅ የአላማ ስላልነበረ በጳጳሱ ላይ አንዳችም እርምጃ አልተወሰደም፡፡ጳጳሱ በኋላ ዘመን የመቀሌ ደ/ሰላም ቅ/ሚካኤል ካቴድራልንና አሁን ወደ ቲዎሎጅ ኮሌጅነት ያደገውን ፍሬምናጦስ የካህናት ማሰልጠኛ በማሰራት ስማቸው ይነሳል፡፡እኚህ ጳጳስ ከ1966 እስከ 1968 ዓ.ም አቡነ ቴዎፍሎስ በደርግ ሲታሰሩ ዐቃቤ መንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡በወቅቱ ዛሬ ከካህኑ አልፎ ወደ ምዕመኑ መጋባት ስለጀመረው የሀገሬና የወንዜ ልጅ መባባል እንዲህ ብለው ነበር “ወንዞች የተፈጠሩ ለልማት እንጅ ሀገርንና የሰውን ልብ ለመከፋፈል አይደለም፤የሀገሬ የወንዜ ልጅ እያላችሁ ቤተክርስቲያንን አታዳክሙ!!”
አሁንም ከአቡነ ዮሐንስ የ96 አመት የቤ/ክ አገልግሎት ታሪክ በጥቂቱ…..2
ReplyDeleteትውልዳቸው በ1887 ዓ.ም በኤርትራ ደቡባዊ ዞን ነው፡፡የብፅዐት(የስለት) ልጅ ስለነበሩ በ3 አመታቸው ለአቡነ ብፁዕ አምላክ ገዳም ተሰጡ፡፡ገዳሙ መልሶ እስ 6 አመታቸው በወላጆቻቸው ስር እንዲቆዩ ተዋቸው፡፡ከ6 አመታቸው ጀምሮ ገዳም ተመልሰው ንባብ ተምረው ዲቁና ተቀበሉ፡፡ከዛ ትግራይ ተንቤን ተሻግረው ዜማና ቅኔ፣ጎንደር ቀጥለው ዝማሬ መዋስዕትና አቋቋም፣ወደ ሸዋ መጥተው ብሉይና ሐዲስ ተማሩ፡፡በ1919/20 በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን በነበረው ኢ/ያ የራሷን ተወላጅ ጳጳስ አድርጋ መሾም አለባት በሚለው የሊቃውንቱ ንቅናቄ አፈጉባኤ ነበሩ፡፡በመሀሉ ጣሊያን ሲመጣ ማይጨው ዘመቱ፡፡በ5ቱ የጠላት ዘመን የቀጨኔ አለቃና የውስጥ አርበኛ ሆነው ቀጠሉ፡፡በ1938 ዓ.ም ሊቀሊቃውንት ተብለው በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ተሾሙ፡፡ከ1940 እስከ 1948 ዓ.ም ደግሞ በአክሱም ንቡረዕድነት ከቆዩ በኋላ በቀዳማዊው ኢ/ዊ ፓ/ክ አቡነ ባስልዮስ ጵጵስና ተሾሙ፡፡መንበራቸው መቀሌ ነበር፡፡ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅን ሊመርቁላቸው ጃንሆይ ሲመጡ ባበረከቱት ጉባኤ ቃና እንዲህ አሉ………….
በዊዐ መቃብር እቅድምከ ኃ/ስላሴ እንዘ ንረውጽ ክልኤነ፣
እንዘ ጴጥሮስ አንተ አምጣነ ዮሐንስ አነ፡፡
ሰሙ፡ጴጥሮስ የጌታን መቃብር ለማየት በመሮጥ ዮሐንስን እንደቀደመው የሚያሳይ ሲሆን ወርቁ ከጃንሆይ ቀድሜ ልሙት ማለት ነው፡፡ጃንሆይ ፡አባታችን ቅኔው መልካም ነው፤ግን ዮሐንስኮ አይደለም ቀድሞ የገባው ሲሏቸው አቡኑ አለቀሱ፡፡ም/ቱም በዮሐንስ ወንጌል ም.20 ቁ 3 ጀምሮ እንደተጻፈው ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ቀድሞ ቢደርስም ዘልቆ የገባው ጴጥሮስ ነበር፡፡አባታችን እንዳሉት(እንደተነበዩት) ጃንሆይ የ66ቱን አብዮት ተከትሎ ህይወታቸው ሲያልፍ አቡነ ዮሐንስ ግን ከደርግ ሰይፍ ተርፈው እስከ 1989 ዓ.ም ቆይተው፣ ከአንድም አምስት ኢ/ዊ ፓትርያርኮችን አይተው በ102 አመታቸው አርፈዋል፡፡አባታችን በወላጆቻቸው ቤት ያሳለፉትን 6 አመት ስንቀንስ አገልግሎታቸው 96 አመት ይሆናል፡፡ከዚህም ውስጥ 35 አመት በጉባኤ ቤት፣20 አመት በአስተዳደር፣41 አመት በጵጵስና ድምር=96 አመት!!
በረከታቸው አይለየን!!
ምንጭ፡ ዝክረ ሊቃውንት በመልአከ ምክር ቀሲስ ከፍያለው መራሂ ገጽ 250 እስከ 258
Great!!!!
DeleteYigermal!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
DeleteDear Be'aman, I like your comment today. please keep on posting such type of constructive comments ... may be you convinced me today ... unlike your comments in issues related with 'church politics'
Deletebless you brothers dn danieal & beaman
DeleteDn Daniel,
ReplyDeletekale hiwot yasemalin. this is a very important teaching for the present time. We need more of this Kahin in our church.
GOD BLESS YOU!!!
u are right Dn. Daniel
ReplyDeleteHe was also one of the most gifted preachers and far sighted fathers. Many of the church establishments we see in Tigrai were built during his time.
ReplyDeletetalaki abat nachw yesachwn tihitina yistln.
ReplyDeleteእኔ የሚገርመኝ የሚጨቀኝ ሁልጊዜ የኢትዮጵያን የአባቶቻችንን ታሪክ ሳነብ፣ ስማር፣ስሰማ… እውነት እኔ/እኛ ከነዚህ ከአባቶቻችን የመጣን ትውልድ ነን ውይስ የሚል ጥያቄ ያጭርብኛል………. ምክንያቱም እኛ የተማርን መስሎን ምን ያክል በአስተሳሰባችን. በኑሯችን፣በእውቀታችን፣በተግባራችን እንደወረድን ማስተዋል የሚችል ሁሉ በእለት እለት የኑር አጋታሚው በመገዶች የምንመላለስ ሰዎችን ማየት በቂ ነው… በእውነት ለእምነቱ፣ ለዓላማው፣ ለሀገሩ ታማኝ የሆነ ትውልድ እንድንሆኑ ያበርታን እናንተም እንዲሁ ማስተማራችሁን ቀጥሉ….
ReplyDeletein what way we are going as we compared with our old father in the past??????????????????????????????????
ReplyDeleteሰው ማለት፤ ጀግና ማለት፣ ጎበዝ ማለት አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ የበላዩን የማይፈራ፤ ፈጣሪውን ብቻ የሚፈራ፡፡ ላመነበት እውነት የሚቆም፡፡
ReplyDeleteሁሉም ነገር መልካም ነዉ፤ይህ ጦማር የስጋም የነፍስም ምግብ ነዉ፡፡ የሚጎረብጥ ነገር የለዉም፤ሁሉም ነገር ተስማምቶኛል፡፡ ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
ReplyDeleteBless you both DN Daniel and Beaman for sharing this with us!!
ReplyDeleteእኔ በጣም የሚገርመኝ ለመንፈሳዊውም ለሥጋዊውም ጽሑፍ ቃለ ሕይወት ያሰማልን የሚል አስተያየት የምትሰጡ አንባብያን ናችሁ። ዲን፣ዳንኤል የሚጽፋቸው ጽሑፎች አስተማሪ ቢሆኑም ብዙዎች ቃለ ሕይወት ያሰማልን የሚያሰኙ አይደሉምና አንባብያን አስቡበት ዲን.ዳኒም ይህን ለማስተካከል ሞክር።በርታ
ReplyDeleteKale Hiwot Yasemalene Dn Danieln ena Beamanen.Yeendenezhe Aynet Abatochen tarke mesmat erasu yehiwot megeb new. Egzehabhere yestelen.
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin!
ReplyDeleteለመንፈሳዊውም ለአለማዊውም ብለህ ለፃፍከው/ሺው ወንድሜ/እህቴ በመሠረቱ ቃለ-ሒወት ያሰማልን ሲባል ምን ማለት ነው እንደኔ አመለካከት እግዚሐብሔርን በግለሰቡ ላይ አድሮ ስላሰማን መልካም /በጎ ነገር/ ትምህርት /ምክር ሁሉ እግዚሐብሔርን እያመሰገን ለነገርን/ ለአስተማረን መምህር ደግሞ እግዚሐብሔር ዋጋውን እንዲከፍለው የምንለምንበት ቃል ነው…. ታዲያ ዲ.ዳንኤል በእግዚሐብሔር ትዕዛዝ እሱም ያለበትን ኃላፊነት/ግዴታ ለመወጣት ሲባል ለሚያስተምረን፣ ለሚመክረን፣ ለሚነግረን ለሚገስፀን ጽሁፎች ሁሉ ቃለ-ሒወት ያሰማልን ቢባል ምንድነው ችግሩ….. ምንስ ሊባል ይችላል….. እንዲያውም ሲያንሰው ነው ሌላ የሚገለጽበት/የሚመሰገንበት ቃል ቢኖር በዚያ ሊመሰገን የሚገባው ወይስ የሱ ፀጋ ለኛ ስላልተሰጠ……… አሁን እግዚሐብሔር ደጋግሞ ቃለ-ሒወት ያሰማልን ዲ.ዳንኤል እግዚሐብሔር ይባርክህ የማናውቀውን እንድናውቅ የማናየውን እንድናይ ታደርገናለህና ከነቤተሰቦችህ አብዝቶ ይባርክህ
ReplyDeleteእግዚአብሔር እንደ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ያለ አባት ይስጠን አንተንም ከነቤተሰብህ ይባርክህ
ReplyDeleteYes we Ethiopians have a lot ,but we have no interest and that is why now we are colonized by westerns,even though we are a sign of freedom for Africa.
ReplyDeleteI fill so sorry BY NOW!